Ethio Sport
this is foot ball
ነፍስህን በገነት ያኑረው
R.Madrid 2 1 R.socidal
sponcer
.mbape
የፊት ማስክ ለማጽዳት ማወቅ ያለብን ነገሮች፡፡
*********************************************
በሃገራችን የፊት ማስክ አንዱና ዋነኛው አላባሽ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ከቫይረሱ መስፋፋት ጋር ታያይዞ ለደህንነታችን ሲባል የፊት ማስክ ማድረግ የግድ ነው፡፡ ነገር ግን የተጠቀምንባቸውን ማስኮች ለማጽዳት የምናደርገው ዘዴዎች በራሱ በሽታውን የማስፋፋት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ ከሚመለከተው አካል ወጥ የሆነ የአጸዳድ መመሪያ አለመኖሩ በህብረተሰቡ ውስጥ ማስክን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እንዳይጠቀም አድርጓል፡፡ባጠቃላይ ሦስት ዓይነት የፊት ማስኮች ማለትም የጨርቅ፣ የሰርጂካል እና ኤን 95 በገበያ ላይ ይገኛሉ።ከነዚህ ውስጥ ሰርጂካል ወይም ኤን 95 (N95) ማስኮች የተሰሩት ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ ቢሆንም ካለው ዕጥረትና ውድነት አንፃር ደግመን መጠቀም ሊኖርብን ይችላል።
ለመሆኑ አንድ ማስክ እንዴት ይፀዳል?
በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በደህንነት አልባሳት ባለሙያ የሆኑት ጄድ ፍሊን ማብራሪየ ከሆነ አንድ ሰው ማስኩን እንዳወለቀ ማድረግ ያለበት የመጀመሪያው ጥንቃቄ እንደማስኩ ዓይነት የሚወሰን ቢሆንም የሚከተሉትን ነገሮች ከግንዛቤ ማስገባትና መተግበር እንዳለበት ይመክራሉ።
1. የጨርቅ ማስክ በላውንደሪ ማሽንም ሆነ በዕጅ በምናጥብበት ጊዜ ከሌሎች አልባሳት ለይተን ማጠብ ይኖርብናል። በምናጥብበት ጊዜም ሙቅ በሆነ ውሃ እና በበቂ ሁኔታ ሳሙና መጠቀም ይኖርብናል ፡፡
2. ማስክ በምናደርግበትና በምናወልቅበት ጊዜ የውጭና የውስጠኛውን ክፍል በዕጃችን አለመንካትና ገመዱን ብቻ መጠቀም።
3. ሰርጂካል ወይም ኤን 95 (N95)ማስኮች ዳግም ለመጠቀም በምናፀዳበት ጊዜ በላውንደሪ ወይም በዕጅ ከማጠብ ይልቅ በጊዜ ብዛት ቫይረሱ ዕንዲጠፋ ቢያንስ ለ3 ቀናት ያህል ከንክኪ ለይቶ ማስቀመጥ ተመራጭ ነው፡፡ ምክንያቱም በሚታጠብብት ጊዜ ማስኩ ይጎዳል (የመከላከል አቅሙ ይቀንሳል) ስለሆነም ቫይረሱ በማስክ ላይ ሊቆይ የሚችለው የተረጋገጠ ከፍተኛው ጊዜ ቢያንስ 72 ሰዓታት ( 3 ቀናት ) በመሆኑ ከንክኪ በራቀ ቦታ ማንጠልጠል ወይም በወረቀት በተሰራ መያዣ ማስቀመጥ ይመከራል፡፡ የፕላስቲክ (ፔስታል) መያዣዎች አየር ስላማያስወጡ ባክቴሪያና ቫይረስ አምቀው የማቆየት አቅም አላቸው ስለሆነም መጠቀም አይመከርም፡፡ ሆኖም ግን እዚ ጋር መረዳት ያለብን አንድ ሰው በትንሹ በየሦስት ቀን ልዩነት ማስክ ለማድረግ ቢያንስ ከአንድ በላይ የፊት ማስክ ሊኖረዉ ይገባል ።
4. የፊት ማስክን ፀሐይ ላይ (ከ72 ሰዓታት በታች) በማስጣት (በማስመታት ) ኮሮና ቫይረስን አያጠፋውም ምክንያቱም የፀሐይ ብርሀን ቫይረሱን ለማጥፋት የሚያስችል በቂ አልትራ ቫዮሌት (uv) የለውም፡፡
5. የፊት ማስክን በእንፋሎት ወይም በማፍላት ለማፅዳት የሚደረገው ጥረት አይመከርም ምክንያቱም የፊት ማስክ አሰራሩ የተደራረበ በመሆኑ ቫይረሱ በምን ያህል የሙቀት መጠንና የጊዜ ርዝመት እነደሚጠፋ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ፡፡
6. ማስክን ለማስወገድ ስንፈልግ በጥንቃቄ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ብቻ መጣል፡፡
የፊት ማስክ ማድረግ ርቀታችንን በጠበቀ ሁኔታ ከተገበርነው የተሻለ ውጤት ያስገኛል ።
@ኮሮናቫይረስ ዕለታዊ መረጃ
ምንጭ፦
https://www.apartmenttherapy.com/face-mask-cleaning-36749054
https://www.sages.org/n-95-re-use-instructions/
Rolando
Cr 7
Like➥
Debruyne
STRENGTH
Cristiano Rolando
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
0990
Addis Ababa, 1230
in this page you can get any kind of short news, panorama news, entertainment