Addis Ketema Woreda one youth association

Addis Ketema Woreda one youth association

bego adragot mahber.

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 23/02/2024

ዜና ማህበር
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ከወረዳና ከ/ከተማ የማህበሩ አመራሮች ጋር በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ዉይይት አካሔደ

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ተረጥቶት እየተሰራ ባለዉ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የደረሰበትን ደረጃ በብሎክ በወረዳና በከ/ከተማ በነበረዉ የወጣቶች ዉይይት ላይ የተነሱ ሀሳቦች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ የሆነ ወይይት የተካሄደ ሲሆን ከአመራሮችም አሁን የተጀመረዉ የስራ እድል ተጠናክሮ እንዲቀጥልና መንግስት ሰፋ ያለ የስራ እድሎችን ለወጣቱ መፍጠር እንዳለበትና ማህበሩም በዚህም ተግባር ላይ በሙሉ ሀይሉና አቅሙ ወደስራ እንደገባ ገልፀዋል በመጨረሻም የማህበራችን ፕሬዘዳንት ወጣት ገዛኸኝ ገ/ማርያም ባስተላለፈዉ መልእክት አሁን ላይ የተጀመረዉን የወጣቶች የስራ እድል እንደዚቀደሙ ሳይሆን መላዉ የማህበራችን አባላትና አመራር የዚህ እድል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም የስራ ማማረጥ አስተሳሰብን ወደ ጎን በመተዉ መላዉ የከተማችን ስራ ፈላጊ ወጣቶች የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን አለበት በማለት ይኸ መድረክ እንዲመቻች ላደረገዉ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊና በየደረጃ የሚገኙ አመራሮችን በማመስገን ዉይይቱን አጠናቀዋል
ኮምንኬሽን ጽ/ቤት የካቲት 2016 ዓ.ም

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 23/02/2024

# # ዜና ማህበር # #

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር በስራ እድል ፈጠራ እና በመደበኛ ተግባራት የተደረሰውን ጠቅላላ አፈፃፀም ከማህበሩ ስራ አስፈፃሚዎች፣ከወረዳ ምክትልና ፀሀፊ ጋር ተወያየ።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር መደበኛ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባውን ከወረዳ ሰብሳቢዎች፣ ምክትል ሰብሳቢና ፀሀፊ ጋር በጋራ ያካሄደ ሲሆን በስብሰባው የ3ወር የስራ እድል ፈጠራ የ2016 ዓ.ም የ3ኛ እሩብ አመት አጀማመር አጠቃላይ እንደ ተቋም የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም አባላት ምልመላ የተደረሰበት አፈፃፀም በስፋት ለመገምገም ተችሏል።

በስብሰባውም የሁሉም ወረዳዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የስራ እድል ፈጠራ፣አባላት ምልመላ እና ክበባትን ከማጠናከር አኳያ የተሻለ ስራ ለመስራት የተቻለ ሲሆን አጠቃላይ በማህበሩ የተሰሩ የንቅናቄ ስራዎችና የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ጥቅል በክ/ከተማው በማህበሩና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተሰሩ ስራዎች በሰፊው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በማረም ለቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ በማስቀመጥና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት ስብሰባው ተጠናቋል።

የካቲት-15-2016 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር / Addis Ababa Youth Association's post 23/02/2024
22/02/2024
19/01/2024

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፥

ውድ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች እና የማህበራችን አመራሮች አባላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

የጥምቀት በዓል ብዙ ትርጉሞችን ይዞ የሚከበር በዓል ነው፡፡ በአንድ በኩል ለክርስቲያኖች ትኅትናን የሚማሩበት፣ በእግዚአብሔር ማመናቸውን የሚያውጁበት፣ ንስሐና ድኅነት የሚያገኙበት ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ሀገር የጥምቀት ክብረ በዓል መልከ ብዙ የሆንን ኢትዮጵያውያን ኅብር ፈጥረን የምንደምቅበት በመሆኑ ታላቅ ቦታ ሰጥተን እናከብረዋለን፡፡

የጥምቀት በዓል ከሀይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ የሃገራችን ብሎም የከተማችን ገፅታ ለዓለም የምናሳይበት፣ለበለጠ ወንድማማችነትና አብሮነት በጋራ የምንነሳበት በመሆኑ ሁላችንም ለበዓሉ መድመቅ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ከማበርከት ባለፈ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትና አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር በማድረግ ማክበር ይጠበቅብናል ።

የከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የማህበራችን አመራርና አባላት የክፍለ ከተማችን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ነዋሪዎች፣የፀጥታ አካላት፣እና የሚመለከታችሁ በሙሉ በዓሉን በፍቅርና በአንድነት፣ በመተባበርና በመግባባት በማክበር የሁላችንም ኃላፊነት በመሆኑ ሁላችንም ለበዓሉ መድመቅና ሰላማዊነት የድርሻችንን ሀላፊነት ማበርከት ይኖርብናል።

በድጋሚ መልካም በዓል

ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ

ጥር ፣ 10 ፣ 2016 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 17/01/2024

የከተራና የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊታቸው ተጠብቆ በወንድማማችነት እና በፍቅር እንዲከበሩ ወጣቶች የአንበሳውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
****

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ከክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት እንዲሁም ከክፍለ ከተማው ብልፅግና ወጣቶች ሊግ ጋር በጋራ በመሆን በመጨው ቀናት በሚከበሩ የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበር ዙሪያ ከወጣቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም የከተራና የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊታቸው ተጠብቆ በአብሮነት፣ በወንድማማችነት እና በፍቅር እንዲከበሩ ወጣቶች የአንበሳውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ በበኩላቸው በዓሉ በዓለም በማይዳሰሱ የቅርስ መዝገብ በዩኒስኮ የተመዘገበ ስለሆነና ሃገራዊና አለማቀፋዊ አንድምታው የጎላ በመሆኑ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ወጣቶቻችን ሁሌም ለሰላምና ለልማት ግንባር ቀደም ሆነው መሰለፋቸውን ይቀጥላሉ ያሉት የክፍለ ከተማው ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ በበኩላቸው ታላላቅ ህዝባዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ለማድረግ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዝግጁ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን
ጥር 8-2016ዓ.ም

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 07/01/2024

የአዲስ ከተማ ወረዳ አንድ ወጣት ማህበር እንደሁል ግዜው የበጎነት ተምሳሌት የሆነው የጎዳና ሻውር በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በጋራ በመሆን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በሲኒ-ማራስ አደባባይ ላይ ከ800 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ምገባ መርዐ-ግብር ማከናወን ተችሏል።
ይህን የመሰለ ተግባር የተሳካ እንዲሆን ላስተባበራቹ አካላት ክብርና ምስጋና ይገባቹአል።
ማህበራችን ትላንት ዛሬም ነገም በማህበረሰቡ ላይ በቀጥታ በሚሰሩ ተግባራት ላይ የተጠናከረ ስራ መስራታችን ሁሌም ይቀጥላል።
!

07/01/2024

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፈው መልዕክት ፤

ውድ በክፍለ ከተማችን የማህበራችን አመራሮች አባላት ወጣቶች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ውድ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች

የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት መወለዱን የምናስብበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

የክርስቶስ ልደት የልዩነትን ግንብ ያፈረሰ፣ የጠብን ግድግዳ የናደ፣ የጥላቻን መጋረጃ የቀደደ፣ የተዋረዱትን ያከበረ፣ የተለያዩትን አንድ ያደረገ፣ የተበተኑትን የሰበሰበ ነው፡፡

የክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣት ‹እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ እጅጉን ይልቃል› ተብሎ እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ካደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ይህ ስጦታ ታላቁ ስጦታ ነው፤ በመሆኑም ይህ በዓል የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆነ ታላቅ በዓል ነው።

እኛም ፈጣሪያችንን ተምሳሌት በማድረግ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ትኅትናን፣ አብሮነትን እና መከባበርን አስቀድመን መጀመር አለብን፡፡

ከትዕቢት ይልቅ ትኅትናን ገንዘባችን ብናደርግ ወደ ጥላቻ እና ወደ መከፋፈል ከሚወስደው መንገድ ወጥተን በሌላ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የአብሮነት ስራን በመስራት ወደ ተሻለ የለውጥ ጎዳና በፍጥነት መድረስ ይኖርብናል ።

ውድ የማህበራችን አመራሮችና አባላት እኛም በዓሉን ስናከብር የአካባቢያችንን ሰላም በመከላከልና የሰላም ዘብ በመሆን የተጀመሩ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከዳር እንዲደርሱ ከሚመለከታቸው አካላት ጎን በመቆምና አስተዋጽዖ በማበርከት እንዲሁም የገና በዓል የስጦታ በዓል በመሆኑ ያለንን ለሌላቸው ወገኖች በማካፈል ልናከብረው ይገባል እያልኩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

በድጋሚ መልካም በዓል

ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ
ታህሳስ 28 ፣ 2016 ዓ.ም

Photos from የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ማህበር's post 06/01/2024
Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 06/01/2024

የአዲስ ከተማ ወረዳ አንድ ወጣት ማህበር
እንደሁል ግዜው እንደምናደርገው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በወረዳች ላሉ በሶስት አይነት ተግባራት የማዕድ ማጋራት አከናውነናል።
#ለተለዩ 30 አባወራዎች
ዱቄት = 6 ኪሎ
መኮረኒ = 4 ኪሎ
ፓስታ = 4 ፍሬ
ዘይት = 2 ሌትር
#ለተለዩ 45 አባወራዎች
ዶሮ = 1
ዘይት = 1 ሊትር
እንቁላል = 12 ፍሬ
ወጣቶች
ለ27 ወጣት*1200 ብር = 32,400 ብር
**
በአጠቃላይ ድጋፍ የተደረገ
ለ101 አባወራና ወጣቶች
በገንዘብ 107,475 ብር የሚያወጣ በማቴሪያልና በገንዘብ መደገፍ ተችሏል።
የገና በአል ምክንያት በማድረግ የአዲስ ከተማ የክ/ከተማ ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ እዲሁም የተለያዩ በየደረጃው የሚገኙ የክ/ከተማችን ም/ሰብሳቢ ወጣት ኢሳ ሰኢድ እና ዋና ፀሀፊ ወጣት ብሩክ በእለቱ ተገኝተው በይፋ የማዕድ ማጋራት አስጀምረው።
በእለቱም የክ/ከተማችን ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት በእለቱ ለታደሙ ሰዎች መልዕክት አስተላልፋል።
በማጠቃለያ የአዲስ ከተማ ወረዳ 1 ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብድረህማን ካሱ ተግባሩ እንዲሳካ ለደከሙና ሁሉ ነገራቸውን ሰተው ተግባሩን ላሳኩ ወንድሞች የምስጋና መልዕክት አስተላልፋል።
!
በዓሉ የሰላም, የፍቅር,የደስታና የተቸገሩትን የምንረዳበት እንዲሆን እንመኛለን።

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 02/01/2024

!
እንደሁል ግዜው ድምቀቱ ቀጥሏል
የፊታችን ለማከበረው የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ለሚከናወነው የማዕድ ማጋራት ተግባር የሽብርቅ እንደቀጠሉ ነው።

21/12/2023

የአዲስ ከተማ ወረዳ 1 ወጣት ማህበር
በወረዳችን ከታህሳስ 10-04-2016 ዓ.ም ጀምሮ
በወረዳችን ራሱን ችሎ በወጣት ማህበራችን ጠንካራ ማህበር እንዲሆን መልሶ በማደራጀት በአዲስ መልክ ለመስራት 37 አባላት ያሉት ማህበር መረጃ ተደራጅታል

1. ፍቃዱ ንጉሴ ....... ሰብሳቢ
2. ዳዊት ደንቡ ........ ም/ሰብሳቢ
3. ሜላት ሞኮነን ...... ፀሀፊ
በመሆን በመረጃ የማደራጀት ስራ ተሰርታል

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 19/12/2023

ዜና ማህበር

""አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም""

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ማህበር ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን የ2016 ዓ, ም የበጋ በጎ ፍቃድ ተግባር አንዱ የሆነውን ደም የማስለገስ ተግባር የተከናወነ ሲሆን በዚህም ከ31 ዩኒት ደም በላይ ለመሰብሰብ ተችሏል።

ታህሳስ-09-2016 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 02/12/2023

የአዲስ ከተማ የወረዳ አንድ ወጣት ማህበር
የ2015 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም የእውቅና የሽልማት እና የ2016 ዓ.ም የሩብ አመት የስራ አፈፃፀምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የግንዛቤ መድረክ
በእለቱም :-
የወረዳ የምክር ቤት መልሶ ተደራጅታል
የስራ-አስፈፃሚና የኦዲት ቁጥጥር አመራሮች መልሶ ተደራጅታል
በእለቱም የአዲስ ከተማ ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ ለተሳታፊ ወጣቶች እስካሁን ወረዳው ላመጣው ውጤት አመስግነው በ2016 ዓ.ም የወጣቶች ተጠቃሚነት እና የማህበራችን ቁልፍ ተግባራት ተጠናክረው እንዲሰሩ ለወጣቱ አፅኖት ሰተው መልዕክት አስተላልፈዋል

Photos from Adiss ketema woreda 1 communication's post 29/11/2023
21/10/2023

* # *
ሰላም የተከበራቹ የወረዳ አንድ የወጣት ሜህበር አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ በ2015 ዓ.ም መደበኛ የማህበራችን ቁልፍ ተግባራት በነበረ ምዘና
ከክ/ከተማችን ወረዳዎች መካከል
1ኛ ደረጃ ወረዳ 1
2ኛ ደረጃ ወረዳ 2
3ኛ ደረጃ ወረዳ 8 ና 13

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 28/09/2023

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወጣት ማህበር ከጎዳና ሻውር በጎ አድራጎት ጋር በጋራ በመሆን የብርሃነ መስቀል በኃልን ምክንያት በማድረግ በሲኒ-ማራስ አደባባይ ደማቅ የሆነ ምገባ ፕሮግራም ማከናወን ችለናል። ተግባሩ የተሳካ እንዲሆን የወረዳ ተ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ላደረገልን ትብብር ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።
#የአ/ከ_ወረዳ_1_ወ/ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 15/09/2023
Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 15/09/2023

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር መደበኛ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባውን አካሄደ።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር መደበኛ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባውን ዛሬ መስከረም 4-2016 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን የጷጉሜ ተግባርና ማዕድ ማጋራት ስራን በሰፊው ለመገምገም ተችሏል።
# # #በተያያዘም በከተማችን አ.አበባ በሰፊው የሚከበሩትን የመስቀልና ኢሬቻ በዓላትን በተመለከተ ከማህበሩ የስራ-አስፈፃሚ አመራሮች ጋር በሰፊው በመወያየት በዓላቱን በተመለከተ በቀጣይ የሚሰሩ የወጣት መድረኮችና ተዛማጅ ስራዎች ከዛሬ ጀምሮ በስፋት መሠራት እንዳለባቸውና በፕሮግራም የተያዙ የወጣት መድረኮች ላይ በተሻለ መልኩ ማሳካት እንደሚገባ በመግባባት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱን ለማጠናቀቅ ተችሏል።
የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 1 ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን
መስከረም -4-2016 ዓ.ም

11/09/2023

!
ወጣት አብድረህማን ካሱ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ
ወጣት ማህበር ሰብሳቢ
በአዲሱ ዓመት ብሩህ ተስፋ ን ሰንቀን በትጋት የምንሰራበት: በተሰማራንባቸው የስራ መስኮች በሁሉም በስኬትና በውጤት የምናመጣበት አመት እንዲሆን እመኛለሁኝ።
በአዲሱ አመት እኛ ወጣቶች ችግሮቻችን ወደ መፍትሄ በመቀየር: መሰናክሎችን በብልዐት እየተሻገርን: በተጠናከረ አንድነት: በተለወጠ አስተሳሰብ: ለስኬት በሚያበቃ የስራ ባህላችን ራሳችን ካሮጌው ዘመን የተሻለ ደረጃ የምንደርስበት ! በሚል መንፈስ በ2016 ዓ.ም አገራችን ሰላሟን ከሚያሳጣት ነገሮች ሁሉ በሙሉ የምፀዳበት ፓለቲከኞች ችግሮቻቸውን በወንበር የሚፈቱበት: የአይማኖት አባቶች ወጣቶችን የሚያንፅበቶ : ችግርና ራሃብ ከአገራችን የሚጠፋበት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት አገራችን ለመገንባት በእኩል ለአገራችን ዘብ የምንቆምበት አመት እንዲሆንልን እመኛለሁኝ።
መጫው 2016 ዓ.ም አመቱ የፍቅር: የሰላምና የአብሮነት በተባበረ ክንድ በማረጋገጥ ለመገንባት እኛ ወጣቶች የራሳችን አሻራ የምንጥልበት ብሩህ ዘመን እንዲሆን እመኛለሁኝ።
!

ወጣት አብድረህማን ካሱ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ወረዳ አንድ ሰብሳቢ

Photos from Addis Ketema Woreda one youth association's post 09/09/2023

***** # *****
የአዲስ ከተማ ወረዳ 1 ወጣት ማህበር
የክ/ከተማችን አመታዊ ሱፐርቪዥን በወረዳችን የመጨረሻ ዙር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
የመጪው አዲስ አመት በማስመልከት የወረዳ 1 ወጣት ማህበር የወረዳችን የወጣት ማህበር አባላትና የአዲስ ከተማ የወጣት ማህበር ስራ አስፈፃሚ አመራሮች በጋራ ደማቅ ፕሮግራምና ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳ ፕሮግራም አድርገናል።

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

#የእናታችን_ምርቃት_ለእኛ_ጉልበታችን_ነው!!!
#ከክምችት_7በሁለቱ የመቻቻል መልዕክት የሆኑት#አንዋር_መስጊድ እና #ራጉኤል_ቤተክርስቲያንየፅዳት ዘመቻና የኬሚካል ርጭት ካከናወንናቸው ተግባራት በጥቂቱ
ገና ብዙ እንሰራለን ምርጦችሁሌም እኮራባችዋለሁኝ

Telephone

Website

Address

Addis Ababa