Degu Samrawi
የበጎ ስራዎች ማስተዋወቂያ
በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ ሕዝበ እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት የቆምኸው አንተው ነህና ለእኛም ታማልደንና ትራዳን ዘንድ በጸሎት እንማጸንሃለን።
አምላካችን እግዚአብሔርም የምሕረት ፊቱን ወደ እኛ በመመለስ በጸብና በጦርነት ምትክ ፍቅርን፣ ሰላምንና መግባባትን፤ በመለያየት ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን።
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡
ቅድስት ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ (መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፮፻፷፱)
ቅድስት ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ ደግሞ በሴት አንቀጽ /ቅድስት ሥላሴ/ ይጠራል፤ ‹‹ቅድስት›› እና ‹‹ልዩ ሦስት›› የሚባልበትም ሃይማኖታዊ ምሥጢር፡-
፩. ቅድስት
ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡ ሴት ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡ ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡፡
፪. ልዩ ሦስትነት
በትምህርተ ሃይማኖት ሥላሴ በቅድምና፣ በፈጣሪነት፣ በሥልጣን፣ በመመስገን፣ በክብር፣ በፈቃድ አንድ /እግዚአብሔር/ ሲሆኑ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡
አቤቱ ከክፍ ሁሉ ጠብቀን
በዓለ ደብረ ታቦር እና ቡሄ
ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡
ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡
እንኳን አደረሰን
በልጅነታችን ያልተውከን በወጣትነታችን የረዳኸን በጎልማሳነታችን የደገፍከን መድሐኔአለም ሆይ ቸርነትህ በዝቶልን አሁንም በምህረትህ ጎብኘን
ይህ ጊዜ የኑሮው ቅጥ ማጣት ለብዝዎች ከባድ ሁኗል በተለይም ለአረጋውያን በችግር ውስጥ ለሚገኙ ደግሞ ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ መገመት አያዳግትም እናም በአለችን ትንሽ የማስተባበር አቅም ልክ አንድ ሰው ካለችው ላይ አለያም ሁለት ሶስት በመሆን በቋሚነት በወር አለያም በሁለት ወር አንድ ሰው እንደ ቤተሰብ ተረክበን ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ብቻችንን ከምንሻገር መሻገር ያቃታቸውን ይዘን ማዝገም ስለሚሻል እኛ እናስባለን እሱ እግዚአብሔር ይፈፅማልና በእሱ ፈቃድ ዛሬ የመረካከቡን ስራ ጀመርነው።
አጥናፍ ይትባረክ ይባላል በሀገር መከላከያ 16 አመት ሰርቷል። ዛሬ በጡረታ በግል ስራ በትንሹ ተሰማርቶ የሚገኝ ወንድማችን ነው ኑሮት አይደለም ታውቁታላችሁ ነገር ግን ከሚያገኛት ላይ አስረክበኝ ብሎ ዛሬ እኝህን እናት በቋሚነት በየወቅቱ ሊጠይቅ የመጀመሪያውን ሃላፊነት ወስዶ አስረክበናል። የእውነት ደስም ብሎኛል። ወንድሜ አጥናፉ አንድ ብሎ ጀምሮታል እኛ ደግሞ እስኪ እናስፋውና ቢያንስ ከተማችን ውስጥ በርሃብ የሚጎዳ የሚሞት ሰው አይኑር።
እናም በዚህ መንገድ በበጎ ተግባር አብራችሁኝ መስራት ለምትፈልጉ በውስጥ መስመር አለያ በቴሌግራም ቻናሌ መመዝገብ ትችላላችሁ
ካለን ቀጥታ ከምትደግፏቸው አረጋውያን ጋር ማገናኘት ነውና ስራየ ከዚህም በላይ ማድረግ የምችለው ስለሌለ መላክ ነውና አድርስ አለያ መልክት መደወል ብቻ በቂ ነው አጥናፉ ወንድሜ ከልብ እናመሰግናለን የእናት አባቶች ፀሎትና ልመና አይለይህ ወንድሜ
እንኳን ለቅድስት ስላሴ አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ/መልካም ስራው እናመሰግናለን/
ደምበጫ ቅድስት ስላሴ ባዞላም በእለተ ቀኑ እንዲህ ተጠናቋል። የተሳተፋችሁ ያሰባችሁ ያስተባበራችሁ በሙሉ ክብሩን ያድልልን በዚሁም አንድ እህታችን መልካም ስራው ከውጭው አለም 1000/አንድ ሽህ ብር ለባዞላ መጠናቀቂያ በሚል ትናንት ገቢ አድርጋለች በአለሽበት ይጠብቅልን እናመሰግናለን።
ነገ ሁላችንም ወደ ንግስ
ወንድም እህቶቼ ሰላማችሁ ይብዛልኝ
አቶ ላቀ አለኸኝ ለአስር በችግር ውስጥ ላሉ የብርድ ልብስ ድጋፍ አደረጉ
እንደምታውቁት ክረምቱ ጠንከር እያለ ብርዱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት በፍሬ ደምበጫ በጎ አድራጎት ማህበር መጠለያ ቦታ ተጠልልለው ለሚገኙ 6/ስድስት/ አረጋውያንና ከውጭ በችግር ውስጥ ለሚገኙ 4/አራት በድምሩ አስር ብርድልብስ ከአዲስ አበባ ለወገኔ ይድረስልኝ ብለው አቶ ላቀ አለኸኝ በዚህ መንገድ በዕለተ እሁድ መልካም ነገር አድርገውልናል። ከልብ እናመሰግናለን።
ለተቸገሩ ወገኖች በአለሁበት አካባቢ መደገፍ ለምትፈልጉ በ0912745936 መደወል ይቻላል እንታዘዛለን
ኪዳነ ምህረት - 16
ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡
ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦ ". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9፥16
እናታችን ኪዳነ ምህረት ሆይ የአስራት አገርሽን ከአለም መፍትሔ አጠናልና ልጅሽ በቃችሁ ይለን ዘንድ ከልጅሽ አሳስቢ
እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ፫
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Office Addis Ababa
Addis Ababa, P.O.BOX21261,CODE1000
We are working for/with the most poorest and potentialy vulnerable elders in Ethiopia!
Bole Subcity, Woreda 03, Zewdu Gessese Bldg, House No. 2414/2nd Foor
Addis Ababa
We are visionary, committed and disciplined young Ethiopians passionate to make a positive difference in the lives of our fellow citizens and the humanity through community service...
Addis Ababa
Rotaract Club of Solyana is one of the 16 clubs in Ethiopia, and has been running since 2007 as a partner in service of Rotary International
Addis Ababa
RAC Ra'ey is a rotaract club with members of different professions and knowledge in Ethiopia working for the realization of Ethiopia's visions VISION IN ACTION!
Nifas Silk Lafto Sub City, Kore Mekanissia Area
Addis Ababa
We are a 501c3 non profit organization, our mission is to bring about transformation from the insideo
EiABC, Dej. Baltcha Aba Nefso Street
Addis Ababa
Welcome to the AIESEC in Ethiopia Official Fan Page! AIESEC is the World's largest student‐run organi
Opposite French Embassy
Addis Ababa
The School of St Yared opened in 2009 with the aim of offering a top class education to talented, imp
Addis Ababa
Addis Ababa, 41303
Great Commission Ministry Ethiopia on the journey of spiritual movement every where is impacting stu
Addis Abeba
Addis Ababa, FUTUREPARK
Goh Be Dembia Charitable Association
Ambo Street, Melka Gefersa
Addis Ababa, 10620,ADDISABABA
This is page of cancer care ethiopia. Updates about works will be presented here.