National Voluntary Association ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎ

National Voluntary Association ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎ

የገንዘብ ዕቁብ ብቻ ሳይሆን የሃሳቡን ዕቁብ በመጣል ለሀገራችን ኢትዮጵያ አንዲት ነገር እንስራ !!

23/08/2022

ግልፅ ደብዳቤ
ይድረስ ለኢትዮጵያ ለድሃው ማህበረሰብ መብት ለቆማችሁ

እኛ የአራተኛ ዙር የብሄራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች ከጅምሩ በሀገራችን በቅጥርም በብዛት የተገፋንበት ምክንያት ቀድሞ ተምሮ በስልጣን ያለ ዘመድ ወዳጅ ባለመኖሩና ተሰሚነት የሌለን ቤተሰቦቻችንም በዝቅተኛ የድህነት ደረጃ ያለን ልጆች መሆናችን እንዲሁም ባለንበት አካባቢም የመልካም አስተዳደር ችግርና በአመራሩ እየተሰሩ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ስለምንጋፈጥም ጭምር ነው ፡፡
®
ክቡር የሰላም ሚኒስተርና አቶ ብናልፍ እንዲሁም ሚኒሰትር አቶ ታዬ ደንዳ እኛ የኢትዮጵያ የመጨረሻው እርከን ውስጥ ያለን የድሃ ልጆች ለሀገራችን ካለን ንቁ ፍቅር የተነሳ እናንተ በምትመሩት የሰላም ሚኒስተር አስተባባሪነት አማካኝነት በአራተኛው ዙር የብሄራዊ በጎፈቃድ አገለግሎት ላይ በመሳተፍ የሀገራችን ያሉ ወደተለያዩ ማህበረሰቦች ጋር ሄደን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራን እንደምንገኝ ይታወቃል፡፡
®
ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ የፈረደባቸው ወላጆቻችን አሰቃይተን እራሳቸው አከራይተው እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አቆይተውናል አሁን ግን አይደለም በተሰማራንበት አካባቢ ቆይተን በጎ ፈቃድ ለመስጠት ወደ ቤተሰቦቻችን ጋር መመለሻ ትራንስፖር አተን እየተሰቃየን በመሆኑ እባክዎን የእርሶን ቀና አመለካከት ተጠቅማችሁ ከዚህ ችግራችን እንድታወጡን በድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንማፀናችኃለን፡፡
#ፍትህ
#ፍትህ

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
Addis Ababa