ወሎ ልማት ማህበር - Wollo Development Association.

WoDA is a local, non-profit, and non- partisan civil society organization.

Photos from ወሎ ልማት ማህበር - Wollo Development Association.'s post 30/12/2022
Photos from ወሎ ልማት ማህበር - Wollo Development Association.'s post 18/12/2022

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው "ወሎ የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ኮንፈረንስና ፌስቲቫል" በደሴ ከተማ እና በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው!

ወሎ በኢትዮጵያ የጥበብ፣ የእውቀት እና የትምህርት ማእከል ሆኖ ረጅም ግዜ አገልግሏል:: በዘመናዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ መንግስታት እና መንግስት አስተዳደር፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በዜማ እና ቅኔ እንዲሁም እደ-ጥበብ እና ስነ-ህንፃ የትምህርት ማእከል ነበር::

በአክሱም ክፍለ ዘመን መሰረቱ የተጣለው እና በክርስትናው ሃይማኖት ጥንታዊቅው እና ግዙፉ የሃይቅ እስቲፋኖሱ አባ እየሱስ ሞአ አንድነት ገዳም በኢትዮጵያ የመጀመርያው ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ብዙ ታላላቅ ሊቆችን አበርክቷል:: ሃይቅ እስቲፋኖስ በ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘመናዊ ቤተ-መፃህፍት እና የካሊግራፊ እና በአባ ሰላማ 2ኛው የሚመራ የትርጉም ስራ ማእከል ነበር::
የሸዋው የደብረሊባኖስ መስራች አቡነ ተክለሃይማኖት
የጣና ዳጋ እስቲፋኖስ መስራች አባ ሂሩተ አምላክ
የደብረ ባህረዩ መስራች አባ ጊዮርጊስ ዘ-ጋስጫ
የደብረ ጎል መስራቹን አባ በፀሎተ ሚካኤል
የደብረ ዳረቱ አቡነ አሮን እና የላስታው
የአክሱሙ አቡነ ኣላኒቆስ:- የአባ ሳሙኤል ዘ-ዋልድባ መምህር የዳውንቱ አቡነ እስትንፋስ - አቡነ ዘ-እየሱስ

በእስልምናው ሃይማኖት በአንድ ወቅት ብቻ ከ200 በላይ የምህርት ማእክላት ነበሩ። ለዚህም "አዝሃሩል ሃበሻ" ይባል ነበር። በሰሜን ወሎ የፈቂህ ዙበይሩ "ጉዋጉር" ማእከል፣ የጌታው ሙጃሂዱ ማእከል "ጀማ ንጉስ"፣ የጌታው ሰይድ እና የጀማሉዲን አንዩ ማእከል "አና"፣ በገርባ የነሼህ ጎጃም ማእከል፣ በእስልምና ሃይማኖት ትምህርት የመጀመሪያ የሆነው ዩኒቨርሲቲ ታላቁ "ዳና የልህቀት ማእከል" በሶስቱ የዳና ከዋክብት የበርካቶች መፍለቂያ ነው። የደባቱ ሼህ አህመድ ያሲን፣የቃጥባሬው ሼህ ኢሳ (ጉራጌ አገር)፣ የአብሬቱ ሼይ ቡሽራ ...የአልከሶው ሼህ በሽር (ስልጤ ሃገር)፣ የሐረሩ ሼህ ሙሀመድ በደቡብ ወሎ መቅደላ የማመዶች የትምህርት ማእከል - የሼህ አሊ ጎንደርና የሌሎች ታላላቅ ሊቆች መፍለቂያዋ ኮሬብ/የርማ፣ የባሆች ማእከል፣ ስስይ፣ ደገር። ከሚሴ አካባቢ ደግሞ የሙፍቲ ዳውዱ ደዌ። ሾንኬ፣ አማን አምባ እና ጡሩሲና ይጠቀሳሉ።

በዘመናዊ ትምህርት በንጉስ ሚካኤል ልጅ ወ/ሮ ስሂን ኑዛዜ የተገነባው የወ/ሮ ስሂን ት/ቤት ዋና ተጠቃሽ ነው። እነ ብርሃነ መስል ረዳ፣ ዋለልኝ መኮነን እና ሌሎች ታላላቅ ተማሪወች የተማሩበትም ነው:: የመጀመርያውን የሴቶች ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ያስገነቡት እቴጌ መነንም የወ/ሮ ስሂን ልጅ ናቸው።

20/11/2022
Photos from ወሎ ልማት ማህበር - Wollo Development Association.'s post 17/10/2022

ወሎ ልማት ማህበር - ወልማ / Wollo Development Association - WoDA

የወሎ ልማት ማህበር /ወልማ/ (Wollo Development Association (WoDA)) መንግስታዊ ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ እና ከማንኛዉም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ እና በኢፊድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁ.1113/2011 መሰረት በግንቦት 24 2013 ዓ.ል የተመሰረተ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው። ወልማ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስበት የሀገራችን ክፍል ሰሜን ምስራቁ የኢትዮጲያ ክፍል ቢሆንም፥ የድርጅቱ ገዥ እቅድ ሁሉንም የሀገራችን አካባቢወች ያካትታል።
የወልማ ገዥ እቅድ በየአካባቢያችን ብሎም በሀገራችን የሚስተዋሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የስነ-ምህዳር ቀውሶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ያስችላሉ ብሎ የለያቸውን ስልቶች እና እቅዶች በግልጽ አስቀምጧል። ካስቀመጣቸው እቅዶች ውስጥ ማህበረሰባችን የተለያየ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋወች ሲጋረጡበት ወልማ የህዝቡን መከራ ሊቀንሱ/ሊያቃልሉ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ነው። እንደሚታወቀው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት አብዛሀኛው የህብረተሰባችን ክፍል በተለይ የወሎ ሙሉ ዞኖችና ወረዳዎች የጦርነት አውድማ በመሆን ያሳለፉ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ማህበረሰባችን በጦርነቱ ንብረቱ የወደመና ወራሪው ሀይል የዘረፈውን ዘርፎ መዝረፍ ያልቻለውን አበላሽቶ( ከማሳ ላይ ያለው አዝመራ ሳይቀር) ሄዷል። በዚህ ምክንያት ማህበረሰባችን ለከፋ ችግርና ርሃብ የተጋለጠ በመሆኑ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች መልሶ ለማቋቋም ወሎ ልማት ማህበር ከተመሰረተበት እለት አንስቶ ለባለፈው አንድ አመት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ስራወች የሰራና በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ባለፈው አመት ጦርነት ሀብትና ንብረታቸው ለወደመባችው አርሶ አደሮች ለመልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን አንድ አውራ እና ሁለት ቄብ ፍየሎችን እያቀናጀ ለተጎጅ ገበሬዎች አከፋፍሏል። ይህ የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ከቱርክ ሀገር በተገኘ ድጋፍ የተከናወነ ሲሆን ብር 2, 646, 000.00 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ስድስት ሺ) ብር ወጪ ተደርጎበታል። ወሎ ልማት ማህበር ፕሮጀክቱን ሀኪድ እና ነጃሽ ከተባሉ ሁለት ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከ 15 - 24/06/2014 ድረስ ለ441(አራትመቶ አርባ አንድ አባወራ) ተደራሽ አድርጓል። በጦርነቱ ሀብትና ንብረታቸው ከተዘረፈባቸው በተጨማሪ ከወለጋ ጭፍጨፋ ሸሽተው በመጠለያ ውስጥ ላሉ የወለጋ ተፈናቃዮችም ድጋፍ ለማድረግ እና በአጠቃላይ ማህበረሰቡ የደረሰበት ውድመት በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ እና የማህበራዊ ቀውሱ ከፍተኛ በመሆኑ መጠነ ሰፊ ስራ መስራት የሚጠይቅ ስለሆነ ተጨማሪ ድጋፎችን በማፈላለግ ለተጎጅዎች የሚያደርስበትን ስርአት በመዘርጋት ተግባራቶችን እያከናወነ ይገኛል። ድርጅቱን ሁሉም በሚችለው አቅም በመደገፍ ለማህበረሰባችን የሚያደርገውን ድጋፍ አድማሱን ማስፋት ያስፈልጋል። ኑ በተባበረ ክንድ የማህበረሰባችንን ችግር እንቅረፍ እያለ ወልማ ጥሪውን ያቀርባል።

ወሎ ልማት ማህበር (ወልማ)

16/10/2022

ወሎ ልማት ማህበር - ወልማ / Wollo Development Association - WoDA

የወሎ ልማት ማህበር /ወልማ/ (Wollo Development Association (WoDA)) መንግስታዊ ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ እና ከማንኛዉም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ እና በኢፊድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁ.1113/2011 መሰረት በግንቦት 24 2013 ዓ.ል የተመሰረተ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው። ወልማ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስበት የሀገራችን ክፍል ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጲያ ቢሆንም፥ የድርጅቱ ገዥ እቅድ ሁሉንም የሀገራችን አካባቢወች ያካትታል። እንደሚታወቀው በሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ብዙ ንብረት የወደመና የሰው ህይወትም የጠፋበት መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ጦርነት ምክንያት ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ንብረት አልባ ሆነው የሚጠለሉበት ቤት፣ የሚለብሱት ልብስና የግብርና ስራቸውን ሊያከናውኑበት የሚችል በሬ ወይም እንስሶች አልቀውባቸው ለከፍተኛ ሰብአዊ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። ወልማ እነዚህ ችግሮች የእቅዱ አካል ስለሆኑ ችግሮችን ለመፍታት አንድ በሬ ለአንድ ገበሬና አንድ ቤት ለአንድ አባውራ በሚል ፕሮጀክት በመስራት ሀብት ሲያፈላልግ ቆይቷል። የተሰራውን ፕሮጀክት በመቀበል ህበብረት ባንክ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል በገባው መሰረት 377,567 ብር በድርጅቱ አካውንት ገቢ አድርጓል። ወልማም ፕሮጀክቶችን በማስፈፅም ድጋፍ ላደረጉ አካላቶች ግልፅ መረጃ የሚያደርስ ይሆናል።
ህብረት ባንክን ከልብ እያመሰገን የማህበረሰባችንን ሰብአዊ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሁላችንም ድጋፍ የሚያስፈልግ ስለሆነ ወልማን በመደገፍ የማህበረሰባችንን ችግር በጋራ እንቅረፍ።

ወሎ ልማት ማህበር (ወልማ)

21/06/2022

ወሎ ልማት ማህበር - ወልማ / Wollo Development Association - WoDA

የወሎ ልማት ማህበር /ወልማ/ (Wollo Development Association (WoDA)) መንግስታዊ ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ እና ከማንኛዉም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ እና በኢፊድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁ.1113/2011 መሰረት በግንቦት 24 2013 ዓ.ል የተመሰረተ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው። ወልማ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስበት የሀገራችን ክፍል ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጲያ ቢሆንም፥ የድርጅቱ ገዥ እቅድ ሁሉንም የሀገራችን አካባቢወች ያካትታል።
የወልማ ገዥ እቅድ በየአካባቢያችን ብሎም በሀገራችን የሚስተዋሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የስነ-ምህዳር ቀውሶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ያስችላሉ ብሎ የለያቸውን ስልቶች እና እቅዶች በግልጽ አስቀምጧል። በዚሁም መሰረት በወልማ ሲኒየር ተመራማሪወች የሚመሩ ጥልቅ እና አካታች የጥናት እና ምርምር ስራወችን ድርጅቱ በቀዳሚነት ሊያስፈጽማቸው እንደሚገባ ተቀምጧል። በምርምር ስራወች ግኝት ላይ የተመሰረተ ሰፊ የአድቮኬሲ ስራ መስራትም ሁለተኛው የድርጅቱ እቅድ አካል ነው። ሶስተኛው የድርጅቱ ገዥ እቅድ አካል የልማት ስራ ሲሆን በተለይም ትምህርት እና ስልጠና፣ ጤና እና የግብርናው ዘርፍ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። በመጨረሻም፥ በተለይም ማህበረሰባችን የተለያየ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋወች ሲጋረጡበት ወልማ የህዝቡን መከራ ሊቀንሱ/ሊያቃልሉ በሚያስችሉ ዘርፎች ላይ ሊሳተፍ እንደሚችል በገዥ እቅዱ በግልጽ ተቀምጧል።
ሆኖም ድርጅቱ ከተመሰረተበት እለት አንስቶ ለባለፈው አንድ አመት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የተለያዩ ግብርመልሶችን እየሰጠባቸው የሚገኙት ዘርፎች የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ስራወች ሲሆኑ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ አምስት ሚሊዮን ብር (ብር 5, 000, 000.00) አካባቢ የሚገመቱ ፕሮጀክቶችን ከተለያዩ ሀገር በቀል እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አስፈጽሟል። እነዚህንም ፕሮጀክቶች በተከታታይነት በዚሁ ገጽ የምናቀርብ ይሆናል።

ወሎ ልማት ማህበር (ወልማ)

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000
Other Addis Ababa non profit organizations (show all)
Noble Cause Elder Care and Support Noble Cause Elder Care and Support
Office Addis Ababa
Addis Ababa, P.O.BOX21261,CODE1000

We are working for/with the most poorest and potentialy vulnerable elders in Ethiopia!

Rotaract Club of Keroggie Rotaract Club of Keroggie
Bole Subcity, Woreda 03, Zewdu Gessese Bldg, House No. 2414/2nd Foor
Addis Ababa

We are visionary, committed and disciplined young Ethiopians passionate to make a positive difference in the lives of our fellow citizens and the humanity through community service...

Rotaract Club of SOLYANA Rotaract Club of SOLYANA
Addis Ababa

Rotaract Club of Solyana is one of the 16 clubs in Ethiopia, and has been running since 2007 as a partner in service of Rotary International

Rotaract club of Ra'ey Rotaract club of Ra'ey
Addis Ababa

RAC Ra'ey is a rotaract club with members of different professions and knowledge in Ethiopia working for the realization of Ethiopia's visions VISION IN ACTION!

Strong Hearts International Strong Hearts International
Nifas Silk Lafto Sub City, Kore Mekanissia Area
Addis Ababa

We are a 501c3 non profit organization, our mission is to bring about transformation from the insideo

AIESEC in Ethiopia AIESEC in Ethiopia
EiABC, Dej. Baltcha Aba Nefso Street
Addis Ababa

Welcome to the AIESEC in Ethiopia Official Fan Page! AIESEC is the World's largest student‐run organi

The School of St Yared, Ethiopia The School of St Yared, Ethiopia
Opposite French Embassy
Addis Ababa

The School of St Yared opened in 2009 with the aim of offering a top class education to talented, imp

imagine1day imagine1day
2Q3W+XV2 Imagine1day, Gabon Street
Addis Ababa, 1000

Educating people to transform themselves, their communities, and the world.

The Ethiopian Film Initiative The Ethiopian Film Initiative
Addis Ababa

Empowering Ethiopian filmmakers

Life4all Life4all
Addis Ababa
Addis Ababa, 41303

Great Commission Ministry Ethiopia on the journey of spiritual movement every where is impacting stu