Multi Ethnic Shoa

ሸዋ የትልቋ ኢትዮጲያ ማዕከልነቱን እንዳስጠበቀ ኅብረ ብሄራዊ ክልላዊ አስተዳደር ይዋቀራል፡፡

14/08/2023

ከሴራው ጀርባ ማን አለ??
=============
ባህርዳር ላይ አመጽ ከመቀስቀሱ በፊት የከተማዋ ባለሀብቶች አመጹን ለማሥተባበርና ለመምራት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ ነበር። እነሱም
1) #ሙለር ሪልስቴትና #ሆምላንድ ሆቴል ባለቤት (ሙሉጌታ ቢያዝን)
2) #ጃካራንዳ ሆቴል ባለቤት (ሀይሌ)
3) #ባህርዳር ሆቴል ባለቤት (በዛብህ አሥማማው)
4) #ድብአንበሳ ሆቴል ባለቤት (ሺባባው የኔአባት)
5) #ራሀናይል ሆቴል ባለቤት (መርዲያ እንድሪሥ እና አበበ ይመኑ)
==
እነዚህ ሁሉ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ከሚባለው ቡድን ጋር ልዩ ልዩ ትስስር ፈጥረው አመጽ ከመቀስቀሱ በፊት ከአመጹ በኋላ ስለሚኖረው አስተዳደር እና አመራር ድልደላ እና የመዋቅር ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር። እነዚህ ባለሀብቶች የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የሚባለውን ቡድን መሪዎች በሁለት ቢላ ከሚበሉ የብልጽግና መሪወች ጋር የሚያገናኙ እና የአመጽ እንቅስቃሴውን በመንግስት መዋቅር ያለው የብልጽግና አመራር ድጋፍ እንዲሰጥ ሲያደርጉ ነበር።
==
ባለሀብቶቹ ገንዘባቸውን በመጠቀም የብልጽግና እና የመንግስት ኃላፊወችን በእከከኝ ልከክህ በጥቅም በመደለል እና እነሱም በሆቴል ማስፋፋፊያ መሬት እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከአመራሩ በኩል በሚያገኙት ድጋፍ እየተጠቀሙ መንግስታዊ መዋቅሩን ተብትበው ይዘው ለሥርዓተ አልበኝነት ምክንያት ሆነዋል። ባለሀብቶቹ ለእነሱ የማይገብረውን ባለሥልጣን በማሕበራዊ ሜዲያ በዘመቻ መልክ ስሙ እንዲጠፋ በማድረግ እና በአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚባለው ቡድን አማካኝነት የደህንነት ስጋት በመፍጠር ሀቀኛ እና ለሕዝብ ተቆርቋሪ አመራር እንዳይኖር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁንም መፍትሄ ካልተበጀላቸው ይቀጥላሉ።
==
የክርስትያን ታደለ የአገር ልጅ እንዲሁም የቲና በላይ አጎት የሆነው የባህርዳር ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሣህሉ ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል እንዲሁም ከባለሀብቶቹ ጋር ጥምረት በመፍጠር የባህርዳር ከተማ ሥርአት አልበኝነት መፈንጫ እንዲሆን ተባባሪ ነበር። የቲና በላይ ባል የሆነው እና ኢንጂነር ማንችሎት የሚባለው የፋኖ አመራር እና እሱ የሚመራው ቡድን የጭስ አባይ የፌድራል ፖሊስ ጠባቂወችን መሳሪያ በመግፈፍ ብዙወችን ከገደለ በኋላ ወደ ባህርዳር ከተማ በመግባት ከትናንት ወዲያ የሳባታሚት ማረሚያ ቤት እንዲሰበር እና ታራሚወች ወጥተው እንዲበተኑ አድርጓል። ከዚህም በላይ መሳሪያ እና ተተኳሽ የተከማቸባቸው ፖሊስ ጣቢያወች ከበባ እየተደረገባቸው በቀላሉ ተሰብረው ዝርፊያ ሲፈጸም ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ደግሞ የከተማው ከንቲባ ድረስ ሣህሉ ባለው መዋቅራዊ ሰንሰለት በቲና በላይ በኩል ተባባሪ ሆኗል።
==
እዚህ ላይ ዋናው ነገር በባህርዳር ከተማም ሆነ ከክልሉ ውጭ ያሉ የአካባቢው ባለሀብቶች በአንድ በኩል በገንዘባቸው ባለስልጣናትን በመደለል መንግስታዊ መዋቅሩን በመዘወር ሥርዓት እና መርህ የሌለው መንግስታዊ አስተዳደር እንዳይኖር ሲያደርጉ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያለውን ኃይል በትክክል ሥራውን እንዳይሰራ የደህንነት ስጋት የሚሆን አስፈራሪ እና ሥርአተ አልበኝነት የሚፈጥር ኃይል በፋኖ ወይም በህዝባዊ ኃይል ስም ሲያደራጁ መኖራቸውን ነው። ብልጽግና ሥር ነቀል ለውጥ ካላመጣ እና ሁኔታውን ከሥር ከመሠረቱ ካልፈታው እንዲሁም ባለሀብቶቹ፣ ባለስልጣኖቹ እና አማጺወቹ ላይ አስተማሪ የማያዳግም ቅጣት እና እርምጃ ካልወሰደ ትናንት ያየነው ነገር ሁሉ መቀጠሉ አይቀሬ ነው።

Multi Ethnic Shoa

10/07/2023

"የዳሩ እሳት እኛም ጋር ደርሷል"

ዛሬ ከኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ የመጣን የቅርብ ዘመዴን አግንቼ ቀኑን ሙሉ የግፍ እና የመከራ መአት ስሰማ ዋልኩ። ንዴት እና ቁጭት ሲያነደኝ ዋለ። ህዝብ በዚ ልክ መውጪያ እና መግቢያ አጥቶ መከራውን ሲበላ የክልሉ ፕሬዝዳንት በብዙ ሺህ አጀብ እና ቪ8 አዲስ አበባ ላይ ሲንፈላሰስ ይውላል በጣም ያሳዝናል።

የኦነግ ሽኔ እንቅስቃሴ ከየትኛውም የኦሮሚያ ስፍራ ይልቅ እዚህ አካባቢ በርትቷል። በርግጥ ከወራት በፊት የቅርብ የምለው ቤተሰብ በዚህ ቡድን ታግቶ በገንዘብ ወጥቷል።ከአ.አ 155 ኪ.ሜ የምትገኘው እና ከ5-10ኛ ክፍል የተማርኩባት ደማቅዋ እና እንግዳ ተቀባይዋ ገ/ጉራቻ ከተማ ጭር ብላ ኦና ከሆነች ሰንብታላች።

የአባቴን የመቃብር ስፍራ ለማየትም ሆነ ለግል ጉዳይ እግሬን ለማንሳት ባልተፃፈ ደብዳቤ ከታገድኩ 3አመት እንደ ቀልድ አለፈ። ይህ ብቻ አይደለም እዛ አካባቢ የለው ችግር እዚህ ያለውን ቤተሰቤን ሊበትን ተቃርቧል። ሞት ምንድነው ከዚ በላይ ምን አለ....?

አቅም ያላቸው የክልሉ ባለስልጣናት ብዚዎቹ ችግር ካለባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ቤተሰባቸውን ማውጣት ከጀመሩ ሰንብተዋል።በዚህ አጋጣሚ የወለጋን ህዝብ ከአመታት በፊት ያን ሁሉ መከራ ሲያሳልፍ በሚገባ ድምፅ ስላልሆንኩለት ይቅርታ እላለሁ ዛሬ ላይ ህመማችሁ ስቃያችሁ ዛሬ ታመምኩት።

"ዳኛውም ዝንጀሮ ፣ ፍርድ ቤቱም ገደል
እምን ላይ ተቆሞ ፣ ይነገራል በደል "

Hana R Waktola

09/07/2023

The breathtaking landscape of Minjar , Amhara region, Ethiopia 🇪🇹
( Inside Africa)

07/07/2023

ደብረብርሃን!!
🔸አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በዘመነ መንግሥታቸው ሰሜን ምስራቅ ባህረ ነጋሽ (የአሁኑ ኤርትራና ቀይ ባህር)እስከ ዳህላክ ደሴቶች እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ እስከ ዛይላ ወደብ ድረስ የባህር በር እንዲኖራት በማድረግ በአውሮፓ ይገኝ ከነበረው የአራጎን ንጉስ አልፎንሶ ፬ኛ አንድ መቶ ሀምሳ መርከቦችን በማስገባት ኢትዮጵያን በእጅጉ ከፍ አድርጓል።
🔸15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሐገራችንየሥነ-ፅሁፍ አብዮት ወቅት ይባል ነቀር።ይህ ባህል የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባልነበረበት በዚያ ጊዜ ቀደምት ኢትዮጵያውያንብራና ፍቀው፣ መፃፊያ ቀለምና ሰበዝ አዘጋጅተው፣ ነበር አብዮት የተባለውን የስነ ፅሁፍ ዘመን ያደመቁት። ይህንን ወርቃማ ባህል አጠናክረው በመቀጠልአፄ ዘርዓ ያዕቆብም ራሳቸው 21 የሚደርሱ መጽሐፍትንፐዋል። ደርሰዋል።

🔸ንጉሱ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እነዚህና መሠል ወርቃማ ገድላቸው በመሠረቷት ከተማ ደምቆ በመፃፍ ለትውልድ ቅርስና ታሪክ ሆኖ ይኖር ዘንድ በትጋት እየሠራን እንገኛለን።

ፈጣሪ ለሐገራችን ሠላሟን የድላት፣ ህዝቦቿንም ይጠብቅ!

ቴዎድሮስ ደመቀ
የደብረብረሃን ከተማ ከስተዳደር ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ

29/04/2023

አቶ ግርማ የሺጥላን ያስገደለውን የፋኖ ቡድን የመራው የራያ ቆቦው በለጠ ሸጋው ይሄ ነው።

18/04/2023

- አጼ ምኒልክ ከመቅደላ ወጥተው ወደ አንኮበር ሊገቡ ሲሉ አቶ በዛብህ አይገቡም ብሎ ተዋጋቸው አጼ ምኒልክም ድል አርገውት አንኮበር ከገቡ በኋላ ሁሉን ረስተው ለአቶ በዛብህ ይቅርታ አደረጉለት፡፡
- አጼ ምኒልክ ከጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር ስለተጋጩ እንባቦ በሚባል ቦታ ጦርነት አድርገው የምኒልክ ጦር አሸነፈ አጼ ምኒልክም በጦርነቱ የተጎዱትን ንጉሥ ተክለሃይማኖትን በመንከባከብ እንኳን ተረፉ እያሉ ቁስላቸውን በማከም ይቅር ተባብለው መልካም ወዳጅ ሆኑ፡፡
- አጼ ምኒልክ ወደ ሐረርጌ ለጦርነት በሄዱ ጊዜ ራስ ጎበና በአዲስ አበባ ሆነው መንግስት ሊገለብጡ ነበር ተበለው ተከሰሱ በመኳንንቱም ዘንድ ጥፋተኛ ተብለው ሞት ተፈረደባቸው አጼ ምኒልክም የሞት ፍርዱን እንዲያፀኑ ሲጠየቁ"ጎበናን እዚህ ለማድረስ ሰላሳ ዓመት ፈጅቶብኛል ለአንድ ቀን ጥፋቱ ብዬ የሰላሳ ዓመት ድካሜን አላበላሽም ምሬዋለሁ እንደጥንቱ ይኑር" ብለው ይቅርታ አደረጉ፡፡
- ኢጣሊያዎች በመቀሌ ጠንካራ ምሽግ ሠርተው ከባድ ውጊያ በሚያረጉ ጊዜ ለውሃ ይጠቀሙበት የነበረውን ወንዝ የኢትዮጵያ ሰራዊት በመቆጣጠሩ ኢጣሊያዎቹ በዛው በምሽጋቸው እንዳሉ በውሃ ጥም ማለቅ ጀምሩ አጼ ምኒልክም ሁሉንም እዛው መጨረስ ሲችሉ ሠላሳ በርሜል ውሃ እና የሚጓጓዙበት በቆሎ ጭምር ሰጥተዋቸው በይቅርታ ሸኞቸው፡፡
- ታላቁን የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሰራዊት ድል ማረጉን ተከትሎ አጼ ምኒልክ የኢጣሊያን ምርኮኞች ላይ መከራ ያደርሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ አጼ ምኒልክ ግን ሁሉን ጠብቀው አቆይተው በሠላም ወደ ሀገራቸው በመስደድ ይቅር ባይነትን ለዓለም አሳዩ፡፡
☞☞ ነገሮች አልፈው ሠላም በሆንን ጊዜ ሁሉ የወጋንንም፣ የተኮሰብንንም የበደለንንም ሁሉ ይቅር ብለን ቂም በቀልን ረስተን ጠላት ከሆነብን ጋር ወዳጅ የምንሆንበት እንደ እምዬ ምኒልክ ያለ አላህ ይወፍቀን አላህ ይቅር ባዮችንምይወዳል ና

14/04/2023

መረጃ !

በትናንትናው ዕለት ትጥቃቸውን ባልፈቱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና በሲቪሎች ላይ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ገርቢ አካባቢ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሀ ቀበሌ ከ ቀኑ10:00 በኋላ እስከ 11:30 ባለው ጊዜ ውስጥ ጥቃት ደርሷል። በዚሁ ሁኔታ ያለው ዕውነታ ምንድነው?

1. መንግስት ያመቻቸውን የምርጫ ሪፎርም ተቀብለው የሚገቡበትን ተቋም መርጠው ካጠናቀቁ በኋላ በደብረብርሃን ከተማ አንድ ቀበሌ የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው የልዩ ኃይል አባላት ከፕሮግራሙ መጨረሻ የተስማሙትንና የሞሉትን ፎርም ትተው ወደ ሀገራችን ነው የምንሔደው ብለው ለዕዝ መሪዎቻቸው ይናገራሉ። ተው አትሒዱ እድሉን ተጠቀሙ የሚል ልመና ከአዛዦችም ከመንግስት ወኪልም ቢደረግላቸው ፈቃደኛ አልሆኑም።

እናም ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ሰሜን ወሎና ደሴ ለመሔድ በሀይሩፍ መኪና ከደብረብርሃን ተነስተው በሸዋሮቢት አድርገው ጉዞ ሲጀምሩ ጀውሀ አካባቢ መኪና ተበላሽቶ ይቆማል። በዚህ ጊዜ በጀውሀ ዙሪያ ያለ የኦሮሞ ብሔር ማህበረሰብ የልዩ ኃይል ዩኒፎርም የለበሱና ትጥቅ የያዙ መሆናቸውን ሲያይ ተሰባስቦ ጥቃት ይከፍትባቸዋል። ገሚሱ ጥቃቱን ለመቋቋም ተታኩሷል ፣ በተኩሱ የተጎዱ እንዳሉና ወደ የለንና ዋጮ ሸሽተው ያመለጡ እንዳሉ መረጃ ደርሶናል። በጥቃቱ ምን ያህል ተጎዳ የሚለው ገና እንዳልታወቀና የነበሩበት መኪና እንደተቃጠለ ከእውነተኛ ምንጭ መረጃ ደርሶናል።

2. በመቀጠል ከሲቪሎች ጋር ሆነው ከደሴ አቅጣጫ ትጥቃቸውን ይዘው ከምኒባሱ ፎርቶ መጋላ ላይ በመሆን እየተጓዙ እያለ ገርቢ አካባቢ ሲደርሱ ከልዩ ኃይሉ ወደ ሰማይ የጥይት ተኩስ ይሰማ ስለነበር ይሔ ደግሞ በአካባቢው ተኩስ የመሰባሰቢያ መልዕክት በመሆኑ የዛው አካባቢ ሰው ተሰባስቦ በሲቪሎችም ከላይ በነበሩት ልዩ ኃይሎችም ላይ ጥቃት ደርሷል። ምን ያክል ጉዳት ደረሰ የሚለው ገና በቀጠናው ያለ የሀገር መከላከያ እያጣራ ነው። በአካባቢው የተሰማራ የሀገር መከላከያ በአጣዬ፣ በሸዋሮቢት ወደ ደሴ መውጫ ጫፍ፣ በሰንበቴ አካባቢ ካምፕ አድርጎ ቀጠናውን እየጠበቀ ያለ ቢሆንም ጥቃቱ የደረሰው መከላከያ በሌለበት ቦታ ነው።

ይሔ ምን ያሳየናል ካልን አንድም ተግባብቶ ተመካክሮ የመረዳዳት ጉድለት፣ ሁለትም ልዩ ኃይል የተባለን ሁሉ ፍፁም የመጥላትና የመጠራጠር በሽታ ከልዩ ዞኑ በኩል አለመታረሙ ነው። በሌላ መልኩ የሁሉም ወገን ፅንፈኛ በሚከተለው ጭካኔ አዘል ተግባር ሰላማዊ ህዝብ አላግባብ ዋጋ እየከፈለ ነው። በቀጠናው ሰላም ለማስከበር የተሰማራው የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ የአካባቢውን አስቸጋሪነት ተረድቶ አሁንም ቁጥሩን ጨምሮ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ቢሰራ መልካም ነው እንላለን።

ከዚህ በዘለለ በርዶ የነበረን ጉዳይ ዳግም ለመቀስቀስ በሚመስል መልኩ ያልተደረገን ተደረገ፣ የተከሰተን ችግር ጠገግ አድርጎ አባዝቶና አጋኖ፣ የከረመን ፎቶ አቀናብሮ በፌስቡክ ፣ በቲክቶክ የማራገቡና ያልተገራ ንግግርና መረጃ መርጨት ለዳግም ችግር ይዳርግ ካልሆነ በስተቀር ትርፍ አይኖረውምና እንቆጠብ ። ችግሩ ግለሰብን ብሔር የማድረግ፣ ሁሌ የጥላቻ ንግግርና ያልተገራ አማርኛን መጠቀም፣ የሰው ሞትን የፖለቲካ አጀንዳ ማሳኪያ መሣሪያ የማድረግ እና ፍፁም ጭካኔን መከተል ነው። ከዚህ እንውጣ! ዝርዝር መረጃ ሲደርሰኝ ይበልጥ አደርሳለሁ።

ሰላም ለሀገራችን!!

12/04/2023

ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ችግሩ በውይይት ተፈታ።

ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎች እና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረገ።

በሰላም ስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል፣ የዞን፣ የምስራቅ አማራ ፉኖ አመራሮች እና የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም በግጭት የሚፈታ አጀንዳ እንደሌለና ሁሉም ጉዳይ በሰላምና በመወያየት መፍታት እንደሚቻልና በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በማዘናቸው ይቅርታም ጠይቀዋል ።

የፋኖ አደረጃጀት ህዝባዊና ከመንግሥት አደረጃጀት ውጭ በመሆኑ መንግሥት ባስቀመጠለት አማራጭ በመጠቀም ህጋዊ ወደሆነው መንግስታዊ መዋቅር እንዲገባ ምቹ ሁኔታ በመንግስት እንደተፈጠረም በመግለጫው ተመልክቷል ።

የዚህ ዓይነት የሽምግልናና የችግር አፈታት ስርዓት ማደግ እንዳለበትና ሌሎችም አካባቢዎች ከሰሜን ወሎ አባቶች በመማር በየአካባቢው የሚፈጠሩት ግጭቶችን በዚህ መልክ መፋታት እንዳለባቸው
ተገልፆዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ከዚህ በፊት በግላቸው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በማወያየት ወደ መደበኛ የጸጥታ አደረጃጀት እንዲገቡ ወይም ደግሞ ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።

©ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን

10/04/2023

ደብረብርሃን‼️
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 2/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦

በዚህም መሠረት

1 . በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ፤

2 . በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፤

3 .በከተማ አስተዳደሩ ለጸጥታ ማስከበር ተልዕኮ ከተሠጠው የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4 . ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

5 . በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው ።

6 . በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

7 . በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

8 . የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
👉የልዩ ኋይል ፣
👉የፓሊስ ፣
👉የመከላከያ ሠራዊት ፣
👉የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ማድረግ ፣ መንገድ መዝጋት የተከለከለ ነው።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ በከተማችን በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው

12 . ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

13. በከተማው ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል።

14. በከተማችን በተፈናቃይ ካምፕ የምትገኙ ተፈናቃይዎች ከምሽቱ 12:00 እስከ ጠዋቱ 12:00 ባለው ጊዜ ከካምፕ ውጭ መውጣት አይቻልም።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት

ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ/ም
ደብረብርሃን፣

06/04/2023

በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ እንሳሮ እና መራሐቤቴን የሚያገናኘው አገር አቋራጭ የጀማ ድልድይ በቀን 27/7/2015 ዓ.ም ሁለት ሲኖ ትራክ ተከታትለው ሲሆዱ አንዱ ሲኖ ትራክ የውሃ መያዣ ቦቴ የጫነ ሲሆን አደኛ በዶውን ሲጓዝ ባልታወቀ ምክንያት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል።

04/04/2023

የሸገር ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ናቸው በሚል እያፈረሳቸው ባሉት ቤቶችና በዜጎች ችግሮች ጉዳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የጀመሩት ሽምግልና ጥረት አበረታች ፍንጭ እያሳየ ነው።

በትናንትና እለት በዚሁ ጉዳይ ላይ ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ በመገኘት ከአቶ ሽመልስ ጋር ሰፊ ዉይይት አድርገዋል።

በዉይይታቸውም ሼህ ሀጂ ህገ ወጥነት መከላከላከል ተገቢ ቢሆንም ለዜጎች ችግሮች መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ በዝርዝር የዜጎችን አቶ ሽመልስ ቤቶች እየፈረሱ ያሉት ህገወጥ ስለሆኑና ህገወጥነትን መዋጋት ግደታችን ስለሆነ እንጂ እኛም ለዜጎች ሳናስብ ቀርተን አይደለም።» በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

በዉይይታቸው መጨረሻም አቶ ሽመልስ ህግ ባከበረ፣ህግ ወጥንነት በማያበረታታ እና የኦሮሞን ሕዝብ አቃፊነት በሚያሳይ መልኩ በሸገር ከተማ ቤቶቻቸው ለፈረሰባቸው ዜጎቻችን ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር መክረው በቅርቡ መፍትሄ እንደሚፈልጉ ለሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቃል ገብተዋል።

31/03/2023
27/03/2023

'ሼህ ቃሲም' እና 'ቅድስት ሥላሴ'... !
'ዓብይ ፆም' እና 'ወርሐ ረመዷን ፆም'... !
❤🌹❤🌹❤
'የትልቅ ሕዝብ ልጆች ነን፤ ትልቅ ነበርን፣ ትልቅም እንሆናለን' የምንለው ያለፉ አሉታዊ የታሪክ ዝክሮች ላይ ብቻ በመቸንከር ሳይሆን የቀድሞዎቻችንን ገንቢና ተምሳሌታዊ ውርሶችንም በማጉላት ነው።
ቀጥሎ ያለውን ከዓመት በፊት አጋርቻችሁ የነበረ ሲሆን እነሆ የዓብይ ፆምና የወርሐ ረመዷን ፆም በገጠሙበት አጋጣሚ ላይ በመሆናችን በድጋሚ እነሆ እላለሁ።
መልካም ፆም !
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
'ሼህ ቃሲም' እና 🌿ቅድስት ሥላሴ🌿
ከመዲናችን 90 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው ደብረ ጽጌ(ሸረሮ) ከተማ ጥቂት ወጣ እንዳሉ ጥንታዊቷን ደብረ ከርቤ ቃሲም ስላሴ ቤተ ክርስቲያንን ያገኛሉ።
'ቃሲም' የሚለው የሙስሊም ስም ከክርስቲያናዊው ምስጢረ መለኮት 'ቅድስት ሥላሴ' ጋር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምስረታ ጀምሮ እንደሚጠራ ስንሰማ ለዛሬው ዘመን ሰዎች ሊደንቀን ይችላል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ በመንፈሳዊ ምሪት አሁን ባለችበት ቦታ ስትመሰረት አከባቢው 'ሼህ ቃሲም' በሚባሉ ዓሊም ይጠራ እንደነበር ይነገራል። ቦታውም የእኒሁ ሙስሊም የሀገር ልጅ የነበረ ሲሆን ለኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሀገራቸው ልጆች ቤተክርስቲያን እንዲያሠሩበት አበረከቱ።
በጣም የሚደንቀው እኒያ የጥንት ሙስሊምና ክርስቲያን አባቶቻችን እንዴት ያለ የከበረ መንፈሳዊ ጸጋ እና ተምሳሌታዊ ምግባር እንደነበራቸው የሚያሳየው፥ የተዋህዶ ልጆችም ለአከባቢው ስያሜ መጠርያ የነበረውን የእኒያን አባት(ሼህ ቃሲም) ስም እየተወሳ እንዲቀጥል ያደረጉበት አስተውሎት ነው። Akkamitti nama dinqisiisaa yaa jamaa ! Akkamitti nama gammachiisa !
ዛሬም በሁለቱ ታላላቅ ዕምነት ተከታዮች መካከል ከዕምነቶቻቸው አስተምህሮ የሚመነጭና ከቀደምት አባቶች በተወረሰ የከበረ ስብዕና ገንቢ የትብብርና የመተሳሰብ ዝክሮች በየቦታው ይታያል። ይህም የበለጠ ጎልብቶ እንደሚቀጥል ምንም ጥርጥር የለውም።
የማስታወሻ ፎቶ፥ በቅዱሱ ስፍራ- እኔ፣ ታናሽ ወንድሜ ዮቤ(Eyobed Atakilt) እና ኤርሚ(Ermias Kiflewengel)።
ክብር ሁሉን ካለመኖር ወደመኖር ላመጣ ቸር አምላክ ይሁን !
እግዚአብሔር ታላቅ ነው !
አስተዋይና ቀና ልቦና ይስጠን 🌿🌻🌹

27/03/2023

እንሳሮ ወረዳ
ለሚ ከተማ
ሰሜን ሸዋ

20/03/2023

ዛሬ ጊዜ የጣለኝን ቦታ ተመልከት

♥ ከደብረብርሃን ድንኳን የሰማሁትን ♥

ልጄ አሉኝ አንድ አባቴን የሚመስሉ አባት ሽምግልና በውብ ሽበት ያደመቃቸው ደከማ አባት እጅግ በደከመ ቁጭትና ንዴት ባበገነው ስሜት ሁለቱም ዓይናቸው ሊያነባ እየፈለገ

ታውቃለህ ልጄ 6ጥንድ በሬ፣ 7 አህያ ፣ አንድ በቅሎ እና 30 ፍየለ ለዓይን የሚከብድ ሰፊ እርሻ ነበረኝ ደግሞ እኔ የአንተ አባት አራት የቆርቆሮ ቤት ነበረኝ ኋላ ራሴ ባሳደጓቸው ልጆች ዓይኔ እያየ በሬዎቼን ፣ ፍየሎችንና ንብረቴን ወሰዱት ፣ ያኔ ተበሳጨው ልቤ ነነደ ወንድነቴ ፈተነኝ። ግን የሚስቴን ወንድም ዓይኔ ፊት ገለውት ስለነበር ለራሴ ሳይሆን ለልጅ ልጆቼ ለህፃናቱ ፈራውና ሸሸው

አየከ ዛሬ ያለሁበትን ሁኔታ በተራ የድንኳን ዳስ ውስጥ ነኝ ያኔ በሃገሬ የእኔ ከብቶች እንኳን በር ያለው የማያፈስ ንፁህ በረት ውስጥ ይኖሩ ነበረ ፣ ዛሬ ግን እኔ ሜዳ ላይ ወድቄ አቅመ ቢስ ሆኛለሁ ፣ ቀንም ማታም ይበርደኛል ፣ ዝናቡ ከዘነበ በድንኳን ስር ጎርፍ ይገባል ያኔ ቆመን እናድራለን።



ተመልከት ዛሬ ከከብቶቼ ያነሳ ባዶ ሜዳ ላይ ነኝ

ያያ ዘልደታ ያሬድ

15/03/2023

የእምዬ ምኒልክ ዘረኝነትን ለመከላከል ያወጡት አዋጅ

ይህ አዋጅ የወጣው የትግራዩ ባላባት ደጃች አብርሃ ምንም በትግራይ አገረ ገዢ ሆነው በእምዬ ቢሾሙም ሸፍተው ነበር። ነገር ግን ወታደር ተልኮ ጦራቸው ተሸንፎ እሳቸውም እጅ ከሰጡ በኋላ አንዳንድ ባለጌዎች የትግራይ ተወላጆችን መሳደብ ጀምረው ነበር። ነገር ግን ይህንን የሰሙት አባታችን እምዬ ይሄንን ነውረኝነት ለማስቀረት ታች የሚገኘውን መቀጫም የሚያስከትል አዋጅ በ1902 አወጡ።

እምዬ ያችን አንድ አድርገው ከቅኝ ገዢ ጅብ መንጋጋ አውጥተው የሰጡንን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አሳዛኝ ሁኔታ ቢያዩ እንዴት ያዝኑ ነበር። እምዬ አሁንም እስከ መቼም ንጉሥ ናቸው።

15/01/2023

ቤዛ ሳህሌ የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ አሸናፊ ከሸዋ

15/01/2023

ቤዛ ሳህሌ ከ ሸዋ የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ አሸናፊ እና የአማራ ቱሪዝም አምባሳደር ሆናለች‼️

10/01/2023

የበላይ ዘለቀ 3 አያቶቹ ወሎ ሲሆኑ አንድ አያቱ ጎጃም ሸበል በረንታ ነው። በላይ የተወለደው ደግሞ ወሎ ወግዲ ነው ስለዝህ ደጃች በላይ ዘለቀ የወሎ ከፍ ሲል የአትዮጵያ ነው። ራስ መስፍን ስለሽ ጎጃም ሄደው ነው በአርበኝነት የታገሉት ስለዝህ ራስ መስፍንን ጎጃም ናቸው ልንል ነው ማለት ነው????? በእርግጥ ሸዋ ታሪኩን አያስቀምስም በወያኔ ጥርስ የተነከሰበትም በዚህ ነው። ሲጀመር ለንጉሰ ነገስታችን ምላስ በማመላለስ አባ ኮስትር በላይ ጥርስ እንዲነከስበት ያስደረጉት እና ያለ ርስቱ ከየትም መጥቶ ተሹሞብን እያሉ አቤቱታ ክስ ሲያቀርቡበት የነበሩት የጎጃም ሰወች ናቸው። እንደ ጎጃሜ ቢያዩት እንዴት እንደዚያ ይላሉ። ደጃች በላይ ዘለቀን ጎጃሜ እንዲሆን በሚገባ በሙዚቃ እየተቀናበረ ስለተሰራ ብቻ ነው ጎጃም የሚመስለው። ዙሮ ለኢትዮጵያ ዋጋ ቢከፍልም ደርግ ነገስታቱን ለማሳጣት ሆነ ብሎ ስሙን በትያትርና በሙዚቃ ከፍ ስላደረገው ነው እንጂ የተለየ ተአምር ተደርጎ መጨቃጨቂያ አይሆንም ነበር።

Photos from Multi Ethnic Shoa's post 03/01/2023

በመሪነት ዘመን ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ ክብርና ኩራት ነው- የበጎ ሰው

በመሪነት ዘመን ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ ክብርና ኩራት በመሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ለዚህ ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ የበጎ ሰው ተሸላሚው አቶ ግርማ ወንድአፍራሽ ተናገሩ።

በታሪክ አጋጣሚ ያገኙትን የመሪነት ዕድል በቅጡና በልኩ ተወጥተዋል፤ የ82 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ እና የበጎ ሰው ተሸላሚው ግርማ ወንድአፍራሽ።

አቶ ግርማ ወንድአፍራሽ ለሽልማት ሲጠየቁ “በሽልማቴ ፈንታ ድልድይ ይሰራልኝ” በማለት የሕዝብ አለኝታነታቸውን በተግባር ያሳዩ ታላቅ የሀገርና የሕዝብ ባለውለታ በመሆን ስማቸው በብዙዎች ዘንድ ይነሳል።

እርሳቸው በተወለዱበት ቀዬ፣ ባደጉበት መንደርና በመሩት ሕዝብ መሀል እንደስማችው የገዘፈው ግርማ ዛሬም አብሯቸው ዘልቋል።

በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር መንዝ አውራጃ አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ የተወለዱት አቶ ግርማ ወንድአፍራሽ፤ በሰሜን ሸዋ ወረዳዎች ተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ለረዥም ዓመታት መርተዋል።

ባገለገሉባቸው ቦታዎችና ወቅቶች የመሪነትን ልኬት በግብር የገለጹ፣ ዛሬም ሕያው የሆኑ ዘመን ተሻጋሪ አሻራቸውን አትመዋል።

በተለይም በተወለዱባት አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ በአስተዳዳሪነት በቆዩባቸው ስምንት ዓመታት የልማት አሻራቸው ለመሪዎች ሁሉ አርዓያ ተደርጎ ይወሳል።

በማምሻ ዕድሜያቸው ኑሯቸውን በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ከተማ በሆነችው መኮይ ያደረጉት አቶ ግርማ፤ በነዋሪው ተከብረው እና ተወደው ይኖራሉ።

ለምን? ቢሉ የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ እና አካባቢው ሕዝብ ዕውቀት የገበየው፣ ርሀቡን ያስታገሰው፣ ኑሮውን ያሻሻለው፣ ተዘዋውሮ ግብይት የሚፈጽመው በአቶ ግርማ የልማት አሻራዎች ነውና።

የኢዜአ ሪፖርተር በትውልድ መንደራቸው ተገኝቶ ያነጋገራቸው አቶ ግርማ ወንድአፍራሽ፤ በዘመናቸው ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ቤት፣ አራት ጤና ጣቢያዎች፣ መንገድና ሌሎች መሰረተ-ልማቶችን ማሰራታቸውን ያስታውሳሉ።

ይህም “ያልተማረ ሕዝቤ ዕውቀት እንዲገበይ፣ ከበሽታ እንዲፈወስና እንዲያመርት መሰረተ-ልማት በመገንባት የተቻለኝን አድርጌያለሁ፤ ፈጣሪም አግዞኛል” ይላሉ።

ሌላው በጉልህ የሚጠቀሰው ሚናቸው በአስተዳዳሪነት ዘመናቸው በ1977 ዓ.ም የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ሕዝባቸው በድርቁ ክፉኛ ተጎድቶ፣ በርሀብ አለንጋ ሲገረፍ፣ ህፃናት በሞት ሲረግፉ የታደጉበት ጥበብ ነው።

በወቅቱ አካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ መልክዓ ምድር በመሆኑ አቶ ግርማ የወቅቱን የወርልድ ቪዥን ኃላፊ አየር ማረፊያ ቢኖር እንደሚረዱ ስለገለጹላቸው፣ 3 ሺህ 600 ሰዎችን በማስተባበር በአንድ ቀን ጊዜያዊ የአውሮፕላን ማረፊያ አሰርተው ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ አድርገዋል።

በወቅቱ ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በማሰራታቸው የወርልድ ቪዥን ኃላፊ ለሽልማት ሲጠይቃቸው “በሽልማቴ ፈንታ የቦርከና ወንዝ ድልድይ ይሰራልኝ ” በማለት ድልድዩ ተሰርቶ ዛሬም ድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በድርቅ ወቅት ወላጆቻቸውን ያጡ በርካታ ህፃናት ‘አባታቸው ግርማ፣ እናታቸው ኢትዮጵያ’ ተብለው በአገር ውስጥና ለውጭ አገር ጉዲፈቻ እንዲሰጡ አድርገዋል።

ወድቆ የተገኘን ህፃንም ባለቤታቸው አጥብተው እንዲያሳድጉ ያደረጉት አቶ ግርማ ወንድአፍራሽ ታትሮ መሥራትን፣ ለሕዝብ ተጨባጭ ለውጥ ፋና ወጊነትና ከሰብዓዊነት ጋር አጣምረው ሰርተዋል።

በአካባቢው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቆሙ በማድረግ ማኅበረሰብ እንዲሰለጥን በጎ ሚናም ተወጥተዋል።

ከከሚሴ እስከ መኮይ የመኪና መንገድ፣ የቦርከና ወንዝ ድልድይ፣ ለእርዳታ አውሮፕላን ማረፊያ በማሰራት ሕዝባቸውን ከተጨማሪ እልቂት ታድገዋል።

በዚህ አኩሪ ታሪካቸውም በ2011 ዓ.ም የ7ኛው ዙር በመንግሥት ተቋማት ኃላፊነት ዘርፍ የበጎ ሰው ተሸላሚ መሆን የቻሉ ታላቅ የሕዝብ ባለውለታ ናቸው።

በሦስት ሥርዓተ-መንግሥታት ውስጥ ያለፉት አቶ ግርማ፤ “ሁሉም ነገር አላፊ ነው፤ በመሪነት የተሰየሙ ግለሰቦች ከግል ጥቅም ይልቅ ወገንን የሚያግዝ፣ አገርን የሚለውጥ ሥራ መሥራት ይገባቸዋል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህ ወቅት እንደ አገር የተጀማመሩ በምግብ ራስን የመቻል እንቅስቃሴዎችን አድንቀው፤ በተለይም በስንዴ ረጂነት ሰበብ ጫና የሚያደረጉ የውጭ ኃይሎችን ተጽዕኖ ለመቋቋም ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡ በሁሉም አካባቢዎች በሰላም አምርቶ የሚኖርበት ድባብ ሊፈጠርም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

18/11/2022

ሰዎች ታሪክ የሚያውቅ ታሪክ ሲነግራችሁ ተማሩ::ሙ/ጥ/ዲ/ን ዳንኤል ይህንን እውነት የጻፈው መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ነው::ጽሑፉም አስታራቂ እንጂ ምንም ችግር የለበትም::

ስንቶቻችሁ የአክሱምን ሕዝብ ታውቁታላችሁ? ዲ/ን ዳንኤልን በእዚህ ጽሑፍ ሾላ በድፍን በሆነ አነጋገር እየተረጎማችሁ ትዊተር ላይ የጻፈውን ኮፒ እያደረጋችሁ የምትወቅሱት ሰዎች ገብቷችሁ ነው? የታሪኩን እውነተኝነትስ ታውቁታላችሁ?

እኔ በመንፈሳዊ ጉዞዎች ወደ ሦስት ጊዜ አክሱምን ለመርገጥ እድል ገጥሞኛል::አንዳንዱ ጉዞ እስከ ሦስት ቀናት ስቆይ አክሱም ነዋሪዎች ከአድዋ ይልቅ ጣና በታሪክ እንደሚቀርባቸው ሌላው ቀርቶ ያኔ በእኔ ጉዞ ዘመን የነበሩትን ቅዱስ ፓትሪያሪኩ አቡነ ጳውሎስን አክሱም ጽዮን እንዳይረግጡ የአክሱም ካህናትና ሽማግሌዎች ወስነው ስለነበር ለምን ብዬ ስጠይቃቸው ከጣልያን ጊዜ ጀምሮ አድዋ ጋር የተጣሉበትን በኋላም በወያኔ ዘመቻ ጊዜ የደረሰባቸውን ቁጭ ብለው አዛውንቶቹ አውርተውኛል::

ቅዱስ ያሬድ ጣና ገዳም የኖረው የትስስሩ ዳራ ነው::ዲ/ን ዳንኤልን ስለ አክሱም ልታስረዱት ስትሞክሩ የአክሱም ሕዝብ ይስቅባችኆል:: ዲ/ን ዳንኤል የአክሱምን ሙዜም ሥራ በማስተባበር ብዙ ሃሳቦች በማመንጨት የሰራውን የአክሱም ሕዝብ ያውቃል::ዛሬ ደርሳችሁ በአክሱም አንፃር ለመጥቀስ መሔድ አለማወቅ ነው::

በመጨረሻ የአክሱም ሕዝብ ከአድዋ ይልቅ ለሌላው ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለእውነት እንደሚቀርብ ለማወቅ አቡነ መርቆርዮስ በስደት እያሉም ስማቸውን ሳያቋርጡ በመጥራት የአክሱም ካህናት ብቸኛ በኢትዮጵያ ምድር የነበሩ ካሕናት የሆኑት አቡነ ጳውሎስ አድዋ ስለሆኑ በሚል ከማድላት ስለፀዱ ነው:: አንድ ጊዜ ስለ አክሱም ጉዳያችን ላይ የዛሬ አስር ዓመት የጻፍኩት ሊንክ ( https://www.gudayachn.com/2012/12/blog-post_20.html?m=1) ያንብቡት::ጽሑፉ መሃል ላይ የአክሱሙ ሰው ምን እንዳለ የጆሮና የዐይን ምስክሬን ነው የጻፍኩት::

የዲ/ን ዳንኤል ጽሑፍ አስተማሪ እና መሬት ላይ ያለውን እውነታ ይዞ የሚያቀራርብ እንጂ ሌላ ችግር የለበትም:: ዛሬ ላይ ሆኖ ሲነገር የሁላችን ዐይን በሌላ እያየን መረዳት አቃተን እንጂ መልዕክቱ በቀና ለሚመለከት ሁሉ ችግር የለውም::
Getachew Bekele

14/11/2022

በደራ ወረዳ በጉንዶ መስቀል የገባው የሸኔ አሸባሪ ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀሩ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ተደምስሰዋል። በአሁኑ ሰዓት ጉnዶ መስቀል እንደ ወትሮዋ ሰላሟ ተረጋግጧል።

08/11/2022

ይባላል! (ሽመልስ አልጋዚ)
ከመሃልሜዳ_አጣዬ የሚያስኬድ መንገድ ነው።

ይህ መንገድ ሲያልቅ የአጣዬ ሽንኩርትናፍራፍሬ በቀላሉ መሃልሜዳ ፣ ዘመሮ ፣ ሞላሌ ፣ ወገሬናግሼ ሌሎች ከተሞች ጋር የገበያ ትስስር ይፈጠራል።

20/10/2022

ዶክተር በለጠ ሞላ በተሰጥኦ ማበልጸጊያ ፕሮጀክት ምረቃ ካደረጉት ንግግር

14/10/2022

አቡነ መልከፄዴቅ ገዳም

ዋሻ ደብረ መድኃኒት አቡነ መልከፄዴቅ አንድነት ገዳም በሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሃን ከተማ 195 ኪ.ሜ ከሚዳ ወረሞ ወረዳ ዋና ከተማ መራኛ ከተማ 4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው አስደናቂ ገዳም ነው፡፡

አቡነ መልከፄዴቅ ገዳም ተፈጥሯዊ ዋሻ ውስጥ በልዩ ጥበብ በመገደሙ፣ የቅዱሳን ነው ተብሎ የሚታመን አጽም ወይም አስከሬን ሳይፈርስ እና ሽታ ሳያመጣ ለዘመናት ያቆየ ቦታ በመሆኑ፣ በአካባቢው መንፈስን በሚያሳርፍ ማራኪ ተፈጥሯዊ አቀማመጥ እና ለቦታው በተሰጠው ቃል ኪዳን በርካታ ጎብኝዎችን ማስደነቅ እና መሳብ የቻለ ገዳም ነው፡፡ 836 ደረጃዎች ደግሞ ምዕመናኑን ከገዳሙ በቀላሉ ማድረስ ተሰርተዋል፡፡

የገዳሙ መስራች አቡነ መልከፄዴቅ ትውልዳቸው ጎጃም ሲሆን ከምንኩስና በኋላ በፈጣሪ ተመርተው ወደ ዋሻው እንደገቡና እንደመሰረቱት ይታመናል፡፡ እስከ ህልፈተ ስጋቸውም በዋሻው ኑረዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ገዳሙ በስማቸው ይጠራል፡፡

ጥቅምት 13/14፣ ግንቦት 4 እና 16 የአቡነ መልከፄዴቅ ዋና የክብረ በዓል ቀናት ናቸው፡፡

13/10/2022

ደብረብረሃን

ወጣቶች ከአመራሩ ጋር ተናበው የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ለመከወን እየመከሩ ነው።

የሚያኮራ ተግባር ነው።

ያልተቀናጀ የልተደጋገፈ ያልመከረ ትውልድ አይሻገርም

ምከሩ!!

Gashaw Debebe

12/10/2022

የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩን 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩን 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታወቀ። የልደት በዓሉ ዋና ዓላማ የጀነራል ታደሰ ብሩ ተሞክሮ እና ለሀገር ያደረጉትን አስተዋጽኦ ለትውልዱ ለማስተማር እና ለመዘከር እንዲሁም በጀነራል ታደሰ ብሩ ስም የተቋቋመውን ፋውንዴሽን ለመደገፍ እንደሆነም ተነግሯል።

የልደት በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን የጀነራል ታደሰ ብሩን የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ምርቃት፣ ሩጫ ውድድሮች፣ ጥያቄና መልስ ውድድር እና የፎቶ ዐውድ ርዕይ እንደሚካሄድ ተገልጿል። በዚህም የፋውንዴሽኑ አዲስ ሎጎ ይፋ እንደሚሆን ተመልክቷል።

በፌናን ንጉሴ
ጥቅምት 2/2015 (ዋልታ)

12/10/2022

አቶ ግርማ ሰይፉ የኢዜማ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ይህን ብሏል።

ሪፖርተር፡- ኢዜማ በቅርቡ የአመራር ምርጫ በማድረግ የአመራር መተካካት ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህ ምርጫ ሒደት ደግሞ በተፎካካሪዎች መሀል የሐሳብ ልዩነት መታየቱ ይታወሳል፡፡ ከምርጫው በኋላ የሐሳብ ልዩነቱ ተፈቶ ሁሉንም ወገን ባቀፈ ሁኔታ ነው ፓርቲው እየተጓዘ ያለው?

አቶ ግርማ፡- የሐሳብ ልዩነት ያለውን ሰው የግዴታ እዚህ ውስጥ ካልገባህ አትለውም፡፡ ለዚህ እኮ ነው ውድድር የሚያስፈልገው፡፡ ሐሳብ ታቀርባለህ፣ ውድድር ታደርግና ያሸነፈው ኃላፊነቱን ይረከባል፡፡ የኢዜማን አመራርነት የሚይዘውና ሥራ የሚያስፈጽመው በምርጫ ያሸነፈው ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አንዳንድ ሰዎች ከአባልነት ወጡ የሚባለውስ?

አቶ ግርማ፡- ከአባልነት መውጣት ልክ እንደ መግባት መብት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ልክ ነው እላለሁ፡፡ እንዲያውም የማታምንበት ፕሮግራምና ፖሊሲ የሚፈጸምበት ፓርቲ ውስጥ ምን ታደርጋለህ? አጠቃላይ በፓርቲው ማዕቀፍ ውስጥ መቆየት ይስማማኛል፣ በሐሳብ ብሸነፍም በሌላ ዙር አሳምኜ እመረጣለሁና እስከዚያው ግን የፓርቲውን ሥራ እፈጽማለሁ የሚል ሰው ከፓርቲው ጋር ለመጓዝ አይቸገርም፡፡ የፓርቲው ዲሲፕሊንም ይኸው በመሆኑ፣ በፓርቲው ውስጥ ያለው ስብስብም ይህን የተቀበለ ነው፡፡ አንዳንዱ ራሱ የሣላቸው አንጋፋ ሰዎች አሉት፣ ግን ይህ ልክ አይደለም፡፡ እኔ አሁን ከኢዜማ ብወጣ ማን ነኝ? አንድ ስንጥር ማለት ነኝ፡፡ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ቢወጣ ሁላችንም አንድ ስንጥር ነን፡፡ እከሌ ከወጣ ፓርቲው የሆነ ነገር ይሆናል የሚባል ሥጋት ትክክል አይደለም፡፡ ኢዜማ የተሠራበትና የተገመደበት ገመድ ብዙ ነው፡፡ እያንዳንዱ የኢዜማ አባል በተናጠል የየራሱ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ይህን አስተዋጽኦ በአግባቡ ማስቀመጥ ችግር የለውም፡፡ ሆኖም በሆነ አጋጣሚ ወይም በሐሳብ ልዩነት አንዳንዶች ቢወጡም ሆነ ሳይወጡ ትችት ቢያቀርቡ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ፓርቲው ተንገራገጨ ማለት ግን አይደለም፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው ያሳለፈው ውሳኔ አለ፣ አመራር ተመርጧል፡፡ ይህ አመራርም ጠቅላላ ጉባዔው የወሰነውን ይፈጽማል፡፡ የሐሳብ ልዩነት ያለው ሰው በልዩነቱ መቀጠል ይችላል፡፡ ያልተስማማው ሰው ካለም አይገደድም፡፡ ሰው ቢወጣም ፓርቲው ተከፈለ ማለት አይደለም፡፡

የተወሰኑ ሰዎች ከኢዜማ ወጥተው ፓርቲ ቢያቋቁሙም መብታቸው ነው፡፡ እኛ አገር እንጂ ብርቅ የሚሆነው ሌላ አገር እኮ የተለመደ ነው፡፡ እስራኤልን ብትመለከት ያልተስማሙ ሰዎች ከአንድ ፓርቲ ወጥተው ሌላ ፓርቲ መሥርተው በምርጫ ሲፎካከሩ ማየት የተለመደ ነገር ነው፡፡ ኢዜማ በዚህ ወጥቶ፣ ኢዜማ እንዲህ ሆኖ የሚልና ያልተመቸው ሰው ካለ እንዲያውም የራሱን አሪፍ ፓርቲ አቋቁሞ ሠርቶ ማሳየት ነው ያለበት፡፡ እኛ የሠራነውን ሩብ የሚሠራ ሰው ካለ ሠርቶ ማሳየት ነው ያለበት፡፡ እኔ የምችለውንና የማውቀውን ነው እየሠራሁ ያለሁት፡፡ ሠርቶ ማሳየት እንጂ መተቸቱ ምን ያደርጋል? ሂስ መቀበል ይኖራል፣ ትችት አንቀበልም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በኢዜማ ላይ የሚቀርቡ አንዳንድ ትችቶች የማይጠቅሙ ናቸው፡፡ ኢዜማ ተልዕኮ አለው፡፡ ኢዜማ ተልዕኮው በኢትዮጵያ ጠንካራ የመድበለ ፓርቲ ፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር ነው፡፡ ይህንን ለመፍጠር ደግሞ ተደራራቢ ኃላፊነት ነው የተሸከምነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ነው የሚባል ዓይን ውስጥ የሚገባ የፖለቲካ ሥራ የሚሠራ ፓርቲ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ዝም ተብሎ የሚተው አይደለም፡፡ ኃላፊነታችንን ወደን ብቻ ሳይሆን ተገደንም ነው የወሰድነው፡፡ ሰርተፊኬት መውሰድ አንድ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ በሰርተፊኬት ሁሉም እኩል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በእኛ ልክ እንኳ ተደራጅቶና የፓርቲ ቁመና ይዞ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል ሆኖ በመቅረብ በኩል ከኢዜማ የተሻለ ፓርቲ ነኝ የሚል ማነው? ኢዜማን መተቸት ሳይሆን ፈጥሮ ማሳየት አለበት፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ መስከረም 29 ቀን 2015)

Tesfaye Andy Tsigie

Photos from Multi Ethnic Shoa's post 11/10/2022

ሸዋ የምንጃር ብራንድ ማኛ ጤፍ!

የምንጃር ማኛ ጤፍ ከሌላው በተለየ መልኩ ባሳለፍነው አመት ኪሎ 70ብር ድረስ ተሸጧል ! ሌላው የአካባቢ በአማካኝ 55 ብር በላይ ተሽጦ አያውቅም ለዚህም ነጋዴዎችን መጠየቅ ይቻላል!

ሌላኛው የምንጃር ማኛ ጤፍ ለየት የሚያደርገው ተጋግሮ ውሎ ቢያድር አይጠቁርም፣ለስላሳ እና ወዛማ መሆኑ ከሌሎች የተለየ ተመራጭ አድርጎታል።

Come To Shoa
Visit shoa Amhara

11/10/2022

በትምህርት ስርዓታችን ላይ ለአመታት ተንሰራፍተው የነበሩ የትምህርት ጥራት እና አግባብነት መዛነፍ ፤ እንዲሁም የስብዕና ግንባታ ጉድለት እና የስርዓቱ ስብራቶችን በተለያዩ አማራጮች ማረም ከአንድ ኃላፊነት ካለበት መንግሥት የሚጠበቅ ግዴታ ነው። በዚህ ረገድ በአሁኑ ወቅት በመንግስት እየተወሰዱ ያሉትን የስርዓተ ትምህርት ለውጥና የመፈተንና - የአፈታተን ባህልን የመቀየር ጅምር ጥረት እንዲሁም ለዘለቄታው እየተሰሩ ያሉ ለውጦችን መደገፍና ለተፈፃሚነቱ መተባበር ለመንግሥት እና ለተቋማት ብቻ የሚተው ተግባር ሳይሆን በእኩሌታ ችግር ፈቺ (problem solver ) የሆነ እና ትውልድ የመፍጠር ኃላፊነት የሚሰማው ፤ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባር ነው።

አቶ ግርማ የሺጥላ
የአማራ ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

Photos from Multi Ethnic Shoa's post 11/10/2022

ደስታ ❤️🙏

እኚህን እናታችን እንደዛ እያለቀሱ ልጃቸውን እየፈለጉ
ብዙ ሰዎች አብረዋቸው አልቀስው ነበር

ዛሬ ግን ያልተገመተው ሆነና..."
ልጃቸውን እንዲህ አግኝተው ስታይ

ክብር ምስጋና የእናትን አንጀት እንደዚህ በደስታ
ለቀየረ ፈጣሪ ::

EBS 👏❤️
እናት ሁሌም ደስ ይበላት

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

10/10/2022

ለጥ ያለውን የሰሜን ሸዋ ሜዳ በአንክሮት እየተመለከቱ ሲጓዙ ነፍስያዎ በደስታ ትታጠራለች ጊዜው ክረምት ሲሆን ደግሞ ሜዳውና ጋራው ሁሉ ለምለም አረንጓዴ ሆኖ አልፎ አልፎ አዲስ የታረሰው መሬት ቡናማ ቀለም ሆኖ አገር ምድሩን ግርማ ሞገስ ያጎናፅፈዋል። በየመንገዱ ዳር ልጆች ቆመው አንዳንዶቹ ሰላም እያሉ ሲጮሁ ይታያሉ ሜዳዉን ካለፉ በኋላ ወደ ጣርማ በር የዋሻ ዉስጥ መንገድ ይደርሳሉ ከረዥሙ የጣርማ በር ዋሻ በኋላ ሁለት አነስተኛ ዋሻዎችን እና ማራኪ የሆነዉን ጠመዝማዛ መንገድ ቁልቁል በመዉረድ ወደ ጥንታዊቷ የደብረሲና ከተማ ይገባሉ።
Usman Kelifa

10/10/2022

ፈተና አቋርጦ መውጣት ወይም ሳይጀመር መመለስ
በራስ ላይ ቅጣተሰ እንደመፍረድ ነው። ተፈታኞች ችግሮችን በመቋቋም የሁለት ቀን ፈተናዎችን አጠናቀው ለመመለስ ጽናት እንዳይጉድላቸው የማድረግ ኃላፊነት የሁላችንም ነው። ሆኖም ተፈታኞ በራሳቸው እጣ ፈንታንን እንወስናለን ለማለት በሚከጅሉበት የእድሜ ደረጃ ላይ ስላሉ የጸጥታ እና መሰል ከአቅም በላይ የሆኑ ተግዳሮቶች ካልተከሰተ በስተቀር ፈተና አቋርጦ መውጣትን ባያስቡት ነው የሚሻለው።

ደቡብ ወሎ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የምስራቅ ጠዋት ከሁነኛ ምንጭ የሰማሁትን መረጃ አስረስ ማረ ዳምጤ "ጎጃሞቹ ደብረ ወርቅ እና ግንደወይንን ጨምሮ የሶስት ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ሳያጠናቅቁ ወጡ" ሲል ጦምሮት አነበብኩ (ለመውጣት በምክንያትነት ያቀረቡትን ጉዳይ ጭምር ባውቅም ጠቃሚ አይደለም በሚል ሳልገልጸው የተውኩት መረጃ ነበር)።

ዋናው ነገር ሁሉም የሚመለከተው አካል ተማሪዎቻችን እጅግ አስገዳጅ ጫና በሌለበት ሁኔታ እንዲህ አይነት ውሳኔዎችን እንዳይወስኑ ማስተማር፣ ማግባባትና ተሞክሮን በማጋራት ፈተናቸውን በተረጋጋ መንፈስ እንዲጨርሱ ማድረግ ይኖርበታል። በግልጽም ፈተና ማቋረጥ ራሳቸው ላይ ቅጣት እንደመወሰን መሆኑንም እስከማስረዳት የደረሰ ተግሳጽ ብናደርግ እንጠቅማቸዋለን እንጂ አይጎዱም።

ረ/ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ

10/10/2022

ሽሬ
ሽሬ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውላለች።
ያበጠውን ጁንታ እያስተነፈሰ ወደ ፊት መገስገሱን ጀግናው እንደቀጠለበት ነው ድል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ይሁን🙏💪💪

Photos from Multi Ethnic Shoa's post 10/10/2022

* ዲዛይን የሚሠራው ለመጨረሻው ከፍተኛ ግምታዊ ክብደት እና በእድሜው ልክ ሊያጋጥመው ለሚችል የባሰው አደጋ እንዲቋቋም ተደርጎ ነው። ይህ አደጋ የተፈጠረው በዲዛይን ወይም ኮንስትራክሽን ችግር ነው።

* የተባለው የሰው ብዛት ከሚጠበቀው በላይ ነው ከተባለ እንኳ ቅድመ ጥንቃቄ የሚሰጡ የሰው ብዛት ገደቦች ማስቀመጥ ይቻል ነበር። አንዳንድ ድልድዮች ላይ ተጠባብቀው እንደ ወለጋው አገምሳ አባይ ድልድይ አንድ መኪና ብቻ በዝቅተኛ ፍጥነት ወይም እንደ ባህርዳር አባይ ድልድይ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማለፍን እንደሚያስገድዱት ማለት ነው።

* ይህ ዓይነት ቅድመ ጥንቃቄ አስቀድሞ በዲዛይን ወቅት የሚወሰን እና በትክክል የሚታወቅ እንጂ በሙከራ (ትራይ ኤንድ ኢረር) የሚደረስበት ውስብስብ ጉዳይ አይደለም!!

* በሙያዬ ዘርፍ ባጋጠመው ስህተት አፍራለሁ፤ የበለጠ ደግሞ መፍትሔ መስጠት እንደማልችል ሲሰማኝ የበለጠ አዝናለሁ።
Wendemsesha A. Angelo

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የሸዋ ህዝብ አስደናቂ የለቅሦ ሥርዓት😍
"ድርጅቱን አዋርዶታል ፣ ድርጅቱን ገድሎታል ፣ ህዝባችንን አዋርዶታል፣ እንዲህ አይነት ወራዳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት አናጭም" ጃዋር መሀመድ በለውጠ ዋዜማ

Website

Address

Addis Ababa
WWW.MULTIETHNICSHOA.COM
Other Social Media Agencies in Addis Ababa (show all)
Kida Digital Solutions Kida Digital Solutions
Addis Ababa, 1874

Kida Digital Solutions is a full-service digital marketing agency.

Dubakko Dubakko
Addis Ababa

welcome to our official page. In this page you will learn more about content marketing and advertisi

እፎይ Advertising Ethiopia እፎይ Advertising Ethiopia
Bole
Addis Ababa

ሽያጭዎን ለማሳደግ ከእኛ ጋር ይስሩ፡፡ ለመሸጥ የፈለጉትን እቃ ወይም አገልግልዎት እኛ ለትክክለኛ ደምበኛ በተመጣጣኝ ዋጋ እናስተዋዉቅልዎታለን ፡፡

WDO Kolfee/Kolfe OUA WDO Kolfee/Kolfe OUA
Ethiopia � Hachalu Street
Addis Ababa

Volunteers

Tesloach Riek Jikany Tesloach Riek Jikany
Addis Ababa, 1000

https://youtube.com/channel/UCwI5ou16JhT7-ew--eaB0Pw

Sololo Intercept Sololo Intercept
Addis Ababa

Social media is the ultimate equalizer. It gives a voice and a platform to anyone willing to engage. Amy Jo Martin Amy Jo Martin

Ethioline Ethioline
Bole Roads
Addis Ababa, 251

ኢትዮላይን

Jossy Man Jossy Man
Addis Ababa

Speak the Truth

Ethio Boost Marketing Ethio Boost Marketing
Addis Ababa
Addis Ababa, 1000

A leading digital marketing agency in Ethiopia, dedicated to helping small businesses and individuals

EwketJobs EwketJobs
Addis Ababa

Pluto Agency Pluto Agency
Addis Ababa

Social Media Marketing Agency -Facebook,IG Ads -Youtube,tiktok ads -Social media automation -web devt