ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch

ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch

Join https://t.me/kenoch12 telegram channel & https://t.me/kinenetlebamochu telegram group

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 02/12/2022

🗣 ድርብ ድግስ 🗣

📢 ያልሰማህ ስማ የሰማህም መልክቱን አሰማ 📢

▪️ ❣

▪️

🔰ሰላም ውድ የቅንነት ቤተሰብ እንዴት ናችሁ

የጊዜ መቁጠሪያችን ከነሀሴ 15/2014 በኀላ አንድ ሁለት ብሎ ቀኑ እየነጎደ
እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ ሶስት ወር ሞልቶናል ነዉ ታድያ በየሶስት ወሩ ደሞ በቅንነት ቤት የተለመደች የመልካም ተግባር ድግስ አለችን
ምን ካሉ ?
! የሚል መርህ ያላት ድግስ 🤗

በእኛ አንድ ከረጢት ደም የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ልንታደግ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርተዉናል 🔃❣ ብዙ ህይወቶች የእኛን እገዛ ይሻሉና እና እኛም ! ብለን ከጎናቸዉ ለመቆም መተናል !

እናም ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች # ኑ ደም በመለገስ ህይወት እንታደግ! እያልን ጥሪያችንን እያቀረብን #1⃣2⃣ ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራማችን በእለተ #እሁድ ማለትም
#ህዳር #25 /2015 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ለማሳወቅ እንወዳለን

ሁላችዉም ለዚህ የመልካሞ ተግባር ድግስ ተጋብዛችዋል👉ጠሪ አክባሪዎ ቅኖቹ

🔰 እንዲሁም የቅንነት ጎዳና ጉዞዋችንን ከጀመርን እንሆ ህዳር 21/2015 ዓ.ም ሶስት አመት ይሞላናል በመሆኑም ይህንን ታሳቢ በማረግ ቀኑን ህዳር 25/ ከደም ልገሳዉ በተጨማሪ በዘዉዲቱ መሸሻ የህፃናት መንከባከቢያ ማዕከል የቡና ጠጡ ፕሮግራም ስላዘጋጀን እዚህም ላይ በመገኘት አብረን የሶስት አመት ጉዛችንን እንዘክር ዘንድ ስንል በአክብሮት ጠርተኖዎታል !

የቅንነት መስፈርቱ ቅን❤️ብቻ ነው !
ቅንነት ከምንም ይበልጣል

ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ !

15/10/2022

እናመሰግናለን

10/09/2022

🌼ዉድ የቅንነት በጎ ፍቃደኞች ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ 🌼

🌻እንሆ እየሸኘነዉ ባለዉ ዘመን እንደ ቅንነት በጣም መልካም የሚባል እና በቅንነት መንገድ እረዥም የተጓዝንበት አመት ነበር 🙏 ፈጣሪ ይመስገን

🌼መጪዉም አመት ፍቅሩን መተሳሰቡን አንድነቱን ሰጥቶን ይበልጥ ከዚህ በላይ የምንጓዝበት አመት ይሆን ዘንድ በቅንነት ስም እንመኛለን 🙏🌼

🌼ቸር ወሬ የምንሰማበት
🌻ቅንነት ከፍ ከፍ የሚልበት
🌼በጎነት የሚለመልምበት
🌻ደጋግ ልቦች የሚበዙበት
🌼ከክፋት ደግነት ሚዛን የሚደፋበት አመት ይሁንልን !

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው
ቅንነት ከምንም ይበልጣል🙏

" ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 31/08/2022

🔰ነሀሴ 15/2014 ዓ.ም

📌 የቅንነት በጎ ፍቃደኞች 1⃣1⃣ ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ

!

በሚል መርህ ዛሬ የተካሄደው ዙር የቅንነት በጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ከታች በፎቶዎቹ በጥቂቱ በምታዩት መልኩ በአማረ እና ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተካሂዷል ! ይህ እንዲሆን የፈቀደ ፈጣሪ ይመስገን🙏

ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እና እዚህ መልካም ተግባር ላይ ለተሳተፋችሁ በሙሉ በቅንነት ስም ክብረት ይስጥልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

"ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

15/08/2022

🗣 አዋጅ አዋጅ አዋጅ 🗣

📢 ያልሰማህ ስማ የሰማህም መልክቱን አሰማ 📢



🔰ሰላም ውድ የቅንነት ቤተሰብ እንዴት ናችሁ

የጊዜ መቁጠሪያችን ከግንቦት 07 በኀላ አንድ ሁለት ብሎ ቀኑ እየነጎደ
እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ ሶስት ወር ሞልቶናል ታድያ በየሶስት ወሩ ደሞ በቅንነት ቤት የተለመደች የመልካም ተግባር ድግስ አለችን
ምን ካሉ ?
! የሚል መርህ ያላት ድግስ 🤗

አዎ በመልካም ተግባር ምሳሌ የምንሆንበት ቀን ደረስኩ እያለ ነዉ 🗣

በእኛ አንድ ከረጢት ደም የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ልንታደግ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርተዉናል 🔃❣ ብዙ ህይወቶች የእኛን እገዛ ይሻሉና እና እኛም ! ብለን ከጎናቸዉ ለመቆም መተናል !

እናም ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች # ኑ ደም በመለገስ ህይወት እንታደግ! እያልን ጥሪያችንን እያቀረብን #1⃣1⃣ ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራማችን በእለተ #እሁድ ማለትም
#ነሀሴ #15 /2014 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ለማሳወቅ እንወዳለን

ሁላችዉም ለዚህ የመልካሞ ተግባር ድግስ ተጋብዛችዋል👉ጠሪ አክባሪዎ ቅኖቹ

የቅንነት መስፈርቱ ቅን❤️ብቻ ነው !
ቅንነት ከምንም ይበልጣል

ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ !

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 08/08/2022

🔰 ነሀሴ 01/2014 ዓ.ም

📍ዉላችን በቅንነት ጎዳና

▪️ትላንት ነሀሴ 01/2014 ዓ.ም የቅንነት በጎ ፈቃደኞች ቤተሰብ በነበረን ዉሎ ቀናችንን በሁለት የበጎ አድራጎት መርሃግብሮችን በማከናወን ዉለናል ።

▪️ጠዋት በነበረን ፕሮግራም የሀምሌ ወር የቤተሰብ ጥየቃችን በሁለት እናቶቻችን ቤት ወርሃዊ አስቤዛ ይዘን በመገኘት እናቶቻችንን በስራ አግዘን ተጨዋዉተን ትንሻን ነገር አድርገን ትልቁን ምርቃት ተቀብለን ደስ የሚል ጊዜን አሳልፈን መተናል 🙏

▪️ከከሰዐት በነበረን ፕሮግራም " እኔ ለአንድ ወገኔ " በሚል መርህ ከእናንተዉ ከቤተሰቦች ክረምቱን ታሳቢ በማረግ የተሰባሰቡትን አልባሳት ለወገኖቻችን እዘን በመሄድ ለግሰናል 🙏

- በሁለቱም ፕሮግራም ላይ ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን ፡፡

መገኘት ባትችሉ ልብሶቹን በማሰባሰብ በሀሳብ በጉልበት በገንዘብ ባላቹበት ሆናቹ ከጎናችን ለሆናቹ ቤተሰቦቻችንም ክብረት ይስጥልን🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

09/07/2022

🕌 🕌

✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙
ዉድ የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ 1443ኛዉ የ ኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉን የሰላም የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንዲሁም በበጎ ተግባር የምታሳልፉት እንዲሆን በቅንነት ስም እንመኛለን።


💫መልካም በዓል💫

01/07/2022

ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን እነሆ ክረምቱ ገብቶ ብርዱም ዝናቡም ከበድ እያለ ነው እኛ በቤታችን ሚያሞቁ ልብሶችን ትኩስ ነገሮችን እየተጠቀምን ብርዱን እንከላከላለን

እስቲ በመንገድ ዳር ላይ ያሉ ወገኖቻችንስ በምን እያለፉት ይሆን?

ሁላችንም የምናውቀው ነው ለዚህም አንድ ሀሳብ ይዘን መተናል

"እኔ ለአንድ ወገኔ". በሚል መሪ ቃል

_ብርድ ልብስ
_ፎጣዎችን
_የተለያዩ ጃኬት ፣ሹራብ፣ቲሸርቶች ብቻ ሊለበሱ የሚችሉ ከእኛ ጎዳና ላይ ላሉ ቤተሰቦቻችን ሚያስፈልጉ ልብሶችን የማሠባሰብ ቻሌንጅ ጀምረናል።እንዲሁም ልብስ የለኝም ወይም ማሰባሰብ አልችልም ካሉ እና ለአንድ ሰው የፎጣ ወይም የብርድ ልብስ መግዣ እችላለው ካሉም በደስታ እንቀበላለን።

ሁላችሁም በዚህ በጎ ተግባር ላይ እንድትሳተፉ ስንል እንጠይቃለን
አለኝ የሚሉትን የልብስ አይነት ለአድሚኖች ይሄን አለኝ ኑና ውሰዱ በሉን ያሉበት መጥተን እንወስዳለን ። ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልምና አንድም ሁለትም በማሰባሰብ የዚህ በጎ ተግባር ተሳታፊ ይሁኑ።

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው!
ቅንነት ከምንም ይበልጣል!!

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 21/06/2022

🔰ሰኔ 12 /2014 ዓ.ም

📌 በዘዉዲቱ መሸሻ የህፃናት መንከባከቢያ ማዕከል የነበረን የቡና ጠጡ ☕ ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ⬆️

▪️በዕለቱ በነበረን የቡና ጠጡ ፕሮግራም እንጦጦ ቁስቋም ማርያም አካባቢ በሚገኘዉ የዘዉዲቱ መሸሻ የህፃናት መንከባከቢያ ማዕከል ተገኝተን ማዕከሉ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተን በማዕከሉ ካሉ ህፃናት ጋር ስቀን ተጨዋዉተን ፍቅርን ሰተን ፍቅርን ተቀብለን የእናት ዘዉዲቱን የማይጠገብ ምርቃት ተቀብለን ደስስስ የሚል የቡና ጠጡ ፕሮግራም አካሂደን የማይረሳ እና ደስስስ የሚል ጊዜን አሳልፈን ተመልሰናል

- ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን በቅንነት ስም እናመሰግናለን ክብረት ይስጥልን

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

17/06/2022

ኑ ቡና ጠጡ ☕

ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የቅንነት ቤተሰቦች

ዳግም ለበጎ ተግባር ልንሰባሰብ እና ልዮ የሆነ የቤተሰብ ጊዜ እና ፍቅር የማካፈል ጊዜን ከወገኖቻችን ጋር ለማሳለፍ " ቡና ጠጡ " የተሰኘዉን ፕሮግራም ይዘንላችሁ መተናል 😊

እንደሚታወቀው ከዘውዲቱ መሸሻ ህፃናት እንክብካቤና ማሳደጊያ ማዕከል አንድ የምናሳድገው ልጅ በሀላፊነት ወስደን በእናንተ ቤተሰቦቻችን አጋዥነት የተሰጠንን ሀላፊነት በአግባቡ እየተወጣን እንደሆነ ይታወቃል ቢሆንም
በማዕከሉ ያሉ ህፃናት እኛ ከምናረገዉ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ከኛ ፍቅርን : እንዴት ናችሁ ብሎ መጠየቅን : ከኛ ጋር መጫወትን የተለያዮ እገዛዎችን ይሻሉ እና ሰብሰብ ብለን ሄደን አብረናቸዉ ጊዜ ለማሳለፍ አስበናል ።

በመሆኑም ዉድ ቤተሰቦች የፊታችን እሁድ ሰኔ 12 እዛ በመገኘት ሰብሰብ ብለን ወደ ማዕከሉ በመሄድ ከልጆቹ ጋር እየተጨዋወትን እንድናወጋ "ቡና ጠጡ" ስንል በክብር ጋብዘነዎታል። ታዲያ ወደ ፕሮግራሙ ሲመጡ የተለያዮ ለልጆቹ ይጠቅማሉ የምትላቸዉን መማሪያ መፅሀፍት አልባሳት እንዲሁም የምግብ ፍጆታዎች ይዛችሁ ትገኙ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን

የፊታችን እሁድ ሰኔ 12 ቀጠርዎን ከኛ ጋር በማረግ ደስ የሚል ጊዜ ከልጆቹ ጋር አሳልፈን እንምጣ በማለት የቅንነት በጎ ፈቃደኞች ቤተሰብ በክብር ጠርቶዎታል።

ሰዐት : ከቀኑ 5:30
መገናኛ ቦታ : ሽሮ ሜዳ የእንጦጦ ታክሲ መጫኛ ጋር

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው
ቅንነት ከምንም ይበልጣል!

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/05/2022

🔰ግንቦት 07/2014 ዓ.ም

📌 የቅንነት በጎ ፈቃደኞች 🔟ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ

!
!

!

! ! በሚል መርህ የተካሄደው #10 ኛ ዙር የቅንነት በጎ ፈቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ከታች በፎቶዎቹ በጥቂቱ በምታዮት መልኩ በአማረ እና ደማቅ በሆነ መልኩ ተካሂዷል።

ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እና እዚህ መልካም ተግባር ላይ ለተሳተፋችሁ ባለ ቅን ልቦናዎች በሙሉ በቅንነት ስም ክብረት ይስጥልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

"ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

10/05/2022

በቀጣይ .....በቅንነት ጎዳና

🔰 10 ኛ ዙር ህይወትን የመታደግ ዘመቻ

📆 ግንቦት 07/2014 ዓ.ም

ዉድ ቤተሰቦቻችን ከወዲሁ ከእኛ ጋር ቀጠሮ ይያዙ ....መልክቱን ላልሰማ ያሰሙ !

ቦታ:- አ.አ ስቴድየም በሚገኘው ቀይ መስቀል ጊቢ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጓዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 06/05/2022

🔰ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም

📌 በፍቅር የኢትዮጵያዉያን የአይምሮ እድገት ዉስንነት ብሄራዊ ማህበር በነበረን ልዮ የበዓል ፍቅር የማካፈል ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ⬆️

ፍቅር የኢትዮጵያዉያን የአይምሮ እድገት ዉስንነት ብሄራዊ ማህበር የተመሠረተው በ 1987 ዓ.ም ነው የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባላቸው ልጆች ወላጆች ስብስብ የተመሰረተ ሲሆን እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱትን ከመንግስት ጋር በመተባበር ትምህርት እንዲማሩ እና እድሜያቸው ከፍ ያሉትን ልጆች ደግሞ የተለያየ ሙያ እንዲማሩ ተምረውም ሲጨርሱ የራሣቸውን ስራ እንዲሠሩ የሚያደርግ ድርጅት ነው ።
በተጨማሪም ለወላጆች እንዲሁም ለተለያዮ ማህበረሰቦች የተለያየ ስልጠና መስጠት ስለ ልጆቻቸው ህመም ስለ አይምሮ እድገት ዉስንነት ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማረግ ስራን እንዲሁም የተለያዮ ድጋፎችን ከአይምሮ እድገት ዉስንነት ጋር የተያያዙ ስራዎችን ይሰራል ።

እኛም ትላንት በማዕከሉ ባዘጋጀነዉ ልዮ የበዓል የመዝናኛ ፍቅር የማካፈል እና የምሳ ፕሮግራም በማዕከሉ ካሉ ወገኖቻችን ጋር የማይረሳ በጣም ልዮ የሆነ ፍቅር ሰቶ የመቀበል ጊዜን አሳልፈናል ... በእናንተ ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች አስተዋፅኦ አማካኝነትም በማዕከሉ ያሉ ድጋፍ የሚደረግላቸዉን ወገኖች የእለቱን ምሳ በመቻል አብልተናል ለማዕከሉም በአቅማችን ያለንን ድጋፍ በአይነትም አበርክተናል ።

ከዚህም በሁአላ በምንችለሁ ሁሉ ለማዕከሉ ድጋፍ ለማረግ እና ከጎናቸዉ ለመሆንም ቃልን ተቀብለናል ።

ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ በእለቱ የተገኛችሁ እና በመንፈስም አብራችሁን የነበራችሁ እንዲሁም በተለያየ መልኩ ከጎናችን የነበራችሁ በሙሉ በቅንነት ስም እናመሰግናለን !

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

https://t.me/kinenetlebamochu

02/05/2022

✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ 1443 ኛዉ የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏 እያልን በዓሉ በጎ በማሰብ በጎ በመስራት ካለን ለሌለዉ በማካፈል የምናሳልፈዉ ይሆን ዘንድ በቅንነት ስም እንመኛለን 🙏

✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨
መልካም በዓል

27/04/2022

ልዮ የበዓል ፍቅር የማካፈል ፕሮግራም !

ሰላም ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች በዓልን በማስመልከት ሁሌም እንደምናረገዉ ካለን ላይ የምናካፍልበት ፍቅር ሰቶ ፍቅር መቀበል የሚል መርህ ያለዉ የበጎ ተግባር ድግስ በአርበኞች መታሰቢያ ቀን ( ሐሙስ ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም ) በፍቅር የኢትዮጵያዉያን የአእምሮ እድገት ዉስንነት ብሄራዊ ማህበር አሰናድተናል እናም በዚህ የመልካም ተግባር ድግስ ላይ ሁላችሁም ትገኙ ዘንድ በቅንነት ስም በአክብሮት ተጋብዛችሁአል !

❇️ እናም ለዚህ ተግባር መሳካት ሁላችሁም የበኩላችሁን አስተዋፆ ታበረክቱ ዘንድ እንደ ሁል ጊዜዉ የኦንላይን እጣ ትኬት አዘጋጅተናል ። እናም እነዚህን የእጣ ትኬቶች ያልገዛችሁ ቤተሰቦች በቀሩት ጥቂት ቀናት ዉስጥ እነዚህን ትኬቶች በመግዛት እዚህ የበረከት ስራ ላይ የበኩላችሁን ታበረክቱ ዘንድ በቅንነት ስም እንጠይቃለን

▪️የትኬት ዋጋ : 15 ብር ብቻ !

▪️ እጣዉ : ከአንድ እስከ ሶስት የተካተቱ እጣዎች ሲኖሩ እጣዉ ምንድነዉ ለሚለዉ በእለቱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል 😊 ምክንያቱም ከእጣዉ ይልቅ አላማዉን አግዝፈን እንድንሳተፍ ስለሚፈለግ ! ትልቁ እጣ ግን ሁላችን ከዚህ መልካም ተግባር በሁአላ የምናተርፈዉ የመንፈስ እርካታ ነዉ 🙏

🅾 በተጨማሪም ከእጣዉ ትኬት በዘለለ
...በገንዘብም
...በግብአትም ▪️የተለያዮ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን
▪️የተለያዮ አልባሳትን
▪️የምግብ ፍጆታዎችን
ድጋፍ ማረግ ስለሚቻል በአዲሚኖች በኩል ያናግሩን !

🔰 ትኬቶቹ ከሁሉም አድሚኖች ዘንድ ማግኘት ይችላሉ

እናመሰግናለን !

ቅንነት በጎፈቃደኞች🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

24/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቅንነት ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን!

በዓሉ የሠላም የጤና የፍቅር የአንድነትና የመተሳሰብ ይሁንልን ለሀገራችን ሰላም ለህዝቦቿ ፍቅርና አንድነትን ይስጥልን! ያጡ የሚያገኙበት የተራቡ የሚጠግቡበት የተቸገሩ በበረከት የሚትረፈረፉበት ያዘኑ የሚፅናኑበት ያለቀሱ እንባቸው የሚታበስበት እንዲሁም ያለዉ የሌለዉ በማካፈል በበጎ ስራ በቅንነት የምናከብረዉ በዓል ይሆን ዘንድ በቤተሰባችን ስም እንመኛለን !

መልካም በዓል !


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 07/03/2022

🔰 የካቲት 27 /2014 ዓ.ም

📌 የየካቲት ወር የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም

▪️በትናንትናው ቀን በነበረን የየካቲት ወር
የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም

ከታች በፎቶዎቹ በምትመለከቱት መልኩ ደስ በሚል ሁኔታ በሁለት እናቶቻችን ቤት ወርሃዊ አስቤዛ ይዘን በመሄድ እናቶቻችንን በስራ አግዘን ተጨዋዉተን ትንሿን ነገር አድርገን ትልቁን ምርቃት ተቀብለን ደስ የሚል ጊዜን አሳልፈን መተናል 🙏

-ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን ፈጣሪ ያክብርልን እናመሰግናለን ፡፡

በሀሳብ በጉልበት በገንዘብ ባላቹበት ሆናቹ ከጎናችን ለሆናቹ ቤተሰቦቻችንም ክብረት ይስጥልን🙏🙏🙏

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 31/01/2022

🔰ጥር 22 /2014 ዓ.ም

📌 የቅንነት በጎ ፍቃደኞች 9⃣ ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ⬆️

!
!

!

! ! በሚል መርህ የተካሄደው ዙር የቅንነት በጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ከላይ በፎቶዎቹ እንደምታዮት በአማረ እና ደማቅ በሆነ መልኩ ተካሂዳል ! ይህ እንዲሆን የፈቀደ ፈጣሪ ይመስገን🙏

ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እና እዚህ መልካም ተግባር ላይ ለተሳተፋችሁ በሙሉ በቅንነት ስም ክብረት ይስጥልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

"ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

26/01/2022

🗣 የዘመቻ ጥሪ 🗣

!

📢 ያልሰማህ ስማ የሰማህም መልክቱን አሰማ 📢



!

🔰ሰላም ውድ የቅንነት ቤተሰብ እንዴት ናችሁ

የጊዜ መቁጠሪያችን ከጥቅምት 21 በኀላ አንድ ሁለት ብሎ ቀኑ እየነጎደ
እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ ሶስት ወር ሊሞላን ነዉ ታድያ በየሶስት ወሩ ደሞ በቅንነት ቤት የተለመደች የመልካም ተግባር ዘመቻ አለችን
ምን ካሉ ?
! የሚል መርህ ያላት ዘመቻ 🤗

አዎ በመልካም ተግባር ምሳሌ የምንሆንበት ቀን ደረስኩ እያለ ነዉ 🗣

በእኛ አንድ ከረጢት ደም የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ልንታደግ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርተዉናል 🔃❣ ብዙ ህይወቶች የእኛን እገዛ ይሻሉና እና እኛም ❣ ! ብለን ከጎናቸዉ ለመቆም መተናል !

እናም ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች # ኑ ደም በመለገስ ህይወት እንታደግ! እያልን ጥሪያችንን እያቀረብን #9⃣ ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራማችን የፊታችን #እሁድ ማለትም
#ጥር #22 /2014 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ለማሳወቅ እንወዳለን

ሁላችዉም ለዚህ የመልካሞ ተግባር ድግስ ተጋብዛችዋል👉ጠሪ አክባሪዎ ቅኖቹ

📍ቦታ : ስታዲየም የደም ባንክ ግቢ ዉስጥ
⏱ ሰዐት : ከ 4:00 ሰዐት ጀምሮ

የቅንነት መስፈርቱ ቅን❤️ብቻ ነው !
ቅንነት ከምንም ይበልጣል

ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ !

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 08/01/2022

🔰ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም

📌 ትናንት በነበረን የገና በዐል የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም መሰረት ቅኖች ሰብሰብ ብለን ወደ እናቶቻችን ቤት ለበዐል የሚሆኑ አስቤዛዎችን ይዘን በመሄድ ከታች በፎቶዎቹ በምትመለከቱት መልኩ አዉድአመቱን እምር ድምቅ ባለ በፍቅር ሰቶ ፍቅር በመቀበል እንዲሁም በእናቶቻችን ምርቃት በታጀበ መልኩ አክብረናል ። ደስ የሚል እና የማይረሳ ቀን ሆና በቅንነት ጎዳና ጉዛችን ላይም ደምቃ ተፅፋለች የዛሬዋ ቀን ።

ሁላችሁም ጥሪዉን አክብራችሁ የተገኛችሁ ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች እንዲሁም መገኘት ባትችሉም ከጎናችን የነበራችሁ ሁሉ በቅንነት ስም ክብረት ይስጥልን የእናቶቻችን ምርቃት ይድረሳችሁ 🙏

በድጋሚ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሁም በቅንነት መንፈስ በጎ በጎዉን የምንሰራበት ,መልካሙን የምናስብበት ያለንን የምናካፍልበት በቅንነት ጎዳና የምንጓዝበት በዐል ይሆን ዘንድ ተመኘን ። መልካም በአል !

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

06/01/2022

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ።

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 07/12/2021

❤️❤️




🔰 ህዳር 26/2014 ዓ.ም

▪️1 ..2... በማለት በጥቂት ባለ ቅን ልቦናዎች እህት ወንድሞቻችን መልካም ሀሳብ አፍላቂነት የተጀመረዉ ጉዛችን ይሄዉ ዛሬ እልፍ ባለ ቅን ልቦናዎችን አፍርቶ በቅንነት ጎዳና የአቅማችንን እና የበኩላችንን ሀላፊነት በመወጣት ዛሬ ላይ ደርሰን ድፍን ሁለት አመታትን አስቆጥረን ቀኑን አስበን ለመዋል በቅተናል እና ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች በድጋሚ እንኩአን ደስ ያለን ደስ ያላችሁ !

ከላይ በፎቶ በምትመለከቱን መልኩ እምር ድምቅ ሽብርቅ ባለ እና በቅንነት እና በበጎነት የተሞላ ቀንን በዘዉዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ እና መንከባከቢያ ማዕከል አሳልፈናል ክብር ምስጋና ለፈጣሪ እና ከጎናችን ለነበራችሁ በሙሉ !

በእለቱም ከምስረታ በአል በተጨማሪ ጉዛችንን ሀ ብለን ስንጀምር በበጎ ተግባር እንደሆነ ሁሉ ሁለተኛ አመታችንን ስናከብርም በበጎ ተግባር በመታጀብ ነበር በዚሁም ከእናንተ ከዉድ የቅንነት ቤተሰቦች በዕጣ ትኬት አማካኝነት እንዲሁም በአይነትም የተሰባሰቡትን ለማህበሩ አስፈላጊ የሆኑትን የተለያዮ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ...አልባሳትን ...እንዲሁም የትምህርት መርጃ መፅሀፍትን ይዘን በመሄድ ለማህበሩ አስረክበን የበኩላችንን በመወጣት እንዲሁም ለቀጣይም ማህበሩ በሚያስፈገዉ ድጋፍ ሁሉ በአቅማችን ለማበርከት ቃልን ገብተን ተመልሰናል !

ሁላችሁም ይህ ቀን እንዲህ ባማረ መልኩ እንዲያልፍ የበኩላችሁን የተወጣችሁ እንቁ የቅንነት ቤቸሰቦች እንዲሁም ጥሪያችን አክብራችሁ የተገኛችሁ የተለያዮ ማህበራት ተወካዮች በቅንነት ስም እናመሰግናለን ! ክብረት ይስጥልን !

ጉዛችን ይቀጥላል ...

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

07/12/2021

📌 አርብ ህዳር 24 / 2014 ዓ.ም የወጣዉ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዕትም ላይ የቅንነት በጎ ፈቃደኞችን ቤተሰብን አመሰራት ...አላማ ....ተሳትፎ እያረገባቸዉ ያሉትን ተግባራት ..የወደፊት ዕቅድ በተለመለከተ በእህታችን ፀሀይ እሸቱ ተወካይነት የነበረን ቆይታ ከላይ በተያያዘዉ ፋይል ላይ ወይም ህዳር 24/2014 ዓ.ም የወጣዉ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ እትም ላይ ገፅ " 7 " ሀገረኛ አምድ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ !

ስለ ቤተሰባችን በደንብ ገላጭ በሚባል መልኩ ለአንባቢዎቹ ስላደረሰልን አዲስ ዘመን ጋዜጣን እና ጋዜጠኛ ራስወርቅ ሙሉጌታን በቅንነት ስም እናመሰግናለን ክብረት ይስጥልን !

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

01/12/2021

2nd_year anniversary


🔰 ቅንነት በጎ ፍቃደኞች

ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች እንኩአን ለሁለተኛ አመት የምስረታ በአላችን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን


እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ የተመሰረተበትን አላማ በአቅማችን እየከወንን አንድ ሁለት ብለን እዚህ ደርሰናል። ይሄንኑ የሁለተኛ አመት የምስረታ በአላችንን ምክንያት በማድረግ የፊታችን እሁድ ህዳር 26/2014 ዓ.ም በዘውዲቱ መሸሻ ህፃናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማዕከል ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር አብረን ለማክበር አስበናል እና ሁላችሁም በፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችሁአል

በእለቱ ሁለተኛ አመታችንን ከማክበር በተጋዳኝ ማዕከሉ የሚያስፈልጉትን ግብአቶች በአቅማችን ይዘን በመሄድ የበኩላችንን ለማበርከትም አስበናል እናም እርስኦም

▪️የተለያዮ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን
▪️ለህፃናት የሚሆኑ አልባሳትን
▪️የትምህርት አጋዝ መፅሀፍታትን
▪️የምግብ ፍጆታዎችን

በአይነትም እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀዉንም የኦንላይን ትኬት በመግዛት የበኩላችሁን ታረጉ ዘንድ በቅንነት ስም እንጠይቃለን (ትኬቱን ሁሉም አድሚኖች ጋር ያገኛሉ )

📆 እሁድ ህዳር 26 /2014 ዓ.ም ቀጠሮአቹሁን ከወዲሁ ከእኛ ጋር ያርጉ

ለቅንነት እና ለበጎነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው
ቅንነት ከምንም ይበልጣል

https://t.me/kenoch12
https://t.me/kinenetlebamochu

30/11/2021

የቅንነት በጎ ፈቃደኛ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለሁለተኛ አመት የምስረታ ቀናችን አደረሰን አደረሳችሁ። ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በዛሬዋ ቀን ህዳር 21 ነበር ቅንነት በጎ ፈቃደኞች የተመሠረተው ።
እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ መልካሙን በጎውን በአቅማችን እየሰራን እዚህ ደርሰናል። ይሄንኑ የሁለተኛ አመት የምስረታ በአላችንን ምክንያት በማድረግ የፊታችን እሁድ ህዳር 26/ 03/2014ዓ.ም በዘውዲቱ መሸሻ ህፃናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማዕከል ለማክበር አስበናል እና ሁላችንም በፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ ሰዎች ከቻላችሁ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያዎችን አልባሳቶችን ይዛችሁ በመምጣት ወይም መምጣት የማትችሉ ከሆነ ከወዲሁ በአቅራቢያዎ ላለ ሰው በማቀበል የበረከቱ ተሳታፊ በመሆን ቀኑን አብረን እናሳልፍ እያልን ጥሪ እናቀርባለን።

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው
ቅንነት ከምንም ይበልጣል
ቅንነት በጎ ፈቃደኞች

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 09/11/2021

🔰 ጥቅምት 28/2014 ዓ.ም

▪️የጥቅምት ወር የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም
ከታች በፎቶዎቹ በምትመለከቱት መልኩ ደስ በሚል ሁኔታ በሁለት እናቶቻችን ቤት ወርሃዊ አስቤዛ ይዘን በመሄድ እናቶቻችንን በስራ አግዘን ተጨዋዉተን ትንሿን ነገር አድርገን ትልቁን ምርቃት ተቀብለን ደስ የሚል ጊዜን አሳልፈን መተናል 🙏

-ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን ፡፡

በሀሳብ በጉልበት በገንዘብ ባላቹበት ሆናቹ ከጎናችን ለሆናቹ ቤተሰቦቻችንም ክብረት ይስጥልን🙏🙏🙏

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

ኑ አብረን በቅንነት ጎዳና እንጎዝ 🙏


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 01/11/2021

🔰ጥቅምት 21/2014 ዓ.ም

📌 የቅንነት በጎ ፈቃደኞች 8⃣ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቆይታ በጥቂቱ⬆️

!

በሚል መርህ የተካሄደው ዙር የቅንነት በጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ከላይ በፎቶዎቹ እንደምታዮት በአማረ እና ደማቅ በሆነ መልኩ ተካሂዳል ! ይህ እንዲሆን የፈቀደ ፈጣሪ ይመስገን

ሁላችሁም ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እና እዚህ መልካም ተግባር ላይ ለተሳተፋችሁ በሙሉ በቅንነት ስም ክብረት ይስጥልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

"ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

18/10/2021

🗣 ድግስ ድግስ ድግስ 🗣

📢 ያልሰማህ ስማ የሰማህም መልክቱን አሰማ 📢



🔰ሰላም ውድ የቅንነት ቤተሰብ እንዴት ናችሁ

የጊዜ መቁጠሪያችን ከሀምሌ 18 በኀላ አንድ ሁለት ብሎ ቀኑ እየነጎደ
እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ ሶስት ወር ሊሞላን ነዉ ታድያ በየሶስት ወሩ ደሞ በቅንነት ቤት የተለመደች የመልካም ተግባር ድግስ አለችን
ምን ካሉ ?
! የሚል መርህ ያላት ድግስ 🤗

አዎ በመልካም ተግባር ምሳሌ የምንሆንበት ቀን ደረስኩ እያለ ነዉ 🗣🗣🗣

በእኛ አንድ ከረጢት ደም የብዙ ወገኖቻችንን ህይወት ልንታደግ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርተዉናል 🔃❣ ብዙ ህይወቶች የእኛን እገዛ ይሻሉና እና እኛም ! ብለን ከጎናቸዉ ለመቆም መተናል !

እናም ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች # ኑ ደም በመለገስ ህይወት እንታደግ! እያልን ጥሪያችንን እያቀረብን #8⃣ ኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራማችን በእለተ #እሁድ ማለትም
#ጥቅምት #21 /2014 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ለማሳወቅ እንወዳለን

ሁላችዉም ለዚህ የመልካሞ ተግባር ድግስ ተጋብዛችዋል👉ጠሪ አክባሪዎ ቅኖቹ

የቅንነት መስፈርቱ ቅን❤️ብቻ ነው !
ቅንነት ከምንም ይበልጣል

ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ !

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 11/10/2021

መስከረም 30/01/2014 ዓ.ም ቅንነት በጎ ፈቃደኞ በሁለት እናቶቻችን ቤት የነበረን ወርሃዊ የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም። ለእናቶቻችን እድሜ እና ጤና ይስጥልን እንዲሁም ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ሁሌም የዚህ መልካም ተግባር ተሳታፊ አባላቶቻችን ክብረት ይስጥልን።
ሁሌም እንደምንለው
"የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነው
ቅንነት ከምንም ይበልጣል"።

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 10/10/2021

እንኳን ለ80ኛው አመት የልደት በአሎት አደረሶት እናት ዘውዲቱ መሸሻ ከዚህ በላይ ረጅም ዕድሜን ሰጥቶ ያቆይልን።የዘውዲቱ መሸሻ ህፃናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማዕከል መስራች

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

አዲሱን ዘመን በቅንነት
አዲሱን አመት በበጎነት
አዲሱን አመት በፍቅር
አዲሱን አመት በፍቅር ሰቶ ፍቅር በመቀበል
ጀምረነዋል🙏 !

🌼 መስከረም 1/2014 ዓ.ም 🌼

ዉድ የቅንነት ቤተሰቦች በመጀመሪያ እንኩአን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን የቅንነት በጎ ፍቃደኞች ቤተሰብ ልክ እንደ ሁል ጊዜዉ የበአል ዕለትን በየቤቱ ከማክበር ይልቅ ሰብሰብ ብለን ፍቅር እና አስታዋሽ ወደ ሚሹ ወገኞቻችን
ዘንድ አቅንተን ለማክበር በያዝነዉ ቀጠሮ መሰረት ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ መገናኛችንን ሽሮ ሜዳ አርገን በዉብ እና አዉዳመት አዉዳመት በሚመስል አልባሳት አሸብርቀን ጉዛችንን በእህቶቻችን አበባዮሽ ጭፈራ እና በወንድሞቻችን የመልካም ምኞት መልዕክት ባላቸዉ ስዕሎች አጅበን በደመቀ ሁኔታ ወደ እንጦጦ ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ወደ ሚገኘዉ
የእናት ዘዉዲቱ መሸሻ የህፃናት መርጃ እና መንከባከቢያ ማዕከል አርገን በማዕከሉ ከሚገኙ ህፃናት ጋር ያዘጋጀነዉን የምሳ ፕሮግራም አከናዉነን ተጨዋዉተን ለ 30 አመት የበጎነት ምሳሌ ከሆኑት ከእናት ዘዉዲቱ❤️ የማይጠገብ ምርቃት እና አደራን ተቀብለን በጣም ደስስስ በሚል እና በማይረሳ መልኩ የ 2014 አዲስ ዘመንን በአልን አሳልፈናል 🙏 ፈጣሪ ይመስገን

በማዕከሉ ዉስጥ ለሚገኙ ህፃናት እንዲሁም ሰራተኞች በሙሉ ላደረጋችሁልን መልካም አቀባበል እና ለሰጣችሁን ፍቅር በቅንነት ስም ከልብ እናመሰግናለን🙏

ለእናታችን እናት ዘዉዲቱም ከዚህ በላይ በበጎነት ምሳሌ የሚሆኑበትን እድሜ እና ጤና ፈጣሪ ይሰጥልን ዘንድ ምኞታችን ነዉ ❤️🙏

ሁላችሁም የቅንነት ቤተሰቦች ቦታ የነገሮች አለመመቻቸት እንዲሁም የተለያዮ ተግዳሮቾች ሳይበግራችሁ ይህን መልካም ጥሪ ተቀብላችሁ ስለተገኛችሁ ክብረት ይስጥልን 🙏 ያልተገኛችሁም በሀሳብ ከእኛ ጋር ነበራችሁ እና እናመሰግናለን 🙏

በአጠቃላይ ሁላችሁም በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ተግባር ላይ ተሳትፎ ያረጋችሁ በሙሉ ፈጣሪ ያክብርልን 🙏

ዘመኑን የሰላም የፍቅር በጎነት እና ቅንነት ከፍ የሚልበት አመት ያርግልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

" ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ነሀሴ 30 /2013 ዓ.ም

የ2013 ዓ.ም የመጨረሻዋ እሁድ
የአመቱ ልዩ ቀን በቅንነት ቤት ከታች በፎቶ በጥቂቱ በምትመለከቱት መልኩ ሽብርቅ ድምቅምቅ ብሎ አልፋል 🤗

ይህ ቀን እኛም እናቶቻችንም በጉጉት ስንጠብቀዉ የነበረ ቀን ነዉ ምክንያቱንም የእናቶቻችን የሁልግዜም ምኞት የነበረዉ ነገር የሚሳካበት ቀን ስለነበር : የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ሆኖም ምኞታችን እዉን ሆኖ እናቶቻችንን በኦርቶዶክስ እምነት መሰረት ቅዱስ ስጋዉን እና ቅዱስ ደሙን ዛሬ ተቀብለዋል ፈጣሪ ይክበር ይመስገን 🙏

ለዚህም ነዉ ይች ቀን የአመቱ ልዩ ቀን ያልንበት ምክንያት 😊 በአጠቃላይ ዛሬ በነበረን ቆይታ የቅንነት ቤተሰብ አባላት የበአል የቤተሰብ ጥየቃ አስቤዛ ለእናቶቻችን ይዘን በመሄድ እንዲሁም የእናቶቻችንን ደስታ አብረን ተካፍለን ተጨዋዉተን የማይጠገብ ምርቃት ተቀብለን ደስስስስስስስስ የሚል ጊዜ አሳልፈን መተናል 🙏

ሁላችሁም በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ተግባር ላይ ተሳትፎ ያረጋችሁ በሙሉ ፈጣሪ ያክብርልን 🙏

መስከረም 1 እንገናኝ

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

" ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰 ነሀሴ 29/2013

ነሀሴ 02 /2013 በነበረን ቤተሰብ ጥየቃ ላይ የአንድ እናታችንን ማለትም የእማማ የሀሳብ ቤት ጎናቸዉን ያሳርፉበት የነበረዉ ሶፋ ከጥቅም ዉጭ በመሆኑ ለእሳቸዉም አመቺ ሁኔታ ላይ ስላልነበረ እዛዉ በነበሩት አባላት እና ከሌሎች አባላት በተሰባሰበ ገንዘብ ሌላ ሶፋ ገዝተን ለመቀየር እና ሪፓርት ለማረግ ቃል በገባነዉ መሰረት ቃላችንን እንደ ፈጣሪ መልካም ፈቃድ ዛሬ ፈፅማል 🙏

ሁላችሁም በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ተግባር ላይ ተሳትፎ ያረጋችሁ በሙሉ ፈጣሪ ያክብርልን 🙏

📍በዚሁ አጋጣሚ በነገዉ እለት የበአል የቤተሰብ ጥየቃ ቀናችን እንዲሁም ሁለቱም እናቶቻችን በኦርቶዶክስ እምነት መሰረት ቅዱስ ስጋ ወ ደሙን የሚቀበሉበት ቀን ነዉ እና ሁላችሁም ተገኝታችሁ የደስታዉ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችሁአል 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

" ኑ በቅንነት ጎዳና አብረን እንጓዝ "

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ነሀሴ 09/2013

በዚህ ቀን በነበረን ዉሎ ሎሚ ሜዳ ወደምትገኘዉ ቤተሰባችን ቤት አቅንተን ነበር ። በዚሁም መሰረት ከእናንተ ከአባላቾች በተሳባሰበዉ ገንዘብ ቤቱን ለማደስ የሚያስፈልጉትን ማቴሪያሎች አማልተን ይዘን በመሄድ በጉልበት ማገዝ ያለብንን ስራ አግዘን በባለሙያ የሚሰራዉን ደሞ ለባለሙያ አስረክበን መተናል 🙏 ቤቱን በጥሩ ሁኔታ ታድሶ አሁን ከላይ በምትመለከቱት መልኩ ይገኛል ፈጣሪ ይመስገን

ሁላችሁም በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ተግባር ላይ ተሳትፎ ያረጋችሁ በሙሉ ፈጣሪ ያክብርልን 🙏

አሁንም ብዙ ድጋፍ የምትፈልግ እናት ናት እና ድጋፍ ማረግ የምትፈልጉ በአድሚኖች በኩል አናግሩን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ትውስታ
ነሀሴ 02/2013 ዓ.ም

▪️ በትላንትነዉ ዕለት በነበረን የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም የነበረን ቆይታ በጥቂቱ ⬆️

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ትውስታ
ሀምሌ 18/2013 ዓ.ም

📌 የቅንነት በጎ ፍቃደኞች 7⃣ ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ቆይታ

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ትውስታ

ሰኔ 27/2013 ዓ.ም

▪️የሰኔ ወር የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም

-ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን ፡፡

በሀሳብ በጉልበት በገንዘብ ባላቹበት ሆናቹ ከጎናችን ለሆናቹ ቤተሰቦቻችንም ክብረት ይስጥልን🙏🙏🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

#ትውስታ
እሁድ ሰኔ 20/2013 ዓ.ም የነበረን ቆይታ

በዛሬዉ ዕለት በነበረን የበጎ ተግባር ቀጠሮ መሰረት ቅኖች ተሰባስበን ጉዞ ወደ አለም ባንክ ..ማህበረ ተስፋ የህፃናት እንክብካቤ የበጎ አድራጎት ድርጅት አድርገን ነበር ።

ለማህበሩ ያስፈልጉ ያልናቸዉን ግባአቶች ከእናንተዉ ዉድ አባላት የተሰበሰቡትን ይዘን በመሄድ ማዕከሉን ጎብኝተን ከጠበቅነዉ በላይ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን መጥተናል 🙏

ጥቂት ስለ ማህበሩ ⬇️

ማህበረ ተስፋ የህፃናት እንክብካቤ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወላጅ አልባ ህፃናትን ሰብስቦ በመንከባከብ ላይ እየሰራ ያለ ድርጅት ነዉ ።

ማህበሩ ስራዉን የጀመረዉ ጥር ወር 2005 ዓ.ም አራት ህፃናትን በመቀበል ነበር አሁን ላይ 20 ህፃናትን በማዕከሉ በመንከባከብ ላይ ይገኛል ...በተጨማሪ 10 ህፃናት በእናቶቻቸዉ እጅ ሆነዉ አባት የሌላቸዉ ምንም መተዳደሪያ የሌላቸዉ በዉጭ ሆነዉ የወርሃዊ አስቤዛ ...የልብስ...የመማሪያ ቁሳቁሶች..የህክምና የመሳሰሉትን ድጋፍ እንዲያገኙ ያረጋል ። ( ማዕከሉ ዉስጥ ካሉ ህፃናት ጋር እኩል ድጋፍ ነዉ የሚያገኙት ) ዉጭ ሆነዉ እንዲረዱ የተደረገዉ ከቦታ ጥበት አንፃር ነዉ

ማህበሩ የተመሰረተዉ ከ 38_40 በሚሆነ በጎ ፍቃደኞች ነዉ አሁን ላይ ግን 10 ቋሚ አባላት (መስራቾች ) ናቸዉ በመስራት ለይ ያሉት

ማህበሩ በዋናነት የሚሰራዉ ህፃናቱ
_ የመጠለያ
_ የምግብ
_የትምህርት
_ የጤና እንክብካቤ .....እና የመሳሰሉትን አንድ ህፃን የሚያስፈልገዉን እንክብካቤ እና ፍቅር አግኝቶ በስርአት ታንፆ እንዲያድግ ማረግ ላይ ነዉ ።

❇️እኛ ከተመለከትነዉ እና ከጎበኘነዉ ማህበሩ አሁን ላይ የሚያስፈልጉት ድጋፎች

▪️ ካለበት የቦታ ጥበት አንፃር ሰፋ ያለ ቦታ ተጨማሪ ህፃናትን ለመቀበል እንዲያስችለዉ እና ልጆቹ እንደልባቸዉ የሚንቀሳቀሱበት የሚጫወቱበት ቦታ እንዲኖራቸዉ ( በመንግሥት ደረጃ ይሄ ድጋፍ ቢደረግላቸዉ !)

▪️አሁን ላይ የተወሰነ ባገኘዉ ተጨማሪ ቦታ ተጨማሪ ህፃናትን ለመቀበል የቤት ግንባታ ለማረግ እቅድ ላይ ነዉ እና ማህበሩ የተለያዮ የግንባታ ግባቶች ድጋፍን ይፈልጋል

▪️የምግብ ፍጆታዎች ( በይበልጥ )
▪️አልባሳት
▪️የንፅህና መጠበቂያዎች
▪️ለህፃናቱ የሚሆኑ የተለያዮ መማሪያ መፅሀፍት
▪️እንዲሁም የገንዘብ ...የሀሳብ...የጉልበት የመሳሰሉትን ድጋፎችንም ይፈልጋል

በጥቂቱ እኛ ካየነዉ እና ከተደረገልን ገለፃ ለእናንተ ልናካፍል የፈለግነዉ ይሄን ይመስላል 🙏

🏢ማህበሩን ለመጎብኘት የምትፈልጉ አድራሻዉ አየር ጤና ...አለም ባንክ ማርያም አካባቢ ይገኛል!

ስልክ : 0911383140
0912392234 መደወል ይቻላል !

ሁላችሁም በዚህ የበጎ ስራ ላይ በሀሳብ በገንዘብም በጉልበትም እንዲሁም ባቀረብነዉ ጥሪ መሰረት ለማህበሩ የሚያስፈልጉትን ግባአትን በአይነት ድጋፍ ያረጋችሁ ..ቦታዉ ድረስ ተገኝታችሁ ማህበሩን ለጎበኛችሁ በቅንነት ስም ክብረት ይሰሰጥልን ብለናል 🙏

የቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰ትውስታ
ግንቦት 20/2013 ዓ.ም

▪️የግንቦት ወር የቤተሰብ ጥየቃ ፕሮግራም
ከላይ በፎቶዎቹ በምትመለከቱት መልኩ ደስ በሚል ሁኔታ በሁለለት እናቶቻችን ቤት ወርሃዊ አስቤዛ ይዘን በመሄድ እናቶቻችንን በስራ አግዘን ተጨዋዉተን ትንሻን ነገር አድርገን ትልቁን ምርቃት ተቀብለን መተናል 🙏

በዛሬው የቤተሰብ ጥየቃችን ላይ ጥሪያችንን አክብራቹ ለተገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር ያክብርልን እናመሰግናለን ፡፡

በሀሳብ በጉልበት በገንዘብ ባላቹበት ሆናቹ ከጎናችን ለሆናቹ ቤተሰቦቻችንም ክብረት ይስጥልን🙏🙏🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !


https://t.me/kinenetlebamochu

Photos from ቅንነት በጎ ፈቃደኞች knenet bego fekadegnoch's post 16/09/2021

🔰 ትውስታ
ግንቦት 5 /2013 ዓ.ም

የቅንነት ቤተሰቦች በዚህ ዕለት በቀረበዉ የሚል ጥሪ መሰረት ከተለያዩ ቦታ ተሰባስበን ፒያሳ 70 ደረጃ አካባቢ በሚገኘዉ ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ የካንሰር ህሙማን መንከባከቢያ ማዕከል በመገኘት #የአብይ እና #የረመዳን ፆም ፍቺ በአልን በጋራ በማዕከሉ ከማገኙ ሙስሊም እንዲሁም ክርስቲያን እህት ወንድሞቻችን ጋር ደስ በሚል ሁኔታ ለማክበር ችለናል 🙏 ...የሚገርም ፍቅርን በማዕከሉ ከሚገኙ ልጆች እና ወላጆቻቸዉ እንዲሁም ከማዕከሉ ሰራቸኞች አግኝተን የማይረሳ እና በታሪክ ማህደራችን ደምቆ የሚፃፍ ልዮ ቀንን ከላይ በምስሎቹ በጥቂቱ እንደምትመለከቱት አሳልፈናል 🙏🙏🙏

📌 ምስጋና እዚህ መልካም ተግባር ላይ እንድንሳተፍ ለረዳን ፈጣሪ 🙏🙏🙏እና ጥሪያችንን ተቀብላችሁ በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሳተፋችዉ በሙሉ ይሁን🙏🙏🙏

📌 ማዕከሉ በተለያየ መልኩ ብዙ ድጋፍን ይሻል

ከጥቂቱ እኛ ከተገነዘብነዉ ⬇️

◾️በማዕከሉ ግቢ ዉስጥ እንክብካቤ ለሚደረግላቸዉ ህፃናት ያለዉን ከባቢ ምቹ ማረግን ( የተለያዮ መሰረተ ልማቶች )

◾️የተለያዮ የንህፅና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን

◾️አልባሳትን

◾️የምግብ ፍጆታዎችን

◾️ህፃናቱ አይምሮዋቸዉን ዘና የሚያረጉባቸዉ የተለያዮ መጫወቻዎችን

◾️ህሙማንን ማንቀሳሰሻ የሚሆን አነስ ያለ መኪና

❇️ እና የመሳሰሉትን ድጋፎች ስለሚሻ ሁላችንም በሀሳብ ,በጉልበት ,በገንዘብ ,በተለያየ አይነት መልኩ ከጎናቸዉ እንሆን ዘንድ ስንል እንጠይቃለን 🙏 ድጋፍ ማረግ የምትፈልጉ በአድሚኖች በኩል አናግሩን 🙏

ፈጣሪ ክብረትን ይስጥልን 🙏

ለቅንነት መስፈርቱ ቅን ልብ ብቻ ነዉ
ቅንነት ከምንም ይበልጣል !

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Abeba
Addis Ababa