Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ

ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም!!!

23/06/2024

ድንገት ከቤት የጠፉት እማማ ቦንቱና በሬ ሊገዙ ሄደው በዛው የቀሩት አባታችን መሀመድ ሰይድ በእናንተ ደጋጎች እገዛ በሰላም ተገኝተዋል! #ክበሩልን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 21/06/2024

" 😭😭ጥላኝ የት ሄዳ ነው??
የተጨነቀው አባት ያለፉትን 7ቀናት እያለቀሰ ነው😭

ሰኔ7 የ14ዓመቷ ህፃን ት/ቤት ለመሄድ ዩኒፎርሟን ለብሳ ደብተሯን ይዛ ቡልጋሪያ ከሚገኘው ቤታቸው አብዝታ ከምትጨነቅለትና ከምትወደው አባቷ ጋር ከቤት ይወጣሉ!!

ከደቂቃዎች በኋላ ግን ህፃን ብሩክታዊት ወደ ቄራ ሰፈር ጓደኛዋ ኤደን ጋር በመሄድ ለወንድሟ "መጣን" ብለውት ይወጣሉ!! ግን ሳይመለሱ በዛው ቀሩ😭
ያለፉትን 7ቀናትም የት እንደገቡ ምን እንደገጠማቸው ሳይታወቅ ቤተሰብ ፍለጋና ጭንቅ ላይ ነው‼️
የት ነው ያላችሁት? ምንስ ሆናችሁ ነው? #ሼር በማድረግ እንፈልጋቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0911474786-መስከረም
0911425123-ዘካርያስ

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 20/06/2024

#አፋልጉኝ🤲🤲🤲
ቤተሰብ ተጨንቋል 😭
ሰናይት ገረንችል ትባላለች እሮብ በ12/10/2015 ከኮልፌ ሆላንድ ኢምባሲ አካባቢ እንደወጣች አልተመለሰችም የ14 ዓመት ታዳጊ ስለሆነች የከፋ ነገር እንዳይገጥማት በፀሎት አስቡን🤲ሼር በማድረግ ለደጋጎች አድርሱልን🤲🤲🤲
0938015580
0946454565

18/06/2024

#አልቻለም😭😭

የ2ዓመት ህፃን ከተወለደ ጀምሮ ከሆስፒታል ሳይወጣ አይኑን አጥቶ አፍንጫው ተደፍኖ በካንሰር ህመም ምክንያት ሲሰቃይ ቆይቶ ትላንት በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወቱ አርፏል😭

እናትና አባት ስለልጃቸው ብዙ መከራ ተቀብለው
ንብረታቸውን ሽጠው ወደ አዲስአበባ ቢመጡም ናቲን ከሞት ማዳን አልቻሉም😭

እናንተ ደጋጎች ለመድሀኒት መግዣና ለህክምናው ስላገዛችኋቸው አባት እያለቀሰ አመሰግኗችኋል!!

ስርዓተ ቀብሩ አስኮ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል!መፅናናቱን ፈጣሪ ያድላችሁ🙏

17/06/2024

ዘካርያስ አፅበሀ ይባላል!ሀሙስ ጠዋት ኮተቤ አካባቢ ከሚገኘው ቤቱ ልጆች ት/ቤት ላድርስ ብሎ እንደወጣ አልተመለሰም!! #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏 0968353939

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 17/06/2024

💖

እናታችን ከኮልፌ ኪቢያድ አካባቢ ድንገት ወጥተው ጠፍተው ልደታ አካባቢ ሲደርሱ አንዲት ልበመልካም እናት አግኝታቸው ጉራጊኛ የሚችል ሰው ፈልጋ ጠይቃቸው ቤት እንዲያድሩ አድርጋ ትላንት በእናንተ ደጋጎች እገዛ ወደ ቤታቸው በሰላም ገብተዋል!ስለትብብራችሁ #እናመሰግናለን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

17/06/2024

ቦንቱ ሁንዴ ይባላሉ! ትላንት እሁድ ከሰፈረሰላም አካባቢ ድንገት ወጥተው ጠፍተዋል!! ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
0923896411 ታዲ

16/06/2024

አባባ ጠፍተዋል😭

መሀመድ ሰይድ ይባላሉ!ትላንት ቅዳሜ በሬ ለመግዛት ቤተል መንዲዳ ሄደው ጠፍተዋል!! በዓልንም የት እንዳሳለፉ አልታወቀም😭 #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
0945355446
0911208385

16/06/2024

አይናቸውን የሚያማቸው እናታችን እማማ #ራዲያ ከስጦታው በኋላ እንዲህ የሚጣፍጥ ምርቃት መርቀዋችኋል!!
#አሜን በሉ🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 16/06/2024

በዓልን ሰው ለሚያስፈልጋቸው ብቸኛ ቤተሰቦቻችን በሬ አርደን ቅርጫ በማከፋፈል እንዲህ በፍቅር እያሳለፍን ነው💖
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 15/06/2024

አፋልጉኝ 🤲🤲🤲
ህፃን ሲፋን አልይ ትባላለች። የ5 ዓመት ህፃን ናት።
እናቷ ሌላ ህፃን ልጇን ይዛ እያነባች ነው። ሰኔ 03 2016ዓ/ም ጠዋት 3 ሰዓት አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ከአጠገባችን ጠፋችብን። ህፃኗን ያየ ወይም የሰማ በሚከተሉት ስልክ ቁጥር አሳውቁን።
ሼር በማድረግ ለደጋጎች አድርሱልን🤲🤲🤲
እናቷ ወ/ሮ ሰዓዳ
አባቷ አቶ አልይ መሐመድ
0960191673
0917431340

15/06/2024

‼️

እኚህ እናታችን ይባላሉ!ዛሬ ከኮልፌ ኪቢያድ አካባቢ ድንገት ወጥተው ጠፍተዋል!!እማማ የመርሳት ችግር ስላለባቸውና የመጡት ከክፍልሀገር ስለሆነ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም!! እባካችሁን #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0932590135
0911525018

15/06/2024

===============
ተማሪ አፀደማረያም ቲመኮ(ስዩም) የወልቂጤ ከተማ የሰላምበር ትምህርት ቤት የ6ተኛ ክፋል ተማሪ ስትሆን ሰኔ 07/2016ዓ.ም ዞናዊ የ6ኛ ክፍል የእርከን ማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን ያበሩስ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት እንደሄደች ወደ ቤት ሳትመለስ ቀርታለች።

ተማሪ አጸደማርያም ዕድሜዋ 16 ዓመት የሆናት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ናት።

ታዳጊዋን ያየ ወይም ያለችበት የሚያውቅ ከታች በተያያዘው ስልክ ደውሎ ቢያሳውቀን ወሮታውን እንከፍላለን ይላሉ ቤተሰቦቿ።
0910782508
0917061177

15/06/2024

ሀምዛ ዘፕረየ ይባላል!ሰኞ ሰኔ 3 በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ አዶሼ ቀበሌ ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ከጉብሬ ገበያ ጠፍቷል! ትንሽ የአእምሮ ህመም ስላለበት ቤተሰብ ተጨንቋል! #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
0912029590
0912853865

14/06/2024

💖

ትንሽ የሚያማቸው እናታችን ሙሪያድ ከክፍልሀገር መጥተው እሮብ ድንገት ከመሪ አካባቢ በር ከፍተው ወጥተው ልጆቻቸው በፍለጋና ሲጨነቁ አድረው በልበቀናው ወንድም የሺ አማካኝነት ትላንት እናንተ አግዛችሁን ወደ ልጆቻቸው መልሷቸዋል!!
#እናመሰግናለን🙏 እንዳንተ ያሉትን መልካም ልቦች ያብዛልን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

13/06/2024

‼️

እኚህ እናታችን " #ሙሪዲያት እባላለሁ፣የልጄ ስም ነው!"ብለዋል!የሚያወሩት ጉራጊኛ ነው!
ልበቀናው ወጣት የሺ ዛሬ ጠዋት መንገድ ላይ እማማን ሲደነጋገሩ አግኝቷቸው ሰፈሬ ነው ያሉት ኮተቤ ይዟቸው ቢዞርም የሚያውቃቸው ሰው ማግኘት አልቻለም!!

በመጨረሻም እንዲያርፉ ቤቱ አስገብቷቸው እኛን እባካችሁ ቤተሰባቸውን አፋልጉኝ ብሎናል!! #ሼር በማድረግ እማዬን በቶሎ ወደ ልጃቸው እንመልሳቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0912063395የሺ

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 12/06/2024

ተፈታኙ " " እያለ ነው😭😭
ቤተሰቡ ውስጥ ስቃይ በዛ😭 #እንድረስለት 🙏

ይህ የ18ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ይባላል!ከፍተኛ ውጤት ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ጎበዝ ተማሪ ሲሆን ከወራት በፊት "ትንሽ አዞረኝ ደም ማነስ ነው መሰለኝ" ብሎ ወደ ጤና ጣቢያ ሲሄድ "የአንተ ህመም ከባድ ነው ከእኛም አቅም በላይ ነው" ተብሎ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ፃፉለት!!

የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ ደግሞ "የአጥንት መቅኔህ ደም ማምረት ስላቆመ ወደ ውጭ ሄደህ መታከም አለብህ"ብለው ታዳጊውን አስደነገጡት😭

ዩንቨርስቲ ለመግባት ጓጉቶ እንደጓደኞቹ ኢንትራንስ ለመፈተን በዝግጅት ላይ የነበረው ሙሌ አሁን ግን በህይወትና ሞት መሀከል ውስጥ ይገኛል😭
ታማሚ እናትና አባቱን ተስፋ በመስጫው ሰዓት ሆስፒታል ተኝቶ በሚያሳዝን ሁኔታ በየቀኑ ደም ይሰጠዋል!በተደራራቢ ህመም አልጋ ላይ ሆኖ ይሰቃያል!
ብቸኛ የ21ዓመት ወንድሙ ዘኪ ትምህርቱን አቋርጦ ለመድሀኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለሟሟለት እየተሯሯጠላቸው የአሁኑ ግን ከአቅም በላይ ሆኖበት ወደ እናንተ ለልመና መጥቷል!በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልገው ከ4ሚሊዮንብር በላይ ስለሆነ በፀሎት እያሰባችሁት እባካችሁን #ሼር በማድረግ አግዙት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000402392607-ዘካርያስ ብርሀኑ(ወንድም)
#ስልክ
0961237095-ዘካርያስ

10/06/2024

እዮብ ዳዊት ይባላል!ግንቦት9 ከዲላ ድንገት ወጥቶ በዛው ቀርቷል!! #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
0930108566
0934773126

09/06/2024

#አፋልጉን🙏
ተፈላጊው አቶ ግርማ ቶላ ይባላሉ፥ ሰበታ ከተማ ካለዉ መኖሪያ ቤታቸዉ ረቡዕ ዕለት ማለትም 28/09/2016 ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም ፤ ቤተሰባቸዉ ጭንቅ ላይ ይገኛሉ ።
መረጃውን የተመለከታችሁ ለሌሎች በማጋራት የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን !
ፈላጊ ቤተሰብ ሥልክ 0912443891
0911056113
0910061167
0910066883
#ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 08/06/2024

ዛሬ ጠዋት 2ህፃናት ከወለቴ ማርያም መውጫ አካባቢ እንደወጡ አልተመለሱም! እድሜያቸው 10ና 11 ነው!
ስማቸው ሳሮንና ሀና ይባላሉ! #ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏
+251913745639
0985286103 የቤተሰብ ስልክ

08/06/2024

💖

እማማ ቦሌ ሚካኤል ከሚገኘው ቤታቸው ቤተክርስቲያን ደርሼ ልምጣ ብለው ወጥተው ከ5ቀናት በኋላ በእናንተ ልበደጎች እገዛ ተገኝተው ለጊዜያዊ ማረፊያነት ከነበሩበት ሜቄዶኒያ ወደ ቤት ተመልሰዋል!
ንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ግራር ፖሊስ ጣቢያና ሜቄዶኒያ ክበሩልን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

08/06/2024

አብድልከሪም ሁሴን የተባለ የኳታር ዜግነት ያለው ወደ ኢትዮጵያ ከ3ቀን በፊት የገባ ግለሰብ ሙሉ ዶክመንት ስለጣለ ምን አልባት የምታውቁት ካላችሁ ንገሩን🙏

08/06/2024

#አፋልጉን🙏
ተፈላጊው አቤሜሊክ አበበ ይባላል!ከአቃቂ መጋላ ሰፈር ረቡዕ ምሽት ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም። ፤ ታዳጊው በወቅቱ ከቤት ሲወጣ ቡራቡሬ ሹራብ እና ጥቁር ሱሪ ለብሶ የነበረ ሲሆን ከጠፋበት ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቡ ጭንቅ ላይ ይገኛል ።
ይህንን ታዳጊ ያያችሁ መረጃ እንድታሳውቁን ሲል ፈላጊ ወላጅ አባቱ ተማጽኗል ፤ መረጃውን የተመለከታችሁ ለሌሎች በማጋራት የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን !
ፈላጊ አባቱ አቶ አበበ ሥልክ 0911502986
ሌሎች አማራጭ ስልኮች
0984868640
0947798416
0947798417

08/06/2024

‼️

እኚህ እናታችን ከየት እንደመጡ አይታወቅም!ትንሽ የአዕምሮ ህመም አለባቸው!አሁን ከሚገኙበት ፖሊስ ጣቢያ ካልወጣሁ ብለው እያስቸገሩ ስለሆነ መልዕክቱን ቶሎ #ሼር በማድረግ ለቤተሰብ አድርሱልን🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

092237 2203-ሳጅን ገነት

07/06/2024

ወንድማማቾቹ ደግመው ላለመጥፋት ቃል ገብተዋል😍
እስኪ አድምጧቸው🙏

ወንድማማቾቹ #ምንተስኖትና #አቢኔዘር ግንቦት25 ገፈርሳ ጉጂ አካባቢ ተገኝተው"ሰፈራችን ቃሊቲ ነው፣ እናታችን " " ብላን ጠፍታብን ነው" በሚል ከመሸ ፖሊስ አግኝቷቸው ጣቢያ ለ4ቀናት አድረው ዛሬ ፎቶአቸው እኛ ጋር ደርሶ እባካችሁን እናታቸውን አፋልጉን ብለን ተማፅነናችሁ ነበር!!
የቀን ስራ የምትሰራው እናት ትግስት ጎረቤቶቿ ነግረዋት ስልክ ደውላልን"ልጆቼ ናቸው፣ተከራይተን የምንኖረው ኮልፌ ነው፣የነገራችሁ መረጃ ውሸት ነው፣ትልቁ የ10ዓመት ልጄ በተደጋጋሚ እየጠፋ አስቸግሮኛል፣የአሁኑ የባሰው ትንሹንም ይዞብኝ መውጣቱ ነው፣በህይወት የማገኘው አልመሰለኝም ነበር😭አመሰግናለሁ"አለች እያለቀሰች!!

እናት ትግስት ከባለቤቷ (ከልጆቹ አባት)ጋር ከተፋታች 3ዓመት የተቆጠረ ሲሆን "የራሳችሁ ጉዳይ"ብሎ ስልኩን ዘግቶና አድራሻውን አጥፍቶ የራሱን አዲስ ህይወት መኖር ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል!
(ሁሌ ስልጆቿ የምትንከራተተው ያው እናት ናት😭)

ምስጋና ለጉጂ ወረዳ ሚሊሻና ፖሊስ አባላት እያበሉና እያጠጡ በእንክብካቤ ያቆዩላትን ልጆቿን ምንም ሳይሆኑባት ወደ ቤት በሰላም ይዛቸው መጥታለች!!

እኛም በተደጋጋሚ እየጠፋ ያስቸገራትን ህፃን ምንተስኖት ለመገሰፅና ምንድነው ችግሩ? የሚለውን ለማወቅ ከመሸ ቤታቸው ተገኘን!

ምንም ምክንያት እንደሌለው አሳወቀን፣ያን ቀንም ወንድሙን አጥቦና ልብሱን ቀይሮለት የወጣው ዝምብለው እግራቸው ወደመራቸው ለመሄድና ታክሲ ጉጄ እያለ ሲጣራ ሰፈራችን እዛ ነው ብለው እንደተሳፈሩ፣ ሲመሽም ዝምብለው መንገድ ላይ ተቀምጠው የእናታቸውን ስልክና ሰፈራቸውን ሲጠየቁ እንደማያውቁ ሆነው እንደዋሹ አመኑ😭

የፈረደባት እናት ግን ለቀናት እንቅልፏን ሳትተኛ፣ ስራዋንና ቤቷን ትታ ስትንከራተት ነበር!

በመጨረሻም ብዙከተወያየን በኋላ ህፃን ምንተስኖት ሁለተኛ እንደማይጠፋ በጎረቤትና በእኛ ፊት ለእናቱ ቃል ገብቶ "አይለመደኝም ብሎ አጎንብሶ #ይቅርታ ጠይቋል!! #እናት እንኳን ደስ አለሽ💖
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

07/06/2024

አፋልጉን ይች ልጅ አያንቱ ቱጆ ትባላለች ግንቦት 23 ከሀያት አካባቢ ከሰዓት 8:30 እንደወጣች አልተመለሰችም ለአካባቢው አዲስ ናት ቤት ጠፍቶባት ሊሆን እባካችሁ ያያችሁ ካላችሁ ጠቁሙን በእግዚአብሄር ስም እማፀናለሁ 0920104994

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 07/06/2024

"ከልጄ ጋር አገናኙኝ😭😭😭" #እናት

ይህ ህፃን ይባላል!እናት ሲቸግራት በ2002ዓ.ም ቤተዛታ ችልድረን ሆም በሚባል ድርጅት በኩል የ5ዓመት ልጇን ወደ አሜሪካ ዋሸንግተን ዲሲ ትልከዋለች!የወሰዱት ሰዎች ባልየው ወታደር ሚስትየው ፎቶ ግራፈር ነች!
እስከተወሰነ ዓመት ድረስ ደብዳቤ ይልክላት የነበረው ልጇ ድምፁና መልዕክቱ ከጠፋባት አሁን 10ዓመት አለፈው!! "የላከው ድርጅትም ፈርሷል"ብላናለች!!
#ሼር በማድረግ እናፋልጋት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

ስልክ-0910261793

Photos from Baysh kolfe ባይሽ ኮልፌ's post 06/06/2024

😭😭😭
የተፈጠረው ከነገርናችሁ በተቃራኒው ነው‼️

ወንድማማቾቹ #ምንተስኖትና #አቢኔዘር ግንቦት25 ገፈርሳ ጉጂ አካባቢ ተገኝተው"ሰፈራችን ቃሊቲ ነው፣ እናታችን " " ብላን ጠፍታብን ነው" በሚል ከመሸ ፖሊስ አግኝቷቸው ጣቢያ ለ4ቀናት አድረው ዛሬ ፎቶአቸው እኛ ጋር ደርሶ እባካችሁን እናታቸውን አፋልጉን ብለን ተማፅነናችሁ ነበር!!
የቀን ስራ የምትሰራው እናት ትግስት ጎረቤቶቿ ነግረዋት ስልክ ደውላልን"ልጆቼ ናቸው፣ተከራይተን የምንኖረው ኮልፌ ነው፣የነገራችሁ መረጃ ውሸት ነው፣ትልቁ የ10ዓመት ልጄ በተደጋጋሚ እየጠፋ አስቸግሮኛል፣የአሁኑ የባሰው ትንሹንም ይዞብኝ መውጣቱ ነው፣በህይወት የማገኘው አልመሰለኝም ነበር😭አመሰግናለሁ"አለች እያለቀሰች!!

እናት ትግስት ከባለቤቷ (ከልጆቹ አባት)ጋር ከተፋታች 3ዓመት የተቆጠረ ሲሆን "የራሳችሁ ጉዳይ"ብሎ ስልኩን ዘግቶና አድራሻውን አጥፍቶ የራሱን አዲስ ህይወት መኖር ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል!
(ሁሌ ስልጆቿ የምትንከራተተው ያው እናት ናት😭)

ምስጋና ለጉጂ ወረዳ ሚሊሻና ፖሊስ አባላት እያበሉና እያጠጡ በእንክብካቤ ያቆዩላትን ልጆቿን ምንም ሳይሆኑባት ወደ ቤት በሰላም ይዛቸው መጥታለች!!

እኛም በተደጋጋሚ እየጠፋ ያስቸገራትን ህፃን ምንተስኖት ለመገሰፅና ምንድነው ችግሩ? የሚለውን ለማወቅ ከመሸ ቤታቸው ተገኘን!

ምንም ምክንያት እንደሌለው አሳወቀን፣ያን ቀንም ወንድሙን አጥቦና ልብሱን ቀይሮለት የወጣው ዝምብለው እግራቸው ወደመራቸው ለመሄድና ታክሲ ጉጄ እያለ ሲጣራ ሰፈራችን እዛ ነው ብለው እንደተሳፈሩ፣ ሲመሽም ዝምብለው መንገድ ላይ ተቀምጠው የእናታቸውን ስልክና ሰፈራቸውን ሲጠየቁ እንደማያውቁ ሆነው እንደዋሹ አመኑ😭

የፈረደባት እናት ግን ለቀናት እንቅልፏን ሳትተኛ፣ ስራዋንና ቤቷን ትታ ስትንከራተት ነበር!

በመጨረሻም ብዙከተወያየን በኋላ ህፃን ምንተስኖት ሁለተኛ እንደማይጠፋ በጎረቤትና በእኛ ፊት ለእናቱ ቃል ገብቶ "አይለመደኝም ብሎ አጎንብሶ #ይቅርታ ጠይቋል!! #እናት እንኳን ደስ አለሽ💖
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

06/06/2024

ጀማል ከማል ይባላሉ የሚኖሩት አዲስ ከተማ ሰባተኛ አካባቢ ሲሆን በትላንትናው እለት እሮብ ከመኖሪያ ቤታቸው እንደወጡ አልተመለሱም በሰዐቱ የለበሱት ልብስ ሰማያዊ ሹራብ በጥቁር ቱታ ነው እናም ያያቸው ሰው ካለ በዚ ስልክ ቁጥር 0940254525 ወይም 0913691604 ላይ በመደወል ብታሳውቁን ከልብ እናመሰግናለን ቤተሰብ 🙏

06/06/2024

ትባላለች!8ዓመቷ ነው!ትላንት ግንቦት28 ከኮልፌ አጠናተራ አካባቢ ድንገት ወጥታ ጠፍታለች!! #ሼር በማድረግ እንፈልጋት🙏
0911889444
0923590482

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

እናት💖
ወንድማማቾቹ ደግመው ላለመጥፋት ቃል ገብተዋል😍እስኪ አድምጧቸው🙏                     ወንድማማቾቹ #ምንተስኖትና  #አቢኔዘር ግንቦት25 ገፈርሳ ጉጂ አካባቢ ተገኝተው"ሰፈራችን ቃሊ...
#የእናትና_ልጅ የየቀን ውሎ ተመልከቱ😭ህፃኑ #5ቀዶ_ጥገና_አድርጓል😭#አንጀት_ይበላል😭😭😭 ይህ የ6ዓመት ህፃን #አሜን_አስፋው ይባላል!ሽንቱን ሲሸና "አቃጠለኝ" እያለ የጀመረው ህመም ፀንቶበ...
#አንጀት_ትበላለች😭😭😭እናግዛት #ሼር በማድረግ እንተባበራት🙏#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ1000553364225-ጠይባ ሁሴን#ሰልክ 0985044283"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"#ባይሽ_...
#ታሳዝናለች😭😭😭በልብ ህመም ምክንያት እድሜዋን ሙሉ በስቃይና በሰቀቀን እያሳለፈች የምትገኘው እህታችንን እንድረስላት🙏 #ሼር በማድረግና #በፀሎት እናግዛት#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ10...
ባለቤታቸውና ልጆቻቸው ሞተውባቸው ጎዳና ወጥተዋል😭እኚህ እናታችን #ጀሚላ_አህመድ ይባላሉ!65ዓመታቸው ነው!አንድ ልበደግ ወንድም ጠቁሞን ልንጠይቃቸውና ልናያቸው ወደ ፓስተር አካባቢ ሄደን አን...
ልጄን አድኑልኝ😭😭😭
ይህች ቆንጅዬ የ3ዓመት ህፃን #መክሊት_ታከለ ትባላለች!ከተወለደች ጀምሮ በልብ ህመም እየተሰቃየች አሁን ደግሞ "በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋታል" ተብላለች!! የምንችለውን እያገዝን #ሼር ...
እናቴን😭😭😭
#ሲተኛም_ከነማሽኑ_ነው😭😭😭 እናንተም #ስለጤናዬ_አመሰግናለሁ_በሉ‼️ይህ የ8ዓመት ህፃን #እዮብ_ታገሰ ይባላል!ከ10ዓመት በፊት ፖሊስ ቤት የተዋወቁት እናትና አባቱ የመጀመሪያ ልጃቸውን ለማግ...
#ጋሽ_ዘርሙ💖እኚህ ማየት የተሳናቸው አባታችን አቶ ዘርሙ ይባላሉ!ልጆቻቸውን የሚያስተዳድሩት በልመና ነው!!ትላንት ማታ በነበረን የጋራ አፍጥር ላይ እንዴት ደስ ብሏቸው እንደነበር ተመልከቱ😍 ...
አድኑኝ

Telephone

Website

Address

Kolfe Addis Ababa
Addis Ababa
Other Nonprofit Organizations in Addis Ababa (show all)
Noble Cause Elder Care and Support Noble Cause Elder Care and Support
Office Addis Ababa
Addis Ababa, P.O.BOX21261,CODE1000

We are working for/with the most poorest and potentialy vulnerable elders in Ethiopia!

Rotaract Club of Keroggie Rotaract Club of Keroggie
Bole Subcity, Woreda 03, Zewdu Gessese Bldg, House No. 2414/2nd Foor
Addis Ababa

We are visionary, committed and disciplined young Ethiopians passionate to make a positive difference in the lives of our fellow citizens and the humanity through community service...

Rotaract Club of SOLYANA Rotaract Club of SOLYANA
Addis Ababa

Rotaract Club of Solyana is one of the 16 clubs in Ethiopia, and has been running since 2007 as a partner in service of Rotary International

Rotaract club of Ra'ey Rotaract club of Ra'ey
Addis Ababa

RAC Ra'ey is a rotaract club with members of different professions and knowledge in Ethiopia working for the realization of Ethiopia's visions VISION IN ACTION!

Strong Hearts International Strong Hearts International
Nifas Silk Lafto Sub City, Kore Mekanissia Area
Addis Ababa

We are a 501c3 non profit organization, our mission is to bring about transformation from the insideo

AIESEC in Ethiopia AIESEC in Ethiopia
EiABC, Dej. Baltcha Aba Nefso Street
Addis Ababa

Welcome to the AIESEC in Ethiopia Official Fan Page! AIESEC is the World's largest student‐run organi

The School of St Yared, Ethiopia The School of St Yared, Ethiopia
Opposite French Embassy
Addis Ababa

The School of St Yared opened in 2009 with the aim of offering a top class education to talented, imp

The Ethiopian Film Initiative The Ethiopian Film Initiative
Addis Ababa

Empowering Ethiopian filmmakers

Life4all Life4all
Addis Ababa
Addis Ababa, 41303

Great Commission Ministry Ethiopia on the journey of spiritual movement every where is impacting stu

Goh Bedembia Charitable Association Goh Bedembia Charitable Association
Addis Abeba
Addis Ababa, FUTUREPARK

Goh Be Dembia Charitable Association

Cancer Care Ethiopia Cancer Care Ethiopia
Ambo Street, Melka Gefersa
Addis Ababa, 10620,ADDISABABA

This is page of cancer care ethiopia. Updates about works will be presented here.