Dr Yilkal Kefal Asires
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Yilkal Kefal Asires, Bahirdar, Bahir Dar.
በሸኔ መንገድ እየሄደን ሸኔን አናሸንፈውም። ጠላት በመረጠልህ መንገድ ከተጓዝክ ተሸናፊ እንጅ አሸናፊ አትሆንም። አሸናፊ ለመሆን ካሰብክ የራስህን መንገድ ቀይሰህ በዚያ መንገድ ብቻ መጓዝ አለብህ። የኦነግ ሸኔና የህወሃት መንገድ የልዩነትና የሞት መንገድ ነው። ከዚህ ውጭ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።
የሸኔና የህወሃት ስትራቴጄ ሁለቱን ብሄሮች አጋጭቶ፣ ቢቻል ስልጣንን መቆጣጠር ባይቻል ደግሞ አገርን ማፍረስ ነው። ለምን? አማራና ኦሮሞ አንድ ሆነው፣ ሌሎችን በዙሪያቸው ካሰባሰቡ፣ እንኳንስ ህወሃት፣ የትኛው ሃይል ሊያሸንፋቸው እንደማይችል ይታወቃል። በተግባርም ታይቷል። ስልጣን ለመያዝም ሆነ ኢትዮጵያውን ለማፍረስ፣ አቋራጩ መንገድ እነዚህን ሁለት ብሄሮች ማጋጨት ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ ለመብት እንቆማለን የምንል ሰዎች፣ ሸኔና ህወሃት በቀደዱልን ቦይ እየፈሰስን፣ ለእነሱ አላማ በተደጋጋሚ ተመቻችተን ስንገኝ እንታያለን። አንዳንድ ጊዜ ያስተውላሉ የምንላቸው ሰዎች ሳይቀሩ፣ በተቀደደላቸው ቦይ እየፈሰሱ፣ ራሳቸውን ተከታዮቻቸውን ለእነዚህ ሃይሎች አመቻችተው ሲሰጡ እናያለን።
ኦነግ ሸኔ በኦሮምያ ክልል፣ አጀንዳውን ከሚደግፉት ባለስልጣናት ጋር ሆኖ፣ የአማራና የኦሮሞ ተውላጆችን ይገድላል። እኛ ደግሞ መርጠን እያለቀስን ገዳዮቹ የሚፈልጉትን ነገር እናደርጋለን። አማራው ሲገደል፣ ኦሮሞው፤ ኦሮሞው ሲገደል አማራው ካላወገዘ፣ የህወሃትና የሸኔ አጀንዳ እየሰራ ነው ማለት ነው። ይህ ግን ከሸኔ ግድያ ጋር ብቻ ተያይዞ የሚታይ አይደለም። ለምሳሌ ባለፈው ሰሞን USAID ለኦሮምያ ክልል ኢንቨርስትመንት 11 ቢሊዮን ብር መደበ ተብሎ፣ የተማረ የሚባለው ሳይቀር፣ "የተረኝነት ማሳያ" እያለ ጻፈ። USAID ቀጠለና ለአማራ ክልል ኢንቨስትመንት 11 ቢሊዮን ብር መድቤያለሁ አለ። ያ "ተረኝነት" እያለ ሲጽፍ የነበረው ሰው ግን ድምጹን አጠፋ። ጎደሎ ሚዛን ማለት ይህ ነው። የብሄርተኝነት ሚዛኑ ጎደሎ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው። እነ ሸኔና ህወሃት በሚቀዱት ቦይ መፍሰስ ማለትም ይህ ነው።
የሸኔን ጥቃት ለመቋቋም፣ በተለይ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት አማራና ኦሮሞ፣ በአንድነት ሊቆሙ ይገባል። እርስ በርስ እየተጠራጠሩና እየተወቃቀሱ መሄዳቸውን ማቆም አለባቸው። መንግስትም ውስጡን ተመልክቶ፣ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ የማድረግ ስራ መስራት አለበት። በተለይ ደጋግሞ በተደጋጋሚ ተፈትኖ ዝቅተኛ ውጤት በሚያገኝበት፣ የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ስራው ላይ፣ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታል። የአንድ አማራ፣ የአንድ ኦሮሞ፣ የአንድ አፋር ወዘተ ደም እንቅልፍ ሊነሳው ይገባል። የአማራና የኦሮሞ ሊህቃን እና የሁለቱ ብሄሮች ህዝብ አንድነቱ እንዲጠናከር፣ ተደጋጋሚ የሊህቃንና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት አለበት። በእይታ ደረጃም ቢሆን ጥርጣሬ የሚፈጥሩትን ነገሮች ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ ማስተካከል አለበት።
ኢትዮጵያን የሚወዱና የዜጎችን እኩልነት የሚፈልጉ ሁሉ፣ በሸኔና በህወሃት መንገድ እየተጓዙ፣ ህዝባቸውን ማዳን እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው። የስልጣን ምኞት ቢኖራቸውም፣ በዚህ መንገድ ስልጣን መያዝ እንደማይቻል ማወቅ አለባቸው። የእነዚህ ብሄሮች መጣላት ኢትዮጵያን ከማፍረስ ውጭ፣ ሌላ ጥቅም አያመጣም። በፈረሰ አገር ላይ ደግሞ እንኳንስ ስልጣን መያዝ፣ ህይወትንም ማቆየት ፈተና ይሆናል።
የሸኔንና የህወሃትን ጥፋት ማክሸፍ የሚቻለው፣ በልዩነት ሳይሆን እንደ ህዝብ አንድ በመሆን ብቻ ነው ነው።
ፋሲል የኔአለም
ለአሸባሪው ትህነግ በዓለም አቀፍ ተቋማት የሚደረገው ድብቅ ድጋፍ ሊያበቃ ይገባል።
ጥቅምት 13/2014 ዓ.ም(አሚኮ) ለአሸባሪው ትህነግ በአንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ባሉት ግለሰቦች በኩል የሚያደርገው ድብቅ ዓለም ዓቀፍ ድጋፍ በቶሎ ሊያበቃ እንደሚገባ ተገለጸ።
ለረጅም ጊዜያት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሠራተኞች በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገቡ የሚያመለክቱ መረጃዎችን ተመድ አለመቀበሉን መኒ ብለድ ኮንሸንስ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ባተተበት ጽሑፉ አመልክቷል።
በቅርቡ የድርጅቱ ሰባት ሠራተኞች በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና ለአሸባሪው ቡድን ድጋፍ በመስጠት ከሀገር መባረራቸውን ያስታወሰው ጽሑፉ መንግሥት ግለሰቦቹ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጭ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ለተመድ በተደጋጋሚ ማሳወቁን ጠቅሷል።
በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ኃላፊዎችና የተመድ ሠራተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂዱትን የጣልቃ ገብነትና የጥፋት እንቅስቀሴ የሚያሳይ የድምጽ መራጃ መኖሩንም ዘገባው ዋቢ አድርጓል።
ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወገንተኛ ተጽዕኖ ጀርባ የአሸባሪው ትህነግ የውጭ አመራር የሆኑት ቴድሮስ አድሃኖም እጅ አለበት ሲል ያመለከተው ጽሑፉ አሸባሪው ቡድን በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ባሉት ግለሰቦች በኩል የሚያደርገው ድብቅ የውጭ ተጽዕኖ በቶሎ ሊያበቃ እንደሚገባ ገልጿል።
ከዚህ ቀደምም የሽብር ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የሚቀርቡበትን ወንጀሎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርቶችና የዘረፋ ድርጊቶች በተመለከተ ለተመድና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚቀርቡ መረጃዎችን በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ባሉ ደጋፊ ግለሰቦቹ በኩል ሲያፍን መቆየቱን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
አሁንም የአሸባሪው ትህነግ አባላትና ደጋፊዎች በዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል የሚያደርጉትን የእጅ አዙር ተጽዕኖ ተቋማቱ ራሳቸውን መርምረው በቶሎ ሊያስቆሙት እንደሚገባ አስምሮበታል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Bahir Dar
Gondar, Bahirdar, Debremarkos, Injibara
Bahir Dar, 1516
It's an open page to creat awareness for the community
Bahir Dar
Serving with the most advanced & state of the art machines with Laboratory technologists
Borena
Bahir Dar, 0983962578
This page is used for sharing new things/over all services related to the hospital and gain best con
Bahir Dar
Dear my friends,in this page, I'm gonna provide you with lattest health informatios concerning on t
Kebele 15
Bahir Dar
አል-ዓፊያ ከፍተኛ የባህል ህክምና ማዕከል - Al Afiya Higher Traditional M