AWDAT Multi Speciality Clinic
Speciality services in Internal Medicine, Surgery, Gyne-obs, Pediatrics!!!
Hepatitis C discovery wins the Nobel Prize The virus is a major cause of liver cancer and can lead to people needing a liver transplant.
Today is World Elder Abuse Awareness Day.
Violence against older people, who are already bearing the brunt of this pandemic, has risen sharply since the beginning of the COVID-19 pandemic and imposition of lockdown measures.
ወሲባዊ እና ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ምንድን?መጠኑስ?
ወሲባዊ ጥቃት ምንድን ነው?
ማንኛውም አይነት ከፈቃድ ውጭ በማስገደድ በማስፈራራት እና በመደለል በግለሰብ ላይ አካላዊ አእምሮአዊ እንዲሁም ስነልቦናዊ ጉዳት የሚያሰከትል ወሲባዊ ድርጊት ወይም ሙከራ ማለት ነው፡፡
ወሲባዊ ጥቃት የት ይፈጸመል
በማንኛውም ቦታ
የህጻናት ጾታዊ /ወሲባዊ ጥቃት ደረጃዎች
1.ፆታን መሰረት ያደረገ ወሲብ ነክ የቃላት ትንኮሳ/ማሸማቀቅ
3. ወሲባዊ የሆነ የአካል ጉንተላ
4. የወሲብ ምስል ወይም አካልን ማየት /ማሳየት
5. አስገድዶ መድፈር
ወሲባዊ ጥቃት በማን ይፈጸማል
ከተጠቂ ጋር የትኛውም ዓይነት ዝምድና ባላቸው ግለሰቦች ሊፈፀም ይችላል፡፡ በብዛት ቅርብ በሆኑ የቤተሰብ አባላት ይፈጸማል።
አሃዛዊ የጾታዊ/ ወሲባዊ ጥቃት መረጃዎች
የአለም ጤና ድርጅት ከሦስት ሴቶች መካከል ቢያንስ አንዷ በህይወት ዘመኗ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለወሲባዊ እና ፆታን መሰረት ላደረገ ጥቃት ተጋለጣለች ይላል፡፡
እኤአ በ 2018 በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ውስጥ 50% የጾታ/ ወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ነበሩ ፡፡ በዚህ ጥናት 13% የሚደርሱት የሀገራችን ሴቶች የመደፈር አደጋ እንደደረሰባቸው ያሳያል። ይህም ኢትዮጵያ ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ከደረሰባቸው ግንባር ቀደም ሀገራት ተርታ ትመደባለች ፡፡
በ ኢትዮጵያ በ Covid 19 የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል..
የልጆች አመጋገብ
በ ዶ/ር አላምረዉ አለባቸዉ(የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት)
ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ፣የሳምባ ምች፣የጀሮ ኢንፌክሽን እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉን በዕድሜ ከፍሎ ማየቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡
1) የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ 30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ፣ቅቤ፣ሻይ፣ዉሃ በስካር የመሳሰሉትን መስጠት ለ ኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡
2) ከ ስድስት እስከ አስራ ሁለት (6-12 ወር)
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ(እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ(እንደ ገንፎ) በቀን 4-5ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡
3) ከ1-2 ዓመት
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ(እንደ እንጀራ፣ዳቦ፤እንቁላል፣ሥጋ፣ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር ይቻላል፡፡
4) ከ 2ዓመት በኋላ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት ምንም ጥቅም ስለሌለዉ ህፃናት ከ እናት ጡት ወተት ዉጭ የሆነ አመጋገብ መቀጠል አስፈላጊ ነዉ፡፡
ተጨማሪ ምግብ የምንለው ለህጻናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ከስድሰት ወር ጀምሮ የምንሰጣቸው ምግብ ማለት ነው፡፡ ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት አያካትትም ነገር ግን ከእናት ጡት ጋር ለልጁ ተጨማሪ የምግብ አማራጭ ነው፡፡
ተጨማሪ ምግብ ልጆች ስድስት ወር ሲሞላቸው ነው የሚጀመረው ምክንያቱም የእናት ጡት ልጆች ስድስት ወር ሲሞላቸው ሙሉ ለሙሉ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ንጥረ ምግቦችን ማሞላት ስለማይችል ተጨማሪ ምግብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
እንዲሁም የህጻናቱ አንጀት ስድስት ወር ሲሞላቸው ምግብ ለመፍጨት ዝግጁ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ምግብን ልጆች ቀደም ብለው ወይም ቆየት ብለው ቢጀምሩ ምን ችግር አለው
ሀ)ከስድስት ወር ቀደመው ቢጀምሩ
ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል
ልጆች ለተቅማጥ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል
ለ)ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ
ልጆች የሚያስፈልጋጨውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
ልጆች የመቀጨጭ ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
ልጆችን እስከ ሁለት አመታቸው ድረስ ጡት መጥባታቸው ጠቀሜታው
የእናት ጡት ለልጆች ዋነኛው የሀይልና የንጥረ ምግብ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል እስከ ሁለት አመታቸው
ከ ስድስት እስከ አስራ ሁለት (6-12 ወር)የእናት ጡት ግማሽ ያክሉን ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮች ያቀርባል፡፡
ከ አስራ ሁለት እስከ ሃያ አራት(12-24 ወር) የእናት ጡት 1/3 ያክሉን ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮች ያቀርባል፡፡
ልጆች እስከ ሁለት ዓመታቸው የእናት ጡት ሲጠጡ ከበሽታ እንዲሁም ከመቀጨጭ(malnutrition) የመጋለጥ እድላቸው ይቀንሳል፡፡
ጡት ማጥባት በእናት በልጁ መሀከል ፍቅርንና መቀራረብን(mother-child bond) ያዳብራል ወይምያጠናክራል፡፡
የላም ወተት መቸ እንጀምራለን?
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከ አንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ከ አንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ 20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከ አንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክኒያት የሚከሰት የደም ማነስ(Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡
ለልጆች የተመጣጠነ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናዘጋጃለን
ምግብ አንድ፡ የልጆች ገንፎ አዘገጃጀት
ሀ) የሚያስፈልጉ ነገሮች
( በመጀመሪያ አጃ፣ገብስ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ጤፍ፣ ዳጉሳ፣ ማሽላ፣ ሽንብራ፣ባቄላ፣ አቾሎኒ፣ ሱፍ፣ ምስር፣ አደንጎሬ፣ አኩሪ አተር እና አብሽ አንድ ላይ አስፈጭተን ዱቄት እናዘጋጃለን፡፡)
ቦሎቄ ፣ ቲማቲም፣ቅቤና አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው
ለ) አዘገጃጀት
በመጀመሪያ ቦሎቄ ማታ ውሃ ውስጥ ነክሮ ወይም ዘፍዝፎ ማሳደር
ቀጥሎ ቦሎቄውን በውሃ መቀቀል እና ሲበስል ቅርፊቱን መላጥና መዳጥ
ከዛም ቲማቲም መቀቀልና መላጥ ከዛም በቀጣጭኑ መክተፍና ፈሳሽ እስከሚሆን መቀጥቀጥ
ውሃ አፍልተን ከዛም ከብዙ አይነት ተፈጭቶ የተዘጋጀውን ዱቄት መክተት(ከግማሽ ስኒ ከፍ ያለ መጠን ያድርጉ)
እያማሰልነው ከዛም የተፈጨውን ቲማቲም መክተት ከዛም ቅቤውን ከዛም የተዳጣውን ቦሎቄ ጨምሮ ማማሰል ከዛም ልክ ልናወርደው ስንል አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው መጨመርና ማውረድ ከዛም በማንኪያ ልጆችን መመገብ፡፡
ምግብ ሁለት የድንች ገንፎ በካሮት በእንቁላል የበለጸገ
ሀ) የሚያስፈልጉ ነገሮች
አንድ ትልቅ ድንች
አንድ እንቁላል
ሁለት ትንንሽ ካሮት
አንድ የሻይ ማንኪያ ቅቤ
አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው
ለ) አዘገጃጀት
ድንችና ካሮቱን በደንብ ማጠብ
ከዛም ድንችና ካሮቱን መላጥ እና መክተፍ ከዛም መቀቀል
ትንሽ ዘይት መጥበሻ ላይ ማድረግ ድንችና ካሮቱን መጨመር ከዛም መጥበሻው ላይ መዳጥ ስንድጠው ግን መጥበሻውን ከእሳት ላይ እያወረድን መሆን አለበት፡፡
ከዛም እንቁላሉን መጨመር ከዛም በደንብ ማማሰል
ከዛም አንድ የሻይ ማንኪያ ቅቤ መጨመርና አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው ጨምረን ማውረድ፡፡
ለልጆቻችን የተመጣጠነ ምግብ በመስጠት ጤናማና ብሩህ አዕምሮ ያላቸዉን ህፃናት ለሀገር ማበርከት የሁሉም ወላጅ ግዴታ ነዉ!!!
የአስም በሽታ
የአስም በሽታ ሳንባችንን የሚጎዳ የህመም አይነት ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበሽታው ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡
የአስም ህመም በአብዛኛው ከልጅነት ጀምሮ በመከሰት ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ የመተንፈሻ አካል ህመም ቢሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን እድሜ ከገፋ በኋላም የሚጀምር የህመም አይነት ነው፡፡
ለአስም በሽታ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎች በትክክል ያልተወቁ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በሽታው ሙሉ በሙሉ ሊፈውስ የሚችል መድሃኒት አልተገኘም፡፡
በአብዘኛው አንድ የቤተሰብ አባል የበሽታው ተጠቂ ከሆነ በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው፡፡
የአስም በሽታ የሚያጠቃው የሳንባችንን የአየር ቧንቧዎች ሲሆን እነዚህን ቧንቧዎች በማጥበብ እና በቂ አየር ወደ ሳንባችን እንዳይገባና እና እንዳየወጣ በማድረግ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡
የአስም በሽታ ምልክቶች
1.ሳል ፡- በተለይም በምሽት ግዜ የሚበረታ
2.ትንፋሽ (አየር) ማጠር
3.የደረት መጨምደድ ወይም መውጋት
4.ደረት አካባቢ በምንተነፍስበት ወቅት የሚሰማ ሲር ሲርታ (Wheezing)
የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል ነገር ግን ከሰው ሰው ሊለያዩ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈላጋል፡፡
1.ሲጋራ ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ የጤና ጠንቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡በተለይም ለአስም በሽታ ተጠቂዎች ማጨስም ሆነ ሲጋራ የሚጤስበት አካባቢ መሆን በሽታው እንዲቀሰቅስ እና እንዲያገረሽ ያደርጋል፡፡
2.የአየር ብክለት
ከተለያዩ ፋብሪካዎች እና ተሽከርካሪዎች ከሚለቀቁ በካይ ጭሶች እና የአካባቢን አየር ከሚበክሉ ሽታዎች ካላቸው ቆሻሻዎች ተጋላጭነትን ማስወገድ አሊያም መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጉዳይ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ እና በሃገር ደረጃ ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
3.በረሮዎች
ጥናቶች እንደሚመለክቱት ከሆነ በረሮዎች እና የሚያመነጩት ብናኝ ለአስም በሽታ መቀስቀስ ምክንያት ናቸው፡፡ በረሮዎች በአብዛኛው በቤታችን የሚገኙ እና ለጤና ጠንቅ ስለሚሆኑ ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡
4.የቤት እንስሳት
የቤት እንስሳትን በመኖሪያ ከማኖር ይልቅ ከመኖሪያ ቤት ውጪ ቤት መስራት እና ንጽህናቸውን ጠብቆ ማኖር ያስፈልጋል፡፡
እነዚህ እንስሳት ብናኝ ስለሚኖራቸው ለአስም ህመም መቀስቀስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡
5.ከዚህ በተጨማሪ እንደ ጉንፋን ፣ የተለያዩ የሳንባ ህመሞች (ኢንፌክሽኖች) ፣ ቅዝቃዜ ፣ የአየር ለውጥ እና የተለያዩ መኣዛ ያላቸው ሽቶዎች የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ እና እንዲያገረሽ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ሁሉም የአስም በሽታ ተጠቂዎች የህክምና መድሃኒት መውሰድ አይጠበቅባቸውም፡፡ የአስም በሽታን ከላይ የተዘረዘሩትን የበሽታው ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮችን በማስወገድ እና የአካል ብቃት እንቀቅስቃሴ በማድረግ መቆጣጠር ይችላል፡፡
የአስም ህክምና መከታተል የጀመረና መድሃኒት የሚወስድ የበሽታው ተጠቂ ሃኪም በሚያዘው መንገድ መድሃኒቶቹን በአግባቡ እና በትክክል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
ወላጆች አስም በሽታ ተጠቂ ከሆኑ ልጆች በሚወልዱበት ግዜ የህክምና ምርመራ እንዲዲርጉ እና በሃኪሞች የሚሰጡ ምክሮችን መከታተል ተገቢ ነው፡፡
መልካም የጤና ግዜ ይሁንልዎ
ስለ ምትከታተሉን ከልብ
አናመሰግናለን
በ ዶ /ር አላምረው አለባቸው
የህፃናት ስፔሻሊስት
የእናት ስጦታዋ
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር አቤንኤዘር እሸቱ
ጠቅላላ ሀኪም
አርታኢ ፡ ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ
የህፃናት እስፔሻሊስት ሐኪም
ከውልደት ጀምሮ እስከ እውቀት እና እርጅና ያለን አመጋገብ ከተለያየ በሽታ የመከላከል ጥቅም እንዳለው ብዙዎች ይስማማሉ። የስኳር፣ የግፊት፣ የልብ፣ የውፍረት እና የካንሰር በሽታዎችን አመጋገብን በማስተካከል መቀነስ ወይም ማስቀረት ይቻላል። ለዚህም ነው ብዙ የሰለጠኑ ሃገራት የበሽታዎችን ስርጭት እና ጉዳት እያጠኑ በየ 5 እሰከ 10 ዓመት ልዩነት የአመጋገብ መመሪያ ለዜጎቻቸው ያወጣሉ እንደ ሁኔታውም ማስተካከያ በየወቅቱ ያደርጋሉ ።
የእናት ጡት ወተት ከጥንት ጀምሮ ለህጻናት አቻ የሌለው ምቹ እና አስተማማኝ የመጀመሪያ የህጻናት ምግብ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ዘመናዊነት ሲጫነን እናቶች ለማጥባት በስራ መብዛት የጊዜ ማጣትም፣ የኑሮ ጭንቀት፣ እና የአቻ ተጽእኖ ሲደራረብባቸው ጡት የማጥባት ፍላጎትና ክህሎት እየቀነሰ መምጣቱን አንዳንድ ጥናቶች ያመለክታሉ። ጡት ማጥባት የራሱ የሆነ ክህሎት አለው።ጡት በምናጠባ ጊዜ የልጅ አስተቃቀፍ እና ጡት አጎራረስ ዘዴ ህጻኑ የተሻለ ጡት እንዲያገኝ እና በአግባቡ እንዲያድግ እናትም የተሻለ እርካታ እንዲኖራት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ውጤታማ ጡት የማጥባት ዘዴ የራሱ የሆነ አቀማመጥ፣ አስተቃቀፍ እና ጡት አጎራረስ አለው። ይህ ክህሎት እናት የጡት ጫፍ ህመም እንዳይሰማት እና እንዳትነከስ ሲረዳ ህፃኑ ደግሞ የሚፈልገውን የወተት መጠን እንዲያገኝ ስለሚያግዝ አዲስ ለወለዱ እናቶች ማስተማር ከጤና ባለሙያ ይጠበቃል ።
፩ . የጥሩ አስተቃቀፍ ምልክቶች signs of good positioning
፩ . የህፃኑን ጭንቅላትና ሙሉ ዳሌ አንድ መስመር ላይ ማድረግ
፪ . የጡትን ጫፍ እና የህፃኑን አፍንጫ ማቃረን
፫ . ህፃኑን ወደ ጡት ማስጠጋት
፬ . የህፃኑን ሙሉ ሰውነት ደግፎ መያዝ
፪ . የጥሩ ጡት አጎራረስ ምልክቶች /signs of good attachment
፩ .የህፃኑን ከንፈር በጡት ጫፍ መንካት
፪ . ህፃኑ አፉን በደንብ እስኪከፍት መጠበቅ
፫ . የጡት ጫፍን ወደ ታችኛው ከንፈር አዘቅዝቆ ማጉረስ
፬ . ህጻኑ በደንብ ጡት መያዙን ማረጋገጫ ምልክቶች
-አፍ በደንብ መከፈት ፣ የስረኛው ከንፈር ወደ ውጭ መገልበጥ
-የአገጩ ጡትን መንካት፣ ጥቁሩ የጡት ክፍል አብዛኛው ከህፃኑ አፍ በላይ መሆኑ ናቸው።
፫ . የመጥባቱ ውጤታማነት ምልክቶች
፩. አጠባቡ ዝግ ያለ፣ተመሳሳይ እና ጥብቅ መሆንና አጭር እረፍት መውስዱ
(slow, regular and deep sometimes pausing)
፪. በየጊዜው በቂ የሆነ ክብደት እና እድገትን መጨመር
፫. ከጠቡ በኋላ በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ይተኛሉ
፬ . ጡት የማጥባት ጥቅሞች
ጡት ማጥባት ለእናትም ለህጻንም ወደር የማይገኝለት ብዙ ጥቅም አለው።
ሀ. ለእናት ያለው ጠቀሜታ
፩ .ከሚገዙ የተዘጋጁ የወተት አይነቶች ይልቅ ርካሽ መሆኑ
፪ . ሁሌም መገኝቱ
፫ . ለእናት ልጅም በራስ መተማመን እና የአእምሮ እርካታ ማጎናፀፍ
፬ . ከወሊድ በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት እና ሳምንታት የእናትን የመድማት አደጋን ይቀንሳል።
፭ . በትክክል የምታጠባ እናት እስከተወሰነ ጊዜ እንደ ተፈጥሮ የወሊድ መቆጣጠሪያነት ያገለግላል
፮ . እናት ላይም ይሁን ህጻናቱ ላይ አላስፈላጊ ክብደትን ይቀንሳል
፯ . በእናትና ልጅ መካከል ልባዊ እና ስሜታዊ ትስስርን ይጨምራል
፰ . የእንግዴ ልጅ ቶሎ እንዲወጣ ያግዛል
፱ . የጡት እብጠትን እና ኢንፌክሽን ይከላከል
፲. የጡት ና የመሃፀን ካንሠርን ይቀንሳል
ለ. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ያሉት ጥቅሞች
፩ . ሙሉ በሙሉ አልሚነት አለው
፪ . በቀላሉ መፈጨትና መመጠጥ
፫ .ንፁህና በማንኛውም ጊዜ ለመስጠት ምቹና የተመጣጠነ ሙቅት አለው።
፬ . ፀረ ጀርም አለው
፭ . የተቅማጥ በሽታን፣ የጆሮ ኢንፌክሽን የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፡የደም በባክቴሪያ መበከልን ይከላከላል
፮ . የስውነት አንዳንድ ነገሮችን አለመቀበል ይቀንሳል reduces incidence of allergies
፯ . የአገጭና የጥርስ እድገትን ያግዛል
፰ . የአእምሮ ብስለት እና እድገትን ያፋጥናል
፱ .ተጨማሪ ምግብ እስኪጀመር ድረስ ለህፃኑ የሚያስፈልገውን ያህል በቂ የውሃ ይዘት አለው።
፲. የስኳር ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
፲፩. የአንጀት የደም ካንሰርን ይከላከላል
፲፪. የተሻለ የእውቀት አድማስ፣ የመግባባት ችሎታ እና የማስታወስ ችሎታ ያጎናፅፋል።
፲፫ . የህጻናት በምግብ እጥረት መጎዳት እና ሞትን ይቀንሳል
እውነታዎች
፩ አንድ ህፃን በተወልደ አንድ ሰዓት ሳይሞላው ጡት መጥባት አለበት።
፪ አንድ ህፃን ተወልዶ ሰድስት ወር እስኪሞላው የእናት ጡት ወተት ብቻውን መስጠት በቂ ነው።
፫ እንገር የሚባለው ቢጫ ወተት ህጻናቱ እንደተወለዱ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናቶች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን
ብዙ ጥቅሞች አሉት ፦ በፕሮቲን የበለፀገ ነው፣ፀረ ባክቴሪያዎች አሉት
እና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል። እንገር የመጀመሪያው የተፈጥሮ ክትባት እንደሆነም ይታመናል።
፬ ጡት በቀን ውስጥ ከ8-12 ጊዜ መጥባት አለባቸው። ቢያንስ በየሦስት ሰዓት ልዩነት መጥባት ይኖርባቸዋል።
በመጀመሪያ ጥቂት ቀናት ያለው የወተት መጠን አነስተኛ ቢሆንም ለህጻናት በቂ መሆኑ ይታወቃል። ጡት በደንብ መመንጨት የሚጀምር በተወለዱ ከ2-5 ቀናት ውስጥ ነው። ይህ የሚሆነው ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጡት በበቂ ሁኔታ ከተጠባ ብቻ ነው።
ስለዚህ ሁለቱንም ጡት በየተራ እስከመጨረሻው እንዲጠቡ ያደርጉ። በየመሀሉ ደግሞ ማስገሳት እና ጡት እንደገና መሞከር ያስፈልጋል።
ጡት ማጥባት የሚከለክሉ ምክንያቶች
፩. እናት በጠና የታመመች እና ጡት አልቦ ለመስጠት ጤንነቷ የማይፈቅድ ከሆነ
፪. እናት የጡት ካንሰር ታማሚ ከሆነች
፫. እናት የኤች.አይ.ቪ ታማሚ ሆና ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ጡት አላጠባም ብላ ከወሰነች
፬. ቲቢ/የሳንባ ነቀርሳ በአክታ የተገኘባት እናመድሃኒት በጀመረች ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጡት ማጥባት የለባትም።
፭. የካንሰር መድሃኒት ወይም የጨርራ ህክምና የምትወስድ እናት።
፮. እናት ታማ የምትወስደው መድሃኒት ጡት ማጥባት የሚከለክል ከሆነ
ይህ ጽሁፍ መታሰቢያነቱ ዘጠኝ ወር አርግዘው አራት ዓመት አጥብተው ለወግ ለማረግ ላበቁን እናቶቻችን ሁሉ ይሁን።
መሰረታዊ የድንገተኛ ህክምናእርዳታ (BASIC LIFE SUPPORT)
- መሰረታዊ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ ማለት አንድን ሰው ህይወቱ አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ በሚሆንበት ወቅት ህይወቱን ለማትረፍ በፍጥነት የሚሰጥ የህክምና አይነትነው።
- የዚህ ሕክምና ዕውቀት ሁሉም ሰው እንዲኖረው እና እንደአስፈላጊነቱ እንዲጠቀምበት ይመከራል።
- ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ብዙ ሰዎች በድንገተኛ ህክምና እርዳታ እጥረት የህክምና ማዕከል ሳይደርሱ ሂወታቸውን ያጣሉ፡፡
መሰረታዊ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ መስጫ መንገዶች ?
1.ደረትን በመጫን የልብን ደም የመርጨት አቅም መደገፍ
2.በአፍ አየር በመሥጠት ወደ ሳንባ የሚገባ አየር መሥጠት
3.እንደ አስፈላጊነቱ የልብ ምት ለማሥተካከል የሚረዳ መሣሪያ (Defibrillator)መጠቀም፦ ይህኛው መሣሪያ እንደአስፈላጊነቱ በሕክምና ባለሙያዎች ቢሰጥይመከራል።
መሰረታዊ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ የሚያስፈልገዉ ለማንነው ?
- በድንገት ራሳቸውን ስተው ወድቀው የልብ ምታቸው በድንገት ያቆመ እና በድንገት መተንፈስ ያቃታቸው ሰዎች ናቸው።
በመሠረታዊ ድንገተኛ የሕክምና እርዳታ(Basic Life Support) በቅደም ተከተል የምንከተላቸው ህክምናዎች
1.በመጀመሪያ ሌሎችን ከመርዳታችን በፊት አካባቢው ለራሳችን ጤና የማያሠጋ መሆኑን ማረጋገጥ
2.የወደቀውን ሠው ትከሻውን በተደጋጋሚ በመንካት እና ጮክ ብሎ በመጥራት አለመንቃቱንማረጋገጥ
3.የወደቀው ሠው የማይሰማ እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማያደርግ ከሆነ ፦
1 ሌሎችሠዎችን ለዕርዳታ መጥራት
2 የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ካሉ ቶሎ መጥራት እና ግዜ ሳናባክን ወደ ድንገተኛ ነፍስ አድን ህክምና መግባት፡፡
3 የህክምና ባለሙያ ካልሆንን በስተቀር ወድቆ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ያላደረገን ሠው የልብምቱ መቆም አለመቆሙን እና በደንብ መተንፈስ አለመተንፈሱን ለማረጋገጥ ጊዜ አለማባከን።
መሰረታዊ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ እንዴት ይሰጣል?
ሁለት ሰዎች ካሉ
- አንደኛዉ ሰዉ ደረት ቶሎ ቶሎ በመግፋት ሲረዳ ሌላኛዉ አየር በመስጠት ሊረዳ ይችላል
- 30 የደረት መግፋት ድግግሞሽ ከተሰራ በኃላ 2 ጊዜ አየር
መስጠት
አንድ ሰዉ ብቻዉን ካለ
- አንድ ሰዉ ብቻዉን ከሆነ ተደጋጋሚ የሆነዉን የደረት መግፋት የህክምና ባለሙያዎች እስኪመጡ መቀጠል፡፡
- የደረት መግፋት ድግግሞሽ በደቂቃ ከ100 ያላነሰ እንዲሆን ይመከራል፡፡
የደረት ግፊት እንዴት ይሰራል፦
ከታች ምስሉ ላይ እንደሚታየዉ ፡
1. ሁለት እጃችንን በማደራረብ መሀል ደረት ላይ በማድረግ
2. ደረት በሚገፋበት ወቅት ወደ ዉስጥ ከ5 ሳንቲ ሜትር በላይ መግባት የለበትም
3. የደረት መግፋት ድግግሞሹ በደቂቃ ከ100 ያላነሰ መሆን አለበት፡፡
አየር እንዴት ይሰጣል፦
ከታች ምስሉ ላይ እንደሚታየዉ፡
- ራስን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ አፍን በተጎጅዉ አፍ ላይ በማድረግ አየር በሃይል ወደ ዉስጥ መግፋት፡፡
ከላይ ያቀረብነዉ ፅሁፍ ስለድንገተኛ ህክምና አስፈላጊነት እና አሰራር ንቃተ ህሊና ለመፍጠር ይረዳል ብለን እናምናለን።
በተጨማሪ ባቅራቢያ የሚገኙ ባለሙያዎችን በማማከር እዉቀትዎን ያዳብሩ፡፡
ጤና ይስጥልን፡፡
ዶ/ር ተመስገን አሰፋ
ህጻናት ለምን በኮሮና በብዛት አይጠቁም?
Why children are less vulnerable to COVID-19?
የመጀመሪያው መልስ ምክንያቱ አይታወቅም ነው።
ሳይንሳዊ መላ ምት ካላችሁ ግን
1. ህጻናት በብዛት የውጭ ተጋላጭነት ወይም የጉዞ ታሪክ ተጋላጭ አለመሆናቸው። ለምሳሌ አሁን ከቤት አይወጡም ስለዚህ ተጋሊጭነታቸው ከቤተሰቦቻቸው ብቻ ይሆናል። children are less exposed to the outside environment than adults. Adults tend to have more travel history as compared to children.
2. በብዛት ጉንፋን ስለሚያጠቃቸው ይህ ለተመሳሳይ ግን አደገኛ ለሆኑት ኮሮና እና ኢንፍሉዌንዛ ያላቸውን የህመም ተጋላጭነት ይቀንሰዋል ( viral interference it is well known fact that a cell infected by a virus develops a resistance to super infection with a similar or different virus: it produces defective interfering mutants and also interfere induced by interferons which stimulate infected and neighborhood cells to be resistant to infection)
3. የኮሮና ተቀባይ ህዋሳት ህጻናት ላይ በቅርጽም በመጠንም ከአዋቂዎች ይለያሉ። ይህ ደግሞ ለቫይረሱ ምቹ እንዳልሆነ ይገመታል። the receptors of COVID-19 angiotensin concerting enzyme 2 receptor tend to be expressed differently in the respiratory tract of children than adults
4. ለኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽን ግብረመልስ የሚሰጡ የመከላከያ ህዋሳት በብዛት አይመረቱም ስለዚህ ሳንባ ላይ የሚደርሰው ጉዳት በዚያ ልክ ይቀንሳል። children has less vigorous immune response to the virus than adults. It is the cytokine response that damages the lung of adults.
5. ህጻናት የቆየ የጤና እክል በብዛት ስለሌለባቸው ( underlining chronic diseases are common in adults as compared to children )
6. የህጻናት ሳንባ ከአዋቂዎች ይልቅ በሽታ ይቋቋማል(children has a resilient lung because it is not damaged by previous disease or air pollution or smoke as compared to the elderly. ).
by Dr. Nigus Chanie
Alcohol based sanitizer available at AWDAT pharmacy
New services at Awdat Speciality Clinic :
- Adult & Pediatrics Bone marrow Aspiration.
- Cervical cancer screening
Awdat Multi Speciality Clinic:
We are giving services in different specialities by Experienced specialists & well equipped laboratory & Radiology services :
- Internal Medicine
- General Surgery
- Orthopedics
- Pediatrics
- Gyne - Obs
- Dermatology
- Pathology
- X-ray & U/S services by Radiologist
- Pharmacy - All necessary Medicines are available with Experienced Professionals advice!!!
" Come & Visit us"
AWDAT speciality Clinic has a complete laboratory & Imaging services:
-CBC
-Chemistry
-Hormone Analysis
-TSh
-T4
- T3
- FSH
- LH
- BHCG
- AFP
- Troponin
- U/S services with Modern machine
- X-ray
AWDAT Speciality clinic wishes you
Merry Xmas & Healthy New Year!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.