የአባዲር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት/Abadir wareda health office

This is the official face book page of abadir health office

23/03/2022

በህይወታችን ከፍ ያለ ቦታ ለመገኘት ትናንሽ ደረጃዎችን መውጣትና መሰናክሎችን ማለፍ ያስፈልጋል!
እሾህ የሌለው መሬት እንቅፋት የሌለው ሂወት የለም እና ሁሉንም በትዕግስት እንለፍ...

የሰውን ልጅ ቀና የሚያደርገው ትራስ ሳይሆን ጊዜ ነው!!! ሁሌም ቢሆን ፈገግ በል ምክንያቱም ለአንተ እንባ ማንም ሰው ግድ የለውምና !

ከፈጣሪህ በቀር በማንም ላይ ተስፋ አታድርግ አብዛኞቹ ሰዎች በምታስፈልጋቸው ስዓት እንጂ በሚያስፈልጉህ ስዓት አይገኙም

መቼም ቢሆን ተስፋ እንዳትቆርጥ በዝግታም ቢሆን ተራመድ እንጂ በፍፁም ወደ ኋላ እንዳትመለስ።

ወድቆ የሚነሳ ወድቆ ከማያውቅ እጅግ ጠንካራ ነው። ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእሞሮ ነው ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍነው::

ፈጣሪ ለእናንተ የከፈተውን በር ማንም ሰው መዝጋት አይችልም! ካሳለፍነው የሚመጣው የተሻለ ይሆናል !

ይህ የዛሬ መልክቴ ነው ፈጣሪ ለሀገራችን ሰላም ለኛ ጤና ይስጠን።

15/02/2022

ለሁለተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ መሳካት መገናኛ ብዙሀንና አመራሮች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠየቀ

ከየካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በዘመቻ መልክ ለሚሰጠው የኮቪድ 19 ክትባት የመላው ህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲጠናከር የመገናኛ ብዙሀን እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች አስፈላጊውን ቅስቀሳና ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

የጤና ሚኒሰቴር በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሁናዊ ሁኔታ እና የኮቪድ 19 ክትባትን አስመልክቶ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ በእናቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር እና የክትባት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ላቀው እንደገለፁት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሁንም የጤና ስጋት በመሆኑና ዜጎቻችንም እየሞቱ ስለሆነ ዘመቻውን ማድረግ አስፈልጓል።

ለክትባት የሚሆን ከ20 ሚሊዮን በላይ ዶዝ ለሁሉም ክልሎች መላኩንና ባለሙያዎችም ሰልጥነው መሰማራታቸውን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ህብረተሰቡ በክትባቱ በሚገባ ተሳተፎ ራሱንና ቤተሰቡን በማስከተብ ቫይረሱ ከሚያስከትለው ስቃይና ሞት እንዲከላከል የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ቅስቀሳ በማድረግና ግንዛቤ በመፍጠር አመራሮች ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

ባለፈው ህዳር ወር ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ዘመቻ አስር ሚሊዮን ሰዎችን በክትባቱ መድረስና ከበሽታው መታደግ መቻሉን አቶ ዮሐንስ ተናግረው ሁለተኛውን ዙር የክትባት ዘመቻም ለማሳካት ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።

የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮርዳኖስ አለባቸው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደ አገር የኮቪድ 19ን በመከላከልና በመቆጣጠር በኩል በተሰራው የተቀናጀና የተደራጀ ስራ ውጤት እንደነበረው ገልፀው በቀጣይም ህብረተሰቡ በሽታውን አቅልሎ እንዳያይና ከመዘናጋት እንዲወጣ ሚዲያዎች ጠንካራ መልዕክቶችን እና ወረርሽኙ የሚያደርሰውን ጉዳት በተለያዩ አቀራረቦች በተከታታይ ማስተላለፍ ይገባቸዋል ብለዋል ።

በስልጠናው የተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ካቀረቡ በኋላ የመላው ህብረተሰብ ተሳትፎ ለማጠናከርና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግና ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተባብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ክትባቱ በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት እና ጊዜያዊ የክትባት ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን እድሜያቸው አስራ ሁለት አመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች ይሰጣል። ክትባት ያልወሰዱ፣ የመጀመሪያውን ዶዝ ወስደው ሁለተኛውን ያልተከተቡና ማጠናከሪያ ክትባት/Booster Dose/ የሚያስፈልጋቸው ክትባቱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ክትባቱን በተመለከተ ያላችሁን ቅሬታና አስተያየት በነጻ የስልክ መስመር 952/8335 በመደወል ማቅረብ ይችላሉ።

07/02/2022

የህጻናት የደም ማነስ
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ
የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት

የደም ማነስ ምንድን ነው?
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
የደም ማነስ ማለት የቀይ የደም ህዋስ ብዛት መቀንስ ሲሆን በተለይም የሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት ልኬት መጠን በላብራቶሪ ሲለካ ከእድሜ አቻ ህፃናት ጋር ሲነፃፀር መጠኑ የቀነሰ ሆኖ ሲገኝ ነዉ።

የደም ማነስ በህጻናት እድሜ

የደም ማነስ ህጻናት ላይ በጣም የተለመደ የህመም ምልክት ነው።

የደም ማነስ ለምን ህጻናት ላይ ይከሰታል?

1. ህጻናት ፈጣን እድገት ስላላቸው አንጻራዊ እጥረት ያጋጥማል
2. ከእናት በጽንስ ጊዜ ከእትብት ያከማቹት የብረት ማእድን ከ4-6 ወር ጊዜ በኋላ የሚቀንስ መሆኑ
3. ለህጻናት በተለምዶ በቤት ውስጥ የሚጀመር ምግብ በቂ የብረት ማእድን የሌለው መሆን።
4. ያለ በቂ ግንዛቤ ተጨማሪ ምግብ መጀመር
5. ህጻናት እያደጉ ሲሄዱ የሰውነታቸው የብረት ማእድን ፍላጎት መጨመር
6. በተፈጥሮ የብረት ማእድን ከሰውነት ጋር ያለው ውህደት አነስተኛ መሆን።

የደም ማነስ የህመም ምልክት እንጅ ራሱን የቻለ ህመም አይደለም። መንስኤውም እንደ እድሜ ክልል የተለያየ መሆኑ ይሰመርበት።የህመም ምልክቶቹ እንደ በሽታው ክብደት ይለያያሉ። በመሰረቱ የህመም ምልክቶችን ለማሳየት መቅኔ፣ ጉበት እና ጡንቻ ውስጥ ያለው የብረት ማእድን እስኪቀንስ ድረስ ብዙ ሳምንታት የዘለቀ ጊዜ ይፈልጋል። ይህም ሰውነታችን የመጠባበቂያ የብረት ማእድን ስንቁ እስኪሟጠጥ ድረስ ከ2-3ወር የህመም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት የደምን የልኬት መጠን ካልወሰድን ባለሙያው በቀላሉ የሚያውቅበት እና ወላጅም የሚጠረጥርበት አጋጣሚ አነስተኛ ነው። ሆኖም ይህንን ለመቅረፍ በተለይ ለደም ማነስ የተጋለጡ እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህጻናትን ቢያንስ ከ3-6 ወር ባለ የጊዜ ልዩነት ሙሉ የደም ቆጠራ (CBC) በማድረግ
አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል። ሌላው ግን ለደም ማነስ አጋላጭ ምክንያት ላላቸው ህጻናት ክትትል በማድረግ የከፋ የደም ማነስ ሳይከሰት ማወቅ እና ማሳከም ይቻላል። ለደም ማነስ አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

የደም ማንስ ዋና መንስኤዎች

1. የቀይ ደም ህዋስ ምርት መቀነስ
2. የቀይ ደም ህዋስ ቶሎ ቶሎ መሞት
3. የደም መፍሰስ

የደም ማነስ አይነቶች

፩. ብረት ማእድን አጠር ደም ማነስ
፪. በደም ህዋስ ቶሎ መሞት የሚከሰት ደም ማነስ
፫. ውልደታዊ ደም ማነስ፡ የቀይ ደም ህዋስ ቅርጽ መጠን እና ይዘት ከተለመደው ተፈጥሮ ውጭ መሆን
፬. የቀይ ደም ህዋስ ምርት አጠር ደም ማነስ
፭. የቀይ ደም ህዋስ ግዘፍ ደም ማነስ

የደም ማነስ አጋላጭ ምክንያቶች
1.በጨቅላነት እድሜ
፩. ከእትብት የደም መፍሰስ
፪. ከወሊድ በፊት የእንግዴ ልጅ መድማት
፫. ሾተላይ
፬. የእናት እና የልጅ የደም አይነት አለመመሳሰል/የእናት ደም አይነት ኦ ሆኖ የጨቅላ ህጻን ደም ኤ ወይም ቢ ሲሆን
፭. የመወለጃ ጊዜው ሳይደርስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን
፮. መንታ ከሆኑ ከአንድ ፅንስ ወደ ሌላኛው ፅንስ በደም ስር መወሳሰብ ምክንያት የደም መለጋገስ
፯. ተፈጥሯዊ የደም ቅርጽና መጠን መዛነፍ

2. በለጋነት እድሜ እና እስከ ሁለት አመት ድረስ አጋላጭ ምክንያቶች
፩. በእርግዝና ወቅት የእናት ብረት ማእድን ማነስ
፪. የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት
፫. መንትያ ህፃናት
፬. የብረት ማእድን ያነሰው ምግብ መመገብ
፭. በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት
፮. ረጅም ጊዜ የዘለቀ ውስጣዊ ህመም
፯. የደም ካንሰር፣ የመቅኔ ህመም
፰. ያልታወቀ ረጅም ጊዜ የዘለቀ የጨጓራ ቁስለት የአንጀት ቁስለት

25/01/2022

ለጤናማ እርግዝና መዘጋጀትና ማቀድ
🩺🔬🩺🔬🩺🔬🩺🔬🩺🔬🩺
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
ለማርገዝ ከመሞከሬ በፊት ሐኪም ማነጋገር አለብኝ?

አዎ ለማርገዝ ሲያስቡ ለቅድመ እርግዝና ምርመራ ሃኪም ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው።በእርግዝና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ነገሮች ሐኪሙ ይጠይቀዎታል።

ለምሳሌ :-
ስለ አመጋገብዎ፣ ስል አኗኗርዎ፣ ስለ የሚወስዱትየወሊድ መቆጣጠሪያ ፣ ስለ ቀደምት እርግዝናዎች፣ ስለ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች እና በራስዎ ወይም በቤተሰብዎ ውስጥ ስላሉ ማንኛውም በሽታዎች ሊጠይቅ ይችላል።

እርግዝናዎ በተቻለ መጠን ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ እርስዎ እና ሐኪምዎ ልታደርጓቸው የምትችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ።

እነዚህ ነገሮች ለማርገዝ ከመሞከርዎ በፊት ቀደም ብለው ሊደረጉ ይገባል
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

💊 የሚወስዷቸውን መድሃኒቶች ካሉ እና ምን አይነት ለውጦች ማድረግ እንዳለብዎት ይወቁ

💉ክትባቶችዎ ወቅታዊ መሆን አለመሆንዎን ይወያዩ

🥗 ፎሊክ አሲድ ያለው መልቲቫይታሚን መውሰድ ይጀምሩ

🥄🍴 የትኞቹ ምግቦች ማቆም እንዳለብዎ እና የትኞቹ ምግቦች ማዘውተር እንዳለብዎ ይወቁ

▪️ሲጋራ ማጨስን፣ አልኮል መጠጣትን፣ ወይም በሃኪም ያልታዘዘልዎት መድሃኒቶችን ከመውሰድ ይታቀቡ

📌 ማንኛውም የሕክምና ሁኔታ ካለዎት ፣ በቤተሰብዎ ወይም በትዳር ጓደኛዎ ቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ በሽታዎች ካሉ በጽንሱ እና በእርስዎ ላይ ሊያስከትል የሚችል ችግር ካለ ይረዱ።

📌 በመኖሪያ ቤትዎ ወይም በስራ ቦታዎ ውስጥ ማንኛውም ጎጂ ነገር እንዳለ አውቀው ምን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብዎ ይወቁ

❇️ ጤናማ የክብደት መጠን ለመድረስ ይሞክሩ

20/01/2022

የማህጸን እጢዎች (uterine fibroids)

የማህጸን እጢዎች ምንድን ናቸዉ?

የማህጸን እጢዎች ድንች መሰል ቅርጽ፣ ይዘትና ጥንካሬ ያላቸው ከማህጸን ጡንቻ የሚነሱና የሚያድጉ እባጮች ናቸው። ማህጸን ስንል በእርግዝና ወቅት ጽንስ የሚቀመጥበት የሴት የመራቢያ አካል ማለታችን ነው

የማህጸን እጢዎች ተራ እባጮች እንጂ ካንሰር ወይም የካንሰር ባህሪ የተላበሱ አለመሆናቸው መገንዘብ ተገቢ ነው።

የማህጸን እጢዎች የህመም ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?

አንዲት ሴት የማህጸን እጢ ቢኖርባትም ምንም አይነት የህመም ምልክት ላይታይባት ይችላል ። ይሁንና የማህጸን እጢዎች ያላቸው ሴቶች ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላል።

❇️ የወር አበባ መብዛት

❇️ የሆድ ህመም ፣ መጫን ፣ መንፋት

❇️ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት

❇️ የሆድ ድርቀት

❇️ መጸነስ አለመቻል

የማህጸን እጢዎች ህክምናቸው ምንድን ነው?

ለማህጸን እጢዎች የሚሆኑ የተለያዩ የህክምና አማራጮች አሉ። እያንዳንዳቸው የህክምና አማራጮች የራሳቸው የሆኑ ጥቅሞችና ጉዳቶች ይኖራቸዋል። ይሁንና አንዲት ሴት የማህጸን እጢዎች ስለተገኙባት የግድ ህክምና ያስፈልጋታል ማለት አይደለም። የህክምናው አስፈላጊነት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

ለምሳሌ

❇️የህመም ምልክቶች መኖር

❇️እድሜ (ለምሳሌ ያረጡ ሴቶች ላይ የእጢው መጠን ስለሚቀንስና የህመም ሰሜቶች ስለሚጠፉ ህክምና ላያስፈልግ ይችላል )

❇️ የመጸነስ ፍላጎት

❇️ የወር አበባ ከመብዛቱ የመጣ የደም ማነስ መኖር

❇️ የማህጸን እጢዎቹ መጠን ፣ ብዛትና የተቀመጡበት ቦታ ወዘተ ናቸው።

ዋናዋናዎቹ የህክምና አማራጮች የሚከተሉት ናቸዉ

✳️ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች

ይህ አማራጭ የወር አበባ ለሚበዛባቸው ጊዜያዊ መፍትሔ ሲሆን የማህጸን እጢዎች ቁጥርና መጠን በመቀነስ ረገድ የጎላ ተጽዕኖ የለውም ።

🔰በቀዶ ህክምና የማህጸን እጢዎችማውጣት (myomectomy)

ይህ አማራጭ በቀዶ ህክምና እጢዎቹን ብቻ ለይቶ ማውጣት ሲሆን ወደፊት ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ጥሩ አማራጭ ነው። ችግሩ ከተወሰኑ አመታት በኋላ እጢው ሊተካ መቻሉና ዘላቂ መፍትሔ አለመሆኑ ነው።

💠በቀዶ ህክምና ማህጸን(ከነእጢዎቹ) ማውጣት (hysterectomy)

ይህ ህክምና ማህጸን አብሮ ስለሚወጣ የበሽታው ፍቱን መፍትሔ ነው።
ችግሩ ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ጥሩ አማራጭ አለመሆኑ ነው።

በሃገራችን ለግዜው ጥቅም ላይ ባይውሉም ሌሎች የህክምና አማራጮችም አሉ።

ለምሳሌ:—

🔰Endometrial ablation

🔰Uterine artery embolization

🔰Uterine fibroid embolization

ለማጠቃለል አንዲት ሴት የማህጸን እጢዎች ከተገኙባትና ህክምና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፤ ከሃኪም ጋር በመመካከር ከተጠቀሱት አማራጮች መምረጥ ይኖባታል።

👉ልጅ የመውለድ እቅድ ያላት ሴት በመድሃኒት ምልክቶችን መቆጣጠር ወይም እጢዎችን ብቻ በቀዶ ጥገና ማውጣት የተሻለ አማራጭ ነው።

⏩ ልጅ የመወለድ እቅድ የሌላት ሴት ሁሉንም አማራጮች መጠቀም ትችላለች ።

⏩ በእድሜ የገፉና በማረጥ እድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ከክትትል የዘለለ ህክምና ላያስፈልጋቸው ይችላል ።

Photos from የአባዲር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት/Abadir wareda health office's post 15/10/2021

ሲሪስ አፕል ጁይስ 100% መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲሪስ አፕል ጁስ 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡

በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በሲሪስ አፕል ጁይስ ውስጥ 100% ስለተገኘ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል፡፡

ይህ ምርት የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ (INFOSAN) በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ያስጠነቀቀ ሲሆን፥ በተመሳሰሳይ የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ የምግብና የመጠጥ አምራች ኩባንያ፤ የፍራፍሬ ጭማቂው ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ እንዳለ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ነው ያሳሰበው፡፡

በመሆኑም ህብረተሰባችን የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% ምርት በሀገራች ገበያ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ምርቱን እንዳይጠቀም ያስጠነቀቀ ሲሆን÷ ምርቱን በማንኛውም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ እንዲቀርብ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡

13/10/2021

ለሐረሪ ክልል ነዋሪዎች በሙሉ
የልጅነት ልምሻ ወይም የፖሊዮ በሽታ የህፃናትን አካል በተለይም የእጅና የእግርን ጡንቻ የሚያዳክምና የሚያልፈሰፍስ ብሎም ለሞት የሚዳርግ ተላላፊ በሽታ ነው::
የልጅነት ልምሻ ወይም የፖሊዮ በሽታ በክልላችን ጨምሮ በሃገራችን በተለያዩ ክልሎች በቅርቡ በመከሰቱ ምክንያት የበሽታውን ሥርጭት ለመቆጣጠር የሚያስችል ክትባት ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ይሰጣል፡፡
በመሆኑም ክትባቱ ከጥቅምት 12-15-2014 ዓ/ም ድረስ ክትባቱን በሚሰጡ ጤና ባለሞያዎች ቤት ለቤት የሚካሄድ በመሆኑ ህፃናት ከዚህ በፊት ይህን ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም ይህንን ክትባት ወላጆችና አሳዳጊዎች በማስከተብ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ እናሳስባለን፡፡
ወላጆችና አሳዳጊዎች ህፃናትን በምናስከትብበት ወቅት የኮሮና በሽታ መከላከያ የጥንቃቄ መንገዶችን ማለትም:
● እጅን በተደጋጋሚ በመታጠብ
●አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣
●አፍና አፍንጫን በመሸፈን እንዲሁም
●ቤት በመቆየት ራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ እናሳስባለን!
ህፃናትን በማስከተብ ከፖሊዮ በሽታ እንታደጋቸው!
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ

13/10/2021
Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Harar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Abadir Wareda
Harar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Other Community Organizations in Harar (show all)
Burka Dimtu Residents Covid-19 supporters group Burka Dimtu Residents Covid-19 supporters group
Burka Dimtu
Harar

Lammiilee harka qalleeyyiif

Harari Region Prosperity Party's Youth Association Harari Region Prosperity Party's Youth Association
Harar

Civil Society Organization

Laga Hama Community Laga Hama Community
Harar/Addis Ababa
Harar

Every place has its own location, it's on histories and it's own agencies

Bezikallii Bezikallii
Harara
Harar, 45994838

ወሬግ አዜባች ሙጋድ Wareg Youth Association ወሬግ አዜባች ሙጋድ Wareg Youth Association
Jegol
Harar

wareg youth association is a legal entity organized and operated for collective , public or social b

Wadaaja Biyyoo Adaree Wadaaja Biyyoo Adaree
Dekker
Harar

Afaan Wadaajaatiin Wal Bohaarsaa Waliis Barsiisuuf Mirqaanna.

Abadir waldach Abadir waldach
Harar
Harar

Harar Senior Secondary School Rover Scout Harar Senior Secondary School Rover Scout
[email protected]
Harar

Knowing what scout means and giving detail about scout movement

Ethical Studies at Haramaya University Ethical Studies at Haramaya University
Eastern Harerge
Harar, 2080

Only my God is Enough 4 me!!!