ሒዳያ

Never give up

03/06/2023

አጃንባ ኑር መስጂድን ዛሬ 26/09/2015 አፍርሰውታል።

03/06/2023

የብልፅግና ሮንግ ተርኖች (wrong turn) ‼
★★★//💢//★★★

ሳብ ሳብ አረጉ በኛ ላይ ሊነዱ
እስኪ እናየዋለን ካስኬደ መንገዱ‼
(ሸኽ አደም ደርቃ)
………………………

ብልፅግና መንግሥት ከሆነ በኋላ በበርካታው ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ልሂቃን ዘንድ በአንድ ወሳኝ ጉዳይ ላይ መግባባት አለ።

የመግባቢያ ነጥቡ የሚከተለው ነው:—

"ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዘመናት ከመጣው መንግሥት ጋር ሁሉ እየተጋጩ፣ እያኮረፉ ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ ከሁለንተናዊ ሱታፌ እየተገለሉ፣ ለስልጣን ለሚቋምጥ ሃይል ሁሉ መጠቀሚያ የሚሆን ትግል እያደረጉ፣ ለስደት፣ ለእስር፣ለእመቃ፣ ለሞት እየተዳረጉ መኖር ትክክል ስለማይሆን ረፍት ያስፈልጋቸዋልና …ከመጣው ሁሉ መንግስት ጋር መጋጨት ብልህነት አይደለምና… በማናቸውም ሁኔታ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ የሚያደርግ እንቅስቃሴ መደረግ የለበትም!

ህዝበ ሙስሊሙን መንግስት ጋር የሚያቃቅሩ፣ የሚያጋጩ፣ የሚያጠራጥሩ፣ የሚያራርቁ እንቅስቃሴዎች በፍፁም መደረግ የለባቸውም!

የፖለቲካ ፍላጎት ኖሮን ስለማያውቅ በመንግስት ፖለቲካ ውስጥ በመግባት ከመንግስት ጋር መጋጨት እና ህዝቡን ድጋሚ ረፍት አጥቶ፣ እየተሰደደ፣ በፍርሃት ድባብ ውስጥ መኖር የለበትምና በተለየ መልኩ ሃይማኖታችንን የሚጋፋ፣ ሰላማዊ ማምለካችንን የሚያቅብ፣ ያለንን የሚያሰጣ፣ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት እስካልፈፀመ ድረስ ሆደ ሰፊ ሆነን የሠላምን መንገድ ሙጥኝ ማለት አለብን፣ እረፍት ማግኘት አለብን።» የሚል የፀና አቋም ነበረን።

በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች ውይይት ተደርጎ በዚህ ስምምነት ላይ መደረሱንም አስታውሳለሁ። ለባለፉት አምስት አመታት በርካታ የሚፈታተኑን ክስተቶች ተፈጥረው በዚሁ መርህ መሰረት፣ በሆደ ሰፊነትና ሠላምን ተቀዳሚ በማድረግ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለመንግስት አንድም ጊዜ እንቅፋት፣ ፈተና፣ ተገዳዳሪ ሳይሆን፣ የረባ ያልረባ ጥያቄና ፍላጎት በማሳደር መንግስትን ማስቸገርን በመፀየፍ የብልፅግና አመራሮች ጭምር "ሙስሊሙ ብቻ ነው" የማይረብሸን እስኪሉ ድረስ እጅግ የሰከነና ሰላም ወዳድ እንቅስቃሴ ተደርጓል‼

መንግስት በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም ህዝቦች፣ በተለያዩ ብሄሮችና በክርስቲያኑ ህዝብ ጋር ለሚፈጥራቸው ግብግቦችና ለሚፈፅማቸው በደሎች የህዝበ ሙስሊሙ ልሂቃን ህዝበ ሙስሊሙ በገለልተኛነት እንዲንቀሳቀስ ሰፊ ጥረትና አመራር እየሰጠ ዘልቋል። ይህ ሁሉ ዙልምን እያዩ እስከማለፍ የደረሰ አቋም ያራመደው "ህዝበ ሙስሊሙ ረፍት ያስፈልገዋል ከመጣው ሁሉ መንግስት ጋር መጋጨት ብልህነት አይደለም!" በሚል መርህ ነበር።
__________________

ግና ሠላምን አጥብቆ መፈለግ፣ ረፍትን መሻት በአንድ ወገን ጥረት ብቻ የሚገኝ አይደለምና፣ የህዝበ ሙስሊሙ ፀብንና ግጭትን መሸሽ ዘላቂ መፍትሄ ሆኖ አልተገኘም። መንግስት የማይደረገውን አድርጎ ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር የማይፋቅ ችግር ውስጥ ራሱ ገብቷል።
_________________

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የትግል ሂደት ላጠና ሰው የብልፅግና "ጠብ ያለሽ በዳቦ" ጉዞ በተለይ የትናንት የግንቦት 25ቱ የአንዋር መስጅድ ጭፍጨፋ በህዝበ ሙስሊሙና በመንግስት መካከል ያለው ጉዳይ ላይቃና መታጠፉንና አዲስ ምእራፍ ከፍቶ ማለፉን መረዳት ቀላል ነው

በ ዐብዱልጀሊል ሸህ አሊ ካሳ

02/06/2023

በአንዋር መስጂድ ውስጥ የነበሩ እህትና ወንድሞች በወንዶች በር በኩል ሁሉም እየወጡ ይገኛል!!

02/06/2023

ዛሬም በሀበሻ ምድር በሙስሊሞች ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው በደልና ጭቆና በአላህ እገዛና በጀግኖች የደም ጠብታ ላይመለስ ይገረሰሳል!!

22/03/2023
08/07/2022

እንዲህ ያማረና የተዋበ በዓል ይሁንልን!!

ኢድ ሙባረክ!!

Photos from ሒዳያ's post 20/06/2022

በወለጋ ምድር መች ይሆን የንፁሀን አማራቾች ደም በግፍ መፍሰስ የሚያቆመው!!

15/06/2022

የሐጅና ዶላር ጉዳይ!

ለዘንድሮ ሐጅ ከኢትዮጵያ ለሚሔዱ ሐጃጆች በጠቅላላው 30 ሚሊየን ዶላር የሚያስፈልግ ቢሆንም እስካሁን ከሚያስፈልገው ማግኘት የተቻለው 5 ሚሊየን ዶላር (16.66 %) ብቻ መሆኑ እየሰማን የምንገኘው አሳዛኝ መረጃ ነው።

የሀጅ ስነ ስርዓት አቅሙ ለቻለ ሙስሊም በግዴታነት የተደነገገ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን አንዳንድ ሙስሊሙን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚጥሩ አካላት ጉዳዩን የሀሰት ወሬ በመፈብረክ ባንኮች ዶላር ማቅረብ ላለመቻላቸው ኡስታዞችንና ተሰሚነት ያላቸውን ዱዓቶች ናቸው በማለት ፍፁም በሆነ ቅጥፈት ከነሱ እሳቤ ጋር ስላልቆሙ ብቻ ለማጠልሸት እየሰሩ ይገኛል።

እውነታው ግን ማንም ባንክ ዶላር ሲያቀርብ በሽያጭ እንጂ በነፃ ባለመሆኑ እነዚህ ባንኮች ዶላሩን ለሐጅ ለሚጓዙ መንገደኞች ከማቅረብ ለነጋዴው ሲያቀርቡ በተሻለ ትርፍ ስለሚሸጡና በሀገራችን ያለው ወቅታዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተጨምሮበት የተፈጠረ የምንዛሪ እጥረት በመሆኑ ባንኮች ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ እንዲሰጡ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ብንከተል።

✓ የሚያስፈልገውን ዶላር በሀገሪቱዋ ውስጥ ላሉ ባንኮች ተከፋፍለው እንዲያቀርቡልን መጠየቅ በአንድና ሁለት ባንኮች አለመገደብ

✓ ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች ጉዳዩን እንደ ኃይማኖታዊ ግዴታነቱ ተረድተው ዶላር እንዲፈቅዱልን እንዲያደርግ መጠየቅ

✓ የዶላር አካውንት ካላቸው ሙስሊም ትላልቅ ነጋዴዎች ላይ ዶላሩን በግዢ አልያም ወደ ፊት ባንኮች በሚመልሱላቸ የብድር ስምምነት መውሰድ

07/06/2022

የፊታችን እሁድ ሰኔ 05/2014 በአዲስ አበባ እስታዲየም በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያው የሆነና ከ40 በላይ በሆኑ ተወዳዳሪዎች ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር የተዘጋጀ ሲሆን እርሶም በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ ከነቤተሰብዎ በመታደም አሻራዎን ያኑሩ።

የፕሮግራሙ ቀን:- እሁድ ሰኔ 05/2014
የፕሮግራሙ ቦታ:- አዲስ አበባ እስታዲየም
ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ሰዓት:- ከጥዋቱ 2፡30
የመግቢያ ዋጋ:- 500 ብር

01/06/2022

#የጎንደር ከተማ ጨለምተኝነት!!

#ገለው የዘረፉትን ለባዛር!!

በጎንደር ሙስሊሞች ላይ በፅንፈኛው ፋኖ በተፈፀመው ጥቃት ጥፋተኞቹ ለሕግ ሳይቀርቡ ከንፁሀን ሙስሊሞች ላይ የተዘረፉ ንብረቶች በባዛር ስም ለገበያ ለማቅረብ የከተማው አስተዳደር የንግድ ትርዒትና ባዛር አዘጋጅቶዋል።

#የጎንደርጭፍጨፋ

23/05/2022

በልጅ አይፈትን !!

በጎንደር ሙስሊሞች በእምነታቸው ምክንያት ተለይተው ሲገደሉ፣ ፆታዊ ጥቃት ሲፈፀምባቸው፣ አካላዊ ጥቃት ሲደርስባቸው፣ ኃብትና ንብረታቸው ሲዘረፉና ሲወድምባቸው፣ መስጂዶች በእሳት ሲጋዩና ጥቃት ሲፈፀምባቸው የድርጊቱ ፈፃሚ የሆኑ ፅንፈኛ ፋኖዎች መሪዎችና ተባባሪዎቻቸው ለህግ ይቅረቡ እያልን ይኸው ያለምንም ፍትህ 27 ቀናት ተቆጥረዋል።

ከተማዋ ሰላም ሳትሆን ዩኒቨርስቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ጠርቶ ልጆቻቸውን ይዘው በሔዱ ወላጆች በኩል ከተማዋ ሰላም ነች በማለት ድርጊቱን ለመሸፋፈን ሲሞክሩ ውሸት ነው ስንል የነበረ ሲሆን ይኸው ሰላም ነች የተባለችው ከተማ ፅንፈኞች ከሀገር መከላከያ ጋር ጦርነት ለመግጠም እየፎከሩና ከተማውን እያስጨነቁ ሲሆን ልጆቹን ለማድረስ ሄዶ ሰላም ነች ያለላት ከተማ ፅንፈኞች ዛሬም ንፁሀንን ሲገድሉ ሲያይ ስለልጆች ምን እያሰበ ይሆን? ሰላም ነች ብሎ የመሰከረባት 👅 ምላሱ ምን እያለችው ይሆን?

#27ፍትህአልባቀናት
#የጎንደርጭፍጨፋ

23/05/2022

ሚያዚያ 18/2014 በጎንደር ንፁሀን ሙስሊሞች ላይ እምነታቸውን መሰረት ተድርጎ በፅንፈኛው ፋኖ ለተከታታይ ቀናት የተፈፀሙት አረመኔያዊና እንስሳዊ ባህሪ የተላበሱ ጥቃቶች መፈፀም የጀመረበት ቀን!!

እንሆ የዚህ ድርጊት ጠንሳሾችና ፈፃሚዎች ዛሬም በከተማዋ ያለምንም የህግ ተጠያቂነት ዛሬም ህዝቡን ለእኩይ ድርጊት በየቤተ ክርስቲያኑ እየቀሰቀሱ ይገኛል።

#27ፍትህአልባቀናት
#የጎንደርጭፍጨፋ

16/05/2022

የፋና ጋዜጠኛ ዲያቆን ዩርዳኖስ ጎንደር ላይ ወጣቶችን በማደራጀት በመቀስቀስ ጎንደር ላይ የሽብር ጥቃት እንዲፈፀም አድርጎ እስካሁን ማንም የጠየቀው የለም

የሀረር ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ሙህዲን የጎንደሩን የሽብር ጥቃት በመቃወሙ ምክኒያት ታስሯል

ይህን ኢ-ፍትሃዊነት መታገል ግዴታችን ነው !

#የጎንደርጭፍጨፋ

15/05/2022

የሐረር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሙሃይዲን የጎንደሩን ጭፍጨፋ በመኃበራዊ ሚዲያ ተቃወምክ በምል ክስ ለ5ቀናት እስር ላይ ይገኛል።

እጃቸው ምን ያክል እንደረዘመ ተመልከቱ ሙስሊም በሚመራው ከተማ ላይ እንኳን ስለጎንደር ጭፍጨፋ እውነት መናገር ያሳስራል።

የሚዋሹት የሚቀጥፉት እየተሞገሱ እውነተኞች ግን ለእስር የሚዳረጉበት ሀገር!!

#የጎንደርጭፍጨፋ


© Musa Nuredin

15/05/2022

በሀሰተኞች አሉባልታ ሳይበገሩ ዛሬም ከእውነት ጎን በመቆም እስላማዊ ወንድማማችነት በተግባር እያሳዩ የሚገኙትን ጀግኖቹ የስልጤ ወጣቶች አሁንም በፅንፈኛው ፋኖ ጎንደር ላይ ለተገደሉ ሙስሊሞች ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛል።

በዞን የምትገኙ ፖለቲከኞች ስልጣናችሁን የሰጣቹህ ህዝቡ መሆኑን ዘንግታቹህ የጨቋኞችን በደል ለመቃወም ስልጣናቹህ ሲያጓጓቹህ ማየት የሚያሳፍር ሲሆን እስልምናችሁን እየተዋቹ ስልጣናቹህን ለማስጠበቅ ድምፃቸውን በሚያሰሙ ወንድሞች ላይ የምታደርጉትን ትንኮሳ ልታቆሙ ይገባል።

#የጎንደርጭፍጨፋ

15/05/2022

ሀገርን ሀገር እሚያስብለው ሰው ነውንጂ……

© Essa Yefetahu Barya እንደፃፈው።

ቤተሰቦቼ ጎንደርን ጥለው አዲስ አበባ ሲከትሙ ምክንያታቸው የሁሉም ባይሆንም የማህበረሰቡ ክፋት አማሯቸው ነበር። አብሮ ለመኗኗር ስለከበዳቸው በአባቴ ሀሳብ አቅራቢነት በእናቴም ተስማሚነት መሀል አራዳ ላይ የነበረውን ምን የመሰለ ቤታቸውን በርካሽ ጥለው፣ ጓዛቸውን ሸክፈውና ልጆቻቸውን ይዘው አዲስ አበባ ላይ በኪራይ ኑሯቸውን ሀ ብለው ጀመሩ። ከዚያ ነው እንግዲህ የአዲስ አበባን ኑሮ ተቃቁመው ለዛሬ የደረስነው። አሁን ላይ እኔ ሀገሩ ደስ ስለሚለኝ ብቻ ለእናቴ እንዴው ጎንደር ሄደን ብንኖር ስላት ያንገሸግሻታል። ግንኮ ቲቪ ላይ የጎንደር ሙዚቃ ወይም ጎንደርን እሚያወሳ ነገር ሲታይ በሀሳብ ምትሰምጠውና በትዝታ ምትነጉደው እሷው ናት። ተወልዳ አድጋበታለቻ፣ ወግ ማእረጓን አይታ ልጆች ወልዳበታለች። ቢሆንም በዚያን ወቅት የገጠሟት ከማህበረሰቡ ጋር የነበራት መጥፎ ትዝታ አንዳንዴ እየሄደች ዘመድ አዝማዶቿን ከመጠየቅ ባለፈ እዚያ ሄዶ መኖሩን አስጠልቷታል። አሁን ላይማ ከጎንደርም አልፎ ዘረኝነቱና እርስ በርስ መጠላላት መመቀኛኘቱ በሀገራችን በመዛመቱ መሄጃ አጥተን እንጂ ኢትዮጵያ ላይ መኖሩም አንገሽግሾናል።

ታድያ ይኸው የቆየ የከረመ ነገር ነበር ከሳምንት በፊት በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የተከሰተው። አሁንም ፍትህ እሚባለው ነገር የውሀ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። ሁሉም ለሀገር አሳቢ በመምሰል ለመሸፋፈን ከመሞከር ውጪ ኸረ የፍትህ ያለህ ሲል አይሰማም። አሁንም ግን አብሮ ለመኗኗር ፍትህና ፍትህ ያስፈልጋልና የዳኛ ያለህ እንላለን።


#የጎንደርጭፍጨፋ

15/05/2022

የጎንደር ይለያል‼
=============
✍ አንዲት እናት ልጇ ለኢፍጣር ወደቤት ይመጣል እያለች ፆሟን ሳታፈጥር ስትጠብቅ አመሸች፤ ድምፁ ጠፍቷል፣ አልደወለም፤ መቅረቱንም አላሳወቃትም፤ ስልኩም አይሰራም፣ወደ ሰፈር ወጥታ ጓደኞቹን ማጠያየቅ ጀመረች ጓደኞቹም ያለበትን አላወቁም፣ ጎረቤትና ቤተዘመድም የት እንዳለ ሊያውቁ አልቻሉም።

ድብዛው የጠፋው ወጣት ወላጅ እናት ልጄን ባገኝ በሚል ተስፋ በጎንደር ከተማ በሚገኙ እስር ቤቶች እየተዘዋወረች ልጇን ፍለጋ ማጠያየቅ ጀመረች፤ በከተማው ባሉ እስር ቤቶች ሁሉ ልጇን ብትፈልግም ልታገኘው አልቻለችም።

ይህች ጭንቀት የወረሳት እናት በየቀኑ በየእስርቤቶች ሳትሰለች ስለልጇ መጥፋት ፖሊሶችን ትጠይቃለች፤ ይህንን ተደጋጋሚ ጭንቀቷን እና ምልልሷን የተመለከተው የፖሊስ አባል ነይ እስኪ በፎቶ ከያዝናቸው ሰዎች ውስጥ ልጅሽ ካለ እንፈልግልሽ ይላትና ፖሊሱ ሞባይሉን አውጥቶ ፎቶግራፎችን ያሳያት ጀመር፤ ከፖሊሱ ስልክ ውስጥ ሰብስቦ ከያዛቸው ፎቶዎች ድብዛው ጠፍቶ የነበረው ወጣት ተገኘ። እናት ደስ አላት። ልጄ ይሄው አገኘሁት ታዲያ የት ነው ያለው? ብላ ፖሊሱን ጠየቀች፤ ፖሊሱም እነኚህ ስልኬ ላይ ስታያቸው የነበሩ ፎቶግራፎች በሙሉ ቤተሰባቸው እና ማንነታቸው ያልተለዩ ሟቾች ናቸው። መዘጋጃ ቀብሯቸዋል። ብሎ ፖሊሱ የልጇን መሞት ባልጠበቀችውና ባላሰበችው ሁኔታ ሞቱን አረዳት።

እናት በድንጋጤ ጩኸት ለቅሶዋን ጀመረች... በዙሪያዋ ያሉ ፖሊሶች ግን ዝም በይ አታልቅሽ ወደቤትሽ ሂጅ ብለው መልስ ሰጧት... አፏን አፍነው ገፏትም... እሷም እያለቀሰች ወደቤቷ ሄደች፤ ፖሊሶችም ድንገት ፎቶውን አውጥቶ ለሟች እናት ያሰየውን የፖሊስ ባልደረባቸውን በጣም በመውቀስ የሟችን እናት ተከትለው ወደቤቷ ሄዱ... ቤቷ እንደደረሱም እንዳታለቅሽ በማለት አስፈራሯት አንገላቷትም፤ የበደል ጥግ ሆነባት... ለለቅሶም አትበቂም አሏትና እንደልጇም ነፍስ ሁሉ ለቅሶዋንም ቀሟት።

ለማልቀስ ከፈለግሽ ሀገር ለቀሽ አልቅሽ በማለት በፖሊሶች ጫና ሀገር ለቃ ብቻዋን ሀዘን ተቀመጠች።






#የጎንደርሙስሊሞችጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 13/05/2022

የጭንቅ ድምፅ ከዛ ሰፈር እየተሰማ ነው!!

እንደው ማነው አብሮት የኖረውን ዕትብቱን በቀበረበት #ጎንደር ላይ አረመኔያዊ ግድያና ጭፍጨፋ ከፈፀመ አካል ጋር ነገ አውሬነቱ ተነስቶ የደም ጥማቱን ምንም ከሚያደርግ ፅንፈኛ ቡድን ጋር አንድ ላይ አምኖ የሚዋጋው ??

ዛሬም የምንለው ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!

#የጎንደርጭፍጨፋ

#17ቀናትያለፍትህ

13/05/2022

#የጎንደርጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 12/05/2022

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ መጀመሩን እየገለፀ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው ባንክ እና ቁጥሮቻቸውን ከታች አስቀምጧል ። ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ኦርጅናሉን ይዞ ይመጣል ።

1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ

2.የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ

3.የታደሰ ፓስፖርት ያለው ፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ሃይሎች ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል ።

4.ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገዝ ሂደቱን የተቀላጠፈ ማድረግ ይቻላል ። ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ደግሞ እየተከታተልን እናሳውቃችኋለን

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት !

ጠቅላላ ክፍያ 183,500.00

10/05/2022

በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ጥቃት እጅግ በጣም አረመኔያዊነትና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መንግስታዊ መዋቅርን ተመስርቶና ማንነትን መሰረት አድርጎ የተፈፀመ ነው።

#የጎንደርጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 10/05/2022

አይ የሰሜን ፖለቲካ! ኧረ ቅጥፈት በቃን! አንገሸገሸን!

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ

@ በከፍተኛ ሁኔታ ተደብድቦ ጳውሎስ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዷል - ምንም አይነት ጥቃት አልደረሰብኝም

@ ምኒልክ ሆስፒታል አከባቢ እንደነበረ በስልክ ነግሮኛል - ጦርሀይሎች አከባቢ ነበር የነበርኩት

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ለ 8 ቀናት ያህል ያለበት ባለመታወቁ መንግስት አግቶት ነው በማለት እንደውም ጳውሎስ ሆስፒታል በከፍተኛ ድብደባ ተጎድቶ ለሕክምና እንደመጣ አንድ ነርስ ነግራናለች ብለው የሰሜን ፖለቲከኞች ሲቀጥፉ ከርመው ጋዜጠኛው ወደ ቤቱ ሲመጣ በታገተበት ወቅት ምንም አይነት ጥቃት እንዳልተፈፀመበት የገለፀ ሲሆን ዛሬ ደሞ የባልደራሱ ስንታየሁ ቸኮል ከተፈታ በኃላ በስልክ አግኝቼው ምኒልክ ሆስፒታል አከባቢ ታስሮ እንደነበረ አሳሪዎቹ በኦሮምኛ ሲያወሩ ሰምቶ እንደነገረው ገልፆ የነበረ ሲሆን ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ግን ለቢቢሲ በሰጠው መረጃ ጦርኃይሎች አከባቢ ታስሮ እንደነበረ ገልፀዋል ።

Photos from ሒዳያ's post 10/05/2022

ሌላ ሞት በጎንደር
——-////————-

እውነትን መደበቅ ችግሩን ከመሰረቱ አይፈታውም።
የግለሰቦችና የቡድኖች ግጭት አይደለም፤ ጥቃቱ በአንድ አንገቱን ደፍቶ በሚኖር ህዝብ ላይ የተፈፀም ወንጀል ነው።

የተቃጠሉት መስጅዶች ናቸው፤ የሞቱት ሙስሊሞች ናቸው፤ የተዘረፈውና የተቃጠለው የሙስሊሙ ንብረት ነው።

ይህንን እውነት አስምሮ ፍትህን ማስፈንና የተጎዱትን ወገኖች ልብ ማሻር ይገባል እንጅ በአስሮች በግፍ የተገደሉበትንና በጠራራ ፀሃይ የተሰራን ወንጀል ተራ ግጭት አድርጎ መሳል ፍፁም ተገቢ አይደለም።

ይህ አጥፊውን የሚደብቅና ተጎጅውን የሚከስ ትርክር መስተካከል አለበት።

#የጎንደርጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 10/05/2022

ከመጅሊሱ ተወካይ በፊት

ጥቃቱ በከተማው አስተዳደሩ ኃላፊ ተደግፎ እንደተፈፀመ እያወቅን ይህን ጥቃት እራሱ አስፈፅሞ እያስጎበኘ ትክክለኛ መረጃ ሊገኝ አይችልምና? የዚህ ጥቃት ዋነኛ ተጠያቂዎች የሆኑት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቅ ።

#የጎንደርጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 10/05/2022

ጥቃቱን እያዩና እየሰሙ የካዱም የፈፀሙም ለኛ አንድ ናቸው!!

ከ 50 በላይ ሙስሊም ተገሎ!!

ከ 113 በላይ ሙስሊሞች በደረሰባቸው አካላዊ ጥቃት ተጎድተው!!

ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ እህቶች ፆታዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸው!!

ከ 10 በላይ መስጂዶች ጥቃት ደርሶባቸው!!

የበርካታ ሙስሊሞች ኃብትና ንብረት ተዘርፎና ወድሞ !!

ይህ ጥቃት በሙስሊሙ ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥቃት ካልተባለ ምን ይባላል??

#የጎንደርጭፍጨፋ

Photos from ሒዳያ's post 09/05/2022

ጭካኔና አረመኔያዊነት በታሪኳ ላይፋቅ በደም ብዕር ተፅፏል!!

ፅንፈኛው ፋኖ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት መከላከያ ትግራይን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ተወላጆች ላይ የግድያ፣ የአካል ጉዳት፣የፆታዊ ጥቃትና አረመኔያዊ ወንጀሎችና በቃላት ለመግለጽ የሚከብዱ በደሎችን ከፈፀመ በኋላ የለመደው የሰውን ደም የመጠጣት ሱስ በጎንደር ወልደው ከብረው ይኖሩ በነበሩ ሙስሊሞችም ላይም ያለምንም ርህራሄ ግድያ፣አካል ጉዳት፣ፆታዊ ጥቃት፣የእምነት ተቋማትን ማውደም፣ኃብትና ንብረት ዘረፋ የፈፀመባቸው ሲሆን ይህ ቡድን ከተማዋ የጭካኔና አረመኔያዊነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑ በገሀድ የተገለፀ እውነታ ነው።

የከተማዋ መገለጫ ይህ ጭካኔና አረመኔያዊነት ሆኖ ሳለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ጠርቶ ልጆቻቸውን ይዘው በሔዱ ወላጆች በኩል ከተማዋ ሰላም ነች በማለት የከተማዋን መገለጫ የሆነውን ጭካኔና አረመኔያዊነት ለመሸፋፈን ቢሞክርም እውነታው ግን ከተማዋ ወንጀለኞችን በህግ ከመጠየቅ ይልቅ ለወንጀለኞች ከለላ በመስጠት የንፁሀንን ደም በግፍ የሚፈስባት ምድር መሆኑዋ እያየነው የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ይህ ላይፋቅ በደም ብዕር የተፃፈው ጭካኔና አረመኔያዊነትዋ ሁሌም መገለጫዎችዋ ሆነው ይኖራሉ።

#የጎንደርጭፍጨፋ

08/05/2022

ተወልደው ባደጉበት ለወግ ማዕረግ በበቁበት ከትውልድ ትውልድ አሻራቸውን በጣሉበት የማንነታቸው እትብት በተቀበረበት እጅግ በጣም ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ የአካል ጉዳት፣ የእምነት ተቋሞቻቸውና ጥረው ግረው ያፈሩዋቸው ሀብቶች ከሚያዚያ 18/2014 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በመንግስታዊ ዕዝ ድጋፍ የታገዘ ሽብርና ጥቃት የተፈፀመባቸው ሙስሊሞች የጎንደር ጭካኔ በትር ሰለባዎች ድርጊቱን የፈፀሙ ፅንፈኛው ፋኖ የጎንደርን ከተማ አረመኔያዊነት ለዘመናት የሚያስወሱ የከተማዋ መገለጫ ሆነው ይኖራሉ።

#የጎንደርጭፍጨፋ

07/05/2022

ለጎንደር ዩኒቨርስቲ!!

በተማሪ ሕይወት ፖለቲካን መነገድ ይቁም!!

አብሮት የኖረውን ማህበረሰብ እምነቱ ሙስሊም በመሆኑ ብቻ ለይቶ በሚገደልበት፣ ንብረቱ በሚወድምበት፣ፆታዊ ጥቃት በሚፈፀምበት፣ መንግስት በማይቆጣጠረው፣ ፅንፈኛ እንደፈለገ በሚፈነጭበት ጎንደር ከተማ የሚገኘው ጎንደር ዩኒቨርስቲ አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ግንቦት 1 እና 2/2014 ወደ ግቢው እንዲገቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን ከተማው ላይ ያለው ፅንፈኛ ቡድን ዛሬም እንዳሻው እየፈነጨ፣ ወንጀለኞች ለህግ ሳይቀርቡ፣ ጭቆናውና ጥቃቱ በቀጠለበት ሁኔታ ተማሪዎችን ወደ ግቢ መጥራቱ ፍፁም ተገቢነት የለውም።

በከተማዋ የሚገኘው ፅንፈኛ ቡድን አብረውት የተኗኗሩትን ያለርህራሄ ገድሎ በአደባባይ በነፃነት በሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ለትምህርት ብለው ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ ተማሪዎችን ቢገድል፣ ፆታዊ ጥቃት ቢፈፅም፣ ቢዘርፍ ተው የሚል ከልካይና የህግ አካል በሌለበት ሁኔታ ለዓመታት ህይወታቸውን ለመለወጥ የለፉ ተማሪዎች ከህልማቸው በዚህ ፅንፈኛ ቡድን ተደናቅፈው እንዳይቀሩ ከተማዋ ወንጀለኞችን ለህግ አቅርባ ጥፋተኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በማድረግና ነገም እንዲህ አይነት ጥቃት እንዳይፈፀም ተገቢው ስራ ተሰርቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሊጠሩ ይገባል እንጂ የውቅያኖስ ውሀ እንኳን የማያጥበውን የከተማዋን ወንጀል ለመደበቅ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ሽፋን ተማሪን ጠርቶ መልካም አቀባበል አድርጌያለው በማለት በተማሪ ህይወት ላይ መቀለድ አይገባም።

#የጎንደርጭፍጨፋ

07/05/2022

ቲውተር ላይ ማታ እንገናኝ
——-////———-////————

ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ2:00-4:00 በሚኖረን የተቀናጀ የትዊተር ዘመቻ ሁላችንም እንሳተፍ::

በጎንደር ወንድሞቻችን ላይ የተቃጣውን የሽብር ተግባር ወደ ርትዕ (ፍትህ) እንስኪመጣ ድረስ መጠየቅ መወትወት ፍትህ ወዴት ነሽ ማለት የሁላችንም ድርሻና ሀላፊነት ነው።

ለዘመቻው የምንጠቀማቸው ሁለት ሐሽታጎች የሚከተሉት ይሆናሉ… ⇩


ሐሽታጎቹን ስፔሊንግ እንዳናሳስት እንጠንቀቅ! ከሐሽታጎቹ በተጨማሪ የተዘጋጁና ክሊክ ተደርገው ትዊት መደረግ የሚችሉ ትዊቶች ቀድመው ስለተዘጋጁ ሁላችንም እንሳተፍ!
የቲውተር አካውንት የሌላችሁ አሁኑኑ ክፈቱ! ፍትህና ሰብዓዊነትን ያላችሁ ሁሉ አብራችሁን ተሠለፉ! መረጃው ላልደረሳቸው ሁሉ አዳርሱ! ቀጠሯችን ዛሬ ማታ ነው!

ቲውተር አፕ ለማውረድ
———————————-
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.twitter.android

07/05/2022

🔴 ከ53 በላይ ንፁሐን ሙስሊሞች በተወለዱባት ቀዬ በፆመኛ አንጀታቸው እንደ ቅጠል ረግፈዋል፤ (አላህ ይዘንላቸውና)

🔴 ከ10 በላይ የተከበሩ የአላህ ቤቶች (መሳጂድ) ወድመዋል፤

🔴 እልፍ ቅዱስ ቁርኣኖች ተቀዳደዋል፤

🔴 ሙስሊም ሴቶች ከነ ፆመኝነታቸው ክብረ—ንጽሕናቸው ተደፍሯል፤

🔴 ለቁጥር የሚታክቱ መኖሪያ ቤቶች ፈራርሰዋል፤

🔴 ለጎንደርን ኢኮኖሚያዊ አቅም ዋርካ የሆኑ የንግድ ማዕከላት ተዘርፈው ወድመዋል፤

🔴 ከ 500 በላይ ሙስሊሞች ያለ ወንጀላቸው ብቻ ሳይሆን ተበዳይ ሆነው ሳለ ለእስር ተዳርገዋል፤

🔴 ሙስሊም ጎንደሬዎች መፈጠራቸውን እስኪጠሉ በማያገግም የሞራል ስብራት ተጎድተዋል።

… ይሄ ሁሉ አስነዋሪና የክ/ዘመኑ ጭካኔ ተፈፅሞ ሲያበቃ መንግስት ጉዳዩን በፕሮፖጋንዳ ለመሸፋፈን በእጥፍ እየተጋ ይገኛል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Harer?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

Ma Sha Allah Addis Ababa Around kara repi

Website

Address

Harer
Other News & Media Websites in Harer (show all)
Hundane Press Hundane Press
Harer

News

Sabati Xeedho Media Sabati Xeedho Media
Harer

Sabati xeedho media waa warbaahin madaxbanaan oo dhex'dhexaad ah waxayna sootabisaa wararka geeska afrika iyo caalamka intiisakalaba, Warbaahinta sabati xeedho media ugu imow wara...