Beteseb

Beteseb

Welcome to DANVAS!

18/12/2023

https://www.youtube.com/playlist?list=PLIxz6IyYKOUwnCvglKr1zKJYKk4Yzi5jg

የህመም ስሜቶችዎን ይረዱ! በዚህ አጫጭር ቪዲዮ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመንን የህመም ስሜቶች ምንነት እንዲሁም በምን ምክኒያት እንደሚመጡ አጠር ያለ ገለጻ እንዳደርጋለን። በሰፊው የሚፈልጉት ርዕስ ካለ ይጻፉልን!

አረንጓዴ ሻይ 17/12/2023

https://youtu.be/c_r7reGWhmg

አረንጓዴ ሻይ ስለ የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጠቀሜታ ና የሰውነት የመቆጣትን አቅም የመቀነስ አስገራሚ አቅም እንመለከታለን፡፡ አረንጓዴ ሻይ ብዙ ሀገራት ለአመታት በጥቅም ላይ በመዋል የሚታወቅ ነው፡፡ ....

አረንጓዴ ሻይ 17/12/2023

አረንጓዴ ሻይ ስለ የአረንጓዴ ሻይና የሰውነት የመቆጣትን አቅም የመቀነስ አስገራሚ አቅም እንመለከታለን፡፡ አረንጓዴ ሻይ ብዙ ሀገራት ለአመታት በጥቅም ላይ በመዋል የሚታወቅ ነው፡፡አረንጓዴ ሻይን ...

ስለአንጀት ቁስለት ማገርሸት ማወቅ ያለቦት 4 ነጥቦች 14/12/2023

https://youtu.be/ewomJaAROsI

ስለአንጀት ቁስለት ማገርሸት ማወቅ ያለቦት 4 ነጥቦች 4 key facts you need to know about inflammation in the body & Inflammatory Bowel Disease flareupCheck out our other videos on the topichttps://youtu.be/jbtvd...

ስለ ስኳር ይህንን ያውቃሉ? ክፍል 1 09/12/2023

https://youtu.be/rRrbQj7VhbM?si=hXVzpQiSuX5yJZVU

ስለ ስኳር ይህንን ያውቃሉ? ክፍል 1 በዚህ የYouTube ቪድዮ ውስጥ ስኳር የመጠጣት ስውር አደጋዎችን እና ለምን አጠቃቀማችንን መቀነስ ወሳኝ እንደሆነ እንቃኛለን። የስኳር መጠን ከመጠን በላይ መጠጣት በጤንነታችንና በደኅንነ.....

15/12/2022

ስለ ሲቲ-ስካን ምን ማወቅ ይፈልጋሉ?
ክፍል 1

~ ሲቲ-ስካን (CT-Scan/Computer Tomography Scan/ ) የX-Ray ቴክኖሎጂን ከኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር የሚሰራ የህክምና መሳሪያ ነው።

~ ይህ መሳሪያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በሰውነታችን የሚገኙ እንደ አጥንት፣ ጡንቻ፣ ስብ፣ እንዲሁም የውስጥ አባላካሎችን በላቀ ጥራት የሚያሳይ የህክምና መሳሪያ ነው።

~ ሲቲ-ስካን የX-ray ጨረሮችን በሰውነታችን ዙሪያ በመልቀቅ አንዱን የሰውነት ክፍል በተለያዩ አቅጣጫዎች በማንሳት መረጃውን ወደ ኮምፒውተር ይልካል፤ በመቀጠልም የተላኩትን ምስሎች በተሰናዳ መልኩ በመከሰት ያሳየናል።

~ ሲቲ-ስካን በሰውነታችን ውስጥ የሚከሰቱ እብጠቶችን ለማየት፣ በሰውነት የውስጥ ክፍል ደም መፍሰስ ሲከሰት ለመለየት፣ በተጨማሪም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ናሙና ለመውሰድ ይጠቅማል።

~ በህክምና ባለሞያ ሲቲ-ስካን በሚታዘዝበት ጊዜ በደም ሥር ወይም በአፍ የሚወሰድ ለንፅፅር የሚጠቅም ማቅለሚያ ጋር አብሮ ሊታዘዝ ይችላል።

ለሲቲ-ስካን ምርመራ እንዴት መዘጋጀት እንችላለን?

~ በመጀመሪያ መውሰድ ያሉብን ቅድመ ጥንቃቄዎች

• እርግዝና መኖሩን ካወቁ ወይም እርግጠኛ ካልሆኑ ለሀኪምዎ ማሰወቅ እና መማከር ያስፈልጋል።

• የታዘዘልን የሲቲ-ስካን ምርመራ በደም ሥር ወይም በአፍ የሚወሰድ ለንፅፅር የሚጠቅም ማቅለሚያ ጋር አብሮ የታዘዘ ከሆነ የኩላሊት ምርመራ እንዲሁም ለባለሞያው የኩላሊት ችግር ካለብን ማሳወቅ ይኖርብናል። በተጨማሪም ከምርመራው ከ3ሰዓታት በፊት ምግብ መውሰድ ማቆም ይኖርብናል።

• የስኳር ህመም ተጠቂዎች ከምርመራው ሶስት ሰዓታት ቀደም ብለው ምግብ እንዲወስዱ ይመከራሉ። እንደሚወስዱትም መድሐኒት አይነት ከምርመራው በኁዋላ ለ48ሰዓታት መድሐኒቱን እንዲያቆሙ ሊታዘዙ ይችላሉ።

Photos from Beteseb's post 06/12/2022

Big shout out to our newest top fan!

Dawet Bayisa

23/11/2022

I will be live with Dr. Selamawit Asmelash who is the owner, medical Director and Pediatrician of Bloom Children’s Clinic.

Forward me your questions you want answered as we discuss all things Pediatrics this evening live only on Tikvah Magazine!

21/11/2022

ከቲክቫህ ማጋዚን ጋር በመተባበር የምናቀርበው ፖድካስት ላይ ቀጣይ እንግዳችንን እናስተዋውቆ! ያሎትን ጥያቄ ያስተላልፉን ቀጥታ ስርጭት ላይ እንጠይቅሎታለን!

health_info_amharic on TikTok 03/10/2022

https://vm.tiktok.com/ZMFFRGscB/

health_info_amharic on TikTok What is Gynaecology? ስለህክምና ቋንቋዎች ይማሩ!

Timeline photos 20/04/2022

https://forms.gle/n9oeZi7A7v4M1J6c8

ስለ አንጀት ቁስለት በሽታ ያሎትን ተሞክሮ ያካፍሉን!

https://forms.gle/W4dPohbJjmFjBUHu7

Timeline photos 13/02/2022

ስለ የአእምሮ ጤና እና የአንጀት ቁስለት
Let's talk about Mental Health & IBD

Timeline photos 30/12/2021
የአንጀት ቁስለት ታማሚዎችን የሚያማክረው የከሮነስ ኤንድ ኮላይተስ ኢትዮጵያ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ -ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ በፋና ቀለማት 23/12/2021

የአንጀት ቁስለት ታማሚዎችን የሚያማክረው የከሮነስ ኤንድ ኮላይተስ ኢትዮጵያ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ -ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ በፋና ቀለማት የከሮነስ ኤንድ ኮላይተስ ኢትዮጵያ ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ -ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ በፋና ቀለማት

03/05/2020

ብጉር የሚመጣው የቆዳ ቀዳዶች በተለያየ ቆሻሻ ሲዘጋ እንዲሁም ባክቴሪያ ኢንፌክሽን ሲያጋጥም ነው።
ከእድሜ ጋር ተያይዞ እንዲሁም ጭንቀት የመሳሰሉት ለብጉር መነሻ ናቸው ተብለው ይጠቀሳሉ።
ብጉር እንዴት ቤት ውስጥ ማከም እንችላለን? እነዚህ መፍትሄዎች ከሰው ሰው ይለያያሉ እንዲሁም ለአንዱ የሰራው ለልላው ላይሰራ ይችላል። ስለዚህ ለእርሶ የሚሰራውን ሞክረው ይከተሉ። እነዚህ መፍትሄዎች የሚሰሩት በየቀኑ ሲከተሉት ነው።
ብጉርን ለመከላከል በየቀኑ ማድረግ ያለብን ጤናማ ባህሎች

ውሀ በሚገባ መጠጣት

ፊትን እንዲሁም ብጉሮችን አለመነካካት

የፊት ሳሙናን በሚገባ መምረጥ። ሽቶ የቀላቀሉ፣ እንዲሁም ጠንካራ ሳሙናዎች አይመከሩም

ጭንቀት መቀነስ

የቡና እንዲሁም አልኮል አዘል መጠጦች መቀነስ

አመጋገብ ማስተካከል፣ የተመጣጠነ አመጋገብ መከተል

ብጉርን እንዴት ቤት ማከም እንችላለን?

ሆሆባ ዘይት (jojoba oil) በሚባል የሚጠራው የተፈጥሮ ዘይት ከ ሆሆባ አትክልት የሚገኝ ሲሆን ለወዛም እና ብጉር ለሚበዛው ፊት ጠቀሜታ እንዳለው ሳይንስ እንዲሁም ብዙዎች ይመሰክሩለታል። ይህንን ዘይት 100% ንፁህ የሆሆባ ዘይት ጠዋት እና ማታ ከታጠቡ በሃላ ሁለት ጠብታ መቀባት ይችላሉ። የተለያዩ የተፈጥሮ የፊት ማስክ ከሰሩም ይህንን አንድ ወይም ሁለት ጠብታ ማድረግ ቆዳዎት ላይ የሚታይ ለውጥ ያመጣል።

አረንጓዴ ሻይ በውስጡ የያዘው አንቲኦክሲዳንት ብጉርን ለመከላከል እንዲሁም ለማከም ይረዳል። የቀዘቀዘ የአረንጓዴ ሻይ ፊትን ለመለክለቅ መጠቀም እንዲሁም የተጠቀምንበትን የአረንጓዴ ሻይ ቅጠል መያዣ ብጉሮቹ ላይ በማድረግ ጥቂት ጊዜ ማቆየት የተቆዳ ቆዳን ለማስተካከል ይረዳል።

ማር ተወርቶ የማያልቅ የተፈትሮ ስጦታ ነው። ብጉር ለማከም እንዴት መጠቀም እንዳለብን እናያለን። ማርን በቀጥታ ብጉሮች ላይ መቀባት እንችላለን። እንዲሁም አንድ ማንኪያ ማር እና ሁለት ማንኪያ ኦትስ ካልተገኘ የቀረፋ ዱቄት በመቀላቅል ማስክ ሰርቶ ሙሉ ፊትን ቀብቶ ለ ሰላሳ ደቂቃ መቆየት ከዛም ለብ ባለ ውሀ መታጠብ ለብጉር ይረዳል።

እሬት ወይም አሎቬራ የተሰኘው ተክል ለብዙ አመታት ፊትን ለማስዋብ እንጠቀምበታለን። ለብጉር እንደሚረዳ ያውቁ ኖሯል? ለተቆጣ ቆዳ የሚጠቅም ከመሆኑም በተጨማሪ ቆዳ ጠባሳ እንዳይዝ ይረዳል። ቤቶ ይህ ተክል ካለ አንድ ማንኪያ በመውሰድ ቆዳዎ ላይ በቀን ሁለቴ ወይም ማታ ተቀብተው እስከ ጠዋት በማቆየት የሳሙናን ቦታ መተካት ይችላል። በቤቶ ከሌለ 100% ንፁህ እሬት ቅባት ካገኙ መጠቀም ይችላሉ።

ሎሚ እንዲሁም ሌሎች ሲትረስ አዘል ፍራፍሬዎች በውስጣቸው በያዙት ንጥረነገሮች ምክኒያት እንደ ስክራብ ያረጀ ቆዳ ክፍልን በማንሳት፣ ቆዳን ማቅላት እንዲሁም ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይረዳል። ይህንን ንፁህ ፊት ላይ የተወሰነ የሎሚ ጭማቂ በጥጥ ላይ አድርጎ ለሰላሳ ደቂቃ በማቆየት ከዛም ቀዝቀዝ ባለ ውሀ መታጠብ ለብጉር ፍቱን መፍትሄ ይሰጣል።

Apple cider vinegar ብጉሮችን ለማትፋት የሚጠቅም ሲሆን ባዶውን ቆዳ ላይ መጠቀም አይመከርም። እኩል ለእኩል ለምሳሌ አንድ ማንኪያ አፕል ሳይደር ቬኔጋር እና አንድ ማንኪያ ንፁህ ውሀ በደንብ ከቀላቀሉ በሃላ በጥጥ በመጠቀም ንፁህ ቆዳ ላይ በስሱ መቀባት ለብጉር የሚመከር የቤት ህክምና ነው።

ተጨማሪ ጥያቄ ካሎት በፅሁፍ መልዕክት ያድርሱን።
ጤናማ ማህበረሰብ እንፍጠር ለሌሎች እናጋራ!

03/05/2020

የሆድ ድርቀት ብዙዎች የሚያጋጥማቸው የጤና ችግር ሲሆን በብዛት የሚከሰተው በአመጋገባችን፣ የአኗኗር ዘርቤ፣ የምንወስደው መድሀኒት እንዲሁም የአንጀት እና የተለያዩ በሽታዎች እንደ ምክኒያት ይጠቀሳሉ።
የሆድ ድርቀት የምንለው በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሶስት በታች ሰገራ ካላሳለፉ ነው። ይህንን እንዴት በቤታችን መከላከል እና ማከም እንችላለን?
ውሀ: ውሀ መጠጣት ለሆድ ድርቀት የሚመከር ሲሆን ከውሀ በላይ አምቦውሀ የበለጠ ሰገራ እንዲያልፍ ይረዳል። ለስላሳ መጠጦች ጤናማ አይደሉም በዛ ላይ ብዙም የሆድ ድርቀትን አያሻሽሉም ስለዚህ ውሀ እና አምቦውሀ ይጠቀሙ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ: በቀላሉ እግር መንገድ ማድረግ እንዲሁም ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የሆድ ድርቀትን መከላከል ይቻላል።
ቡና: ቡና የሆድ እንቅስቃሴ ይጨምራል ስለዚህ ከምግብ ጋር ቡናን መጠጣት ለሆድ ድርቀት መፍትሄ ይሆናል።
ቴምር: ቴምር በተፈጥሮ ሶርቢቶል የሚባል ንጥረነገር የያዘ ሲሆን ይህ በተፈጥሮ መንገድ ሆድ ድርቀትን ማከሚያ የሚመከር ነው። በቀን ሰባት ቴምር በቀን ሁለቴ መውሰድ ይመከራል።
ተልባ: ተልባ ሁሉም የሚያውቀው የሆድ ድርቀት መፍትሄ ነው። እንደሚፈልጉት መጠን እና አሰራር መስራት ይችላሉ። ሆድ ማለስለስ እንዲሁም ሰገራ በቀላሉ እንዲያልፍ ይረዳል።
ፋይበር: የአመጋገብ ዘይቤያችንን መቀየር ለሆድ ድርቀት በጣም ጠቃሚ ነው። ፋይበር ሰገራን ለአንጀታችን ገፍቶ ለማስወጣት አመቺ ስለሚያደርግ ፋይበር ያለበትን ምግብ ማዘውተር ጠቀሜታ አለው። ለምሳሌ: ጥራጥሬ፣ ኦትስ\አጃ፣ አትክልት፣ ፍሬሽ እና የደረቁ ፍራፍሬዎች ፋይበር በውስጣቸው የያዙ ምግቦች ናቸው ስለዚህ እነዚህን ማዘውተር ለሆድ ድርቀት ይመከራል።

ጤናማ ማህበረሰብ እንፍጠር!
ጤናሊንክ

02/05/2020

የአንጀት ቁስለት ምንድን ነው?

የአንጀት ቁስለት በኢግሊዘኛው Inflammatory Bowel Disease ተብሎ የሚጠራው ህመም ሲሆን ክሮንስ (Crohn's Disease) እና አልሰሬቲቭ ኮላይተስ (Ulcerative Colitis) ተብለው የሚጠሩትን በሽታዎች በስሩ ያካተተ ነው። የአንጀት ቁስለት ማንን ያጠቃል? እድሜ: ይህ በሽታ በብዛት የሚታየው ወጣቶች ላይ ሲሆን አንዳንዴ ተለቅ ያሉ ሰዎች ላይ ይታያል። አብዛኛው የሚያጠቃው እድሜ ክልል ከ20-40 አመት ላይ ያሉትን ነው። ፆታ: የአንጀት ቁስለት በሽታ ፆታ አይለይም።

የአንጀት ቁስለት የትኛውን የአንጀት ክፍል ያጠቃል?

ይህ በሽታ የሚያጠቃው ቦታ ከበሽታው ስሜቶች ጋር ይያያዛል። አብዛኛው ምልክቶች በሁለቱም በሽታዎች የሚታዩ ሲሆን አንዳንድ ስሜቶች በየህመሙ እና የተጠቃው የአንጀት ክፍል ይወሰናል።
የክሮንስ በሽታ ከአፍ ጀምሮ እስከ ፊንጢጣ ሊያጠቃ ይችላል። ሆኖም በብዛት የትንሹ አንጀት ማለቂያ እና ትልቁ እና ትንሹ አንጀት መገናኛ ቦታ ያጠቃል።
አልሰሬቲቭ ኮላይተስ በብዛት ትልቁ አንጀትን ያጠቃል። በሚቀጥለው የእያንዳንዱን በሽታ ስሜቶች እናያለን።

ምልክቶች:

ከባድ የሆድ ቁርጠት

ከሰገራ ጋር የሚወጣ ደም እንዲሁም ንፍጥ

ተደጋጋሚ ተቅማጥ\ ቀጭን ሰገራ

ሆድ መነፋት እንዲሁም ከልክ ያለፈ የአንጀት ጋዝ

ድካም

የሰውነት ክብደት መቀነስ

ፊንጢጣ አካባቢ ቁስለት እንዲሁም መግል መያዝ የመሳሰሉት ይገኙበታል

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ!
ጤናማ ማህበረሰብ እንፍጠር!

20/04/2020

ውድ የጤና ሊንክ ቤተሰቦች…. እስካሁን ድረስ ያነሳናቸው ጤና ተኮር መረጃዎች እንደጠቀሟችሁ እርግጠኞች ነን፡፡ አሁን ደግሞ እናንተ የምትፈልጉት የጤና እክል፣ የምግብ አይነት እና ሌሎችንም የጤና መረጃዎች በእናንተ ጥያቄ መሰረት ለማቅረብ ተዘጋጅተናል፡፡
ስለዚህም ጥያቄዎቻችሁን በቴሌግራም እና በፌስቡክ https://www.facebook.com/tenalink/ ይላኩልን፡፡

የመጀመሪያዎቹን 10 ጥያቄዎች እናስቀድማለን፤
ጤናማ ማህበረሰብ እንፍጠር!!

Telegram: Contact @tenalinket 13/04/2020

ውድ የጤና ሊንክ ቤተሰቦች በአሁኑ ጊዜ ወደ ሆስፒታል መሄድ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።
በሀኪም ታይተው የቤት ክትትል ያስፈልጎታል ተብለው ከሆነ እኛ ጋር በመፃፍ ከባለሙያ ጋር እናገናኞታለን። ለምሳሌ ቁስል ማጠብ እንዲሁም ለአዛውንት፣ የተለያዩ እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉ በስትሮክ የተጠቁ ሰዎች እና ሌሎች የመሳሰሉትን እንክብካቤ የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ በፅሁፍ መልዕክት t.me/tenalinket ማስተላለፍ ይችላሉ።

ለሌሎችም ያካፍሉ።

Telegram: Contact @tenalinket

10/04/2020

ሃባብ

1) ለሰውነት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖችን፣ ማዕድንና ሳይበዛ ለሰውነት በሚያስፈልግ መጠን ካሎሪንም የያዘ ተወዳጅ ፍራፍሬ ነው።
2) ውፍረት ለመቀነስ ይረዳል፡፡
3) ከስኳር በሽታ
4) ከልብ ህመም ችግር
5) ለሰውነት ተጨማሪ ሃይል መስጠት
6) ለጤናማ የጸጉር እድገት
7) ለጤናማ የምግብ መፈጨት ስርአት እና የሰውነት ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል፡፡
8) ደም ግፊት፣
9) ሃባብን መመገብ ሌላው ጠቀሜታው ከጉልበት በታች የሚከሰትን ከፍተኛ የሆነ የደም ዝውውር ወይም ግፊትን ማስወገድ መቻሉ ነው።
ለካንሰር፣ ሰውነት ላይ የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ በሚረዱ የቪታሚን ሲ አይነቶች የበለጸገው ሃባብ ሌላኛው ጠቀሜታ የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉ ነው።

t.me/tenalinket

03/04/2020

❗️

ውድ የጤና ሊንክ ቤተሰቦች .....ነገ መጋቢት 26 , 2012 ዓ.ም ስለ #ኮሮና ቫይረስ እና ተያያዥ ጉዳዮች #በአዋሽ FM 90.7 በ መልካም 74 የሬድዮ ፕሮግራም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት የምንወያይ ሲሆን ከታች በተጠቀሱት ስልኮች በፕሮግራሙ ሰዓት በመደወል አስተያየት እና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።

ይህ በባለፈው የተጀመረውን ውይይት ክፍል ሁለት ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ከህፃናት እና ነፍሰጡሮች ጋር አያይዘን እንወያያለን። በተጨማሪም ስለ ማስክ ጥቅም እና ጉዳት እንዲሁም ስለ ኮሮና ቫይረስ እና የደም አይነት የተጠና ጥናት እናያለን።

ተጨማሪ መወያያ ነጥቦች፣ ሀሳብ ወይም ጥያቄ ካሎት በ ቴሌግራም ገፃችን t.me/tenalink ይፃፉልን። በነገውም ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ከፈለጉ በታችኞቹ ቁጥሮች ከ ጠዋቱ 2-3 ሰዐት ያገኙናል።

☎️ 0115543316
☎️ 0115543319

ይህን የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅተው የሚያቀርቡልን መልካም 74 የሬድዮ ፕሮግራም ከThink አቢሲኒያ እና ጤና ሊንክ ጋር በመተባበር ነው ።

T.me/tenalinket

30/03/2020
28/03/2020

ውድ የጤና ሊንክ ቤተሰቦች
ስለ ኮሮና ቫይረስ እና ተያያዥ ጉዳዮች በአዋሽ FM 90.7 መጋቢት 20 2012 በ መልካም 74 የሬድዮ ፕሮግራም ከ 11 እስከ 12 ሰዐት ከምሽቱ የምንወያይ ሲሆን ከታች በተጠቀሱት ስልኮች አስተያየት እና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።

0115543316
0115543319

እንድንወያይበት የሚፈልጉት ርዕስ ካለ ቀድመው በ t.me/tenalinket በፅሁፍ መልዕክት ያድርሱን።
እናመሰግናለን!

TENA.ET – ከኮሮና ቫይረስ ራስን መመርመሪያ 26/03/2020

https://tena.et በመጠቀም በቀላሉ ራሳችንን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታችንን እንመርምር🏨
አሁኑኑ ሼር በማድረግ ሁሉም እራሱን እንዲመረምር ያርጉ 👪

👉 tena.et

Www.facebook.com/tenalink
T.me/tenalinket

TENA.ET – ከኮሮና ቫይረስ ራስን መመርመሪያ በቀላሉ ራሳችንን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታችንን እንመርምር

26/03/2020

ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ማድረግ ያለብን እና የሌለብን ነገሮች
ሼር TenaLink

Www.facebook.com/tenalink

Videos (show all)

ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ማድረግ ያለብን እና የሌለብን ነገሮች ሼር TenaLinkWww.facebook.com/tenalink

Telephone