Wassie Dessie Kidie

Wassie Dessie Kidie

የራስ የሆኑ እይታዎች ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ተሰናስለው ይቀ

18/10/2021

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1496ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

07/10/2021

መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-

1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

በተጨማሪም፡
- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤
- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

//

Photos from Wassie Dessie Kidie's post 21/09/2021

The donkey told the tiger,
"The grass is blue."

The tiger replied, "No, the grass is green ."

The discussion became heated, and the two decided to submit the issue to arbitration, so they approached the lion.

As they approached the lion on his throne, the donkey started screaming: ′′Your Highness, isn't it true that the grass is blue?"

The lion replied: "If you believe it is true, the grass is blue."

The donkey rushed forward and continued: ′′The tiger disagrees with me, contradicts me and annoys me. Please punish him."

The king then declared: ′′The tiger will be punished with 3 days of silence."

The donkey jumped with joy and went on his way, content and repeating ′′The grass is blue, the grass is blue..."

The tiger asked the lion, "Your Majesty, why have you punished me, after all, the grass is green?"

The lion replied, ′′You've known and seen the grass is green."

The tiger asked, ′′So why do you punish me?"

The lion replied, "That has nothing to do with the question of whether the grass is blue or green. The punishment is because it is degrading for a brave, intelligent creature like you to waste time arguing with an ass, and on top of that, you came and bothered me with that question just to validate something you already knew was true!"

The biggest waste of time is arguing with the fool and fanatic who doesn't care about truth or reality, but only the victory of his beliefs and illusions. Never waste time on discussions that make no sense. There are people who, for all the evidence presented to them, do not have the ability to understand. Others who are blinded by ego, hatred and resentment, and the only thing that they want is to be right even if they aren’t.

When IGNORANCE SCREAMS, intelligence moves on.

20/09/2021

እኛ.....

በእኛነት ውስጥ ስንት ትርፍ አለ ? እኛ ግን ስንት ነው? ብተለው እኛ ባለው የመንጋው መሪ የሚወሰን ነው።
ለነገሩ አዳምም አፕል ከበላ በኋላ "እሷ" ብሎ ጌታውን ለመሸወድ በመሞከሩ ይመስለኛል ከገነት የተባረረው። "እኛ በላን" ቢል ኖሮ ይቅር የሚባል ይመስለኛል።

በዚች ሀገር እኛ ብሎ ያገኘውን ትርፍ እኔ ብሎ ያጣጥመዋል። "በኛ " ስም ይሰርቃል፣ይቾምሳል፣ይከሳል፣ይሸልማል
እኛን እየመሸነ(ሜንሽንእያደረገ)ይቸረችራል። እኛ ውድ ነው ። መንጋው ችስታ ነው። ግን የፈለከውን ያደርግልሃል ። ይገላል፣ያምፃል፣ ሂድ ስትለው ይሄዳል ፣ተጣላም ተውም ስትለው በእርሶ መጀን ይላል ፣ ያደንቃል።

በተለይ እኛ እያልክ ማለቃቀስ ከቻልክ በዚህ ሁሉ በእጅህ ነው
እኛን ጨቁነውን
እኛን ገለውን
እኛን የሉም እያሉን
እኛን ታሪካችንን ደብቀው ...

ብቻ ይሄ ህዝብ በፉክክር የሚኖር ነው
የታሪክ ፉክክር
የባህል ፉክክር
የሐይማኖት ፉክክር
የኢኮኖሚ ፉክክር እንኳን ብዙም አይታወቅም ብቻ በጎረቤቱ ፉክክር ውስጥ ገራሚ አልቃሽ ከሆንክለት ያለውን ሁሉ የሚሰጥህ ይመስለኛል

አፍሪካ ውስጥ እኔ ለማለት እኛ ነው የሚባለው። መንጋ ይከተልሃል። በጣም ትርፍ አለው ። ስለ ጎጆክ እያሰብክ ጎጆክን ለመገንባት አገሬ ትላለክ ጎጆክን መገንበያ ማሞቅያ ገንዘብ ማግኛ ትቀምራለክ ።

"በእኛ" ስንት የደሀ ልጅ ስንት ገበሬ ረገፈ ? የስንቱ ስልጣን እና የስንቱን ኑሮ አደልበው እነሱ የት ናቸው ?.....ስንቱን ?

17/09/2021

The White Post Flood
to
The White House ❗️

18/08/2021
Photos from Tesfahun Alemneh ተስፋሁን አለምነህ's post 12/08/2021
Fasil Demoz - Cha Bel - ፋሲል ደሞዝ - ጫ በል - New Ethiopian Music 2021 (Official Video) 06/08/2021

ጫ በልና ስማኝ ❗️

Fasil Demoz - Cha Bel - ፋሲል ደሞዝ - ጫ በል - New Ethiopian Music 2021 (Official Video) Fasil Demoz - Cha Bel - ፋሲል ደሞዝ - ጫ በል - New Ethiopian Music 2021 (Official Video)Ethiopian Music: New Music Video from Fasil Demoz...Cha Bel! Don't miss it!...

03/08/2021

💎ሰው የሚዘራውን ያጭዳልና መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል። ግዴለም ሁሌም ፍቅር ዝራ፣ ለሰዎች መልካም ልብ ይኑርህ።

Photos from Ministry of Education  Ethiopia's post 13/07/2021
Photos from The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia's post 07/07/2021
Photos from University of Gondar's post 03/07/2021

Great Job Solomon Fantaw , Asrat Atsedeweyn (PhD) Binyam Tilahun (PhD) University of Gondar ተቋማት በእንዲህ አይነት ሁሉን አቀፍ ስራዎች መሰማራት ሊበረታታና ሊቀጥል የሚገባው ተግባር ነው፡፡

02/07/2021

የቡሬ ግቢ እና ዋናው ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው ቴለሌግራም ገጽ ይፋ ሆነ፡፡

በ2013 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በማምጣት የኢፌዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባካሄደው የተማሪዎች ምደባ መሰረት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ሐምሌ 05 እና 06/2013 ዓ.ም መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የምዝገባ ቦታ፡-
 በማህበራዊ ሳይንስ የተመደባችሁ ከ ‘L’ እስከ ‘T’፣ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ ከ ‘N’ እስከ ‘z’ ባሉ ፊደላት ስማችሁ የሚጀምር ተማሪዎች ቡሬ ከተማ በሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ምዝገባ የምታካሂዱ ሲሆን ከዚህ ውጭ የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ መመዝገብ የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን ስም ዝርዝራችሁን በዩኒቨርሲቲው የቴሌግራም ገጽ t.me/Debre_Markos_University ማየት ትችላላችሁ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ www.dmu.edu.et
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ቴሌግራም https://t.me/Debre¬¬_Markos_University በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

02/07/2021
18/06/2021

Ministry of Science and Higher Education - Ethiopia Debre Markos University

የሽልማት ስነ-ስርዓቱን በተመለከተ ከህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን የተሰጠ አጭር መረጃ
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን የሚሸልምበት ዓመታዊ ስነስርዓት አርብ ሰኔ 11/2013ዓ/ም የዋዜማው መሠናዶ በአማራ ፖሊስ ማርሽ ባንድ በደብረማርቆስ ከተማ አደባባይ ትርኢት በማቅረብ ተሸላሚ ተማሪዎች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ትውውቅ ያደርጋሉ።

ትርኢቱም በአገራዊና ትምህርት ነክ ዜማዎች በፖሊስ ማርሽ ኦርኬስትራ እየተካሄደ ከንጉስ ተክለሃይማኖት አደባባይ መነሻውን አድርጎ ሸበል ሆቴል ፣ ከሸበል ሆቴል በቀጥታ የዩኒቨርስቲው መስመር ሐዲስ አለማየሁ አደባባይ፣ ከሃዲስ አለማየሁ አደባባይ ወደ ሰንተራ ሆቴል በማድረግ በሙሉ ሆቴል አድርጎ በቀጥታ ወደ ጎዛምን ሆቴል ደሴት መዳረሻውን ያደርጋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በዚህ ደማቅ የሽልማት ስነስርዓት ዋዜማ አደባባይ በመውጣት ጎበዝ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰላምታ ይሰጣል፣ ክብርና አድናቆት ይሰጣል። በእለቱ ሰኔ 12/2013ዓ/ም ከዩኒቨርሲቲው ዋናው በር ጀምሮ ተሸላሚ ተማሪዎች በማርሽ ባንድ ትርኢት ታጅበው ወደ ሐዲስ አለማየሁ የጉባኤ አዳራሽ ይገባሉ።የክብር እንግዶች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም መምህራን አቀባበል ያደርጉላቸዋል።

የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በታዋቂው ድምጻዊ ዳዊት ጽጌ ዜማ ይደምቃል። በገጣሚ አበረ አዳሙ ቅኔ ይሞቃል። ተማሪዎቻችን ይሸለማሉ።

የሽልማት ስነስርዓቱ በዶ/ር አልማው ክፍሌ አነቃቂ ንግግር ቁምነገር ይሸመትበታል። በአምናዋ የፕሬዚደንት አምባሳደሯ የዘንድሮዋ የዩኒቨርስቲው አስተማሪ ሐናን ፈድሉ ንግግር ይዋባል።

የዩኒቨርስቲው መምህራን፣ እና ሰራተኞች ተማሪዎች ቅዳሜ በ12/10/2013 ከ1:00ጀምሮ ቀድመው ቦታ ይይዛሉ። የማይረሳ፣ የሚያምር ውብና ማራኪ እለት ይሆናል።

2ኛው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚደንት ሊስት አምባሳደሮች ቀን!!!
እንኳን አደረሳችሁ።

09/04/2021

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቸ የደብረ ማርቆስ ቴክኖሎጅ ተቋምን ይከትሉ ይወዳጁን
በሊንክድን https://www.linkedin.com/in/debre-markos-institute-of-technology-ethiopia-42553b20b/
በቲውተር https://twitter.com/DebreOf
በፌስቡክ ያግኙን ይወዳጁን

Photos from ‎አባይ ግድብ / Nile _ dam / سد النهضة الاثيوبى‎'s post 02/04/2021
NYT Offering a Dangerous Version of ‘Truth’ in Ethiopia | The American Conservative 15/03/2021

NYT Offering a Dangerous Version of ‘Truth’ in Ethiopia | The American Conservative Irresponsible reporting by The New York Times could lead to lasting damage in Ethiopia.

20/02/2021

መሀንዲሶቻችንን ጋር ለመምከር ዝግጁ ሆናል!!
በኮንስትራክሽን በእንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራችሁ ከ7.30 ጀምሮ ከች በሉ!!

Photos from Debre Markos University's post 12/02/2021
Photos from Wassie Dessie Kidie's post 11/02/2021

የጀግናዉና ለሀገር ሞገስ ለሆነዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል መሆን ትልቅ ኩራት ነው !!!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የሠራዊት አባል በበርካታ የሙያ ዘርፎች መልምሎ ለማሰልጠን በምዝገባ ላይ ይገኛል ። በመሆኑም እድሜዉ የደረሠ የአማራ ወጣት ሁሉ የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን መመዝገብ አለበት ።

የሀገር መከላከያ ሚንስቴር የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ ወጣቶች ተመዝገቡ ። ይህን እድል በከንቱ ማሳለፍ አይገባም። የክልሉ መንግስት የተሠጠዉን የሠዉ ሀይል በአግባቡ እንዲጠቀም ይመለከተኛል የሚል አካል ሁሉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እንስራ ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለክልሉ የሰጠውን የሠዉ ሀይል ኮታ ሙሉ በሙሉ ሊጠቀም ግድ ይላል። ለልዩ ሀይል የተሠጠዉ ፍቅርና ተኩረት እዚህ ላይ ሊጨምር እንጂ ሊቀንስ አይገባም ።

የወታደርነት ስልጠና ሳይወሰድ :ተራ ወታደር ሳይሆን ጀኔራል አይገኝም ። እንደ ሀገር በመከላከያ ሰራዊት ውሰጥ የሚኖረዉን ድርሻ ለማስጠበቅ መሠልጠን ግድ ይላል። ይህን አይነት ነገር በተለያዩ ሠበቦች እያመካኙ አለመመዝገብ ሞኝነት ነዉ ። የዞን: የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ልዩ ትኩረት ሠጥተዉ እንዲሠሩ የሚመለከተዉ አካል ትዕዛዝ ማስተላለፍ አለበት።

የሚመጣዉን እድል ሳንጠቀም ሌላ ጊዜ የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ አይነት ነገር አይሠራም። አሁኑ በቀሩት ቀናቶች ተመዝገቡ ። ሁሉም ሀላፊነቱን ይወጣ !!!!

06/02/2021

ማሬ ባገር ወዝሽ ፣
ማሬ ባገር ድምጥሽ ፣
ማሬ ባገር ልብስሽ ማሬ ወለላዬ ማሬ በጥለቱ ፣
ለባቲው ከራማ ትመለሽለት ዘንድ ምንድን ነው ስለቱ ?።
ያነ ባለ ሓድራ ፣
የተራራው መጀን ፣
የአምባሰልሽን ማር
ከባቲሽ ቡርቱካን ከጦሳ ተራራ ጠይም ውሃ ቀድቶ ፣
ባራዳ ቀን እርሾ በገራዶው አብሲት ፣ ሸዋ በር አብክቶ ፣
አይጠገብ ብሎሽ ፣
ደጃች ይማም ቀዬ ፣
አላንሻ ራስጌውን ፣
ላኮመንዛ መሀል ናፍቆቱን ሊያበርድ አንቺን እያለመ፣
ደሴ ከተማው ላይ ፣
ማር ማር የሚል ዘፈን በቅኝትሽ ምጣድ ሲጋግር ከረመ ።
መገን ጉድ መዋደል ፣
የዘፈኑን ጣና ፣
የዜማሽን አባይ ፣
አጃኢቡን ሙላት ፣
ጠጥቶት ላይጠግብ ጨልፎት ላይጎድል ፣
የዘራፍሽን ቃል ...
የጀግናውን ዜማ በጆሮ ትክሻ አስሮ ሊያደላድል።
ገምሻራየዋዬ ፣
ማሪቱን እያለ ሌት ተቀን በቁሙ በስምሽ ሽክና ፣
ሲያምገው ይከርማል ፣
ወልፉ ሰከን እንዲል የድምጥሸን አወል የዜማሽን ቶና።
መች ሶብር ሊያገኝ ዜማ ምሴ የሚል ብርቱ ዛር ነውና።
ጉድ እኮ ነው ማሬ ...
አውሳ ዝናብ የለም ያብቅላል በመስኖ ፣
ያልሺው ሽው ብሎት አቅሉ ስር መንኖ ፣
እንኳንስ የራሱ ፣
የኽልቁ አንገት ጋራ ፣
መቃ ሸጋ አንገትሽ ጃምዮ ‘ሸት መስሎ ፣
ከተፍ ይለበታል ናፍቆት እንደ ጀማ ባንድ ተቀላቅሎ ፣
ኧረ ና ድማሙ ፣
ኧረ ና ድማሙ ፣
ኧረ እንደምን አለህ -
( ስትይው ጊዜና ... )
እንደምን ነኝ እንጂ ፣
ምን ሊልሽ ማሬዋ ቃል ከየትስ ሊዋስ ፣
በቅኝት ኸለዋው ባካሌውቤሽ ደጅ ናፍቆት ለሚያጫጭስ።
መገን !
በትዝታ መብገን ።
ይስማ ንጉስ ደጃፍ እንዳይሆኑ ሆኖ ጎልቦን ተሻገረ፣
አይጠገብ ማዱ በጋገረው ዜማሽ ደሴ በልቶ አደረ።
አንግድህ ምን ያስችል ...
የጁን በጅህ ብሎት ፣
መርሳ ላይ እስኪደርስ ፣
ደራርቦ ተኝቶ ሀድራውን ሊሞቀው ፣
ሲሻበት ሆነና እራስ ወገብ ትቶ ባቴን ባቴን ሊለው፣
የትዝታሽ ጋዲ ባቲ መዳረሻ ቀርሳ አጋድሞ ጣለው።
እህህ !
ማሬ ባገር ወዝሽ ፣
ማሬ ባገር ድምጥሽ ፣
ማሬ ባገር ልብስሽ ማሬ ወለላዬ ማሬ በጥለቱ ፣
ለባቲው ከራማ ትመለሽለት ዘንድ ምንድን ነው ስለቱ ?።
ገምሻራዬዋ ፣
ወሎ አባ ጥለቴ ፣
ይሄው ይዣለሁኝ ፣
የጁን ምን ይገደው ፣
በሃጃው ማንደጃ ግለጠው ብለናል አሚኑ ሊከበር፣
ሳትፈልጊ አልምዶ ለቀዬሽ ለወንዝሽ የከላሽን ጀንበር

06/02/2021

✍️✍️"የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶች"✍️✍️
~አዲስ መጽሐፍ~
ደራሲ✍️ ታፈረ መላኩ(ፒኤች ዲ)

"የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶች" የተሠኘ አዲስ መጽሐፍ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ ተጽፎ ለንባብ ቀረበ። መፅሐፉ በአራት ክፍሎችና በ20 ንዑሳን ምዕራፎች የተዋቀረ ሲሆን ስለዩኒቨርሲቲዎቻችን ወቅታዊ ሁናቴና አገራዊ ሁነቶች ይተነትናል። ያስገነዝባል፣በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች ተነስተውበታል።
የኢትዮጵያ እናቶችን ዕንባና ዎይታ፣ በባለፋት ቅርብ ዓመታት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጨምሮ የዜጎችን ሰቀቀንና ሰቆቃ እያነሳ ሁሉንም አካላት ይሞግታል።

አድሮ ቃሪያው ፖለቲካችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሀገር ደረጃ የፈጠረውን ሰባዊ ቀውስ በሰፊው ይዳስሳል።

ፀሐፊው በማስታወሻቸው አነሳሽ ምክንያታቸውንና የጽሁፍን ማዕከላዊ አትኩሮት አስቀምጠዋል።

"የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶች" የዶ/ር ታፈረ መላኩ አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን በደብረ ማርቆስ ይመረቃል።

መጽሐፉን ለመግዛትና/ለማግኘት የምትፈልጉ በቀጣዮች አድራሻዎች ማግኘት ትችላላችሁ።
ሐብታሙ መኮንን
📲+251 913 05 00 49
[email protected]

ግርማው አሸብር
📲+251 912 28 82 36
[email protected]

Photos from Wassie Dessie Kidie's post 24/01/2021

ጎንደር ቅርስ አላት፤ ታሪክ አላት፤ ባህል አላት፡፡ ዩኒቨርሲቲም፡፡
ደመናው አልፎ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በድምቀት አስመርቋል፡፡
(ሄኖክ ስዩም ~ ድሬቲዩብ)
---
በከተማው የሚምል ዩኒቨርሲቲ ከጠየቃችሁኝ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እላችኋለሁ፡፡ ኮሮናው ገብቶ ሀገር ሲታመስ መንግስት ከወሰዳቸው ተከታታይ እርምጃዎች ቀዳሚው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነበር፡፡

ያኔ ዶክተር አስራት አጸደወይን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልብ የሚነካ መልእክት አስተላልፈው ነበር፡፡ "ደመናው አልፎ ብሩህ ቀን ሲመጣ ዳግም እንገናኛለን" የሚል፡፡ እያለቀሱ በሀዘን የተበተኑ ተማሪዎች እየሳቁ ትናንት ተመርቀዋል፡፡
በማኅበሰብ አቀፍ ስራዎች ተከታታዮቹ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና የተተካኩት የማኔጅመንት አባላት አንዳች የጠባይ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ሁሉም ጎንደር ዩኒቨርሲቲን የጎንደር አድርገው የመሩ ናቸው፡፡ ለማኅበረሰብ ቀርበው ማኅበረሰብን አለንልህ ያሉ ናቸው፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተበሰረ የሚባለው ማኅበረሰብን የማቀፍና የማገልግል ትልቅ መርህ ጎንደር ሲደርስ ዋነኛ መገለጫ ሆኗል፡፡ በሁሉም መስክ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በአንድ ድምጽ የሚግባባበት ጉዳይ ለማኅበረሰብ ጉዳይ ባለቤት መሆንና ቀጠናውን መደገፍ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ቀድሞ መንፈሱን፣ ቀጥሎ እውቀትን አልፎም ካዝናውን ሳይሰስት አብሮነትን አሳይቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለሚኖር የትብብር ስራም አውራው ነው፡፡

በሀገራችን ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ሳያጣ አካባቢያዊ ትርጉሙ ያልተፋለሰበት ዩኒቨርሲቲ በመሆን አስመስክሯል፡፡ ከተማዋ፣ ዞኑና አልፎም ክልሉ የኔ የሚለው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል፡፡ ደግሞ በሀገር ደረጃ ተመዝኖ ያልቀደመበት፣ ተወዳድሮ ዋንጫ ያላነሳበት የብቃት መስፈርት ኖሮ አያውቅም፡፡

ትናንት ደመናው አልፎ ለምረቃ የበቁት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሰባት ሺህ በላይ ነበሩ፡፡ የምረቃው የክብር እንግዳ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ናቸው፡፡ በጥምቀት ማግስት በተካሄደው ደማቅ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ መደማመጥና መከባበርና አንድነት የተመራቂዎቹ እሴት እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አገኘሁ ተናግረዋል፡፡

ብዙ ፈተናዎች የነበሩበት የአለፈውን አመት የትምህርት ዘመን አልፈው፤ በዚህ አመት የጋጠመውን ትርምስ ተሻግረው ተመርቀው ወደየመጡበት የተመለሱት ተማሪዎች በእርግጥም ፈተናን ድል ያደረጉ ስኬታማ ሰዎች ናቸው፡፡

Was Midea and Promotion - YouTube 23/01/2021

የYou Tube ቻናላችን ሳብስክራይብ በማድረግ ወዳጃችን ሁኑ ።

Was Midea and Promotion - YouTube Share your videos with friends, family, and the world

Photos from Tamagne Beyene's post 23/01/2021
Photos from Gondar City Prosperity Party /GPP/'s post 21/01/2021
19/01/2021

!

🧠ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ስኬት የሚጠነሰሰው፣ በሁለት ትከሻዎች መሃል ባለው ሁለት ኪሎ ግራም በሚመዝነው ጭንቅላት ውስጥ ነው፡፡ አሊያም በእያንዳንዷ ደቂቃ በአዕምሮህ ውስጥ በምትመላለሰው አስተሳሰብ ነው፡፡ በዙሪያህ ያለው ዓለም የሚያንፀባርቀው የውስጥህን ማንነት ነው። አስተሳሰቦችህን እንዲሁም በሕይወትህ ውስጥ ስለሚያጋጥሙ ነገሮች አፀፋዊ ምላሽ መስጠት መቻል፣ የዕጣ ፈንታህን መዳረሻ መቆጣጠር ያስችልሃል።እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ በአንተ በቁጥጥር ውስጥ ካዋልከው የሀይል ብክነት አያጋጥምህም።ተሰፍሮ የማያልቅ ሀይል እና ጊዜ ይኖርሃል።

🔥አብዛኛዎቻችን ማብቂያ በሌለው ጭንቀት ውስጥ ተውጠናል። ይህም የተፈጥሮ ንቃታችንን እና ሃይላችንን አድርቆ አቀጭጮታል። አሮጌ የባይስክል ጎማ ከመነዳሪ አይተህ ታውቃለህ።በአየር ሲሞላ ወደ አሰብከው ቦታ ያደርሰሃል። ሆኖም ቀዳዳ በውስጡ ካለው የጉዞህ ማብቂያ ያልታሰበ ቦታ ይሆናል። አንጎላችን የሚሰራው እንደዚህ ነው። አጅሬ ጭንቀት ውድ የሆነውን ሀይልህን ያባክነዋል።ልክ አየር ከከመነዳሪው ውስጥ እንደሚባክነው ሁሉ የአእምሮ ብርታት ተንጠፍጥፎ ያልቅና ተጨማሪ ሀይል አይኖርህም። የፈጠራ ችሎታህን በውስጥህ እንዲሞት ያደረገዋል።

🔶መጥፎ ልማዶች አይጠፉም።ነገር ግን መጥፎ ልማዶች በጠቃሚ ልማዶች ሊተኩ ይችላሉ። አዲሱን ልማድ ለማጽደቅ ብቸኛው መንገድ ደግሞ ፣ እምቅ ሀይልህን ለአዳዲስ ልማዶችህ ላይ ማሳረፍ ነው፡፡ ያኔ አሮጌ ልማዶች እንኳ ደህና መጣህ እንዳልተባለ እንግዳ ሹልክ ብለው ይወጣሉ። ጠቃሚዎቹን ልማዶች በውስጥህ ለማስረጽ 21 ቀናት ይወስድብሃል፡፡”በርካታ ሰዎች ከመኝታቸው ልክ እንደነቁ ሳያስቡት ዘወትር ተመሳሳይ ነገር ያከናውናሉ፡፡አይናቸውን እንደገለጡ ከአልጋ ተስፈንጥረው ይነሱና ፊታቸውን መታጠብ ይጀምራሉ። በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ማንበብም ይሁን የትኛውም ልትሰራው ያሰብከውን ነገር ፣ በድግግሞሽ የፊት መታጠብን ያህል እየቀለለህ ይሄዳል።” ስለዚህ በድግግሞሽ ምክንያት አዲስ ባህርይ ተላብሰህ ራስህን ታገኘዋለህ፡፡

🔷አንድ ምርጥ ዘዴ አለ ይሄም ልታሳካው የምትፈልገውን ግብ በዙሪያህ ላሉት ሰዎች መንገር እና ግብህን ተፈፃሚ ለማድረግ መንቀሳቀስ ወዲያውኑ ይህንን ነገር እውን ለማድረግ በትከሻዎችህ ላይ ጫና ያርፋል፡፡ ምክንያቱም ማናችንም ብንሆን ብቁ ያልሆንን ሆነን መታየት አንፈልግም።

🎯ምስል መፍጠር( imagination) አዕምሮህ የሚሰራው በምስል ነው። ምስሎች ደግሞ አመለካከትህ ላይ የጎላ ተፅእኖ ይፈጥራሉ:: ፣ ህሊናህ ላይ ያሰፈርከው የራስህ ምስል፣ በየእለቱ በምታከናውነው ሥራና ውጤት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡መንፈስህን ለተሻለ ነገር የሚያነቃቃ ምናባዊ ምስል በአዕምሮህ ሰሌዳ ላይ ጎልቶ የተቀመጠ ከሆነ፣ በነባራዊ ህይወትህ እነዚህ ነገሮች ወደ እውነት መቀየር ይጀምራሉ፡፡ አንስታይን እንዳለው፣ በዓይነ ህሊናችን ውስጥ ያለው ምናባዊ ምስል፣ ከተጨባጭ እውቀት በላይ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።(Imagination is more important than Knowledge)

♦️"ህልምህን እውን ለማድረግና ግቦችህን ለመቀዳጀት በምታደርገው ጉዞ (ሂደት) በጣም ተደሰት፡፡ ያለሳቅና ፍንደቃ ያለፈች እንዲት ቀን፣ ወይም ያለፍቅር ያለፈች ጀምበር የባከነች ተደርጋ ትቆጠራለች።” ግብህን ለመቀዳጀት በምታደርገው ረጅም ጉዞ ተዝናና፡፡ በምድር ላይ ያለውን የፍጥረት ውበት አድንቅ፡፡ የዛሬዋ እለት ይህቺ ቅጽበት ከተፈጥሮ የተቸረች ስጦታ ነች። አትኩሮትህ በራስህ ሕይወት ውስጥ ይሁን፡፡ እና ከራስህም አልፎ ሌላውን በማገልገል ትጋ። የተቀረውን
በሙሉ የጽንፉ ዓለም ያከናውነዋል። ይህ ከተፈጥሮ ሕጎች ውስጥ አንደኛውና እውነተኛው ሕግ ነው።”

💜 ከዛሬዋ ቀን አንስቶ በሕይወትህ ላይ ራስህን ሹም፡፡ የዕጣ ፈንታ ጌታ ለመሆን ወስን፡፡ በራስህ መንገድ የራስህን ሩጫ ሩጥ፡፡ የመክሊትህን ጥሪ አድምጠህ ስሜትህን በሚነሸጥ መልኩ መኖር ጀምር፡፡ በስተመጨረሻም ዘወትር ልታስታውሰው የሚገባህ ነገር፣ መሆን የምትፈልገውን ህይወት ወይም መድረስ የምትፈልግበት ደረጃ ለማሳካት የሚያስችልህ በውስጥህ ያልተገደበ ሀይል እንዳአለ ነው።

✍️ሮቢን ሻርማ

18/01/2021

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ ።

እነሆ በሀገራችን አቆጣጠር በመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ከ30 ዓ.ም. ጀምሮ የጥምቀት በአል በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ታስቦ ይውላል።

በተለይም በሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች የተለየ ትርጉም ያለው ብዝሀነት በይፋ የሚንጸባረቅበት ታላቅ ብሄራዊ በዓል ነው።
"ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ" እንዲሉ በዓሉ ደስታችንንና የወደፊት ተስፋችንን በታቦተ ህጉ ፊት የምንገልጽበት ቀን ነው።

የክፋትን እድፍ አጥበን የምናጠራበት፣ የቂምና ጥላቻን ሰንኮፍ ነቅለን ወደጥልቁ ባህር የምንወረውርበት ድንቅ ቀን ነው።

የጥምቀት በዓል ከመንፈሳዊ ገጽታው ባሻገር የሀገርና የህዝብ ሀብት ፣ የማይንቀሳቀስ ቅርስ ነው።

በዓሉን ባልተገባ መንገድ መረዳትና የዜጎችን ቅስም በመሰባበር ፣ እርስ በእርስ በመናቆር ፣ ከበአሉ መንፈሳዊና ታሪካዊ አንድምታ ይልቅ በተራ ስሜት መጫጫን ለጸብና ለእርስ በእርስ ግጭት እንዲውል መፍቀድ በየትኛውም ወገን ይሁን መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው።

የጥምቀትን በዓል ስናከብር እርስ በእርስ እንጠባበቅ። ደስታችንንና ፌሽታችንን በልኩ እናድርግ። የአካባቢያችንን ሰላም በንቃት እንጠብቅ። ትርፍ ከማያስገኝልን ህገወጥ ድርጊት እንቆጠብ።

በዓሉ ሰዎች እንዲተሳሰቡበትና በሰላምና በፍቅር ሆነው ፈጣሪያቸውን እንዲያመሰግኑበት ከፈጣሪ የተሰጠ ሀብት ነው።

በመለያየት ፣ በመፎካከርና እርስ በእርስ በመናቆር እናከብረው ዘንድ የተሰጠን በአል አይደለም። ስለሆነም እርስ በእርስ ከመዋደድና ከመከባበር የምናጎድለው ነገር ስለሌለ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ወንድማማችነትን እናጥብቅ። ሀገራችን ኢትዮጵያን ከክፉዎች መዳፍ ፈልቅቀን እናውጣት። የክፉዎች መንፈስ የሚሸነፈው በአንድነታችን ብቻ ነው። እንድ እንሁን !!!

በማያባራ የአውሬነት ባህርይ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ነፍስ በገነት ያሳርፍልን። በህይወት ለተረፉት መጽናናትን ያድልልን።

የጠላት ዲያብሎስን የሞት ደብዳቤ በባህረ ዮርዳኖስ እንደተሻገርነው ሁሉ ያለምንም ጥርጥር ከፊት ለፊታችን ያለውን የፈተና ክምር ደረማምሰን በድል በመሻገር የብልጽግና ጉዟችንን እናሳካለን።

ሀገራችንና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይጠብቅልን !!!

17/01/2021

ሚዛናዊ አስተሳሰብ ❗️

ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሚዛናዊ ህይወት መሰረት እንደሆነ አስብ። የአንድ አስተሳሰብ እስረኛ አትሁን። የሰው ልጅ ብስለት የሚለካው አንድ አስተሳሰብ ላይ ሙጥኝ በማለት ሳይሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት ማስተናገድ የሚችል አእምሮ በመገንባት እንደሆነ እወቅ።

አንድ አስተሳሰብ ብቻ ማስተናገድ ለህይወትህ ጠቃሚ የሆኑ ምቹ አጋጣሚዎችን መገደብ እንደሆነ ተረዳ። የአስተሳሰብ መብዛት የስኬት አማራጭ ማደራጀት እንደሆነ አስብ። ማንኛውም አስተሳሰብ ሀብት እንጂ ጠላት እንዳልሆነ አስታውስ።
አስተሳሰብን መገደብ እውቀት የሚገኝበትን እድል መዝጋት እንደሆነ አስተውል። አንድ አስተሳሰብ በራሱ እስራት እንደሆነ ተገንዘብ። ብስለት ማለት የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት በማስተናገድ የሚገኝ የህሊና ነፃነት እንደሆነ አስብ። አንድ አስተሳሰብ ብቻ ማራመድ የህሊና ባርነት እንደሆነ ተገንዘብ።

መልካም አሁን 🙏🙏🙏

17/01/2021

ጥምቀትን በጎንደር

ለ200 ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና በነበረችው ጎንደር አፄ ፋሲለደስ ጥምቀት በየቦታው ተበታትኖ ሳይሆን ታቦታት በአንድ ላይ ተደብረው መከበር እንደሚገባቸው አዋጅ ካስነገሩበት ወቅት ጀምሮ ጥምቀትና ጎንደር የገጠሙ እለት እንኳንስ ለጎብኝዎች ለነዋሪዎችም ታይተው አይጠገቡም፡፡

የጎንደር ጥምቀት በዓል ከመላ ኢትዮጵያ አከባበር የሚለይባቸው በሁለት ተያያዥ ምክንያቶች ሲሆን ከተማዋ ለረዥም ዓመታት መናገሻ ከተማ ሆና መቆየቷ፣ በጊዜው የነበረው ኃይማኖታዊ መንግስት በመሆኑ አብዛኛው ነዋሪ ጥብቅ የኦርቶዶክስ ክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከሌላው አካባቢ (ከተማ) በተለየ መልኩ “የአርባ አራቱ ታቦታት” መገኛ መሆኗ የመጀመሪያው ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ምስረታ በኋላ ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ በኩል አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ18 ሺህ ካሬ ሜትር ምድረ ግቢ ውስጥ በግሩም የስነ ሕንፃ ውበት ለጥምቀተ ባህር መዋኛና ታቦታት ማደሪ ተብሎ በአፄ ፋሲል የተሰራው የፋሲለደስ መዋኛ መገኘቱና ለበዓሉ ድምቀት የጎላ ተፅዕኖ ማሳደሩ የጎንደርን የጥምቀት በዓል የተለየ ያደረገው ፡፡
የፋሲለደስ መዋኛ ስፋት 50 ሜትር በ30 ሜትር ሲሆን፣ ጥልቀቱ ደግሞ 2.5 ሜትር ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት ስፋት ያለው መዋኛ ገንዳ በዛ ዘመን መገንባቱ በራሱ ድንቅ ነው፡፡

የከተራ በዓል

ጥር 10 ቀን 200 ጧት ቅዳሴ እንዳለቀ በመንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ታቦታቱ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ የምሕላ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ይከናወናል ፡፡ ይህ የምሕላ ሥነ ሥርዓት በየዓመቱ ይፈጸማል፡፡ ከዚያ በአንድ ላይ ማኅሌት ተቁሞ ያድራል፡፡ ማኅሌቱ ሲፈፀም የቅዳሴ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ የባሕረ ጥምቀቱ የቡራኬ ሥርዓትም ይካሄዳል፡፡

ከዚያ ታቦታቱ ወጥተው ሃዲጎ ተስአ ወተስአተ ነገድ የሚለው ማኅሌታዊ ዝማሬ ተዘምሮ ሁለቱ የቅ/ ሚካኤል ታቦታት ከዚያው ይቆያሉ ሌሎቹ ግን በ7 ምዕራፍ ታቦታቱ እየቆሙ የማኅሌቱ ሥርዓት የዝማሬው ሥርዓት እየተካሄደ ወደየ መንበረ ክብራቸው ይመለሳሉ፡፡

በሁሉም የኢትዮጵያ ቤ/ክ አከባበር የማኅሌት ሥርዓቱ 7 ምዕራፍ አለው፡፡

አማኞች በቡድንና በተናጠል ጧፍ፣ ዘቢብና መሰል ስጦታዎችን በታቦቱ ፊት ያበረክታሉ ፣ የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየባሕረ ጥምቀቱ የሚከበሩ በመሆናቸው፣ አገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብነትን በመጎናጸፉ፣ ቱሪስቶችን ይስባል፡፡
ከህጻናት ጀምሮ ኮበሌው፣ ኮረዳው ፣ እና እድሜ ጠገብ አባቶችና እናቶች የጎንደር ጥምቀትን በአል ልዩ ውበት ናቸው . . .

አንተ የት መጣህ አይባልም …ማን የማንን ይጫወት አይባልም! ኦሮሞው ፤ከንባታው ፤ ጉራጌው፤ ሃረሪው ፤ትግሬው ፤ አማራው ፤ ሱማሌው ይዘፈናል ፣ የደለቃል ፣ ጃሎ ይባላል! ኢትዮጵያዊ በጎንደር የጥምቀት በአል አንድ ሆኖ ባንድ ክብረ በአሉን ይታደማል ! አገር ጎብኝው ፈርንጅና ጥቁሩ ከሃገረ አሜሪካ ፤ ከአውሮፓን ከሩቅ ምስራቅና ከአውስትራልያና ከተለያዩ አለማት የመጡት ሀገር ጎብኝዎች በካሜራቸው እያጠመዱ ጥምቀትን በጎንደር ሲያከብሩ የኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ነው!

የእረፍት ጊዜያችውን በዓለ ጥምቀትን ተጠግተው ጎንደርን ሲጎበኙ በጨዋታው ደምቀው ተውበው፣ የዚያን ዘመን የእነ አጼ ፋሲልን ቤተ መንግስቶች ፣ የቅድመ አያቶቻችን ድንቅና ውብ ባህልና ያለፈ መልካም ስራ እየተደነቁ የሚያልፉበት ትዕይንት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማየት ጎንደርን በጥምቀት ማየት ያሰኝዎታል! በሀገሬው ሆታ ጭፈራ ተደምመው የደስታ የፌስታ ቀንወትን እያሳመሩ ኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ጥምቀትን ያከብራሉ

Photos from አዝመራው ተዘራ በላይ /Azmeraw Tezera Belay /'s post 15/01/2021

ከክለብም በላይ ሩጫ በጎንደር ከተማ ለፋሲል ከነማ ❗️
ፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ / Fasil Kenema Sport Club በርቱ ህዝብና መሪዎቻቹህ ከጎናቹህ ናቸው

11/01/2021

የሚዲያ ጥቆማ ጥምቀትን በጎንደር ❗️

Photos from Agegnehu Teshager's post 05/01/2021
04/01/2021

Good job ሞላ መልካሙ ከበደ Molla Melkamu kebede ተሾመ አግማስ ዓለሙ /Teshome Agimas Alemu/ አዝመራው ተዘራ በላይ /Azmeraw Tezera Belay / በርቱ ከዚህ በላይ ከእናንተ እንጠብቃለን ።

Telephone

Website