Glory Amanuel
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Glory Amanuel, Public Figure, .
“ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ማን ነው? ሥራውን ከጥበብ በሆነ በመልካም አኗኗር ያሳይ።”
— ያዕቆብ 3፥13
💪
🙏
Prayer is touching God in the spirit.
John 13
¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁴ I give you a new commandment. that you should love one another. Just as I have loved you, so you too should love one another.
³⁵ By this shall all know that you are My disciples, if you love one another .
እግዚአብሔር ለአንተ/ቺ እንዲህ ነው ወዳጄ!
◌በወንዝ የመስጠም ስጋት ወንዝን በፈጠረ አምላክ አብርሆት ይሻራል።
◌በውኃ የመወሰድ ፍርሃት ውኃን በፈጠረ አምላክ መገኘት ይሻራል።
“በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።”
— ኢሳይያስ 43፥2
♥️♥️
Glory Amanuel on TikTok #መዝሙር
“And who is he that will harm you, if ye be followers of that which is good?”
— 1 Peter 3:13
“And, behold, I come quickly; and my reward is with me, to give every man according as his work shall be.”
— Revelation 22:12
You can't stop someone who is hungry for a better life according to God's word.
“Let the word Christ (the Messiah) have its home and dwell in you in richness, as you teach and admonish and train one another in all insight and intelligence and wisdom psalms and hymns and spiritual songs, making melody to God with grace in your hearts.”
— Col 3:16 (AMP)
“He shall cover you with His feathers, And under His wings you shall take refuge; His truth shall be your shield and buckler.”
— Ps 91:4 (NKJV)
“I will say of the LORD, He is my refuge and my fortress: my God; in him will I trust.”
— Psalms 91:2
“Therefore if any man be in Christ, he is a new creature: old things are passed away; behold, all things are become new.”
— 2 Corinthians 5:17
“He that dwelleth in the secret place of the most High shall abide under the shadow of the Almighty.”
— Psalms 91:1
ምን እንደሰማህ ስማ
═════════
✔️ ወደ ጆሮህ የገባን ሀሳብ ሁሉ አትመን፣ አትፍራውም። በጆሮህ የሰማኸውን እንደገና በልቦናህ ጆሮ በእግዚአብሔር ቃል ቅኝት ስማው እንጂ። (በጆሮ የሰማኸውን በልብ አጣርተህ ስማው)
➢ሁሌም ሀሳብን ስትሰማ በእግዚአብሔር ቃል አዕምሮህን አያደስክ ስማ
➢በጩኸት በታላቅ ድምፅ የተነገረ ሀሳብ ሁሉ ትክክል ነው ማለት አይደለም፤ በእርጋታ የተነገረም እንዲሁ።
✔️ኢየሱስ ስለመስማት ይህንን ተናግሯል:-
“በመቀጠልም፣ “ስለምትሰሙት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ይጨመርላችኋል።”
— ማርቆስ 4፥24 (አዲሱ መ.ት)
➥ይህ ቃል በአሁኑ ጊዜ ሕይወታችንን እየቀረጸ ያለ የሰማነው ነገር እንዳለ በማስረዳት “ስለምትሰሙት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ” ይለናል። እንዲሁም መስማትም ዘር መሆኑን ያሳያል።
➥ስለዚህ ውሳኔዎችህን በሰማሃማቸው ሀሳቦች ልክ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል እሳቤ አድርግ።
✔️የምንሰማው ዘር እምነትን ወይም ፍርሀትን ይወልዳል፤ እምነት ወይም ፍርሃት ደግሞ ሕይወትን ወይም ሞትን በነገሮች ላይ ያፈራሉ።
➢ዳግም እንደተወለደ አማኝ ምርጫችን ሊሆን የሚችለው ሕይወት ስለሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ " ጻድቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል" ይላል (ሮሜ 1:17)።
ጻድቅ የሕይወት ኑሮ ዘይቤው በእምነት ነው።
ይህች እምነት ደግሞ የምትመጣው ከመስማት እንደሆነ በሮሜ 10:17 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል:-
“እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”
— ሮሜ 10፥17
🙏እንዲሁም ከዚህ ቃል እንማር:-🙏
ምሳሌ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል።
²¹ ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት።
²² ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
²³ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።
✔️በቃ በአጭሩ እነዚህን ተግባራዊ አድርግ:-
▪ስለራስህ ለምሰትማው ነገር ተጠንቀቅ
▪ስለሌሎች ለምትሰማው ነገር ተጠንቀቅ
▪ለራስህ የምትናገረውን ተጠንቀቅ
▪ለሌሎች የምትናገረውን ተጠንቀቅ
🔑ስለራስህም ስለሌሎችም የሰማሃቸውን ሀሳቦች እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደገና ስማቸው።🔑
ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ለሌሎች በረከት ይሁኑ😇
በ Glory Amanuel
በቀን 22/07/2015 የተፃፈ
ጥርጣሬ የሚናገረውን መስማት እንዳትችል እምነትህ እጅግ በጣም ይጩኽ።
ታዛዥ ልጆች
═════════
✔️ሁላችንም እንደምናውቀው ኢየሱስ ታላቅ የሆነን ተልዕኮ አደራ ሰጥቶናል ➜ “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።”
— ማርቆስ 16፥15
▪ነገር ግን ይህንን ተልዕኮ ለማስፈጸም ታዛዥ እና ታማኝ ልጅ መሆንን ይጠይቃል። ምክንያቱም ቸልተኛ ልጆችም ስላሉ።
✔️በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እንኳ ካየነው ወላጆች አንድ ቦታ ለመላክ ከልጆቻቸው ውስጥ የሚመርጡት በተላከ ቁጥር እሺታውን የሚያሳይን ልጅ ነው። ሌሎቹ በዚህ ምክንያት ልጅነታቸው ይቀራል ማለቴ ሳይሆን ከተልዕኮ አንፃር ቸልተኛ ያልሆኑ ልብ አርኪ ልጆች አሉ።
➥ልክ እንዲሁ አይነት ታዛዥ ሰዎች በመሥሪያ ቤት፣ በትምህርት ቤት፣ በሰፈር፣ በቤተክርስቲያን አሉ። እነዚህ ሰዎች ተልዕኮን በመፈፀም የሚረኩ እና ሌላውንም የሚያረኩ ናቸው።
▪ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ሲላኩ ልብ የሚያሳዝኑ፤ እሺ ብለው ቢሄዱ እንኳ አኩርፈው የ15 ደቂቃ ተልዕኮን በ 1 ሰዓት የማይመለሱ አሉ። እንደ እነዚህ አይነት ልጆች ለቤተሰብ፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለሀገር እድገት ዝግመትን ያመጣሉ።
✔️እንግዲያውስ ታዛዥ፣ ታማኝ እና ልብ አርኪ ልጆች ከሆንን ይህንን ታላቁን የእግዚአብሔር ሥራ እንሥራ። በዮሐንስ 6:28-29 እንዲህ ይላል➜ ²⁸ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት።
²⁹ ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።
➥ሰዎች እግዚአብሔር በላከው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ የምስራችን እናብስር። የእግዚአብሔር የልቡ ሀሳብ የእኛም የልባችን ሀሳብ ሊሆን ይገባል።
▪ኢየሱስ ታዛዥ ልጅ ሆኖ ተልዕኮውን ፈፅሟል።➜ “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤”
— ዮሐንስ 17፥4
▪ እኛን ደግሞ ልኮናል።➜ “እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።”
— ማርቆስ 16፥15
ማጠቃለያ መልዕክቴ፦
👆ይሄንን ቃል የምናደርግ እንሁን👆
“ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።”
— ያዕቆብ 1፥22
!
ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ለሌሎች በረከት ይሁኑ😇
በ Glory Amanuel
በቀን 13/07/2015 የተፃፈ
የመንፈስ ሰይፍ
═════════
✔️መልካሙን የእምነት ገድል ለመዋጋት የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የመንፈስን ሰይፍ እንዴት መጠቀም እንዳለብን መማር አለብን።
➥“የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።”
— ኤፌሶን 6፥17
✔️መልካሙን የእምነት ገድል መዋጋት ማለት በልብህ የምታምነውን የእግዚአብሔርን ቃል በአፍህ መናገር ነው። ለዚያም ነው የእግዚአብሄር ቃል በሙላት ሊኖርብን የሚያስፈልገው።
✔️በእግዚአብሔር ቃል ሙላት የማትመላለስ ከሆንክ ለአጋንንታዊ ጥቃቶች የተጋለጥክ ነህ።
ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።
¹¹ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።
¹² መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
¹³ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።
¹⁴-¹⁵ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
━━━━━━━━━━━
ከክርስቶስ ጋር ስለተነሣን
ሀሳባችንንም ከሞት ስፍራ እናንሳ
═══════════
ቆላስይስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤
² በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።
³ ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤
━━━━━━━━━━━
ሳምሶንን ሊበላ በመንገዱ የመጣ ጠላት
የሳምሶን ምግብ አቅራቢ ሆኖ ተገኘ
═══════════
መሳፍንት 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሶምሶንም ወደ ተምና ወረደ፥ በተምናም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ።
² ወጥቶም ለአባቱና ለእናቱ፦ በተምና ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አይቻለሁ፤ አሁንም እርስዋን አጋቡኝ አላቸው።
³ አባቱና እናቱም፦ ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለምን? አሉት። ሶምሶንም አባቱን፦ ለዓይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ አለው።
⁴ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን ላይ ምክንያት ይፈልግ ነበርና ነገሩ ከእርሱ ሆነ አባቱና እናቱ ግን አላወቁም። በዚያን ጊዜም ፍልስጥኤማውያን በእስራኤል ላይ ገዦች ነበሩ።
⁵ ሶምሶንም አባቱና እናቱም ወደ ተምና ወረዱ፥ በተምናም ወዳለው ወደ ወይኑ ስፍራ መጡ፤ እነሆም፥ የአንበሳ ደቦል እያገሣ ወደ እርሱ ደረሰ።
⁶ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደ ጠቦትን እንደሚቆራርጥ በእጁ ምንም ሳይኖር ቈራረጠው ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልነገረም።
⁷ ወርዶም ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ እጅግም ደስ አሰኘችው።
⁸ ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፥ የአንበሳውንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመንገድ ፈቀቅ አለ፤ እነሆም፥ በአንበሳው ሬሳ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፥ ማርም ነበረበት።
⁹ በእጁም ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ መጣ፥ ማሩንም ሰጣቸው፥ እነርሱም በሉ ማሩንም ከአንበሳው ሬሳ ውስጥ እንደ ወሰደ አልነገራቸውም።
━━━━━━━━━━━━
እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?
════════════
ዮሐንስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።
² ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።
³ ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦
⁴ መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።
⁵ ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።
⁶ የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤
⁷ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።
⁸ ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።
⁹ እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።
¹⁰ ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
¹¹ እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።
━━━━━━━━━━━
እንግዲህ ነፋስም ባሕርም
የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?
═══════════
ማርቆስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፦ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው።
³⁶ ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ።
³⁷ ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር።
³⁸ እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።
³⁹ ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።
⁴⁰ እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው።
⁴¹ እጅግም ፈሩና፦ እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ።
━━━━━━━━━━
ኢየሱስ ሽባን መፈወሱ እና አስደናቂው እምነት
══════════
ማርቆስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ።
² በደጅ ያለው ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ቃሉንም ይነግራቸው ነበር።
³ አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት።
⁴ ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፥ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ።
⁵ ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
⁶ ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውም፦ ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል?
⁷ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ።
⁸ ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ?
⁹ ሽባውን፦ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?
¹⁰ ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤
¹¹ ሽባውን፦ አንተን እልሃለሁ፥ ተነሣ፥ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
¹² ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፥ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና፦ እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።