ናትናኤል ታምሩ ፔጅ- Natnael Tamiru Page

ናትናኤል ታምሩ ፔጅ- Natnael Tamiru Page

ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ጠቃሚና አስተማሪ ፅሁፎች እንዲሁም ፈጣን፣ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች ይቀርቡበታል።
ቴሌግራም👉 t.me/GafatStudio

26/06/2023

♦♢19♢♦
⇨ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ
⇨ከቀናት ሳትዘገይ ሳይጎድል ደቂቃ
⇨ወደ ድንግል መተህ ደስታን አበሰርክ
⇨የዐምላክን ሰው መሆን ለአለሙ ሰበክ (2)
⇨ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ 2x
⇨ስንጠራህ ተሎ ድረስ ድምጽህን እንስማ

ቅዱስ ገብርኤል ረዳት፣ ጠባቂያችን ነው!

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ ሲሰደድም ከስደት ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው። (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)

ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ" እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ...
ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ። (ሉቃ.፩፥፲፱)

ቅዱስ ገብርኤል ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት ...

"በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል" እንዲል። (መዝ.፺፩፥፲፩)

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል" (መዝ.፴፬፥፩) "በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡" (ዘጸ.፳፫፥፳)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ //

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement

20/06/2023

❗️ይህ ሰው ሰሞኑን❗️

እምነትና ሃይማኖት መቀየር ፋሽን የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናልና በርካቶች በዚህ ጥፋት ውስጥ እያለፉ ይገኛሉ። ከሰምኑ ይህ ልጅ ሃይማኖቱን ቀየረ በሚል በስፋት እየተነገረ ይገኛል።

🔴 እስቲ እንጠይቅ።

🔘 ይህ ልጅ ሃይማኖቱ ምን ነበር?
🔘 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ነበር?
🔘 ያስቀድስ ነበር?
🔘 ይፀልይ ነበር?
🔘 ንስሃ አባት ነበረው?
🔘 ንስ ሃ ይገባ ነበር?
🔘 የየትኛው አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ አባል ነበር?

በየጭፈራ ቤቱና በየምናምን ቤቱ ሲዞር የከረመው ሁሉ የሆነ ነገር ሲጎድልበት አዲስ የቢዝነስ ዕቅድ እያወጣ በለፈለፈ ቁጥር ነገሩን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጋራ ማገናኘት ጥሩ አይደለም።

ቤተክርስቲያንን ሳያውቋት ኖረው ሃይማኖት ሲቀይሩ ግን ኦርቶዶክስ ነበርኩ ማለት ቂልነት ነው። ስም ከማጥፋት የዘለለ ነገር የለውም። ለአንድ ሰሞን የዩቲዩብ መሸቀያ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም።

ልብ ያለው ልብ ይበል
ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👉 t.me/GafatStudio

የሚገርመኝ የጨለማው ኑሮ አበቃ የሚሉት ነገር ነው😥

29/05/2023

ድንግል ማርያም ስትወደስ ምን ያናድዳል? ቅናት ሰይጣናዊ ካልሆነ በቀር።
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽዕት ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የበላያሰብዕ እመቤት፤ የሁላችን ንግስት፤ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነች፤ ክብሯንና ምስጋናዋን ዘንዝረነው ልንጨርስ የማንችል፤ ለገባውና ላወደሳት ጣዕሟ ወደር የሌለው፤ የሀጥአን አማላጅ፤ የሰው ልጆች የመዳናችን ተስፋ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አማልዳ፤
የእናት ልመና ፊት አያስመልስ
አንገት አያስቀልስ ነውና ቸርነቱ በቃላት ሊገለጽ የማይቻለው እግዚአብሔርም ልመናዋን ተቀብሎ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ። የእመቤታችንም ዘርፋፋ ቀሚሷ ከክፉ መቅሰፍት ሁሉ ይከልለን አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ //

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement

27/05/2023

አብሰራ ገብርኤል
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ/2/ ትወልዲ ወልድ
ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሐ
ትርጉም
ገብርኤል ማርያምን አበሰራት አበሰራት
ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ አላት
ሚካኤል መልዓክ በክንፋ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንፅህት ናትና በድንግልና/2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ-----
አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር
በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር
ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት
እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት

ንፅህት ናትና በድንግልና/2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ-----
እግዚአብሔር የላከው የከበረው መልዐክ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ
በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ
የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ

ንፅህት ናትና በድንግልና/2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ-----
ደስተኛዪቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል
የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል
አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ
መድኃኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ

ንፅህት ናትና በድንግልና/2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አዝ-----
አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ
አንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ
ይኩነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ
ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ

ንፅህት ናትና በድንግልና/2/
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና

🙏 የተዋህዶ ልጆች በቴሌግራም መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ስብከቶችን፣ ዝማሬዎችን፣ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ! እንዲሁም የክርስቶስን አምላክነት፤ የእናታችን የወላዲተ አምላክ የድንግል ማርያምን አማላጅነት፤ የቅዱሳን ገድላቸዉን፣ ተዓምራታቸውን፣ ክብራቸውን እና አማላጅነታቸዉን እንሰብካለን እንመሰክርበታለን።
እንዲሁም ስለእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዙሪያ እንማማራለን፤
ጠላትን በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ድል እናደርገው ዘንድ እናንተም የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ 🙏
!
አሜን🙏🙏🙏

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ //

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇👇
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement

20/05/2023

በሰማይ ሰልፍ ሆነ ውጊያው ተጀመረ
በሚከኤል ነገድ ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በአይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
ዳቢሎስ አልቻለም ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳለም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው አይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን አይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ

ቅዱስ ሚካኤል ከሚመጣብን ክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን🙏

🙏 የተዋህዶ ልጆች በቴሌግራም መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ስብከቶችን፣ ዝማሬዎችን፣ እንለቃለን። እንዲሁም የክርስቶስን አምላክነት እንሰብካለን፤ የእናታችን የቅድስተ ቅድስት የወላዲተ አምላክ የድንግል ማርያምን አማላጅነት፤ የቅዱሳን ገድላቸዉን፣ ተዓምራታቸውን፣ ክብራቸውን እና አማላጅነታቸዉን እንመሰክርበታለን።
እንዲሁም ስለእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዙሪያ እንማማራለን፤
ጠላትን በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ድል እናደርገው ዘንድ እናንተም የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ 🙏
!
አሜን🙏🙏🙏

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ // 🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
JOIN 👉 Tewahdo Group ✍️ t.me/GafatAdvretisement

Photos from ናትናኤል ታምሩ ፔጅ- Natnael Tamiru Page's post 20/05/2023

ግንቦት 12 ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ገዳም

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በፎገራ ወረዳ ገናና ታሪክና ሥም ካላቸው መንፈሳዊ የጉብኝት መዳረሻዎች ደሴተ ጓንጉት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ገዳም ከቀዳሚዎቹ አንዷ ናት

ገዳሟ ከወረዳው ዋና ከተማ ወረታ ወደ ባህርዳር በሚወስደው ዋና መንገድ 4 ኪሎሜትር እንደተጓዝን በኋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ታጥፈን 21 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከጣና ሃይቅ በሥተምስራቅ አቅጣጫ ተራራማ በሆነ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ላይ የተመሰረተች በሀገራችን፣ በክልላችን፣ በዞናችን ብሎም በወረዳው ቀደምት ታሪክ ካላቸው መካነ ቅርሶች ውስጥ አንዷ ናት።

እናታችን ቅደስት ክርስቶስ ሠምራ በአማራ ክልል በሠሜን ሸዋ ዞን በቡልጋ ቅዱስጊ በተባለ ቦታ በ848 ዓ.ም ተወለደች፡፡

መፅሀፍ ብሉይን እና ሐዲስን ተምራ እንደጨረሰች እድሜዋ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ በቤተክርስቲያን ዶግማ መሠረት ከቄስ ሠምረ ጊዮርጊስ ጋር በትዳር ተጣመሩ ትዳራቸውም ፍሬ አፍርቶ 10 ወንድ ልጆችን እና 2 ሴት ልጆችን በድምሩ 12 ልጆችን ወልደው በሥርዓት አሣድገዋል።

በኋላም ዙሮ ዙሮ ከቤት ኑሮ ኑሮ ወደ መሬት ነው እና ባለቤቷ ቄስ ሠምረ ጊዮርጊስ በሞት ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ ከዚህ በኋላ ዓለም በቃኝ በማለት የምናኔውን ጉዞ በደቡብ ወሎ ዞን በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳምና በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ7 ዓመታት ደግሞ በባህር ውስጥ ሥጋዋ አልቆ አጥንቷ እስኪታይና አሣ እስከሚሾልክባት ድረስ በድምሩ ለ39 ዓመታት የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ የኑሮ ጣጣ በመተው መንፈሳዊ ተጋድሎን ፈፅማለች።

በምድርም ላይ ለ375 ዓመታት ያህል በህይወት ኑራልች፡፡ በገዳሟ ለ24 ዓመት ቆይታለች፡፡

ገዳሟ የተመሰረተችው በአፄ ገብረ መስቀል /በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት በ1223 ዓ.ም እንደሆነ ገድለ ክርስቶስ ሰምራ በአፀደ ነፍስ /በህይወት/ እያለች እንደሆነ ገድሏ ላይ የተፃፈው መረጃ ያሥረዳል።

በክርስቶስ ሠምራ ገዳም አካባቢ የሚገኙ ዘመን ያስቆጠሩ ገዳማት
✅ ቅድስተ ሃና
✅ ጣና ቂርቆስ
✅ ቅዱስ ያሬድ
✅ ገዳመ ሥላሴ
✅ ገዳመ ፅዮን
✅ ገዳመ ቅድስት ቁስቋም
✅ ቅዱስ ፋሲለደስ
✅ ሪማ መድኃኒዓለም
✅ ናርጋ ሥላሴ፣ ዳጋ እስጢፋኖስና ሌሎችም ታሪካዊ ቅርሶች፣ አስደናቂ መልካም ምድራዊ ውብና አይጠገቤው የጣና ዳርቻ ልዩ ልዩ አዕዋፋት፣ ባህላዊ የአካባቢው አኗኗር ወደ ሥፍራው የሚጓዙ ሰዎች እግር መንገዳቸውን የሚመለከቷቸው ታሪካዊ ሥፍራዎች የክርስቶስ ሠምራ ገዳም ከመንፈሳዊ ቱሪዝም ባሻገር የሀገር ውስጥ ቱሪዝም መገለጫ እንዲሆን አድርጓታል።

የክርስቶስ ሠምራ ገዳም የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አፅመ ቅዱሣኗ ያረፈበት፣ ለክብሯ ከሰማይ የወረዱላት 7 አክሊሎች እና ፅዋ እንዲሁም ቁማ የፀለየችበት በትረ መስቀል ይገኛሉ።

በየአመቱ ግንቦት 12 እና ነሐሴ 24 ቀን በልዩ ሁኔታ የንግስና በዓሉ ይከበራል፡፡ ከ792 አመታት በላይ ግንቦት 12 እና ነሐሴ 24 ቀን የንግስና በአሉ በልዩ ሁኔታ ሲከበር ኖሯል።

ለበአሉ ድምቀት ደግሞ ከመልካም አጋጣሚዎች መካከል ገዳሟ ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ባለቤት ከመሆኗም በላይ የባህር ትራንስፖርት እንዲሁም ገዳሟ ለባህርዳር እና ለጎንደር አየር ማረፊያዎች በቅርብ ዕርቀት ላይ የምትገኝ በመሆኗ የአየር ትራንስፖርትን በመጠቀም ከመላው ኢትዮጵያ በተለይም ለግንቦት 12 ቀን የንግስና በዓል በብዙ መቶ ሽዎች
የሚቆጠሩ ምዕመናን ወይም መንፈሳዊ ተጓዥዎች ወደ ስፍራው ይመጣሉ።

ከአራቱም አቅጣጫ ለሚመጡ ተጓዦች ወይም ምዕመናን ለሚመጡባቸው ልዩ ልዩ መኪናዎች በመቆሚያነት የሚያገለግል የተንጣለለ የመኪና ማቆሚያ /ፓርኪንግ/ ሜዳ አላት።

በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ተጓዥዎች የሚታደሙበት የክርስቶስ ሠምራ የንግስና በዓል በአንድ ጉዞ በርካታ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ መዳረሻዎች የሚጎበኙበት መልካም አጋጣሚ ነው።

በመሆኑም በዓሉ በዛሬው ዕለት ማለትም ግንቦት 12, 2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

ግንቦት 12 ክርስቶስ ሰምራ ገዳም አይቀርም።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👇
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ // 🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement

Photos from ናትናኤል ታምሩ ፔጅ- Natnael Tamiru Page's post 19/05/2023

የማዳበሪያ ነገር…!

"…በዐማራ ወፍ የለም። የዐማራ ገበሬ በገንዘብም አያገኝ። ያውም በውድ። ስልቡ ብአዴን ደንታው አይደለም። የዐማራ ገበሬ ለምን ድንጋይ አይበላም። ኬሬዳሽ ነው ብአዴን።

• በኦሮሚያስ…?

"…በኦሮሚያ ሸኔ በሌለበት አካባቢ ማዳበሪያ በኩንታል ርካሽ ነው። ካነሳቸው ዐማራ በ2ሺ ብር የገዛውን ከዐማራ መልሰው ወስደው በ4 መቶ ብር ሁላ ይሸጡለታል። ሸኔ ባለበት ቦታስ ደግሞ ኦሮሞ ነኝ ያለውን ገበሬ በሙሉ ይሰበስባል። ከዚያ "እናንተ መሃል ዐማራ አለ ?" ብሎ ይጠይቃል? አዎ አለ ካሉ ዐማራውን ድራሽ አባክ ይጥፋ ብለው ያባርሩታል። ከዚያ የማዳበሪያ መጋዘኑ ይሰበራል። ኦሮሞ ነኝ ያለ ሁሉ ማዳበሪያውን በነፃ ይከፋፈለዋል።

"…በኢትዮጵያ ገንዘብ፣ በዐማራ ገበሬ ግብር ማዳበሪያው ይገዛል። በነፃ ለኦሮሞ ገበሬ በሲስተም ይከፋፈላል። የ4 ኪሎው ሸኔ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ መንጋውን ያደነዝዛል።

"…በነገራችን ታች ልክ እንደ ማዳበሪያው የሸኔ ደሞዝም የሚከፈለው በዚሁ ዘዴ ነው። ሸኔ የደሞዙ ሰዓት ሲደርስ ለ4ኪሎው ሸኔ ያሳውቃል። የ4 ኪሎው ሸኔ ለንግድ ባንኩ ሸኔ መመሪያ ያወርዳል። የንግድ ባንኩ ሸኔ የጫካው ሸኔ ወደሚገኝበት ቅርንጫፍ ባንኮች በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያከማቻል። ከዚያ የመከላከያና የፌደራል ፖሊሱ ሸኔ ብሩ ባንክ መግባቱን ሲያረጋግጥ አካባቢውን ለቆ ይወጣል። ይህን ጊዜ የጫካው ሸኔ ወደ ከተማ ገብቶ ከ4ኪሎው ሸኔ የተከለትን ደሞዝ በዘረፋ ስም ይረከባል።

"…የበሻሻው አራዳ ይሄን የጠነባ፣ የሸተተ፣ ጊዜ ያለፈበት አራድነት ሲጫወት የባህርዳር የጣና ዳሩ በድኑ ብአዴን የዐማራን ገበሬ ከፋኖ ጋር ተዋጋ እያለ እንቅልፍ አጥቶ ይዞራል። ወያኔ እንኳ በአቅሟ ወልቃይት ያላችሁ ገበሬዎች ማዳበሪያ ከፈለጋችሁ ሽሬ ኑና ውሰዱ አላለችም…😂

• ዐማራ…! ማዳበሪያ ነው? …ኤለም።
በዘመድኩን በቀለ

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 t.me/GafatStudio

Photos from ናትናኤል ታምሩ ፔጅ- Natnael Tamiru Page's post 19/05/2023

ወር በገባ በ11 የአባታችን የአቡነ ሐራን ድንግል ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

አምስት መነኮሳት ከአባታችን ሐራ ድንግል ገዳም ወደ ዳውንት ወደ ሚባል ሀገር ሄዱ እነርሱም ለምግባቸውና ለልብሳቸው የሚሆናቸውን ገንዘብ ከሀገሩ ሰዎች ይለምኑ ዘንድ ወደ ዳውንት ደረሱ፡፡
ወደዚያም በደረሱ ጊዜ በድንገተኛ በሽታ የታመመ አንድ ሰውና በከብት በሽታ የታመመ አንድ በሬ አገኙ የሀገሩ ሰዎችም እነዚያን መነኮሳያት በሀገራችን ሁለት በሽተኞች አሉ አንዱ ሰው ነው አንዱም በሬ ነው ለእነዚህ መድኃኒት የሚሆናቸው ምንድነው አሏቸው፡፡
መነኮሳያቱም ለጠየቋቸው ሰዎች የአባታችን ሐራ ድንግል ከሚሉት ከጻድቁ አባታችን መቃብር ያመጣነው አፈር አለ ሁለቱንም እንቀባቸዋለን አሏቸው፡፡
የሀገሩ ሰዎችም እናንተ እንዳላችሁ ይሁን አሏቸው ወዲያውም ሰውየውንም በሬውንም ቀቧቸው ሁለቱም በአባታችን ሐራ ድንግል የረድኤት ኃይል ከደዌያቸው ተፈወሱ፡፡

በገዳመ ወንያተ አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም አሁንም ድረስ በህመም ለሚሰቃዩ ፀበሉን እየተጠመቁ፣ እምነቱን እየተቀቡ፣ የበረከት ስራን እየሰሩ ፃድቁን በማመን ከህመማቸው እየተፈወሱ ፃድቁን ለማመስገን በቅተዋል።
የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሐራ ድንግል ጸሎታቸው በረከታቸው ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ // 🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
✍️Group 👉 t.me/GafatAdvretisement

15/05/2023

አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ስላሴ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ነው

እንኳን አደረሳችሁ!! 🙏🙏🙏



#ሰለሰ ~ ወይም ሶስት (3) ማለት ነው።



፦ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው።

➠ ፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው።

➠ ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ _ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም።
( "ዘፍጥረት1፡ 2 " | "ምሳሌ 30፡4")

➠ ፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው።

#እነርሱም ፦
➠ #መውለድና - ማስረጽ የአብ
➠ #መወለድ - የወልድ
➠ #መስረጽ - የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ።
("መዝሙር2፡7")

➠ ማለት ደግሞ
#ለአብ - ፍፁም መልክ፣ ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም አካል አለው።

#ለወልድ - ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

- ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።
-የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም

#አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤ የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።

#ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው።
("መዝሙር2፡7")

#መንፈስ ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ፣ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። ("ኢዮብ 26፡13")

የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከታቸው ከሁላችንም የተዋህዶ ልጆች ጋር ለዘለዓለሙ አይለየን አሜን🙏🙏🙏

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መንፈሳዊ ትምህርት፣ ስብከት፣ ዝማሬ እና የተለያዩ ለህይወታችን አስተማሪ የሆኑ ቪዲዮዎች የሚተላለፉበትን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ በማድረግ አገልግሎታችንንን እንዲሰፋ ያግዙን ይተባበሩን ቤተሰባችን ይሁኑ!🙏🙏🙏

ዩቲዩብ ቻናል➠ https://youtube.com/

ቴሌግራም ቻናል ➠ t.me/GafatStudio

ፌስቡክ ፔጅ ➠ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063708640109

14/05/2023

✝️ግንቦት (6) ቅድስት አርሴማ🙏🙏

#አርሴማ ማለት :-በወርቅ ልብሶች የተጎናፀፈች ፣ የተሸለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነዉ!

#በዘንባባሽ ባርኪኝ እናቴ🤲🤲🤲🤲

#ቅድስት አርሴማ

በሰላም እመለሳለው
በግሮቸ ቁሜ ሄዳለው
ጠላቴ አታስፈራኝም
አርሴማ አታስነካኝም

#አዝ

ስሟን ጠርቼ የእናቴን
ለሷ ሳማክር የጭቀቴን
በእምነት ፀበሏ ታብሰኛለች
ከአልጋዬ ላይ ታነሳኛለች
#አዝ

እማፀናለሁ ደጇ መጥቼ
እፈወሳለው ፀበል ጠጥቼ
የጠላት ዛቻ አያስፈራኝም
የወረወረው ጦር አይነካኝም
#አዝ

አልጋዬን ልያዝ ልሸከመው
ያለፈ ዘመን ታሪኬ ነው
ከበሽታዬ ዛሬ ድኛለው
አርሴማ ብዬ ተፈውሻለው
#አዝ

ከወደኩበት ቀርቶ መድከሜ
ተመልክቻለው ታብሷል ደሜ
እግሮቸ ፀንተው ይራመዳሉ
ከናፍሮቸ አርሴማ እያሉ
👏👏👏👏👏👏 💒

#ቅድስት አርሴማ ሰማእትነትን የተቀበለችበት እለት ነው ለአምላካችን መስእዋት እስከመሆን ድረስ መታመንን ከቅድስት አርሴማ ልንማርና እኛም መስእዋት እስከመሆን ለማህተባችን ልንታመን ይገባል!!!!

የቅድስት አርሴማ አማላጅነት አይለየን🙏✝️🙏

➠ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ስብከት፣ ዝማሬ እና የተለያዩ ለህይወታችን አስተማሪ የሆነ ቪዲዮዎች የሚተላለፉበትን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ በማድረግ አገልግሎታችንንን እንዲሰፋ ያግዙን ይተባበሩን ቤተሰባችን ይሁኑ!🙏🙏🙏

ዩቲዩብ ቻናል➠ https://youtube.com/

ቴሌግራም ቻናል ➠ t.me/GafatStudio

ፌስቡክ ፔጅ ➠ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063708640109

26/04/2023

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች አንድ ጊዜ አዳምጡኝ።
በኢትዮጵያ ደረጃ በፌስቡክ ኮሜንት እና የተዋህዶ ቻናል ሪከርድ ለመስበር አስበናል! እርሱም ኮሜንት ላይ #ማርያም የሚለውን ጣፋጭ ስም በመፃፍ እና የተዋህዶ ቻናሉን በመቀላቀል ነው ።
ጀምሩ 🙏
➣ ከስር ያለውን የተዋህዶ ቻናል በማድረግ🙏
➣ ላይክ // LIKE በማድረግ 🙏
➣ ኮሜንት ላይ ጣፋጭ የሆነውን የማርያምን ስም በመፃፍ🙏
የተዋህዶ ቻናሉ ሊንክ 👇👇👇 🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች 👇
➢ ሼር // SHARE በማድረግ 🙏
➣ #የፔጁ አባል በመሆን 🙏
➣ ላይክ // LIKE በማድረግ 🙏
‼️ ➣ #የሚቃጠል ይቃጠል 😎

13/04/2023

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች አንድ ጊዜ አዳምጡኝ።
በኢትዮጵያ ደረጃ በፌስቡክ ኮሜንት ሪከርድ ለመስበር አስበናል! እርሱም ኮሜንት ላይ #ማርያም የሚለውን ጣፋጭ ስም በመፃፍ።
ጀምሩ 🙏
➣ ከስር ያለውን ሊንኩ ተጭነው የፔጁ አባል በመሆን 🙏
➣ ላይክ // LIKE በማድረግ 🙏
➣ ኮሜንት ላይ የማርያምን ስም በመፃፍ 🙏 🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸🔹🔸 t.me/GafatStudio 🔸🔹🔸
🔸 t.me/GafatStudio 🔸
🔸 🔸
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች 👇
➢ ሼር // SHARE በማድረግ 🙏
➣ ላይክ // LIKE በማድረግ 🙏
✍️ ➣ #የፔጁ አባል በመሆን 🙏
‼️ ➣ #የሚቃጠል ይቃጠል 😎

ሊቀ መዘምራን ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ በባህርዳር መስቀል አደባባይ_-_ ሆሳዕና በአርያም_-_ ድንቅ ዝማሬ 10/04/2023

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በባህርዳር መስቀል አደባባይ በሆሳዕና ዕለት በብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም መሪነት በተካሄደው እጅግ ደማቁ ጉባኤ ላይ ያቀረበው ድንቅ ዝማሬ
ሙሉ ቪዲዮ ➠

ሊቀ መዘምራን ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ በባህርዳር መስቀል አደባባይ_-_ ሆሳዕና በአርያም_-_ ድንቅ ዝማሬ

18/12/2022

ወይ ጉድ በማርያም አድምጡት 🙏

03/12/2022

ኦርቶዶክሳዊያን ከነዚህ 4ቱ ሀጢያቶች ተጠንቀቁ ያጠፋሉና!???
በርዕሰ ሊቃውንት በአባ ገብረኪዳን ግርማ | ሁሉም በየቀኑ ሊሰማው የሚገባ እጅግ ጥዑም የሆነ ትምህርት
ሙሉ ቪዲዮ 👉https://youtu.be/ZYUSkoOJki8

በቴሌግራም ለመከታተል US 👉 t.me/GafatStudio

25/11/2022

የሰው ልጅ ሀጢያት የሚሰራው ለምን ይመስላችኋል!? _-_ ዋጋዋ ብዙ የሆነች እንቁ _ ኦርቶዶክሳዊያን ሁልጊዜ በኑሯችሁ ይህን አድርጉ በርዕሰ ሊቃውንት በአባ ገብረኪዳን ግርማ _ ግሩም የሆነ ስብከት 👉 https://youtu.be/AYMsVLeRrXo

በቴሌግራም ለመከታተል 👉 https://t.me/gafatstudio/1718

21/11/2022

እየሱስ ያለው ጭፈራ ቤት ነው? ህጿኗን አዳምጧት

18/11/2022
17/11/2022

በማርያም ይህንን ቪዲዮ አይታችሁ #ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏





ማለት ❤❤❤

አገዳደልም እኮ ወግ አለው 😭 ህዝቡ በሙሉ አለቀሰ _ እስከመቼ ድረስ _ #ድንቅልጆች ጦቢያ Ethiopian New[ Seifu On Ebs] Donkey Tube 13/11/2022

https://youtu.be/jkyuD-K1LVw

አገዳደልም እኮ ወግ አለው 😭 ህዝቡ በሙሉ አለቀሰ _ እስከመቼ ድረስ _ #ድንቅልጆች ጦቢያ Ethiopian New[ Seifu On Ebs] Donkey Tube ለዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ በመሉ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏 'ው ከተመቻችሁ ካልተመቻችሁ እንዲሁም 'ው ለሌሎች ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ #...

ልብ የሚነካ ድንቅ የሆነ ትምህርት ሁሉም ሊሰማው የሚገባ ስብከት በመምህር ኢዮብ 12/11/2022

ህዝቡን በእንባ ያራጬው ስብከት ልብ የሚነካ ድንቅ የሆነ ትምህርት ሁሉም ሊሰማው የሚገባ _-_ | በመምህር ኢዮብ ይመኑ

ሙሉ ቪዲዮ 👉

ልብ የሚነካ ድንቅ የሆነ ትምህርት ሁሉም ሊሰማው የሚገባ ስብከት በመምህር ኢዮብ ለዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ በመሉ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏 'ው ከተመቻችሁ ካልተመቻችሁ እንዲሁም 'ው ለሌሎች ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ #...

በአርቲስቶች የታጀበው እጅግ ደማቁ ዝማሬ በቦሌ ሰማት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን | መታየት ያለበት ድንቅ ዝማሬ 07/11/2022

በአርቲስቶች የታጀበው እጅግ ደማቁ ዝማሬ [ በ27 ] በቦሌ ሰሚት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን _-_ | ሁሉም ሊመለከተው የሚገባ ድንቅ ዝማሬ 👉

በአርቲስቶች የታጀበው እጅግ ደማቁ ዝማሬ በቦሌ ሰማት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን | መታየት ያለበት ድንቅ ዝማሬ ለዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ በመሉ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏 'ው ከተመቻችሁ ካልተመቻችሁ እንዲሁም 'ው ለሌሎች ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ #...

ገንዘብህን በከንቱ አታባክን! ህሊና ይኑራችሁ የሰው ልጅ መቼ ነው ፈጣሪውን የሚያውቀው? ግሩም ትምህርት በአባ ገብረኪዳን ግርማ #ቴቄል #ድንቅልጆች #video 01/11/2022

ገንዘብህን በከንቱ አታባክን _-_ ለዚህ ትውልድ ትልቅ አስተምህሮ _ | በአባ ገብረኪዳን ግርማ | እጅግ የሚገርም ልዩ ስብከት 👉

ገንዘብህን በከንቱ አታባክን! ህሊና ይኑራችሁ የሰው ልጅ መቼ ነው ፈጣሪውን የሚያውቀው? ግሩም ትምህርት በአባ ገብረኪዳን ግርማ #ቴቄል #ድንቅልጆች #video ለዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ በመሉ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏 'ው ከተመቻችሁ ካልተመቻችሁ እንዲሁም 'ው ለሌሎች ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ #...

24/10/2022

ልብ የሚነካ ምዕመኑ በእንባ የተሞሉበት ድንቅ ስብከት ሁሉም ሊሰማው የሚገባ ስብከት 👉
https://youtu.be/PhLQs6NC4y0

Videos (show all)

ወይ ጉድ በማርያም አድምጡት 🙏
እየሱስ ያለው ጭፈራ ቤት ነው? ህጿኗን አዳምጧት
በማርያም ይህንን ቪዲዮ አይታችሁ #ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏ተዋህዶማለት ❤❤❤
Subscribe For 👉 [Gafat Studio - ጋፋት ስቱዲዮ]   YouTube 👉 https://youtube.com/channel/UCDyU3JEPFmMGjc31oE2JSRg?Sub_Confirmat...

Telephone