Sidama News Network /SNN/

Sidama News Network /SNN/

Tefera K Keta󱢏

11/04/2024
07/03/2024

ማስታወቂያ
በሲዳማ የእርቅና የዳኝነት ስርዓት ላይ ያተኮረው እና በሀገራችን እውቅ ተዋንያን ተሳትፎ የተሰራው የአፊኒ ፊልም ተመርቆ እነሆ ለእይታ ቀርቧል፡፡
በሲዳማ ባህል ቱርዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት እና በዘታሪያን ፕሮዳክሽን የተሰራው የአፊኒ ፊልም ቅዳሜ የካቲት 30 / 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እንዲሁም በድጋሚ 10፡00 ላይ በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ ለእይታ ይቀርባል፡፡ በዚሁ እለት በሲዳማ ቡና አቅራቢ ገበሬዎች ዩኒየን ህንፃ ጎን እና በሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በኩል ባሉት የሚሊኒየም አዳራሽ መግቢያ በሮች ቀደም ብለው በመገኘት እና የመግቢያ ቲኬት በ300 ብር በመግዛት ይህን ተወዳጅ ፊልም ኢንዲመለከቱ የሲዳማ ልማት ማህበር በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ማሳሰቢያ፡
ፊልሙን ለመመልከት ሲመጡ ማንኛውም አይነት የሞባይል ስልክ ፣ ካሜራ ፤ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት እንዲሁም የድምፅ መቅረጫና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዘው እንዳይመጡ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
ይህን ምርጥ ፊልም እንዲመለከቱ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡ እንዳያመልጥዎ !

የካቲት 30 / 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እንዲሁም 10፡30 ላይ በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ

06/03/2024

767 የቤተሰብ ብልጽግና ኢኒሼቲቭ በሲዳማ ክልል !
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ክልላችን በተጀመረው ወል ብልጽግና ጎን ለጎን የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በ7 ኢኒሼቲቭ የታቀፈ 67 ፓከጆችን የያዘ፤የቤተሰብ ብልጽግና ኢኒሼቲቭን ይፋ አድርጓል ። በክልሉ ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ሀሳብ አፍላቂነት ታቅደው ይፋ የሆነውና አንዳንድ ግዜ የፕሬዝዳንቱ ኢኒሼቲቭ ተብሎ የሚጠራው ይህ ኢኒሼቲቭ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ ታምኖበታል።
የኢኒሸቲቭ ዝርዝር

1.የእርሻ ኢኒሼቲቭ በውስጡ 19 ፓኬጆችን የያዘ

2.የእንስሳት ሀብት ኢኒሼቲቭ በውስጡ 7 ፓኬጆችን የያዘ

3.የቱሪዝም ኢኒሼቲቭ በውስጡ 7 ፓኬጆችን የያዘ

4.የትህምርትና ሙያ ኢኒሼቲቭ በውስጡ 9 ፓኬጆችን የያዘ

5.የማሕበረሰብ እና የአከባቢ ንጽህና ኢኒሼቲቭ በውስጡ 4 ፓኬጆችን የያዘ

6.ኢንዱስትሪ ኢኒሼቲቭ በውስጡ 17 ፓኬጆችን የያዘ

7.የሲዳማ ቻሪቲ ኢኒሼቲቭ በውስጡ 4 ፓኬጆችን የያዘ ኢኒሼቲቭ ሲሆኑ ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

767 Family Prosperity Initiative in Sidama Region!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Our region has announced the Family Prosperity Initiative, which contains 67 packages that are comprised of 7 initiatives to ensure family prosperity alongside the general prosperity that was started. He believed that this initiative, which was planned and announced by the president of the region, Mr. Desta Ledamo, and is sometimes called the President's Initiative, is crucial to ensuring family prosperity.
List of initiatives
1. Farm Initiative which contains 19 packages
2. Livestock Initiative which contains 7 packages
3. Tourism Initiative which contains 7 packages
4. Education and Career Initiative which contains 9 packages
5. Community and Environmental Cleanliness Initiative containing 4 packages
6.Industry Initiative which contains 17 packages

7. The Sidama Charity Initiative is an initiative that contains 4 packages and training is being provided from leaders to professionals to implement it.

03/03/2024

አንድ መቶ ሀያ ሶስት ዜጎችን ያስተማሩት ፤ እጅግ የተከበሩት የሲዳማ የሀገር ሽማግሌ አቶ ደዩ መሌሎ የ80ኛ ቀን መታሰቢያ እና የሀውልት ምርቃት ስነ ስርዓት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ። ..
የአቶ ደዩ መሌሎ ሸራኮ አጭር የህይወት ታሪክ

የአቶ ደዩ መሌሎ ሸራኮ በቀድሞው አጠራር በሲዳሞ ክ/ሃገር በዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ ልዩ መጠሪያዉ ራሳ በሚባል ቦታ ከአባታቸው ከአቶ መሌሎ ሽራኮ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዶሮቴ ሀውጤ በ1946ዓ/ም ተወለዱ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ገመጦ ጋሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በሐዋሳ ፊላደለፊያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ደግሞ ታቦር እንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲከታተሉ ቆይተው በወቅቱ በቤተሰባቸው ከነበረባቸው የኑሮ ጫና አንጻር ትምህርታቸውን አቋርጠው አነስተኛ የንግድ ስራ ጀመሩ ፡፡

አቶ ደዩ በ1972 ዓ/ም ትዳር መስርተው ዘጠኝ ወንድ እና አስራ አንድ ሴት ልጆችን አፍርተው አርባ የልጅ ልጆችን አይተዋል፡፡ አቶ ደዩ በተለይ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን በህክምና ዶክትሬት ፣ አንድ ሴት ልጃቸውን ውጪ በመላክ እያስተማሩ የሚገኙ እንዲሁም ስምንት ልጆችን በዲግሪ ያስመረቁ እና ከልጆቻቸው በተጨማሪ ከዛየን ኮሌጅ ሀዋሳ ጋር በመነጋገር ከፍለው መማር ላልቻሉ አንድ መቶ ሃያ ሦስት ዜጎች በዲግሪና በዲፕሎማ አስተምረዋል፡፡

አቶ ዴዩ መሌሎ የጀመሩትን የንግድ ስራ እየሰሩ ጎን ለጎን በ1966ዓ/ም በደርግ አገዛዝ በለውጡ መንግስት መሬት ላራሹ የሚል አዋጅ ሲታዎጅ በቀበሌ በዋና ጸሐፊነት በመመረጥ በፍትሃዊነት መሬት ለእርሶ አደሮች ሲታደል ከፍተኛ አበርክቶ የነበራቸው ትጉህ እና ታማኝ አባት ነበሩ፡፡ ከቀበሌ አመራርነት ጎን ለጎንም በእርሻ ልማት ድርጅት ተቀጥረው ካላቸው ታማኝነትና ታታሪነት የተነሳ በሃላፊነት ሰራተኞችን በመልካም ስነ ምግባር ያገለገሉ ፤ በሰው ዘንድም ትልክ ይሁንታና አክብሮት የነበራቸው ጀግና የሲዳማ ልጅ ነበሩ ፡፡

አልፎ አልፎ በሲዳማና በአጎራባች አካባቢዎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ፤ የተጣሉትን በማስታረቅ ከፍተኛ የሀገር ሽማግሌነት ድርሻቸውን የተወጡ ኩሩ አባት ነበሩ፡፡ አቶ ደዩ በአካባቢያቸው ውስጥም ሆነ በሲዳማ አጠቃላይ በተለያዩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ጉዳዩች ዘንድም ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ለበርካታ ግለሰቦችም ዋርካና መጠለያ የነበሩ ፤ ለምስኪኖችና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ የሚያደርጉ ፣ ለአካባቢ ልማት ከፍተኛ አበርክቶ የሚያደርጉ አባት ነበሩ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩል ዓይን የሚያዩ ትልቅ የአካባቢው ባለውለታ ነበሩ፡፡ ከመንግስት የሚወርዱ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችንም ተቀብለው ህዝብን ከማሳመን ረገድም ከህዝብና ከመንግስት ትልቅ አመኔታን ያተረፉ ጀግና አባት ነበሩ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ በግብርና ስራ ዘርፍ በመሰማራት በታታሪነትና በሞዴል አርሶአደርነት የሚታወቁ በክልልና በሀገርአቀፍ ደረጃ ከከፍተኛ አመራሮች እጅም በተለያዩ ጊዜያት በግንባር ቀደምትነት ሜዳሊያና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላችዋል፡፡

አቶ ደዩ የሲዳማ ባህልና ወግ እንዲሁም ስርዓት እንዲዳብር ካላቸው ቁርጠኝንት የተነሳ ባህላዊ የዳኝነት ቦታ ጉዱማሌ በማስጠበቅ እና ባህላዊ የዳኝነት ቤት በሀዌላ ወሜ ቡናሞ በማስገንባት ትልቅ አበርክቶ ያደረጉና ተወልደው ባደጉበት በዳቶ ኦዳሄም ደረጃውን የጠበቀ የዳኝነት ስፍራ ለመገንባት የሀገር ሽማግሌዎችንና ህዝቡን በማስተባበር ላይ እያሉ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ70 ዓመታቸው ህዳር 23 ቀን 2016ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የ80ኛ ቀን መታሰቢያቸው ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016ዓ/ም በሀዋሳ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስተያን የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት የመታሰቢያ ሀውልታቸው ተመርቋል።

03/03/2024

አንድ መቶ ሀያ ሶስት ዜጎችን ያስተማሩት ፤ እጅግ የተከበሩት የሲዳማ የሀገር ሽማግሌ አቶ ደዩ መሌሎ የ80ኛ ቀን መታሰቢያ እና የሀውልት ምርቃት ስነ ስርዓት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ። ..
የአቶ ደዩ መሌሎ ሸራኮ አጭር የህይወት ታሪክ

የአቶ ደዩ መሌሎ ሸራኮ በቀድሞው አጠራር በሲዳሞ ክ/ሃገር በዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ ልዩ መጠሪያዉ ራሳ በሚባል ቦታ ከአባታቸው ከአቶ መሌሎ ሽራኮ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዶሮቴ ሀውጤ በ1946ዓ/ም ተወለዱ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ገመጦ ጋሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በሐዋሳ ፊላደለፊያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ደግሞ ታቦር እንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲከታተሉ ቆይተው በወቅቱ በቤተሰባቸው ከነበረባቸው የኑሮ ጫና አንጻር ትምህርታቸውን አቋርጠው አነስተኛ የንግድ ስራ ጀመሩ ፡፡

አቶ ደዩ በ1972 ዓ/ም ትዳር መስርተው ዘጠኝ ወንድ እና አስራ አንድ ሴት ልጆችን አፍርተው አርባ የልጅ ልጆችን አይተዋል፡፡ አቶ ደዩ በተለይ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን በህክምና ዶክትሬት ፣ አንድ ሴት ልጃቸውን ውጪ በመላክ እያስተማሩ የሚገኙ እንዲሁም ስምንት ልጆችን በዲግሪ ያስመረቁ እና ከልጆቻቸው በተጨማሪ ከዛየን ኮሌጅ ሀዋሳ ጋር በመነጋገር ከፍለው መማር ላልቻሉ አንድ መቶ ሃያ ሦስት ዜጎች በዲግሪና በዲፕሎማ አስተምረዋል፡፡

አቶ ዴዩ መሌሎ የጀመሩትን የንግድ ስራ እየሰሩ ጎን ለጎን በ1966ዓ/ም በደርግ አገዛዝ በለውጡ መንግስት መሬት ላራሹ የሚል አዋጅ ሲታዎጅ በቀበሌ በዋና ጸሐፊነት በመመረጥ በፍትሃዊነት መሬት ለእርሶ አደሮች ሲታደል ከፍተኛ አበርክቶ የነበራቸው ትጉህ እና ታማኝ አባት ነበሩ፡፡ ከቀበሌ አመራርነት ጎን ለጎንም በእርሻ ልማት ድርጅት ተቀጥረው ካላቸው ታማኝነትና ታታሪነት የተነሳ በሃላፊነት ሰራተኞችን በመልካም ስነ ምግባር ያገለገሉ ፤ በሰው ዘንድም ትልክ ይሁንታና አክብሮት የነበራቸው ጀግና የሲዳማ ልጅ ነበሩ ፡፡

አልፎ አልፎ በሲዳማና በአጎራባች አካባቢዎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ፤ የተጣሉትን በማስታረቅ ከፍተኛ የሀገር ሽማግሌነት ድርሻቸውን የተወጡ ኩሩ አባት ነበሩ፡፡ አቶ ደዩ በአካባቢያቸው ውስጥም ሆነ በሲዳማ አጠቃላይ በተለያዩ ማህበራዊና ሰብዓዊ ጉዳዩች ዘንድም ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ለበርካታ ግለሰቦችም ዋርካና መጠለያ የነበሩ ፤ ለምስኪኖችና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ የሚያደርጉ ፣ ለአካባቢ ልማት ከፍተኛ አበርክቶ የሚያደርጉ አባት ነበሩ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩል ዓይን የሚያዩ ትልቅ የአካባቢው ባለውለታ ነበሩ፡፡ ከመንግስት የሚወርዱ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችንም ተቀብለው ህዝብን ከማሳመን ረገድም ከህዝብና ከመንግስት ትልቅ አመኔታን ያተረፉ ጀግና አባት ነበሩ፡፡

አቶ ደዩ መሌሎ በግብርና ስራ ዘርፍ በመሰማራት በታታሪነትና በሞዴል አርሶአደርነት የሚታወቁ በክልልና በሀገርአቀፍ ደረጃ ከከፍተኛ አመራሮች እጅም በተለያዩ ጊዜያት በግንባር ቀደምትነት ሜዳሊያና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላችዋል፡፡

አቶ ደዩ የሲዳማ ባህልና ወግ እንዲሁም ስርዓት እንዲዳብር ካላቸው ቁርጠኝንት የተነሳ ባህላዊ የዳኝነት ቦታ ጉዱማሌ በማስጠበቅ እና ባህላዊ የዳኝነት ቤት በሀዌላ ወሜ ቡናሞ በማስገንባት ትልቅ አበርክቶ ያደረጉና ተወልደው ባደጉበት በዳቶ ኦዳሄም ደረጃውን የጠበቀ የዳኝነት ስፍራ ለመገንባት የሀገር ሽማግሌዎችንና ህዝቡን በማስተባበር ላይ እያሉ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ70 ዓመታቸው ህዳር 23 ቀን 2016ዓ/ም

01/03/2024

የመላው ኢትዮጵያውያን ህብረትና አንድነት ፤ ቆራጥነትና ጀግንነት የታየበት፤ የጥቁር ህዝቦች ተጋድሎና አይበገሬነት በድል የተጠናቀቀበት ፤በባርነት ለሚማቅቁ ጥቁር ህዝቦች የነፃነትን መንገድ ለጠረገ የአድዋ ድል ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን፦አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

የመላው ኢትዮጵያውያን ህብረትና አንድነት፤ ቆራጥነትና ጀግንነት የታየበት፤የጥቁር ሕዝቦች ተጋድሎና አልበገሬነት በድል የተጠናቀቀበት፤ በባርነት ለሚማቅቁ ጥቁር ህዝቦች የነፃነትን መንገድ ለጠረገ ለ128ኛው የአድዋ ድል ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን ሲሉ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የአድዋ ድል የነጮች የበላይነትንና የቀኝ አገዛዝ ሥርዓትን የሚያቀነቅኑ ምዕራባዊያን ያሳፈረና ያስደነገጠ፤የኢትዮጵያ ሐገራችንን ልዕልና ያስጠበቀ፤የህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያ አንድነትና ጀግንነት የተንፀባረቀበት ፤ ፤የአፍሪካዊያንን የአሸናፊነት ስነ ልቦና ከፍ ያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

አውሮፖውያን የቀኝ አገዛዝ ፖሊሲያቸው ነድፎ አፍሪካን ሲቀራመቱ ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን በቀኝ አገዛዝ ቀንበር ለማንበርከክ ወረራ አካሄዶ አልተሳካላትም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም የሆነው አባቶቻችን ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው በአንድነትና በህብረት፤ በቆራጥነትና በጀግንነት ፤ባደረጉት ተጋድሎና በከፈሉት መስዋዕትነት ነው ብለዋል።

የአድዋ ድል በቀኝ አገዛዝ ሥርዓትና በባርነት ለሚማቅቁ አፍሪካዊያንና ጥቁር ህዝቦች ታግሎ ማሸነፍ እንደሚቻል ተስፋን እንዲሰንቁና ብሎም ለነፃነታቸው እንዲታገሉና አሽናፊነትን እንዲጎናፀፉ ያስቻለ ድል እንደሆነ አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናግረው ዛሬም ይህ ትውልድ ዘመናዊ የቀኝ አገዛዝ ሥርዓትን ማሸነፍ የሚችለው ድህነትንና ኋላቀርነትን አሸንፎ ሀገራችንን የብልፅግና ከፍታ ላይ ሲያሻግር ነው ብለዋል።

በበታችነትና በባርነት ለሚማቅቁ ጥቁር ህዝቦች ከተኙበት እንዲነሱ የአድዋ ድል የማንቂያ ደውል እንደሆነና የፓን አፍሪካኒዝም ፅንሰ ሀሳብ እንዲጎለብት መሠረት የጣለ እንደሆነም ተናግረዋል።

ዘንድሮ የመላውን የጥቁር አፍሪካዊያን ኩራትና ድምቀት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ተገንብቶ የተጠናቀቀና ለእይታ ክፍት የሆነውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህ የአድዋ ድል መታሰቢያ ለዘመናት የከፋፋይነትን አጀንዳ ይዘው ህዝብን ወደ ጥፋት ሲዘውሩ ለነበሩ የፀረ ሰላም ሃይሎች የአቅላይነት ትርክታቸውን ያከሰመና የህብረ ብሔራዊ አንድነት ወንድማማችነትን ፤ጥንካሬንና ድምቀትን ፤ፍቅርና ህብረትን የሚያገዝፍ መሆኑን ገልፆዋል።

አድዋ ሲታሰብ ህብረብሔራዊ አንድነትን ፥ ወንድማማችነትን፥ ህብረትን ፥ቆራጥነትን ፥ የአላማ ፅናትን ፥ጠንካራ ስነልቦናን ፥ ጀግንነትን ፥ድልና ድምቀትን ፥ነፃነትን፥ የያዙ ታሪካዊ አውዶች በመላው ኢትዮጵያዊያን ስነ ልቦና ውስጥ የሚታወሱ መሆኑን ገልፀው ይህም የማንነታችንን ክብርና ኩራት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነታችንን ሃያልነት በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ህያው ሆኖ እንዲኖር ያደርገዋል ብለዋል።

ስለዚህም በአድዋ ያገኘነውን ድልና አሸናፊነት አስቀጥለን ለትውልድ የምናሻግረውና የምንዘክረው የማንነታችን መገለጫ ታሪካዊ አውዳችን መሆናቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀው ድህነትን በስራና በቆራጥነት አሸንፈን ትውልዳችንን ወደ ብልፅግና ማማ ከፍ የምናደርግበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በድጋሚ ታሪካዊ የበላይነታችንን ላገዘፈ፤ ጀግንነታችንን ላደመቀ፤ ለመላው ጥቁር አፍሪካዊያን የነፃነት ትግል ፋና ወጊ ለሆነው ለ128ተኛ ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል !

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 21/02/2024

''ከኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ያገኘነውን ልምድ ተግባራዊ በማድረግ ከተማችንን በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ እናደርጋለን።''አቶ መኩሪያ ማርሻዬ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ

በዎላይታ ሶዶ በኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ውድድር ላይ እየተወዳደረች የሚትገኘው ውብቷ ሀዋሳ የብዙሀን ጎብኞች ምርጫ በመሆን በቀዳሚነት እየመራች ትገኛለች ።የአመቱ አሸናፊ ትሆናለች በማለት ብዙዎች በልበ ሙሉነት ግምታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ።

በቁርጠኝነትና የህዝብ ጥቅም ባማከለ መልኩ እየመሩ ያሉ የከተማ አመራሮችም እያመጡ ያሉ ለውጦች የሚደነቅ ነው።

መልካም ዕድል ለሀዋሳችን!

20/02/2024

የወይባ ጭስ (ቦለቅያ)

የወይባ ዛፍ በኢትዮዽያ ቆላማ አካባቢዎች ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ ተክል ነው። ወይባ ከሚበቅልባቸውና ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው አካባቢዎች ደግሞ ወሎ እና አፋር በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

የወይባ እንጨቶች ቦግ ብሎ የመንደድ ባህርይ የሌለው ዝግ እያለ የሚጨስና የጭሱ ሽታ ለአፍንጫ ጥሩ ስሜትን የሚሰጥ የእጽዋት ዓይነት ነው፡፡

የወይባ ጭስ ለቆዳ ጥራትና ውበት ተመራጭ ሲሆን ጭሱ የቅባትነት ባህርይ ስላለውና በሰውነት ላይ ስለሚጣበቅ ቆዳን በማሣመር የተለየ ውበትና ወዝ ያጎናጽፋል፡፡ የወይባ ጭስ በአብዛኛው ሴቶች የሚሞቁት ሲሆን የተለያዩ ሕመሞችን እንደሚፈውስ ተጠቃሚዎች ይገልፃሉ።

ወይባ የተለየ ባህላዊ የአሟሟቅ ዘዴ አለው።

መጀመሪያ ለወይባ መሞቂያ የሚሆን 50ሴ.ሜ ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ወይም "ቦለቅያ" ይቆፈርና ይዘጋጃል። ከዚያም በቦለቅያ ጉድጓዱ ወስጥ ወይባው ባጭር ባጭሩ ተከርክሞና ተፈልጦ ከገባ ቀኋላ በእሳት እንዲያያዝና እንዲጨስ ይደረጋል።

ጉድጓዱ ክብ ቅርፅ ያለውና ዳር ላይ የእግር መቀመጫ ይኖረዋል፤ ከጉድጓዱ ውጭ ደግሞ በአንድ በኩል መቀመጫ ያለውና በዙሪያው 50ሴ.ሜ አካባቢ ከፍታ ያለው ጭሱን ለማፈንና ለመደገፊያ እንዲያገለግል ሆኖ ይሰራል።

ከዚያም ጭሱ ሁሉንም የሰውነት ክፍል እንዲያገኝ ተስተካክሎ በመቀመጥ በቆዳና በመሳሰሉት መሸፈኛዎች እስከ አንገት ድረስ ተሸፍኖ ይሞቃል። ጭሱን ሰውነትን እስኪያልብ ድረስ ለረጂም ደቂቃዎች ይሞቃል። ከሞቁ በኋላ ሲጨርሱ ገላን በመታጠብ የጥሩ መዓዛና ጥሩ ወዝ ባለቤት ይሆናል።

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 19/02/2024

አፊኒ ፊልም
ሙሉ ፊልሙ 1:56 ሰዓት የሚወስድ ስሆን በዓይነቱም በይዘቱም የተለዬ እና ወቅቱ የምፈልገውን የጥራት ደረጃውን ጠብቆ በድንቅ አርቲስቶች አስደናቂ የትወና ብቃት የታየበት ግሩም ፊልም ነው።
በቅርቡ አዘጋጆቹ በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት ለእይታ ይበቃል።

19/02/2024

ካርድዎን ሳያስገቡ፤ ገንዘብዎን ያውጡ!
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካርድዎን ኤቲኤም ማሽን ውስጥ ሳያስገቡ በማስጠጋት ብቻ የይለፍ ቁጥርዎን አስገብተው ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
የያዙት ካርድ እና ATM ማሽኑ ያለንክኪ እንደሚሠሩ የሚያሳየውን የሞገድ ምልክት (የዋይፋይ ምልክት) ልብ ይበሉ፡፡

መረጃውን ከድርጅቱ ማህበራዊ ድህረገጽ አገኘን

16/02/2024

ክቡር የክልላችን ፕረዝዳንት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽና በቀጣይ መንግስታቸው አቅጣጫ ላይ የሰጡት ማብራሪያ

07/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል
****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የምክር ቤቱን 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ እና 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች መርምሮ በማፅደቅ የዕለቱን መደበኛ ስብሰባ የሚጀምር ይሆናል፡፡

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት ከ1ኛ ልዩ ስብሰባ የተሸጋገሩ የተለያዩ አጀንዳዎችንም መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

ከተሸጋገሩት አጀንዳዎች ውስጥ የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የፕላን፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ደንቡን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት እንዲሁም የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የሚቀርብ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 28/01/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት ነው የተበረከተው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ልዑካን ቡድኖች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ በጣልያን የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ተልዕኮዎች አባላት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት ዓመታት በግብርናው መስክ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶችን ያደረገች መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልከቷል፡፡

ለአብነትም በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ሥራዎችን በማከናወንና በዐበይት ምርቶች ላይ ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገቧ ተገልጿል፡፡

25/12/2023

ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻ የሲዳማ ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሾሙ

ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻ የሲዳማ ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሹመዋል። ወ/ሮ ወይንሸት ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በተለያዩ የስራ ድርሻ ያገለገሉ መሆናቸው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል ።

25/12/2023

ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሐብት ጥቅም ላይ በማዋል ወደ ብልጽግና ለምታደርገው ጉዞ ማሳያ ነው
__________________________________
ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሐብት ጥቅም ላይ ለማዋል የገነባችውን አቅምና ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ ማሳያ ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው ጨበራ የዝሆን ዳና ፕሮጀክት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በዳውሮና በኮንታ ዞን አዋሳኝ ቦታ ላይ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ከትናንት በስትያ መመረቁ ይታወሳል፡፡

ሎጁን አስመልክተው የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚፈልጓቸውን መስህቦች አሟልቶ የያዘ ነው፡፡

አካባቢው የቱሪስት መስህብ የሚሆን ተፈጥሯዊ ገጽታ ያለው ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሳይሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አካባቢው ያለው የተፈጥሮ ጸጋ በመገንዘብ ሎጅ እንዲገነባ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከቤተ-መንግስት የተጀመረው የልማት ፕሮጀክት ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች በመስፋፋት በርካታ አካባቢዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ይህም ያሉንን እምቅ ሐብቶች ፈልፍሎ በማውጣትና ጥቅም ላይ የማዋል አቅምን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች እንዲገነቡ መመሪያ ለሰጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

(ኢዜአ)

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 24/12/2023

Panacea Hospital - Hawassa, Ethiopia 2,094 Gallbladder Stones were Successfully Removed from a 40-year-old woman on December 16, 2023 G.C.

The patient had been suffering from Right upper abdominal crampy and epigastric burning pain after fatty meal ingestion for the past three years. For this complaint she decided to visit Panacea Hospital - Hawassa and was evaluated by Dr. Tsegaye Chebo, General Surgeon at Panacea Hospital - Hawassa.

Preoperatively the patient was thoroughly evaluated with Laboratory, Imaging and Clinical parameters.

Abdominal ultrasound revealed numerous gallstones in the gall-bladder and it was fully occupied with stones measuring 3mm to 10mm with no signs of acute Cholecystitis.
So with Diagnosed of Symptomatic Multiple Cholelithiasis and patient was advised on Surgical options and modes of anesthesias.

But, there were Patient related factors that made the Surgery more challenging. The Challenges were, Our Patient Previously had three/3x Thyroidectomy Surgeries for Thyroid Malignance with repeated recurrency at different Hospital. The last, third Thyroidectomy was done 3years back.

After Surgery she had Bilateral vocal cord paralysis in Paramedian Position with intermittent breathing difficulties, weak and change in voices.

Because of associated commorbidity and compromised airway, anesthesiologist performed careful preoperative evaluation and strict intraoperative monitoring.
General Anesthesia Combined with Thoracic Epidural Analgesia was conducted by, Dr. Henok Esayas (Anesthesiologist)

The patient underwent elective Open cholecystectomy On Saturday, December 16, 2023. More than 2,094 Gallbladder Stones were Successfully removed after a surgical procedure that lasted approximately 2hours and 30minutes.

The stones were counted by operating teams and the team sat through more than 45 Minutes to count the stones.

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 24/12/2023

በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት የመጀመሪያ የሆነ - 2,094 የሀሞት ከረጢት ጠጠር በፓነሲያ ሆስፒታል - Panacea Hospital -ሀዋሳ በተሳካ ቀዶ ህክምና ወጥቷል።

More than 2,094 ( Two Thousand Ninety-Four) Gallbladder Stones Removed in Panacea Hospital - Hawassa, Ethiopia.

በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ 2,094 (ሁለት ሺህ ዘጠና አራት) የሀሞት ከረጢት ጠጠር በቀዶ ህክምና ከአንዲት 40 ዓመት ሴት በሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት በዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ እና በዕለቱ የቀዶ ህክምና ቡድንን አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በቁጥር ብዛት የመጀመሪያ የሆነና እስከዛሬ ያልተመዘገበ ከ2,094 በላይ ቁጥር ያለው የሀሞት ከረጢት ጠጠር (Symptomatic Multiple Cholelithiasis) ለ2 ሰዓታት ከ30 ደቂቃዎች በተደረገው ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ ተችሏል።

የሀሞት ከረጢት ጠጠሮች በቀዶ ህክምና ቡድን የተቆጠሩ ሲሆን ጠጠሮቹን ለመቁጠር ከ45 ደቂቃ በላይ ፈጅቷል።

እስካሁን ባሉ መረጃዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳይንሳዊ መጽሔቶች እና ምርምር ሪፖርቶች ላይ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው የሀሞት ከረጢት ጠጠር በህንድ ምድር በሪከርድነት ተይዞ ይገኛል።

©Hakim

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 23/12/2023

በአማራ ክልል የሰላም ጥሪውን ተከትሎ 251 ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከል ገቡ

የአማራ ክልል መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጭስ ዓባይ፣ በወረታ እና በአዲስ ዘመን አካባቢዎች የነበሩ 251 ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት ቀርበው መሳሪያ ማስረከባቸውን የደንቢያ አካባቢ ኮማንድ ፖስት አባል ሌተናል ኮሎኔል አዛናው ነጋሽ ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ቆላ ድባ ከተማና አካባቢው እንዲሁም ከሻውራ ወረዳ የመንግስትን የምኅረት ጥሪ ተከትሎ ታጣቂዎቹ ወደ ተዘጋጀላቸው የመሰብሰቢያ ስፍራ መግባታቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡

ጥሪውን ተቀብላችሁ መምጣታችሁ ለሠላም ያላችሁን ፍላጎት ያመላክታል፤ ሌሎችም የእናንተን ፈለግ ተከትለው የቀረበላቸውን የሠላም ጥሪ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ስል FBC ዘግቧል ።
#

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 23/12/2023

የቦኖራ ፏፏቴ እና ታርካዊው ዋሻ!

ሰናይ ቀን!

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 22/12/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም 62 በመቶ መድረሱን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ አድርገዋል።

በዚህም “ከ2013 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄድኩት የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በለወጥነው የፕሮጀክት አስተዳደር እና ክትትል ስርዓት የተነሳ የአጠቃላይ ግንባታው ሂደት 62 በመቶ መድረሱን በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነታቸው አንደኛ እና ሶስተኛ የሆኑት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች ባለቤት በመሆናችን የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን እና ጥረታችንን አቻ የሌለው ያደርገዋል” ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፡፡

በቅርብ ርቀት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 22/12/2023

ብልጽግና ፓርቲ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮቹ ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል መሪ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በአባላት ደረጃም እንደቀጠለ ነው።

ከእዳ ወደ ምንዳ የተሰኘው ሀገር አቀፍ የስልጠና መርሀ ግብር መንግስታዊ የመሪነት አቅማችንን ለማሳደግ ጉልህ ሚና አበርክቷል። በተለያዩ ዙሮች እና ማዕከላት ባካሄድናቸው ስልጠናዎች እንደ ሀገር በርካታ ትሩፋቶችን ያገኘንበት እንደሆነ ለመታዘብም ችለናል።

በዛሬው እለትም ለፌደራል ብልፅግና ዞን አባላት የሚሰጠው ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል።

በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው በገዢ ትርክት ግንባታ ዙሪያ ስልጠና የሰጡት የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ሲሆኑ በርካታ ገንቢ ሀሳቦችን አንስተዋል።

እንደ ሀገር በትርክት ግንባታ ዙሪያ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙን ገልፀው አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት ሂደት የተፈተንባቸውን ፈተናዎች ድል መንሳት እንድንችል የብሔራዊነት ትርክትን መምረጣችን ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች እንዳሉት ገልፀዋል።

ትርክቶች የሚቀረፁበት እና የሚሰራጩበትን መንገድ በማጥናት፣ነጠላ ትርክቶች እና ገዢ ትትክቶች ያላቸውን ልዩነት በመገንዘብ እንዲሁም እንደ ሀገር ያለንን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የብሔራዊነት ትርከት ሀሳብን ለማዳበር እንደተሞከረ ጠቅሰዋል።

እንደ ብልፅግና ፓርቲም ይህ አሰባሳቢ እና ብዝሀነትን እና ሀገራዊ አንድነትን ያስታረቀ ትርክት ፍሬ ያፈራ ዘንድ ሰፊ ስራ በመስራት ላይ እንደምንገኝና አባላትም የበኩላቸውን ድርሻ የሀሳቡን ቀናኢ ፍሬ ተገብዝበው እንዲያበረክቱ አስገንዝበዋል።

ለተከታታይ 4 ቀናት በሚቆየው ይህ የስልጠና መርሀ ግብር ገዢ ትርክት፥ሃብት መፍጠርና መምራት፣ የሰላም ባህልና አመለካከት የመፍጠርና የመገንባት ክህሎትና አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ መገንባትና መምራት በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል።

ከአመራር እስከ አባላት እየተሰጠ ያለው ስልጠና በፓርቲው መዋቅር ውስጥ ጠንካራ የሃሳብና የተግባር አንድነት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 22/12/2023

የ70 ዓመቱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ

የ10 ልጆች አባትና የልጅ ልጆችን ያዩት አቶ ዮሐንስ አዲሴ በ70 ዓመታቸው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለመማር ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አቅንተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡

በአቀባበሉ ላይም የ70 ዓመቱ አዛውንት አቶ ዮሐንስ አዲሴ የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ በ2015 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ ፈተና አልፈው ወደ ተመደቡበት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በልጅነታቸው ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩና ባጋጠማቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆታቸውንም በአቀባበሉ ላይ ተናግረዋል፡፡

ለትምህርት ካላቸው ፍላጎት አኳያም ያቋረጡትን ትምህርት በመቀጠል ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ለጠቦ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አዛውንቱ ተማሪ÷ ከተማሩበት ትምህርት ቤት የ2015 ዓ.ም በሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ካለፉ ጥቂት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች አንዱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውንም በትጋት ለማስኬድ በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ ማለታቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል፡፡

ዘገባው የFBC ነው

Timeline photos 22/12/2023

የብልጽግና ራዕይ

1.በ2018 ከሀሳባዊ ብልጽግና ወደ የሚጨበጥ ብልጽግና መድረስ

2.በ2023 በአፍሪካ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ብልጽግና መፍጠር

3.በ2040 በአለም ተምሳሌት የሆነ ብልጽግና መገባንት ናቸው ።

መልካም የብልጽግና ግዜ !

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 21/12/2023

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የግል ስኳር ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ ተጣለ

ለፋብሪካው የሚሆነውን የሸንኮራ ልማት ላለፉት ሁለት አመታት ሲያካሄድ ቆይቶ የፋብሪካውን መሰረት ድንጋይ ተጣለ።

ኢትዮ ስኳር አክሲዮን ማህበር በ24 መስራች አበላት በ2011 ዓ.ም ተቋቋመ። ድርጅቱ አሁን ላይ ከ5ሺ በላይ አባለት ሲኖሩት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አክሲዮን በመሸጥ ከልማት ባንክ የቱርክ አሊሚ ኤሌሲ አዲስ እህት ኩባንያ ከሆነው OMO Valley የወሰደውን መሬት 250 ሚሊዮን ብር በመግዛት በሀመር ወረዳ ካራ ቆርጮ ቀበሌ 10ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ቦዬ፣ ሃባብ፣ ስኳር ድንች፣ ሩዝና ብርቱካን እያመረተ ይገኛል።

መሰረተ ዲንጋይ ሲጣል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደና የክልሉ ም/ርዕሰ ማስተዳደርና የመንግሥት ዋና ተጠሪ ለሆኑት ለአቶ አለማየሁ ባዉድ እንዲሁም የክልሉ የቢሮ ሃላፊዎች የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደርና የሀመር ወረዳ አስተዳደር የካራ ባህል ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል።

ፋብሪካው ተገንብቶ ከአንድ ዓመት በኃላ ምርት እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን ለፋብሪካው የሚያስፈልገው የሸንኮራ ልማት በፍጥነት ጎን ለጎን እየለማ ስገኝ ድርጅቱን በኢኮኖሚ የሚዶግም የሙዝ ምርት ከሶስት ወር በኃላ ይጀመራል ሲል ህባ ዮሴፍ ከሀመር መረጃውን አድርሶናል።

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 20/12/2023

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ሲዳማ ቡናን በድጋሚ ለማሰልጠን ተስማማ::

ዘላለም ሽፈራው በቅጽል ስሙ ሞሪኒሆ ሲዳማ ቡናን በድጋሚ ለማሰልጠን ክለቡን ተቀላቅሏል::ዘላለም ሽፈራው ሲዳማ ቡናን በኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ለዋንጫ የሚወዳደር ጠንካራ እና ገናና እንዳደረገ እና በክለቡ ታሪክ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ማስቻሉ ይታወሳል::

ዘላለም ሽፈራው (ሞሪኒሆ) ሲዳማ ቡናንንም ከፍ በማድረግ እራሱን በትልቅ ደረጃ እንዲያሰለጥን በር የከፈተለት ክለብ እንደነበር የሚታወቅ ነው::

ሲዳማ ቡና ከዘላለም ሽፈራው በኃላ ብዙም የተሳካ አሰልጣኝ ባያገኝም በድጋሚ ወደሚያውቀው ክለብ መመለሱ ቡድኑን ከፍ ባለ ደረጃ እንዲጫወትና ውጤታማ እንደሚያደርገው ከወዲሁ በደጋፊዎቹ እምነት ተጥሎበታል::

አሰልጣኙ ከዚህ በፊት ደቡብ ፖሊስ ፣ ደደቢት፣ አዳማ ከተማ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዲያ ከተማ፣ ወላይታ ዲቻ፣ ሰበታ ከተማ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት እና በተለያዩ የሃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡

©TD

Photos from Sidama News Network /SNN/'s post 20/12/2023

የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ህዝቡን እንደሚቀላቀሉ ተገለጸ

የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ከነገ ጀምሮ ህዝቡን ይቀላቀላሉ ተብሏል።

ሰልጣኞቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ የተሀድሶ ስልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል።

በተሀድሶ ስልጠና ቆይታቸውም ወደ ማህበረሰቡ ተመልሰው ሰላማዊ ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችላቸውን ትምህርት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

የተሃድሶ ሰልጣኞቹ በአባ ገዳዎች አማካኝነት በድለናል ያሉትን ህዝብ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን መሰል እኩይ ተግባራት ላይ ላለመሳተፍ ቃል ገብተዋል።

የተሀድሶ ሰልጣኞቹ ከነገ ጀምሮ ወደ ማህበረሰቡ እንደሚቀላቀሉ ተገልጿል።

Videos (show all)

ማስታወቂያበሲዳማ የእርቅና የዳኝነት ስርዓት ላይ ያተኮረው እና በሀገራችን እውቅ ተዋንያን ተሳትፎ የተሰራው የአፊኒ ፊልም ተመርቆ እነሆ ለእይታ ቀርቧል፡፡በሲዳማ ባህል ቱርዝምና ስፖርት ቢሮ ...
ክቡር የክልላችን ፕረዝዳንት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ  ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽና በቀጣይ መንግስታቸው አቅጣጫ ላይ የሰጡት ማብራሪያ
SOOREESSU GUDUMAALINNI
ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ
የአርቲስት ዓሊ ቢራ የአስከሬን ሽኝት በድሬዳዋ
የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ መሪ፣ የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት በተመለከተ የተካሄደውን የሠላም ንግግር አስመልክቶ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ▶: የአፍሪካ ኅብ

Telephone

Website