Sinan Woreda Prosperity party

Sinan Woreda Prosperity party

የስናን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ ቤት/sinan woreda prosperity party

02/08/2023

"ልዩነት ያለው አካል ሁሉ ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ውይይት ይምጣ" ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ባለፉት ጊዜያት ጀምሮ በክልሉ የፀጥታ ችግር አጋጥሟል ብለዋል። መንገድ በመዝጋት የሰዎችን እንቅስቃሴ በመግታት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት። ያለው ግጭት እርስ በእርስ እያገዳደለና ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።

እርስ በእርስ መጠፋፋት ዘላቂ ችግር እንጂ ዘላቂ ሰላም አያመጣም ነው ያሉት። ሁሉም ለሰላም መረባረብ አለብንም ብለዋል። የክልሉ የፀጥታ መዋቅርና የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም አስታውቀዋል። የክልሉ ሕዝብ እየተደረገ ያለውን ሕግ የማስከበር ሂደት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ መሆኑን ማወቅ ይገባል ነው ያሉት።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የተውጣጣ የኢትዮጵያውያን ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ መከላከያን ያለ ስሙ ስም መስጠትና መተንኮስ አግባብ አይለምም ብለዋል። የፀጥታ ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ሁሉም ጥያቄ አለኝ የሚል ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መረባረብ አለበት ነው ያሉት።

ልዩነት ያለው አካል ሁሉ ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ውይይት እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ለሰላም ዘብ በመቆም ችግሮቻችን መፍታት ይገባናል ነው ያሉት። ክልሉን ዋጋ የሚያስከፍል ችግር ከመከሰቱ አስቀድሞ ሁሉም ለሰላም መረባረብ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

አሁን ያለው አካሄድ ክልሉን አደጋ ውስጥ የሚከት በመሆኑ የክልሉ ሕዝብ ለሰላም እንዲሠራም ጠይቀዋል። እርስ በእርስ በመገዳደል ያመጣነው ለውጥ የለምም ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ለሰላም በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በማስቆም ሁሉም ወደ ሰላም እንዲመጣም ጥሪ አቅርበዋል።
አሚኮ
°~°

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

01/08/2023

የሁሉም ነገር መነሻ ሰላም ነው፣
***************

የአማራ ክልል ሰላምና መረጋጋት የእያንዳንዱ አካባቢ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድምር ውጤት መሆኑን ሁሉም የሚስማማበት እውነት ነው።

ሰላም ልማት ነው፣ ሰላም ዕድገት ነው፣ ሰላም አብሮነትና አንድነት ነው፣ ወጥቶ ለመግባት፣ ሠርቶ ለመኖር፣ ነግዶ ለማትረፍ፣ ተምሮ ውጤታማ ለመሆን በአጠቃላይ ሰላም ለሁሉም መሠረት ነው።

ለዚህም ነው በርካቶች ሰላም የሚተመንበት አሊያም የሚሰፈርበት ልኬት የለውም ሲሉ የሚሞግቱት።

ኢትዮጵያዊያኖች ለሰላም የሚሰጡት ዋጋም ሆነ ክብር እጅግ ከፍ ያለ ነው። ምክንያቱም ሰላም ምን እንዳስገኘላቸው፤ በአንጻሩም የሰላም እጦት ምን እንደሚያጎድልባቸው ከህይወት ልምዳቸው ጠንቅቀው ተረድተውታልና ።

የሰላም እጦት ሞትን፣ አካል መጉደልን፣ የንብረት መውደምን፣ ስደትን፣ ረሃብን፣ መታረዝን በአጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን አስክትሎ የሚያልፍ መሆኑን ከማንም የተደበቀ አይደለም።

አገራት በሰላም እጦት የተነሳ እየደረሰባቸው ያለውን ሁለንተናዊ ክስረትና በአንጻሩ ደግሞ ሰላምን አጥብቀን በመያዛችን የተነሳ እንደ አማራ ክልልም ሆነ እንደ አገር ባለፋት ጊዚያት ያስመዘገበችውን የኢኮኖሚ እድገት ስንመለከት የሰላም ዋጋው ምን ያህል ከፍ ያለ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡

ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ ሁከቶች እና ግጭቶች ክልሉን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመምራት መንገድ የሚከፍቱ ናቸው።

ለሁከቶቹ መፈጠር ምክንያት የሆኑ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ቢኖሩም የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው ርካሽ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚሯሯጡ ሃይሎች ስለመኖራቸው ግን ጥርጥር የለውም፡፡

መንግስት በክልላችን የተከሰቱትንና ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ግጭቶችንና የሰላም እጦቶችን ለመከላከል ከህዝብ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል።

ህብረተሰቡም ያለስጋት መውጣትና መግባት እንዲችል፣ ሕዝብና መንግስትን የበለጠ ተናበው ልማቱን ለማሳለጥ እንዲቻል፣እርስ በእርስ ያለንን ግንኙነት የሚያቀራርቡ፤ ከልዩነት ይልቅ ብሄራዊ አንድነትና መግባባትን የሚፈጥሩ፣ የመቻቻል የመከባበር፣ የአንድነት ወዘተ እሴቶቻችን የበላይነትን እንዲያገኙ የአማራ ክልል መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ህዝቡ የክልሉ የሰላም አምባሳደር እንዲሆን ሃላፊነት አለበት። ህዝቡም የተጣለበትን የሰላም አደራ ተረክቦ በክልሉ የትኛውም ክፍል ምንም አይነት ኮሽታ እንዳይፈጠር ተግቶ በመሥራት የሚከሰቱ ችግሮች ቢኖሩ እንኳን ጥያቄዎቹን በሰለጠነ መንገድ የማቅረብ ሃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

ከምንም በላይ የአንድ አገር ሰላም የሚረጋገጠው በህዝብ እንጂ የጸጥታ ሃይሉ በሚወስደው እርምጃ አይደለም፡፡ ይህ ሲባል ግን የጸጥታ ሃይሉ በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ የሰላም ጉዳይ ላይ አይመለከተውም ማለት አይደለም፡፡

የአንድ አገር የጸጥታ ሃይል የህዝቡንም ሆነ የሀገሩን ደህንነት ማስከበር ከመንግስት የተረከበው ሀገራዊ አደራ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ስለሆነም በሰላም ጉዳይ ህዝቡ ከጸጥታ አካሉ ጋር መተባበር ይኖርበታል፤ ምክኒያቱም ሰላም ለህዝቡም ሆነ ለጸጥታ አካሉ የጋራ አጀንዳቸው ነው፡፡

መንግስት የትኛውንም ያህል የጸጥታ ሃይል ቢኖረው በእያንዳንዱ አካባቢ የጸጥታ ሃይል ሊያሰማራና ሰላም ሊረጋገጥ አይችልም።

የጸጥታ ሀይሉ ለህብረተሰቡም ሆነ ለክልሉ ደህንነት አስፈላጊ መሆኑን ከልብ መገንዘብ ይገባል፤ ህብረተሰቡም ለጸጥታ ሀይሉ ዋና ድጋፍ ሰጪ ነው፡፡

ሰላም ለልማት፣ ሰላም ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት፣ ሰላም ለመድብለ ፓርቲ መጠናከር፣ ሰላም

01/08/2023

የአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር ውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው

የአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ የሚመክርና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ መድረኩን አስመልክቶ እንደገለፁት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የሰላም ችግር በጋራ ተወያይቶ መፍትሄ ለማምጣት ያለመ ውይይት ነው።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር እና ህብትና ንብረት የማጥፋት ሁኔታዎች እየተስተዋሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የጸጥታ ችግሩ በተለያዩ አካባቢዎች የልማትና የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመግታት የክልሉን ህዝብ ወደባሰ ችግር ውስጥ እያስገባው መሆኑን አቶ ግዛቸው ተናግረዋል።

በመሆኑም እየተስተዋለ ያለውን ችግር በሰከነ መንገድ ለመፍታት ከክልሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር መወያየትና መመካከር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጸዋል።

አቶ ግዛቸው እንዳሉት ውይይቱ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን በጋራ በማስቀመጥ የተጀመሩ የልማትና የለውጥ ስራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ ነው። ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ተወያይቶ መፍታት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ላለው ሥራ የሚኖራቸው ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ ግዛቸው፣ "በመድረኩም ችግሩን ለመፍታት የሚረዱ ግብአቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል።

በውይይቱ ላይ በክልሉ ከሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ ከ400 በላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
•~•~•

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 01/08/2023

በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላምና የልማት ሂደቱ እንዲጠናከር መስራት ይገባል - ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

ከአማራ ክልል የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

ከአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በሠላምና ፀጥታ አዝማሚያዎች ላይ በባህር ዳር ከተማ እየመከሩ ነው።

ክልላዊ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን እና የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዎችን አመላካች መነሻ ሀሳብ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ቀርቧል።

የውይይት መድረኩ በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎችና አዝማሚያዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላምና የልማት ሂደቱ እንዲጠናከር ፋይዳዉ የጎላ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል።

በሰላም እና በውይይት እንጂ በጦር መሳሪያ የተፈታ ችግር አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን የአማራ ክልል ህዝብ ጦርነት ሳይሆን ልማት የሚሻ ህዝብ በመሆኑ ልማቱን ይበልጥ በማተኮር የህዝቡት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባልም ተብሏል።
•~•~•

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 31/07/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አሥተዳደር ከ102 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አቶ ገዳሙ_መኮነን ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ፣ በክልሉ መንግሥት ድጎማ፣ ከከተማ አሥተዳደሩ የውስጥ ገቢና ከማኀበረሰብ ተሳትፎ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ተመርቀው አገልግሎት መሥጠት የጀመሩት ፕሮጀክቶች ፦
👉በአንድ ጊዜ ከ350 መኪና በላይ ማስተናገድ የሚችል የመኪና መናሃሪያ ፣
👉 የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ፣
👉የጎርፍ መፋሰሻ ዲች፣
👉የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ፣
👉የመንገድ አካፋይ ግንባታ፣
👉ድልድይ፣
👉የሰባቱ ዋርካ መዝናኛ ማዕከልን
👉በየቀበሌው ያሉ የመዝናኛ ማዕከል ጨምሮ በአጠቃላይ #43 ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ከንቲባው ተናግረዋል።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ በከተሞች ኀብረተሰቡ ሊሳተፍባቸው በሚገቡ የማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሥራዎች ላይ ሕዝቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በአይነት የሚያደርገው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱም ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

በዞኑ የዓለም ባንክ ድጋፍ የመሰረተ ልማት ሥራዋች የእቅዱን 98 ነጥብ 7 በመቶ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ተችሏል። ከዓለም ባንክ ውጭ የሆኑ ከተሞች ፕሮጀክት ብዛት 104 ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ የክልሉ መንግሥት ከተሞችን በመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።

የማኀበረሰቡ ድርሻ እያደገ ስለመማጣቱ የተናገሩት ኀላፊው ማኀበረሰቡም ፕሮጀክቶቹን በባለቤትነት ስሜት እንዲጠቀምባቸው አሳስበዋል።

የከተማው ነዋሪዎች የፕሮጀክቶች መመረቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው እና በክረምት ወቅት ይደርስባቸው ከነበረው እንግልት እንደታደጋቸዉ ተናግረዋል። የተገነቡ መሰረተ ልማቶቹን በኀላፊነት እንደሚጠቀሙባቸው ተናግረዋል።

24/11/2015 ዓ.ም

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 31/07/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ "የጋራ መነሻና መዳረሻ ካበጀን ከአሸናፊነት መንገድ ላይ እንገናኛለን " በሚል መሪ ቃል ከረቡዕ ገበያ ከተማ ከተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎችና የሀይማኖት አባቶች ጋር የምክክር ውይይት ተካሄደ::

በአማራ ክልል ህዝቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ በየደረጃው ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በውይይቱ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስሜነህ አዝመራውና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን መኩሪያው በጋራ የመሩት ሲሆን ማህበረሰቡ ለሰላሙ ዋጋ በመስጠት የድርሻውን በመወጣት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተግባራትን በውጤት ለመፈጽም ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ሠላምን ለመጨበጥ ከራሳችን ይልቅ ለሌሎች ፍላጎት ቦታ መሥጠት ያስፈልጋል፤ከእኔነት አስተሳሰብ በመውጣት የእኛነት አስተሳሰብን መጨበጥ እንደሚገባ አቶ ስሜነህ ተናግረዋል።አቶ ስሜነህ አያይዘውም ይህ ድርጊት በብዙዎች ዘንድ ሲተገበር እና ሲመላለስ አንዳአችን ለአንዳችን ሠላም መስጠትን እና መሸጥን እንጀምራለን።

የሰላም አባሳደር የሆነውን የስናን ህዝብ በቀጣይ ችግር ፈች የመሰረተ ልማት ስራዎች እየመጡለት ስለሆነ በተለይም የመንገድ ፣የኢንቨስትመንት አማራጭ ተጠቃሚ ለማድረግ የፀጥታ አደረጃጀት በማጠናከር ለሰላም ትርጉም ሰጥቶ ሁሉም መስራት አለበት ሲሉ አቶ ሙሉቀን አሳስበዋል።

"የጋራ መነሻና መዳረሻ ካበጀን ከአሸናፊነት መንገድ ላይ እንገናኛለን " በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የሰላም ኮንፈረንስ በወረዳ ማዕከል እና በየቀበሌዎች የተካሄደ ሲሆን ውይይቱ እንደቀጠለ ይገኛል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳነሱት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር መኖሩ፣የአቡላስ እና የባጃጅ ህገወጥ አሰራር፣የፀጥታ መዋቅር ኃላፊነትን በአደረጃጀት መሰረት ተግባሩን በውጤት አለመምራት የሌሊት የኬላ እና የሮድ ጥበቃ ችግር፣የማዳበሪያ አጠቃቀምና ፍትሀዊ ስርጭት ግብርና ተቋሙ በአግባቡ አለመምራት ፣የጤና ጣቢያ የታማሚ አገልግሎት አሰጣጥ ሙያተኛ በጥቅማ ጥቅም አኩርፈው በተገቢው መንገድ አለማስተናገድ የሚሉ እና መሰል ጉዳዮችን በድፍረት አንስተው ውይይት ተደርጓባቸዋል።

"ሠላም የሁሉም ነገር የልማት በር ከፋች መሠረት ነው!!"

ሀምሌ 24/2015 ዓ.ም

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 31/07/2023

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ክልል አቀፍ የ2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን የስንዴ ሰብል የኩታ ገጠም የዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም እያካሄደ ነው።

አገራችን ስንዴን በስፋት በማምረት በምግብ እራስን ለመቻልና ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት በአገር ውስጥ ምርት በመተካት የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት በምስራቅ ጎጃም ዞን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በአገሪቱ የስንዴ ምርት በሰፋት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው - የምስራቅ ጎጃም ዞን። በዞኑ በተያዘው 2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን የስንዴ ሰብል በስፋትና በጥራት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጿል።

በዞኑ በስፋት የስንዴ ሰብል ከሚመረትባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ጥጃጎጠር ቀበሌ የአንድ ጀንበር ኩታ ገጠም የስንዴ ዘር ክልላዊ በዓል በማካሄድ ላይ ነው።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አቶ ፈንታሁን ቸኮል በተያዘው 2015/2016 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከ607 ሽህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር በመሸፈን ከ22 ሚሊዮን ኩንታል በሊይ ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በመኸር ምርት ዘመኑ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የኩታ ገጠም አሰራር በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት መምሪያ ኀላፊው በዞኑ 212 ሽህ 068 ሄ/ር የሚሆነው በስንዴ ሰብል የሚሸፈን መሆኑን አስረድተዋል።

በዛሬው ዕለት ክልላዊ የአንድ ጀንበር የስንዴ ዘር በዓል እየተከበረ በሚገኝበት ደብረ ኤልያስ ወረዳ ከ5 ሽህ ሄክታር በላይ መሬት በአንድ ጀንበር የስንዴ ዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን አቶ ፈንታሁን አስረድተዋል።

በዞኑ በምርት ዘመኑ በዘር ከሚሸፈነው አጠቃላይ ማሳ ጤፍ ፣ስንዴና በቆሎ ሰብሎች 497 ሽህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን የገለፁት መምሪያ ኀላፊው በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የኩታ ገጠም አሰራር እየተተገበረ ነው ብለዋል።

በተያዘው 2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን በዘር ከሚሸፈነው ከ607 ሽህ ሄክታር በላይ ማሳ 68 በመቶ የሚሆነው በማሳ ኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን አቶ ፈንታሁን ጨምረው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን 5 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር ለመሸፈን መታቀዱንና እስካሁን ባለው ጊዜ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው አስረድተዋል።

ከ160 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የግብርና ምርት ለማግኘት መታቀዱን የገለፁት ምክትል ቢሮ ኀላፊው
በክልሉ በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን 1 ማሊዮን ሄክታር ማሳ በስንዴ ሰብል ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን በዘር ከተሸፈነው ማሳ ውስጥ 1 ነጥብ 1 ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠም አሰራር መዘራቱን ያስረዱት አቶ ቃልኪዳን በአጠቃላይ በዘር ከሚሸፈነው ማሳ ውስጥ 2 ሚሊዮን ሄክታር በኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን ጨምረው አስረድተዋል።

ማሳቸውን በኩታ ገጠም አሰራር በስንዴ ሰብል እየሸፈኑ የሚገኙ በደብረ ኤልያስ ወረዳ የጥጃጎጠር ቀበሌ ነዋሪዎች በበኩላቸው ሰብላቸውን በኩታገጠም ዘዴ መዝራታቸው ለአሰሳ ስራ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠረ በተጨማሪ በምርት ጭማሪ ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው !

31/07/2023

በሁለት አፅናፍ ቆሞ መጓተት ለውጥ አያመጣም!!
**************************

ፍቅርና ይቅርታ፣ ዕርቅና ሰላም፣ መግባባትና አንድነት የሚሉትን የለውጡ ሐሳቦች በጉልህ ማስተጋባትና ወደ ተግባር በመቀየር ውጤት እንዲመጣ ማስቻል በለውጡ ሂደት ውስጥ ያየናቸው ደማቅ ምስሎች ናቸው፡፡

የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት ብሎም በሁሉም መስኮች የተጀማመሩ የልማት ዕቅዶች እንዲሳኩ ልዩነቶቻችንን በይደር አስቀምጠንና መቅደም የሚገባቸውን ክልላዊ አጀንዳዎች አስቀድመን፣ በጠረንጴዛ ዙሪያ በሰከነ መንፈስ፣ከግል ስሜትና ፅንፍ ከወጣ አውዳሚ አስተሳሰብ ወጥተን የመፍትሔ ባለቤቶች መሆናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

ሁላችንም የምንጠብቀው የአማራ ክልል አጀንዳ በሚፈለገው መንገድ ተግዳሮቶችን ተሻግሮ እና ተሳክቶ ለማዬት እንድንችል ከጅምሩ የለውጡን ምንነት፤ ባህሪያት፤ እንዲሁም መዳረሻችን የት ነው የሚለውን ወደኋላ መለስ ብሎ በወጉ መረዳት ይገባል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እና አውዳሚ አስተሳሰብ በሁለት አፅናፍ ላይ ቆመው በሚጓተቱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነን የምንፈልገውን ክልላዊ ለውጥ ማምጣት አይደለም ማሰብ በእጅጉ ያስቸግራል፡፡

ከግል ስሜቶቻችን ወጥተን የአማራ ክልልን ህዝብ ማስቀደም ብልህነት ብቻ ሳይሆን ወቅቱን የዋጀ የአስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡

ክልሉን ከህገ ወጥ አሰራሮችና ተግባራት በመታደግ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማስቻል እንዲሁም ከማያባራ ቀውስ በመታደግ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ወቅቱ የሚጠይቀው የውዴታ ግዴታ ነው፡፡

በህዝቡ እና በአመራሩ ዘንድ የአመለካከት፤ የአስተሳሰብና የተግባር፤ እንዲሁም የአሰራርና መዋቅር መስተጋብር በመፍጠር በጦርነት የደቀቀውን የክልሉን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ለነገ የማይባል የጋራ ስራችን ሊሆን ይገባል፡፡

በክልሉ ከሰሜኑ ጦርነት ማግስት እየፈተኑት ያሉ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ፈተናዎችን ተሻግሮ የህዝብን ፍላጎት ማሟላት መቻል የግድ ከሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡

የብሔር ፖለቲካ ነጋዴነት አዝማሚያ፣ የግጭት ፖለቲካን በማስቀደም የስልጣን ጥምን ለማርካት እንደስልት የመጠቀም አዝማሚያ፣ አገራዊ አንድነትንና ብሔራዊ ማንነትን ማጠናከር ላይ ያለውን ሚዛን አለመጠበቅ፣ የውስጥ አንድነት የሚያጎለብቱ ስራዎች ላይ ያለው የአስተሳሰብ መዛነፍ፣ ዕለት ከዕለት እየባሱ የመጡ ብልሹ አሰራሮች፣ ሌብነት፣ መልካም አስተዳደር ችግሮችና የመሳሰሉት ችግሮች እንደ ክልል የሚፈለገውን ያህል ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡

ስለሆነም እነዚህን እና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ውስጥን መፈተሽና እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ሊፈጠር ይገባል፡፡ በመካከላችን ሊኖር በሚገባዉ የጋራ እሴት ላይ ትርጉም ያለዉ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ይህን ማድረግ ሲቻል ወጣቱ ስለ ክልሉ ወቅታዊ ሁኔታው የተስተካከለ አመለካከትና ግንዛቤ እንዲጨብጥ ከተደረገ፣ አልፎ አልፎ ለሚታዩ የስሜታዊነት ችግሮች የክልሉ ወጣት ራሱን ዋነኛ ችግር ፈቺ ኃይል መሆኑን በግልጽ ማስረዳት ይገባል፡፡

•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ!

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 30/07/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደባይ ጥላት ግን ወረዳ በህብረተሰቡ ተሳትፎና በመንግስት ወጭ የተገነቡ የመሠረተ ልማት ስራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ።

በወረዳው 57 ሚሊዮን 506 ሽህ 803 ብር ወጭ የተደረገባቸው የትምህርት ተቋማት ማስፋፊያ፣ በ10 ሚሊዮን 988 ሽህ በ116 ብር ወጭ የተገነባው 14 ሜትር ርዝመት ያለው የወደብ እየሱስ እነመብሬ ድልድይ ጨምሮ ከ33 ሄክታር በላይ የማልማት አቅም ያለው በ18 ነጥብ 45 ሚሊዮን ብር የተገነባው ቦራ አነስተኛ የመስኖ ግድብ ካናል ስራ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጎጃም ሠውአለ እንደገለፁት ዛሬ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን በሚገባ ሠርተን በማጠናቀቅ ለህዝባአችን ክፍት ማድረግ የቻልነው በየደረጃው ካአለው ባለድርሻ አካላትና ከተከበረው ማህበረሰብ ጋር ተናበንና ተቀናጅተን በመሥራታችን በመሆኑ በቀጣይ በሁሉም ዘረፍ ይህን አፈፃፅማችን አጠናክረን በማስቀጠል እንደ ወረዳ የጀመርናቸውን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ የህዝባአችንን የመልማት ፍላጎት እውን እናደርጋለን በማለት ገልፀዋል ።

አያይዘውም አቶ ጎጃም አክለውም በቆላማ መስኖ፣በትምህርት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በልዩ ልዩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ያሳየውን የተሳካ ድምር ውጤት በቀጣይነት የሠላም ግንባታችንንም በማጠናከር ቀጣይነት ያለው የልማትና ጉዳናችንን በማይናወፅ ፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም ሌት ተቀን እንታትራለን ብለዋል።

ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጤፍን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጥራጥሬና ለፋብሪካ በሠፊው ግብዓት የሚሆኑ እንደ ቢራ ገብስና ድንች በብዛት የሚመረቱበት ወረዳ ስለሆነ በቀጣይ ወደ ወረዳችን ለሚመጡ አልሚ ባላሃብቶች የወረዳ አስተዳድራችን ሁሉንም ነገር በማመቻቸት በፀጋ የሚቀበል መሆኑን አቶ ጎጃም ለተሳታፊው አስገንዝበዋል ።

ሌላው በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ የትምህር ቤቶችን ገጽታ በመቀየርና ተደራሽነታቸውን በማስፋት ሂደት ውስጥ በርካታ ስራ እየተሰራ ነመሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ አመት የዞናችን የትምህርት ማህበረሰብ ለትምህርት ስራ በሰጠው ልዩ ትኩረት ማህበረሰቡን በማነቃቃት አልማን እንደትልቅ ጉልበት በመጠቀም ፤ የክልሉን ትምህርት ቢሮና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማቀናጀት ትምህርት ቤቶች ገጽታቸው እንዲቀየርና የተደራሽነት ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች እንንዲፈቱ በርካታ ስራዎች ተሠርቸዋል በማለት ኃላፊ በመልዕክታቸው አመላክተዋል ።

አቶ ጌታሁን ፈንቴ አክለውም እነዚህን ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ አልማ እና በወረዳው አስተዳደር በቅንጅት የተገነባ ሲሆን ለሚቀጥለው 2016 የትምህርት ዘመን ለመጀመር ዝግጁና የሚጀምር መሆኑን አሳስበዋል ።

በ2014 ዓ.ም የመስኖ ስራ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት የገጠመን ቢሆንም በ2015 ዓ.ም ግን በዘርፉ አመርቂ ስራ ለመስራት ተሞክሯል፣ ያሉት የአብክመ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አየልኝ መሳፍንት በጥናት እና ዲዛይን በዚህ ስምንት አመት ውስጥ በክልሉ 8134 ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል በማለት ገልፀዋል ።

ኃላፊው አክለውም ጠቅላላ በክልሉ 2.2 ሚሊዮን ሄክታር በመስኖ የሚለማ መሬት አለን ያሉት ኃላፊው የተገነቡ የግንባታ ፕሮጀክቶች በአጠቃቀም ረገድ የግጭት መንስኤ እንዳይሆኑ ፍትሃዊ የውሃ ክፍፍል መኖር እንደገባ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።

በወረዳው በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ማህበረሰብ የረጅም ዓመት ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ኢኮኖሚውን ለማሻሻል ጠቀሜታቸው ከፍተኛ መሆኑን በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

በአጠቃላይ በደባይ ጥላት ግን ከ86.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የመስኖ ካናል፣ የድልድይና የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታዎች ጨምሮ ሌሎች የመሠረተ ልማት ስራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኀላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

30/07/2023

እንደ ሕዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር የዉስጥ ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ መግባቢያችን ሊሆን ይገባል።

ሀገር ማለት የሰዉ ልጆች ማኅበራዊ ስሪት ነዉ። ይህ ማኅበራዊ መስተጋብር በዜጎች መካከል በሚፈጠር ተፈጥሯዊም ሆነ ሰዉ ሰራሽ ልዩነት ዉስጥ በሚፈጠር የተቃርኖ ስንጥቅ የሚሰፋዉ እና የሚደፈርሰዉ በሰላም እጦት ነዉ። ይህ ሁኔታ ሰላም የሰዉ ልጆች የእለት ከእለት ኑሮ ዉስጥ በአጽንዖት ከሚፈልጉት አንኳር ጉዳይ አንደኛዉና ብቸኛዉ መፍትሄ መሆኑን ያስረዳናል።

በዘልማድ ሰላም ከዉስጥ የሚመነጭ መሆኑን ባለመረዳት አንዳንዶቻችን አንጋጠን ሰላምን ከኛ ዉጭ እንናፍቃለን። አለፍ ሲልም ሀሳብን ወደ ጠረጴዛ ከማምጣት ይልቅ ወደ አክሳሪ እና ከፋፋይ ግጭት እንወስደዋለን። ያኔ የሰላም አየር ከባለቤቱ ይርቃል፤ አብሮነት ይናጋል፤ አንድነት ይኮሰምናል።

ሰላም በናፍቆት ወይም በመሻት አይመጣም ይልቅ ከራስ የሚጀምር አልፎም ለሌሎች የሚተርፍ ሰዋዊ እሳቤ ነዉ። በግርግር ወይም በብጥብጥ ዉስጥ ሰላምን መፈለግ ደመናን እነደመጨለፍ ይቆጠራል። በልዩነት እና በግጭት የሚገኝ ሰላም፣ የሚጸና አንድነት እና የሚቆም ሀገር የለም። የሚመለስ የክልሉ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄም አይኖርም። ፍላጎቶቻችንና ጥያቄዎቻችን ሁሉ የሚመለሱት በሰላማዊ ትግልና በሰላም ብቻ ነው።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ የከረሩ ልዮነቾችን ምክንያት አድርጎ እየጎላ የመጣዉ መጠራጠር እና አለመተማመን ሰላምን የሩቅ አገር አድርጎብናል። የዚህ ፈተና እያደገ መምጣት ደግሞ ሰላምን ከራስ የሚመነጭ ሳይሆን ከሌሎች የሚቸረን አድርገን በማሰባችን ነዉ።

እንደ ህዝብ አንድ ሆኖ ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ልማት ለማምጣት ከዉስጥ የጀመረ ሰላም ብቸኛዉ ጋሻ ነዉ። ሰላም ሲኖር አንድነት፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ እድገትና ልማት ተከታትለዉ ይመጣሉ።

የተለያዬ አሰላለፍ ውስጥ የገባ ማህበረሰብ ወይም ህዝብ የተሰናኘ የህዝብ አቅም ኑሮት ችግሮችን በአሸናፊነት መሻገር እንደማይችል የምንረዳበት ጊዜዉ አሁን ነዉ።

ስለሆነም እንደ ህዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ ቋንቋችን ሊሆን እንደሚገባ በመገንዘብ ለሰላም እና ለዉይይት በራችን ክፍት አድርገን ለጋራ ሰላማችን ዘብ በመሆን እንድ ሆነን በአንድ በመቆም በጋራ መስራት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን ልንረዳ ይገባል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 30/07/2023

ሁለተኛ ዙር የ2015 የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምስራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ ተፈታኞች ፈተናቸዉን ለመውሰድ ወደ ተመደቡበት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አሸኛኘት ተደረገላቸው።

መልካም የፈተና ጊዜ!

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 29/07/2023

በሰሜን ሜጫ ወረዳ የሚገኘው የቢኮሎ ዓባይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን መንገድ ቢሮ አስታወቀ።
*****
የቢኮሎ ዓባይ የኮንክሪት ድልድይ መጠናቀቅ ፋይዳው የላቀ መሆኑን በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሐመድ ያሲን ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የክልሉ እንዲሁም የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የመንገድ ቢሮ ኀላፊው አቶ መሐመድ ፕሮጀክቱ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የመንገድ ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር እምርታዊ ለውጥና ውጤት ያመጣበት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህ ደግሞ ቁልፍ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጥራት ያለው ዕቅድ ማዘጋጀት ፣ በተዘጋጀው ዕቅድ ዙሪያ ከፈጻሚ እና አስፈጻሚ ጋር የተሟላ መግባባት ላይ መድረስ እና ጠንካራ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት በመከተል የመጣ ለውጥ ነው ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ 44 የተንጠልጣይና የኮንክሪት ድልድይ ፣ 111 የመንገድ ፣ 17 የዲዛይን ጥናት ፣ 369 የመንገድ ጥገና በድምሩ 541 ፕሮጀክት በማቀድ ወደተግባር የተገባ ሲሆን 500 የሚሆነው ፕሮጀክት በማጠናቀቅ "ፕሮጀክት ላንጨርስ አንጀምርም " የሚለውን ግባችን 95 በመቶ አሳክተናል ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት ለጀመረው ሁለንተናዊ ሪፎርም የመሠረተ ልማት ግንባታና በፍትሃዊነት ተደራሽ ማድረግ መሠረታዊ ጉዳይ ሲሆን ከመሠረተ ልማት ውስጥ ደግሞ የመንገድ ዘርፍ የደም ሥር ስለመሆኑ አያጠያይቅም ያሉት ሃላፊው ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት በክልሉ 59 የመንገድ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ያሉ ሲሆን ሌሎች ከ 38 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ደግሞ በምህንድስና ግዥና በዲዛይንና ጥናት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ።

የቢኩሎ አባይ የኮንክሪት ድልድይ መጠናቀቅም የብዙ ፀጋዎች ባለቤት በሆነው በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫና በአዊ ብሔረሰብ ዞን ዳንግላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ህብረተሰቦችን የሚያገናኝ ድልድይ እንደመሆኑ ፋይዳው ብዙ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ የተያዘለት ቢሆንም በነበረው ቅንጅትና ቁርጠኝነት በአጭር ጊዜ የተጠናቀቀ ፕሮጀክት በመሆኑ የቢሮውን የፕሮጀክት የመምራትና ውጤታማነትደረጃ ያሻሻለ ነው ብለዋል ሃላፊው።

ሃላፊው አክለውም ለዚህ ስኬት የላቀ ሚና የተጫወቱ ተቋራጮች ፣ አማካሪዎች ፣ ከቢሮው እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ ባለሙያዎችንና የአካባቢውን ማኅበረሰብ አመስግነዋል።

መረጃው የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

22/11/2015

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 28/07/2023

ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን አጠናቀው በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ከሀምሌ 19-21/2015 ፈተናቸውን ሲወስዱ የቆዩ የስናን ወረዳ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሰላም ወደ ወላጅ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል።

መልካም የእረፍት ጊዜ መልካም ውጤት ይግጠማችሁ!!!

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 28/07/2023

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻችሁን የተወጣችሁ አካላት በነበራችሁ የስራ ትጋትና የባለቤት ስሜት በእጅጉ ኮርተንባችኋልና ፤ እናመሰግናለን።

አቶ ጌታሁን ፈንቴ
የምስራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ

የምስራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በሰላም መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ የምስጋና መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ አስተላልፈዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለዉ ቀርቧል፦

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር በዩንቨርስቲዎች እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ከ14,279 በላይ የሚሆኑት የዞናችን የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በባህርዳር፤ በመካነ-ሰላምና በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ተመድበው ከሀምሌ 19-21/2015 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተሰጠውን የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በመልካም ስነ-ምግባር አጠናቀዋል።

የባለፈው ዓመት ችግር እንዳይደገምና የፈተና ሂደቱ እንዳይታወክ የተሰራው ጠንካራ የቅድመ-ዝግጅት ስራ እና የባለድርሻ አካላት የትብብርና የቅንጅት ስራ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ ምክንያት ሁኗል።

የተማሪዎቻችንን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትም እጅግ መልካም ነበሩ። የቅድመ ዝግጅት ስራ በአግባቡ መስራት ለተግባር ምዕራፍ ስራው ስኬታማነት ቁልፍ መንደርደሪያ መሆኑንም በዚህ ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና አፈጻጸም ማረጋገጥ ችለናል።

የፈተና ሂደቱ እጅግ ሰላማዊና የተረጋጋ እንዲሁም የተሻለ ልምድ የተወሰደበትም ነበር።

ተማሪዎቻችንን ከቀለም ትምህርት በዘለለ በስነ-ምግባር ማነጽ ቁልፍ ተልዕኮ ተደርጎ ሲሰራ በመቆየቱ የተሻለና ተደማሪ ስኬት ታይቶበታል።

እንደነዚህ አይነት ተግባራት በሃገር አቀፍ ፈተና ብቻ ሳይሆን በክፍል ምዘናዎችና አጠቃላይ በመማር ማስተማር ሂደቱ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኝ ተማሪዎቻችን የፈተና ሂደት ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ ሌት ከቀን ያለመታከት የተጋችሁ የፈተና አስፈጻሚዎች፤ የዩንቨርስቲ አመራሮችና የግብረሃይል አባላት፤ ለፈተና ስራው የተመደባችሁ የጸጥታ አባላትና አመራሮች፤ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ተጠሪ መ/ቤት ሰራተኞችና የተሽከርካሪ ባለቤቶች እንዲሁም አሽከርካሪዎች ፤ በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች፤ የተማሪዎችን እውቀትና ስነምግባር ለማስተካከል ሌት ከቀን የደከማችሁ ውድ መምህራንና የትምህርት አመራሮች፤ የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት በመሆን አደራችሁን የተወጣችሁ ውድ ተፈታኝ ተማሪዎችና ወላጆች፤ በጥቅሉ የፈተና ሂደቱ ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ ድርሻችሁን የተወጣችሁ አካላት በሙሉ በነበራችሁ የስራ ትጋትና የባለቤት ስሜት በእጅጉ ኮርተንባችኋል፤ ምስጋናችንም በእጅጉ ከፍ ያለ ነውና በዞናችን የትምህርት ማህበረሰብ ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን።

ለትውልድ ማሰብ፤ ለሃገር ግንባታ መጨነቅ፤ ለጋራ ተልዕኮ በጋራ መረባረብና ባለቤት ሁኖ ያለድካም መታከት፤ መደማመጥና ተቀናጅቶ መስራት በእጅጉ የታየበት የፈተና አፈጻጸም ነበር። ይህ መልካም አፈጻጸም ቀጣይ ከሀምሌ 25-28/2015 ዓ.ም በሚሰጠው ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናም ከመጀመሪያው ዙር ባደገ መልኩ እንደሚፈጸም በመተማመን ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም የፈተናና ጊዜ እንዲሆንላቸው እመኛለሁ።

" በጋራ ጥረታችን ወደ ቀደመ ከፍታችን"!

አቶ ጌታሁን ፈንቴ
የምስራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 28/07/2023

ታላቁ የጮቄ ተራራ ጥብቅ የማህበረሰብ ስፍራ አስደማሚ አሁናዊ ልዩ የተፈጥሮ ገፅታ 👇 ጎጃም-አምሃራ

ጮቄን በጋራ በማልማት የቱሪዝም ማዕከል በማድረግ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 28/07/2023

የጤና ጣቢያዎችን የአገልግሎት አሰጣጥና የዉስጥ መሰረተ ልማቶችን በማሟላትና በማዘመን ጤናዉ የተጠበቀ ማህበረሰብን መፍጠር ይገባል፡፡

አቶ አዛዥ ይዘንጋዉ
የስናን ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ

የጤና ጣቢያችንን የዉስጥ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት እንዲሁም ለማህበረሰባችን ተገቢዉን የጤና አገልግሎት በመስጠትና በማዘመን ጤናማ ዜጋን መፍጠር ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ሃላፊዉ አያይዘዉም በወረዳዉ ዉስጥ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በተሻለ ሁኔታ የህፃናት የክትባት አገልግሎት፣ የእናቶች የማቆያ አገልግሎት እንዲሁም በሌሎችም በጥሩ ሁኔታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዉ በረ/ገበያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የዉስጥ ለዉስጥ መንቀሳቀሻ መንገዶችን ለሁሉዎችም ዜጎች ምቹ በሆነ መልኩ 1.1 ሚሊዬን ብር ወጭ በማድረግ በ2015 በጀት አመት ያሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የዉስጥ ለዉስጥ መንቀሳቀሻ መንገዶቹ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋዊያንና ለሴቶች እንዲሁም ለህፃናት ምቹ እንዲሆኑ ተደርገዉ የተሰሩ እንደሆነ ተናግረዉ በ2015 በጀት አመት ሞዴል ጤና ጣቢያ ለመፍጠር በተሰራዉ ስራ ዉጤታማ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

የእናቶች እና የህፃናት ጤናን ለማሻሻል አበረታች ስራዎችን በትኩረት ሲሰሩ እንደቆዩ አቶ አዛዥ ገልፀዉ በሁሉም የወረዳዉ ጤና ጣቢያዎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥም ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸዉንም ተናግረዋል፡፡

የአንቡላንስ አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠት የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ምክንያት በጤና ጣቢያችን ከፍተኛ የሆነ ችግር የነበረ መሆኑንና በዚህ በአዲሱ በጀት አመት ይህን ችግር ለመፍታት ከወረዳዉ አስተዳደር ምክር ቤት ጋር በመነጋገር ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዛዥ ተናግረዉ ሌሎችንም ጤና ጣቢያዎችን እንደ ረ/ገበያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሞዴል ለማድረግ እቅዶችን አቅደዉ እየሰሩ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

“ጤናማ ህይወት ለጤናማ ማህበረሰብ!!”

ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም
መረጃው የስናን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

28/07/2023

ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት በቀለ እንደገለጹት በ2015 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት 1ቢሊዮን 881ሚሊዮን 547 ሽህ 002 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እሰከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ 1ቢሊየን 725ሚሊዮን 599 ሽህ 973 ነጥብ 15 ብር ወይም የእቅዱን 91 ነጥብ 71% መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 360 ሚሊዮን 290 ሽህ 918 ነጥብ 45 ብር ወይም 26 ነጥብ 38 በመቶ ብልጫ እንዳሳየ አመላክተዋል ፡፡

መምሪያው ይህን ማሳካት የቻለው በየደረጃው ያለ የገቢ አመራሩ፣ማኔጅመንት እና አጠቃላይ ሰራተኛው የመፈፀም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ ፣ በየደረጃው ያለው አመራር ክትትልና ድጋፍ ጠንካራ መሆኑ ፣የአገልግሎት አሰጣጣችንን ለማሻሻል ጥረት መደረጉ፣ የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ሰራተኞች ከስራ አስከማሰናበት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ፣ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለን ቅንጅታዊ አሰራር እየተሻሻለ መምጣቱ እንዲሁም የተለያዩ መመሪያዎችን እና አሰራሮችን ፈጥኖ ወደ ተግባር መቀየር መቻሉ ለተገኙ ውጤቶች ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ ያሉት ወይዘሮ ገነት በበጀት
አመቱ እቅዱን 100 በመቶ እንዳይሳካ ደግሞ የህገ ወጥ ግብይት መስፋፋትና ሃሰተኛ ደረሰኞ መበራከት፣ ግብር ከፋዮች ደረሰኝ አለመስጠት እና ተጠቃሚውም ግብይት ሲፈጽም ደረሰኝ አለመጠየቅ እና ውዝፍ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ አለመቻል ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ ብለዋል።

በተያዘው 2016 በጀት ዓመት በተጠናቀቀው አመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማሰቀጠል ፣ ጉድለቶችን በማረም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ ወይዘሮ ገነት ተናግረዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው ።

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

28/07/2023

ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት !!

የተረጋጋ ዴሞክራሲያዊ ስርዓተ መንግስት ለሀገር ብልፅግና እና ለዜጎች ዘላቂ ሰላም ፋይዳው የጎላ መሆኑ አያሻማም። በመደመር ሀገር በቀል እሳቤ የተቃኘውና በአደረጃጀት፣ በስትራቴጂውና በፖሊሲው እንዲሁም በአባላትና በደጋፊዎቹ ብዛት በሀገራችን ከሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እጅጉን ልቆ በመገኘቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ለአምስት ዓመት እንዲመራው ይሁንታውን በድምፁ ያረጋገጠለት ብልፅግና ፓርቲ ጠንካራና ዘለቄታዊ ተቀባይነት ያለው ሀገረ መንግስት የመገንባት ፅኑ እምነት ተጥሎበታል፤ አቅሙም አለው።

ጠንካራና የተረጋጋ ሀገረ መንግስት ካለመገንባት ጋር ተያይዘው በሚመጡ ችግሮች በርካታ የአፍሪካና የዓለም ሀገራት ሉዓላዊነታቸው ለአደጋ ይጋለጣል ዜጎቻቸውም በሰላም እጦት ይሰቃያሉ። በአንፃሩ በሀገር ጉዳይ የማይደራደሩ ጥራት ያላቸው ጠንካራ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏቸው ሀገራት በተፈጥሯዊና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ውስጥም ሆነው ለችግሮቻቸው በቀላሉ እጅ አይሰጡም።

ብልፅግና ፓርቲም በሀገር ህልውና ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለብዙዎች ለማመንና በሚከብድ መልኩ በጥበብ እያለፈ መሆኑ ሲታይ በእርግጥም ትክክለኛውን መንገድ እንደያዘ መረዳት ይቻላል።

"የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል" እንደሚባለው ብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ከማስፋት በተጨማሪ በህዝብ ይሁንታ ካገኘው ሀገር የመምራት ሀላፊነት ላይ ተፎካካሪ ፓርቲዎችንም በማሳተፍ ቀጣይነት ያለው ሀገረ መንግስትን በፅኑ መሰረት ላይ እየገነባ መሆኑን እያስመሰከረ በመደመር ጎዳና ጉዞውን ቀጥሏል።

በፖለቲካዊ አሰላለፍ ሁሉም ፓርቲ አማራጭ የሚለውን ሀሳብ ለህዝብ ያቀርባል፤ በምርጫ ተቀባይነት ያገኘው ልክ አሁን ብልፅግና ፓርቲ እያደረገ እንዳለው ሀገር ይመራል። በሀገር ጉዳይ ደግሞ ያለው ብቸኛ አማራጭ በአንድነት መቆም በመሆኑ ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ከህዝብ መብትና ፍላጎት የሚፃረር ነውና የትም አያደርስም።

ፓርቲያችን ብልፅግና በጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ ሀገረ መንግስት እውን እንዲሆን በተራማጅ እሳቤው እራሱን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ በተቋም ግንባታ፣ በህዝብ አሳታፊነትና በአሰራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም የህግ የበላይነት መከበር ላይ በትኩረት ይሰራል። እየሰራም ይገኛል።

ሰላም እና ብልፅግና ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ !!


Party

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 28/07/2023

የእኛ እያለን አንድም ተማሪ በደብተር እስክርቢቶና በኢንፎርም እጦት ከትምህርት ገበታዉ አይቀርም!!
****************************************-

በምስራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የወጣቶች ማካተት ንቅናቄና ተሳትፎ ቡድን ዛሬም እንደ አምናና ታች አምናዉ የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ የለኝምና አልማርም ብለዉ ተስፋ የቆረጡ ህፃናትን አለሁልሽ፣አለዉልህ ብላችሁ ለበርካታ አመታት ስትሰጡ እነሱ ደግሞ ከጓደኛ ሳያንሱ በሙሉነት፣በኩራትና በደስታ በትምህርት ገበታቸዉ ተገኝተዉ በርካታ እህት ወንድሞቻችን ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ስለዚህ እንደዚህ ቀደሙ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለወላጅ አልባዎች፣ቤተሰቦቻቸዉ በሀብት ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች ለደብተርና እስክቢርቶ እንዲሁም ወላጅ አባታቸዉ ዘመቻ ሄዶ ለኛ ሲል መተኪያ የሌላትን ህይወታቸዉን ለሰጡን የጀግኖቻችን ልጆች ከደብተርና እስክርቢቶዉ በተጨማሪ ዩኒፎርም ለመግዛትና እንደማንኛዉም ተማሪ ሙሉ ለማድረግ በወረዳው በጎ አድራጊ ወጣቶች እና የስናን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የወጣቶች ማካተት ንቅናቄና ተሳትፎ ቡድን የበጎ አድራጎት ስራውን በንቅናቄ የጀመረ ሰለሆነ እንደዚህ ቀደሙ በቻላችሁትና አቅማችሁ በሚፈቅድላችሁ መጠን ከዛሬ ጀምሮ ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን ማስተላለፍ እንወዳለን።

በዛሬው ዕለት ማለትም20/2015 በተደረገው የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ የማሰባሰብ ስራ ላይ ድጋፍ ያደረጉ እና አቅማቸው የሚፈቅደውን አስተዋፅኦ ያደረጉ ለጋስ ማህበረሰቦችን የስናን ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የወጣቶች ማካተት ንቅናቄና ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ ውብሸት ነጋሽ መረጃውን ለተቋማችን አድርሰውናል።

በዕለቱ በበጎ ፍቃቅድ ንቅናቄው የተሳተፉ
1. አቶ ዋለልኝ መንገሻ የማሰሮ ትሬዲንግ ባለሀብት 10,000 ብር የሚያወጣ የትምህርት ቅሳቅስ ገዝተው ሊያቀርቡ ቃል ገብተዋል፤
2. አቶ አግደው በቀለ 1500 ብር አስገብተዋል
3. አቶ ብናልፋው ባሴ 500 ብር
4. አቶ እንደሰው አዘነ 1ደርዘን ደብተር
5. አቶ ዘውዱ ላመስግን 500 ብር
6. አቶ አስራቱ አላምኔ 500 ብር
7. አቶ በረከት ዘውዱ 1ደርዘን ደብተር
8. አቶ ግዛቸው ጌታነህ 1ደርዘን ደብተር ከነእስኪብርቶው
9. አቶ ሙሉሰው ምንይዋብ 500 ብር
10. አቶ ውባረገ ይርሳው 1ደርዘን ደብተር ከነእኪብርቶው
11. አቶ ይሁን ጎሹ ለ2 ተማሪ ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ከነ ዩኒፎርሙ
12. አቶ ዋለ አንተነህ እምሬ 500 ብር
13. አቶ አወቀ ምናሉ 500 ብር
14. አቶ አዛዥ ይዘንጋው 1ደርዘን ደብተር
15. አቶ ሀብታሙ ስንሻው 1ደርዘን ደብተር
16. አቶ ጥጋቡ አሻግሬ 1 ደርዘን ደብተር
17. አቶ ባንቴ አለሙ 200 ብር
18. አቶ ይስማው ቀራለም 200 ብር
19. አቶ መንግስቱ አደመ 200 ብር
20. አቶ ታደገ ፈንታ 100 ብር
21. ወ/ሮ ትሁን ዳኛው 100 ብር
22. አቶ ሀብታሙ 50 ብር
23. አቶ ወርቁ ገላ 50 ብር
24. አቶ አንማው ልመኔ 5 እስኪብርቶ ቃል የገቡና በአካውንት ገቢ ያደረጉ ነጋዴዎቻችን ሲሆኑ ድጋፍ አድርጋቹሁ ስማቹሁ ያልተጠቀሰ እና የተዘለለ ካለ ይቅርታ እየጠይቅን ድጋፉ በይፍ የተጀመረ መሆኑን አውቃቹሁ በቀጣይም የትምህርት ቁሳቁስ የሀብት ማሰባሰብ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ስለሆነ እንድትሳተፉ ጥሪ ማስተላለፍ እንወዳለን።

ሀምሌ 20 /2015 አ.ም
መረጃው ስናን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን

Photos from Sinan Woreda Prosperity party's post 27/07/2023

ምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያና ሸበል በረንታ ወረዳ በበጀት አመቱ ዜጎችን ከዐይነስውርነት በመታደግ በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር 1ኛ በመውጣታቸዉ የዋንጫና የቁሳቁስ ተሸላሚ ሆኑ፡፡

ዞኑ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ የሆነው በአንድ ዓመት ውስጥ 13ሽ 874 ሰዎችን ከዓይነ ስውርነት በመታደጉ በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር 1ኛ በመውጣቱ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ሽልማት የተበረከተለት ትራኮማን በመከላከልና መቆጣጠር ሥራው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለመገምገምና በቀጣይም በሽታውን ለማስወገድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር በተካሄደበት የማጠቃለያ ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው የትራኮማ በሽታን ከዞኑ ነጻ በማድረግ ዜጎችን ከዓይነ ስውርነት ለመታደግ ሌትና ቀን የሰሩ አካላትን አመስግነዋል፡፡ አቶ አብርሃም በመልእክታቸው ይህ ተግባር ተወዳድሮ አንደኛ ከመውጣት በላይ በዓይነ ስውርነት የሚሰቃዩ ዜጎችን ቀዶ ጥገና በማድረግ ከአይነ ስውርነት በመታደግ ብርሃን እንዲያገኙ ማድረግ የሚሰጠው የህሌና እርካታ ይበልጣል ብለዋል፡፡

በዚህ ስራ የተሳተፉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች አስተዳደሩ በእጅጉ ያመሰግናል ያሉት አቶ አብርሃም በቀጣይ ትራኮማን ለማስወገድ ለምንሰራው ስራ ሁሉም አካል ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለስራችን መሳካት በጤናው ዘርፍ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በተጨማሪ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ ነበር ያሉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት በበጀት አመቱ በተደረገ ርብርብ 13ሽ 874 ሰዎችን ከዓይነ ስውርነት መታደግ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ስራ በርካቶች እንዲሳተፉበት አድርገናል ያሉት አቶ መልካሙ የታካሚ ልየታ በሚካሄድበት ወቅት ከፍተኛ እርብርብ ያደረጉ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ፣የመንግስት ሰራተኛ፣ጤና ባለሞያዎች፣በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና አጋሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በሽታው የዞኑ ህዝብ የጤና ችግር ከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በሚደረገው ትግል የሚጠበቅብንን እንድንወጣ በማለት ጠንካራ ጥሪ አቅርበዋል።

✅ምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር 1ኛ በመውጣት
✔ ዋንጫና ሰርተፍኬት
✅ ምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ 1ኛ በመውጣት
✔ ዲስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ✔ ኤልሲዲ✔፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን
✅ ሸበል በረንታ ወረዳ 1ኛ በመውጣት
✔ ዲስክቶፕ ኮምፒዩተር፣
✔ ኤልሲዲ✔፣
✔ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣
✔ ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሲሆኑ ከዞኑ

✅ 3 ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው ሰርትፍኬትና 2000 ሊትር የሚይዝ ሮቶ እና 4 የዓይን ቆብ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ከ16-12ሽ ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

27/07/2023

"በማንነታችን ላይ ዳግም ለአፍታ እንኳን ተዘናግተን የተራዘመ መከራ እና ባርነት ለመቀበል ፍጹም አንፈቅድም" !
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

የግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ ሴራ እና ተንኮል መጋለጫ፣ የሩብ ምዕተ ዓመት አምባገነናዊ አገዛዝ መሸኛ፣ የሦስት አስርት ዓመታት የጨለማ ጉዞ ምዕራፍ መቋጫ እና የአዲሱ ትውልድ የነጻነት አደራ ርክክብ ትናንት በቅርቡ የተስተዋለ ክስተት ነበር፡፡ እልፎች ማንነታችን ይከበር ብለው አደባባይ ድረስ ዘልቀው በመውጣት የከበረ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ከተፈጥሯዊ ነጻነት ባሻገር የጠየቋቸው እና ለትግል የሚያበቁ አያሌ ምክንያቶች ነበሯቸው፡፡

ማኀበረሰባዊ ማንነትን የሚያስቀጥል ትግል ደግሞ በትውልድ ቅብብሎሽ መካከል የሚጸና የነጻነት መርከብ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለማንነት መከበር በሚደረግ ትግል ውስጥ ውስኖች እንደ አብሪ ኮከብ ጎልተው ቢታዩም የትግሉ ባለቤት እና ሞተር ግን ሕዝብ መኾኑ አይካድም፡፡ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ ሕዝብ የዘመናት የነጻነት ትግል መልህቅ በታሪክ አጋጣሚ በአዲሱ ትውልድ መዳፍ ውስጥ ገብቷል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በጀቱ የሕዝብ ቁጭት እና ብሶት ነው ያሉት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ናቸው፡፡ የወልቃይት ወረዳ በቅርቡ ያስገነባቸውን የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች አጠናቆ አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓተ ላይ የተገኙት የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብን ለዘመናት ሞት፣ ስደት እና እንግልት ከዳረጉት የህወሐት ፖለቲካዊ ሸፍጦች መካከል አንዱ ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት አለመኖር እንደነበር አንስተዋል፡፡

ለዘመናት በማንነቱ ምክንያት ፍትሐዊ ልማት ናፍቆት የኖረ ሕዝብ በጥረቱ የሠራውን የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በማየት ትናንት የበደሉን ሁሉ ሊሸልሙን እና ሊያመሰግኑን በተገባ ነበር ብለዋል፡፡

ወልቃይት ጠገዴ በርካታ የመልማት ጸጋዎች እና አቅሞች ያሉት አካባቢ ነው፡፡ ነገር ግን ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በህወሃት አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ ውስጥ እንዲቆይ በመገደዱ ለከፋ ሰብዓዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማኀበራዊ ስብራቶች እንዲዳረግ አድርጎት እንደቆየ ኮሎኔል ደመቀ አንስተዋል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በተለያዩ የትግል ስልቶች እና አማራጮች የተጫነበት የባዕድ ማንነት እንደማይገልጸው ተናግሯል፡፡ ነገር ግን የነበረው ሥርዓት ነባር ባለእርስቶችን አፈናቅሎ የእኔ ነው የሚለውን ማኀበረሰብ ማጽናት በመኾኑ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን ብዙ እርቀት ተጉዞ ነበር፡፡

የወልቃት ወረዳ ማዕከል የኾነችው ወፍ አርግፍ ከተመሠረተች አያሌ ዓመታትን ብታስቆጥርም ይህ ነው የሚባል የመሠረተ ልማት ግንባታ የላትም፡፡ ኮሎኔል ደመቀ እንደሚሉት በከተማዋ መካከል አልፎ የሚሄደው የአስፓልት መንገድ የተሠራበት ዓላማ ግልጽ ቢኾንም ወፍ አርግፍን ሳይነካ እንዲያልፍ ለማድረግ የተሠራውን ሴራ ሕዝብ ያውቀዋል ብለዋል፡፡ በሕዝብ እምቢተኝነት መንገዱ በከተማዋ መካከል አልፎ እንዲሄድ ቢገደዱም፡፡

ኮሎኔል ደመቀ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ የነበረውን መዋቅራዊ ሴራ በሚገባ ተረድቷል ነው ያሉት፡፡ “የማንንም ርስት አልፈን አልነካንም፤ ያስመለስነውም ለረጂም ጊዜ ታግለንና መስዋእትነት ከፍለን ማንነታችንን ነው” ብለዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ የወልቃይትን እውነት መመስከር እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ እና አሥተዳደር አሁን በሙሉ አቅሙ ልማት ላይ ነው፡፡

"ከማንም ጋር ግጭት አንፈልግም በማንነታችን ላይ ግን ዳግም ለአፍታ እንኳን ተዘናግተን የተራዘመ መከራ እና ባርነት ለመቀበል ፍጹም የማንፈቅድ መኾኑን ሊታወቅ ይገባል" ብለዋል የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊው፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር በሀገረ አሜሪካ ገብቶ የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እየሰማን ነው ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የትግራይ ሕዝብ በውሸት መመራት ይበቃኛል ማለት አለበት ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ መገናኛ ብዙኀኖች ሳይቀር የሚሰብኩትን እና የሚጎስሙትን የጦርነት ነጋሪት ሊገነዘበው እንደሚገባም ኮሎኔል ደመቀ ተናግረዋል፡፡

ህወሃት አካባቢውን የግጭት ቀጠና ለማድረግ የሚሠሩትን ዘርፈ ብዙ ሙከራ በሚገባ እናውቃለን ነው ያሉት ኮሎኔል ደመቀ። የተለየ ሃሳብ እና ፍላጎት ያለው ሁሉ ሃሳቡን አደባባይ አውጥቶ ይሞግት፤ ሃሳብ ያሸነፍል ወይም ይሸነፋል፡፡

ይሁን እንጅ ውስጥ ለውስጥ መሄድ እና የአካባቢውን ሕዝብ ዳግም ያማያባራ ዋጋ ለማስከፈል የሚደረግ የትኛውም አይነት እንቅስቃሴ ተገቢነት የለውም ብለዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው፡፡

°~~~~°
"ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

26/07/2023

“ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ቀብታ ሁመራ፣ የበጌ ምድር ግዛት እንጂ የትግራይ አካል ኾነው አያውቁም" አቶ ገ/መድህን አርአያ፣ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የሥራ አመራር የነበሩ

"ከዛሬ 45 ዓመታት በፊት፣ ኢትዮጵያውያን የግራ ዘመም ፖለቲከኞች አውራ የኾነው ትህነግ (ወያኔ) በተከለው አሜኬላና በቀበረው የሴራ ፖለቲካ ፈንጅ እርስ በርስ ተባልተው ዛሬ ላለንበት የፖለቲካ መድረክ ከመብቃታችን እና ሀገሪቱ በዘር በሽታ ከመታመሟ በፊት፣ ትህነግም ወልቃይት ጠገዴን የቅዠቱ አካል አድርጎ ካርታ ላይ ሳይስል፣ በወያኔ ከፍተኛ አመራር አባላት አማካይነት ለወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አንድ ኹነኛ ጥያቄ ቀርቦ ነበር" ይላሉ የቀድሞ ታጋይ ገ/መድህን አርአያ።

በወቅቱ ይላሉ፣ እኒኽ ጉምቱ ፖለቲከኛ፣ "ወልቃይት ጠገዴ የማን ግዛት አካል ነው...?" ተብለው ሲጠየቁ፣ በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ያለምንም ፍርሓትና ማመንታት “ወልቃይት ጠገዴማ፣ የበጌ ምድር ክፋይ፣ የአማራ ሕዝብ ርስቱ ነው" ብለው መለሱላቸው ይሉናል።

አቶ ገብረመድህን አርአያ በትህነግ ቤት ከከፍተኛ አመራር አባልነታቸው ባሻገር፣ የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ ኾነው ሰርተዋል። ስለኾነም የትህነግን የተንሸዋረረ እያታና የተወላገደ አሥተዳደግ ጠንቅቀው የተረዱና ለዘመናት በተለያዩ የትግል ሥልቶች ሲታገሉ የመጡ ጨዋ ኢትዮጵያዊ ናቸው ..።

የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራርና የፋይናንስ ኃላፊ አቶ ገብረመድህን አርአያ በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም በኢትዮ ሚዲያ ጎልጉል ድረ-ገጽ ላይ "በወልቃይት ጠገዴ የዘር ማጥፋት ወንጀል" በሚል ፅሁፋቸው ወልቃይት መሰረታችን የበጌ ምድር ነው፤ ይህ መሬት ከጥንት ጀምሮ የጎንደር በጌ ምድር ግዛት ተብሎ ይጠራ ነበር ዋና ከተማውም ጎንደር ነው ይህም ከጥንት ጀምሮ የበሩት የኢትዮጵያ ነገስታት እስካሁን ድረስ ያሉ መንግስታት እውቅና ሠጥቷቸዋል በማለት ይናገራሉ።

በተጨማሪም ተከዜ ወንዝ አማራንና ትግራይን የሚለይ ድንበርም ነው ሲሉ ገ/መድህን አርአያ ይገልፃሉ።

በወያኔ በኩል "ወልቃይት የማን ነው...?" ለሚለው ተደጋጋሚ ጥያቄ የታሪክ መዛግብት እንደሚያሳዩት የአማራ ተወላጆች ለእነዚህ ጥያቄዎች ግልጽና ቀጥተኛ መልስ በመስጠታቸው ተደብድበዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተረሽነዋል ሲሉ አቶ ገ/መድህን አርአያ ያስረዳሉ።

የቀድሞ የህውሓት ታጋይ ገ/መድህን አርአያ ከሌሎች ሚዲያ ጋርም ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ ግዛት ኾኖ አያውቅም፤ ተከዜ አማራንና ትግራይን የሚለያቸው ድንበር ነው ታሪካዊ እውነታው ይህ ነው ሲሉ መስክረዋል።

ወያኔ ከኢትዮጵያ የመገንጠል እና የራሱን ታላቋን ትግራይ የመመስረት የጥላቻ ህልም ነበረው የሚሉት አቶ ገ/መድህን አርአያ እውነታውንም በግልጽ አስረድተዋል።
ሕወሀት ከመጀመርያው ጀምሮ ከኢትዮጵያ በመገንጠል የራሱን ህልም የሆነች "ታላቋ ትግራይ" ለመመስረትና የወልቃይት መሬት ለም በመሆኑና በእርሻ ከሁሉም የተሻለ ስለሆነ ወደ ራሱ የመሠልቀጥ በሽታ ተጠናውቶት ነበር።

ወያኔ የወልቃይት መስመር የኢኮኖሚ ኮሪደር ከመሆኑ ባሻገር ወደ ሱዳን ለመግባትና ለመውጣት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ወልቃይትን በጉልበት ወደ ራሳቸው ግዛት ጠቅልለውት እንደነበር ተናግረዋል።

ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ቀብታ ሁመራ የአማራ ሕዝብ ግዛት አካል ብቻ ሳይኾን የበጌ ምድርም መፈጠሪያ ነው ሲሉም አስረግጠዋል።

አሚኮ

•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•

Telephone

Website