Gofa Area Realities

Gofa Area Realities

የጋራ እድገትን ማረጋገጥ።

17/03/2021

"ከየትም መጥቶ አያስተዳድራችሁም፤ አመራሮች የገዛ ልጆቻችሁ ናቸው።" እያለን ነው በእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ድኩማን ለዘመናት ሽባ ያደረገን ኢህአዴግ😁😉😁
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

👨‍🎓የጎፋ ምሁራንና የህዝቡ የነፃነት ትግል አንድምታ👩‍🎓
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

የነፃነት ታሪክ ሲወሳ በኢትዮጵያ 🤴 👸 አመክንዮ እንደገል ክስክስ ያለበት እና የተማሪዎች፣ የምሁራንና የህዝቡ እንከን የለሽ ትግል በአርሶ አደሩና በከተማ ነዋሪው ላይ "እግዚአብሔር የቀባን የሠለሞን ግንደ ውላጅ ደመ ንፁህ ነን" ባዮች የጫኑብንን እርጥብ የግፍ የበደል ቀንበር እንደ ቦቆሎ አገዳ በእጁ እምሽክ አድርጎ ህዝቡ የጓጓውን የተጠማውን ነፃነት ሊጎናፀፍ እጆቹን በዘረጋ ጊዜ ከጉልበት በቀር #ለጥበብ #ለዕውቀትና #በሀሳብ ብልጫ በመሸበት ለማደር ፈቃደኛ ያልነበረው #የደርግ ወታደራዊ ጁንታ ከሥልጣኑ አተያይ የተነሣ ስመ ጥር ምሁራንና ተማሪዎችን እንደ በግ ፈጅቷቸው የተራበውን ሥልጣን እንደሸማ በእጁ ጠቅልሎ አስገባ።

? ፣ እያለ ወጣቱን ማገደ። ያመለጡት ጥቂቶቹ በእግራቸው ኳትነው በአቋራጭ አውሮፓና አሜሪካ ገብተው ስለእናት ሀገራቸው እና በህዝባቸው ላይ የሚፈጸምን ግፍ እና ሰቆቃ ለአፍታም አንደበታቸውን ሳይገቱ የዓይናቸውን ቅንድብ ሳይከድኑ በብዕራቸው ቀስት እንደሞገቱ እንደተዋጉ ትናንትን አልፈው ዛሬ ላይ ደርሰዋል።

ደርግን ገዳይ ጨፍጫፊ አምባገነን ነው ያለው #ኢህአደግ የሰው ልጅ ህይወት እንደቅጠል ከረገፈ በኋላ የሥልጣን ኮርቻውን ተቆናጠጠ። "ተጠምታችኋል ፣ ታሪዛችኋል ፣ ተርባችኋል ፣ ምድራዊ ቤት ተነፍጋችሁ ለቁር ለሀሩር ተዳርጋችኋል " ሲል ሠፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ በደም #በአጥንት እና #ጉልጥምት ቆጠራ #ከፋፍሎ ማለትም በግርድፉ ሲተረጎም "የእኔ መንገድ እውነተኛ እና ብቸኛው መንገድ ነው " " በሚል ስብከት ጀመረ። ህዝቡ የደርግን በጭካኔ የታጨቀ አገዛዝ ሳይረሳ "ባህላችሁን ቋንቋችሁን አሳድጉ" በሚል #የአሞራ #ግርዶሽ የሠው ልጅ ራሱን እንዲጠራጠር ከባልንጀራው ጋር በቅራኔ እንዲፋጠጥ ወቅትና ጊዜ እየለየ የሚፈነዳ ። በዚህም ምክንያት በብዙ ድካምና መከራ የተሰበሰበ የሀገር ሀብት እና ንብረት እንደ ጠላት ሀብት እና ንብረት በከንቱ ጋዬ። ክቡር የሆነው የሠው ልጅ ህይወት እንኳን ለሰው ልጅ ይቅር እና ህይወት ላለው ማንኛውም ፍጥረት ሊደረግበት በማይገባ ጥላቻ በወለደው ጭካኔ ተወልዶ ባደገበት ፣ ወልዶ በሳመበት ፣ ዘርቶ በቃመበት ፣ በሃገሩ ፣ ወገን የወገኑን አንገት በካራ ፣ ስጋውን ለአውሬ እንዲሰጥ ተደረገ። ባልና ሚስት ባጠቃላይ በተሰብ ደልቷቸው ከማይኖሩበት ሁሌ ሞልቶ ከማይሞላው ኑሮ ፣ ኑሮ ተባለና ከሚያፈሰው ጎጆአቸው ተፈናቀሉ ፣ በሀገራቸው እና በወገኖቻቸው መካከል ተሰደዱ ፣ የስደተኛ ክብር ቢሰጣቸው ባልከፋ ነበር ፣ ነገር ግን ድንኳኑን እየናፈቁ ካዛፍ እና በቅጠል ስር ሲጠለሉ ተመለከትን። ወደ መጣህበት ወደ መጣሽበት ተብለው ታረዱ ተሳደዱ ፣ ዘርህ ዘርሽ ተባብለውም እንዲፋቱ ተሰበኩም ተፋቱም። ህፃናት ሴቶች በጎልማሳ ወንዶች ተደፍረው ሽንት ሰገራቸውን መቆጣጠር የማይችሉበት ግፍ የተፈጸመባቸውን ዜጎች በሃገራችን አቅመቢስ ሆነን እንደዘበት ቁጭ ብለን እንደተለመደ ዜና ተመለከትን።

በሂደቱ ሁሉ "ከየትም መጥቶ አያስተዳድራችሁም አመራሮች የገዛ ልጆቻችሁ ናቸው" ያለው ኢህአዴግ በኛው ልጆች አናታችን ላይ ያለፉትን ጊዜያት በተንኮል የመለያየትን ክፉ የሆነን የመልካም አስተዳደር ሚጥሚጣ ሲድጥ ኖሯል። በጉዳዩ የተገፋ ፣ ያዘነ ግለሰብ ፣ ቡድን ይግባኝ እንኳ እንዳይጠይቅ ተደርጎ በዘርና በጥቅማጥቅም ከወረዳ እስከ ክልል በሹመት ገመድ የተጋመደው አመራር ዓይንና ጆሮ ቢኖረው እንጂ ልብ እንዳይኖረው ተደረጎ ተበጀ። ኢህአዴግም የሴራውን ሀፍረት ለመሸፈን በጠና እንደታመመ በሽተኛ በግምገማ ወሳንሳ ወይም ቃሬዛ አመራሩን ከአንዱ ሕክምና ተቋም ወደ ሌላኛ ተቋም ሲያጓጉዝ ጊዜው መሸበት።

ከላይ ለማስታወስ የፈለግነው " ፣ " እንዲሉ እና የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ብቻ ሳይሆን እውነትም ስለሆነ ነው። ከላይ በጠቀስናቸው የሃገራችን ታሪክ ውስጥ ስለአካባቢያችን እና በኖርንበት በኢህአዴግ ዘመን የአካቢያችንን እውነታ ለመዳሰስ እና ለማስገንዘብ ይሆናል። የጎፋ ምሁራን እንደ አሸዋ እንዲበተኑ እርስ በርሳቸው እንዳይያዙ ፣ በኩር የሌለው አካባቢ እንዲሆን ፣ አንዱ የሌላውን ዋጋ እንዳይረዳ ፣ በመጠላለፍ እና በማጠላለፍ እንዲፋጁ እንጂ የላቀ ሀሳብ አመንጭተው የአካባቢያቸውን ስብራት እንዳይጠግኑ እንዲሸሹና ተወልደው ባደጉበት ህብረተሰብ ባይተዋር ሆነው እንዲገፉ ያደረጋቸው ምንድነው? የሚለው መጠይቅ የጽሁፋችን ማዕከላዊ ሀሳብ ይሆናል ።

ያኔ በዚያ ዘመን መስማት ከመናገር ይልቃል በማለት በትምህርት ቡቃያ ሰንብተው ዕውቀት ቃርመው ፣ ሃሳብ ቋጥረው የተመለሱ የአካባቢችን ተወላጆች አናሳ ነበሩ። በተፈጥሮ ልበ ብሩህ የነበሩ ልጆቻችን በተማሩበት የሙያ ዘርፍ አካባቢያቸው ላይ እንዳይሰሩ ከማድረጉም በላይ ፣ እንደውሀ ቧንቧ የተቀበለውን ብቻ ፣ ወደታች የሚያፈስ በየደረጃው የተቀመጠ ወንበርተኛ ካድሬ የተማረውን ክፍል ማየት አለመፈለጉ የተቀመጠበት አላማ ውጤት ነው። "ትምክተኛ " የሚል የዳቦ ስም አውጥቶ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶ ማሳደድ። ዕውቀቱ የፈጠረለትን በራስ የመተማመን ስሜት አንግቦ የህዝብን ፣ በልማት ተጠቃሚና ዴሞክራሲያዊ መብቱን አውቆ ፣ እንዲከበርለት በተገኘው መድረክ ሁሉ ሳይፈራ ሳይቸር ተንትኖ አፍ አስከፍቶ እንደ አንበሣ ከሚያገሣው ኢህአደግ ጋር ግንባር ለግንባር የተጋፈጠ የግል ጥቅሙ ሳያጓጓው የአደርባይነትን ጭምብል በመግፈፍ አቋም ወስዶ ይታገል የነበረው ምሁር ወዴት ተሰደደ? ማንስ አሳደደው? የተማሩ ልጆችን አስተባብሮ በመያዝ አካባቢን ማሳደግ እና መለወጥ አይቻልም ነበርን? ወይስ ደናቁርቱ የሚበጠብጡት እና ግራ እያጋቡ የሚያፋጁት ፣ እያፋጁ የሚዘርፉት ፣ ባለቤት አልባው ህዝብ በምሁራን መመራት አልፈልግም ሰለሚል ይሆን?

በእርግጥ ፖለቲካዊ አመለካከት እንኳን በህዝብ ውስጥ ይቅር እና በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እንኳን ልዩነት ለኖር እንደሚችል ብንገነዘብም ፣ እስቲ ለማንኛውም ህመማችሁን አንድ አንዱን እውነታ በጨረፍታ ልናሰታውስ ወደድን ፣ ዛሬ ላይ ለምን ኢዜማን መረጠ? ተምሮ ተመራምሮ ሲመጣ ለህዝብ እንዲያገለግል ኢህአዴግ ሹመት ሰጥቶት አልነበር? ዶ/ር #ፍሬው ጎፋ ዙሪያ ተሹሞ አልነበር?የትምህርት ዕድል ሰጥተናል በማለት በዘዴ ዞር አላደረጉምን? ለምን የጎፋ ዞን ጥያቄ አነሳ ብለው ከቢሮ ሀላፊነት አላወረዱትምን? አቶ ጨርቁን ማቁን እንዳይዝ ተደርጎ ለምን ተባረረ? እንደዚሁ በጎፋ ታሪክ የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው በተጋ አቋማቸው አምባገነን ለነበረው ኢህአዴግ ደረታቸውንና ጀርባቸውን ለግምገማ ጅራፍ ሰጥተው ኤሎሄ ኤሎሄ በማለት የህዝባቸውን ጥያቄ በጩኸት አስተምተው የታገሉለት የት አሉ ? እነ #ሹጉጤ ፣ #መሠለ ፣ #ጉጃ ፣ #ትምህርቴ ፣ #ዳዊት ፣ #ቱርቃቶ ፣ #ግጥሜ ፣ #ሲሳይ ፣ #ወንዱ ፣ #አሸናፊ ፣ #ዘለቀ ፣ ገ/መድህን ወዘተ... እነዚህ እንግዲህ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው። ለምን ተገፉ? የት የት እንደወደቁስ አንባቢያን ይድረሱበት። የእነርሱን ኮቴ ተከትለው በአካባቢው መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ " #ሆ "ብለው ለውጡን የተቀላቀሉ ወጣቶች በዞን መዋቅር መምጣት ደስታቸውን የገለፁትን ታክከው የለውጥ መሪ ነን ባዮች የግል ፍላጎታቸውን ለማርካት በሚያማስሉ ባለጊዜዎች " " አካባቢው የልማትና የመልካም አስተዳደር ርሀብተኛ እንዲሆን ተዳርጓል። በዚህም ምክኒያት ህዝባችን በመልካም አስተዳደር እጦት እና የኑሮ ውድነት ጅራፍ መልሶ መላልሶ እየተጋረፈው የቁም ስቅሉን እያየ ይገኛል።

ህዝቡን የሰለቸው
" " ነው። ህዝቡ የጩኸታችሁን ድምፅ ከመስማት ባለፈ ምንም እንዳላለፈለት ያውቃል። ዛሬም ያን ድምፅ ይዛችሁ ሲትመጡ አፍሮባችኋል። ፣ ሲጮሁበትም ስያወግዙትም "እናንተ ካላችሁ እንግዲህ ይሁና" ብሎ የተቀበለ እንጂ። እናማ ታዲያ ምርጫ ሲደርስ ብቻ ነው እንደ አዲስ ፊት በማሳየት ህዝብን ልክ እንደ ህጻን ልጅ በከረሜላ ማታለል የጀመራችሁት? ትናንት በለውጥ እሳቤ ወደ
? ማን በላቸው ? የትኛው ጸሃይ ወይስ ጨለማ ዋጣቸው?

? ከዚህ የባርነት አገዛዝና ካከበደው ቀንበር ህዝቡ መላቀቅ የሚችለው ለነፃነቱ በሚያደርገው በመጨረሻ የይበቃኛል ውሣኔያዊ የቅብብሎሽ ትግል ነው። ይህም እንደሚሳካ እርግጠኛ ነን። ውጤቱ ያማረ ሆኖ እንድናገኝ የተማሩ የቀለም ቀንድ ልጆቻችን የዛገውን ሥርዓት አምርረው ከእርሱ ማንም እንደሚሻል አምነው በተገፉት ልክ በአማራጭ ፓርቲዎች እጩ ሆነው ቀርበዋል። ለጎፋ ህዝብ የጽድቅ ፀሐይ እንዲወጣ ከታማኝ ልጆቻችን ጎን እንቆማለን !
በልጆቿ መራር ትግል የጎፋ ትንሣኤ ይረጋገጣል !!!!

ፎቶዎች በታሪክ ማህደራችን በተለያዩ አጋጣሚዎች የያዝናቸው እንጂ በአካባቢው የነበረው ጭንጋፍ ፖለቲካ ያሳደዳቸውን በሙሉ የያዘ ባለመሆኑ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ በተለያዩ አጀንዳዎች በሰፊው እንመለሳለን።

Photos from Ethio Visionary's post 04/03/2021
24/02/2021

#ብርሃን ፣ #አምፖል እና መሰል የምርጫ ምልክት ወጎች
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

"አምፖል ሳይሆን ብርሃን ነው ይዘን የመጣነው" ..... ሲለን በበኩላቸው "ብርሃን በአምፖል ነው የሚበራው" የሚሉ የቃላት ጦርነቶች ለሚቀጥሉት 4 ወራት እኛን ማዛጋቸው አይቀሬ ነው🙆‍♀️🙆‍♂️🤦‍♀️🤦‍♂️


?
# # # # # # # # # # # # # # # # # #

ውድ የገጻችን ተከታታዮቻችን እና አንባቢዎቻችን እንዴት ቆያችሁ? እንዴትስ ከረማችሁ? እኛም ከዚህ ክፉ ቸነፈር በፈጣሪ ጠባቆት በህይወት እንገኛለን እያልን ለዛሬ ደግሞ ከፊታችን በጉጉት ከሚጠበቀው ምርጫ ጋር በተያያዘ በቅድመ ምርጫ ዝግጅት ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ የመጀመሪያው በመሆን እና ቀጥሎም በይፋ የምርጫ ቅስቀሳውም ተጀምሯል። ይህንኑ በማስመልከት ከወዲሁ የምርጫ ምልክቶች እና ትርጉሞቻቸው የህዝባችንን ትኩረት የሳበ ሆኖ በመገኘቱ ለግዜው ከላይ በርዕሳችን በጠቀስናቸው ምልክቶች ምንነት ዙሪያ የራሳችንን ዕይታ ልናስቃኛችሁ ወደድን። እነሆ ተጀመረ...

በእውነቱ ከሆነ የብርሃን ምንነት እጅግ ጥልቅ እና ውሰጠ ወይራም ይመስላል ፣ በተለይ ደግሞ እንቅፋት ለበዛው ጽልመት ለረበበት የሃገራችን ፖለቲካ። የታሰበበት የተደከመበትም ይመስላል ፣ አሁን ለምሳሌ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚከተለው ይላል...


1፤ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
2፤ ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
3፤ እግዚአብሔርም፡— ብርሃን ይሁን፡ ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።
4፤ እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።

ቃላት በፊደላት ይወከላሉ ፣ ፊደላት ቃላት ያረገዙትን የሀሳብ ጽንስ ያመለክታሉ ፣ ምልክቶች ቀላት ያረገዙትን ጽንሰ ሃሳብ ያዋልዳሉ ይህም ማለት የቃለትን ተምኔታዊ እና አመክንዮአዊ ኑባሬነትን ምልክቶች በመልካ ምስል ይከስታሉ ማለት ነው። ለዚህም ይመስላል በምልክት ተወክለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩት። አንድ የፖለቲካ በእርግጥ ከፓርቲው መሪ ስምነት ባለፈ የስሙን ትርጉም እና ግዝፈት የሚወክል መሆን እንዳለበት ይጠበቃል።

ቅዱስ መጽሐፉ ከላይ እንደሚያትተው " " ሲል ጨለማውን ገፍፎ ቀን እንዳደረገ ይናገራል ፣ ይህም ማለት ጸሃይ ወጣች ማለት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው የብርሃን ምንጭ ጸሃይ (🔆) ነበረች ማለት ነው። እንግዲህ ሌሎች የብርሃን ምንጮች ከመጀመሪያው ቀጣይ ናቸው ማለት ነው ፣ አሁን ለምሳሌ ጨረቃ ፣ ኮከብ (✡) ፣ እሳት (🔥) ፣ ኤሌክትሪክ (⚡💡) እና ወዘተርፈ...
ለዚህም ይመስለናል " #ብርሃን-ነኝ_ምረጡኝ " ሲል ጸሃይን እንድናስብ እና ጸሃይን ስናስብ ደግሞ የምንጭነትን ምንታዌ በተረዳ መሆኑን የገለጡት ይመስላል። ስለዚህ ነው ወዳጄ የብርሃንን ሃይል የጨለማው ደጆች አይችሏትም የሚሉት እና ሰለዚህ #አሜከላዎችን ወይም #ጎጠኝነት ፣ #ዘረኝነትን ፣ #ሌብነትን ወዘተ... ከተጸየፍክ ወንድሜ ምርጫህ ብርሃን ይሆናል የሚል ይመስላል።

ከወዲሁ ልክ እንደ ስሟ ብልጣብልጥነት ይሁን ባይታወቅም አምፖል ተሸክማ ብርሃኑ አለኝ ፣ ያለ እኔ ብርሃኑን አታዩም በማለት ፣ ስለ ብርሃን ምንጭ ያላትን በማስረዳት ከወዲሁ አግራሞትን በጫረ መንገድ ልክ አምፖል መርጣ ስታበቃ ፣ መፍቴ ነው ብላ ጨረር አምፖሉ አናት ላይ በማስቀመጥ ከወዲሁ እያለች ያለ ይመስለናል። የብልጧማ ጉዳይ አጃኢብ እያሰኘ ነው ልክ አዕምሮዋን የተነጠቀች ነው የሚመስለው ለነገሩ ባትነጠቅ ነው የሚገርመው በሰሜን ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል የገጠማት ፈተናም ሊሆን ስለሚችል ብለን ብናልፍ መረጥን። አይ ግዜ ክፉ ከታች ከላይ እያጠደፏት እንጂ እንደኛ ቁጭ ብላ ነገር ፈልፋይ ብትሆን ኖሮ ብርሀኑን ትመርጥ ነበር።
ብልጥግና አስቀምጦ ብርሃን አለኝ ማለቱ😂😂😂😂 ያስብላል።

ቀድሞ ማሰብ ነበር አምፖልን ሲመርጡት፣
አሁን ምን ያደርጋል ብርሃኑን ቢሰርቁት፤

በቅርብ ቀን ሰፋፊ አጀንዳዎችን ይዘን እንመለሳለን!

Photos from Gofa Zone's post 03/12/2020
01/10/2020

~~~~~~~~~
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶች በዞን አስተዳደር ስቀርቡለት ምንም ያለምንም አስተያየት የምያጸድቅ በብዛት አባላቱ ግራ የተጋቡ በመሆናቸው ሰፍውን የጎፋን ህዝብ ተጠቃሚነት የማያረጋግጡ መሆናቸውን የውስጥ የመረጃ ምንጮቼ እየገለጹ ነው። ለአብነት፦ ምክር ቤቱ መስከረም 13/2012ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዙር 8ኛ ዓመት መርሐ-ግብር 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በጎፋ ህዝብ ላይ በሰሩት ደባ ማረምያ መግባት ያለባቸውን፦

፩ አቶ ማሩፋ መኩሪያ:- የጎፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ
፪ አቶ ድንበሩ ድርቤ ዲላ:- የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ
፫ አቶ ንክሰን ለማ:- የጎፋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አድርጎ ገልጃጃው አስተዳደር ሳቀርብ ምክር ቤቱ በጭፍን ማጽደቁ ደንባራ ምክር ቤት መሆኑን አረጋግጦልናል ይላሉ የመረጃ ምንጮቻችን።


~~~~~~~~~
የጎፋ ዞን የመንግስት እና የድርጅት አመራር ሹመት ከረጃጅም እጆች መውጣት ባለመቻሉ ጠንካራ የድርጅት አመራሮች ምንም አይነት መረጃ ሳይኖራቸው በፕሮሞሽን መልክ ወደ ወረደ ደረጃ እንዲሄዱ ከኃላፊነት ተበራው በምትካቸው በተግባራቸውም ሆነ በስነምግባራቸው የወረዱ ሴሰኞች እና ሌቦች
፩ አቶ መስፍን ስለሺ:- የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
፪ አቶ ተመስገን ጣሰው:- የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የርዕዮተ አለምና ፖለቲካ ዘርፍ ኃለፊ ሆነው በረጃጅም እጆች መሾማቸው ህዝብን በመናቅ የጎፋን ህዝብ ከዲጡ ወደማጡ ለመክተት የተሰራ ሴራ እንደሆነ የውስጥ ምንጮች እየገለጹ ነው። አዲሱ የዞኑ አስተዳደር እነዚህ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ካልወሰደ ብዙ ሳይሰራ በሴራቸው ተጠልፎ ልወድቅ እንደምችል የውስጥ የመረጃ ምንጮቼ አምርረው ገለጹ። እመለስበታለሁ.....
!!

Telephone