Harvard Medium Clinic Plc

Harvard Medium Clinic Plc

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harvard Medium Clinic Plc, Medical and health, Wendo, Aleta Wendo, Sidama region, .

27/10/2023

የጨጓራ ህመም ወይም ቁስለት

# መንስኤዎች

-የጨጓራ ባክቴሪያ
-ለህመም ማስታገሻ የሚወሰዱ መድሃኒቶች ማብዛት
-የስራ ጫናና መጨናነቅ
-ከልክ በላይ መመገብ
-ቅመም/ቅባት የበዛባቸው ምግቦቾ ማዘውተር
-መጠጥና ሲጋራ ማጨስ ..ወ.ዘ.ተ.
-ካፊን(caffeine ☕..) ማብዛት

#ምልክቶቹ
- ከእምብርት ከፍ ብሎ ሆድ የማቃጠል ስሜት
-ቅመም የበዛበት ምግብ ያለመመቸት (ማቃጠል,ማስገሳት,ያለመፈጨት)
-ምግብ መብላትን መፍራት ወይም እንዲያስታግስ መብላት/መጠጣት
-ማቅለሽለሽ, ትውከት

#መዘዞቹ
-በተደጋጋሚ በህመም መስተጟጓል
-ከቁስለቱ መድማት(ደም መስመለስ)
-የጨጟራ መበሳት

# መፍትሄ
-መንስኤዎቹ ማስወገድ
-የአሲድ መቀነሻ መድሃኒት መውሰድ
-የጨጓራ ባክቴርያ ምርመራና ህክምና ማድረግ
-የህመሙ ደረጃ ተመርምሮ ማወቅና ማከም
#ሐርቫርድ መካከለኛ ክሊኒክ - አለታ ወንዶ

25/10/2023

የትርፍ አንጀት (Appendicitis) ህመምና ምልክቶች
1. ቀላል ህመም እምብርት አካባቢ ወይም የላይኛው የሆድ ክፍል መሰማት ከዚያም ወደ ታችኛው ቀኝ የሆድ ክፍል ይዞራል ፡፡
ይህ ብዙን ጊዜ የተለመደ የመጀመሪያ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
2. የምግብ ፍላጎት ማጣት፡፡
3. ማቅለሽለሽና ማስታወክ፡- ይህን ተከትሎ የሆድ ሕመም ይጀምራል፡፡
4. የሆድ እብጠት፡፡
5. ከ99 እስከ 102 ዲግሪ ፋራናይት የሚደርስ ከፍተኛ ትኩሳት፡፡
6. ከሆድ ጋዝ (ፈስ) ለማውጣት መቸገር ያጋጥማል፡፡
7. ድርቀት ወይም ተቅማጥ ከጋዝ ጋር ሊታይ ይችላል፡፡

ይሁንና እነዚህ ምልክቶቸ አንዳንድ ጊዜ ከሀሞት ጠጠርና ከሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ጋር ስለሚመሳሰሉ ከዚህ በታች ያሉ ምርመራዎችን ማደረግ የበለጠ ሕመሙ የትርፍ አንጀት ስለመሆኑ ያረጋግጥልናል፡፡

1. የሆድ ምርመራ፡- ይህ ትርፍ አንጀት መቆጣቱንና አለመቆጣቱን ለማወቅ ይረዳል፡፡

2. የሽንት ምርመራ ፡-ይህ የፊኛ ኢንፌክሽን አለመሆኑን ያረጋግጥልናል፡፡

3. የትልቁ አንጀት ምርመራ፡፡
4. የደም ምርመራ፡- ሰውነታችን በኢንፌክሽን መጠቃቱን ለማወቅ ይረዳል፡፡
5. የአልትራሳውንድ ና የሲቲ እስካን ምርመራ ማድረግ የትርፍ አንጀቱን ደረጃ ያሳያል፡፡

የትርፍ አንጀት ህመም ሕክምና በዋናነት ቀዶ ጥገና ሲሆን አፔንዴክቶሚ (Appendectomy) ይባላል፡፡

05/10/2023

አያርገውና ድንገት ታመው የተሻለ ህክምና ካሻዎት ሀሳብ አይግባዎት ሩህሩህ ልቦችን ከፈዋሽ እጆች ጋር ይዞላችሁ ብቅ ብሎላችኋል ።

ሃርቫርድ መካከለኛ ክሊኒክ የተሻለ የህክምና አማራጭ ይዞ የሕብረተሰቡን ኪስ በማይጎዳ መልኩ ሁሉንም የሕክምና አገልግሎት እንካችሁ እያለ ነው። ዝርዝሩን ከፎቶው ላይ ያገኙታል።
ሁሉንም አገልግሎት መስጠቱ ልዩ ያደርገዋል ። ሀርቫርድን መምረጥ ጤናን መምረጥ ነው።

አድራሻ፦ አለታ ወንዶ ከዋራ በር ወደ ማሪያም ቤ/ክ መሄጃ መንገድ ላይ በድሮ ግቢ ውስጥ።

27/09/2023

ሐርቫርድ ክሊኒክ ኃ/የተ/ግ/ ማህበር

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

1. መለስተኛ ቀዶ ህክምና
~ የቀለበት ግርዘት
~ የተለያዩ እባጮች ቀዶ ህክምና
~ የእንቅርት ምርመራና ህክምና
~ የሽንት ቧንቧ ምርመራና ህክምና
~ የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች ምርመራና ህክምና
2. የውስጥ ደዌ ህክምና
~ የስኳር ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የደም ግፊት ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የመገጣጠሚያ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የኩላሊት ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የጉበት ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የልብ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የሳምባ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የጨጓራ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
3. የማህጸንና ፅንስ ህክምና
~ የእርግዝና ምርመራ ፣ ክትትል እና የማዋለድ አገልግሎት
~ የወር አበባ መዛባት ችግር ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት
4. የህጻናት ህክምና
~ የሳምባ ህመም ምርመራ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የተቅማጥ ፣ የትኩሳት እና ትውከት ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የወባ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የታይፈስ እና የታይፎይድ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
~ የልብ ህመም ምርመራ ፣ ህክምና እና ክትትል
5. የራዲዮሎጂ ምርመራ
~ የአልትራሳወንድ ምርመራ
~ ራጅ የማንበብ አገልግሎት
~ CT እና MRI የማንበብ አገልገሎት
6. የስነ ደዌ ምርመራ
~ ናሙና የመውሰድ አገልግሎት
~ በቀዶ ህክምና የወጣ ናሙና የመመርመር አገልግሎት

እኛ ሐርቫርዶች የእርሶን ጤንነት ለመጠበቅ በቀን 24 ሰዓት በስፔሻሊስት ዶክተሮች አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን ። ስለሆነም ይምጡና ይጎብኙን ፤ ልምድ ባካበቱ እጆችና በእውቀት በበለጸጉ አዕምሮዎች ተገልግለዉ በደስታ ይመለሳሉ።

ልምድ ያካበቱ እጆች እና ጥንቁቅ አዕምሮዎች!

አድራሻችን፦ አለታ ወንዶ ከተማ ጨፌ ቀበሌ ከዋራ አደባባይ ወደ ማሪያም ቤተክርስቲያን መሔጃ 50 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ፡-0916959697/0916676869
HARVARD MEDIUM CLINIC ..ለላቀ ህክምና የሚመርጡት

27/09/2023

እኛ ሐርቫርዶች የእርሶን ጤንነት ለመጠበቅ በቀን 24 ሰዓት በስፔሻሊስት ዶክተሮች አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን ። ስለሆነም ይምጡና ይጎብኙን ፤ ልምድ ባካበቱ እጆችና በእውቀት በበለጸጉ አዕምሮዎች ተገልግለዉ በደስታ ይመለሳሉ።

ልምድ ያካበቱ እጆች እና ጥንቁቅ አዕምሮዎች

አድራሻችን፦ አለታ ወንዶ ከተማ ጨፌ ቀበሌ ከዋራ አደባባይ ወደ ማሪያም ቤተክርስቲያን መሔጃ 50 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ፡-0916959697/0916676869
HARVARD MEDIUM CLINIC ..ለላቀ ህክምና የሚመርጡት

Website