DMV Tewahedo

DMV Tewahedo

DMVTewahedo page is created to serve Ethiopian Orthodox Tewahedo Church community in Washington DC,

01/08/2022
Photos from DMV Tewahedo's post 01/07/2022
01/07/2022
01/07/2022
01/07/2022
01/06/2022
01/06/2022

Live from Lalibela, Ethiopia

01/06/2022

Happy Christmas

ዕለት፦ ፳፱ ታሕሣሥ ፳፻፲ወ፬ ዓ.ም.ግዕዝ (07/01/2022ፈ.)

ርሑስ በዓል ልደት ይግበረልና

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

Photo: His Reverend Abune Qerlos, the 5th Patriarch of Eritrea’s Orthodox Tewahdo Church
(ብጹዕ ወቅዱስ ኣቡነ ቄርሎስ ቀዳማይ ፣ 5ይ ፓትርያርክ ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን)

ገና ዓርብ ነው - ሥጋ ይበላል ወይ? ካላወቁ አሁን ያውቃሉ 01/06/2022

ገና ዓርብ ነው - ሥጋ ይበላል ወይ? ካላወቁ አሁን ያውቃሉ ገና ዓርብ ነው - ሥጋ ይበላል ወይ? ካላወቁ አሁን ያውቃሉበመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማቅንብር:- e-BZ SolutionsJanuary 2022 - Washington DC

01/06/2022

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕስራ ምእተ ዓሠርቱ ወአርባዕቱ ዓመተ ምሕረት፣

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡-

እኛን ለማዳን ሥጋችንን ተዋሕዶ ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው በመሆን በዚህ ዓለም የተወለደው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ወውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ @ ያ ቃል ሥጋ ሆነ” (ዮሐ. 1*04)@
ቅዱስ እግዚአብሔር በአንድነት በሦሥትነት ኖላዊው፣ ጥንት በሌለው ጥንት የነበረ፣ አሁንም ያለ፣ ወደፊትም ፍጻሜ በሌለው ህላዌ የሚኖር አምላክ ነው፡፡

ከሦስቱ አካላት “ቃል” ተብሎ የተገለፀው አንዱ አካል ማለትም እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ በብሥራተ ገብርኤል፣ በግብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት ሃያ ዘጠኝ ቀን በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመተ ዓለም በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ተጸነሰ፡፡

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ@ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ@ ቃል እግዚአብሔር ነበረ” ተብሎ ማንነቱ በቅዱስ ወንጌል የተረጋገጠለት “እግዚአብሔር ቃል” በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድሰት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ በመዋሐድ እንደኛ ፍጹም ሰው ሆነ፡፡

“እግዚአብሔር ቃል” ሰው ከሆነበት ቅፅበት አንሥቶ መለኮትነቱ ከሰውነቱ፣ ሰውነቱም ከመለኮትነቱ ባለ መለያየት፣ ባለ መጠፋፋት፣ ባለ መለዋወጥ፣ ባለ መከፋፈልና ባለ መቀላቀል አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ በመሆን የተፈጸመው የአምላካችን ምሥጢረ ተዋሕዶ ለዘላለሙ የጸና ነው፡፡ ይህ ምሥጢረ ተዋሕዶ እግዚአብሔር ለሰው ያለው የፍቅር ጥግ ያሳየ አምላካዊ ድርጊት ነው፡፡ ይህ አምላካዊ ፍቅር ሰውነትን ከባርነት ነጻ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ሰውነት በተዋሐደው መለኮት ምክንያት በመንበረ ጸባኦት ተቀምጦ የፍጥረት ሁሉ ገዢ እስከ መሆን ያበቃ ስለሆነ፣ ተመሳሳይም ሆነ ተነጻጻሪ ምሳሌ የማይገኝለት፣ ከፍቅር ሁሉ የሚበልጥ የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር ነው@ ለዚህም ነው “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” እያለ ቅዱስ መጽሐፍ የሚያስተምረን @ የአምላክና የሰው ተዋሕዶ በማኅፀነ ድንግል ማርያም ከተፈጸመበት ጊዜ አንሥቶ መለኮትነቱንና ሰውነቱን በሚገልጹ ስሞች አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ መሢሕ፣ ክርስቶስ፣ መድኃኔ ዓለም እየተባለ ይጠራል፡፡ እነኝህ ስሞች መለኮትነትን ብቻ፣ ወይም ደግሞ ሰውነትን ብቻ የሚያመለክቱ ሳይሆን የመለኮትና የሰውነት ተዋሕዶን በምሥጢር የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ በመሆኑም በዛሬው ዕለት ታሕሣሥ ሃያ ዘጠኝ ቀን የተወለደው ሕፃን ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው እንጂ ሰው ብቻም አይደለም፣ አምላክ ብቻም አይደለም@ ይህም በመሆኑ ነው በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር፣ ለሰውም በጎ ፈቃድ” ተብሎ ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ለፍጡር የማይቀርብ ክብርና ምስጋና ከሰማይ ሠራዊተ መላእክት የቀረበለት፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት@

ሁሉ በእርሱ የሆነ፣ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የሌለ “እግዚአብሔር ቃል” ሰው ሊሆን የቻለው ሰውን ለማዳን ነው፡፡ ሰውን ለማዳን ሲባል የተፈጸመው ይህ ተዋሕዶ፣ በአምላክ ዘንድ ሰውን ማዳን ምን ያህል ታላቅ ነገር እንደሆነ ማስተዋል ለሰው ልጆች ሁሉ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ምሥጢር ይልቅ ዓለምን ያዳነበት እንደሚበልጥ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል፡፡ ይህ የአምላካችን አድራጎት እኛም ሰውን ከማዳን የበለጠ ሥራ ሊኖረን እንደማይገባ የሚያስገነዝብ ነው፡፡

ከጌታችን ልደት ምሥጢራዊ መልእክት እንደምናስተውለው አንድነትን፣ ፍጹም ፍቅርን፣ ምሉእ ሰላምን፣ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገንን እና ማምለክን፣ ከተቸገሩት ማኅበረሰብ መካከል ተገኝቶ የሰውን ችግር ተካፋይ መሆንን ከአምላክ የተቸረን ፍጹም በረከት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ምሥጢረ ተዋሕዶ፣ ዝማሬ መላእክቱ፣ በከብቶች በረት መወለዱ፣ ለእረኞች መገለጡ፣ በዕለተ ልደቱ ከተገለጡ ዓበይት ክሥተቶች ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በዚህም ቤተልሔም የእግዚአብሔር ክብር የበራላት፣ የመላእክትና የእረኞች መዝሙር የደመቀላት፣ እግዚአብሔር፣ መላእክትና ሰዎች በአንድነት የተገኙላት የእውነተኛይቱ መንግሥተ እግዚአብሔር ማሳያ ሆኖ ተገኝታለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፣

በቤተልሔም የታየው አምላካዊ መገለጥ ተአምረ አምላክ ብቻ ሳይሆን፣ በዕለቱ ከታየው ጣዕመ ሕይወት ትምህርት ወስደን እሱን እንድንለማመድ ብሎም እንድንከተል የሚያስገነዝብ አምላካዊ መልእክት የተላለፈበት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡

እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በመካከላችን የተገኘበት ዓቢይ ምሥጢር በአንድነት፣ በሰላምና በፍቅር የተወደደ እንደ ዕለተ ልደት ያለ ጣዕመ ሕይወት እንዲኖረን ብሎ እንደሆነ ልናውቅ ይገባል፡፡ ይኸውም እሱ እንደ ተዋሐደን እኛም እርስ በርሳችን ተዋሕደንና አንድ ሆነን በፍቅርና በሰላም እንድንኖር ነው፡፡ ይህንን ስናደርግ በዚህ ከእርሱ ጋር እንዋሐዳለን@ ለወደፊቱም እግዚአብሔር ሁሉን አዋሕዶ በሚመጣው ዓለመ መንግሥቱ እውን የሚያደርገው ጣዕመ ሕይወት ይኸው እንደሆነ መገንዘብ አለብን፣ መላእክት በቤተልሔም ለተወለደው ሕፃን ምስጋናና አምልኮ እንዳቀረቡ እኛም ለምስጋናና ለአምልኮ ተጠርተናል፣ እሱ ዓለመ ፍጥረትን በእጁ ጨብጦ የያዘ አምላክ ሲሆን፣ በከብቶች በረት ከእረኞች ጋር ውሎውና አዳሩ እንዳደረገ፣ እኛም ሁሌም ውሎአችንና አዳራችን ከምስኪኑ የኅብረተሰብ ክፍል ጋር በማድረግ የተራበውን በማብላት፣ የተጠማውን በማጠጣት፣ የታረዘውን በማልበስ፣ የታመመውንና የታሠረውን በመጠየቅ የጣፈጠ ጣዕመ ሕይወትን መምራት ይኖርብናል፡፡

ዛሬ ሀገራችን በመከራ እየተፈተነች ያለችበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ የተፈናቀሉ፣ የተጐዱና ኑሮ የተመሰቃቀለባቸው ወገኖች በየአካባቢው በብዛት መኖራቸው ይታወቃል፣ በቤተልሔም የተወለደው ሕፃን ክርስቶስም ከእነሱ እንደ አንዱ ሆኖ በመካከላቸው እንደሚገኝ እሱ ራሱ ነግሮናል፣ ታድያ እኛም እዚያው ተገኝተን እንድናስተናግደው የወቅቱ ዓቢይ ጥሪያችንና መልእክታችን ነው፡፡

በመጨረሻም፡-

በቤተልሔም ዙሪያ የጐረፈው የእግዚአብሔር ክብርና ብርሃን፣ ሰላምና ዕርቅ፣ ተዋሕዶና ምስጋና በሀገራችንም ሰፍኖ ወደ ፍጹም ሰላምና አንድነት እንደርስ ዘንድ፣ እግዚአብሔርን በጸሎት ከመለመን ጋር ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሰላም ለፍቅርና ለአንድነት ያላሰለሰ ጥረት እናደርግ ዘንድ አባታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ይቀድስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ታሕሣሥ !9 ቀን !)04 ዓመተ ምሕረት፣
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፎቶ ከፋይል

01/06/2022
01/02/2022
12/27/2021
11/28/2021
06/28/2021

የአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በተጠቀሱት ዕለታት ይከበራል። የዚያ ሰው ይበለን።

Photos from የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/'s post 05/17/2021
05/11/2021

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በትግራይ ጉዳይ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም አለች። ቤተክርስትያኗ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ፓትሪያሪኩ የሰጡት የቪዲዮ መግለጫ የግላቸው ነው ብላለች። ቅዱስ ፓትርያሪኩ ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ሳይወስን በግላቸው ቤተክርስትያንን ወክለው መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና የሲዳማ እና ጌዴኦ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ መግለጻቸውን መንግስታዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።ቀደም ሲል ይወጡ የነበሩ መግለጫዎች «የምልዓተ ጉባኤው እና የቋሚ ሲኖዶስ አዎንታ ሲያገኙ መሆኑን » አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል።ኢቲቪ እንደዘገበው ከሰሞኑ በማሕበራዊ መገናኛ ትስስሮች ላይ ሲዘዋወር የነበረው የሰሞኑ የቅዱስ ፓትርያሪኩ መግለጫ የሲኖዶሱን አሰራር ያልተከተለ እና ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ የተደረገ ነውም ብለዋል።

05/10/2021

Message of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Patriarchate Foreign Affairs Department concerning the recent violence of Coptic Monks on the Ethiopian monastery of Deir Al-Sultan in the Old City of Jerusalem

++++++++++++++++++++++++++++++++++

Recently the Coptic monks and leaders who are living in the Jerusalem made an aggression on the Ethiopian monastery at Deir Al-Sultan located in the Old City of Jerusalem during the celebrations of the Holy Week spiritual services. Although such irrelevant harassments are very common throughout the entire modern history, the recent attack was much more organized and openly made some days before the celebration of the holy Easter holiday.

Our historical monastery of Deir El-Sultan located on the roof of the Church of the Holy Sepulcher in Jerusalem is a site on which our Lord Jesus Christ’s crucifixion, burial and resurrection taken place. However the frequent attack and dispute of the Coptic monks hindered the restoration and the proper development of our long-lived heritage. The recent attack was first a violation of the Status Quo made between religious communities, applies to the site.

This groundless and provocative behavior of Coptic monks and their leader angered our Community in Israel, the Monastic organization as well as our Archbishop in Jerusalem, the office of our Monastery and Ethiopian Diaspora in Jerusalem. As Dier El sultan is one of the most important historical sites for the Ethiopian and the Sign of African Presence in the Holy Land for more than three millennia. The case went to the attention of the Ethiopian Embassy in Israel and reported to the Israel Ministry of Interior as well as office of the Security.

This action which brings unspiritual harassment against Ethiopian Monks reached to Security office and Ethiopian only demanded the withdrawal of the Copts as the moment is the time of prayer and supplication in commemoration to the Suffering, Death, and resurrection of our Lord Jesus Christ. Moreover Ethiopian did not want to harm their Coptic friends who adheres the same faith and tradition in the Orthodox Christianity.

However, while the Copts refused to leave peacefully the Israeli police lawfully removed them form the Ethiopian Historic Sacred site despite the illegal and violent aggression of the Copts. It is to be reminded that the Holy Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church and the holy Synod asked the Coptic Authorities several times to stop these violent actions especially during the holy week and Easter celebrations.

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church patriarchate foreign affairs department acknowledges and conveyed its gratitude to Ethiopian Archbishopric of Jerusalem, the monastic community of our Monasteries in the holy Land, Ethiopian Diaspora in Jerusalem, the Ethiopian Embassy in Israel and Israeli Deputy Public Security Minister, Gadi Yevarkan for their Joint Collaborations to safeguard Ethiopian Long lived Heritage and guarantee the peaceful celebration of the most Spiritual Feast of Easter.

We are very much grateful for the lawful action taken by the Public Security Ministry and Israel Police and sincerely request the responsible office of the Israel government to issue a lasting solution so that we will be protected from such illegitimate and violent action every time in our own historical site.

Along with these we call upon all Ethiopian in all corners of the world to jointly move forward hand in hand to safeguard the Historical and sacred properties of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in the holy Land.

We also call upon the Coptic Communities who are families in the same Orthodox faith not to repeat such aggressions in our Historical and sacred site.

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
Patriarchate Foreign Affairs Department
Addis Ababa, Ethiopia,
May 7, 2021

05/09/2021
05/02/2021
05/02/2021
Want your business to be the top-listed Media Company in Alexandria?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Alexandria, VA
Other Media in Alexandria (show all)
rubicat.com rubicat.com
Alexandria, 22306

Graphic designer, brand manager, and social media expert with a love of gardening, tea, cheese, and cats.

Missing Link Missing Link
277 S Washington Street Suite 210
Alexandria, 22314

MISSING LINK is a a Latina-owned strategy-driven, creatively fueled production co-op. From ideation to creation, we craft human connections through intelligent, engaging and inform...

NOVA Student Film Festival International NOVA Student Film Festival International
5000 Dawes Avenue
Alexandria, 22311

NOVA Student Film Festival (NSFF) is a non-competitive film festival of short films open to all Nort

Marine DP Insight Marine DP Insight
Alexandria

Maritime Dynamic Positioning Information Page.