Ethio Worldwide News
Welcome to my page if you subscribe to my channel you get more benefits. worldwide news, b
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በኮሮናቫይረስ ምክኒያት፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እንጂ ወንዶቹን የሚቀበላቸው መጠለያ ጣቢያ ገና እንዳላገኙ ተናግረዋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ከተደረገ በኃላ፣ የእናት ጡት ወተት በቅጡ ያልጠገና ገና ክፉ እና ደጉን ያልለዩ ሕፃናትን ጨምሮ እስከ ባለትዳር ሴቶች ድረስ በቤተሰብ አባላቸውና በቅርብ ሰዎቻቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ ነው። በኢትዮጵያም ከኮቪድ 19 በኋላ የተሰራና የቁጥሩን መጨመር የሚያሳይ ጥናት ባይኖርም በቅርብ የቤተሰብ አባላት ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ግን እየታዩ ነው ያሉን የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ናቸው።
በተመሳሳይ የቤት ውስጥ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉት ሴቶችና ህፃናት ከኮሮና በፊት በመጠርለያ ጣቢያዎች ያገኙ የነበረውን ከለላ በወረርሽኙ ምክንያት ማግኘት አልቻሉም። ይህም የሆነው መጠለያ ጣቢዎች የቫይረሱን ስርጭት በመፍራት አዲስ የጥቃት ሰለባዎችን መቀበል ባለመቻላቸው ነው። ወ/ሮ ሜሮን ከኮቪድ 19 በኃላ በተከፈተ የለይቶ ማቆያ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከሳምንት በፊት ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 27 ሴቶች ጥቃት ደርሶባቸው መግባታቸውን ገልፀው ክስተቱ ለጥቃቱ መጨመር ማሳያ ነው ይላሉ ።
የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ከ1993 አመት ምህረት ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ለሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት የመጠለያ፣ የህግና የስነልቦና ድጋፍ የሚሰጥ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። በተለይ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ህፃናት ወንዶች በብቸኝነት ከለላ በመስጠት የሚሰራው መጠለያ ጣቢያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደቀድሞው ጥቃት የደረሰባቸውን ህፃናት ተቀብለው ማስጠለል እንዳልቻሉ የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ መቅደስ ዘለለው ገልፀዋል።
በአሁኑ ሰአት ከ 5 አመት እስከ 17 አመት የሚሆኑ 18 ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶችና ሴቶች ህፃናትን በመጠለያ ጣቢያቸው እየረዱ እንዳሉ የነገሩን ወ/ሮ መቅደስ ሁሉም ህፃናት ጥቃቱ የደረሰባቸው በቤታቸውና በአካባቢያቸው ባሉ ሰዎች ነው ይላሉ።
ተጎጂዎቹ ሴቶችና ህፃናት ከጥቃቱ በኋላ በማኅበረሰቡ የሚደርስባቸውን ጫና አሸንፈው፣ ፖሊስ ጋር ከደረሱ በኃላ ጉዳያቸው እስኪጠናቀቅ ጥቃቱን ካደረሱባቸው ሰዎች ገለል ብለው መቆየት አለባቸው። የኮሮና ቫይረስ ከገባ በኃላ ግን ነገር ግን እነዚህን
ተጎጂዎች በተለይ ወንዶቹን ተቀብሎ የሚያቆያቸው ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ምርመራና እንክብካቤ ሀላፊ ኮማንደር አፀደ ወርዶፋ ይናገራሉ።
አሜሪካዊ ጥምረት መሥራችና መሪ ቄስ ጄሲ ጃክሰን በኅዳሴና በአባይ ጉዳይ ደብዳቤ ላኩ የአባይን ውኃና ኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ ግብፅ በላከችለት ደብዳቤ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አንዳች እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የዩናይትድ ስቴትስ የተ.....
የአባይን ውኃና ኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ ግብፅ በላከችለት ደብዳቤ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አንዳች እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ጥቁር እንደራሴዎች ክንፍ ፈጥኖ ጠንካራ መግለጫ እንዲያወጣ “ቀስተዳመና / ሰብዕናን ለመታደግ የተባበረ ሕዝብ” የሚባለው አሜሪካዊ ጥምረት መሥራችና መሪ ቄስ ጄሲ ጃክሰን ጠየቁ።
ከወጣትነት ዕድሜአቸው አንስቶ ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር የሲቪል መብቶች ተሟጋችና ተደማጭም የሆኑት ጄሲ ጃክሰን በድርጅታቸው ስም በፈረሙበትና ለጥቁር እንደራሴዎቹ ኅብረት ሊቀመንበር ካረን ባስ ከትናንት በስተያ በላኩት ደብዳቤ ላይ የኅብረቱ መግለጫ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም. ከወጣው የቅኝ ግዛት ውል የተቀዳውን ግብፅ “በናይል ላይ ያሉኝ የውኃ መብቶቼ” የምትለውን አቋሟን የሚደግፈውን የአረብ ሊግ ውሣኔ የሚቃወም እንዲሆን ጠይቀዋል።
በቄስ ጄሲ ጃክሰን ደብዳቤ ላይ የተሰናዳውን አጭር ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
#መቀሌ
በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ 05 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተሰብስበው የነበሩ ወጣቶችን ኮሮና ከመከላከል ተብሎ ለመበተን በተደረገው እንቅስቃሴ ግጭት ተከስቶ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ ተብሏል።
የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት የወጣቱ ህይወት ካለፈ በኋላ በተፈጠረው አለመግባባትም በሁለት ወጣቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በጉዳዩ ላይ ከከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ይሁን ሌሎች የሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥርያ ቤቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
ትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ያካሂዳል ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል።
ትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ያካሂዳል ሲሉ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል ትግራይ ክልል የኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶች በመጠቀም የራሱን ምርጫ ያካሂዳል ሲሉ ምክትል መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል። የሚያካሂዱት ምር...
ትግራይ ክልል የኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶች በመጠቀም የራሱን ምርጫ ያካሂዳል ሲሉ ምክትል መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል። የሚያካሂዱት ምርጫ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑና የምርጫ ቦርድም እንደሚሳተፍበት አስታውቀዋል።
የኮቪድ 19ን ስርጭት ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ጥሳችኃል በሚል የቤተሰብ አባላቶቻቸው በቁጥጥር ስር ከዋሉባቸው ግለሰቦች አንዱ በፈቃዱ ሃይሉ ነው። በፍቃዱ እህት እና ወንድሙ ግንቦት 5.2012 ዓመተ ምህረት ማለዳ ላይ ወደ ስራ በሚየቀኑበት ወቀት ፖሊሶች «ተነካክታችኋል» በሚል በቁጥጥር ስር እንዳዋላው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ወላጆቻቸው በዕድሜ የገፉ ስለሆኑ ቫይረሱ ወደ ቤታቸው ዘልቆ የጤና ስጋት እንዳይሆን መላ የቤተሰብ አባለት ከፍተኛ የጥንቃቄ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ የሚያወሳው በፍቃዱ ፣ፖሊስ እህት እና ወንድሙን በቁጥጥር ስር ባዋለበት አፍታ ባይገኝም-በቁጥጥር ስር ሊያውል የሚያስችል ተግባር እንደማይፈጽሙ እንደሚያምን ያስረግጣል።
ከዚያ ይልቅ ወንድም እና እህቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኀላ የተከተለው የጤናም ስጋት የሰብአዊ መብት ጥሰትም እንደሆነ ያወሳል።በሰብአዊ መብት ተሟጋችነቱ የሚታወቀው በፍቃዱ ሃይሉ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ የአዲስ አበባ ስፍራዎች በእሱ አነጋገር «የጅምላ እስር »ሲከናወን ውሏል።
ፈረንሳይ ለጋሲዮን እና አራት ኪሎን በመሰሉ ስፍራዎች ፖሊሶች በርካታ ሰዎችን በመኪና ሲጭኑ ማየቱንም ይናገራል። መሰል የፖሊስ እርምጃዎችን ህጋዊነትም ሆነ ውጤታማነትም ይጠራጠራል።
መሰል ቅሬታዎች ለመስሪያቤታቸው እንደደረሱ የሚናገሩት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በአስተማሪነት ሊረዳ ይቻላል በሚል ዕምነት ግለሰቦችን እየሰረ መሆኑን መስማታቸውን ይናገራሉ። ሆኖም የተወሰደው እርምጃ ከሁኔታው ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ካለው ሀገራዊ የጤና ስጋት አንጻር ፖሊስን የመሰሉ ህግ አስፈጻሚ አካላት ፣ አዋጁን ለማስፈጸም ያሉባቸውን ፈተናዎች የሚረዱ መሆናውን አውስተዋል። አዋጁን ለማስፈጸም የሚወሰዱ እርምጃዎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጥሱ መልኩ ሊተገበሩ እንደሚገባም መክረዋል።
በቀረቡ ቅሬታዎች እና ሀሳቦች ላይ ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ስልክ ላይ ደጋግመን ብንደውልም ሳይሳካልን ቀርቷል።
ይህ በእንዲህ እያለ በኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ህዝብ በስፋት በሚገኝባቸው ቦታዎች ላይ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳይጠቀሙ በተገኙ እና እርቀታቸውን ባልጠባቁ 1305 ሰዎች ላይ በአዋጁ መሰረት እርምጃ መውሰዱን ገለጿል፡፡
ኮሚሽኑ ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸው 23 ስፍራዎች ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረገው አሰሳ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው 990 ወንዶችና 315 ሴቶች መሆናቸውን አክሎ አስታውቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Atlanta, GA
30013
1601 W Peachtree Street NE
Atlanta, 30309
The South's first television station, WSB-TV, brings you breaking news, live video, traffic, weather
Atlanta, 30274
Entertain, Educate, Inspire! Not only entertainment, its life #6twelvemagazine #imso612 #sixtwelvemag
5555 Glenridge Connector, Suite 200
Atlanta, 30342
Atlanta's Favorite Real Estate news site with information on Atlanta new homes, builders, and constr
Peach Tree Street
Atlanta
Staying on top of Business News. Keeping a heart beat on all things moving on Wall Street and other Business . This is what we do here at Wealthbuilderz Business News
Atlanta
NRIPulse is an Atlanta based free monthly newspaper that serves the Indian American community in pa
211 Georgia Avenue
Atlanta, 30312
404Live is the premier online urban radio station featuring listener-produced media. With 35% of the programming being submitted by listeners, 404Live.com has been established a...
1440 Dutch Valley Place NE, #165
Atlanta, 30324
The leading hyperlocal publications for the news you need and the stories you crave in metro Atlanta.
Atlanta
Football Fashion features news about the world's greatest game - football (or soccer if you prefer).