Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

This page is dedicated to information regarding the religious and social and services of St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahido Church in San Antonio Texas.

[email protected] Tel. 210-920-0871

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 07/29/2024

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
++++
በ2024 የዓለም ኦሎምፒክ ስፓርታዊ ውድድር መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የተካሄደውን አስነዋሪ ትዕይንት አስመልክቶ

“ይእዜ ኀሥረ ክብሮሙ ወተኀፍረ ገጾሙ ወተቃወመቶሙ ኀጢአቶሙ ከመ ኀጢአተ ሰዶም ወገሞራ አስተርአየት ወተዐውቀት ላዕሌሆሙ፤ አሌ ላ ለነፍሶሙ እስመ መከሩ እኩየ ምክረ ላዕለ ነፍሶሙ፡- ዛሬ ክብራቸው ተዋረደ፣ የፊታቸውም ዕፍረት ይመሰክርባቸዋል ኀጢአታቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ኀጢአት ተቃወመቻቸው በላያቸውም ተገልጣ ታወቀች፡፡ ክፉ ምክርንም መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት፡፡
ኢሳ.3 ፥ 9”

የ2024 የዓለም ኦሎምፒክ ስፓርታዊ ውድድርን በማስመልከት ባለፈው ዓርብ በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር July 26 በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የሚሠጠውን ምስጢረ ቊርባንን ያቀለለ፣ የተመሳስይ ጾታ ጋብቻን፣ የግብረ ሰዶማውያንን እኩይ ተግባር በወገንተኛነት የተደገፈ ትርኢት ማሳየታቸውን በዓለም ዜና ማሰራጫ ተመልክተናል።
በየዐራት ዓመቱ በሚከናወነው የዓለም ኦሎምፒክ ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የቀረበው የረከሰ ድርጊት ሲታይ በተቀደሰው ምሥጢረ ቊርባን ላይ የተፈጸመ የድፍረት ኃጢአት ነው፡፡ በተጨማሪም የሃይማኖትን ነጻነት የሚጋፋ፣ ጾታ የሚለውጡ ሰዎችን የሚያበረታታና በአጠቃላይ በክርስትና ሃይማኖትና በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመ ቀጥተኛ ጥቃት ስለሆነና ከሰለጠነው ዓለም የማይጠበቅ፣ የሌሎችን የእምነት የባህልና የማኅበራዊ ዕሴት ማክበር ልዩ ቦታ በሚሰጠው የኦሎምፒክ ስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በሰው ልጅ ሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡
በመሆኑም አንዱ የሌላውን የእምነትና የአምልኮ ነጻነት በማክበር እንዲኖር በሃይማኖት ቀኖናት ብቻ ሳይሆን በዓለማችን ላይ ባሉት ሀገራት የሰብአዊ መብትና የእምነት ሕግጋት የተደነገገ ሆኖ ሳለ ከኦሎምፒክ ስፖርት ጋር በማይገናኝ ሁኔታ በውድድሩ መክፈቻ ትዕይንት የተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር ሃይማኖታችንን የሚጋፋ፣ መንፈሳዊ እሴቶቻችንን የሚያጠፋ ክብረ ነክና ሊወገዝ የሚገባው ሰይጣናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡ የዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ኮሚቴና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላትም ይህንን በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ የቀሰቀሰውን ጸረ-ሃይማኖት የሆነ አስነዋሪ ድርጊት በመኮነን የአምኮልን መብትና ነጻነት እንዲያስከብሩ፣ ድርጊቱን በግልጽ እንዲቃወሙ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Statement from the Permanent Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

Regarding the scandalous scene at the opening ceremony of the 2024 World Olympic Games

The shew of their countenance doth witness against them; and they declare their sin as S***m, they hide it not. Woe unto their soul! For they have rewarded evil unto themselves. (Isa. 3:9)

In the opening ceremony of the 2024 World Olympic Games, that took place on Friday, July 26 2024 in in the city of Paris, France, we saw a scandalous scene that degrades the sacrament of Holy Communion, which is highly respected by all Christians and promotes same-sex marriage, homosexual activities and anti-Christian cults.

The act of showing such scene is a blasphemous sin against the sacrament of Holy Communion; it violates religious freedom and encourages transsexuals. In general, the scene is a direct attack on the Christian religion and Christians. Such act is unacceptable both in human life style and Christian scriptures.

The shown disgraceful act is forbidden and condemned not only by religious canons but also by the laws of the various countries in the world. The disgraceful act that was openly broadcasted on the world stage is a satanic act that should be condemned. Therefore, the Permanent Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church strongly condemns and sends a spiritual call to all affiliated bodies to condemn the disgraceful act that has aroused great anger among the Christian religion and all Christians, to respect the rights and freedom of worship, and to openly oppose the act.

July 29, 2024
Addis Ababa, Ethiopia

07/25/2024

የካህናቱ ጸሎት ....
++++++
** "ተዘከራ እግዚኦ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ፣ መፍቀሪተ እግዚአብሔር አምላክ፣ ወዕቀባ እስከ ለዓለም በዳህና ወበሰላም፤"

ትርጉም:-
** "አምላካችን እግዚአብሔርን የምትወድ ሀገራችን ኢትዮጵያን አስባት፤ ለዘለዓለሙ በደኅንነት በሰላም ጠብቃት።"

(መጽሐፈ ቅዳሴ ተመልከት፤ ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 3 አንቀጽ 202)

07/24/2024

** "አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በድቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።"(መጽሐፈ ምሳሌ 20፥20)

** የአምላክ እናት (እመ አምላክ) እመቤታችንን የሚያዋርድስ?

07/14/2024

የዕለቱ መምህር፦ ቀሲስ አክሊለ ሰማዕት፤

07/13/2024

ቅዱስ ቊርባንን ከመቀበል በፊት የሚጸለይ ጸሎት
+++++

አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኵስት ከሆነች ከቤቴ (ከሰውነቴ) ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም፤ እኔ አሳዝኜሃለሁና።፡ በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና። በአርአያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና። ሥራም ምንም ምን የለኝምና።

ነገር ግን እኔን ስለመፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፤ ስለ ክቡር መስቀልህም፤ ማሕየዊት ስለምትሆን ስለ ሞትህ፤ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም፤ ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ፤ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። እማልድሃለሁም።

የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩት ጊዜ ለወቀሳና ለመፈራረጃ አይሁንብኝ። ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ። የዓለም ሕይወት ሆይ፤ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት፤ የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ።

በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም፤ በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፤ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም፤ በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን።
(መጽሐፈ ቅዳሴ፤ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቁ. 110-112)
+++++

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 06/27/2024

እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!!
++++++
"ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሀነጻ ወልድ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ"
(ሊቁ ቅዱስ ያሬድ)
+++++
(መ/ር ዮሐንስ ለማ፤ ረቡዕ ሰኔ 21/2015 ዓ/ም ከጻፉት ላይ የተወሰደ)

በሰኔ 20 ቀን በሐዲስ ኪዳን ለመዠመሪያ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባረገች በአራተኛው ዓመት (በ54ዓ/ም) በፊልጵስዩስ ቂሳሪያ ከሦስት አዕባን (ዓለቶች) መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በስሟ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ የከበረበት ታላቅ ዕለት ነው። ዕለቱም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው።

“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ፣
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ፣
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ፣
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ፣
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ፣
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ።"

ትርጉም፦
"ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራትን ከፈጸመ በኋላ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ" እንዲል ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል።

👉 ምሳሌነቱም፦
፩ኛ. ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ምሳሌዎች።
፪ኛ. ከታች አቀማመጣቸው 3 ከላይ ሕንፃቸው 1 ነው።
፫ኛ. የአንድነታቸው እና የሦስትነተኛው ምሳሌ።

👉 ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ኪዳን፦
በብሉይ ኪዳን የመጀመዠሪያዋ ቤተክርስቲያን ደብተራ ወይም ድንኳን ነበረች። ከዚያም ቤተ መቅደስ በዘሩባቤል ዘመን 46 ዘመን ፈጅቶ ተሠርቷል።
** "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" (ዘጸ.25÷8)።

👉 ሕንጻ ቤተክርስቲያን በሐዲስ ኪዳን፦
በሐዲስ ኪዳንም ሰኔ 20 ቀን ጌታችን ከሦስት ድንጋዮች ቤተ መቅደስ አንጾ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው። (ማቴ.16÷13-19)

👉 ቤተ ክርስቲያን ስለምን ቅድስት ትባላለች?:-
፩ኛ. የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታልና፣
፪ኛ. ክርስቶስ በደሙ አክብሯታልና፡፣
፫ኛ. ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ይሰጥባታልና፡፣
፬ኛ. በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና፡፡

“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ፣ ዘትጼንዊ መጽርየ፣ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ፣ ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ፤ እንደ ቀጋ የምትሸቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኁ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)

👉 ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ስለ3 ነገር ይነገራል።
፩ኛ. እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል:-
** በጥንተ ፍጥረት ከምድር አፈር አበጅቶ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ብሎ የራሱ ቤተ መቅደስ ያደረገን እሱ ነው።
** (ዘፍ.1÷27) "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው"
** (ኢሳ.28÷16) እነሆ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ የተፈተነውን የከበረውን መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምንም አያፍርም።

ከጽዮን ከድንግል ማርያም የተወለደው የጸናው ዓለት ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ፈጣሪ እንደሆነ የሚያምን ሁሉ በዚህ ዓለት ላይ ታንጿል። መሠረቱም የጸና ነው። ቤተ አይሁድ ተሰናከሉበት። ብዙዎችም ዛሬ የባሕርይ ክብሩን አቃለሉ። ኃይሉን ካዱ። አስቀድሞ በዳዊት የተነገረው ትንቢት ይደርስ ዘንድ።
** (መዝ.118÷22) "ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች ለዓይናችንም ድንቅ ናት"።

፪ኛ. የተቀደሰው ህንጻ ቤተክርስቲያን ይባላል፦
** “እንተ ተሐንጸት በስሙ፣ ወተቀደሰት በደሙ፣ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጌሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ፣ በስሙ ታነጸች በደሙም ከበረች በዕፀ መስቀሉም ተባረከች ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ። የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና" (ሊቁ ቅዱስ ያሬድ)

** (መዝ.118÷20) "ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ"
** (1ጢሞ.3÷15) "ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው" ሕንጻውም:-

፩ኛ. ለእግዚአብሔር ክብር የምንዘምርበት፤
፪ኛ. ስለተደረገልን ነገር ሁሉ ምስጋና የምናቀርብበት፤
፫ኛ. ማሕሌቱ፣ ሰዓታቱ፣ ኪዳኑና ቅዳሴው የሚከናወንበት፤
፬ኛ. የተሰበረው ልባችንና እንባችን የሚታበስበት፤
፭ኛ. ታሪካችን የሚቀየርበት የጸጋው ግምጃ ቤት፤
፮ኛ. ሐዘናችን ወደ ደስታ ለቅሶአችን ወደሳቅ የሚቀየርበት፤
፯ኛ. እንቆቅልሻችን የሚፈታበት ነው።
፰ኛ. የጸጋ ግምጃ ቤት የበረከት ማዕድ ናት። (መዝ.65÷4)
፱ኛ.የእውነት ዓምድና መሠረት ጻድቃን የሚገቡባት ናት
-------

፫ኛ. የምዕመናን አንድነት (ሕብረት) ቤተክርስቲያን ይባላል:-
“ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ፤ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) በማለት እንደገለጸው:: ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን እንዲል ጸሎተ ሃይማኖት።

የመዠመሪያዎቹ ምዕመናን:-የሚባሉትም:-
፩ኛ. አስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣
፪ኛ. 36ቱ ቅዱሳት አንዕስት፣
፫ኛ. 72 አርድእት (ሐዋ.14፥27፣ ሐዋ.16÷5፣ ኤፌ.2÷20፣ 1ጴጥ.2÷5 ፣1ኛቆሮ.3÷16)

“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ፣ ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ፤ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ፤ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ፣ ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን። በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ። ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ። ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን" እንዳለ ሊቁ ለእኛም የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: ሀገራችንን ከጥፋት ሕዝባችንን ከስደት ከመለያየት፤ ቤተ ክርስቲያናችን ከፈተና ይጠብቅልን።

አሜን

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 06/24/2024

‹‹በዚያን ጊዜ ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፮)
++++++
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት በዓለ ጰራቅሊጦስ በዋለ ማግስት ጀምሮ የሚጾመው ጾም ጾመ ሐዋርያት ተብሎ ይጠራል። የዚህ ጾም የመግቢያው ቀን በየዓመቱ የሚለያይ ሲሆን “ቢፈጥን ከግንቦት ፲፮ አይቀድምም፤ ቢዘገይ ደግሞ ከሰኔ ፳ አያልፍም” ብለው ሊቃውንት አባቶቻችን ያስተምራሉ። ይህ ጾም የሚፈታበት ቀን ግን እንደ መግቢያው የማይቀያየር ሲሆን ሁልጊዜ ሐምሌ አምስት በቅዱሳን ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል ቀን ጾሙ ይጠናቀቃል።

በዚህ ጾም የሐዋርያት ክብራቸው፣ ቅድስናቸው እንዲሁም አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይታወሳል፡፡ ስለ ተሰጣቸው የወንጌል አደራ እስከ ሞት ድረስ መታመናቸው ይሰበካል።

ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን ጾም ሁለት ነገሮችን መሠረት በማድረግ ጾመውታል። የመጀመሪያው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወላቸውን ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ የማድረግ አርአያነት ነው። ይኸውም ክብር ይግባውና አምላካችን ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ አብ በሰማይ ተናግሮ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ክብሩ፣ አምላክነቱ የባሕርይ ልጅነቱ የተገለጠ ሲሆን ከተጠመቀ በኋላ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ ፵ ቀን እና ፵ ሌሊት ጾሟል። (ማቴ.፫ እና ፬) ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህን ጌታችን ያደረገውን ተግባር አርአያ በማድረግ በበዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ፣ ኃይልን ተቀብለው የጸጋ ልጅነታቸው ሲገለጥ ለአገልግሎት ከኢየሩሳሌም ከመውጣታቸው በፊት ጾምን የአገልግሎታቸው መጀመሪያ በማድረግ ጾመዋል። ይህም አርአያነት ቀጥሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና በርናባስ ለስብከት አገልግሎት በተለዩ/በተመረጡ ጊዜም ጾመዋል። (ሐዋ.፲፫፥፪-፫) ስለዚህ ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ ማድረግ የመጀመሪያው መሠረት ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀራጭ በነበረው በማቴዎስ ቤት ተቀምጦ ሳለ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ‹‹እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ነው። ይኽውም ‹‹ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ›› ብሎ የመለሰው መልስ በሐዋርያት በተግባር መፈጸሙን እንድረዳ ነው። ይህም ቃል ይፈጸም ዘንድ ሚዜዎች የተባሉ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙሽራው ክርስቶስ ከእነርሱ በተለየ/ባረገ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጾመውታል። (ማቴ.፱፥፲፴-፲፮)

ዛሬ ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች ከቅዱሳን ሐዋርያት በረከት እንሳተፍ ዘንድ ይህን ቅዱስ ጾም እንጾማለን። እነርሱ ጾመው በጀመሩት አገልግሎት ዓለምን በስብከተ ወንጌል ጨው ሆነው እንዳጣፈጡ በክህነት የሚያገልግሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክላቸው፣ ይቀበልላቸው፣ ያሳካላቸው ዘንድ በትጋት ሆነው ይጾሙታል። ይህ ሲባል ግን ምንም እንኳን ይህን ትልቅ በረከት የሚያሰጥ ጾም ‹‹የቄስ ጾም›› እያሉ ራሳቸውን የሚያስቱ ቢኖሩም ቤተ ክርስቲያናችን ግን በቀኖና ወስና የዐዋጅ ጾም ብላዋለችና ሁላችንም ክርስቲያኖች ከሰባት ዓመት ጀምሮ ልንጾመው ይገባል። (ፍት.ነገ.፲፭፣ገጽ.፭፻፷፮)

በዚህ ጾም ቅዱሳን ሐዋርያት ራሳቸውን ለአገልግሎት እንዳዘጋጁ፣ እንደጸለዩ እና አገልግሎታቸውንም እንደፈጸሙ እኛም በቀጣይ ልንጀምረው ያሰብነው በልቦናችን ያለው መልካም አሳብ ይፈጸም ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመንን እንጾመዋለን። የእነርሱን አገልግሎት የባረከ አምላክ የእኛንም አገልግሎታችንን፣ ሥራችንን፣ ትምህርታችንን፣ ትዳራችንን በአጠቃላይ ሕይወታችንን እንዲባርክልን እየተማጸንን እንጾመዋለን።

የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤት፣ በረከት፣ ድል የምትነሣ፣ ጥርጥር ነቅዕ የሌለባት ሃይማኖታቸው ከሁላችን ጋር ትሁን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

(© Mahibere kidusan)

+++++
** ቅዱሳት ሥዕላት ከቤተ ክርስቲያናችን እና ከሌሎች ..... የተወሰደ!!!

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 06/22/2024

መንፈስ ቅዱስ ማለት ከሦስቱ አካላት (ከቅድስት ሥላሴ) አንዱ፤ የእግዚአብሔር አብ፣ የእግዚአብሔር ወልድና የራሱም አካላዊ እስትንፋስ የኾነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

*ወረደ መንፈስ ቅዱስ* የሚለው የግእዝ ዓረፍተ ነገርም *መንፈስ ቅዱስ ወረደ* የሚል ትርጕም ያለው ሲኾን፣ ይህ ሲባልም በሰዉኛ ቋንቋ ከከፍታ ወደ ዝቅታ፣ ከሩቅ ወደ ቅርብ መምጣቱን ወይም መውረዱን ሳይኾን የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዋርያት ላይ አድሮ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትን፣ ጥበብን መግለጹንና ልዩ ልዩ ጸጋን ማደሉን ያመላክታል፡፡

ይህ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ለጊዜው ለሐዋርያት ቢሰጥም፣ በእነርሱ ላይ ብቻ ሳይገደብ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በምእመናን ላይም አድሮ ይኖራል፡፡

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ወረደ የሚለው ትምህርት መንፈስ ቅዱስን በቦታ፣ በጊዜና በወሰን መገደቡን አያመለክትም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በዓለሙ ኹሉ የሞላ ነውና፡፡ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ሲገልጽ ግን ሞላ፤ አደረ፤ ወረደ ተብሎ ይነገራል፡፡ ይኸውም ሥራዉን በሰው ላይ መግለጡን፣ ጸጋዉንም ማብዛቱን ለማመልከት የሚያገለግል ቋንቋ ነው፡፡

ከላይ እንደ ተገለጸው እግዚአብሔር በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ፍርኃትን አስወግዶ ጥብዓትን (ጭካኔን)፣ ስጋትን አጥፍቶ ቈራጥነትን (ድፍረትን) ማሳደሩን፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትን፣ ጥበብንና ጸጋን እንዲያገኙ ማድረጉን፤ በዚህም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌልና ለሰማዕትነት የሚያበቃ ቅድስና ላይ መድረሳቸዉን ያመለክታል፡፡

መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት፣ በተጠመቀባትና ከሞታን ተለይቶ በተነሣባት በዕለተ ሰንበት (በሰንበት ክርስቲያን) ሲኾን፣ መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ሰንበት (ከኀምሳኛው ቀን) ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሰንበት ያለው ጊዜም (ስምንቱ ቀናት) ዘመነ ጰራቅሊጦስ ወይም ሰሙነ ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡ ይህም መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ ስለ መውረዱና በምእመናን ላይ ስለ ማደሩ የሚነገርበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ሰሙን በቤተ ክርስቲያን የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር፣ የሚሰጠውም ትምህርት የመንፈስ ቅዱስን በሐዋርያት ላይ መውረድ የሚመለከት ነው፡፡ ስለዚህም ከኀምሳኛው ቀን (ከበዓለ ጰራቅሊጦስ) ቀጥሎ በሚመጣው እሑድ (በስምንተኛው ቀን) በሌሊት በሊቃውንቱ የሚዘመረው መዝሙር፡- *ወረደ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ሐዋርያት ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኵሉ በሐውርት* የሚል ሲኾን፣ ትርጕሙም መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በሐዋርያት ላይ መውረዱንና በእርሱ ኃይል በዓለሙ ኹሉ ቋንቋዎች መናገራቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡

በዚህ ዕለት በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም፡- የሚከተሉት ናቸው፤
* ኤፌ.፬፥፩-፲፯፤
* ፩ኛዮሐ.፪፥፩-፲፰፤
* የሐዋ.፪፥፩-፲፰፤
* መዝ.፷፯፥፲፰ (ምስባክ)፤
* ዮሐ.፲፬፥፩-፳፪ (ወንጌል)፡፡

የምንባባቱ ፍሬ ዐሳብም
** የጳውሎስ መልእክት፡-
እያንዳንዳችን መንፈስ ቅዱስ በገለጸልን መጠን የየራሳችን ልዩ ልዩ ጸጋ እንዳለን፤ የዮሐንስ መልእክት፡- የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ለዘለዓለም ሕያው እንደ ኾነ፤

** የሐዋርያት ሥራ፡-
መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ እንደ ወረደና በዓለሙ ኹሉ ቋንቋዎች መናገር እንደቻሉ፤
** መዝሙረ ዳዊት (ምስባኩ)፡- እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ልዩ ልዩ ጸጋን እንደሚሰጥ፤
** የዮሐንስ ወንጌል፡- እግዚአብሔር እኛን ልጆቹን እንደ ወላጅ አልባ እንደማይተወን ያስረዳሉ፡፡

** ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን፣ ይህም ምሥጢረ ሥላሴን፣ የጌታችንን ሰው መኾን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና መንፈስ ቅዱስን መላኩን ይናገራል፡፡

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በኹላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
(© ዲ/ን ኤፍሬም የኔሰው)

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 06/18/2024

ቅዱስ ሚካኤል
++++++++
እንኳን አደረሳችሁ!!!!!!
ሚካኤል ማለት የስሙ ትርጓሜ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው ማለት ነው። የመላእክት አለቃ ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጠባቂ መልአክ ነበር። በብሉይ ዘመን በግብጽ ባርነት ስር የነበሩ ሕዝበ እስራኤልን ቀን በደመና እየጋረደ፣ በሲና በረሀ እየመገበ ማር እና ወተት ወደምታፈሰው ከነዓን ያገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው። በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የባሕራንን የሞት ደብዳቤ የሰረዘ፤ አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነ፤ በሕይወቷ ዘመን ሁሉ የረዳት ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነው።

ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ባሕረ ኤርትራን እንዲያልፉ የረዳበት ዕለት ሲሆን ሰኔ 12 ቀን ደግሞ አፎምያን የረዳበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት ይከበራል። ቅዱሳን ነቢያትን፣ ቅዱሳን ሊቃውንትን፣ ከእግዚአብሔር በተሰጠው የመርዳት ጸጋ በተለያየ መንገድ ይረዳቸው እንደነበር ተጽፏል። እኛም የመልአኩን ረድኤት ለማግኘት በወር በወር በ12 በ12 እናከብረዋለን::

የመልአኩ ረድኤት አይለየን።
አሜን
(© Betremariam Abebaw )

06/13/2024

ለበዓለ ዕርገቱ እንኳን አደረሳችሁ
+++++
"ወበዕርገቱ ጼሐ ለነ ፍኖተ ሰማያት ወአርኀወ ለነ ኆኀተ ሰማይ::"

ትርጉም፦
"በዕርገቱም የሰማያትን ጎዳና ጠረገልን የሰማይንም ደጅ ከፈተልን::" (ድርሳነ ማሕየዊ)
++++

"ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደ ምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።"
(ዮሐ. 14፥1)

06/06/2024

የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ
ጉባኤ መግለጫ
++++++

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1. በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

2. በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤

3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

4. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡

በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስመልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል።

6. የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

7. በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

8. ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማ*ዊ*ነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቡና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

9. በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡

10. ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

12. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

06/03/2024

"ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።" (ራእየ ዮሐንስ 1:5-6)

Photos from Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's post 05/28/2024

አደጋ ላይ የወደቀው ሲኖዶስና ሲኖዶሳዊነት (ለውይይት የቀረበ ጽሑፍ)
+++++
(ከቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)

ዛሬ “ሲኖዶሳዊነት ምንድነው? ሲኖዶሳዊነት ለምን ያስፈልጋል? በሲኖዶሳዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ ምን ያህል አደገኛ ነው? ካህናትና ምዕመናን ለሲኖዶሳዊነት ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው ለምንድን ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ግድ ነው። ጊዜው ነዋ!!!

መነሻ
++++
ቅዱስ ሲኖዶስ “በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ፣ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት” የሆነ፣ “ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካል” ነው። ከዚህም ባሻገር “ሕጎችን፣ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የዳኝነት ሥልጣን” ያለው አካል መሆኑን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይደነግጋል። ይሁንና የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም በጠቅላላው በቅ/ሲኖዶስ የበላይነት የመተዳደሩ መንፈሳዊ እሳቤ በዘመናችን ሁነኛ አደጋ ላይ ወድቋል።

መጠነኛ ሐተታ
++++
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደማንኛውም በሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ውስጥ እንዳሉ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሳዊት (Synodal) ቤተ ክርስቲያን ናት። ሲኖዶሳዊነቷ (Synodality) የሚጀምረው የራሷን ሀገር በቀል ጳጳስና ፓትርያርክ ከሾመችበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ከሐዋርያት ጉባዔ እንዲሁም ቀዳሚ የመንበረ ማርቆስ አባት ከሆነው ከቅ/ማርቆስ ነው፡፡ “እስከንድርያ እናታችን፣ ማርቆስ አባታችን” በሚለው አባባል የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ ማንነት እና ምንነት በአጭሩ ይገለጻል።

በርግጥ ራስን ለመቻልና የራስን ሀገር አጠቃላይ መንፈሳዊና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማከናወን፤ “የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ” በሚለው ብሒል በተደረገው ጥረት፤ ሀገራችን የራሷ ልጆች ጳጳሳት ሆነው ማገልገል የጀመሩበትን ዘመን የሲኖዶሳችን መጀመሪያ አድርገን ብንናገርም፣ ሐዋርያዊ ቅብብሎሹን በሚያጠይቅ መልኩ ሲኖዶሳዊ ታሪካችንን ከቅ/ማርቆስ ዘመን ብሎም ከሐዋርያት ጉባዔ አለመጀመራችን በሌላ በኩል አሁን ለገባንበት ችግር አስተዋጽዖ አድርጓል።

“ሲኖዶስ የተመሠረተልን በቅርቡ ከሆነና ያለ ሲኖዶስ የኖርንበት ዘመን ለሁለት ሺህ ጥቂት ፈሪ ዓመታት ብቻ ከሆነ፣ አሁንስ ሲኖዶስ ለምን ያስፈልገናል፣ ምን ያደርግልናል፤ ይህንን ሁሉ ችግር ያመጣብን አሁን የመጣብን ይህ ሲኖዶስ ነው” የሚል አስተሳሰብ ሊያመጣ ችሏል።

እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ያለ ሲኖዶሳዊነት የኖረችበት ዘመን የለም። በዓለም አቀፍ ደረጃ ክርስትና ወንጀል ተደርጎ በሚቆጠርበት በዘመነ ሰማዕታትም ሆነ ክርስትና ሕጋዊ እምነት ሆኖ እንዲኖር በተፈቀደበት ዘመን የክርስትና ሕይወት ከአበው ጉባዔ (ሲኖዶስ) እና ከአበው ትምህርት (ሲኖዶሳዊነት) የተለየበት ጊዜ አልነበረም። ይህ ከሆነ ዘንዳ በጃንደረባው አማካይነት፣ በፊሊጶስ ትምህርትና ጥምቀት ወደ ሀገራችን የገባው የክርስትና እምነት ከሲኖዶሳዊነት የተለየበት ጊዜ የለም ብሎ መናገር ታሪክን ለራስ ትርጉም መለጠጥ አይሆንም።

አባ ፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃን አክሱምን ከእስክንድርያ ሲያገናኝ እና ጵጵስናን ሲቀበል ሐዋርያዊ ሠንሠለቱ በማይበጠስ ሁኔታ መተሳሰሩን ያሳያል። ሶርያዊ እንደመሆኑ ወደ ሶሪያ ሳይሄድ ወደ እስክንድርያ መሔዱ የአጋጣሚ ጉዳይ ብቻ ሊሆን አይችልም። በመልክዓ ምድር ቅርበት ብቻ ነው ብሎ መውሰድም አይቻልም። እግዚአብሔር ባወቀ የተደረገ ከመሆኑም በላይ በአክሱምና በእስክንድርያ መካከል የቀደመ ግንኙነት መኖሩን መገመት የዋህነት አይሆንም። (በተጨማሪም ሁልጊዜ የሚደንቀኝን የእግዚአብሔር ጥበቃ እዚህ ላይ እንድጠቅሰው ያደርገኛል።)

ሶርያዊው አባ ፍሬምናጦስ ከእስክንድርያ ይልቅ በሥጋ ዘመዶቹ ወደሚሆኑት ሶርያውያን ቢሔድና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም በሶርያ መንበርና ትውፊት የምትመራ ብትሆን ኖሮ ኋላ በሶርያውያን መካከል የተፈጠረው የምሥራቅና የምዕራብ ሶርያ የእምነት ክፍፍልና ቁርቋሶ ወደ ሀገራችንም ሊገባ ይችል ነበር። በሕንድ ኦርቶዶክስ ያለው ዓይነት ክፍፍልም ይወድቅብን ነበር። ቤተ ክርስቲያናችንም አሁን በምናያት መልክ በተዋሕዶ ጸጋዎቿ በልጽጋ ላናገኛት እንችል ነበር ብዬ አስባለሁ።

አባ ፍሬምናጦስ ከቅ/አትናቴዎስ ክህነትን ብቻ አላመጣም። የእስክንድርያ ሲኖዶሳዊነትም ገንዘባችን ሆኗል:: በዚህም የእስክንድርያ ብቻ ሳይሆን የሐዋርያት አንድነት አካል ሆነናል። ምክንያቱም የአባ ፍሬምናጦስ ክህነት እውነተኛ ክህነት የሆነው ከሐዋርያት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው አማናዊ የክህነት ሥርዓት ውስጥ ያለ ስለሆነ ነው። ያ ክህነት በሲኖዶሳዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ያለ ነው። በሐዋርያት ቀኖና፣ በሐዋርያት ሥርዓት፣ በሐዋርያት ትውፊት፣ በሐዋርያት ትምህርት ላይ የጸና ሐዋርያዊ ክህነት በመሆኑ ነው እኛም ልጆቹ በአማናዊቱ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነን ብለን የምናምነው፣ የምንናገረው።

ከዚህ አፈንግጠው የራሳችን ጳጳስ፣ የራሳችን መንበር፣ የራሳችን ቤተ ክህነት ፈጠርን ያሉ ሰዎች ከዚህ ሐዋርያዊ ዛፍ ተገንጥለው የወደቁ የደረቁ ቅርንጫፎች ስለሆኑ ክህነታቸው ፍሬ አያፈራም። ቢቀድሱ፣ ቢያቆርቡ፣ ቢያጠምቁ፣ ክህነት ቢሰጡ ሁሉም ተራ ዕቃዕቃ ጨዋታ ነው::

ሲኖዶሳዊነት ኮሚቴነት አይደለም!!
++++
ኮሚቴ አንድን ተግባር ለመከወን በጊዜያዊነት የሚቋቋም የተግባር ቡድን ነው። ሲኖዶስ ኮሚቴ አይደለም። አስተዳደራዊ ሥራን ቢሠራም እውነቱን ለመናገር አስተዳደራዊ ሥልጣንም አይደለም። የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ዓላማ (ድኅነትን) ለመፈጸም የሚተጋ መንፈሳዊ ተቋም ነው። የቤተ ክርስቲያን ነገረ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊ፣ ትውፊታዊ እና ማሕበራዊ ጤንነት የሚጠበቀው በሲኖዶሳዊ ሥርዓት ነው።

የመጀመሪያው የሐዋርያት ሲኖዶስ ከተደረገበት ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነሡ ሃይማኖታዊ ጦርነቶች (ኑ*ፋ*ቄዎች) መልስ እያገኙ የመጡት በዓለም አቀፍ ሲኖዶሳዊ ጉባዔዎች ነው። ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጡ ችግሮች በጊዜው መፍትሔ ሊበጅላቸው የሚገባው በሲኖዶሳዊ ጉባኤ ነበር:: እውነታው ግን ከዚህ በጣም እየራቀ ነው:: ሲኖዶሳዊነትም ዓይናችን እያየ በመናድ ላይ ይገኛል። ለዚህም ደግሞ ውጪአዊ/ አፍአዊ ምክንያቶች ያሉትን ያህል በራሳቸው በቅ/ሲኖዶስ አባላትም የሚፈጸመው ሐዋርያዊውን ሥርዓተ-ሲኖዶስ የመናዱ እንቅስቃሴ ከባድ ታሪካዊ ወቅት ላይ ደርሷል።

ሲኖዶሳዊነትን የሚገዳደረው ማን ነው?
++++++
ሀ/ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ሕይወት ዋነኛ ተግዳሮት ፖለቲካ መሆኑን ካወቅን 50 ዓመት አለፈን። የሀገራችን ፖለቲካ ፓትርያርኳን ገድሎ፣ ጳጳሳቷን አሰድዶና አሥሮ፣ ንብረቷን ዘርፎ፣ ልጆቿን ጨፍጭፎ፣ ታሪኳን ጥላሸት ቀብቶ፣ ሲኖዶሷን ለሁለት ከፍሎ፣ ፓትርያርኳን አሰድዶ መከራ አጽንቶባታል። በዘመናችን ደግሞ አድማሱን እና ኃይሉን በመጨመር ሲኖዶስን በነገድ ደረጃ ለመሸንሸን ቆርጦ የተነሣ ፖለቲካ ገጥሞናል።

ለዚህም የመጀመሪያው ምክንያት በዘር ሐረግ የሚመራ ፖለቲካ ቤተ ክርስቲያንም የዘር ሐረግን የእምነቷ መሠረት እንድታደርግ ለማስገደድ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ሲኖዶሳዊነትን በመናድና በመከፋፈል በጎችን ያለ እረኛ ለማስቀረት የሚተጋ ሲኖዶሳዊ ሥርዓት የሌለው የቀበሮ ሰብሰብ የሆነ የእምነት ቡድን የፖለቲካ ሥልጣንን እየተጠቀመ መሆኑ ነው።

እንደታሰበውም አገልግሎታችን የዘር ሐረግን የተከተለ በማድረግ ላይ እንገኛለን። ጳጳሳትን ሳይቀር በዘር ሐረግ ለይተን በመሾም ላይ ነን። ምእመኖቻችን የኔ አባት የሚሉት ከራሣቸው ወንዝ የተገኘውን ብቻ ወደ መሆን እየደረስን ነው። የምንደግፈውም የምንቃወመውም ትውልደ ነገዳችንን፣ ሀገር ሙላዳችንን እየተመለከትን ብቻ ነው። ስለዚህም ፖለቲካው ያቀደልን ሁለት ዓላማዎች እየተሣኩለት ነው ብንል ማጋነን አይደለም።

ለ/ ፖለቲካው የፈቀደውን ማድረግ የቻለው ዓላማውን ሊያስፈጽምባቸው የሚችልባቸው አበው ጳጳሳትና ካህናት በመኖራቸው ነው። ሰይጣን በእባብ አድሮ ገነት ገባ። ሰይጣን በአስቆሮቱ ይሁዳ አድሮ ከሐዋርያት ጉባዔ ገባ። ሰይጣን በነአርዮስ፣ ንስጥሮስ፣ መቅዶንዮስ አድሮ ከአበው ሲኖዶስ ገባ። የዘመናችንም ከዚህ የተለየ አይደለም። በራሳችን ሥጋዊ ድካም ሰይጣንን ወደ ጉባዔያችን አስገብተናል። መፍትሔውም ግልጽ ነው። “ሑር እምኔየ ሰይጣን”!!!!!

ሐ/ ከላይ የተዘረዘረውን የፖለቲካውንም የአበውን ድካምም በመረዳት ችግሩን ለመዋጋት የሚደረገው ትግል ደርዝ እና ፈር እየለቀቀ በመምጣቱ ትግሉ ሲኖዶሳዊነትን ወደመቃወም እያደገ ይመስላል። ለቅ/ሲኖዶስ ዓላማ ተጻራሪ ሥራ የሚሠሩ ጳጳሳትን ለመቃወም የሚነገሩ፣ የሚጻፉ፣ የሚደረጉ ተግባራት ጵጵስናንና ጉባዔቸውን (ሲኖዶስን) ጭምር ወደ መገዳደር ማደጉ በራሱ ተጨማሪ ተግዳሮት ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ። “ሲኖዶሱ ይህንን የማያደርግ ከሆነ ይህንን አደርጋለሁ” የሚል ክፍል መበራከቱ አንድን ጳጳስ በመቃወም እና ሲኖዶሳዊነትን በመቃወም መካከል ያለው ቀጭን መስመር እንዲጠፋብን አድርጓል።

ምን ይሻላል ጎበዝ?!!!
++++
በዘር ሐረግ ማንነት ላይ የቆመው የዘመኑ የሀገራችን ፖለቲካ ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ጋራ የማይታረቅ ቅራኔ ነው ያለው። በምንም መልኩ ብናባብለው ዓላማውን ትቶ አይገራም። የቤተ ክርስቲያን መኖር ለዓላማዬ እንቅፋት ነው ብሎ የወሰነና ለዚህም ላለፉት 60 ዓመታት ተግቶ የሠራ እንደመሆኑ በዘመነ ወያኔም በዘመነ ብልጽግናም ያለው ጸረ ኦርቶዶክሳዊነት ይቀጥላል። መፍትሔው ቤተ ክርስቲያን ዘረኝነት ኢክርስቲያናዊ መሆኑን እንደምታምን ተግቶ ማስተማር፣ ለዚህም የሚፈለገውን ዋጋ መክፈል ብቻ ነው። ዘረኛ ሰው ሃይማኖት የለውም። “አሁን የፕትርክናው ተራ የእኛ ነው” የሚል ሰው ሃይማኖት የሌለው ሰው መሆኑን ማስተማር ነው መፍትሔው።

በተጨማሪም ይህንን በጎሳ (ዘረኝነት) ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ተጠግቶ የመጣውንና ሥልጣን የተቆጣጠረውን ፖለቲካ ለበስ እምነትም ከመቃወም ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም። በአፍም በመጣፍም መታገል ይገባናል። በየዘመናቱ ከዓላውያን ነገሥታት፣ ከግኖስቲኮችና ከሐሳውያን ወንድሞች (መ*ና*ፍ*ቃ*ን) ጋራ እንደተደረገው ክርስቲያናዊ ተጋድሎ በዘመናችንም በክርስቲያናዊ ጥብዓት ያንኑ መድገም ይገባናል።

በሌላ መልኩ ለቤተ ክርስቲያን በመቆርቆር ስም የሲኖዶሳዊነታችን ተግዳሮት በመሆን ላይ ያሉ አካላትን ግን ለጊዜው ሃይ ባይ የተገኘ አይመስልም። ፍፁም ክርስቲያናዊነት በጎደለው መልክ እየተካሄደ ያለው ይህ ስመ-ለቤተ-ክርስቲያን-ጥብቅና መቆም ዞሮ ዞሮ የሚጎዳው ቤተ ክርስቲያናችንን ነው። እግዚአብሔር የማይከብርበት ፍጹም ዓለማዊ ፉክክር፣ ዘለፋ፣ የሰው ኃጢአት የመቆፈር ተራ ተግባር ስለሆነ ምንም ክርስቲያናዊነት የለበትም። ሰዎችን በማዋረድ ላይ ያተኮረ ዓለማዊ ሩጫ ስለሆነ ፍሬ የለውም። ፍሬ አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሰዎች የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ደጉንም ነገር እንዲጠሉ፣ እንዲጠራጠሩ፣ እንዲሸሹ ያደርጋቸዋል።

ቅ/ሲኖዶስ በዚህ ሁሉ ውስጥ ሆኖ የግንቦት 2016 ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባዔውን ያደርጋል። ፓለቲካውም፣ አጽራረ ኦርቶዶክሱም፣ በዚህ መካከል ሥልጣን አገኝ ብሎ የሚተጋውም፣ የሲኖዶሱ አባል ሆኖ ልቡ ለሌላ ያደረውም ሁሉም የአቅሙን ያህል መፍጨርጨሩ አይቀርም።

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ያውቃል!!!!!

05/20/2024

ግንቦት 12 ቀን ፍልሰተ ሥጋሁ ለአቡነ ማር ተክለሃይማኖት
+++

"ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወዐፅሙ"

** ትርጉም

"ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ ታመሰግነዋለች የሥጋውና የዐፅሙ ፍልሰት በውስጧ ተደርጓልና"
++++

* የፍልሰተ ዐፅሙ መታሰቢያ ግንቦት 12 ቀን
* እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ

05/09/2024

የጌታ እናት ልደት፤ ታላቅ ቀን፤
+++++
ለክርስቲያን ሁሉ የእመቤታችንን ልደት ማክበር ቀላል አይምሰለው፤ የከበረ ገናና ነውና።

እንኳን አደረሳችሁ፣
ጣዕሟን በአንደበታችን - ፍቅሯን በልቡናችን ይሳልብን። ያሳድርብን። አሜን

05/06/2024

✞ ✞ ✞ ፋ ሲ ካ እ ና ት ን ሣ ኤ ✞ ✞ ✞
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐨𝐯𝐞𝐫 𝐚𝐧𝐝 𝐑𝐞𝐬𝐮𝐫𝐫𝐞𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧

እንኳን ለ1982ኛው የጌታችን ብርሃነ ትንሣኤ አደረሰን።

በእለተ እሑድ መጋቢት 29 ቀን 34 ዓ.ም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑ ተነስቷል። ይህም ማለት ዘንድሮ የምናከብረው የትንሣኤ በዓል 1982ኛው ይሆናል ማለት ነው።
የትንሣኤን በዓል ማክበር የጀመሩት ቅዱሳን ሐዋርያትና ሰብዐ አርድእት፣ ኋላም በየጊዜው የተነሡት ሊቃውንትና ምእመናን ናቸው፡፡ ድምቀቱና የአከባበር ሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂ መከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡ እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ኢየሩሳሌም ባሉ ታላላቅ ገዳማት ደግሞ በዓሉ እጅግ በጣም በታላቅና በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡

ለምንት ተኃሥሣሁ ለሕያው ምስለ ምውታን ? ተንሥአ ኢሀሎ ዝየሰ !
ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም። (ሉቃስ 24:5)
ሞተ በፈቃዱ ወተቀብረ በሥምረቱ እንዲል በፈቃዱ ሞቶ በውዱ ተቀብሮ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በገዛ ሥልጣኑ በዘመነ ማርቆስ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት ተነስቷል፡፡

«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡
መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግስ ሲሆን፡፡
«ትንሣኤ» ማለት = መነሣት፥ አነሣሥ፥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» ( Resurrection) በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዓይነቱ ሲተረጐም 5 ክፍል አለው፡፡
1ኛ «ትንሣኤ» ማለት ኅሊና ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡
2ኛ «ትንሣኤ» ማለት ልቡና ማለት ነው፡፡ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡
3ኛ «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4ኛ «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡
5ኛ የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጕባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፥ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤
ይገብሩ በዓለ ደመናት፤
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

«ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» /ፐሳኽ/፣
በጽርዕ (በግሪክኛ) /ፓስቃ/ «ስኻ» ይባላል፡፡ በግእዝና በዐማርኛ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገር፣ መሸጋገር ማለት ነው፡፡
በእንግሊዝኛ «ፓስኦቨር» (Passover) ይሉታል፡፡

ፋሲካ በ1513 ዓ/ዓ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን ጊዜ ለማስታወስ አይሁዳውያን የሚያከብሩት በዓል ነው።
የዚህም ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደ ነጻነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ኅዘን ወደ ፍጹም ደሰታ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡
የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብጽ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል።
በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ። በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡ የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምሥጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህን በዓል አቢብ በተባለው ወር (ይህ ወር ከጊዜ በኋላ ኒሳን ተብሎ ተጠርቷል) በ14ኛው ቀን በየዓመቱ እንዲያከብሩ እስራኤላውያንን አዟቸው ነበር።—ዘፀአት 12:42፤ ዘሌዋውያን 23:5

እስራኤላውያን በፋሲካ በዓል ዕለት ከበግ ወይም ከፍየል ሥጋ በተጨማሪ፣ ቂጣ እና መራራ ቅጠል ይበሉ ነበር።—ዘፀአት 12:8
እስራኤላውያን ከፋሲካ በኋላ ባሉት ሰባት ቀናት የቂጣ በዓልን ያከብሩ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ እርሾ ያለበት ዳቦ አይበሉም ነበር።
ዘፀአት 12:17-20፤ 2 ዜና መዋዕል 30:21

በሐዲስ ኪዳን የጌታችንን ትንሣኤ ፋሲካ የምንለው ሞት ከእኛ ያለፈበት የመጀመሪያው በዓላችን በመሆኑ ነው፡፡ ስለ ብዙዎች ይቅርታ የፈሰሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም በግብጽ ከተሠዋው በግ ይልቅ የከበረ መሥዋዕት ነውና ያሉትን ከማዳኑም ባሻገር የሞቱትንም ከመቃብር አውጥቷል፡፡ በእርሱ ትንሣኤ ሞት ከእኛ ማለፉንና የሰው ባሕርይ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱንም ‹‹ለምንት ተኀሥሣሁ ለሕያው ምስለ ምዉታን፤ ሕያዉን ከሙታን ጋር ስለ ምን ትፈልጉታላችሁ›› ከሚለው ኃይለ ቃል እንረዳለን (ማቴ. ፳፰፥፮)፡፡ ምዉታን ያላቸውም አጋንንት ናቸው፡፡ በጌታችን ትንሣኤ ሰው ከሙታነ ሕሊና ከአጋንንት ተለይቶ ተነሥቷል፡፡ ‹‹ኦ! አዳም መሬት አንተ ወትገብዕ ውስተ መሬት፤ አዳም ሆይ ቀድሞም መሬት ነህ፤ ወደ መሬትነትህም ትመለሳለህ›› የሚለው አዋጅ አሁን ተቀይሯል፡፡ የጌታችን ትንሣኤ ከሚያረጀው ወደማያረጀው፣ ከሚበሰብሰው ወደማይበሰብሰው ሰውነት የተሸጋገርንበት በዓል ነው፡፡ ይህ ዂሉ መሸጋገር የተፈጸመው በፋሲካው በግ ምክንያት በመኾኑ ክርስቶስን ፋሲካችን እንለዋለን (፩ኛ ቆሮ. ፭፥፯)፡፡

በሐዲስ ኪዳን የጌታችንን ትንሣኤ ፋሲካ የምንለው ‹‹መሥዋዕተ ኦሪት አለፈ፤ መሥዋዕተ ወንጌል ደረሰ›› የምንልበት ወቅት ስለ ኾነ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለደቀ መዛሙርቱ በሰጠበት ዕለት በፋሲካ የተጀመረችውን ሕግ በፋሲካ ይሽራት ዘንድ የሚያልፈውን መሥዋዕተ ኦሪት አስቀድሞ፣ የሚመጣውን መሥዋዕተ ወንጌል አስከትሎ ፋሲካን አደረገ፡፡ ለደቀ መዛሙርቱም ‹‹ዝ ውእቱ ደምየ ዘይትከአው ለሐዲስ ሥርዓት በእንተ ቤዛ ብዙኃን፤ ስለ ብዙዎች ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው›› (ማቴ. ፳፮፥፳፰) በማለት ወደ ሐዲስ ኪዳን መግባታቸውን አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ትንሣኤ አሮጌውን ትተን ወደ አዲስ ሕይወት የተሸጋገርንበት በዓል በመኾኑ ፋሲካ እንለዋለን፡፡

የደስታችን ማረጋገጫ ስለ ኾነ ነው፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት በግእዝ ቋንቋ ‹ደስታ› ማለት ነው፡፡ ደስታችን የተረጋገጠው በጌታችን ትንሣኤ ሲኾን ፍጻሜውን የሚያገኘው ደግሞ በትንሣኤ ዘጉባኤ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን በዕለተ ዓርብ በቈረሰው ቅዱስ ሥጋውና ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ተመሥርታለች፡፡ ምንም እንኳን በሕዝብና በአሕዛብ ፊት ደስታዋን የምትገልጥበት ጊዜ ገና ቢኾንም፣ በትንሣኤው ግን በዝግ ቤት ውስጥ ኾና የክርስቶስን ሰላምታ ተቀብላ ተደስታለች (ዮሐ. ፳፥፲፱)፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ደስ ትሰኛለች›› እያልን የምንዘምረው፡፡

ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስ የትንሣኤዋ በኵር ኾኖ ተነሥቶላታልና ሊገድሏት በሚጎትቷት ሰዎች ፊት ለሽልማት እንደ ተጠራ ብላቴና ደስ እያላት ትቀርባለች (፩ኛ ቆሮ. ፲፭፥፳)፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደስታዋን በትንሣኤ ፍጹም እንደምታደርገውም ቅዱስ አርክዎስ በሃይማኖተ አበው ፱፥፩ ላይ ‹‹በዛቲ ዕለት ተፈጸመ ፍሥሐሃ ለቤተ ክርስቲያን፤ በዚች ቀን የቤተ ክርስቲያን ደስታ ፍጹም ኾነ›› በማለት ይመሰክርላታል፡፡ በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የጌታችን ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ ይጠራል፡፡

በአጠቃላይ የትንሣኤ በዓል ፤

 በዘመነ ሐዲስ የምንገኝ እስራኤል ዘነፍስ የሆንን ምዕመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የምናከብረው፤
 በእርሱ ትንሣኤ ከኀጢአት፤ ወደ ጽድቅ፣
 ከኀሳር ፥ ከውርደት፤ ወደክብር፣
 ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ፤ ወደ ዘለዓለማዊ ነፃነት፣
 ከአደፈ፥ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት፤ ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገርንበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡
ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት እናከብረዋለን፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡

በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጥተናል÷ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል ።
ሙታን የነበርን ሕያዋን÷ ምድራውያን የነበርን ሰማያውያን÷ ሥጋውያን የነበርን መንፈሳውያን ሆነናል፡፡
«ሞት ሆይ÷ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ÷ ድል መንሣትህ የት አለ?» የምንል ሆነናል፡፡ ሆሴ ፲፫÷፲፬ ፣ ፩ኛቆሮ ፲÷፶፭፡፡
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና÷ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡» የምንል ሆነናል፤ ፊል ፫፥ ፳-፳፩፡፡
ናፍቆታችን ሁሉ በትንሣኤ ያገኘነውን ጸጋ እውን ማድረግ ነው፡፡ «ድንኳን የሚሆነው ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና፡፡ በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና÷ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድን ለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም» ይላል፡፡ (፪ኛቆሮ ፭፥፩-፪)
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ÷ እድፈትም ለሌለበት÷ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ» ብሏል፡፡ (፩ኛጴጥ ፩÷፫)
ቅዱስ ጳውሎስም፡- «በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳየን ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊው ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን» ብሏል። ኤፌ፪÷፮-፯።
በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ የምንገኝ እስራኤል ዘነፍስ የሆንን ምዕመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የምናከብረው፤ በእርሱ ትንሣኤ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር ከውርደት ወደ ክብር፣ ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ ከአደፈ፥ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት፤ ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገርንበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት እናከብረዋለን፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡

እንኳን ለ1982ኛው የጌታችን ብርሃነ ትንሣኤ በዓል አደረሰን
በዓሉን የሰላም ያድርግልን ‼

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in San Antonio?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የዕለቱ መምህር፦ ቀሲስ አክሊለ ሰማዕት፤
Ethiopian Orthodox Tewahido Hymn by Debre Edom St. Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Church children.የእንግሊዝኛ መዝሙርCourtesy...
መዝሙር ኪነ ጥበቡ ከጥቅምት ፫ - ፱+++(በ፫/የ) ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ ለዘሀሎ መልዕልተ አርያም አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ ...
የብዙኃን ማርያም ክብረ በዓል፤ በደብራችን ....

Category

Telephone

Website

Address

8102 Midcrown Drive
San Antonio, TX
78239

Opening Hours

4am - 10pm
Other Churches in San Antonio (show all)
The Hills Church The Hills Church
2255 Horal Street
San Antonio, 78227

Glorifying God through Transformed Lives Know God. Love Others. Live the Gospel.

KBC Ministries KBC Ministries
16010 University Oaks Ste. 104
San Antonio, 78249

http://kbc-ministries.org

GFC Youth GFC Youth
10907 W 1604 N
San Antonio, 78254

Middle & High School Ministry of Gateway Fellowship Church. • Helping Friends Become Devoted Followers of Jesus. • Wednesday Service at 7PM

Bracken Methodist Church Bracken Methodist Church
20377 FM-2252
San Antonio, 78266

A Church where we Love All, Grow Disciples, Serve Community. We also love our Bracken Preschool!

New Vision Church of God New Vision Church of God
10050 W Commerce Street
San Antonio, 78227

Helping people find God, grow their faith, discover their purpose and to build God’s Kingdom

Exchange Life Church Exchange Life Church
11503 Big Mesa Drive
San Antonio, 78245

We lead people far from God into a life-changing encounter with Jesus.

Great-Commission Christian Church - GCC Great-Commission Christian Church - GCC
2718 Frontier Drive
San Antonio, 78227

Taking the gospel light to all nations

Lutheran Church of the Good Shepherd Lutheran Church of the Good Shepherd
San Antonio, 78223

We are spiritual community that celebrates the gift of God that empower us to engage in the struggles of life,to care for each other, and to serve Christ where we work and live.Joi...

Brujos y Chamanes de Latinoamerica Brujos y Chamanes de Latinoamerica
Latinoamérica
San Antonio

Se hacen trabajos esotéricos con brujos y chamanes de toda Latinoamérica

The Church at Brooks The Church at Brooks
2623 SE Military Drive
San Antonio, 78223

The Church at Brooks is a Christian community which serves the Brooks City Base area in San Antonio, TX. We meet Sunday mornings at 10am at City Base Cinema. Theatre 9. Families...

The Rim Church The Rim Church
4114 Lockhill Selma
San Antonio, 78249

At The Rim, we desire to create space for people to discover the beauty of Jesus.

All Things New Worship Center San Antonio All Things New Worship Center San Antonio
San Antonio

Founded on biblical principles and empowered by God; knowing Jesus and making Jesus known, by reaching up, reaching out and reaching in to help others be saved, equipped, and empow...