Lemi kura woreda 08 public service

Lemi kura woreda 08 public service

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lemi kura woreda 08 public service, Government Organization, .

Photos from Lemi kura woreda 08 public service 's post 04/08/2023

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የጽ/ቤቶች የ12 ወር ምዘና

Photos from Lemi kura woreda 08 public service 's post 30/06/2023

የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ወጥ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት በሚያስችለው የዜጎች ስምምነት ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም በተቋማት ደረጃ የሚሠጡ አገልግሎቶች ወጥ አለመሆኑን ተከትሎ በከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ወጥ የሆነ አገልግሎት ለተገልጋዩ ለመስጠት ያመች ዘንድ በከተማ አስተዳደሩ በተዘጋጀው የዜጎች ስምምነት ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የዚህ ዜጎች ስምምነት ሰነድ መዘጋጀት በዋናነት አስፈላጊነቱ አገልግሎት ሰጪው አካል የሚሠጡ አገልግሎቶችን እንዲያውቅና ተገልጋዩ የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በቀላሉ ተተቋማት የሚሠጡ አገልግሎቶችን በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማግኘት እንዳለበት እንዲረዳና አገልግሎቱን በተገቢ ሁኔታ ያልሠጠውን አካል ደግሞ ተጠያቂ የሚያደርግበት ህጋዊ አግባብ ለመፍጠር እንዲረዳ ያግዝ ዘንድ እንደሆነም በመድረኩ ተገልጿል።

ይህ መድረክ የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድርብሳ ተስፋ ይህ ውይይት መደረጉ በዋናነት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ወጥ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ተናግረው ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ግንዛቤ መያዝ ተችሏል ሲሉም ተናግረዋል።

የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ሰኔ 22/2015 ዓ.ም

Website