Dilamo Wolde
Private page
LESSON FOR TODAY
A lady worked at a meat distribution factory.
One day, when she finished with her work
schedule, she went into the meat cold room
(Freezer) to inspect something, but in a
moment of misfortune, the door closed and
she was locked inside with no help in sight.
Although she screamed and knocked with
all her might, her cries went unheard as no
one could hear her. Most of the workers had
already gone, and outside the cold room it's
impossible to hear what was going on
inside.
Five hours later, whilst she was at the verge
of death, the security guard of the factory
eventually opened the door.
She was miraculously saved from dying that
day.
When she later asked the security guard
how he had come to open the door, which
wasn't his usual work routine.
His explanation: "I've been working in this
factory for 35 years, hundreds of workers
come in and out every day, but you're one of
the few who greet me in the morning and
say goodbye to me every night when leaving
after work. Many treat me as if I'm invisible.
Today, as you reported for work, like all
other days, you greeted me in your simple
manner 'Hello'. But this evening after
working hours, I curiously observed that I
had not heard your "Bye, see you
tomorrow".
Hence, I decided to check around the
factory. I look forward to your 'hi' and 'bye'
every day because they remind me that I am
someone.
By not hearing your farewell today, I knew
something had happened. That's why I was
searching every where for you."
Be humble, love and respect those around
you. Try to have an impact on people who
cross your path every day, you never know
what tomorrow will bring.
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tadela Beyene, Wondimu Melese Darago, Getahun Kusa Tenke, Tamrat Katiso
እግዚአብሔር ሁለተኛ ዕድል የሚሰጥ አምላክ ነው።
++++++++====++++
ከሞቱ 3 ቀን ሆኖዋቸው ነበር ግን ደግሞ ጌታ ሌላ ዕድል ተሰጥቷቸው ከትላንት ጀምሮ አዲስ ሕይወት መጀመራቸውን እየሰመን ነው።🙏
2፤ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።
3፤ አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።
4፤ የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል።
5፤ ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።
6፤ እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።
7፤ እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
8፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።
9፤ እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።
10፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
1ሳሙ 2÷2-10❤
የመልካምነት አባት፤ ሮቤርቶ ሪባቶኒ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ😭😭
||የቼንትሮ አዩት ለኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር ናቸው። በአገራችን በተለያዩ ክልሎች በልማት ስራዎቹ የሚታወቁ፣ በተለይም የወደቁትንና ድጋፍ ላጡት የመልካምነት አባት ሮቤርቶ ሪባቶኒ፣ ከዚህ ዓለም ድካም ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ማረፋቸውን ሰምተናል።
በእጅጉ አሳዛኝ ነዉ። ግን ምንም ማድረግ አንችልም። ፈጣሪ በኢትዮጵያ ምድር፤ በኢትዮጵያውያን ልብ የሰራዉን መቼም አንረሳም።
ሮበርቶ ራባቶኒ
👉በሀዲያ ዞን በሶሮ ወረዳ÷
👉በዱና ወረዳ
👉በሆሳዕና ከተማ የባልሎ ወንጭሶ ት/ቤት ዕድሳት
👉የአቡና የ1ኛ እና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ወጪውን ሸፍነው አሰርተዋል።
ሮበርቶ ራባቶኒ
ባደረባቸው ህመም በትውልድ ሀገራቸው ጣሊያን ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ጥር 21 ቀን 2ዐ16 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
10 African countries with the lowest cost of living in 2024
1. Nigeria
2. Libya
3. Kenya
4. Madagascar
5. Rwanda
6. Tanzania
7. Ghana
8. Egypt
9. Somalia
10. Tunisia
Credit| Business Insider Africa
Countries In Africa By Population:
1. Nigeria 🇳🇬 223,804,632
2. Ethiopia 🇪🇹 126,527,060
3. Egypt 🇪🇬 112,716,598
4. Democratic Republic of Congo 🇨🇩 102,262,808
5. Tanzania 🇹🇿 67,438,106
6. South Africa 🇿🇦 60,414,495
7. Kenya 🇰🇪 55,100,586
8. Sudan 🇸🇩 48,109,006
9. Uganda 🇺🇬 48,582,334
10. Algeria 🇩🇿 45,606,480
11. Morocco 🇲🇦 37,840,044
12. Angola 🇦🇴 36,684,202
13. Ghana 🇬🇭 34,121,985
14. Mozambique 🇲🇿 33,897,354
15. Madagascar 🇲🇬 30,325,732
16. Ivory Coast 🇨🇮 (Côte d'Ivoire) 28,873,034
17. Cameroon 🇨🇲 28,647,293
18. Niger 🇳🇪 27,202,843
19. Burkina Faso 🇧🇫 23,251,485
20. Mali 🇲🇱 23,293,698
21. Malawi 🇲🇼 20,931,751
22. Zambia 🇿🇲 20,569,737
23. Chad 🇹🇩 18,278,568
24. Senegal 🇸🇳 17,763,163
25. Somalia 🇸🇴 18,143,378
26. Zimbabwe 🇿🇼 16,665,409
27. Guinea 🇬🇳 14,190,612
28. Rwanda 🇷🇼 14,094,683
29. Benin 🇧🇯 13,712,828
30. Tunisia 🇹🇳 12,458,223
31. Burundi 🇧🇮 13,238,559
32. South Sudan 🇸🇸 11,088,796
33. Togo 🇹🇬 9,053,799
34. Sierra Leone 🇸🇱 8,791,092
35. Libya 🇱🇾 6,888,388
36. Congo 🇨🇬 6,106,869
37. Central African Republic 🇨🇫 5,742,315
38. Liberia 🇱🇷 5,418,377
39. Mauritania 🇲🇷 4,862,989
40. Eritrea 🇪🇷 3,748,901
41. Gambia 🇬🇲 2,773,168
42. Botswana 🇧🇼 2,675,352
43. Namibia 🇳🇦 2,604,172
44. Gabon 🇬🇦 2,436,566
45. Lesotho 🇱🇸 2,330,318
46. Guinea- Bissau 🇬🇼 2,150,842
47. Equatorial Guinea 🇬🇳 1,714,671
48. Mauritius 🇲🇺 1,300,557
49. Eswatini 🇸🇿 1,210,822
50. Djibouti 🇩🇯 1,136,455
51. Réunion 🇷🇪 981,796
52. Comoros 🇰🇲 852,075
53. Cabo Verde 🇨🇻 598,682
54. Western Sahara 🇪🇭 587,259
55. Mayotte 🇲🇫 335,995
56. Sao Tome & Principe 🇸🇹 231,856
57. Seychelles 🇸🇨 107,660
58. Saint Helena 🇦🇮 5,314
Via OPPFY
ኮትዲቯር ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግብጽን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግብጽን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች አራተኛዋ ሀገር ሆነች።
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ግብጽ ባደረጉት የመደበኛና የጭማሪ ሰዓት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
በመሆኑም በመለያ ምት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 8 ለ 7 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
እስካሁን አንጎላ፣ ናይጄሪያ፣ ጊኒ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
🌲🌲🌲
Time matters,
ሰዎች ያልደከሙበትን እና ያልዘሩትን ለምን ያጭዳሉ ?
Uses and Health Benefits of Common Rue Common Rue, scientifically known as Ruta graveolens, is an herbaceous plant that has been used for centuries for its various medicinal and culinary properties. This herb is native to southern Europe but is now cultivated in many parts of the world. In this article, we will explore the uses and…
How to Grow Tomatoes Fast and Achieve Big Harvests at Home
Full guide in the first comment 💬👀
Africàn Moors from North Africa cònquered and ruled Spain 🇪🇸 for 781 years! They ruled Spain from 711-1492.
They passed through Morocco and crossed the Strait of Gibraltar to enter Iberian Peninsula, Spain.
Africàn Moors built universities and mosques in Spain. They also made huge contributions to Mathematics, Medicine, Chemistry, Philosophy, Astronomy, Botany, Masonry and History.
📸 Afrofuturism Central
Guys kindly click this link below to subscribe to our youtube channel (YT: Africa is home podcast ) to keep up with our weekly conversations about the progress and future of Africa 🙏🏿.
http://m.youtube.com/
Credit| Yemi Melikhaya
This plant is abundant in most backyards, and we cut it down without knowing it has properties capable of treating more than 10 diseases.💚
Full guide in the first comment 💬👀
በደንና በደን ውጤቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች አስቀጭነት
ደን ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ያለማው ሊሆን የሚችል ሲሆን ተፈጥሮአዊ ደን በተፈጥሮ የበቀሉ የተለያዩ የዛፍ ዝርያዎች፣ ቁጥቋጦና ሌሎች የእንጨትነት ፀባይ ያላቸው ተክሎች የበቀሉበት እና ከፍተኛ የብዝሀ ህይወት ክምችት የሚገኝበት ነው፡፡ የተፈጥሮ ደን አካባቢዎች መኖር የሥነ-ምህዳራዊ (ecosystem) ጤንነትን እና ከፍተኛ ብዝሀ ህይወት ስብጥር እና ክምችትን በመጠበቅ የአካባቢ ንብረት መለወጥን (climate change) በመከላከሉ ረገድ የማይተካ ሚና ከመጫወታቸው በተጨማሪ ሰፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ሆኖም ለነዚህ የተፈጥሮ ደኖች የሚደረገው ጥበቃ አጥጋቢ ባለመሆኑ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ወደ ሌላ የመሬት አጠቃቀም እየተለወጡ በከፍተኛ ሁኔታ በመመናመን ላይ ይገኛሉ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የደን ሀብት መመናመን በአካባቢ፣ በኢኮኖሚ እና በማኅበረሰብ ላይ እያስከተለ ያለውን ተጽዕኖ ለመግታት ሰፊ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፣ በአለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራት የደን ሀብትን በማልማት እና በመጠበቅ ዙሪያ የተዘጋጁ ስምምነቶችን በመቀበል እንደራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ሀገራችንም የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ስምምነትን ጨምሮ ሌሎች ከደን ሀብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ተቀብላለች፡፡ በዚህ አጭር የፅሁፉ ይዘት ደንና የደን ውጤቶች ምንነትና ጠቀሜታ፣ የተከለከሉ ተግባራትና የሚያስከትሉትን ቅጣት እንመለከታለን፡፡
ደንና የደን ውጤቶች ምንነት
በ2010 ዓ/ም የወጣው የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/10 በአንቀፅ 2(1) መሰረት ደን ማለት በደን መሬት፣ በመንገዶች ዳርቻ፣ ወንዝ ዳርቻ፣ በእርሻና የግጦሽ መሬቶች ውስጥና በዙሪያቸው እንዲሁም በመኖሪያ አካባቢዎችና ፓርኮች ውስጥ በተፈጥሮ የበቀሉ ወይም ተተክለው ወይም በሌላ ዘዴ የለሙ የዛፎችና የዕፅዋቶች እንዲሁም ሌሎች ብዝሀ-ሕይወቶች ክምችት እንደሆነ ትርጉም ሰጥቶታል፡፡
በዚሁ ህግ በአንቀፅ 2(18) መሰረት የደን ውጤት ማለት ማንኛውም ከደን የሚገኝ የእንጨትነት ባህርይ ያለውና የሌለው ምርት እንዲሁም የደን ካርበንን ጨምሮ ማንኛውንም የደን ሥርዓተ-ምህዳራዊ ግልጋሎት የሚያካትት ነው በማለት ተርጉሞታል፡፡ በመሆኑም የደን ውጤት ሲባል የእንጨትነት ባህሪ ካላቸው እንደጣውላ፣ ቅጠላ ቅጠልና አጣናን ጨምሮ የእንጨትነት ባህሪ የሌላቸው እንደከሰል፣ የዛፍ ብስባሾች፣ ፍቅፋቂዎችና የእንጨት ዱቄቶችንም ሊያካትት ይችላል፡፡
ደንና የደን ውጤቶች ጠቀሜታ
የደን ሀብት የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ የደን ዋነኛ ጠቀሜታው የተፈጥሮን ሚዛን በመጠበቅ የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ እንዳይከሰት ማድረጉ ነው፡፡ ደን ዓለማችን በተለያየ ምክንያት የምታመነጨውን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተሰኘውን ጋዝ/አየር በመምጠጥ በምላሹ ህይወት ላላቸው ፍጥረታት ህልውና ጠቃሚ የሆነውን ኦክስጅን የተባለውን ጋዝ/አየር ይሰጠናል፡፡ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተባለው አደገኛ ጋዝ በደኖች ባይመጠጥ ኖሮ የፀሀይ ሙቀት በቀጥታ መጥቶ መሬት ላይ እንዳያርፍ ሀይሉን የመቀነስ አቅም ያለውን ኦዞን የተባውን የጋዝ ንጣፍ የማሳሳት ባህሪ ወይም አቅም ስላለው ኦዞንን በማጥፋት ወይም በከፍተኛ ደረጃ እንዲሳሳ በማድረግ በመሬት ላይ የምንኖር ፍጥረታት የፀሀይን ሙቀት መቋቋም ወደ ማንችልበት ደረጃ እንደርስ ነበር፡፡
ሌላኛው የደን ጥቅም የመሬት ለምነትን እንዲጠበቅ ማድረጉ ነው፡፡ ደኖች በስሮቻቸው የመሬትን አፈር አቅፈው በመያዝ በጎርፍ ተሸርሽሮ እንዳይወሰድ ይረዳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የደኖች ብስባሽ በጊዜ ብዛት ወደ አፈርነት ስለሚለወጥ መሬት በመአድናትና በንጥረ ነገሮች እንድትበለፅግ የራሱን አስዋፅኦ ያበረክታል፡፡ የደን ልማት ላይ በሚገባ የሰሩና በቂ የደን ክምችት ያላቸው አካባቢዎች የዝናብ እጥረት አያጋጥማቸውም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የድርቅ መከሰት ዕድሉ የጠበበ ይሆናል ማለት ነው፡፡ መሬቱ ለም ከሆነና በበቂ ሁኔታ የዝናብ ስርጭት ካለ አርሶ አደር ከመሬቱ ሊያገኝ የሚገባውን የምርት መጠን ያገኛል፡፡ በዚህም የኑሮ ደረጃውንም ለማሻሻል ይረዳዋል ማለት ነው፡፡
በተጨማሪ ደን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ከሀይል ምንጭነት ጀምሮ ለግንባታና ለፋብሪካዎች በግብአትነት ያገልግላል፡፡ ደን እና በውስጡ የሚይዛቸው የብዝሀ ህይወት ስብጥር የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን በመሳብ ወይም ጭስ አልባ ኢንዱስትሪ በመሆን ለስራ ፈጠራና ለውጪ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
የተከለከሉ ድርጊቶች
ከደንና የደን ውጤቶች ጋር በተገናኘ ህበረተሰቡ ሊያከናውናቸው የሚገቡና እንዳይፈፅማቸው የተከለከሉ ድርጊቶች በአዋጅ ቁጥር 1065/2010 ላይ ሰፍረው እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህም መሰረት ህጉ ለአጠቃቀማቸው ገደብ የጣለባቸውና ፈፅሞ ሊነኩም የማይገቡ የደን ዓይነቶችን በዋናነት በሁለት ከፍሎ እንደሚከተለው አስቀምጧቸዋል፡፡
እንዳይቆጠሩ የተከለከሉ ደኖች፡-
እነዚህ የደን ዓይነቶች ‘‘በመጥፋት ላይ የሚገኙ በተፈጥሮ የበቀሉ ሆነው በመንግስት አለያም በማህበረሰብ ይዞታ ስር…’’ የሚገኙ የደን ዓይነቶች ሲሆኑ እንዳይቆረጡ ህጉ ክልከላ አስቀምጦላቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ምናልባትም የደን ዓይነቶቹ ቀድሞውኑ በመጥፋት ስጋት ላይ ያሉ በመሆናቸውና አንዴ ከጠፉ በኋላ ለመተካት የማይቻል ወይም ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ከመሆኑ አንፃር ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም፡፡ የደኖቹን ዓይነት በተመለከተ ማለትም አንድ ዛፍ በመጥፋት አደጋ ላይ መሆን ስላለመሆኑ የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር በመመሪያ በሚወስነው መሰረት ሊሆን እንደሚገባ በአዋጁ አንቀፅ 25/2/ ስር ተመላክቷል፡፡ ይህ ሚኒስቴር መ/ቤት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀፅ 36(17) በኋላም አሁን በሥራ ላይ ባለው የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀፅ 106(37) መሰረት ስልጣን ተግባሩ ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተላልፏል፡፡
በግል ይዞታ የሚገኝ ደን፡-
አንድ ግለሰብ በራሱ ይዞታ ስር እራሱ ያለማው ደን ኖሮት ለመጠቀም ቢፈልግና የደኑ ዓይነት በመጥፋት አደጋ ላይ የሚገኝ ከሆነ ለደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ስልጣን የተሰጠው አካል አረጋግጦ በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት መጠቀም የሚችል መሆኑ ተደንግጓል፡፡
ከግል ይዞታ ውጪ ያለ ደን፡-
ከላይ የተገለፀው ሀሳብ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ሰው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ወይም አግባብነት ካለው የክልል ባለስልጣን የፅሁፍ ፈቃድ ካልተሰጠው፣ ከግል ባለይዞታው ፈቃድ ውጪ ወይም ደኑ በይዞታው ስር የሚገኝ ካልሆነ በስተቀር ከማንኛውም ደን ውስጥ፡-
ሀ. ዛፍ መቁረጥ
ለ. በቋሚነትም ሆነ በጊዝያዊነት በደኑ ውስጥ መስፈር
ሐ. የቤት እንስሳትን ለግጦሽ በደኑ ማሰማራት
መ. አደን ማካሄድ
ሠ. የእንጨት መሰንጠቅያ መጋዞችና ሌሎች ለደን መጨፍጨፍያ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ይዞ በደኑ ውስጥ መገኘት
ረ. በደኑ ውስጥ ቀፎ መስቀል፣ ማር መቁረጥም ሆነ መሰል ድርጊቶችን መፈፀም ክልክል መሆኑን በአዋጁ አንቀፅ 25/4/ ተደንግጓል፡፡
ሌሎች የተከለከሉ ተግባራት፡-
የደን ምልክቶችን ማጥፋት፣ ማበላሸት ወይም ከቦታቸው ማዛወር፣
ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት እሳት በመለኮስም ሆነ በሌላ ሁኔታ በደን ላይ ጉዳት ማድረስ፣
ደንና የደን ልማት መሬት ተብሎ በተከለለ ስፍራ መስፈር፣ የእርሻ ቦታ ማስፋፋት ወይም ማንኛውንም ግንባታ ማካሄድ፣
ያልተፈቀደ የደን ውጤት ማጓጓዝ፣
የደን ባለቤት ሆኖ በደኑ ውስጥ ተባይ፣ ተስፋፊነት ያላቸው አረሞችና በሽታዎች መከሰታቸውን እያወቀ ለሚመለከተው አካል አለማሳወቅ፣
የደን ባለቤት ሆኖ በደኑ ውስጥ ያልተፈቀዱ ዕፅዋትን፣ እንስሳትን ወይም ደቂቅ ነፍሳትን ማስገባት የተከለከሉ ተግባራት ናቸው፡፡
ቅጣት
በህገ ወጥ መንገድ ለማገዶ እንጨት፣ ለከሰል፣ ለጣውላ ውጤቶች መስርያ ወዘተ ደንን የሚጨፈጭፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ለመቀነስ ከማስተማር አና ግንዛቤ ከመስጠት ባለፈ በዚህ ለማይገደቡ ግለሰቦች ክልከላውን ተላልፈው ሲገኙ ለሌላው የህበረተሰብ ክፍልም ማስተማሪያ የሚሆን ቅጣት መስጠቱ ተገቢነት ያለው በመሆኑ አዋጁ ለየጥፋት ዓይነቶቹ ተከታዩን ቅጣት አስቀምጧል፡፡ እኛም አንባብያን በቀላሉ ይረዱት ዘንድ እንደሚከተለው አስቀምጠነዋል፡፡
1 በአዋጁና አዋጁን ለማስፈፀም በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ካልሆነ በስተቀር ከመንግሥት፣ ከማህበረሰብ እና ከግል ደኖችና የደን መሬቶች ዛፎችን ከባለ ይዞታው ፈቃድ ውጭ የቆረጠ ወይም የደን ውጤቶችን የወሰደ፣ ለዚህ ተግባር የተባበረ ወይም በማንኛውም በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ የደን ውጤት ይዞ የተገኘ ወይም የተጠቀመ ማንኛውም ሰው የደን ውጤቱ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ1 እስከ 5 ዓመት ፅኑ እስራት ከ10 ሺ እስከ 20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
2 የደን የወሰን ምልክቶችን ያጠፋ፣ ያበላሸ ወይም ያዛባ ከ1 እስከ 3 ዓመት ፅኑ እስራት ከ10 ሺ እስከ 30 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
3 ሆነ ብሎ እሳት በመለኮስ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ በደን ላይ ጉዳት ያደረሰ ከ10 እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት -
4 ጉዳቱ የደረሰው በቸልተኝነት ከሆነ ከ1 እስከ 2 ዓመት ቀላል እስራት ከ5 እስከ 10 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
5 ደን እና የደን መሬት ተብሎ በተከለለ ስፍራ የሰፈረ ወይም የእርሻ ቦታ ያስፋፋ ወይም ማንኛውንም ግንባታ ያካሄደ ከ2 እስከ 4 ዓመት ፅኑ እስራት ከ10 እስከ 40 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
6 ያልተፈቀደ የደን ውጤት ያጓጓዘ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ቀላል እስራት ከ5 ሺ እስከ 10 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
7 ማንኛውም የደን ባለቤት በደን ውስጥ ተባይ፣ ተስፋፊነት ያላቸው አረሞችና በሽታ መከሰቱን እያወቀ አግባብ ላለው አካል በአፋጣኝ ያላሳወቀ እንደሆነ ከ6 ወር አስከ 1 ዓመት ቀላል እሰራት ከ1 ሺ እስከ 5 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
8 ማንኛውም የደን ባለቤት በደን ውስጥ ያልተፈቀዱ ዕፅዋትን፣ እንስሳትን ወይም ደቂቅ ነፍሳትን ያስገባ እንደሆነ ከ1 እስከ 3 ዓመት ፅኑ እስራት ከ10 ሺ እስከ 30 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
9 ዝርያቸው በመጥፋት ላይ የሚገኙ የዛፍ አይነቶችን በህገወጥ መንገድ ከመንግስት፣ ከማህበራት፣ ከማህበረሰብና ከግል ይዞታ ላይ የቆረጠ፣ ያጓጓዘ፣ ያከማቸና ለሽያጭ ያቀረበ ከ5 እስከ 8 ዓመት ፅኑ እስራት ከ15 ሺ እስከ 20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ
ደን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ብሎም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ያለው በመሆኑ ዜጎች ደን እንዲጠበቅ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ህጉን ማክበር እና በሌሎችም እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይገባል፡፡
በንቃተ ሕግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ጥቅምት 16/2016 (አዲስ ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች፡-
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ነው፡፡ በሀገራችን ግለሰቦች በግል መረጃዎቻቸው ላይ ያላቸውን መብት በዝርዝር የሚደነግግ ሕግ ባለመኖሩ፣ የአገራችንን የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት ዓለማአቀፋዊ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ በመገንባት ፋይዳው ዘርፈ ብዙ በመሆኑ እንደዚሁም የግል ዳታ ጥበቃ ባህልና አሠራርን በማጎልበት ተዋናይ በሆኑ አካላት መብትና ግዴታ የሚደነግግ የሕግ ማዕቀፍ እና የማስፈጸሚያ ሥርዓት በመዘርጋት ውጤታማ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ አስፈላጊነት የታመነበት በመሆኑ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲሆን የአርሶ አደሩን፣ ከፊል አርብቶ አደሩን እና የአርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ እድገት ጋር ለማጣጣም እንዲቻል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሥርዓት መዘርጋት ስለሚገባ፣ የባለመብቶችን የይዞታ ዋስትና ማጠናከር የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ የገጠር መሬት ምዝገባና መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በማደራጀት ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱበትን ስርዓት ማበጀት የሚገባ በመሆኑ፣ የተለያዩ የሀገሪቱን የስነ ምህዳር ቀጠናዎችን ያገናዘበ ዘላቂ የገጠር መሬት አጠቃቀም ስርዓት በመዘርጋት የዛሬው ትውልድ ተጠቃሚነት የመጪውን ትውልድ ጥቅም የማይጎዳ መሆኑን የሚያረጋግጥ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው በልዩ ኢኮኖሚ ዞን ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለዉን የኢንደስትሪ ፓርኮች ሥርዓት ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሥርዓት በማሸጋገር የአገራችንን ኢኮኖሚ እድገት ፍጥነት ማላቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን መርሃ ግብር ቀልጣፋ እና አመቺ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ከባቢ ሁኔታ ለመፍጠር አይነተኛ መሳሪያ መሆኑ ስለታመነበት፣ የሃገራችንን በዓለምአቀፍ የንግድ እሴት ሰንሰለት ተጠቃሚነት ለማጎልበት፣ በቀጠናዊ የንግድ ትስስር ውጤታማ በሆነ መንገድ የመወዳደር አቅማችንን ለማጠናከር እንዲሁም አዋጭ እና ስትራቴጂያዊ በሆኑ አካባቢዎች የሚመሰረቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ልማት አስተዳደር እና ቁጥጥር የሚመራ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት
ሀይማኖት ተቋም አፍርሶ ሆቴል ይሰራ ማላት የክፍለ ዘመኑ የሕግ አተረጓጎም ስህተት ነው።😭
"የእምነት ና ሃይማኖት ተቋማት የሕዝብ ጥቅምን (public interest) ከንግድ ድርጅቶች ባለቀ ደረጃ የያዙ ናቸዉ። አንድን የሃይማኖት ተቋም ለሆቴል ወይም ለማንኛውም የንግድ ድርጅት ማስለቀቅ (expropriate) ህጋዊም ምክንያታዊ አይደለም።
በድሬዳዋ ከተማ መከነየሱስ ቤተክርስቲያን እያደረሰ ያለዉ አስተዳደራዊ በደል በመንግስት በኩል በተቻለ ፍጥነት መታረም ያለበት ነዉ።
ይህ አይነት የዘፈቀደ አስተዳደራዊ እርምጃ ለወደፊትም እንዳይደገም የሚመለከታቸው አካላት አስተማሪ የእርምት ዉሣኔ በመስጠት የተሰጠዉን ዉሣኔ ለሕዝብ ይፋዊ ማድረግም ተገቢ ነዉ።"
G*T የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️
" 62 እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ "
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National G*T) የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።
በዚህም መሠረት ፤ አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።
በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ፤ በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test-NG*T) ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይወሳል።
(ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)
Top 10 African countries with the highest food prices
1. 🇿🇼 Zimbabwe
2. 🇪🇬 Egypt
3. 🇸🇱 Sierra Leone
4. 🇬🇭 Ghana
5. 🇧🇮 Burundi
6. 🇲🇼 Malawi
7. 🇷🇼 Rwanda
8. 🇳🇬 Nigeria
9. 🇪🇹 Ethiopia
10. 🇬🇲 Gambia
Source - Trading Economics, Business Insider Africa.
ማስታወቂያ‼
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኝ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር አመልካቾችን ዛሬ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም መቀበል ጀምሯል፡፡
የአመልካቾች ምዝገባ እስከ አርብ ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እና በተመረጡ ሌሎች ማዕከላት ይከናወናል፡፡
አየር መንገዱ ብዛታቸው ያልተገለጸ በርካታ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት፣ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን፣ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ፣ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ እና ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኤጀንት እንደሚፈልግ ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡
የስልጠና መጠሪያዎች ፦
✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን
(Trainee Aircraft Maintenance Technician)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic)
✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors)
✓ ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኢጀንት (Trainee Customer Service Agent) ናቸው።
አመልካቾች ለምዝገባ ፤ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒው፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ካርድ፣ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት ማረጋገጫ ካርድ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ማሟላት አለባቸው።
አመልካቾች ከተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ውስጥ ማመልከት የሚችሉት በአንዱ ብቻ ነው።
ምዝገባእ ከነሐሴ 15 ጀምሮ እስከ 19/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው የሚቆየው።
የምዝገባ ቦታ፡-
- አዲስ አበባ በኦንላይን (አዲስ አበባ)
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ (አምቦ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ (አርባምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (አሶሳ)
- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ (ባህርዳር)
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ (ደ/ብርሃን)
- ደብረ ማርቆስኦኒቨርሲቲ፣ (ደ/ማርቆስ)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ድሬዳዋ)
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ (ፍቼ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ (ጎንደር)
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀረር ካምፓስ ሀረር)
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ (መቐለ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሚዛን ቴፒ)
- ሮቤ ቲቺንግ ኮሌጅ፣ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ)
ዕድሜ ፣ ቁመት ፣ ክብደትና ሌሎች መረጀዎችን ከላይ በተያያዘው የተቋሙ ይፋዊ ማስታወቂያ ይመልከቱ። https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies?fbclid=IwAR1ZLHg_fw9VhghmXo-oOL9ykrsCmq3vcUISCzYl8QtRPPg5fnW4VW_Yfig
Vacancies Ethiopian Airlines Group would like to invite international qualified candidates in the capacity of Expat Captain B777 position.
በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ህይወት ያጠፉ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ምርመራ ቀጥሏል።
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
በሀድያ ዞን በዱና ወረዳ ሀጌ ደጌ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሰሙኤል አበራ ዶሌ የተባለው ግለሰብ የተለየዩ ንግድ ሥራዎችን የሚሰረሁን ሞች አቶ አባተ ኢቶሬ ደንተሞን ከኦሮሚያ ክልል በአይሱዙ ያመጣሁን የበቆሎ ብር የ613000ሽ ብር ግምት ያለዉን ቦቆሎ ብሩን ነጌ እሳጠለሁ በሚል ተስማምተው ጥር 13/2015 በመጋዘን እንድያራግፍ አድርጎ በነገታው ጥር 14/2015 እንድትመጣ በማለት ይጠራል ፤
በጥር 14/2015 በለንብረቱ ሞች አቶ አባተ የተዋዋለውን ብር ለመቀበል እስክመጠ ድረስ ገደይ ከሁለት ግብረ አበሮቹን ጨምሮ ለመግደል ተመካክሮ ሽጉጥና ስለቶችን በማዘጋጀት ቤቱ ጠብቆ በሰዓቱ የመጣውን ሞች አቶ አባተ እቶሬን ስመጣ አቶ ሳሙኤል የተበለ ግለሰብ እሽ ቤቴን ግበ በማለት ቤቱን አስገብቶ ወንበር ሰጥቶ ከጓደ ብር የሚያመጠ አስመስሎ ሄዶ ሽጉጥ ይዞ መጥቶ በጥይት ጭንቅላቱን ስመታ አልሞት ስል ግብረ አበሮቹ ባዘጋጁት ስለቶች እንድቆርጡ ስጠራቸው ለመግደል 300,000ሺ ለመውሰድ በተስማሙት መሠረት ሁለቱ ወጣቶች በካበድ ጭካኔ የቀኝ እጅንና አንገቱን ለያይተው ስቆርጡ፤
በመቀጠልም ቀሪውን የግራ እጅን ራሱ/አቶ ሳሙኤል አበራ/ በቆንጮራ በመቁረጥ አስክሬኑን ከፋፍለው በኩንታሎች አስገብተው ሽንት ቤት በማስገባት በከባድ ጭካኔ የሰው ነብስ አጥፍቶ ይደብቃሉ።
የሞች ቤተሰብ ዕለተ እሁድ የወጠ ሞች ሰይመለስ ስቀርና ስልኩም ስላልሰራ እስከ ሳሙኤል ቤት ድረስ በመምጣት ተመላልሰው አበተ የት ሄደ? በማለት ሰጠይቁ አቶ ሳሙልመልሶ እኔ ሰው ጭምር በለበት ብሩን ስሰጥ ይዞ የመጣውን የራሱን ሞተር እኔ ዘንድ አስቀምጦ ሀላበ ከተማ እሄዳለሁ በማለት ሄዷል ስል መቆያቱን ህብረተሰቡ ይነገራል ።
ተጠርጣሪዎችም በጥር 16/2015 ህብረተሰቡ በቀረበው ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ተከታትለው ወንጀል ተጠርጣሪዎች ሁለቱ በህግ ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ 3ኛው ግብረአበር በራሱ በ18/05/2015 በፖሊስ እጅ ልሰጥ ችሏል ።
በጥር 16/2015 ተጠሪዎች ቁጥጥር ሥር ከሆኑ በኃላ በሳሙኤል መኖሪያ ቤት እና ግቢ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በደረገው ብርበራ የሞች አስከሬን በተለያዩ ኩንታሎች ተደርጎ በሽንት ቤት መገኘት ተችሏል ።
ተጠሪዎችም በህግ ቁጥጥር ሥር ለይ ከሆኑ በኃላ በፖሊስ እና በፍርድ ቤት ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው በዝርዝር እምነት ቃላቸውን ሰጥቷል ።
በዚሁ መሠረትም አጠቃላይ ህብረተሰቡ በተጠርጣሪዎቹ ተገቢና አስተማሪ ውሳኔ መስጣት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሠላም ግምባታ ወሳኝ መሆኑን እያቀረቡ በመሆኑ የህግ ተቋማትም ተገቢ ውሳኔ እንደሚሰጡ ይጠበቃል ።
የአካባቢው ህብረተሰቡም ጉዳዩን በህግ ውሳኔ እንድሰጥ በተገቢው ሁሉ ከመንግሥት ጎን በመሆን እንድትሰለፉ እና ለሠላም ግምባታ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን ።
ፍትህ ለሁሉም!
የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የወንጀል ተጠያቂነት በኢትዮጵያ
መግቢያ
በሕግ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡፡ እነሱም የተፈጥሮ ሰው እና በሕግ ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው ናቸው፡፡ በሕግ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው ማለት የንግድ ድርጅቶች፣ ማህበራት እና መሰል ሌሎች ድርጅቶችን የሚመለከት ነው፡፡ የተፈጥሮ ሰው ወንጀል ሲሰራ በህግ እንደሚጠየቅ ሁሉ የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበት ሁኔታ በህጉ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ፅሁፍ በሀገራችን ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበትን ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንዳስሳለን፡፡
የድርጅት ምንነት
በሀገራችን የድርጅት የወንጀል ተጠያቂነትን በተመለከተ መነሻ የሆነው የወንጀል ህጉ አንቀፅ 34 ሲሆን ለድንጋጌው አላማ ለድርጅትን ምንነት ትርጓሜ ሰጥቶ እናገኛለን፡፡ በዚህ ድንጋጌ ንኡስ አንቀፅ 4 መሰረት "ድርጅት" ማለት መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ወይም ሕዝባዊም ሆነ ግላዊ መዋቅር ያለው አካል ሲሆን ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለፖለቲካ፣ ለሃይማኖት ወይም ለሌላ ሕጋዊ ዓላማ የተቋቋመንና በመንግስት ዕውቅና ያገኘን ማናቸውንም ማኅበር እንደሚያጠቃልል ደንግጓል፡፡ ሆኖም የመንግስት አስተዳደር አካላት ወይም ተቋማት በህግ ሰውነት የተሰጣቸው ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ ውስጥ በድርጅትነት የሚሸፈኑ አይደሉም፡፡
ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበት ሁኔታ
የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚችለው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 34 በተመለከቱት ሁኔታዎች ነው፡፡
ይኸውም
አንድ የወንጀል ድርጊት በድርጅት ከተፈፀመ አስቀጪ እንደሆነ በህጉ በግልፅ ሲደነገግ እና
ከሀላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የድርጅቱን ጥቅም በህገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ካደረገ ነው፡፡
የድርጅትን የወንጀል ተጠያቂነት ያካተቱ ህጎች
ድርጅት በወንጀል ሊጠየቅ የሚችለው አንድ ወንጀል በድርጅት በተፈፀመ ጊዜ ድርጅቱ በወንጀል ሊጠየቅ እንደሚችል በህጉ በግልፅ ሲደነገግ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግም በሀገራችን በሥራ ላይ ያሉ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎችን ያካተቱ ልዩ ህጎች ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ደንግገዋል፡፡ ለአብነት የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881/2007 በአዋጁ አንቀጽ 5፣ በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 132፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 33፣ በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 18፣ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 17 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥር አዋጅ 1177/2012 አንቀፅ 22(11) ይጠቀሳሉ፡፡
ህጋዊ ሰውነት በተሰጠው ድርጅት ላይ የሚጣል የወንጀል ቅጣት
ድርጅት በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም ድርጅትን እንደተፈጥሮ ሰው ማሰር ስለማይቻል በድርጅት ላይ በዋናነት የሚጣለው ቅጣት በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90(3) የተመለከተው የገንዘብ መቀጮ ነው። ይህ ማለት አንድ ወንጀል በተፈጥሮ ሰው ሲፈፀም በእስራት የሚያስቀጣ ከሆነ እና ወንጀል ፈፃሚው ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ሆኖ ከተገኘ ለእስራቱ ተመጣጣኝ ነው ተብሎ በህጉ በተደነገገው የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ከመቀጮ በተጨማሪ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ድርጅት እንዲታገድ፣ እንዲፈርስ፣ እንዲዘጋ ሊወሰን እንደሚችል ከወንጀል ሕጉ አንቀፅ 34(2) መረዳት ይቻላል፡፡
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 90(3) መሰረት የመንግስት የአስተዳደር አካላትን ሳይጨምር የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል ተካፋይ ሆኖ ሲገኝ የድርጅቱ ሀላፊዎች ወይም ሰራተኞች በየግላቸው መጠየቃቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅቱ ወንጀል ተጠያቂ ተደርጎ
1. እስከ 5 አመት ቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አስር ሺህ ብር
2. እስከ 5 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ሀያ ሺህ ብር
3. እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ሀምሳ ሺህ ብር
4. ከ10 አመት በላይ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር፣ መቀጮ እንዲከፍል ይወሰንበታል፡፡
የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ በመቀጮ ብቻ ሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ደግሞ በድርጅቱ ላይ ሚጣለው ቅጣት የመቀጮውን አምስት እጥፍ እንደሚሆን በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90(4) ተደንግጓል፡፡
ሆኖም ይህ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90 የተደነገገው ቢኖርም በልዩ ህጎች የተለየ ቅጣት ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 18 መሰረት
1. በቀላል እስራት ወይም እስከ 5 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር
2. ከ5 አመት እስከ 15 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከአምስት መቶ ሺህ እሰከ አንድ ሚሊዮን ብር
3. ከ15 እስከ 20 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከአንድ ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር
4. ከ20 አመት በላይ በሆነ እስራት ወይም ሞት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከሁለት ሚሊዮን እስከ ሶስት ሚሊዮን ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
በተመሳሳይ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥር አዋጅ 1177/2012 እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881/2007 ለድርጅት ተፈፃሚ የሚሆን የየራሳቸውን የመቀጮ መጠን ደንግገዋል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በዘመናዊ የህግ ሥርአት የተፈጥሮ ሰው ብቻ ሳይሆን በህግ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅትም የወንጀል ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ማወቅና ድርጅቶችን የወንጀል ተጠያቂ ከሚያደርጉ የወንጀል ተግባራት መታቀብ ያስፈልጋል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ