የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት /Ethiopian Reformed Congres/

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት /Ethiopian Reformed Congres/

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት /Ethiopian Reformed Congres/, Political organisation, .

20/06/2022

ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ አስመልክቶ ከኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ፦
በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች በንጹሃን ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ሞት የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያወግዛል ። ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የሀሳብ ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እንድያደርጉ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል ።
ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ከዚህ በታች ያቀረበውን የሰላምና የጸጥታ አማራጭ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች እንድደግፉት ፣ እንድቀበሉትና ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉት የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ጥሪውን ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ለኢትዮጵያ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ያቀርባል።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት የሰላም ፕሮጀክቶች
Ethiopian Reformed Congress Peace and Security Projects
1. ውይይት ማስፋፋት / Promoting dialogue/
2. ፀጥታና ደህንነት ማስፋፋት/ Promoting security/
3. የተረጋጋ መዋቅር ማስፋፋት/ Promoting structural stability/
በተጨማሪ በሚከተሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ግጭትን ለመከላከልና ሰላምን ለማስፈን ይረዳል ፡ በድህነት ማጥፋት ፣ በዴሞክራሲ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ በሰብዓዊ መብት መከበር ፣ በእኩልነት ፣ መገናኛ ብዙሃን መሻሻል ፣ ሙስና እና ኤችአይቪ መከላከል ላይ መስራት ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
በጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ሰኔ 2014 አ.ም

20/06/2022

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት የሰላም ፕሮጀክቶች
Ethiopian Reformed Congress Peace and Security Projects
1. ውይይት ማስፋፋት / Promoting dialogue/
2. ፀጥታና ደህንነት ማስፋፋት/ Promoting security/
3. የተረጋጋ መዋቅር ማስፋፋት/ Promoting structural stability/
በተጨማሪ በሚከተሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ግጭትን ለመከላከልና ሰላምን ለማስፈን ይረዳል ፡ በድህነት ማጥፋት ፣ በዴሞክራሲ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ በሰብዓዊ መብት መከበር ፣ በእኩልነት ፣ መገናኛ ብዙሃን መሻሻል ፣ ሙስና እና ኤችአይቪ መከላከል ላይ መስራት ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
በጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ሰኔ 2014 አ.ም

20/06/2022

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመዘዋወር ላይ የሚገኘውን እና በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ በማድረግ በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ተመልክቶ ሰዎችን በጅምላ በጥይት ደብድቦ የመግደልን ድርጊት ወይም ተግባር አውግዟል ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኢሰመኮ ባወጣው ርፖርት መሰረት በታህሳስ ወር 2014 አ.ም የተፈፀመ ነው የተባለውን ሰዎችን በጅምላ በጥይት ደብድቦ የመግደልን ድርጊት የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያወግዛል ።
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ግዚያት በማንኛውም አካል በንጹሃን ላይ ከፍርድ ዉጭ የሚደረገውንም ግድያ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያወግዛል ።
ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ከዚህ በታች ያቀረበውን የሰላምና የጸጥታ አማራጭ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ህዝብና የኢትዮጵያ መንግስት እንድደግፈው ፣ እንድቀበለውና ተቀብሎ ተግባራዊ እንዲያደርገው የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ጥሪውን ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያቀርባል።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት የሰላም ፕሮጀክቶች
Ethiopian Reformed Congress Peace and Security Projects
1. ውይይት ማስፋፋት / Promoting dialogue/
2. ፀጥታና ደህንነት ማስፋፋት/ Promoting security/
3. የተረጋጋ መዋቅር ማስፋፋት/ Promoting structural stability/
በተጨማሪ በሚከተሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ግጭትን ለመከላከልና ሰላምን ለማስፈን ይረዳል ፡ በድህነት ማጥፋት ፣ በዴሞክራሲ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ በሰብዓዊ መብት መከበር ፣ በእኩልነት ፣ መገናኛ ብዙሃን መሻሻል ፣ ሙስና እና ኤችአይቪ መከላከል ላይ መስራት ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
በጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ሰኔ 2014 አ.ም

20/06/2022

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት የሰላም ፕሮጀክቶች
Ethiopian Reformed Congress Peace and Security Projects
1. ውይይት ማስፋፋት / Promoting dialogue/
2. ፀጥታና ደህንነት ማስፋፋት/ Promoting security/
3. የተረጋጋ መዋቅር ማስፋፋት/ Promoting structural stability/
በጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ህዳር 2014 አ.ም

20/06/2022

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመዘዋወር ላይ የሚገኘውን እና በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ በማድረግ በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ተመልክቶ ሰዎችን በጅምላ በጥይት ደብድቦ የመግደልን ድርጊት ወይም ተግባር አውግዟል ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኢሰመኮ ባወጣው ርፖርት መሰረት በታህሳስ ወር 2014 አ.ም የተፈፀመ ነው የተባለውን ሰዎችን በጅምላ በጥይት ደብድቦ የመግደልን ድርጊት የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያወግዛል ።
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ግዚያት በማንኛውም አካል በንጹሃን ላይ ከፍርድ ዉጭ የሚደረገውንም ግድያ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያወግዛል ።
ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ድህነትና የዴሞክራሲ እጦት በመሆኑ ፡ ኢትዮጵያውያን ከመከፋፈል አንድ በመሆን ድህነትን በማሸነፍና የዴሞክራሲ ስርአተ ግንባታ ላይ በሰላማዊ መንገድ በትኩረት እንድሰሩ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ያሳስባል ። የኢትዮጵያ መንግስትም ድህነትን በማጥፋትና በዴሞክራሲ ስርአቴ ግንባታ ላይ በትኩረት እንድሰራ የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ጥሪውን ያቀርባል ወይም ያሳስባል ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ሰኔ 2014 አ.ም

21/05/2022

ኃላፊነት ለማህበረሰቡ- ለማህበረሰቡ ኀላፊነት አለበት ፡ በተለይም አባሉ ዜጋየመንግስት አካል እና የህዝብ አንድ ክፍል በሆነበት ያሉበት ኃላፍነቶች ግልጽ ናቸው ።
1 በስልጣን ላይ ያሉትን የማክበር ኀላፊነት አለበት ።
2 ለሕግና ለባለስልጣን የመታዘዝ ኃላፊነት አለበት ።
3 ግብር ወይም ቀረጦችን የመክፈል ኃላፊነት አለበት ።
4 ፍትህና ምህረትን በተግባር ማስፈን ፣ ተቀጣሪዎችን በትክክል ማስተዳደር ፣ ድሆችን ፣ ስደተኞችን ፣ የተጨቆኑትን ፣ ደካሞችን ( ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን) ከችግራቸው ለማላቀቅ መስራት ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 29
ጥበቡ ዳንኤል

14/05/2022

ፖለቲካ ለእኔ የተራበውን መመገብ ነው ። ፖለቲካ ለእኔ የታረዘውን ማልበስ ነው ። ፖለቲካ ለእኔ መኖሪያ ቤት ላጣው መኖሪያ ቤት መገንባት ነው ። ፖለቲካ ለእኔ ንጹህ ዉሃ ለሚፈልጉት ንጹህ ዉሃ ማቅረብ ነው ። ፖለቲካ ለእኔ ስራ ላጡት ስራ መፍጠር ነው ። ፖለቲካ ለእኔ መንገድ ላላገኙት ህብረተሰብ መንገድ መዘርጋት ነው ።
ጥበቡ ዳንኤል
ግንቦት 2014 አ.ም

12/05/2022

መልካም አስተዳደር ሰላምን ለማስፈን አስፈላጊ ነገር ነው ።
መልካም አስተዳደር ለማሰፈን፦
የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር
የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል
የህግ የበላይነት ማስፈን
ሙስናን መዋጋት ያስፈልጋል ።
ጥበቡ ዳንኤል
ግንቦት 2014 አ.ም

09/05/2022

ሳይንስና ተክኖሎጂ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን የተፈጥሮ አደጋ ፣ ህመም ፣ ስቃይ ፣ ድህነት ምንጩን በማወቅና መብትሄ በመሻት ረገድ የሚሰራ ልሆን ይገባል ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 73, ንዑስ አንቀጽ 2
ጥበቡ ዳንኤል

09/05/2022

የሳይንስና ተክኖሎጂ አላማ ድህነትንና በሽታን ማስወገድ መሆን አለበት ።
ጥበቡ ዳንኤል

01/05/2022

ምርጫው የህዝብ ነው ። ዉሳኔውም የህዝብ ነው ። ህዝብ የፈለገውን መምረጥና መወሰን ይችላል ። ህዝብ ከምመርጠውና ከምወስነው የትኛውም ምርጫና ውሳኔ ጋር አብሮ ተጠያቂነት አለበት ።
ጥበቡ ዳንኤል
ሚያዝያ 2014 አ.ም

19/04/2022

ኃላፊነት ለባለንጀሮቹ ወይም ለወገኖቹ- ለባለንጀሮቹ ወይም ለወገኖቹ ኃላፊነት አለበት ፡ ይህም ፦
1 የተራበውን ከመመገብ ቸል ማለት ፣ የታረዘውን አለማልበስና የተጨቆነውን አለመንከባከብ ከባድ ቅጣት የሚያስከትል ነው ።
2 ስለዚህ ለሰዎች ህይወት ወይም ጤና ጠንቅ የሆኑ የተፈጥሮ አደጋዎችን እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመቋቋም የተቻለንን ማድረግ ኃላፍነታችን ነው ።
3 ላስወግደው የምችለውን የሰዎችን ችግር ችላ ማለት ምግባራዊ ቸልተኝነት ነው ያስጠይቃል ።
4 ቸልተኝነት አንድ ድርጊት ወይም ቃል ከጉዳት የሚያድን ሆኖ ሳለ ምንም አለማድረግ ወይም አለመናገር ነው ።
5 በቸልተኝነት ምክንያት የምደርሰው ውድቀት ገደብ የለሽ ነው ።
6 ከዚህ የተነሳ ንቁዎችና ርኁሩሖች ወይም የሰዎች ቸግር የምገባን እንድንሆን ይገባል ።

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 28
ጥበቡ ዳንኤል

14/04/2022

ጤና
1 ጤናቸው ( የአካል ፣ የአዕምሮ ፣ የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የማህበራዊ ጤናቸው) አደጋ ላይ የሆኑ ዘጎች የጤና አገልግሎትን በሚያገኙበት ሁኔታ መስራት ።
2 ዘጎች ለሚደረገው የጤና አገልግሎት ድጋፍ በፍላጎትና በምርጫ ማድረግ ይችላሉ ።
3 በአደገኛ ማህበራዊ ሱስ ውስጥ ላሉት አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት መስጠት ።
4 በአደገኛ ማህበራዊ ሱስ ውስጥ ያሉትን በጤና አገልግሎት ውስጥ ማሳተፍ ።
5 የተመጣጠነ አመጋገብ ዙሪያ መሰራት ።
6 በግልና በአካባቢ ንጽህና ላይ በትኩረት መስራት ።
7 ተላላፊ በሽታዎችን በመቅረፍና በማስወገድ ዙሪያ መስራት ።
8 የእንዱስትሪ በሽታን በማስወገድና በመቅረፍ ዙሪያ መስራት ።
9 የዘሬ መል በሽታን በመቅረፍና በማስወገድ ዙርያ መስራት ።
10 የሰው ልጆች ጤንነት በተመለከተ ከተለያዩ አካላት ጋር መስራት ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 58
ጥበቡ ዳንኤል

09/04/2022

ትምህርት
1 ተማሪዎች ትምህርት የመማር መብታቸው የተጠበቀ ነው ።
2 ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ወይም ተቋም እንዳይባረሩ መስራት ።
3 ተማሪዎች ለምያጠፉት ጥፋት ካሳ በመካስ ይለውጣሉ ።
4 ተማሪዎች በትምህርት መማር ውስጥ እንዳይወድቁ ወይም ወደ ኀሏ እንዳይቀሩ መስራት ።
5 የተማሪዎች እውቀት ደረጃ በተለያዩ ሁኔታዎች ወይም መንገዶች ይመዘናል ።
6 ተማሪዎች ያላመኑበትን ትምህርት ለሎች ተማሪዎችን በማይጎዳ መልኩ አለመማር ይችላሉ ።
7 የተማሪዎች ውጤት ለጥናትና ምርምር ይውላል ።
8 ተማሪዎች ትምህርት ባጠናቀቁ ጊዜ የፈለጉትን ስራ ባገኙት እውቀት ይሰራሉ ።
9 ከትምህርት የራቁትን ወደ ትምህርት ማቅረብ ።
10 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የተማሪዎችን ሰብአዊነት በመገንባትና አዕምሮአቸውን ለሚቀጥለው ትምህርት በማዘጋጀት በኩል እንድሰጥ መስራት ።
11 በሁለተኛ ደረጃ የምሰጠው ትምህርት ስራ ተኮር መሆን አለበት ።
12 የከፍተኛ ደረጃ ወይም የከፍተኛ ተቋም ትምህርት የስራ ትምህርት ሀገር አቀፋዊና አለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 57
ጥበቡ ዳንኤል

02/04/2022

በቂ ምግብ ፣ በቅ መጠለያና በቅ ልብስ ያላገኙ ህዝቦች ባሉበት ሀገር ውስጥ ለሰው ልጆች ሞት ፣ ለረሃብ ፣ ከመኖሪያ ቤት ለመፈናቀልና ለእርዛት ምንጭና ምክንያት የሆነውን ጦርነትን መምረጥና ወደ ጦርነት መግባት ትልቅ ስህተት ነው ። ከባለፉት ስህተቶች መማር አለብን ።
ጥበቡ ዳንኤል
መጋቢት 2014 አ.ም

02/04/2022
01/04/2022

ድሃውን ህዝብ የሚበዘብዝ ፣ የሚጮቅን ፣ የሚዘርፍና ድሃውን ህዝብ ተጠቃሚ የማያደርግ የትኛውም ፖሊሲ ፣ ስትራቴጂ ፣ እቅድና ፕሮግራም ልማት ሳይሆን ጥፋት ፣ ውድመትና ወንጀል ነው ። ከእንደዚህ አይነት ተግባር ራሳችንን መጠበቅ አለብን ።
ጥበቡ ዳንኤል
መጋቢት 2014 አ.ም

26/03/2022

በሀገር ግንባታ ፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ፣ ድህነትን በማሸነፍ ፣ የሰው ልጆችን ኑሮ ማሻሻል ውስጥ ፣ ፍትህና ምህረትን በማሰፈን ውስጥ የሰው ልጆች ወይም ዘጎች አንድ መሆን ፣ መደጋገፍ ፣ እጅ ለእጅ መያያዝ ፣ በጋራ መስራትን ይጠይቃል ።
ጥበቡ ዳንኤል

25/03/2022

የህዝብ ስራ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ
1 የስራ ፈጠራ አላማ
ሀ/ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለማስመዝገብ ።
ለ/ ንቁና የሚያስተጋባ ህብረተሰብ ለመፍጠር ።
ሐ/ ጠንካራ ቤተሰብን ለመገንባት ።
2 የስራ ፈጠራ መንገዶች
ሀ/ ማህበረሰብ ተኮር የስራ ማሰልጠኛ ኘሮግራም ።
ለ/ የስራ ሽግግር ኘሮግራም ።
ሐ/ የብዝነስ አማካርነት አገልግሎት ።

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 86
ጥበቡ ዳንኤል

25/03/2022

የህዝብ ስራ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ
1 የስራ ፈጠራ አላማ
ሀ/ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለማስመዝገብ ።
ለ/ ንቁና የሚያስተጋባ ህብረተሰብ ለመፍጠር ።
ሐ/ ጠንካራ ቤተሰብን ለመገንባት ።
2 የስራ ፈጠራ መንገዶች
ሀ/ ማህበረሰብ ተኮር የስራ ማሰልጠኛ ኘሮግራም ።
ለ/ የስራ ሽግግር ኘሮግራም ።
ሐ/ የብዝነስ አማካርነት አገልግሎት ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 86
ጥበቡ ዳንኤል

24/03/2022

የማህበረሰቡን ፍላጎቶች ማለትም ፦ አደንዛዥ ዕፅ ፣ወንጀል ፣ የቆሸሹ መኖርያዎችን ፣ ድህነት ፣ ስደተኞች ፣ ወስባው ጽሑፎች ፣ ዘረኝነት ፣ የቤተሰብ ህይወት ፣ ስራ አጥነት ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር ፣ በሽታ ፣ ትክክለኛ ያልሆነ ቀረጥ ፣ አድልዎ እና ብልሹ ፖለቲካ የመሳሰሉትን ማጥናት አለበት ።
ግልጽ የሆኑ እውነተኞች ምንድናቸው?
ስለእነዚህ ችግሮች ምን ማድረግ ይኖርብናል ? መቼና እንደት እንጀምር?
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ ምዕራፍ ሶስት - የአባላት የግለሰብ ምና , አንቀጽ 29,ንዑስ አንቀጽ 6
ጥበቡ ዳንኤል

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት/ Ethiopian Reformed Congress/ 23/03/2022

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ተግባራት
1. ፖሊሲዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ
ሀገርቱ የምትተዳደርበትን ወይም የምትመራበትን ህዝባዊ ፖሊሲዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ ።
2. በምርጫ መወዳደር
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፖሊሲዎችን በማስተዋወቅና በማስፋት ለስልጣን በምርጫ መወዳደር ።
3. ሀገርቱን ማስተዳደር
በስልጣን ላይ ሆኖ ሀገርቱን እንደ መንግስት ማስተዳደር እና መምራት ። መንግስት ውስጥ ሆኖ ያዘጋጃቸውን ፖሊሲዎችን መፈጸም ።
ተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ አማራጭ ፖሊሲዎችን በማቅረብና በማሰማት የመንግስት ተጠያቂነትን ማስፈን ። ተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ ላዘጋጃቸው ፖሊሲዎች መሟገት ወይም ተሟጋች መሆን ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

t.me/EthiopianReformedCongress
ህዳር 2014 አ.ም

የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት/ Ethiopian Reformed Congress/ You can view and join right away.

21/03/2022

መንግስት የሚያዘጋጃቸውና የሚፈጽማቸው ፖሊሲዎች ፣ ስትራቴጂዎች ፣ ፕሮግራሞችና እቅዶች ድሀውን ህብረተሰብ ከድህነት የሚያወጣ እና የድሆችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽልና ድሆችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን አለበት እንጂ ሀብታሞችን የበለጠ ባለሀብት የሚያደርግ ብቻ መሆን የለበትም ።
ድህነትን በማሸነፍ ዙሪያ የድሆች መሳተፍ ወይም ተሳታፊነት ወሳኝ ምና ይጫወታል ።
ጥበቡ ዳንኤል
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
መጋቢት 2014 አ.ም

19/03/2022

ማንኛውም ሰው ዘሩ ፣ ሃይማኖቱ ፣ የፍቱ ቀለም ፣ ባህሉ ፣ መደቡ ፣ ጾታዊ ፣ ወይም እድሜው ምንም ሆነ ምን የተፈጥሮ ክብር አለው ፡ ልከበርና አገልግሎት ልያገኝ ይገባል ፡ መበዝበዝ የለበትም ።
የኢትዮጵያውያን ተሃድሶ ምክር ቤት መተዳደሪያ ሰነድ አንቀጽ 2
ጥበቡ ዳንኤል

Website