Ewawa Tube
important and valuable information for all
20/03/2023
"የሰው ልጅ መኖርን ብቻ በሌጣው አይሻም። የሚኖርለት የሕይወት ፍቺ ይፈልጋል፤ እንዲያ ካልሆነ በምድር ላይ ከመቆየት ይልቅ እራሱን በራሱ ቢያጠፋ ይመርጣል ይላል ዶስቶቭስኪ። 115/6
፧
"ሰው እና እንሰሳት የሚለዩበትን ነጥቦች በዝርዝር ማተት አንዱ የፍልስፍና ትምህርት ዘርፍ ነው። እንሰሳት ቀጥተኛ የተፈጥሮ ጥገኞች ሲሆኑ የሰው ልጅ ግን ከተፈጥሮ ተገኝቶ ተፈጥሮን የራሱ ግኝት ለማድረግ የሚጥር እንግዳ ፍጡር ነው።" 26
፧
"የሰው ጆሮ ካየኸው ጥያቄ ምልክት ነው። ለዚህኮ ነው ሲጠይቅ ኖሮ ሲጠይቅ ሞቶ እንደገና ገነትን ከሕይወት በኋላ የሚጠይቀው…" 123
፧
"ማሸነፍ ውስጥ መሸነፍ፣ መሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ እንዳለ ገባኝ። የትኛውም የድል በዓል ጀርባው የሽንፈት ንክኪ አለው።" 24
፧
"ማፍቀር እራሱ ጥቅም ነው። በማፍቀር መናወዝ መቼም የትም የማይገኝ ስሜት ጋር ያስተዋውቃል። በአንፃሩ ደግሞ ማፍቀር አለመቻል ፀፀት ነው። በሰው ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ያስገባል።" 120
•
"ሐሰተኛው በእምነት ሥም" በዓለማየሁ ገላጋይ
14/02/2023