Ethio ጤና እና ጠቅላላ ዕዉቀት

Ethio ጤና እና ጠቅላላ ዕዉቀት

health for all

19/08/2023

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን ፀደቀ
**********
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው።

በዚህም መሠረት:-

የም ዞን

ምስራቅ ጉራጌ ዞን

ጠምባሮ ልዩ ወረዳ

ቀቤና ልዩ ወረዳ

ማረቆ ልዩ ወረዳ

ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡

13/12/2015

Photos from South Ethiopia Region - ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል's post 19/08/2023
25/03/2022

ሃንግኦቨር
************
ሃንግኦቨር አንድ ሰዉ ከመጠን ያለፈ መጠጥ(አልኮል) ከወሰደ በኃላ የሚከሰት ጥሩ ያልሆነ ስሜት ነዉ፡፡
አንድ ሰዉ ምን ያህል መጠን አልኮል ቢወስድ ሃንግኦቨር እንደሚከሰት እና እንደማይከሰት መናገር ቢያዳግትም ባጠቃላይ ግን ብዙ መጠጥ በወሰዱ ቁጥር ሃንግኦቨር በሚቀጥለዉ ቀን ሊከሰት እንደሚችል መናገር ይችላል፡፡
ምንም ያህል ጥሩ ስሜት ባይፈጥርም ሃንግኦቨር በ24 ሰዓታት ዉስጥ ስሜቱ ይጠፋል፡፡
የሃንግኦቨር ምልክቶች የሚጀምሩት በደም ዉስጥ ያለዉ የአልኮል መጠን በጣም ሲቀንስ ወይም ወደ ዜሮ ሲጠጋ ሲሆን እንደተወሰደዉ የአልኮል መጠንና አይነት የሚከተሉት ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡-
 የሰዉነት ድካም
 የራስና የጡንቻዎች ህመም
 የዉሃ ጥማት
 ማቅለሽለሽ፣ትዉከት ወይም የሆድ ህመም
 እልቅልፍ ማጣት ወይም የእንቅልፍ ስሜት መቀነስ
 በብርሃንና ድምፅ በቀላሉ መረበሽ
 የማዞር ስሜት፣የቤት ክፍሎች በእርሶ ዙርያ የመዞር ስሜት
 የልብ ትርታ መጨመር
 የአይን መቅላት
 የሰዉነት መንቀጥቀት
 አትኩሮት ማነስ
 የስሜት መዋዠቅ
 ድብርት፣መቅበጥበጥ፣ጭንቀት
መጠጥ ከመጠን በላይ የጠጣ ሰዉ ወደ ጤና ተቋም መወሰድ ያለበት መቼ ነዉ?
• የመዘባረቅ ወይም እራስን የመሳት ምልክቶች ካሉ (stupor or confusion)
• የማያቋርጥ ትዉከት ካለዉ
• አተነፋፈሱ ከተለወጠ (ትንፋሹ በደቂቃ ከ8 በታች ከሆነ)
• የአተነፋፈስ ስርዓቱ የተዛባ ከሆነ (irregular breathing)
• የቆዳዉ ቀለም እየነጣ ከመጣ ወይም
• የሰዉነቱ ሙቀቱ ከመጠን በታች ከቀነሰ
• ሙሉ በሙሉ እራሱን የሳተ ከሆነ (Coma)
ለሃንግኦቨር መከሰት ምክንያት ናቸዉ ተብለዉ ከሚወሰዱት ዉስጥ ጥቂቶቹ
• አልኮል ሰዉነታችንን ብዙ ሽንት እንዲያመርት ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለፈሳሽ እጥረት መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡
• አልኮል የራሳችን የበሽታ መከላከያ ዘዴን በማነሳሳት ሰዉነታችን እንዲቆጣ ያደርጋል- ይህ ለመርሳት፣የምግብ ፍላጎት መቀነስና ትኩረት ማጣት ምክንያት ይሆናል፡፡
• አልኮል በደም ዉስጥ ያለዉን ስኳር በጣም እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ይህ ለሰዉነት መንቀጥቀጥ፣ስሜት መዋዠቅና ድካም ያጋልጠናል፡፡
• አልኮል የጨጓራችንን የዉስጠኛዉ ክፍል እንዲቆጣና የጨጓራ አሲድ መመረት እንዲጨምር ያደርጋል--ይህ ደግሞ ለማቅለሽለሽ፣ትዉከትና የሄድ ህመም መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡
• አልኮል የደም ስሮቻችን እንዲሰፉ ስለሚያደርግ ለራስ ምታት መከሰት መንስኤ ይሆናል፡፡
ሃንግኦቨር እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች ዉስጥ
• በባዶ ሆድ መጠጣት፡- የአልኮልን ወደ ሰዉነት የመሰራጨት ሂደትን ያፋጥናል፤
• እንደ ኒኮትን (ሲጋራ ) ያሉ ሌሎች መድሃኒቶችን ከአልኮል ጋር አብሮ መዉሰድ
• ከጠጡ በኃላ በቂ እንቅልፍ ያለማግኘት ወይም ጭራሹኑ ያለመተኛት
• በቤተሰብ ዉስጥ አልኮል በጣም የሚጠጣ ሰዉ ካለ ( family history of alcoholism)
• መልካቸው ጠቆር ያሉ መጠጦች መጠጣት--እነዚህ መጠጦች በዉስጣቸዉ ኮንጅነርስ የሚባለዉን ንጥረነገር በብዛት ይይዛሉ፡፡ እነርሱም ብራንዲ፣የውስኪ ዘሮች፣ተኪላ፣ቢራ እና ቀይ ወይን ይገኙበታል፡፡
ምንም እንኳ ሃንግኦቨር በጊዜ ሂደት እየቀነሰ ቢመጣም የሚተሉትን ምክሮች በመተግበር የደህንነት ስሜት እንዲሰማዎት ማድረግ ይችላሉ
• ፈሳሽ በአግባቡ መዉሰድ፡-የፈሳሽ እጥረትዎን ለመከላከል ዉሃ ወይም የፍራፍሬ ጭማቂ በአግባቡ ይጠቀሙ፤ ነገር ግን ተጨማሪ አልኮል ከመዉሰድ ይቆጠቡ፤ ምክንያቱም ችግሩን ያባብሰዋልና፡፡
• መክሰስ ይጠቀሙ፤ ከዋናዉ አመካገብ ስርዓት መሃል አነስ ያሉ መክሰስ መመገብ፡፡
• የህመም ማስታገሻ መዉሰድ፤ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡፡
• በቂ እንቅልፍ መተኛት፡፡
Share and Like

24/03/2022

ሎሚ ለጤናችን ስለሚያበረክተው ጥቅሞች በአጭሩ እናያለን፡፡
**********
ሎሚ
ሎሚ በብዙሐኑ ቤት ውስት የማይጠፋ ምግቦች ላይ ትንሽ በመጨመር ቃናን የሚለውጥ ፍራፍሬ ነው፡፡ ሰዎች በኮማጣጣነቱ የተነሳ ሎሚን ብቻውን አይጠቀሙም፡፡
ሎሚ አቻ የማይገኝለት የቫይታሚን ሲ ምንጭ ነው፡፡ የቫይታሚን ሲ እጥረት ለተለያዩ የጤና እክሎች ይዳርጋል፡፡
የሎሚ የጤና ጥቅሞች
· በስትሮክ በሽታ (Stroke) የመመታት እድልን ይቀንሳል
· የደም ግፊትን ያስተካክላል
· ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው
· የቆዳን ጤንነት ይጠብቃል
· የአስም በሽታን ለመከላከል ይረዳል
· ሰውነታችን አይረን (Iron) የተባለውን ንጥረ-ነገር እንዲጠቀም ይረዳል
· የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም እጅጉን ይጨምራል
· ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

13/03/2022

ማዲያት
*********
ማዲያት (Melasma) ምንድነው?
ማዲያት አብዛኛውን ግዜ የሚከሰተው በሆርሞኖች መዛባት ምክንያት ነው፤ እነዚህ Progesterone & estrogen የሚባሉ ሆርሞኖች መዛባት ቆዳችን ሰር ያሉትን melanin የተባሉ ለቆዳ ቀለም አስተዋፅዎ የሚያደርጉ ሆርሞኖች ያበዛሉ፡፡ ይህም ለ ማዲያት ያጋልጣል፡፡
አንዳንዴ ለረዥም ሰዓት ለፀሀይ መጋለጥና ጭንቀት እንዲሁም የእንቅርት እጢ ማደግ በተጨማሪም በእርግዝና ሰዓት እንዲሁም ጭንቀትን ድብርት የሚያበዙ ሴቶች ላይ ይስተዋላል፡፡
በቤት ውስጥ ስለሚዘጋጁ የማዲያት ማጥሪያ መድሃኒቶች
እነዚህ የቤት ውስጥ ውህዶች በመድሃኒት ለተጐዳ ቆዳና ለእነዚህ ውህዶች አለርጂክ የሆኑ ሰዎችን አያጠቃልልም
1. ሎሚ፡- Acid & Vitamin C ስላለው ቆሻሻን በማውጣት ቆዳን ይጠግናል
ከ 20 ደቂቃ በላይ ቆዳ ላይ ባይቆይ ይመረጣል
2. ማር፡- ተፈጥሮአዊ ባክቴሪያ መከላከያ አለው
2 ሻይ ማንኪያ ማር + ግማሽ ሎሚ + ለብ ያለ ውሃ = ለ15 ደቂቃ
ግማሽ ሎሚ + ውሃ + እርድ
3. ገብስ + 2 ሻይ ማንኪያ ማር = ለ30 ደቂቃ የተጐዳው ቆዳ ላይ ማሸት
4. Castor oil በጥጥ ነክሮ የተጐዳው ቆዳ ላይ ማሸት
5. ፓፖያ ቆርጦ ለ 15-20 ደቂቃ በሣምንት 2 ጊዜ ማሸት
የተጨመቀ ፓፖያ + 2 የሻይ ማንኪያ ማር ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ከመጣ ቶሎ መታጠብ ወይም ውህዱን ደግሞ አለመጠቀም
6. በተጨማሪ ራስን ከፀሀይ ጨረርና ቆዳን ከሚጐዱ cosmetics ማራቅ::

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

11/03/2022

የስኳር ህመምን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች
*********
የስኳር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ዉስጥ ዛሬም ቢጀምሩት ዘገዩ የማይባሉበት የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡
በብዛት ከሚከሰቱ የስኳር አይነቶች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ ተይፕ (2) መከላከል ትልቅ ነገር ነዉ፡፡ እርስዎ ለስኳር ህመም ተጋላጭ ከሆኑ ለምሳሌ የሰዉነት ክብደትዎ ከፍተኛ ከሆነ ወይም በቤተሰብዎ ዉስጥ የስኳር ህመም ያለበት ሰዉ ካለ የስኳር ህመምን መከላከል ቅድሚያ መስጠት ይገባዎታል፡፡

የስኳር ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ/ከሚመከሩ መንገዶች ዉስጥ ዋናዋናዎቹ
በቂ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡
ተከታታይነት ያለዉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነትን ክብደት ለመቀነስ፣ የደም የስኳር መጠንን ለመቀነስና ለኢንሱሊን ሆርሞን የመስራት አቅም መጨመር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ከሚመከሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ኤሮቢክስና የሬሲስታንስ ትሬንግ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡
የፋይበር/የቃጫነት ይዘታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር፡- ይህን ማድረግ በደምዎ ዉስጥ ያለዉን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለህመሙ ተጋላጭነትዎን እንዲቀንስ ያደርጋል፤ለልብ ህመም ተጋላጭነዎን ይቀንሳል፤ የሰዉነት ክብደትዎን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ የፋይበር መጠን ካለቸዉ ምግቦች ዉስጥ የሚመደቡት አትክልትና ፍራፍሬ፣ባቄላ፣ጥራጥረዎችና ኦቾሎኒ ናቸዉ፡፡
ጥራጥሬዎች/ሆል ግሬይንስ መጠቀም: ምንም እንኳ በምን ዘዴ እንደሆነ ባይታወቅም ጥራጥሬ ምግቦችን ማዘዉተር የደም የስኳር መጠንን በመቆጣጠር የስኳር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ከነዚሀ ምግቦች ዉስጥ የሚመደቡት የተለያዩ ዳቦዎች፣ፓስታና ጥራጥሬዎች ናቸዉ፡፡
ክብደት መቀነስ፡- የሰዉነት ክብደትዎ ከፍተኛ ከሆነ ክብደትዎን መቀነስ የስኳር ህመምን ለመከላከል ትልወቁን ቦታ ይወሰወዳል፡፡ የሚቀንሱት እያንዳንዷ ኪሎ የጤንነትዎ ሁኔታ እንዲሻሻል የማድረግ አቅም አለዉ፡፡ በጥናት እንደታየዉ የሰዉነታቸዉን ክብደት በፊት ከነበረዉ በ7 በመቶ የቀነሱና ተከታታይነት ያለዉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የስኳር እመም ተጋላጭነትን እስከ 60 በመቶ ድረስ የመቀነስ አቅም አለዉ፡፡
ጥናማ አመጋገብን መከተል፡- የስኳር ይዘታቸዉ መጠነኛ የሁኑ ምግቦችን እንዲሁም ጤናማ አመጋገብ ዘዴን በመከተል የስኳር መጠንን መቀነስ ይቻላል፡፡

09/03/2022

የእንቅልፍ አስፈላጊነት

ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ያለው የጤና ጥቅም አጠያያቂ አይደለም፤ እንደውም ከመመገብ እና ከእንቅስቃሴ ማድረግ የማይተናነስ ነው፡፡ በተለያዩ የእለት ተይለት እንቅስቃሴ አንፃር ተፈጥሮአዊው የእንቅልፍ ልምድ ሊያዛባው ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደሚታየው ከሆነ ሰዎች በቂ እንቅልፍ ካለማግኘታችን በላይ ጥሩ የሚባል የእንቅልፍ ጊዜ የለንም፡፡
እንቅልፍ አስፈላጊ ነው?
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ክብደት ከመጨመር ጋር ይያያዛል
አጭር የእንቅልፍ ሰዓት ያላቸው ሰዎች በቂ እንቅልፍ ከሚያገኙት ጋር ሲነፃፀር ክብደታቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ እንደውም አጭር እንቅልፍ ከልክ ላለፈ ውፍረት እንደ አጋላጭ ነገር አስቀምጠዋል፡፡ እንቅልፍ እና ክብደት መጨመር በብዙ ነገሮች ሊያያዝ እንደሚችል ይነገራል፤ እንደ ሆርሞን እና የእንቅስቃሴ ፍላጎት ጋር ይያያዛል፡፡ ሌሎች ጥናቶች ደግሞ ክብደት ለመቀነስ በቂ እንቅልፍ ማግኘትን ይመክራሉ፡፡
በቂ እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ብዙ አይበሉም
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዕንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች ምግብ የመብላት ፍላጎታቸው ከፍተኛ ስለሚሆን ብዙ ይመገባሉ፡፡ የእንቅልፍ መዛባት ለምግብ ፍላጎት መስተካከል የሚረዱ ሆርሞኖችን በማዛባት የምግብ ፍላጎታችንን መቆጣጠር እንዳንችል ያደርገናል፡፡
በቂ እንቅልፍ ማግኘት ውጤታነትን እና አትኩሮትን ይጨምራል
እንቅልፍ የአእምሮ ስራው (እንደ አትኩሮት፣ ማስታውስ፣ መተግበር እና ምርታማነት) እንዲውጣ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ረጅም ሰዓት የሚሰሩ ሰዎች አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ከማግኘታቸው ጋር ተያይዞ በአእምሮ ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ከአልኮል ስካር ጋር ያመሳስሉታል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ በቂ እንቅልፍ ማግኘት ልጆች እና አዋቂዎች ላይ ችግሮችን የመፍታት እንዲሁም የማስታወስ ችሎታቸውን እንደሚያሻሽል ጥንክሮች ያትታሉ፡፡
በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሰውነት አካል ብርታትን ይጨምራል
አንዳንድ ጥናቶች ጥሩ እንቅልፍን ከ ፍጥነት፣ ልክነት፣ ብርታት እና የአእምሮ ጤና ጋር ያያይዙታል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ዝግ ብሎ ከመራምድ፣ ፍጥነት የሌለው እንቅስቃሴ እና የግል ክንውኖች ላይ መቸገር ይስተዋላል፡፡
በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች ለልብ በሽታ እና ለአእምሮ ውስጥ ደም
መፍሰስ ተጋላጭ ናቸው
የምናገኘው የእንቅልፍ ጥራት እና ርዝመት ጤናችን ላይ በብዙ መልኩ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ ለምሳሌ ለተለያዩ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች (እንደ የልብ በሽታ) ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡
እንቅልፍ የደም ውስጥ ስኳር አጠቃቀም ረገድ የስኳር በሽታ የመከሰት
እድልን ይጨምራል
ጥናታዊ ምርምሮች እንዳሳዩት ከሆነ የእንቅልፍ እጦት የሰውነት ሴሎች ለኢንሱሊን ያላቸውን ምላሽ በመቀነስ የደም ውስጥ የስኳር መጠንን እንዲያሻቅብ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በቀን ከ6 ሰዓት በታች የሚተኙ ሰዎች ለአይነት 2 የስኳር በሽታ ይጋለጣሉ፡፡
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ከድብርት ጋር ይያያዛል
የተለያዩ የስነ-ልቦና ችግሮች እንደ ድብርት፣ ራስን ማጥፋት ከእንቅልፍ ማጣት እና የእንቅልፍ ችግሮች ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው፡፡ የድብርት በሽታ ካለባቸው ሰዎች ወደ 90% የሚሆኑት የእንቅልፍ ችግር እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው እንደ ማንኮራፋት፣ እንቅልፍ ማጣት በድብርት የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
እንቅልፍ በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል
ትንሽ እንኳን የእንቅልፍ ሰዓትን መቀነስ የበሽታ የመከላከል አቅምን አጅጉን ይቀንሳል፡፡
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የሰውነት መቆጣትን ይጨምራል
እንቅልፍ የሰውነታችን ሴሎች መቆጣት ጋር ተያይዞ ጉልህ ሚና አለው፤ እንደውም እንቅልፍ ማጣት የማይፈለጉ ንጥረነገሮችን በመጨመር የሴሎችን ጉዳት ያመጣል፡፡
እንቅልፍ ስሜትን እና ከሰዎች ጋር የሚኖርን ግንኙነት ጋር ተፅዕኖ ይኖረዋል
የእንቅልፍ ማጣት ከሰዎች ጋር የሚኖር ግንኙነትን ይቀንሳል፡፡ እንቅልፍ የሚያጡ ሰዎች ራሳቸውን መግለፅ ላይ ይቸገራሉ ሲገፋም የማህበረሰባዊ ኑሯቸው ሲቃወስ ይታያል፡፡
ስለዚህ በቂ እንቅልፍ (በቀን 8 ሰዓት) ማጣት ካሉት የጤና ችግሮች አንጻር ለጤናማ ህይወት ጥሩ እንቅልፍ እናግኝ!!

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

07/03/2022

ከመጠን በላይ ማላብ / Hyperhidrosis /
********************
ላብ ምንድነው?
ላብ ሰውነታችን ራሱን የሚያቀዘቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው፡ ፡ አብዛኛው ይህ ሁኔታ ተፈጥሯዊ እና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ተደጋጋሚ እና የማያቋርጥ ላብ ይታይባቸዋል እና ይህ ሁኔታ በህክምና ቋንቋ ሃይፐርሃይድሮሲስ/Hyperhidrosis/ ይባላል፡፡
ሃይፐርሃይድሮሲስ/ከባድ ላብ/ በላብ ዕጢዎች የሚመረተው ላብ ሰውነት ራሱን ለማቀዝቀዝ ከሚፈልገው በላይ ነው፡፡ ይህ በሽታ በአብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ የዕለት ተዕለት ስራን ከማወኩም በተጨማሪ ከባድ ላብ ማህበራዊ ጭንቀት እና የመሸማቀቅ ስሜት ብሎም ራስን ማግለል ሊያስከትል ይችላል፡፡
ጥሩው ነገር ግን ይህንን ችግር ለማከም የተለያዩ ዘዴዎች መኖራቸው ነው፡፡ ከባድ ላብ እጅግ ከባድ ሲሆን እስከ ቀዶ ጥገና የሚያደርስ ህክምና አለው፡፡ ምንም እንኳን መቼ፣ የት እና ምን ያክል ያልበናል የሚለው በስፋት ቢለያይም አብዛኛው ሰው ከበድ ያለ የጉልበት ስራ ሲሰራ፣ ሞቃታማ ቦታ ሲሆን፣ ድንጋጤ ወይም ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ያልበዋል፡፡ ከባድ ላብ ሃይፐርሃይድሮሲስ ያለበት ሰው የላብ ሁኔታ ግን ከላይ ከተጠቀሰው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡
የከባድ ላብ ዋና ዋና ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መምጣቱ የሚታይ ከሚገባው በላይ የሆነ እና ብብትን የሚያበሰብስ ሲሆን ነው፡፡ ከሚገባው በላይ የሆነ የሚያስጨንቅ የላብ መኖር በተለይም በእግር ስር፣ በብብት፣ በራስ እና በፊት ላይ የሚታይ ሲሆን፣ የቆዳ ማጣበቅ ወይም ከእጅ መዳፍና ከእግር መርገጫ ጠብ ጠብ የሚል ላብ ሲታይ ነው፡፡
ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚለው ስያሜ የሚሰጠውን የተቸጋሪውን የዕለት ተዕለት ስራን የሚያደናቅፍ ከፍተኛ የላብ መጠን/ከባድ ላብ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ክስተት ያለ ምንም በቂ ምክንያት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ይታያል፡፡ ለእነዚህ ሰዎ ች ከባድ ላብ የማህበራዊ ህይወትን ያውክባቸዋል፡፡
እጃቸው ያለማቋረጥ ስለሚረጥብ ስራ መስራትም ሆነ መዝናኛ ቦታ ራሳቸውን ማዝናናት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከሰው ጋር ሲጨባበጡ በእጃቸው ላብ ምክንያት እና ሸሚዛቸው የላብ ቅርፅ ስለሚያሳይ አንዳንዴም ጠረን ስለሚኖረው በዚህ በሚፈጠርባቸው መሸበር ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ፡፡
እንደዚህ ያለ ችግር ያለበት ሰው ከተለመደው በላይ ድንገት ከፍ ያለ ላብ ሲያይ፣ ላብ የዕለት ተዕለት ስራውን ሲያደናቅፍበት፣ እና የሌሊት ላብ ያለ በቂ ምክንያት ሲኖረው ሐኪም ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የብርድ ላብ የታየበት ማንኛውም ሰው ሐኪም ዘንድ መቅረብ አለበት፡፡
በተለይም ደግሞ ሁኔታው ከጭንቅላት ቅል መቅለል እና የደረት ወይም የሆድ ህመም ስሜት ጋር አብሮ ከመጣ የልብ በሽታ፣ የጭንቀት ወይም የሌላ ከፍተኛ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፡፡
የከባድ ላብ ምንጩ ሰውነታችን ሙቀቱን ከሚቆጣጠርበት የቁጥጥር ስርዓት ይመነጫል በተለይ ደግሞ የላብ ዕጢዎች ቆዳችን ሁለት አይነት የላብ ዕጢዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛው ደግሞ አፓክራይን ዕጢዎች ይባላሉ፡፡

ኢክራይን ዕጢዎች በአብዛኛው ሰውነታችን ውስጥ ሲገኙ በቀጥታ አፋቸው ወደ ቆዳ ላይኛው ክፍል ይከፈታል፡፡ አፓክራይን ዕጢዎች ግን የሚገኙት በብዛት ፀጉር በሚሸፍናቸው የቆዳ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የራስ ቅል፣ ብብት እና ጭገር አካባቢ ነው፡፡
የሰውነታችን ሙቀት ሲጨምር አውቶኖሚክ ነርቨስ ሲስተም የተባለው የአዕምሮ ክፍል እነዚህን ዕጢዎች ላብ ወደ ቆዳ የላይኛው ክፍል እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ ላቡም ሰውነታችንን ከቀዘቀዘ በኋላ ይተንና ቆዳችን ይደርቃል፡፡ ይህ ላብ በውስጡ በአብዛኛው ውሃ እና ጨው ይይዛል አልፎ አልፎ ደግሞ ሌሎች ኬሚካሎችም በተጨማሪ ይይዛል፡፡

ከባድ ላብ በአንድ ቦታ የተወሰነ ወይም ጠቅላላ ወይም በርካታ ሰውነታችንን የሚያካትት /generalized hyperhidrosis/ በመባል ይከፋፈላል፡፡ የመዳፍና የእግር ከባድ ላብ በአብዛኛው ቀን ቀን የሚ ከሰት ነው፡፡ አንዳንዴም በብብት አካባቢም ይታያል፡፡ ይህ ላብ ሌሊት በአመዛኝ አይታይም፡፡
በሁለቱም የሰውነታችን ክፍል በእኩል መልኩ ይታያል፡፡ ይህ አይነት ከባድ ላብ ወደ ሃያው የዕድሜ ክልል አካባቢ በአብዛኛው ይጀምራል፡፡ ከሌላ በሽታ ጋር ግንኙነት የሌለውና ራሱን የቻለ ችግር ነው፡፡ ትክክለኛው ምክንያት ወይም መነሻ ገና አይታወቅም፡፡ ነገር ግን በዘር የመምጣት አዝማሚያም ይኖረዋል፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን የሚያጠቃው የከባድ ላብ ችግር አይነት በድንገት የሚጀምር ነው፡፡

በርካታ የሰውነት ክፍልን ያጠቃል፡፡ በአብዛኛው ሌላ ምክንያት አለው፡፡ ለምሳሌ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት፣ የበሽታ ምልክት፣ የማረጥ ምልክት፣ የስኳር መጠን በደም ውስጥ ዝቅ ማለት፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ካንሰር በሽታ፣ የልብ ድካም በሽታ ወይም የአንድ ወይም የሌላ ኢንፌክሽን በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን መድሃኒት በመውሰድ ወይም መንስኤውን በሽታ በማከም ላቡን ያጠፋዋል፡፡

በከባድ ላብ መንስኤነት የሚመጡ በርካታ የአካልና የስነ ልቦና ች ግሮች መካከል የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ በባክቴሪያ ምክንያት የቆዳ እና የቆዳ ፀጉር አካባቢ ኢንፌክሽን በእግር ጣቶች አካባቢ የሚመጡ ኢ ንፌክሽኖች፣ የቆዳ ኪንታሮት /wart/ በሽታ ወይም ኪንታሮት ሲታከም ቶሎ ያለመዳን ችግር፣ በቆዳ ላይ በሙቀት የሚመጡ ሽፍታዎች መብዛት፣ እና ማህበራዊ መገለል ዋናዎቹ ናቸው።
ለአንዳንድ ከባድ ላብ ላላባቸው ሰዎች መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ከፋርማሲ በሚገዛ ላብ መከላከያ ሊቆም ይችላል፡፡ እነዚህ የላብ ማቆሚያ መድሃኒቶች የላብ መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ይህንንም በአልሙኒየም ጨው አማካኝነት ወደ ቆዳ የሚደርሰውን የላብ መጠ ን ይቀይሳል፡፡ ማስታወስ ያለብን ላብ መከላከያ ላብ ሲከላከል ዲኦድራንት ደግሞ የላብን መጥፎ ጠረን ብቻ ነው የሚከላከለው፡፡

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

06/03/2022

ማንኮራፋት / Snoring /
**********
ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ማንኮራፋት አንድ ሰዉ በሚተኛበት ወቅት የጎረነነ ወይም የማይመች ድምፅ የአየር መተላለፊያ ቧንቧ በከፊል መዘጋት በሚኖርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ አንዳንዴ ማንኮራፋት አሳሳቢ የሆነ የዉስጥ ደዌ ችግርን ሊያሳይ ይችላል፡፡
ማንኮራፋት የትዳር አጋርዎን ሊረብሽ የሚችል ሲሆን እስከ ግማሽ በሚደርሱ አዋቂዎች ላይ ችግሩ ሊታይ ይችላል፡፡ ማንኮራፋት በትናጋዎ ዉስጥ ባሉ የላሉ ክፍሎች ዉስጥ የሚተነፍሱት አየር በሚያልፍበት ወቅት እንዲርገበገቡ ስለሚያደርግ ማንኮራፋት እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
ምልክቶች
ማንኮራፋቱ እንዲከሰት እንዳደረጉት ችግሮች የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፤
- በእንቅልፍ ሰዓት የሚረብሽ ድምፅ መኖር
- ቀን ቀን እንቅልፍ መብዛት
- ትኩረት ማጣት
- የጉሮሮ ህመም
- ያልተረጋጋ እንቅልፍ መኖር
- የአየር ማጠር ወይም ትንታ መኖር
- የደም ግፊትና
- ማታ ማታ የደረት ህመም መከሰት
ለማንኮራፋት ለምን ይከሰታል?
· የአፍና ሳይነስ አፈጣጠር፡- ዝቅ ያለና የወፈረ ትናጋ የአየር መተላለፊያን ያጠባል፡፡ በጣም ወፍራም የሆኑ ሰዎች በአየር መተላለፊያ ቱቦዎች(ጉሮሮ ጀርባ) ትርፍ አካል/ tissues ስላለቸዉ የአየር መተላለፊያ ቱቦዉ እንዲጠብ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንጥልዎ ረጅም ከሆነች የአየር መተላለፍን ሊዘጋ ስለሚችል መርገብገቡ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
· አልኮሆል/መጠጥ መጠጣት፡- ከእንቅልፍ በፊት አልኮሆል አብዝተዉ የሚወስዱ ከሆነ ማንኮራፋት እንዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎች እንዲላሉ ስለሚያደርግ ሰዉነታችን በተፈጥሮ የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ የሚከላከልበትን መንገድ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
· የአፍንጫ ችግሮች፡- ለረጅም ጊዜ የአፍንጫ መጠቅጠቅ ችግር ከነበረ ወይም የአፍንጫ ዉስጥ ችግሮች ካሉ ማንኮራፋት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
· በተደጋጋሚ የአተነፋፈስ መቆራረጥ መኖር/ Sleep apnea:- ይህ ዋና መገለጫዉ ካንኮራፉ በኃላ ለተወሰኑ ሰከንዶች መተንፈስ ማቆም ሲኖር ነዉ፡፡ ከዚያን ድንገት አየር አጥሮት ከእንቅልፈዎ በድንገት ይነቃሉ፡፡
ለማንኮራፋት ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
· የሰውነት ክብደት መጨመር:- በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል
· አልኮል መጠጥ ማብዛት፡- የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል
· በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፡- በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ
· ወንድ መሆን
· ጠባብ የአየር በተላለፊያ ያላቸዉ
· በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር
የሚያንኮራፉ ሰዎች
- በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ
- የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል
- የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል
- ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል
- በእንቅለፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል
- የደረት መጨምደድና የደም ግፊት የመምጣት እድል መጨመር
ከማንኮራፋት ጋር ተያይዞ ምን አይነት ችግሮች ሊታዩ ይችላሉ?
- ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት
- ቁጡነት/ብስጩነት መጨመር
- ለነገሮች ትኩረት ማጣት
- የደም ግፊት፣የልብ በሽታ እና ስትሮክ ተጋላጭነት መጨመር
- እንደ ሃይለኝነት፣የመማር ችግርና የመሳሰሉት የባህሪ ለዉጦች መጨመር (በተለይ በህፃናት ላይ)
- የትደር/ፍቅር አጋርዎን እንቅልፍ ማሳጣት እና መረበሽ
- በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ
ማንኮራፋትን ለመከላከል ምን ይመከራል?
· አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ በጀርባዎ መተኛት ምክንያት እና ለስላሳ ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንዳናሰማ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም ሲተኙ የመኝታዎን ራስጌ ከፍ ማድረግ፡፡
· የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡
· የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡ ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡
· የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡
· አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡
· ትራሰዎን የቀይሩ በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡
· ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡
· ናዛል ስትሪፕ መጠቀም
ሐኪሞትን ጋር መቼ ያማክሩ?
- የማንኮራፋቱ ድምፅ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የትዳር/ ፍቅር አጋርዎን የሚረብሽ ከሆነ
- ትንፋሽ እያጠረዎ ወይም በትንታ ምክንያት ከእንቅልፍዎ የሚነቁ ከሆነ
የእነዚህ ነገሮች መከሰት ማንኮራፋቱ እንደ ኦብስትራክቲቭ እስሊፕ አፕኒያ ባሉ አሳሳቢ/ serious በሆኑ የጤና ችግሮች የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡
ህፃናት ማንኮራፋት ካላቸዉ ለህፃናት ህክምና ባለሙያ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡ ኦብስትራክቲቭ እስሊፕ አፕኒያ የሚባለዉ ህፃናትም ላይ ሊታይ የሚችል ሲሆን እንደ ቶንሲል፣ዉፍረትና የአፍንጫ/ጉሮሮ ችግሮች ለችግሩ መከሰት መንስኤ ናቸዉ፡፡

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

05/03/2022

ቡግንጅ ምንድነው?

በጣም ስለተለመደው እና ብዙውን ጊዜ በቤት ውስጥ ስለምናክመው የቆዳ በሽታ - ቡግንጅ ለምን እንደሚመጣ፣ ምልክቶቹ፣ ተጋላጭነት፣ ሀኪሞትን መቼ ማየት እንዳለቦት፣ የመከላከያ መንገዶች እና በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንደምንችል እናወራለን፡፡
ቡግንጅ
ቡግንጅ ከፀጉር ጥቃቅን ቀዳዳዎች እና የቅባት እጢዎች የሚነሳ የቆዳ ኢንፌክሺን ነው፡፡ ሲጀምርም ኢንፌክሺኑ ያለነት የቆዳ ክፍል ይጠቁራል፤ በመቀጠልም ጠጥሮ እባጭ ሊፈጥር ይችላል፡፡
ቡግንጅ የትኛውም የሰውነት ክፍላችን ላይ ሊከሰት ቢችልም ፊት፣ አንገት፣ ብብት፣ ትከሻ እና መቀመጫ ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ እንዲሁም በብዛት አንድ ቦታ ከተከሰተ የከፋ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡
ቡግንጅ በምን ምክንያት ይመጣል?
ብዙውን ጊዜ ስታፊሎኮከስ (Staphylococcus ) የተባለ ባክቴሪያ አማካኝነት ይመጣል፡፡ ይህ ባክቴሪያ በቆዳችን ላይ ሊኖሩ በሚችል ቁስል ወይም በፀጉር ስር ቀዳዳዎች አማካኝነት ወደ ሰውነታችን ይገባል፡፡
ለቡግንጅ እና ተመሳሳይ የቆዳ በሽታዎች ተጋላጭ ማን ነው?
· የስኳር በሽተኛ
· ደካማ በሽታ የመከላከል አቅም ያለው ሰው
· በምግብ እጥረት ህመም የሚሰቃይ
· የሰውነትን ንጽህና በአግባቡ አለመጠበቅ
· ቂዳን ሊያስቆጡ ለሚችሉ ኬሚካሎች መጋለጥ
ምልክቶች
ቡግንጅ መጀመሪያ ጠንካራ፣ ቀይ፣ ከፍተኛ ህመም ያለው እባጭ ሆኖ ይወጣል፡፡ ከቀናት በኋላ ይህ እባጭ ለስለስ በማለት የበለጠ እያደገ ህመሙ ይጨምራል ፡፡ በኋላም ከአናቱ መግል መፍሰስ ይጀምራል፡፡
ከበድ ያለ ኢንፌክሺን ካለ የሚከተሉት ምልክቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ፤
- በዙሪያው ያለ ቆዳ በኢንፌክሺን ስለሚጠቃ ቀይ ሆኖ እብጠት ይኖረዋል እንዲሁም ሲነካ በመሞቅ ከፍተኛ የህመም ስሜትም ይኖራል
- አንድ ቡግንጅ ከወጣ ሌሎች በዙሪያው ይወጣሉ
- ትኩሳት
- በሰውነታችን ውስጠ ያሉ እጢዎች (Lymph Node) ሊያብጡ ይችላሉ
ሃኪሞ ጋር መቼ መሆድ አለቦት?
- ከፍተኛ ትኩሳት ካሎት
- በዙሪያው ያለው ቆዳ ከቀላ ወይም ከጠቆረ
- ከፍተኛ የህመም ስሜት ካለ
- ቡግንጁ ካልፈረጠ
- ሌላ ቡግንጅ ከወጣ
- ተያያዥ የልብ ችግር፣ የስኳር ብሽታ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚቀንስ ማንኛውም ሁኔታ ወይም መድሀኒቶች እና ቡግንጅ ከወጣቦት
በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይቻላል?
· በሙቅ ውሃ የተነከረ ፎጣ በመጠቀም አካባቢውን መሸፈን እና ጠበቅ አድርጎ መያዝ ይመከራል፡፡ ይህም የህመም ስሜቱ እንዲቀንስ እና በቀላሉ መግል እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ መግሉ የሚወጣው ብዙ ጊዜ በ8-10 ባሉት ቀናት ነው፡፡
· መግሉ ወጥቶ እስኪያልቅ ድረስ በአንታይባክቴሪያል ሳሙና በተደጋጋሚ መታጠብ እና በአልኮል ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡ ካስፈለገም የሚቀቡ አንቲባዮቲኮችን በመቀባት በንፁህ ባንዴጅ ማሰር፡፡ ቁስሉ ጨርሶ እስኪድን ድረስ ቦታውን ቢያንስ በቀን ሲስት ጊዜ መታጠብ አለቦት፡፡
· መግሉን ለማፍረጥ መርፌም ሆነ ሹል ነገሮችን መጠቀም ያባብሰዋል፡፡
ቡግንጅን እንዴት እንከላከል?
- ቡግንጅ ከሰው ሰው ስለሚተላለፍ ንክኪ በቀነስ እና ንፅህናን መጠበቅ
- ማንኛውንም የቆዳ ቁስል በአግባቡ ማፅዳት እና ማከም
- ምንጊዜም የሰውነት ንፅህናችን በአግባቡ መጠበቅ
- በተቻለ መጠን ጤናማ መሆን

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

04/03/2022

የሆድ ድርቀት
***********
አንድ ሰዉ ለተከታታይ ሳምንታትና ከዚያ በላይ በቂ ጊዜ ሰገራ መዉጣት የሚያስቸግረዉ ከሆነ ወይም በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ የሚወጣ ከሆነ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት አለዉ ተብሎ ይገለፃል፡፡
ጊዜያዊ የሆነ የሆድ ድርቀት ብዙ ጊዜ የሚከሰት ነገር ነዉ፡፡ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚከሰትበት ወቅት የታማሚዉን የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴ ከማወኩም በላይ ታማሚዉ ሰገራ በሚወጣበት ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ የማስማጥና ሌሎች ምልክቶችም አሉት፡፡
የሆድ ድርቀት ምልክቶች
· በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መዉጣት
· የደረቀ ሰገራ መዉጣት
· ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት ማስማጥ
· ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት አንዳች ነገር ደንዳኔዎትን የዘጋዉ ነገር ያለ ስሜት መሰማት
· ሰገራ ለመዉጣት እርዳታ መፈለግ(በእጅዎ ሆድዎትን መግፋት፣በጣትዎ ሰገራን ለማዉጣት መሞከር)
ለሆድ ድርቀት የሚጋልጡ ነገሮች
· በእድሜ መግፋት
· ሴት መሆን
· በቂ ፈሳሽ ያለመዉሰድ
· በፋይበር( fiber) የበለፀጉ ምግቦችን ያለመጠቀም(አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸዉን ምግቦች ማዘዉተር)
· አነስተኛ ወይም ምንም አይነት የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ
· ለድርቀት ሊያጋልጡ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡-ለምሳሌ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ፣ለስነዓዕምሮ ችግሮች የሚሰጡ(ሴዳቲቭስና ናርኮቲክስ) የመሳሰሉት
የሆድ ድርቀት መንስዔዎች
የሆድ ድርቀት አብዛኛዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ከምግብ መፈጨት በኃላ የሚቀረዉ ቆሻሻ ወይም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ(ጉዞ) በጣም ዘገምተኛ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚከተሉት መንስዔዎች አሉት፡-
1. በትልቁ አንጀት ወይም በደንዳኔ ዉስጥ መዘጋት በሚኖርበት ወቅት
· የፊንጢጣ መቀደድ( A**l fissure)
· የአንጀት መታጠፍ
· የትልቁ አንጀት ካንሰር
· የትልቁ አንጀት ጥበት
· አንጀት ላይ ጭነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሌሎች የሆድ ዉስጥ ካነሰሮች
· የደንዳኔ ካንሰር
· በደንዳኔ ግድግዳ ለይ አድገዉ የሰገራን መተላለፊያ ሊዘጉ የምችሉ ነገሮች(ሬክቶ ሲል)
2. በትልቁ አንጀትና በደንዳኔ አካባቢ ባሉ ነርቮች ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት
· የነርቭ ችግር መኖር በዳንዳኔና ትልቁ አንጀት ጡንቻዎች ላይ መኮማተርን ስለሚያስከስት የሰገራን እንቅስቃሴ ይገድባል፡፡ ይህን ችግር ሊያስከስቱ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ፡
· የህብለ ሰረሰር (Spinal cord) ጉዳት መኖር
· ስትሮክ( Stroke)
· የፓርኪንሰንስ ህመም
· አዉቶኖሚክ ንይሮፓቲይ የሚባል የነርቭ ህመም
· መልትፕል ስክሌሮሲስ የመሳሰሉት
· ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ በሚረዱ ጡንቻዎች ላይ ችግር መከሰት
· ሰገራን ለማስወገድ የዳሌ ጡንቻዎች መለጠጥ ያለመቻል( Inability to relax the pelvic muscles)---አንስመስ
· የዳሌ ጡንቻዎች በደንብ በተቀናጀ መልኩ ያለመለጠጥና ያለመኮማተር-----ዲሲነርጂ
· የዳሌ ጡንቻዎች መልፈስፈስ
3. በሰዉነት ዉስጥ ባሉ ሆርሞኖች ላይ ችግር መከሰት
· ሆርሞኖች በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ ፈሳሽ ተመጣጥኖ እንዲገኝ የሚያደርጉ ሲሆን ይህንን ስርዓት የሚያዛቡ ህመሞች ካሉ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ፡-
· የስኳር ህመም
· የፓራታይሮይድ ዕጢ ችግር(ሃይፐርፓራታይሮይድዝም)
· እርግዝና
· የታይሮይድ ዕጢ ሆርሞኖች ማነስ(ሃይፓታይሮይድዝም)
የሆድ ድርቀት ህክምና
ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚኖርበት ወቅት ከሚመከሩ ነገሮች ዉስጥ የአመጋገብና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ሲሆን ይህም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚቆይበትን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ይህን ማድረግዎ ለዉጥ ካላመጣ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡ የህክምና ባለሙያዎት የሚከተሉትን ነገሮች ሊመክሮት ይችላል፡፡
· የፋይበር አወሳሰዶትን መጨመር እና በቂ ፈሳሽ መዉሰድ፡- ቀስ በቀስ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የጥራጥሬ ዘሮች በብዛት መመገብ
· የአካል እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ይህ የአንጀትን የጡንቻዎችን እንቅስቃሴ ስለሚጨምር ድርቀትን ይከላከላል
· የሰገራ መምጣት ስሜት ባለዎት ጊዜ ሳያሳልፉ መዉጣት
· የሰገራ ማለስለሻ መጠቀም፡- ፋበሮች፣ሰገራ ማለስለሻ መድሃኒቶች፣ሰገራን ሊያላሉ የሚችሉ ነገሮችን መጠቀም( Stool softeners)
· የዳሌ ጡናቻዎች ስልጠና፡- በዚህ ረገድ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ የሚረዱትን ጡንቻዎችን በማላላትና በማጠንከር ማሰልጠን ሰገራን በቀላሉ ለመዉጣት ይረዳል፡፡
· የቀዶ ጥገና፡- በቀዶ ጥገና ሊስተካከሉ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለምሳሌ የፊንጢጣ መቀደድ፣ሬክቶሴሌና የአንጀት ጥበት የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ ሁኔታዎች ሲኖሩ የቀዶ ጥገና ባለሙያን ማማከር ይመከራል፡፡

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

03/03/2022

ደም ማነስ

ደም ማነስ ምንድነው?
ሰውነት ኦክስጂን ለተለያዩ አካላት የሚያደርስ በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሤል ሳኖረው ሲቀር ደም ማነስ ይባላል፡፡ ብዙዎች ላ እንደሚታየው ደም ማነስ ድካም ሲብስም ራስን መሳት ሊያመጣ ይችላል፡፡
ደም ማነስ ብዙ አይነት አለው፡፤ እያንዳንዱ የራሱ ምክንያቶች አሉት፡፡ እንዲሁም ጊዜያዊ ወይም ቋሚ፤ ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ደም ማነስ የሌሎች ለህይወት አስጊ የሆኑ በሽታዎች ምልክትም ሊሆን ስለሚችል ችላ ሊባል አይገባም፡፡
ህክምናው ከመድሐኒት እስከ ደም መስጠት እና ሌሎችም ድረስ ሊሄድ ይችላል፡፡ አመጋገብን ማስተካከል አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶችን ለመከላከል አልፎም ምልክቶቹን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ምልክቶች
እንደየምክንያቱ ደም ማነስ የተለያዩ ምልክቶች ሊኖረው ይችላል፤ አንዳንዴም ምንም ምልክት አያሳይም፡፡ እንዲሁም ቀለል ያለ ወይም መጀመሪያ ላይ ደም ማነስ ምልክት አይኖረውም፤ ቀስ በቀስ ግን ምልክቶቹ እየከፉ ይሄዳሉ፡፡
· ድካም
· አቅም ማጣት
· የቆዳ መንጣት ወይም መገርጣት
· የተዛባ የልብ ምት
· ትንፋሽ ማጠር
· ማዞር ወይም ራስን መሳት
· የደረት ህመም
· የእጅ እና እግር መቀዝቀዝ
· ራስ ምታት
ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?
- ያለምክንያት በጣም የሚደክሞት ከሆነ
- ራሶትን ከሳቱ
ደም ማነስ በምን ምክንያት ይመጣል?
· በአጠቃላይ ደማችን በቂ ቀይ የደም ሴሎች ከሌለው ደም ማነስ ይመጣል፡፡
· ይህም በሚከተሉት አማካኝነት ሊሆን ይችላል፤
· ሰውነት በበቂ መጠን ቀይ የደም ሴል ካላመረተ
· ሰውነት መተካት ከሚችለው በላ ደም ካጣ (ብዙ መድማት)
· ሰውነት ቀይ የደም ሴሎቹን ካጠቃ
ተጋላጭነት
- አስፈላጊ የሆኑ ቫታሚኖች እና ሚነራሎች የሌሉት የአመጋገብ ስርዓት
- የአንጀት በሽታዎች
- የወር አበባ
- እርግዝና
- ለረጅም አመታት አብረው የሚኖሩ በሽታዎች (ካንሰር፣ ስኳር፣ የኩላሊት መድከም)
- በቤተሰብ ደም ማነስ ካለ
- እድሜ (65 እና ከዛ በላይ)
- ሌሎች ተያያዥ ሁኔታዎች (እንደ ኢንፌክሺን፣ አልኮል መጠጣት፣ ለተለያዩ ኬሚካች መጋለጥ፣ አንዳንድ መድሐኒቶች)
በወቅቱ ካልታከመ፤
· ከፍተኛ ድካም
· ከእርግዝና ጋር የተያያዙ ችግሮች
· የልብ ችግር
· ሞት
እንዴት መከላከል ይቻላል?
አብዛኛዎቹን የደም ማነስ አይነቶችን ለመከላከል ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በአመጋገብ ስርዓት (በአይረን እና ቫታሚን እጥረት፣ ) ምክንያት የሚመጡትን ግን መከላከል ይቻላል፡፡
ለዚህም በአይረን፣ ፎሌት፣ ቫይታሚነ ቢ12 እና ቫታሚነ ሲ የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ይመከራል፡፡

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

02/03/2022

የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ምን ያክል አውዳሚ ናቸው?

የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ከፍተኛ ውድመት እንዲያደርሱ ተደርገው ነው የተሰሩት።

ጦር መሳሪያዎቹ የሚያደርሱት የጉዳት መጠን በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረት ይሆናል። እነዚህም፤

የአረሩ መጠን
ፍንዳታው ከምድር በምን ያክል ከፍታ ላይ እንደሚከሰት እና
ፍንዳታው የሚያጋጥምበት የአካባቢ ሁኔታ ናቸው።
ባለሙያዎች አነስተኛ የአረር መጠን ያለው የኒውክሌር ቢሆን እንኳ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳትን ሊያደርስ እንደሚችል ይናገራሉ።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሺማ 146 ሺህ ሰዎችን የደገለው ቦምብ ክብደቱ 15 ኪሎቶን (15 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበር።

ዛሬ ላይ ያሉት የኒውክሌር አረሮች ከ1ሺህ ኪሎ ቶን በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ።

የኒውክሌር ፍንዳታ ሲያጋጥም ከፍተኛ ኃይል ያለው ብርሃን ያወጣል። ፈንዳታው የሚፈጥረው የኃይል ንዝረት በርካታ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኙ ሕንጻዎችን ጨምሮ በዙሪያው የሚያገኘውን ሁሉ እንዳልነበር ያደርጋል።

ከእአአ 1945 ወዲህ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በግጭት ወቅት ጥቅም ላይ ውሎ አያውቅም።

ሩሲያም የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿን የምትጠቀመው በአራት አስገዳጅ ሁኔታዎች ውስጥ መሆኑን የአገሪቱ መመሪያ ያዛል።

የሩሲያ ፌዴሬሽን አልያም አጋሮቿን ለማጥቃት ረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ከተተኮሰ
በሩሲያ ፌዴሬሽን አልያም በአጋሮቿ ላይ ኒውክሌር ጦር ወይም የጅምላ ፍጅት የሚያስከትል መሳሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ
የሩሲያን የኒውክሌር ባለቤትነት የሚገዳደር በቁልፍ የመንግሥት ወይም የጦር ተቋማት ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ እና
የሩሲያ ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ አገሪቱ በውጪ ኃይል ከተጠቃች ሩሲያ የኒውክሌር ኃይሏን ልትጠቀም ትችላለች።

01/03/2022

የአንጀት ካንሰር ምልክቶች

የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የካንሰር በሽታ ቀድሞ መመርመር የተሸለ እንደሆነ ይታወቃል፤ በመሆኑም ለዚሁ እንዲረዳዎት የአንጀት ካንሰር ምልክቶችን እናነሳለን፡፡

#የአንጀት #ካንሰር
አብዛኛዎቹ የአንጀት ካንሰር ምልክቶች የሌሎች ቀለል ያሉ በሽታዎች ለምሳሌ እንደ ኢንፌክሺን፣ ኪንታሮት፣ የአንጀት መቆጣት ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን መሰል ምልክቶችን ካስተዋሉ ወደ ጤና ተቛም መሄድ ይኖርቦታል፡፡
ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው?
· ከቀናት በላይ የቆየ ተቅማጥ ወይም የሰገራ ድርቀት
· ለመፀዳዳት ፈልገው የሚወጣ ነገር ሳኖር ሲቀር
· በፊንጢጣ በኩል ደም ከወጣ
· የሰገራ መጥቆር ወይም ሰገራ ውስጥ ደም ማየት
· የድካም ስሜት
· ክብደት መቀነስ
የአንጀት ካንሰር እነዚህን ምልክቶች የሚያሳየው ግን ካደገ አንዳንዴም ከተሰራጨ በኋላ ነው፡፡ ካንሰሩ በጊዜ ካልተገኘ ለማከም በጣም አዳጋች ስለሚሆን በተለይ በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ በጊዜ መመርመ እጅጉን የተሸለ ይሆናል፡፡ ቀድሞ መመርመር ካንሰሩ ገና ብዙ ሳያድግ እና ሳይሰራጭ ስለሚገኝ ህክምናው የተሻለ ይሆናል፡፡

ለአንጀት ካንሰር ተጋላጭ የሆኑት እነማን ናቸው?
75% የሚሆኑት ተጠቂዎች ምንም አይነት ተጋላጭነት የላቸውም፤ ለዚህም ነው ቛሚ የሆነ የጤና ምርመራ ማድረግ የሚመከረው፡፡ ካንሰሩ ወንዶችንም ሴቶችንመ በእኩል መጠን ያጠቃል፡፡ ነገር ግን እድሜአቸው ከ50 ዓመት በላ የሆኑ ሰዎች ላይ በብዛት ይታያል፡፡
- የዘር ተጋላጭነት (በቤተሰብ ውስጥ ነአንጀት ካንሰር የተያዘ ሰው ካለ)
- የአንጀት መቆጣት በሽታ ካለቦት
- በሌሎች የካንሰር አይነቶች (የጡት ወይም የማህጸን) ተጠቂ ከሆኑ
- የአፍሪካ ወይም የሂስፓኒክ የዘር ግንድ
- እንቅስቃሴ አለማድረግ
- ከልክ ያለፈ ውፍረት
- አመጋገብ (በተለይ በፋብሪካ የተቀነባበ ስጋ)
- ሲጃራ ማጨስ
- ከልክ በላይ አልኮል መጠጣት

ጠቃሚ ትምህርትና መረጃን ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ:: Like & share

28/02/2022

10 የብርቱኳን የጤና ጥቅሞች

#ብርቱኳን
ብርቱኳን አያሌ የጤና ጥቅም የሚሰጥ ፍራፍሬ ነው፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃም ተወዳጅ እና ተፈላጊ ከሆኑት ተርታ የሚሰለፍ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ብርቱኳን ከዘወትር ምግባችን እንደተጨማሪነት ከመወሰዱ በላይ እንደ ዋና ምግብም እንጠቀማለን፡፡ በተለይ የብርቱኳን ጭማቂ ለቁርስነት ተወዳጅ እና ጠቀሜታውም ላቅ ያለ ነው፡፡
ብርቱኳን የመመገብ ጥቅም፤
1. የሰውነትን የቫይታሚን ሲ ክምችት ለመጨመር
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት
3. የቆዳን ጉዳት ለመቀነስ
4. የደም ግፊትን ለመቆጣጠር
5. የደም ውስጥ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ
6. የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ለማስተካከል
7. የሰውነትን አሲድ - ቤዝ መጠንን ለማመጣጠን
8. ለዓይን ጤንነት
9. ድርቀትን ለመከላከል
10.በካንሰር የመያዝ እድልን ለመቀነስ

24/02/2022

ሪህ/ Gout
**************
ሪህ በመገጣጠሚ ላይ በተለይ ደግሞ በእግር ትልቁ ጣት ላይ በድንገት የሚጀምር ከፍተኛ ህመም ስሜት፣እብጠትና መቅላት የሚመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡ሪህ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም ሴቶች ካረጡ በኃላ ለህመሙ ተጋላጭነታቸዉ እየጨመረ ይመጣል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የሪህ የህመም ምልክቶች ብዙዉን ጊዜ ያለማስጠንቀቂያ በድንገት የሚከሰት ሲሆን በብዛት የሚጀምረዉ ማታ ላይ ነዉ፡፡
የህመሙ ምልክቶች
• ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚ ላይ ህመም፡- ምንም እንኳ ሪህ በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ የእግር አዉራ ጣት ላይ ቢሆንም በእግር መዳፍዎ፣በቁርጭምጭሚትዎ፣ በጉልበትዎ፣ በእጅዎ መገጣጠሚያዎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ከጀመረ የመጀመሪያዎቹ ከ4 እስከ 12 ሰዓታት ዉስጥ በጣም ሊባባስ ይችላል፡፡
• ቀጣይነት ያለዉ የህመም/ምቾት ያለመሰማት ስሜት፡- ከፍ ያለዉ ህመም ካለፈ በኃላ የተወሰነ ህመምና ምቾት ያለመሰማት ከቀናት እስከ ሳምንታት ድረስ ሊቀጥል ይችላል፡፡
• የመቆጥቆጥና የመቅላት ስሜት፡- በህመሙ የተጎዳዉ መገጣጠሚያ የማበጥ፣ ሲነካ የማመምና መሞቅ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪ ይኖረዋል፡፡
• እንቅስቃሴ መገደብ፡- ህመሙ እየፀና ሲመጣ መገጣጠሚያዉ መታዘዝ/መንቀሳቀሱን ይቀንሳል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የህመም ምልክቶች ካሎት ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከመጣ በኃላ ህክምና ሳይደረግ በራሱ ጊዜ ከጠፋ ህመሙ እየተባባሰና መገጣጠሚያዉን ስለሚጎዳዉ መታከም ያስፈልጋል፡፡
የህመሙ ምክንያት
ሪህ የሚከሰተዉ ዩሬት ክሪስታል የሚባለዉ ኬሚካል መገጣጠሚያ ዉስጥ ተጠራቅሞ የመቆጥቆጥ ስሜት/inflammation/ እንዲጀምር ወይም እንዲነሳ በማድረግ የህመሙ ምልክቶች እንዲመጣ ያደርጋል፡፡ዩሬት ክሪስታል የሚመጣዉ በደማችን ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን ከሚፈለገዉ መጠን በላይ ከፍ ሲል ነዉ፡፡
ሰዉነታችን ዩሪክ አሲድን ፕዩሪንስ የሚባሉ ኬሚካሎችን በሚሰባብርበት ወቅት የሚመረት ሲሆን ፕዩሪንስ በተፈጥሮ በሰዉነታችን ዉስጥና በተወሰኑ እንደ ስጋና የባህር ምግች ዉስጥ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከፍ ያለ ዬሪክ አሲድ በሰዉነታችን እንዲኖር ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) እና እንደ ፍሩክቶስ ባሉ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች መጠጣት ናቸዉ፡፡
ዩሪክ አሲድ በደምዎ ዉስጥ በመሟሟት ከሰዉነትዎ በኩላሊት አማካይነት እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ ነገርግን ሰዉነታችን ከሚፈለገዉ መጠን በላይ ዩሪክ አሲድን ካመረተ አሊያም ኩላሊትዎ ከሚገባዉ በታች ከሰዉነታችን እያስወገደች ከሆነ የዩሪክ አሲድ መጠን በሰዉነታችን ዉስጥ በመጨመር ዩሬት ክሪስታል በመገጣጠሚያ ዉስጥ እንዲፈጠር በማድረግ የህመም ስሜቶች እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
ተጋላጭነተዎን የሚጨምሩ ነገሮች
በሰዉነትዎ ዉስጥ በጣም ብዙ ዩሪክ አሲድ ካለዎ ሪህ ሊከሰት ይችላል፡፡
በሰዉነትዎ ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንቶች ዉስጥ
• አመጋገብ፡- አመጋገብዎ ዉስጥ ስጋ፣ የባህር ምግችን/seafood/፣ በፍሩክቶስ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች፤ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) ማዘዉተር የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርጉ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን ሊጨምር ይችላል፡፡
• ዉፍረት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላ ከሆነ ሰዉነትዎ ብዙ ዩሪክ አሲድ እንዲያመርት ስለሚያደርግና ኩላሊትዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለሪህ ያጋልጥዎታል፡፡
• የዉስጥ ደዌ ችግሮች፡- የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ ያልታከመ የደም ብዛት፣ ሜታቦሊክ ሲንድረምና የኩላሊት ችግር ካለዎ ለሪህ ተጋላጭነትዎ ይጨምራል፡፡
• መድሃኒት፡- ለደም ብዛት ህክምና ሊሰጥ የሚችሉ እንደ ታያዛይድ ዳይዩሬቲክስና ሌሎች እንደ አስፒሪን ያሉ መድሃኒቶች የዩሪክ አሲድ መጠንን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡
• በቤተሰብዎ ዉስጥ መሰል የጤና ችግር ካለ፡- አንዱ የቤተሰብዎ አባል መሰል ችግር ከነበረዉ እርስዎም በችግሩ የመያዝ/የመጠቃት እድልዎ ከፍተኛ ነዉ፡፡
• እድሜና ፆታ፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በወጣትነት እድሜያቸዉ ሪህ ሊይዛቸዉ ይችላል፡፡ ሴቶች እድሜቸዉ እየጨመረ ሲመጣና በተለይ ሲያርጡ ለሪህ ተጋላጭነታቸዉ እየጨመረ ይመጣል፡፡
• ከአደጋ በኃላ ቀዶ ጥገና በቅርቡ ተደርጎሎት ከነበረ
ለሪህ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች
• ፈሳሽ ካለ ናሙና ተወስዶ መመርመር
• የደም ምርመራ
• ራጅ
• አልትራሳዉንድ የማሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የኑሮ ዘይቤና የቤት ዉስጥ ህክምና
ምንም እንኳ ዋናዉ ህክምና መድሃኒት መጀመር ቢሆንም የተወሰኑ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ህመሙን ለመቀነስ ሊረዳዎ ይችላል፡፡
• የሚወስዱትን የአልኮል መጠጥና በፍራፍሬ ስኳር/ፍሩክቶስ/ የጣፈጡ መጠጦችን መገደብ፡- ከነዚህ ይልቅ ዉሃ በብዛት በጠጣት
• የፕዩሪን መጠናቸዉ ከፍተኛ የሆኑ እንደ ቀይ ስጋ፣የባህር ምግቦችን ያለማዘዉተር
• መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ክብደትን መቀነስ
ሪህን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የህመም ምልክቶች በሌሉበት ወቅት ተጨማሪ የህመም ስሜቶች እንዳይመጡ
• ፈሳሽ በብዛት መዉሰድ፡- ዉሃ በደንብ መጠጣት
• የአልኮል አወሳሰድዎን መገደብ፡-
• የፕሮቲን ምንጭዎን መጠነኛ ስብ ከሚሰጡ የእንስሳት ተዋፅኦ ዉጤቶች ማድረግ
• የስጋ፣የዓሳና የዶሮ ምግችን መመጠን
• ክብደት መቀነስ ናቸዉ፡፡

23/02/2022

ከባድ ኩላሊት በሽታ መነሻው ምንድን ነው? ምልክቶቹ እና ህክምናውስ?
*****************************************
ከባድ የኩላሊት በሽታ በረጅም አመታት ቀስ እያለ ኩላሊታችንን እየጎዳ ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው። ከግዜ በኋላ የበሽተኛው ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆማል።
ከባድ የኩላሊት በሽታ ወይም ክሮኒክ ኪድኒ ዲዚዝ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ በማህበረሰቡ የተንሰራፋ በሽታ ነው። ስር እስኪሰድ ድረስ ለረጅም ግዜ ሳይታወቅ ኩላሊታችንን የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ኩላሊት ጤናው ወርዶ በ25% ብቃት መስራት ሲጀምር በበሽታው እንደተያዙ ማወቅ የተለመደ ነው። የኩላሊት መስራት ማቆም እየበረታ ሲሄድ ሰውነታችን ውስጥ አደገኛ መጠን ያለው ቆሻሻ እና ፍሳሽ ይከማቻል። ለዚህ በሽታ ያለው ህክምና የኩላሊትን መዳከም ለማቆም ወይም የሚዳከምበትን ፍጥነት ለማዘግየት የሚሞከርበት ነው። ይህንንም ማድረግ የሚቻለው የበሽታውን መነሻ የሆነውን በሽታ ለማከም እና ለማስታገስ በመሞከር ነው።
👉👉👉 ምልክቶች
ክሮኒክ የኩላሊት በሽታ ቀስ በቀስ ዘግይቶ እኩላሊታችን የሚዳከምበት በሽታ ነው። አንዱ ኩላሊት መስራት ቢያቆምም ሌላኛው ያለ ችግር ሊቀጥል ይችላል። ብዙ ግዜ ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ እስኪደርስ እንደታመምን ላናውቅ እንችላለን። ህመም መሰማት ከመረ በኋላ ብዙ ግዜ ጉዳቱን ማከም አይቻልም።
ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየግዜው የኩላሊታቸውን ጤንነት እየተመረመሩ ማረጋገጥ አለባቸው። በሽታው እንዳለብን በግዜ በማወቅ እራሳችንን ከከባድ የኩላሊት ጉዳት ማዳን እንችላለን።
የከባድ እኩላሊት ህመም ምልክቶች እንደሚከተለው ናቸው፦
• የደም ማነስ
• ደም የተቀላቀለበት ሽንት
•የጠቆረ ሽንት
• ንቁ አለመሆን
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ
• የድካም ስሜት
• የደም ግፊት
• እንቅልፍ እጦት
• የሚያሳክክ ቆዳ
• የምግብ ፍላጎት መጥፋት
• ወንዶች ላይ ብልትን ማስነሳት መቸገር
• በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ
• የትንፋሽ እጥረት
• ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት
• በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት
•እራስ ምታት
👉👉👉 የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች
ጂኤፍአር ሬት(GFR rate) የኩላሊት ጤንነት የሚታወቅበት መለኪያ ነው። የጂኤፍአር መጠን የኩላሊታችንን ጤነንት ይናገራል።
ስቴጅ 1 – የጂኤፍአር መጠናችን ጤነኛ ነው። ቢሆንም ግን የኩላሊት በሽታ እንዳለ ታውቋል።
ስቴጅ 2 – የጂኤፍአር መጠናችን ከ90ሚሊሊትር በታች ሲሆን ኩላሊታችን ውስጥ በሽታ እንዳለ ታውቋል።
ስቴጅ 3 – የጂኤፍአር መጠናችን ከ60ሚሊሊትር በታች ነው።
ስቴጅ 4 – የጂኤፍአር መጠናችን ከ30ሚሊሊትር በታች ነው።
ስቴጅ 5 – የጂኤፍአር መጠናችን ከ15ሚሊሊትር በታች ነው። የኩላሊት ማቆም አጋጥሟል።
አብዛኛው የኩላሊት በሽታ ታካሚ በሽታው ከስቴጅ 2 አያልፍበትም። ነገር ግን ህመሙ እንዳይባባስ ህክምና በማድረግ የኩላሊትን ጉዳት መከላከል ተገቢ ነው።
ስኳር በሽታ ያላቸው ሰዎች አመታዊ ህክምና ማድረግ አለባቸው። ሽንታቸው ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን በመለካት ኩላሊታቸው አለመታመሙን ማረጋገጥ አለባቸው።
👉👉👉ህክምና
ኩላሊት በሽታን የሚያድን መድሃኒት የለም። ነገር ግን የተለያዩ ህክምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር አገልግሎት ላይ ይውላሉ። ከባድ ኩላሊት በሽታ ያላቸው ሰዎች ብዙ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል።
የደም ማነስ ህክምና
አንዳንድ ደም ማነስ ያለባቸው ኩላሊት በሽተኞች የደም ዝውውር ማድረግ ይኖርባቸዋል። ብዙ ግዜ ግን በሽታው ያለበት ህመምተኛ አይረን ንጥረ ነገር ያላቸውን ክኒኖች መውሰድ ወይንም በመርፌ መልክ ማግኘት ይኖርበታል።
ፎስፌት ባላንስ
ኩላሊት ህመም ተጠቂዎች ሰውነታቸው በተገቢው ሁኔታ ፎስፌት ማስወገድ ይቸገራል። ታካሚዎች በአመጋገባቸው ላይ ፎስፌት እንዲቀንሱ ይመከራሉ። የወተት ምርቶች፣ ቀይ ስጋ፣ እንቁላል እና አሳ ፎስፌት ስለያዙ አይመከሩም።
የደም ግፊት
የኩላሊት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ብዙ ግዜ ደም ግፊታቸው ከፍተኛ ነው። ኩላሊትን ለመጠበቅ ደም ግፊትን መቆጣጠር ያስፈልጋል።
ቆዳ ማሳከክ
እንደ ክሎሮፌናሚን እይነት መድሃኒቶች የቆዳን ማሳከክ ያስታግሳሉ።
👉 ህመምን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች
ኩላሊት መስራት ሲያቆምና ሰውነት ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ሲከማቹ ታካሚው የማቅለሽለሽ ወይም የመታመም ስሜት ይሰማዋል። በዚህ ግዜ እንደ ሳይክሊዛይን አይነት መድሃኒቶች ህመምን ያስታግሳሉ።
👉👉👉 የመጨረሻ ደረጃ ህክምናዎች
ኩላሊት አቅሙ ተሟጦ በ10-15 ፐርሰንት ደረጃ መስራት ሲጀምር ከላይ የተዘረዘሩት ህክምናዎች ብቻቸውን በቂ አይሆኑም። የመጨረሻ የኩላሊት ደረጃ የደረሱ ታካሚዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማቸውን ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያለ እገዛ መቋቋም አይችሉም። ታካሚው በህወት ለመኖር ዳያሊሲስ ያስፈልገዋል።
ኩላሊት መጨረሻው ደርሶ አስፈላጊ ካልሆነ ዶክተሮች ዳያሊሲስ እና ንቅለ-ተከላን ለማድረግ አይመርጡም። እነዚህ ህክምናዎች በኢንፌክሽን ምክንያት መወሳሰብ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ዳያሊሲስ
ዳያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሰውነት ቆሻሻን ማጥራት ስራ ነው። ሁለት አይነት የዳያሊሲስ አይነት አለ። አንደኛው ሂሞዳያሊሲስ ነው። ይህ የዳያሊሲስ አይነት ደም ከሰውነታችን ፓምፕ እየተደረገ በማሽን ውስጥ አልፎ እየተጣራ እንዲገባ የሚደረግበት ህክምና ነው። 3 ሰአት የሚፈጅ ህክምና ነው። ህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህን ህክምና በተደጋጋሚ ማድረግ ለታካሚው ጤና ጥሩ ነው።
ሌላኛው የዳያሊሲስ አይነት ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ ሲሆን የታካሚው ደም በራሱ ሆድ ውስጥ እንዲጣራ ይደረጋል። ሆድ ውስጥ በሚገባ ካቴተር ውስጥ የዳያሊሲስ ውህድ በመጨመር ቆሻሻ እና ፍሳሽ እንዲወጣ ይደረጋል።
👉 ኩላሊት ንቅለ-ተከላ
ከኩላሊት መስራት ማቆም በቀር ሌላ ኩላሊትን የሚጎዳ በሽታ ለሌላቸው ታካሚዎች ኩላሊት ንቅለ-ተከላ ከዳያሊሲስ የተሻለ አማራጭ ነው። ቢሆንም ግን ንቅለ-ተከላ ከማድረጋቸው በፊት ታካሚዎች የዳያሊሲስ ማሽን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
ኩላሊት ለጋሹ እና ተቀባዩ ተመሳሳይ የደም አይነት፣ የሴል ሰርፌስ ፕሮቲን እና አንቲቦዲ ሊኖራቸው ይገባል። ካልሆነ የተቀባዩ ሰውነት ኩላሊቱን ላይቀበለው ይችላል። ብዙ ግዜ የዘመድ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የተሻለ ለጋሽ ይሆናሉ።

19/02/2022

የታላቁ ህዳሴ ግድብ እውነታዎች
**************
👉 ግድቡ 5,150 ሜ.ዋ ሀይል የማመንጨት አቅም አለው
👉 13 የሀይል ማመንጫ ዩኒቶች (ተርባይኖች) የተገጠሙለት ነው
👉 እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜ.ዋ በላይ የማመንጨት አቅም አለው
👉 ግድቡ 145 ሜትር ወደ ላይ ይረዝማል፤ ወደ ጎን ደግሞ 1.8 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሆኖ ነው የተገነባው
👉 ከዋናው ግድቡ ሞልቶ የሚወጣው ውሃ ሳድል ግድብ (ኮርቻ ግድብ) ውስጥ ይከማቻል
👉 ኮርቻ ግድብ 50 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ ጎን 5.2 ኪ.ሜ የሚሸፍን ነው
👉 በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ግድብ ነው።
👉 አጠቃላይ እስካሁን ባለው መረጃ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 16.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
👉 ግድቡ አሁን ያለበት ደረጃ 1ኛ እና 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቋል
👉 አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 83.9% ተጠናቋል
👉 ግድቡ ለቱሪዝም፣ ለአሳ ሀብት ለኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ጠቀሜታዎች አሉት
👉 ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ 246 ኪ.ሜ የሚሸፍን አርቴፊሻል ሀይቅ ይፈጠራል።

19/02/2022

አገር የፖለቲካ ፍልስፍና ስሪት ናት
******************
አገሪቱ ነዳጅ ስታገኝ ሁሉም የኤምሬትስ ጎሳዎች ጥል ውስጥ ገቡ። ሁላቸውም ጎሳቸውን እየሰበሰቡ እከሌ የሚባለውን ጎሳ አሸንፈን ስልጣን መያዝ አለብን እያሉ ወታደር ማስልጠን ጀመሩ። ያነየ ለሁላቸውም መሳሪያ አቅራቢዋ እንግሊዝ ነበረች። አሁን አገሪቱን የሚመሩት የነ መሀመድ ቢን ዛይድ አያት ሁሉንም ጎሳዎች ሰበሰባቸው።
ስብሰባ ጀመረ። ወገኖቼ ሁላችንም አረብ ነን። ሁላችንም ሙስሊሞች ነን። ሁላችንም አንድ አገር ነው ያለን። ሁላችንም ድሀ የደህ ልጆች ነን። ሁላችንንም የፈጠረን አንድ ፈጣሪ ነው። ሁላችንም ሰው ነን። ሁላችንም ጎሳ አለን። ሁላችንንም ጎሳችንን እንወድዋለን። ሁላችንም ተጣልን ጥላቶቻችን ለሁላችንም መሳሪያ አቅርበው ተጋደሉ ሲሉን ተገዳድለን መጨረሻ ላይ የምናገኘው ትርፍ ምንድነው .? ሲል ጠየቃቸው። ሁሉም የጎሳው መሪዎች ለጥያቄው መልስ አተው ዝም አሉ። መልሱልኝ እንጅ ሲል ጠየቃቸው። አሁንም ዝም አሉ። እሽ ምን እንሁን አላቸው። ዝም አሉ። እናተ ዝም ካላችሁ እኔ ልናገር አላቸው እነሱም እሽ ተናገር አሉት።
ይች አገር የሁላችንንም ናት። አንዱ በልቶ አንዱ ተርቦ የሚኖርባት አገር አይደለችም። ሁላችንም የአገሪቱ ባለቤት ነን። ስለዚህ አንድ አስማምቶ የሚመራን ሰው እንምረጥ አላቸው። እዚህ የተሰበሰበው ጎሳ አንድ አ መንግስት መመስረ አለበት አላቸው። እነሱም እሽ አሉት። አንድ መንግስት መሰረቱ። የመንግስት ካቢኔም ከየጎሳው ተመረጡ። የዛኑ ቀን በእምነታቸው ቃለ መሀላ ፈፀሙ።
ሸህ ዛይድም የመጀመሪያ የኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ተደርጎ ተሾመ። ያሁሉ የጎሳ መሪ ወደቤቱ ሊሄድ ሲል ሸህ ዛይድ (ፕሬዝዳንቱ ) አንድ ንግግር ተናገሩ። ለጦር ያዘጋጃችሁትን ጎሳችሁን ለልማት እንዲዘጋጅ ንገሩት አላቸው። ጉባዔው እንዴት ተጠናቀቀ ጦርነት አለ ቀረ እያለ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ወታደር ሁሉ መንግስት መስረትናል፣ ጦርነት የለም። ለልማት ተዘጋጅ ተብለናል አሏቸው።
ወዲያው ልማት ጀመሩ። ይሄው አሁን አረብ ኤምሬትስ የመካከለኛው ምስራቅ የንግድ እና የኢንቨስትመንት፣ የቱሪስት ዋና ከተማ ሆና ዜጎቿን አንደላቃ እያኖረች ነው።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን የቤት ሰራተኛ ቀጥራ እያሰራች ነው። የዜጎቿ የወር ወጭ የኢትዮጵያ የአንድ አመት በጀት ነው። አገሪቱ በ2 ወር ውስጥ የምታስገባው ገቢ የኢትዮጵያ የአመት ከ3 ወር በጀት ነው።
ከሷ በፊት ስንት መንግስት ያላት ኢትዮጵያ ግን ዛሬ አንዱ አንዱን ለመብላት ሲፈላለግ ዜጎቹን እንዲህ በረሀብ አዋርዶ እያኖረ፣ ዛሬም ከችጋር በማያወጣ ብሔርተኝነት ይባላል። አገር የፖለቲካ ፍልስፍና ስሪት ናት። ቅን የፖለቲካ ፍልስፍና አገርን እንዲህ ያገናል። በተንኮል የታከነ ፍልስፍና ግን አገርን አድቆ ዜጋውን በችጋር እያሰቃየ ዛሬም ስለ ጦርነት ይሰብካል።

Website