Let ethio lern

Let ethio lern

To learn

22/07/2022

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የሥራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል ደንብ በአዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ወጣ፡፡
# የደንቡ አጠቃላይ ይዘት ስለስራ መደቦች ምዘና፣ የደረጃ ምደባና አተገባበርና የደሞዝ ስኬል የሚደነግግ ደንቡ ነው፡፡
================
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣20014ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል ደንብ ቁጥር 124/2014 በአዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱ ታውቀል፡፡
ደንቡ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 381/1995 አንቀፅ (23 ) ንዑስ አንቀፅ 1 (ረ) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 አንቀፅ 97 ንዑስ አንቀፅ (1 ) መሰረት ማውጣቱም በታተመው ነጋሪት ጋዜጣ ላይ ተገልፆል፡፡
በአራት ክፍሎች ተከፋፍሎ በተዘጋጀው በዚህ ደንብ ላይ በክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፣ በክፍል ሁለት የስራ መደብ መመዘኛ መስፈርቶችና የደረጃ አመዳደብ ሂደት፣ በክፍል ሶስት የደመወዝ አወሳሰን እና የደመወዝ ጭማሪ አፈፃፃም፣ በክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን አካትቶ የወጣ ደንብ እንደሆነም ለመረዳት ተችለል፡፡

https://t.me/psrhrd

Website