ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ

ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ

ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 20/07/2023

በወረዳችን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአትክልት እና ፍራፍሬ ችግኞች ተከላ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 18/07/2023

በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ትላንት ማለትም ሐምሌ 10/2015ዓ/ም የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከተካሄደ በኃላ የተተከሉ ችግኞች የተፈሉበት ፕላስቲክ በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ብክለት የሚፈጥር በመሆኑ የመልቀም እና የማስወገድ ስራ ተሰርቷል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 18/07/2023

የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር በስኬት መጠናቀቁን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ እንደገለፁት በወረዳችን በአንድ ጀንበር ማለትም ሐምሌ 10/2015ዓ/ም ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በነበረው የተከላ ስራ እንደ ወረዳ 1785611 ችግኞችን በ190 ሄ/ር መሬት ላይ ለመሸፈን አቅደን በዕለቱ በወረዳው ውስጥ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች በተደረገ የተከላ ስራ 1982028 ችግኞችን በ210.9 ሄ/ር ላይ መትከል መቻሉን ገልፀዋል ይህም የእቅዳችንን 111% መፈፀም በመቻላችን እንኲን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በዕለቱ የተተከሉ ችግኞች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ፣ የጌሾ ፣ የአካባቢውን ስነ ምህዳር የሚጠብቁ የደን ችግኞች እና የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው የእንስሳት መኖ ችግኞች መተከላቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም መትከል ብቻ ግብ ስላልሆነ ዛሬ የተከልናቸውን ችግኞች ዕለት ከዕለትክትትል እና እንክብካቤ ማድርግ ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ዛሬ ተከላላይ የተሳተፉ አካላት ከአንድ ወር በኃላ ወይም ነሐሴ 15 /2015ዓ/ም በንቅናቄ በመውጣት እንደተከልነ ሁሉ በንቅናቄ በመውጣት የኩትኲቶ እና አረም የማረም ስራ ለመስራት መዘጋጀት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል። በተከላው ወንድ= 32025 ሴት= 10675 በድምሩ = 42700 ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 17/07/2023

በአንድ ጅንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በ14ቱም ቀበሌዎች በድምቀት እየተከናወነ ነው።
በወረዳው በአንድ ጀንበር 1.7 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ስራ እየተሰራ ይገኛል ።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 09/07/2023

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የጽ/ቤቱን አመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም በቀን 30/10/2015ዓ/ም ሁሉም የቀበሌ እና የወረዳ ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በቲሊሊ ከተማ ገምግሟል። የአመቱ የሁለም የግብርና ዘርፎች ግቦች አፈፃፀም በምክትል ጽ/ቤት ኃላፊዎ ወ/ሮ ሳምራዊት ከበደ የቀረበ ሲሆን ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል። በግምገማው ወቅት በአመቱ ውስጥ በሁሉም የግብርና ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቀበሌዎች የምስጋና እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል። በመጨረሻም በቀጣይ በትኩረት ተይዘው የሚፈፀሙ ተግባራት በጽ/ቤት ኃላፊው በአቶ ደረጀ ወ/ገሪማ በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን የቀበሌ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳ አመራሮች እና ባለሙያዎች በጋራ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀትን እየገመገምኩ በመምራት እና በመፈፀም ኃላፊነቴን እወጣለሁ በማለት ቃል ገብተዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 21/06/2023

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አሲዳማ መሬቶችን በኖራ ማከም አስፈላጊ ነው ተባለ።
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ እንዳሉት ወረዳችን በከፍተኛ ሁኔታ በአፈር አሲዳማነት የተጠቃ መሆኑ በተለያዩ ጥናቶች እና በተደጋጋሚ ጊዜ በተደረጉ የአፈር ምርመራ ውጤቶች ተረጋግጧል ብለዋል። ስለሆነም ይህንን በወረዳችን ስር የሰደደውን የአፈር አሲዳማነት ችግር ለመከላከል እና ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር ኖራ መጠቀም ዋናው መፍትሄ መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም አሁን ላይ የአፈር ናሙናው ወደ ባህርዳር ተልኮ በላብራቶሪ ተመርምሮ አሲዳማነቱ ተረጋግጦ እና ምን ያህል የኖራ መጠን እንደሚያስፈልገው ውጤት በመጣላቸው መሬቶች ላይ ኖራ የማቀላል ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው አሁን ላይ ያለውን ከፍተኛ የአፈር አሲዳማነት ለመከላከል እና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በኖራ ከማከም ጎን ልጎን ሌሎች የተቀናጁ የአፈር ለምነት የሚያሻሽሉ እና አሲዳማነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጅዎችን እና አሰራሮችን አቀናጅቶ መፈፀም ተገቢ እንደሆነ እና ተግባሩም እንደ ወረዳ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 09/06/2023

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /Food System Resilience Program /FSRP/ የትውውቅ እና የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ በቀን 01/10/2015ዓ/ም ከቀበሌና ከወረዳ ከተገኙ በርካታ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቲሊሊ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ከዚህ በፊት በግብርና እድገት ፕሮግራም በወረዳው ውስጥ የተሰሩ ተግባራት በግብርና ጽ/ቤት ኃላፊው በአቶ ደረጀ ወ/ገሪማ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን የግብርና እድገት ፕሮግራም በወረዳው ውስጥ ለሰራቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት በወረዳው ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል። በመቀጠልም አዲሱ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /FSRP/ በቀጣ 7 ዓመታት ውስጥ የሚሰራቸው ተግባራት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው የበሰለ ውይይት ተደርጒበታል ። በመጨረሻም የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ወረዳችን በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም እንዲታቀፍ ላደረጉ አካላት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 12/05/2023

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የግብርና ቴክኖሎጅ ማስረጫ ስርዓት የሆነው ዲጅታል ግሪን ወይም ቪዲዮ ኤክስቴንሽን ተግባር በወረዳው ባሉ 14ቱም ቀበሌዎች እየተተገበረ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም በዛሬው እለት ማለትም በ04/09/2015ዓ/ም በቲሊሊ ከተማ ሁሉም የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው የወረዳ ባለሙያዎች በተገኙበት ገምግማ እና የማነቃቂያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 11/05/2023

በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በዛሬው እለት ማለትም በቀን 03/09/3015ዓ/ም በወረዳው ባሉ 14ቱም ቀበሌዎች በየቀበሌው ለተመለመሉ 200 ለሚሆኑ ሞዴል አ/አደሮች የ2015/16 ምርት ዘመን የንቅናቄ መድረክ በቀበሌ ደረጃ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 09/05/2023

በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ አማካኝነት የ2015/16 የምርት ዘመን የተመረጡ የሠብል እና የአት/ፍራፍሬ ልማት ፓኬጅ የባለሙያዎች ቴክኒካል ስልጠና
እና የንቅናቄ መድረክ ወይም የግንዛቤ ፈጠራ ከ28/08/15 ጀምሮ ለ3ተከታታይ ቀን ሲሰጥ ቆይቶ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቊል። ለባለሙያዎች የመግቢያ እና የመውጫ ፈተና ተሰጥቷል በፈተናው የተሻለ ውጤት ላመጡ ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት በጽ/ቤቱ ኃላፊዎች ተሰጥቷል። በመጨረሻም የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ ከቀጣይ መድረኮች አኮያ እና በቀጣይ በትኩረት ተይዘው በሚሰሩ አጠቃላይ የግብርና ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫ እና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 26/04/2023

በበጋ መስኖ የቢራ ገብስ ምርት ከ45ሚሊየን ብር በላይ ለጎንደር ብቅል ፋብሪካ ለግብይት መሰብሰቡን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

ቲሊሊ:-ሚያዚያ 18/2015 ዓ.ም

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የበጋ መስኖ የቢራ ገብስ ምርት ከ45ሚሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈፀሙን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ደረጀ ወልደ ገሪማ እንዳስታወቁት በ2015 በጀት አመት በበጋ መስኖ 5መቶ ሄክታር መሬት በቢራ ገብስ በማልማት 10ሺ ኩንታል ለጎንደር ብቅል ፋብሪካ ለማቅረብ አቅዶ በመስራት ሰፊ ርብርብ ሲያደርግ እንደቆየና በተደረገው ጥረትም የታቀደው 5መቶ ሄክታር መሬት ፈጥሮ እንዲለማ በማድረግ እስከዛሬ ድረስ ከ11ሺ ኩንታል በላይ በመሰረታዊ ማህበራት በማሰባሰብ እና ከጎንደር ብቅል ፋብሪካ ጋር በመዋዋል ከ45 ሚሊዮን ብር ግብይት እየተፈፀመ ያለበት ሂደት ላይ እንደሆነ በመግለፅ አርሶ አደሩም በዘርፉ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ጥሬ ግብዓቱን ለፋብሪካው በማቅረባችን ከ818ሺ ዶላር ምንዛሬ ፍለጋ መታደግና ለኢኮኖሚው ጉልህ ሚና እንዳለው የተናገሩት አቶ ደረጀ አሁን ላይ ግን ብቅል ፋብሪካው በህብረት ስራ አማካኝነት ግብይት የተፈፀመበትን የአርሶ አደሩን ምርት ከመጋዝኖች ለማንሳት መዘግየት በማሳየቱ አርሶ አደሮች በወቅቱ ገንዘባቸውን አግኝተው የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴአቸው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረባቸው ስለሚገኝ ፋብሪካው በገባው ውል መሰረት ግብይት የተፈፀመበትን ምርት በወቅቱ በማንሳት የአርሶ አደሩ ገንዘብ በፍጥነት እጁ ላይ እንዲደርስ ማድረግ አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።

16/04/2023

ውድ መላው የተቊማችን ባለሙያዎች ውድ የወረዳችን አ/አደሮች መላው የወረዳችን ነዋሪዎች በመላው በሃገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኲን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የጤና የፍቅር የመተሳሰብ እና የአንድንት እንዲሆንላችሁ እየተመኘን መጭው ጊዜ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እምርታ የምናመጣበት ይሁንልን።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 05/04/2023

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በግብርና እድገት ፕሮግራም ድጋፍ የሰብል በአይነት ዘር ስርጭት ፣ አሰባሰብ እና አጠቃቀም የማስፈፀሚያ ሰነድ ትውውቅ እና በ2015 ዓ/ም በግብርና እድገት ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ ተገዝቶ ለአ/አደሮች የተሰራጨ የበጋ መስኖ የስንዴ ዘር እንዴት መመለስ እንዳለበት ከቀበሌ እና ከወረዳ ግብረ ሃይሉ፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፣ ከስትሪንግ ኮሚቴዎች እና ከባለሙያዎች ጋር በቀን 27/07/2015ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም ሁሉም ቀበሌዎች ዘሩን እንደሚያስመልሱ መግባባት ላይ ተደርሷል። የቀበሌግብረ ሃይሉ ላይም እንደ ወረዳችን ተጨባጭ ሁኔታ ስራውን ሊያግዙ ይችላሉ ያልናቸውን የቀበሌ ተ/ሃብት ባለሙያዎች፣ የቀበሌ ኮማንደሮችን እና የቀበሌ ማህበራዊ ሸንጎ ሰብሳቢዎችን የግብረ ሃይሉ አባል በማድረግ አካተናቸዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 20/03/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በአስኩና ቀበሌ በስራ እድል ፈጠራ የተደራጁ ወጣቶች ያለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ በፎቶ

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 16/03/2023
Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 16/03/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት በአስኩና ቀበሌ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም ድጋፍ በስራ ዕድል ፈጠራ በተደራጁ ወጣቶች ላይ ሞተር ፓምፕ በመጠቀም ባለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ በቀን 05/07/2015ዓ/ም የገበሬ በዓል ተካሂዷል ። በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ግ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ ሌሌች ወጣቶች የአስኩና ቀበሌ ወጣቶችን ተሞክሮ በመውሰድ የትኛውንም አይነት ቴክኖሎጅ እና የትኛውንም የዉሃ አማራጭ በመጠቀም በተሰጣቸው ውስን መሬት ላይ በመስኖ ልማት በመሰማራት የባለሙያን ድጋፍ በመቀበል በዓመት 3ጊዜ እና በላይ በማምረት እራሳቸውን መለወጥ እንዳለባቸው እና ከመስኖልማቱ ጎን ለጎን በሌሎች የግብርና እና የእንስሳት ተግባራትን በመፈፀም ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል በበዓሉ የወረዳ አመራሮች ፣ የቀበሌ አመራሮች ፣ አ/አደሮች የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በበዓሉ ወቅት ወጣቶች የግብርና እድገት ፕሮግራም ላደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

16/03/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት በአስኩና ቀበሌ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም ድጋፍ በስራ ዕድል ፈጠራ በተደራጁ ወጣቶች ላይ ሞተር ፓምፕ በመጠቀም ባለሙት የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ በቀን 05/07/2015ዓ/ም የገበሬ በዓል ተካሂዷል ። በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ግ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ ሌሌች ወጣቶች የአስኩና ቀበሌ ወጣቶችን ተሞክሮ በመውሰድ የትኛውንም አይነት ቴክኖሎጅ እና የትኛውንም የዉሃ አማራጭ በመጠቀም በተሰጣቸው ውስን መሬት ላይ በመስኖ ልማት በመሰማራት የባለሙያን ድጋፍ በመቀበል በዓመት 3ጊዜ እና በላይ በማምረት እራሳቸውን መለወጥ እንዳለባቸው እና ከመስኖልማቱ ጎን ለጎን በሌሎች የግብርና እና የእንስሳት ተግባራትን በመፈፀም ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ አሳስበዋል በበዓሉ የወረዳ አመራሮች ፣ የቀበሌ አመራሮች ፣ አ/አደሮች የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በበዓሉ ወቅት ወጣቶች የግብርና እድገት ፕሮግራም ላደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 06/03/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በወንጀላ ቀበሌ እየለማ ያለ የበጋ መስኖ ስንዴ አሁን ያለበት ሁኔታ

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 06/03/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት በወንጀላ ቀበሌ በግብርና እድገት ፕሮግራም /Agp/ ድጋፍ በክላስተር በለማ የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ በቀን 27/06/2015 ዓ/ም የገበሬ በዓል ተካሂዷል በቀበሌው በ3 ክላስተር 471.75 ሄ/ር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑን የቀበሌው የመስኖ ባለሙያው አቶ ደመላሽ ዳኛው ገልፀዋል። የወረዳ ግ/ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ በያዝነው ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በወረዳው የተሻለ አስተማሪ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና በተሰራ ስራ ላይ ባለፈው ሳምንት በዛላ ቀበሌ ወረዳዊ የገበሬ በዓል መዘጋጀቱን አስታውሰው ቀበሌዎች ደግሞ በራሳቸው ቀበሌያዊ የገበሬ በዓል ማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ካሉ በኃላ ሌሎች ቀበሌዎችም ልምዱን በመውሰድ የገበሬ በዓል እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል ። ኃላፊው አያይዘውም በበጋ መስኖ ስንዴ ያየነውን በክላስተር የማምረት ልምድ ትምህርት በመውሰድ በመኸርም ስራዎቻችንም አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል። በመጨረሻም የገበሬ በዓሉን ላዘጋጁት አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የበዓሉ የክብር እንግዳየነበሩት የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም መንክር እንደ ሀገርበስንዴ ምርት እራሳችንን በመቻል ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በማስቀረት እኛ ወደ ውጭ ስንዴ ለመላክ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በዛሬው እለት በወንጀላ ቀበሌ በክላስተር የለማው የበጋ መስኖ ስንዴ በጣም አስተማሪ እና ት/ት የሚወሰድበ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ በየቀበሌው በርካታ አስተማሪ የግብርና ስራዎች መኖራቸውን ገልፀው የገበሬ በዓል እየተደረገባቸው ወደ ሌሎች መስፋት እንዳለባቸው አሳስበዋል አያይዘውም መካናይዜሽንን ለማስፍፍት አ/አደሩ እየተደራጀ ትራክተር መግዛት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል በመጨረሻም የመስኖ ስንዴ ልማቱ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። በበዓሉ የወረዳ አመራሮች፣ የወረዳ ባለሙያ፣ የቀበሌ አመራሮች እና አ/አደሮች ተሳትፈዋል። በመጨረሻም የበዓሉ ተሳታፊዎች የግብርና እድገት ፕሮግራም ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 02/03/2023

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በዛላ ቀበሌ በግብርና እድገት ፕሮግራም /Agp/ 2 ድጋፍ በለማ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እና በተሰሩ ሠርቶ ማሳያዎች ላይ በቀን 20/06/2015 ሰፊ ወረዳዊ የገበሬ በዓል አካሂዷል። በበዓሉ ወቅት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ እንደገለፁት በወረዳው 2500 ሄ/ር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ሁሉም የሚመለከተው አካል ባደረገው ርብርብ 3228ሄ/ር የዕቅዱን 129% መፈፀም መቻሉን ገልፀው በስንዴ ከሚለማው መሬትም ከ126 ሽህ ኩ/ል በላይ ምርት ይገኛል ተበሎ ይጠበል ብለዋል በእለቱ የገበሬ በዓል የተደረገበት ክላስተርም 184 ሄ/ር ሲሆን በዚህም 416 አ/አደሮች ተሳትፈዋል ብለዋል፡ በአጠቃላይ እንደ ወረዳ በ38 ክላስተሮች በመደራጀት የመስኖ ስንዴ ልማቱ እየለማ መሆኑን ገልፀዋል። በእለቱ የገበሬ በዓል የተደረገበት ክላስተር የለማው በግብርና እድገት ፕሮግራም በጀት በተገነባው የዝንግኒ መለሀ ቁ 1 የመስኖ አውታር መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የግብርና እድገት ፕሮግራም በያዝነው ዓመት ለመስኖ ስንዴ ልማት የንቅናቄ መድረክ እና የግንዛቤ ፈጠራ፣ ለስንዴ ዘር እና ለአፈር ማዳበሪያ መግዥያ ፣ለባለሙያ ስልጠና መስጫ፣ ለገበሬ በዓል ማስኬጃ እና ለክትትል እና ድጋፍ ከ16ሚሊዮን ብር በላይ በመድገፍ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጎልናል ብለዋል በዚህም 1705.26ኩ/ል የስንዴዘር 757 NPS 860.5 ዩሪያ ተገዝቶ ለአ/አደሩ ተሰራጭቷል ብለዋል። በመጨረሻም የግብርና እድገት ፕሮግራም /Agp/ የመስኖ ስንዴን ጨምሮ በወረዳው ውስጥ ላደረገልን እና እያደረግልን ላለው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በወረዳው ህዝብ ስም ከፍተኛምስጋና አቅርበዋል። በበዓሉ ላይ የክልል ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የዞን አመራሮች እና የግብርና መምሪያ ቡድን መሪዎች፣ ወረዳው ውስጥ ካሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተውጣጠው የተወከሉ ባለሙያዎች ፣ ጥቅል የወረዳ አመራሮች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ አጠቃላይ የወረዳ እና የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች፣ የወረዳው የንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ ፣ የአድማስ ዩኒየን የቦርድ ሰብሳቢ፣ የተመረጡ ሞዴል አ/አደሮች፣ የዞን እና የወረዳ ምክር ቤት ቊሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ፣ በርካታ የቀበሌው አ/አደሮች እና የሚዲያ አካላት በዓሉ ላይ ተሳትፈዋል። አጠቃላይ በበዓሉ ከ400 በላይ ተሳታፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በዓሉ የደመቀ እና ሰፊ ትምህርት የተወሰደበት የገበሬ በዓል ተካሂዷል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 20/02/2023

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2ኛውን ሩብ አመት ወይም የ1ኛው ግማሽ አመትን አጠቃላይ የግብርና ተግባራት አፈፃፀም እና የዋና ዋና ወቅታዊ ተግባራትን አፈፃፀም የ14ቱም ቀበሌ አስተዳዳሪዎች ፣ ሁሉም የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች እና የቀ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ሁሉም የወረዳ ግብርና ባለሙያዎች በተገኙበት በቀን 13/06/2015ዓ/ም በቲሊሊ ከተማ ገምግሟል። የ6ወሩን አጠቃላይ አፈፃፀም እና አጠቃላይ በ6ወሩ ቀበሌዎች ያሉበትን ሁኔታ የዕቅድ ቡድን መሪው አቶ አይሸሽም ታደለ በዝርዝር አቅርበዋል። በግምገማው ወቅት የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ ተግባራት በየወቅቱ እየተገመገሙ መመራት እንዳለባቸው እና ለወደፊትም ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ እየተገመገሙ እንደሚመሩ ያሳዎቁ ሲሆን ባጠቃላይ በ6ወሩ ያሉ ክፍተቶችን ሁሉም የሚመለከተው አካል ድርሻ ድርሻውን ወስዶ ክፍተቶችን መሙላት ይኖርበታል ብለዋል አያይዘውም ከዚህ ግምግማ በመነሳት ክፍተቶችን በመለየት በክፍተቶች ላይ ለባለሙያዎች የአቅም መገንቢያ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል ። በመጨረሻም በቀጣይ 6ወራት የሚፈፀሙ ተግባራትን በቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 17/01/2023

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሽንኩርታ ቀበሌ በላይኛው ልፍጣ ተፋሰስ የ2015 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የማህበረሰብ ስራ ወረዳዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በቀን 09/05/2015 ዓ/ም በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል በፕሮግራሙ ላይ አካላት በፎቶ

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 17/01/2023

ቦረቦር መሬትን ለማዳን ክትር በመስራትና በመከለል ከእንስሳት ንክኪ ነፃ ለማድረግ የ2015 ዓ/ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በሽንኩርታ ቀበሌ በላይኛው ልፍጣ ተፋሰስ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የዞን፣የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ተሳታፊ አካላት ተገኝተዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 17/01/2023

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሽንኩርታ ቀበሌ በላይኛው ልፍጣ ተፋሰስ የ2015 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የማህበረሰብ ስራ ወረዳዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በቀን 09/05/2015 ዓ/ም በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል በፕሮግራሙ ላይ የዞን፣የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ወጣቶች፣ በቀበሌው የሚኖሩ ማህበረሰቦች ፣የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች እና ፈረሰኛ ማህበራት ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 14/01/2023

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2015 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የማህበረሰብ ስራ ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በወረዳ ደረጃ ከወረዳ እና ከቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች፣ ከወረዳ እና ቀበሌ አመራሮች ጋር በቲሊሊ ከተማ በቀን 06/05/2015ዓ/ም ውይይት ተደርጒል

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 03/01/2023

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በሽንኩርታ ቀበሌ የአ/አደር ማሰልጠኛ ተቊም የተዘራ ስንዴ በቀን 25/04/2015 ዓ/ም በኮምባይነር እየተሰበሰበ ይገኛል

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 27/12/2022

የጒጉሳ ሽኩዳድ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አምሳሉ ጥሩነህ 2ኛ ዲግሪያቸውን ለመማር እንጅባራ ዩንቨርስቲ ስለገቡ የተቊሙ ሰራተኛች መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላቸው በመመኘት ተቊሙን በኃላፉነት በመሩበት ወቅት ላስመዘገቡት ውጤት ትልቅ ምስጋና እና ክብር በመስጠት በዚህ መልኩ ሸኝቷቸዋል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 20/12/2022

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በአስኩና እግዚያብሄር አብ ቀበሌ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በክላስተር የተደራጁ አ/አደሮች በቀን 11/04/2015ዓ/ም ሁሉም በተመሳሳይ ሁኔታ ዘር የመዝራት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 04/12/2022

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የተፈጥሮ ሃብት ልማት የፓኬጅ ስልጠና ለቀበሌ እና ወረዳ ባለሙያዎች መስጠት ጀመረ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት ለባለሙያዎች የመግቢያ ፈተና ተሰጥቷቸዋል

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 24/10/2022

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በዛላ ቀበሌ በአ/አደር ማሰልጠኛ ተቊም በቀን 14/02/2415 ዓ/ም የኮምፖስት ዝግጅት የገበሬ በዓል ተካሂዷል በበዓሉ የወረዳ አመራር እና ባለሙያዎች ከየማህብረሰቡ የተውጣጡ አ/አደሮች ተገኝተዎል

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 11/09/2022

ለውድ የቀበሌና ለወረዳ ግብርና ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች ለውድ አ/አደሮቻችን ለተቊማችን አጋር እና ባለድርሻ አካላት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኲን ለ2015 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድንት፣ የመተሳሰብ እና ሀገራችን በግብርናው ዘርፍ ትልቅ እምርታ የምታመጣበት ክፉ የማንሰማበት ዓመት ይሁንልን።

02/08/2022

በ2014 በጀት ዓመት አፈፃፀም ተቋማችን በዞኑ ውስጥ ካሉ አቻ ተቋማት ጋር ተወዳድሮ የተሻለ በመፈፀም 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ በመሆኑ ለመላው ለቀበሌ እና ለወረዳ ባለሙያዎቻችን ፣ ለቀበሌ እና ለወረዳ ኃላፊዎቻችን ፣ ለአጠቃላይ ማኔጅመንቱ ፣ ከጎናችን ሆነው ላገዙን ባለድርሻ እና አጋር አካላት ፣ ለውድ አ/አደሮቻችን እና ለአጠቃላይ የወረዳው ህዝብ ፣ ድጋፍ ላደረጋችሁልን የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እያልን ለዚህ ውጤት መምጣት የቀበሌ እና የወረዳ ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ እና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ማኔጅመንቱ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ሲሆን ውጤቱ ባጠቃላይ ከጎናችን ሆነው ሲደግፉን የነበሩ አጋር እና ባለ ድርሻ አካላት ፣ የውድ አ/አደሮቻችን ፣ ድጋፍ ያደረጉልን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ የመላው ህዝብ ውጤት ነው ሁላችሁንም እናመሰግናለን ሽልማቱ 1ኛ. ባሳለፍነው በጀት ዓመት ለሰራነው ጥሩ ስራ እዉቅና ያገኘንበት 2ኛ. በቀጣይ ለምንሰራቸው አጠቃላይ የግብርና ስራዎች ከዚህ በተሻለ እንድንፈጽም እና መላዉ የወረዳውን ህዝብ ተጠቃሚ እንድናደርግ የተሰጠን ትልቅ ሀላፊነት እና አደራ ስለሆነ አደራቾንን ለመወጣት ካሁኑ ጠንክረን እና ተባብረን መስራት ይኖርብናል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 27/11/2020

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2012/13 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት የስራ ግምገማ በቲሊሊ ከተማ ከአጠቃላይ የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች ጋር አካሂዷል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 27/11/2020

የጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የመስኖ ልማት እና የኮምፖስት የንቅናቄ መድረክ በቀን 14/03/2013 በቲሊሊ ከተማ ተካሂዷል። መድረኩ ላይ 42 የወረዳ አመራሮች ፣ 28 የቀበሌ አመራሮች ሁሉም የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሁነወል።

Photos from ጓጉሳ ግብርና ጽ/ቤት/Guagusa Agricultural Office / ቲሊሊ's post 27/11/2020

በጒጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ የወንጀላ አጉታ ቀበሌ አ/አደሮች የአፈር አሲዳማነትን የሚከላከሉ ተግባራትን በመፈፀማቸው ምርታቸው እየጨመረ መምጣቱን አስታወቁ። በቀበሌው በቀን 13/03/2013 ዓ/ም አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም በክላስተር በተዘራ ጤፍ ላይ እና ከመሬት በታች በክላስተር በተዘጋጀ ኮምፖስት ላይ የገበሬ በዓል ተካሂዷል በበዓሉ ወቅት አ/አደሮች አፈራቸውን በማስመርመር ኖራ በመጠቀማቸው እና ጥራት ያለው ኮምፖስት አዘጋጅተው በመጠቀማቸው ምርታቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል። የቀበሌው የሰብል ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘለዓለም አበበ እንዳሉት በቀበሌው የተለያዩ የአፈር አሲዳማነት የሚያሻሽሉ ተግባራትን አቀናጅተው በመፈፀማቸው የአ/አደሮች ምርት እየጨመረ የመጣ መሆኑን ገልፀው ተግባሩን ለቀጣይ በሰፊው ለመስራት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል። የወረዳው የአፈር ልምነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጀ ወ/ገሪማ እንዳሉት ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል የተቀናጀ ስራ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው የአፈር ለምነት የሚያሻሽሉ ተግባራት በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል: ባለሙያው አክለውም አ/አደሮች ለቀጣይ - አፈራቸውን በማስመርመር ኖራ በመጠቀም - ጥራት ያለው ኮምፖስት አዘጋጅተው በመጠቀም - ቨርሚ ኮምፖስት አዘጋጅተው በመጠቀም - ህያው ማዳበሪያ በመጠቀም - የባዮ ጋዝ ተረፈ ምርት /ባዮ ሳለሪ/ የመሳሰሉትን የአፈር ለምነትን የሚያሻሽሉ ተግባራትን አቀናጅተው መፈፀም እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመጨረሻም የአፈር ለምነትን ለማሻሻል የተሻለ ለፈፀሙ አ/አደሮች የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቊል። በፕሮግራሙ ላይ የቀበሌ አ/አደሮች፣ የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሁነዋል።

Website