Damot woyde health office

Damot woyde health office

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Damot woyde health office, Medical and health, .

Photos from Damot woyde health office's post 28/07/2022

የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኙ ቀበሌያት ውስጥ በቀን 21/11/2014 ዓ.ም በ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ሞዴል በማድረግ የአንካ ሻሻራ:ሙንደጃ ሳኬ እና የግራራ ማዘጋጃ ቀበሌያትን አስመርቋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ጦና የምረቃ ስነ ስርዓት አስመልክተው በአንድ ቀን ሶስት ቀበሌያትን በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ሞዴል ሆነው በመመረቃቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የተመረቁት ቀበሌያት የ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አድርገው እና በቀጣይም ከማስቀጠል አንጻርም ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሚና ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
በዚህ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ እንደገለጹት በ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግና ቀጣይነቱን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ ጤናውን በራሱ በማምረት ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች በመጠበቀ ጤናው እንዲሻሻል እና የጤና ችግሮች እንዳይከሰቱ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በጓሮው የተለያዩ አትክልቶችና ፍራፍሬዎችን በመትከል በምግብ እራሱን የመቻል እንዲሁም በኢኮኖሚም ረገድ የተሻለ መሆን እንደሚገባ ጭምር ገልጸዋል።
በመጨረሻም ወረዳው ቀበሌዎችን እያስመረቀ የመጣ ቢሆንም በአንድ ቀን 3ቀበሌያትን በማስመረቅ ለህብረተሰቡ እየተሰጠ ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ እንደሆነ እና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለዚህ ተግባር መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት በመስጠትና ለቀበሌያቱ የሞዴልነት ማረጋገጫ ነጭ ባንዲራ በመስቀል ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል።
21/11/2014
ዳሞት ወይዴ

Photos from Damot woyde health office's post 14/07/2022

የግራራ ማዘጋጃ ቀበሌ 18ቱን የሁለተኛ ትውልድ ጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆችን በግለሰብ፣በልማት ቡድን እንዲሁም በተቋማት ተግባራዊ በማድረግ የሞዴል ቀበሌ እውቅና ይሰጠው ዘንድ በተጠየቀው መሰረት በዛሬው ዕለት ከዞን ጤና መምሪያ ባለሙያዎች ቀበሌውን መልሶ ማጣራት በመስራት የሞዴል ቀበሌ እውቅና ሊሰጠው እንደምገባ አረጋግጠዋል።

በፕሮግራሙ ማገባደጅያ ላይ በተቀመጠው ሀገራዊ አቅጣጫ መሠረት የ30-40-30 የአረንጓዴ አሻራ የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

እንኳን ደስ አለን!! አላችሁ!!
ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 09/06/2022

በዳሞት ወይዴ ወረዳ 3ኛ ዙር የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።
የማስጀመሪያ ፕሮግራሙን የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ ታደመ ኤቼ ያስጀመሩ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት ጀምሮ ላሉ ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ከዛሬ ሰኔ 2/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን በትምህርት ቤቶች በጤና ኬላ በመንግስት መ/ቤቶች እንዲሁም በጊዚያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም የዚህን በሽታ ጫና በማህበራዊ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካው የሚያደርሰውን ከፍተኛ ጫና በማሳሰብ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ዕድሜው ከ12 ዓመት ጀምሮ ያለው ክትባቱን መውሰድ እንደሚገባው ገልጸዋል።
የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አድማሱ አበበ የዚህ በሽታ ጉዳቱን በማስቀመጥ እና መከላከል ከምንችለው መንገድ አንዱ ክትባት እንደሆነ በማሳሰብ የኮቪድ ክትባት ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት ጀምሮ ያለ የህብረተሰብ ክፍል መውሰድ እንደሚገባው በመግለጽ ክትባቱ በወረዳው ባሉ በሁሉም ቀበሌያት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የወረዳው ረዳት መንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ታደመ ኤቼ ክትባቱ በይፋ የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮቪድ 19 በሽታ መከላከል ከኔ ከአንቺ ከአንተ ከእናንተ ይጀምራል!!
😷💉💉
በአቅራቢያዎ በሚገኝ የክትባት መስጫ ጣቢያ በመሄድ ይከተቡ!!!
የመከላከል አቅሞን ያዳብሩ!!
02/10/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 08/06/2022

የ3ኛ ዙር ኮቪድ19 ክትባት ዘመቻ ንቅናቄ መድረክ የወረዳ አጠቃላይ አመራር የቀበሌ ሊቀመንበሮች የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህሮች የጤና ኤክስቴንሸን ሰራተኞች የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ትስስር ፎካሎች የክትባት ፎካሎች ከወረዳ ጤና ጽ/ቤት የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
1/10/2014 ዓ.ም
በዴሳ

11/05/2022

*በማይረቡ አሉባልተኞች የወረዳችን የጤናው ተግባር አይደናቀፍም!!!!
በጤናው ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሰብ እየተገነባ ባለበት ወረዳ ይህን አይነት የበሬ ወለደ ወሬ ማሰራጨት የህብረተሰቡን ክብርና ማንነት መናቅ ይሆናል።
ስለዚህ በፌክ አካውንት እራስን ደብቆ ማህበረሰቡን ማወክ አላዋቂነት መሆኑን በመገንዘብ የወረዳችንንም ሆነ የዞን ጤና መምሪያ ተግባርን ማጠልሸት ከጀመርነው የሪፎርም እንቅስቃሴ እንደማያግደን እናረጋግጣለን!!!!

Photos from Damot woyde health office's post 04/05/2022

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ካሉ ጤና ጣቢያዎች መካከል በበዴሳና ኮዮ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በስራቸው ካሉ ጤና ኬላዎች በቶራ ሳዴቦ:ቶራ ኦፎሬ:ማዮ ቆቴ እና ቶራ ውሊሾ እንዲሁም በወረዳ ጤና ጽ/ቤት በተሰሩ የሪፎርም ተግባራት ከቀን 25-26/8/2014 ዓ.ም ድረስ ከክልል ጤና ቢሮ በመጡ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች እንዲሁም ከዞን ጤና መምሪያ ጋር በመሆን ያደረጉት የመልሶ ማረጋገጥ /verification/ በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀዋል።
26/8/2014
ዳ/ወ/ወ/ጤ/ጽ/ቤት
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 01/04/2022

በዛሬው ዕለት በዳሞት ወይዴ ወረዳ ከስሩ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አንዱ በሆነው ኮዮ ጤና ጣቢያ ላይ ጥምረት ለጥራት ግምገማ ተደርጓል ።ይህን ስብሰባ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ጦና በንግግር የከፈቱ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ይህ ጥምረት ለጥራት ውይይት በበላይነት በበዴሳ ጤና ጣቢያ መሪነት እየተደረገ የቆየ ቢሆንም በዚህ ሩብ ዓመት የመሪነቱን ብትር የኮዮ ጤና ጣቢያ በመረከብ እና እያንዳንዱን ተግባር ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በዞን ጤና መምሪያ በተደረገው ranking verfication ባመጣው ውጤትና ከበዴሳ ጤና ጣቢያ በመቀጠል ባስገኘው ውጤት መሰረት ይህንን ጥምረት ለጥራት ግምገማ እንዲያዘጋጅ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም ቀሩት ሁለት ጤና ጣቢያዎችም ተሞክሮን ሼር በማድረግ በቀጣይ ጊዜያት ይህን አይነት ግምገማ ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው አቅጣጫ አስቀምጠው ውይይቱን አስጀምረዋል።በመቀጠልም ሁሉም ጤና ጣቢያዎች የራሳቸውን የሪፎርም ተግባራትን አቅርበዋል።በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ የወረዳው የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ አስራት ወ/ጊዮርጊስ መድረኩን የመሩ ሲሆን በሪፖርቶቹ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።በመጨረሻም በዚህ ግምገማ ላይ የፊት አመራሮች:የጤ/ጽ/ቤት ኃላፊ/ም/ኃላፊ;የማነጅመንት አካላት የሶስቱ ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይ 3ወራት ጤና ጣቢያዎቹ ተግባራቸውን ለቅመው በመስራት በተለይ ሞዴል ቀበሌን በተመለከተ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ በጤና ጣቢያዎች አገልግሎት ላይ ህብረተሰቡ ረክቶ የሚሄድበትን ሁኔታዎች በመዘርጋት ማከናወን እንደሚገባ በመግለጽ የዕለቱን የጥምረት ለጥራት የግምገማ ውይይት ተጠናቅቋል ።
23/7/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 17/02/2022

በዛሬው ዕለት በዳሞት ወይዴ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት የኮቪድ19 ክትባት መሰጠት ተጀምሯል። የዚህ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በበዴሳ ከተማ አዲስ ከተማ ቀበሌ የወረዳው ፊት አመራሮች የጤናው ሴክተር አመራርና ባለሙያዎች በተገኙበት ዘመቻው ተጀምሯል።
የካቲት 10/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 15/02/2022

መመረጥ ተለውጦ ሀገር ለመለወጥ በሚል መሪ ቃል በዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አጠቃላይ የግምገማና ስልጠና መድረክ መካሄድ ተጀምረ።
የካቲት 8/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 03/01/2022

በዛሬው ዕለት በዳ/ወ/ወ/ጤና ጽ/ቤት የ6 ወር PRT ግምገማ
1)የጤና ጽ/ቤት ማኔጅሜንት
2) አጠቃላይ የየክላስተር ሱፔርቫይዘሮች( ደጋፊዎች)
3) የ4ቱም ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ባሉበት
ሀ) በ6 ወር የተከናወኑ መደበኛ ዕቅድ ክንውን (KPI's ጨምሮ)
ለ)መደበኛ የጤና ተቋማት አገ/ት አሰጣጥን በተመለከተ
ሐ) ቅንጅታዊ አሠራርን ማለትም ጤና ጽ/ቤት ከጤና ጣቢያዎች፤ ጤና ጣቢያዎች ከጤና ኬላዎችና community ጋር ያለው) በተመለከተና ወዘተ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ግምገማ ተካሂዷል።
25/04/2014 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 13/12/2021

በዛሬው ዕለት በበዴሳ ካችመንት ከሚገኙ ቀበሌያት መካከል የቶራ ኦፎሬ ቀበሌ በ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ሞዴል መሆኑን ለማረጋገጥ ከዞን ጤና መምሪያ የተወጣጣ ቡድን በመምጣት verification ተሰርቷል። በዚህ የማረጋገጥ ስራ ላይ በልማት ቡድን በቤተሰብ በተቋማት እንዲሁምበጤና ኬላ ደረጃ መረጃዎች እና መሬት ላይ ያለውን ተግባር በሚገባ የታየ ሲሆኖ መስተካከል ባለባቸው ተግባራት ላይ አስተያየት ተሰጥቷል ።የተሰጠውን አስተያየት በመቀበል በተወሰነ ቀን በማስተካከል ቀሌውን ለማስመረቅ የወረዳው ጤና ኃላፊ እንዲሁም የቀበሌው ሊቀመንበር አስተያየት ሰጥተዋል።
4/4/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 29/11/2021

የመሪያችንን ፈለግ በመከተል ድሎችን እናፋጥን በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በዳሞት ወይዴ ጤና ጽ/ቤት ውይይት ተካሂዷል ። በዚህ ውይይት ላይ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አድማሱ አበበ የተዘጋጀውን ሰነድ በንባብ ካሰሙ በኋላ ውይይት እንዲደረግበት መድረኩን ክፍት አድርገዋል።
አስተያየት የሰጡ አካላትም በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ልዩነት እንደማይኖር ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንደሚሰለፉ እንዲሁም ከኛ የሚጠበቀውን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን የሚለውን አቋም በመያዝ ጭምር እንዲሁም በሁሉም ሀይማኖት ተቋማት ጾም ጸሎት ቢታወጅ ሲሉም አስተያየት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም መንግስት በሚፈልገው መንገድ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አካባቢን ነቅቶ ከመጠበቅ በአውደ ውጊያ ላይም በመሳተፍ ልማትን በማፋጠን በሁሉም መልኩ ለሀገራቸው እና ለመንግስታቸው እንደሚያገለግሉ በመግለጽ እንዲሁም ይህ አሸባሪ ጁንታ እና የሱ ሞግዚቶች ግብዓተ መሪት በቅርቡ እንደሚሆን ጭምር በመግለጽ የዕለቱን ውይይት አጠናቀዋል።
ድል ለመከላከያ ሰራዊታችን።!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹💪💪💪
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🙏🙏🙏🙏🙏
20/3/2014

በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 22/11/2021

ለቀጣይ አስር ቀናት የሚሰጠውን የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ የዳሞት ወይዴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማትዮስ ጦና እንዲሁም የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አስራት ወ/ጊዮርጊስ በበዴሳ 01ቀበሌ አስጀምረዋል።

Photos from Damot woyde health office's post 19/11/2021

በዛሬው ዕለት በዳሞት ወይዴ ወረዳ ስር ካሉ ቀበሌያት አንዱ የሆነው የማዮ ቆቴ ቀበሌ በ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በእያንዳንዱ አባወራ እማወራ ደረጃ ተግብሮ በመገኘቱ ሞዴል ሆኖ ተመርቋል።

10/3/2014
በዴሳ

19/11/2021

የኮቪድ 19 በሽታ ለመከላከል በወረዳችን ባሉ ቀበሌያት ሁሉ በጤና ኬላዎች እና በጊዚያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ከህዳር 13-22/2014 ዓ.ም የሚሰጥ በመሆኑ ምንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው ክትባቱን እንዲወስድ እና እየጨመረ የመጣውን የኮቪድ19 በሽታ ወረርሽኝን መከላከል እንዲችል እናሳስባለን።
የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤ/ጽ/ቤት

Photos from Damot woyde health office's post 17/11/2021

በዛሬው ዕለት በዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በሀገር ደረጃ ከ10/03/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 19/3/2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ ዙሪያ ለጤና ጣቢያ ሃላፊዎች ለክትባት ክፍል ፎካሎች ለጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች እንዲሁም ለጽ/ቤት ሱፐርቫይዘሮች ስለ ዘመቻው ኦረንቴሽን ተሰጥቷል። በኦረንቴሽን አሰጣጡ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ይህ ኦረንቴሽን በክላስተር ደረጃ እሰሰከ ጤና ኤክስቴንሽኞች ድረስ በቀጣይ ሁለት ቀናት እንዲወርድ አቅጣጫ ተቀምጧል።
08/03/2014 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 13/11/2021

በኮዮ ጤና ጣቢያ ስር ከሚገኙት ቀበሌዎች የማዮ ቆቴ ቀበሌ 18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችን በመተግበር ሞዴል ለመሆኑ የዞን ጤና መምሪያ የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን verfication አድርጓል። በዚህ መሰረት የተሰጡ አንዳንድ ተግባራት ላይ ማስተካከያ በማድረግ ቀጣይ ላይ ማስመረቅ እንደሚቻል ሀሳብ በመስጠት አጠናቅቀዋል።
በዴሳ 3/3/2014 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 02/11/2021

በአዲስ ምዕራፍ አዲስ አስተሳሰብ በሚል መሪ ቃል በየጤና ጣቢያዎች ውይይት ተደርጓል።

02/11/2021

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በስሩ ባሉት በ4ቱም ጤና ጣቢያዎች የጤና ኤ/ሽን ሰራተኞች የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በተገኙበት በአዲስ ምዕራፍ አዲስ አስተሳሰብ በሚል መሪ ቃል ውይይት ተደርጓል።
በዚህ ውይይት ወቅት በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም በተለይ በሞዴል ቀበሌ በጤና መድህን ሀብት አሰባሰብ በጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም መረጃ አብዮት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ በአብዛኛው በሁሉም ጤና ተቋማት አስተያየት የሰጡ አካላት እንደገለጹት ክላስተሩን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት ተግባራቱን እንደሚመሩ እና ጽ/ቤቱ መደገፍ ባለበት ልክ እንዲደግፍ አንዳንድ ተግባራትን ወደ ኃላ የሚጎትት በተለይ ከግብዓት ጋር በተያያዘ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲመራ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በመጨረሻም ከወረዳ ጽ/ቤት በየጤና ጣቢያ ለማወያየት የሄዱ ባለሙያዎች ስብሰባውን ሲያጠቃልሉ በአዲስ ምዕራፍ አዲስ አስተሳሰብ የሚለው መሪ ቃል ከቃልነቱ ባሻገር በተግባር ሁላችንም በአንድነት በመተባበር እና ተግባራትን በአግባቡ ከመራን ህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚ መድረግ እና በራሱ ጤናውን መጠበቅ እንዲችል የማነደርግበት ምንም ነገር የለም በማለት የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቅቋል።
በአዲስ ምዕራፍ አዲስ አስተሳሰብ!!
በዴሳ
22/2/2014 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 29/10/2021

በዛሬው ዕለት የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ አድማሱ አበበ ከአጠቃላይ የጽ/ቤት ሰራተኞች ጋር በተግባር ;በድጋፍና ክትትል:ከሰራተኞች የስራ ሰዓት መግቢያና መውጫ የጽ/ቤቱን ሚስጥር ከመጠበቅ: በሪፖርት አጠነቃቀርና አላላክ ዙሪያ በሰፊው ውይይት በማድረግ ለቀጣይ እነዚህን ተግባራት መሰራት ባለበት አግባብ ሰራተኛው በሰራዊት መልክ በመጠናከር ህዝባችንን በማገልገል የተሻለ ወረዳ በመፍጠር የጤናው ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት የዕለቱን ውይይት አጠናቅቀዋል።
19/2/2014 ዓ.ም በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 25/10/2021

የዳ/ወ/ወ/ጤ/ጽ/ቤት ከ12/2/2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ባለው nOPV2 ዘመቻ ላይ ከወረዳ ሱፐርቫይዘሮች ጋር የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ወ/ጊዮርጊስ የውሎ ግምገማ አድርገዋል። በዚሁ ግምገማ ላይ በእያንዳንዱ ቀበሌያት ያሉ አፈጻጸም ምን እንደሚመስል እንዲሁም በቤት ለቤት ጉብኝት ላይ ያሉ ከሰፍተቶች በተለይ ቤቶች ላይ ትክክል ማርክ መደረጋቸው በተከተቡ ህጻናት እጅ ላይ ቀለም መቀባታቸውን እንዲሁም የተጎበኙ ቤተሰብ እና የተከተቡ ህጻናት በትክክል ክትባቱን መከተባቸውን በታሊ ሽት ላይ መመዝገቡን ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባ ሌላው ከህጻናት እድገት ክትትል ልኬት ጋር በተያያዘ እየመጣ ያለው ሪፖርት በደንብ መፈተሽና ማየት እንደሚገባ እና ህጻናት በምግብ እጥረት በሽታ ተይዘው እንዳይሰቃዩ ከወዲሁ የልኬቱ ስራ ተጠናክሮ መሰራት እንደሚገባ በዚሁ ልክም እናቶችንም በማየት ከ21cm በታች የሆኑትን ለይቶ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ ሌላው ከዚህ ዘመቻ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰሩ ተግባራትን ለምሳሌ መደበኛ ክትባት:ቲቢ ልየታ የወባ በሽታ መከላከል የኮቪድ መከላከል እንዲሁም ክትባት እንዲወስዱ ወደ ጤና ጣቢያ የመላክ ስራ መሰራት እንዳለበት በመግለጽ ይህን ዘመቻ በጥሩ ሁኔታ በየቀበሌው ለማጠቃለል ሁሉም ሱፐርቫይዘር ሀላፊነት ወስዶ መንቀሳቀስ እንዳለበት በመግለጽ በየቲሙ የተሰሩ አፈጻጸሞች የእስካሁኑ ጥሩ እንደሆነ ከሪፖርቶችም ቤት ለቤት በመሄድም የታየ እንደሆ እና በጉድለት የተገመገሙትም በተለይ ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ከመስጠት አንጻር በአንዳንድ ቀበሌዎች የታየውን በማረም ህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት በአግባቡ አንዲያውቅ መደረግ እንደሚገባ በመግለጽ የዕለቱን ግምገማ አጠናቅቀዋል ።
15/2/2014ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 18/08/2021

እኔ የጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን ነኝ!
በዳ/ወ/ወ/ጤ/ጽ/ቤት ሥር ያሉ የ4ቱም ጤ/ጣቢያዎች አጠቃላይ ሠራተኞች በጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን ከወር ደመወዛቸው ከ20% እስከ 100% መልቀቃቸውን በሙሉ ድምጽ የወሰኑና እንደአስፈላጊነቱ እስከ ሕይወት መሰዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን በተለያዩ የሁለት ቀን በወቅታዊ ውይይት አጀንዳ ላይ አንስተዋል።
ተሳታፊዎቹ ለጀግናው ሠራዊታችን የደም ልገሳ ለማድረግ መወሰናቸውም ታይቷል!
መቼም፣የትም በምንም ለሀገሬ እዘምታለሁ!!!
ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 16/08/2021

"እኔ የጀግናው ሀገር መከላካያ ሠራዊት ደጀን ነኝ።"
በዛሬው ዕለት በዳ/ወ/ወ/ጤ/ጽ/ቤት አጠቃላይ ሠራተኞች በመንግሥት ጥሪ መሠረት ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት ከወር ደመወዛቸው ከ20%አ እስከ 100% ድጋፍ ለማድረግ በሙሉ ድምጽ የወሰነ ሲሆን በውይይቱ በተከታታይ አስተያዬት ሰጪዎች የተስተዋለው አሳብ:-
@ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ የትኛውንም አስፈላጊ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን በማለት
በተጨማሪም ደም ለመለገስም ተስማምቷል።
የትም፣ መቼም በምንም ለሀገሬ እዘምታለሁ!!!!
ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም
በዴሳ

Photos from Damot woyde health office's post 07/08/2021

እንኳን ደስ አላችሁ/ደስ አለን
የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በ2013 ዓ/ም በጤና ትራንስፎርሜሽን
ባስመዘገበው ውጤት በወላይታ ዞን ባሉት በ22 መዋቅሮች ውስጥ በጤና ጽ/
ቤት 1ኛ ፣በጤና ጣቢያዎች በዴሳ ጤና ጣቢያ 1ኛ እና ኮዮ ጤና ጣቢያ 3ኛ
በመውጣት በዛሬው ዕለት ተሸላሚ ሆነዋል።
በወላይታ ዞን ጉታራ አዳራሽ ለሁለት ቀናት በተካሄደው በተግባር አፈፃፀም ግምገማ የዳሞት
ወይዴ ወረዳ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የዋንጫ፣የኮምፕዩተር እና የእውቅና
ሴርትፍከት ሽልማት ተበርክተዋል ።
ለሽልማቱ እንዲበቃ ያደረጋቸው ዋና ዋና ነጥቦች በወረዳና በገጠር ቀበሊያት
በጤና ዘርፍ የተሰጡ ተግባራትን በአግባቡ በማከናወን ነው።
የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ሴክተር ያለፉት ተከታታይ ዓመታት በዞን፤በክልል እና እስከ አገር አቀፍ ደረጃ
ተሸላሚ ሆኖ ቆይቶ በ2013 ዓ/ም ይህን ተግባር በማስቀጠል ባስመዘገበው በጤና ትራንስፎርሜሽን
ተግባራት በዞን ደረጃ ባሉት መዋቅሮች በጤና ጽ/ቤት እና በጤና ጣቢያዎች
መካከል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት ታሪክን በዳግም በማስመዝገቡ
እንኳን ደስ አላችሁ /ደስ አለን።
ቀን 1/12/2013 ዓ/ም
ዳሞት ወይዴ
በዴሳ!!

Photos from Damot woyde health office's post 07/08/2021

በቀን 30/11/2013 በደማቅ ሁኔታ የተጀመረው የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ
የ2013 አመታዊ ማጠቃለያ ጉባኤ የ2ኛ ቀን ውሎን የጀመረ ስሆን ትናንትና
በቀረበው በአፈፃፀም ሰነድ እና በዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሳ ጤና አጠባበቅ
ጣቢያ የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮ ዶክሜንቴሪ ዙሪያ እስከ ምሳ ሰዓት ውይይት
ይደረጋል። ይቀጥላል...

Photos from Damot woyde health office's post 06/08/2021

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የ2013 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና
የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ የሚደረግ የምክክር ጉባኤ ተጀመረ።
፡፡፡፡፡፡፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከ30/11/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የወላይታ ዞን
ጤና መምሪያ የ2013 በጀት ዓመት ማጠቃለያ አፈጻጸም እና 2014 ዓ.ም ዕቅድ
ዙሪያ የሚደረግ የምክክር ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ በታላቁ ጉታራ አዳራሽ
መካሄድ ጀምሯል።
የእለቱ ክብር እንገዳ እና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ
ጉባኤው መክፈቻ ላይ ጤንነቱ የተጠበቀ ግለሰብ፣ ቤተሰብ እና ማህበረሰብ
ለሀገር እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የጤናው
ሴክተር ቁልፍ የማህበራዊ ዘርፍ እንደመሆኑ የጤና ሥራዎች በየደረጃው
በአመራሩ፣ በሴቶች አደረጃጀት፣ በአጋሮች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር
በቅንጅት እየተመራ መቆቱን በመግለጽ በቀጣይም ቅንጅቱ ተጠናክሮ መቀጠል
ይገባል ብለዋል ።
የእናቶችና ህጻናት ጤና ከማሻሻልና አገልግሎቶችንም ተደራሽ ከማድረግ አንፃር
ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው ነገር ግን አገልግሎቱ በሁሉም ደረጃ
በጥራት ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታወችን በተለይም ወባን ከመከላከል አንፃር ከዞን
ጀምሮ እስከ ወረዳ እና ጤና ኬላዎች ድረስ ብርቱ ጥረቶች በመደረጋቸው
ልከሰት የምችለውን ጫና መከላከል እንደተቻለ ጠቁመው በቀጣይም
የመከላከሉ ስራ በህብረተሰብ ንቅናቄ ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል ብለዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቨድ 19 ወረርሽኝ ጫና ለመቋቋም
በሚደረግ ጥረት ከጤና ኬላ እስከ ሆስፒታል ድረስ ጤና ባለሙያቸው ውድ
ህይወታቸው ሳይሰስቱ በሽታውን በመከላከል እና በማከም ታሪክ የምዘክረውን
ገድል እየፈፀሙ የሚገኙ በመሆናቸው በዞን አስተዳደር እና በዞኑ ህዝብ ስም
ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በ2013 በጀት ዓመት በትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በተቀመጡ ዋና ዋና የትኩረት
መስኮችና ግቦች መነሻ የመሠረታዊ ጤና አገልግሎቶች መርሆዎችን መነሻ
በማድረግ ህብረተሰቡን አሳታፊ ያደረገ፣ ዘላቂነት ያለው፣ ጥራቱን የጠበቀ እና
ፍትሀዊ የሆነ የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ
መመራቱን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ገልጸዋል።
የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነው ኮቭድ- 19 ተጽኖን በመቋቋም መሠረታዊ የጤና
አገልግሎት ለህብረተሰቡ ሳይቆራረጥ ተደራሽ ለማድረግ በተደረገው ጥረት
ሞዴል ቀበሌያትን ከማፍራት፣ የማዐጤመ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ፣
በእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ
በሽታዎችን ጫና ከመቀልበስ አንጻር ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን ነው
የመምሪያ ሀላፊ የገለጹት።
በበጀት ዓመት በርካታ ውጤት የተመዘገቡ ቢሆንም በሆስፒታሎች፣ ጤና
ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመድሀኒትና
ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የአቅርቦት እና
የስነምግባር ችግሮች እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓት ጠንካራ ያለመሆን በዋናነት
የሚጠቀሱ ውስንነቶች መሆናቸውን በመግለጽ የጉባኤ ተሳታፊዎች አፈጻጸሙን
በጥልቀት ገምገሞ ክፍተቶችን በመለየት ለ2014 ዓ.ም አቅጣጫ ልያስቀምጥ
ይገባል ብለዋል።
በጉባኤው የ2013 ዕቅድ አፈጻጻም፣ የ2014 ዕቅድ እንዲሁም የላቀ አፈጻጸም
ላስመዘገቡት መዋቅሮች እና ከዞን ጤና መምሪያ በጡረታ ለተገለሉ ሠራተኞች
የእውቅናና ምስክር ወረቀት በመስጠት ጉባኤው ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Photos from Damot woyde health office's post 26/07/2021

ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የእውቅና ምስክር ወረቀት
እና ዋንጫ ሽልማት ተበረከተ።
የጤና ባለሙያዎች እና የጤና ክብካቤ ሠራተኞች ሀገር አቀፍ የምስጋናና
የእውቅና ፕሮግራም ማጠቃለያ ላይ በወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ስር የሚገኙ
ጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ክብካቤ ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የኮቭድ-19
ወርሽኝ በመከላከል እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን
በማስቀጠል ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ምስክር ወረቀት እና ዋንጫ
ሽልማት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አበርክቷል።
የኮቭድ-19 ወረርሽን በክልላችን ሆነ በዞናችን ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ጤና
ባለሙያዎች፣ ጤና ክብካቤ ሰራተኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሽታውን
በመከላከል እና በመቆጣጠር ያደረጉት አስተዋጽኦ መቼም ሊዘነጋ አይገባም
ያሉት የዞኑ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በቀጣይም ጤና
ባለሙያው እና ጤና ክብካቤ ሠራተኞች ምንም ዓይነት ፈተናዎች ቢያጋጥምም
እንኳ ሙያዊ ስነምግባር በተላበሰ ሁኔታ ህዝባቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉ
ከዚሁ ትምህርት መወሰድ ይገባል ብለዋል።

Photos from Wolayta Zone Health Department /ወላይታ ዞን ጤና መምሪያ's post 08/07/2021
Photos from Damot woyde health office's post 02/07/2021

በዛሬው ዕለት በቀን 25/10/2013 ዓ.ም በዳ/ወ/ወረዳ ቶራ ሳዴቦ ቀበሌ በ18ቱ ጤና ኤክ/ሽን ፓኬጅ ዙሪያ ሞዴል የማድረግ ሥራን ለማጣራት የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ አጣሪ ቡድን በጥልቀት verify ያደረገ ሲሆን ከልማት ቡድን መሪ ቤት ጀምሮ እስከ ግለሰብ ቤት ድረስ እንዲሁም በተቋማት ደረጃም በአጠቃላይ በ4ቱ የሞዴል ቀበሌ መስፈርቶች መነሻ የተሻለ አፈጻጸም እንዳለው በመግባባት መመረቅ ም እንደሚችል በመግለጽ የዕለቱ ውይይት ተጠቃልሏል።

Photos from Damot woyde health office's post 15/06/2021

ወርዶ በመደገፍ፤ ስቦ በመገምገም እና ተመጣጣኝ ግብረ-መልስ በመስጠት የጤና ተቋማትን አቅም እንገንባ!!!
በዛሬው ዕለት በቀን 08/10/2013 ዓ.ም ዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት የ2013 በጀት ዓመት የ11 ወራት አፈጻጸምን የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፤ የጽ/ቤቱ ቴክኒካል ስታፍና የየክላስተር ደጋፊ ባለሙያዎች ባሉበት ሲገመግም ውሏል።
የግምገማወን መድረክ የመሩት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊና የበ/መ/ጤ/ማ/ሥ/ሂደት አስተባባሪ አቶ አድማሱ አበበ ሲሆኑ የግምገማውን ዋና ትኩረት መስኩ የ11 ወሩ አጠቃላይ አፈጻጸምና የመጨረሻዋ ወር ቀሪ ቀናት አጭር ድርጊት መርሓ-ግብር በማዘጋጀት ነበር። በውይይቱም ላይ የ11 ወር የ4ቱም ጤና ጣቢያዎች ሪፖርት በል/ዕቅድ ባለሙያ በአቶ ክፍሌ ላሽኮ በኩል በተደራጀ ሁኔታ ቀርቧል።
ከpresentation በኋላ የውይይቱ ዋና አጀንዳዎች የነበሩ:-
1) የሪፎርም ተግባራት/EHCRIG/ ያለበት ደረጃ
2)ቁልፍ ዋና ዋና ተግባራት/KPIs/
3)የሞደል ቀበሌያት ያሉበትን ደረጃ
4)የመረጃ አቢዮት ሥራን በተመለከተ
5)የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ
6)NCD and NTD ተግባራትን ለቅሞ የመስራትን
7) ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ነበር። በተጨማሪም የጤና ተቋማት ድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስም በአጭሩ ቀርቧል። ስለሆነም በቀረቡ ሪፖርት ላይ የጋራ አቋም በመያዝ ለአጭር ቀናት ወሳኝ አጭር ድርጊት መርሓ ግብርን በመፈራረም ግምገማው በዚሁ ተጠቃልሏል።

Photos from Damot woyde health office's post 19/05/2021

በዛሬው ዕለት ቀን 11/9/2013 ዓ.ም ዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ከ22ቱ ቀበሌ ጤ/ኤክ/ኖች፤ ጤ/ጣቢያና ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች፤ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፤ከጽ/ቤቱ ማኔጅሜንትና ሠራተኞች በተገኙበት ወቅታዊ የወባ በሽታ መከ/መቆጣጠር ሥራ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡
በንቅናቄ መድረክ ላይ የወረዳው ዋና አስ/ሪ አቶ ማንደፍሮ ግርማ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ የበልግ ዝናብ መቆራረጥ መነሻ የሚከሰተውን የወባ በሽታ ስርጭት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የመጨመር አዝማሚያ ስለሚኖር 4ቱ የመከላከል መንገዶችን ማጠናከሮ፤ የበልግ ዝናብ መዘግየት ምክንያት በምግብ እጥረት ተጎጂ ቤተሰብና ከ5 ዓመት በታች ሕጻናት ልየታና ሕክምና፤ ሞዴል ቀበሌ(አዲስና ፌስቲቫል) ሥራ ማጠናከር፤ በየጤና ተቌማት የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲጠናከር ወ.ዘ.ተ በተመለከተ የወረዳው የፖለቲካ አመራርም የማይለሳለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አጥብቀው ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ መድረክ የሴክተሩ የ10 ወር አጠቃላይ ሪፖርትም ቀርቦ በማጠቀለያ የወረዳው ም/አስ/ሪና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሥራት ወ/ጊዮርግስ እንዲሁም ም/ጽ/ቤት ኃላፊና በ/መ/ጤ/ማ/ዳ አስተባባሪ አቶ አድማሱ አበበ በመሩበት ጥልቀት ያለው ግምገማ ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም
1)የጤና ልማት ሠራዊት በማጠናከር የወባ መከ /መቆጣጠርናየምግብ እጥረት ተጎጂዎችን መለየትና ማከም
2)የTb ተጠርጣሪዎች Referral ማጠናከር
3)ሞዴል ቀበሌ ጉዳይም ተያያዥ ተግባር እንደሆነ ወ.ዘ.ተ በማሳሰብ ተጠቃልሏል፡፡
ዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት
በዴሳ
11/9/2013 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 05/05/2021

የሰውን ሕይወትን ከግዜ ወደ ግዜ እየቀጠፈ የመጣውን Covid-19 ዓለም-ዐቀፋዊ ወረርሽኙን በጋራ እንከላከል፤ የአዋጅ መመሪያውንም በጋራ እንተገብር!!
በዛሬው ዕለት በቀን 27/8/2013 ዓ.ም ከተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የኮቪድ 19 የመከላከል ግብረ-ኃይል ውይይት አድርጔል፡፡
በመድረኩ ላይ የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የጤ/ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሥራት ወ/ጊዮርግስ(የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢ) ውይይቱን የመሩ ሲሆን የፀጥታና የህግ ማዕቀፍ አካላትም ተሳትፈውበታል፡፡
ሁሉም ተሳታፊ ቀጥሎ ስለሚሠሩት ሥራ በጥልቀት ተወያይተው አጭር ድርጊት መርሐ-ግብርንም በማውጣት ተለያይተዋል::

Photos from Damot woyde health office's post 30/04/2021

በጤናው ሴክተር የተጀመሩ ጤናማና ምርታማ ዜጋ ተፈጥሮ የማየት ራዕይ ሞዴል ቀበሌን በመፍጠር ይረጋገጣል!!
በዛሬው ዕለት ቀን21/8/2013 ዓ.ም በዳ/ወ/ወረዳ ጋልቻ ሣኬ ቀበሌ በ2ኛው ትውልድ ጤ/ኤ/ሽን ፕሮግራም በየደረጃው ያሉ ግለሰቦችና ተቌማት በስታንዳርዱ መሠረት ሞዴል ሆኖ ተመርቌል፡፡
የተከበሩ አቶ ዮሐንስ በየነ የወላይታ ዞን ብ/ፓርቲ ፖለቲካና ርዮተዓለም ዘርፍ ኃላፊ፤ የተከበሩ አቶ አሳምነው አይዛ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና ማኔጅሜንቶቹ፤ የተከበሩ አቶ ማንደፍሮ ግርማ የዳ/ወ/ወ/ዋና አስተዳዳሪና የወረዳው የፊት አመራሮች፤ የጤናው ሴክተር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ባሉበት ይህ የማህበረሰብ ጤና በተጨባጭ የሚረጋገጥበት ደማቅ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
በዕለቱም ከላይ የተጠቀሱ ክቡር እንግዳዎች ጠለቅ ያለ መልዕት ለተሰበሰባው ቀበሌ ማ/ሰብ በማስተላለፍ
ተጠናቅቌል፡፡
የዜጎች ጤና ለሀገር ብልፅግና!!

Photos from Damot woyde health office's post 02/04/2021

በዳሞት ወይዴ ጤና ጽ/ቤት እና በ4ቱ ጤና ጣቢያዎች የCovid 19 Vaccine ለጤና ባለሙያዎች እና ለአስተዳደር ሰራተኞች እየተሰጠ ይገኛል።

Photos from Damot woyde health office's post 12/03/2021

ወቅታዊ በሆነ የተግባር አፈጻጸም ግምገማ የጤናው ሴክተር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ እውን እናደርግ!!
በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 03/07/2013 ዓ.ም የዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት የጤ/ተቌማት የበጀት ዓመቱ ደ8 ወር ተግባር አፈጻጸምና በባለፉት የተሠራውን የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ-መልስን የጤ/ጣቢያ ኃላፊዎች፤ የጤ/ጣቢያና ጤ/ኬላ ትስስር ፎካሎች፤የጽ/ቤቱ ማኔጅሜንትና አጠቃላይ ሠራተኞች ቦታ ገምግሟል፡፡
የዕለቱን ግምገማውን የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የጤ/ጽቤቱ ዋና ኃላፊ አቶ አሥራት ወ/ጊዮርግስ በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት ሲሆን ቀጥሎ የሁሉም ተቌማት ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጔል፡፡
በሪፖርቱ መነሻነት በጉድለት የተገመገሙ ተግባራትን በቀጣይ ወራት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ አጭር ድርጊት መርሐ-ግብር በማዘጋጀት የዕለቱ ግምገማው በዛሁ ተጠቃልሏል፡፡

Photos from Damot woyde health office's post 10/03/2021

በበዴሳ ክላስተር በቢልቦ በዴሳ ቀበሌ በወረዳ ጤና ጽ/ቤት በዛሬው ቀን የተወጣጣ ቡድን የፊስቲባል ቅድመ ማጣሪያ በማድረግ የቀበሌ አመራር:የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ባሉበት ግብረ መልስ ተሰጥቷል።

Photos from Damot woyde health office's post 09/03/2021

በተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትልና ችግር ፈቺ በሆነ ግብር መልስ የወረዳችን የጤና ተቌማት ህልውና በማስጠበቅ የበኩላችንን ሚና እንወጣ!!
በዛሬው ዕለት ማለትም ቀን 30/6/2013 ዓ.ም የዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ተክኒክ ኮሚቴ በተከታታይ 4 ቀናት በ4ቱም ጤ/ጣቢያዎች Randomly በተመረጡ ጤና ኬላዎች እስከ ማህበረሰብ ደረጃ(ቤት ለቤት) የተደረገውን ሣምንታዊ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስን ገምግሟል፡፡
በግምግማው ላይ የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊና የበ/መ/ጤ/ማ/ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አድማሱ አበበ ተክኒክ ኮሚቴ ግብረ-መልስ መነሻነት፡-
1)የጤና ል/ሠራዊት አደረጃጀትና አሁናዊ ተግባራዊነት(Current functionality)
2)የጤና ተቌማት አገ/ት አሠጣጥ CRC አተገባበር ያለበት ደረጃ
3)ቀበሌዎችን በጤና ሞዴል ማድረግና ሞዴል የሆኑ ቀበሌዎች ዳግም ልደት(Festival cermonies) ያለበትን ደረጃ
4)የመረጃ አቢዮት ሥርዓት ያለበት ደረጃ
5)ቀጣይ አቅጣጫንም በማስቀመጥ
ወ.ዘ.ተ መነሻ በማድረግ በጥልቀት ገምግሟል፡፡
በግብረ-መልስ ግምገማው ላይ የተሣፉ ተክኒክ ኮሚቴ ጠንካራና መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮችን ቆጥሮ በመያዝ ጤ/ተቌማትን በቅርበት በመደገፍና በመከታተል የማህበረሰባችን የጤና ባለቤት ለማድረግ በመስማማት የዕለቱ ውይይት ተጠቃልሏል፡፡
በጤና ዘርፍ የተያዙ አጀንዳዎች በብልፅግና እውን ይሆናል!!!!!!

Photos from Damot woyde health office's post 08/12/2020
Photos from Damot woyde health office's post 08/12/2020

ለገጠር የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች:ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች እና ጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች በማህበረሰብ ጤና መረጃ ስርዓት ላይ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።ይህን ስልጠና በይፋ ያስጀመሩት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ወ/ጊዮርጊስ ሲናገሩ ይህ ስልጠና ለመስጠት ያስፈለገበት ዋና ዓላማ የተሰሩ ተግባራት በአግባቡ በመዝገብ በካርድ ተሞልቶ ሪፖርት መደረግእንደሚገባ እንዲሁም የተሰጠ አገልግሎት ከመረጃ ጋር በማገናኘት በመረጀ አብዮት ሞዴል ሆኖ መገኘት እንደሚገባ በመግለጽ ለተከታታይ 4ቀን የሚሰጠውን የማህበረሰብ ጤና መረጃ ስርዓት/CHIS/ስልጠና በይፋ ከፍተዋል። ህዳር 29/2013 ዓ.ም

Photos from Damot woyde health office's post 13/11/2020

በዛሬው ዕለት የዳ/ወ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ ቤት አጠቃላይ ሠራተኞች መንግስታችን ህግን ለማስከበርና ሀገርንና ህዝብን ለመታደግ በህገ ወጡ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍና ከመንግስታችን ጎን በመሠለፍ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ውይይት አድርጔል::
በመሆኑም መንግስት ከረጅም ትዕግስቱ በኃላ የቀይ መስመር ያለፈውን የስልጣን ጥመኛው ሕወኣት አማጺ ቡድንና የጡት ነካሽ ጁንታ ቡድን በሰመን ዕዝ መከላከያ ኃይል ላይ ያደረሰውን ጥቃት የመመከት እርምጃ እየወሰደ ያለዉን ለመደገፍ በቂ ምክንያት ይኖራል በማለት እርምጃዉ ግን የቂም በቀል ሳይሆን ህግን የማስከበርና የሕዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ነዉ ብሏል፡፡
ስለሆነም የጤና መዋቅሩ አጠቃላይ ሠራተኞች በመንግስት ጎን እንዲቆሙና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ በማስተላለፍ ወቅታዊ መደበኛ ተግባራችንንም በኃላፊነት እንድንወጣ በማለት ሁሉም የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀረበው አጀንዳ ላይ አስተያየት በመስጠት በመንግስት ጎን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

Website