Offa Woreda Administration

Offa Woreda Administration

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Offa Woreda Administration, Public Figure, .

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/07/2024

ለመላው ወላይታ ዞን አመራሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ባለሀብቶች፣ ንግድ ማህበረሰቦች በሙሉ፦

እስካሁን በወንድም ጎፋ ህዝብ ላይ ለደረሰው ድንገተኛና ልብ በሚሰብር አደጋ እያደረጋችሁ ላላችሁ በጎ ምላሽ የወላይታ ዞን አስተዳደር የላቀ ምስጋና ያቀርባል።

በመቀጠል ከዓይነት ድጋፍ በተጨማሪ መላው ህዝባችን በተደራጀ ተሳትፎ የሚያደርግበት ህጋዊ አካውንት

CBE 1000641435318

ስለሆነ ሁላችንም በፍጥነት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ትብብራችንን እናጠናክር!
ለወገን ደራሽ ወገን ነውና!

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/07/2024

የኦፋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አዲሱ ወርቁ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳና መደርመስ ምክኒያት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው በዚህ አደጋ የማህበረሰባቸውን አባላት ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ላጡ ወገኖች እንዲሁም ለመላው ህዝብና መንግስት መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በምንችለው ሁሉ ከጎናችሁ የምንቆም መሆኑን ላረጋግጥ እወዳለሁ ሲሉም ገልፀዋል፡፡

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/07/2024

የኦፋ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ዴማ ኃይሌ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ለሞቱት ወጎኖች የተሰማቸውን ልባዊ ሐዘን ገልፀዋል ።

በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ የሚያሳዝንና ልብ የሚሰብር ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን በማለት ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ለጎፋ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

በድጋሚ መፅናናትን ተመኝተው የወረዳው መንግሥት ሁሌም ከተጎጂዎች ጎን እንደሚሆን ገልፀዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 22/07/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ምሁራን ለአብሮነትና ለሰላም እሴት ግንባታ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

ኦፋ፣ ሐምሌ 15/2016:- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ምሁራን ለአብሮነትና ለሰላም እሴት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ አስገነዘቡ።

የክልሉ መንግሥት ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ ምሁራን ጋር በሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ እየመከረ ነው።

አቶ አለማየሁ በመድረኩ ላይ እንዳስገነዘቡት ምሁራን አብሮነትን የሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶችን በመገንባት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ማጎልበት ይጠበቅባቸዋል።

በተለይ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በሚከናወኑ ሥራዎች ውስጥ ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው በዞኑ ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ የምሁራን ሚና ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በመሆኑም ምሁራን በሁሉም መስኮች ገንቢ ሀሳቦችን በማፍለቅና ችግር ፈቺ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለአካባቢው ዘላቂ ሰላምና ልማት የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

ምሁራኑ በቅርቡ የተመሰረተውን የአሪ ዞንን የሰላምና የአብሮነት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት በተለያየ መንገድ እንዲያግዙም ጠይቀዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሰላም ሚኒስቴር አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና ምሁራን ታድመዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 22/07/2024

"አመራሩ ተግባርን አቀናጅቶ በመምራት በሁሉም የትኩረት መስኮች ውጤት በማስመዝገብ ሊሰራ ይገባል" ፦ አቶ አዲሱ ወርቁ

ኦፋ፤ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ሳምንታዊ የተግባር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አጠቃላይ አመራር በተገኙበት ተካሂዷል።

ሳምንታዊ ግምገማ መድረክ በዋናነትም የፈፃሚ መድረክ አፈፃፀም ፤ የክረምት በጎ ተግባራት ፣ የገቢ አሰባሰብ፣ የመኸር ሥራዎች፣ የትራንስፎርሜሽን ተግባራት አፈፃፀም እና በሌሎች ተግባሮች በተዘጋጀ ግብረመልስ ላይ ነው።

በመድረኩ የኦፋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ወርቁ እያንዳንዱን ተልዕኮ ወደ ሕዝብ የምናወርደው ከሕዝብ ተጠቃሚነት አኳያ መሆኑን ገልጸዉ አመራሩ በተሰጠው ስምሪት ራሱን በማዘጋጀት ለውጤት መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ብልፅግና ዕሳቤ በመፍጠንና በመፍጠር ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት ይጠበቃል ያሉት አቶ አዲሱ አመራሩ ችግር ፈቺ ድጋፍ በማድረግ ለሁሉ-አቀፍ ለውጥ ርብርቡን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለው የሃይማኖት ተቋማት ፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች፣ ባለሃብቶችን በማስተባበር በክረምት ወራት መከናወን የሚገባቸውን በጎ ተግባራትን ያሉበት ደረጃ በጥልቀት ገምግሞ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል ።

ግብርና የህዝባችን የጀርባ አጥንት መሆኑን በመግለጽ በመኸር አፈፃፀም የተሻለ ምርት በማምረት የምግብ ዋስትናችንን በማረጋገጥ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ቁልፍ ተግባር ነው ብለዋል።

አያይዘው ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት የሚውል አቅም በመፍጠር ለገቢ አሰባሰብ ሥራ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል ።

የኦፋ ወረዳ ም/አሰተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዘኻኝ ጌታቸው በበኩላቸው ሁሉንም የትራንስፎርሜሽን ተግባራትን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ የተፈለገውን ግብ ለማሳካት የባለድርሻው ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

በመኸር ላይ የተሻለ ምርትና ምርታማነት ለማስመዝገብ አርሶ አደሩን በቅርበት በመከታተል በመኽር እርሻ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ስጥተዋል።

አክለው በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሁሉም ህብረተሰብ በነቂስ በመውጣት በወጣቶች አደረጃጀት ፣ በሴቶች አደረጃጃት አጠናክረው ለወገናቸው ያላቸውን አለኝታነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የኦፋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ወርቁ፣ የኦፋ ወረዳ ም/አሰተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዘኻኝ ጌታቸው ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት እንዲሁም አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 20/07/2024

የኮሬ ዞን ወጣቶች ሊግ #በጎነትለአብሮነት በሚል መሪ ቃል ከዞን ወደ ዞን የበጎ ፈቃድ ስራዎች እና ወጣት ለወጣት ግንኙነት ለማጠናከር ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ ገቡ።

ኦፋ፡ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም የኮሬ ዞን ወጣቶች ሊግ "በጎነትለአብሮነት በሚል መሪ ቃል ከዞን ወደ ዞን የበጎ ፈቃድ ስራዎች እና ወጣት ለወጣት ግንኙነት ለማጠናከር ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ ገብተዋል።

ወጣቶቹ ወደ ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ ስገቡ የቡርጂ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አካሉ ሳሙኤል የቡርጂ ዞን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ጨምሮ ለሎች አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

የኮሬ ዞን ወጣቶች ከቡርጂ ዞን ወጣቶች ጋር በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሠሩና የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል።

መርሃግብሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርቅነህ ጌታሁን፣ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሴይ ይርጉን ጨምሮ የወጣቶች አደረጃጀት አመራሮች ተገኝተዋል

Photos from Offa Woreda Administration's post 20/07/2024

የኢትዮ- ጣሊያን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፎረም በሚላን-ጣሊያን ከተማ እ.አ.አ ጁላይ 18-19 /2024 ተካሂዷል፡፡

ፎረሙ በሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት በሁለቱ ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ታስቦ በሮም በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተዘጋጀ ነዉ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በፎረሙ ላይ ለተገኙ ለጣሊያን ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እድልና አማራጮችን፣ የፖሊሲ እና ህግ ማሻሻያዎችን፣ ማበረታቻዎችንና አዲስ ለዉጭ ባለሀብቶች የተከፈተ የንግድ ዘርፎችን አስመልክቶ ዝርዝር ገለጻ አድርጓል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት የመጡ ባለሃብቶች እና የተቋማት ሀላፊዎች የአንድ ለአንድ ምክክር በማድረግ በጋራ ለመስራት እርስበርስ ልምድ እንዲለዋወጡ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ኩባንያዎችን በአካል ጉብኝት በማድረግ ኢትዮጵያ ገብቶ ኢንዲያለሙ ግብዣ የማቅረብ ሥራ ተሰርቷል፡፡መረጃው የኮሚሽኑ ኮሙኒኬሽን

Photos from Offa Woreda Administration's post 20/07/2024

ክልላዊ የሴቶች ሊግ የሌማት ትሩፋትና የክረምት በጎ ተግባራት የማቀጣጠያ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀመረ

ኦፋ፤ሐምሌ 13/2016 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ቅ/ጽ/ቤት የሌማት ትሩፋትና የክረምት በጎ ተግባራት የማቀጣጠያ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

"በጎነት ለእህትማማችነት፣ ለትውልድ ግንባታና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ ክልላዊ የሴቶች ሊግ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

እንደክልል ከ600 ሺ በላይ ሴቶች በክረምቱ በፓርቲና መንግስት ከተለዩ የንቅናቄ አጀንዳዎች መካከል 7ቱ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ሴቶች በሌማት ትሩፋት፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት የሴቶች ተሳትፎ ለማጎልበት፣ የአረጋውያን ቤት ግንባታና ዕደሳ እንዲሁም የአከባቢ ፅዳትና የሰላም ግንባታ ላይ እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የክልሉ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ አባልና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ህሊና መብራቱ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ፣ የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤልን ጨምሮ የክልሉና የሁሉም ዞኖች ሴት አመራሮች እየተሳተፉ ናቸው።

Photos from Offa Woreda Administration's post 20/07/2024

"በዘንድሮው መኸር በሁሉም የሰብል አይነቶች መሬት ፆም እንዳያድር አሟጠን መጠቀም አለብን"- አቶ አለማየሁ ባዉዲ

ኦፋ፣ ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም፦ "ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ለብልፅግና ራዕይ ስኬት" በሚል መሪ ቃል የ 2016 ክልላዊ የመኸር አዝመራ ዕቅድ ግቦችና የፈፃሚ ዝግጅት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በንቅናቄው የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ክልሉ ከራስ አልፎ ለሀገር የሚበቃ የግብርና ፀጋዎች ያሉት ክልል መሆኑን ተናግረዋል።

ዓምና በነበሩ የሽግግር ስራዎች በተለያዩ ስራዎች የመጠመድ ሁኔታ እንደነበር የጠቀሱት ኃላፊዉ በዘንድሮው መኸር ምንም አይነት ምክንያት ሳያበጁ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ያሉ የፖለቲካና የግብርና አመራሮች ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ቁመና ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበዋል።

በሀገር ደረጃ ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመረው ስራ በዘንድሮው መኸር ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን አመልክተው ልመናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት የግለሰብ እና የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ሁለንተናዊ ለብልፅግናን መፍጠር እንደሚቻል አስረድተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃ/ማርያም ተስፋዬ ክልሉ በአዲስ መልክ መደራጀቱን ተከትሎ የሰላም፣ የልማትና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

ክልሉ ሰፊ ለም መሬት፣ የከርሰና ገፀ ምድር ዉሃ፣ አምራች የሰው ኃይል የሚገኝበት ክልል መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ግብርና የምግብ ሰብል፣ የዉጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ ከፍተኛው የስራ ዕድል የሚፈጠርበት በአጠቃላይ የኢኮኖሚ መሠረት በመሆኑ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ግብርና ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ መሆን እንደሚገባው የጠቀሱት አቶ ኃ/ማርያም ቴክኖሎጂን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ በክላስተር በማምረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

አምና በተከናወነው የመኸር እርሻ 140 ሚሊዮን ኩንታል ምርት በአዝርእትና ሆርቲካልቸር ሰብሎች መገኘቱን ጠቅሰው በተያዘው በልግም 1.7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት በክልሉ 15 በመቶ የግብርና ዕድገት ለማስመዝገብ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፓርቲና መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የመንግስት ተጠሪዎች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጠንክር ጠንጋ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 16/07/2024

በ2015/16 የምርት ዘመን በመኸር፣ በመስኖና በበልግ ከ139 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መመዝገቡን የክልሉ የግብርና ቢሮ አስታወቀ

ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም፦ የእርሻ ልማት ዘርፍ በምርት ዘመኑ ተጨባጭ ውጤት ከተመዘገበባቸው የግብርና ትኩረቶች መካከል ቀዳሚው መሆኑ ተመልክቷል።

በክልሉ በምርት ዘመኑ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሲተገበሩ ከቆዩ የትኩረት መስኮች መካከል የእርሻ ልማት ሥራዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በ2015/16 የተከናወኑ የመኸር አዝመራ ማጠናቀቅ፣ የ2016 የበጋ መስኖና የበልግ አዝመራ ዕቅዶችን ማሳካትን ጨምሮ የመኸር አዝመራን መተግበር በዘርፉ ግብ ከተቀመጠላቸው የትኩረት መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ በ2015/16 የምርት ዘመን የእርሻ ልማት ዘርፍ ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ መረጃ ሰጥተዋል።

ምክትል የቢሮ ኃላፊው በእርሻ ልማት ዘርፍ በምርት ዘመኑ በ2015 የመኸር አዝመራ 752 ሺህ 447 ሔክታር መሬት በዘር በመሸፈን 52 ሚሊየን 334 ሺህ 468 ኩንታል ምርት መመዝገቡ እንደ መነሻነት መወሰዱን አንስተዋል።

በበጋ የመስኖ ልማት ተግባራት ስንዴን ጨምሮ ለማምረት በተያዘው ዕቅድ በተሠሩ ተግባራት ከ27 ሚሊየን በላይ ምርት ለማምረት መቻሉም ተመልክቷል።

የመኸር አዝመራ መጠናቀቁን ተከትሎ "በአዲሱ ክልል፣ በአዲስ ዕሳቤ ወደ አዲስ ምዕራፍ!" በሚል መሪ ቃል በዲላ ዲክላሬሽን ከተጠቀሱ 11 ነጥቦች መካከል አንዱ የመስኖ ልማትን ማስፋፋትና ማጠናከር እንደሚጠቀስ ተብራርቶ ወደ ትግበራ ተገብቶ ስንዴን ጨምሮ በልዩ የሆርቲ ካልቸር ሰብሎች ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገ ርብርብ ዕቅዱን ለማሳካት መሠራቱን አቶ አድማሱ አስታውሰዋል።

የበልግ አዝመራ በልዩ ትኩረት ታቅዶ የተተገበረ እንደነበር ያስታወሱት ምክትል የቢሮ ኃላፊው ዕቅዱን ተፈፃሚ ለማድረግ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ብቻ ሳይሆን ወቅቱንና ስርጭቱን ጠብቆ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የጣለው ዝናብ የስኬት በር መክፈቱን አመልክተው በሁሉም ሰብሎች ከ60 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት መቻሉን አስረድተዋል።

የበልግ አዝመራው በተገቢ ድጋፍና ክትትል ተፈፃሚ መደረጉን የጠቀሱት ምክትል የቢሮ ኃላፊው በምርት ዘመኑ በእርሻ ልማት ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሆርቲካልቸር ሰብሎች ቀትኩረት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የተጀመረውን የግብርና ልማት ዕድገት ለማስቀጠል ቢሮው ከምንጊዜውም በላቀ ዝግጅትና የአመራር ቁርጠኝነት ለማስፈፀም እንደሚተጋ መገለፁን የግብርና ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 08/07/2024

የኦፋ ወረዳ የ2016 የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ጉዞ ጀምረዋል።

ኦፋ፤ ሐምሌ 1/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ የ2016 የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ጉዞ ጀምረዋል።

በዘንድሮው ዓመት በወረዳችን ዉሰጥ የ12ተኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች 341 የማህበራዊ ሳይንስ መሆናቸው ከወረዳው ት/ት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ውድ ተማሪዎቻችን በሰላም ወደ ተመደባችሁባቸው ተቋማት ደርሳችሁ በሰላም እና በስኬት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና አጠናቃችሁ እንድትመለሱ እንመኝለን።

ተማሪዎቻችን በሠላም ጀምራቹ በሠላም እንድታጠናቅቁና በጥሩ ዉጤት ታጅባቹ በድል ተመለሱ!!

07/07/2024

👉በተያዘዉ ክረምት በልዩ ንቅናቄ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ገቢ አሰባሰብ ቀዳሚዉ ነዉ።

👉በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች ገቢ አሰባሰብ ከ ሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚቀጥሉት 7 ተከታታይ ቀናት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ይካሄዳል።

👉በክልሉ 112 ሺ 448 የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች ሲኖሩ ለተከታታይ 7 ቀናት በሚካሄደው የገቢ አሰባሰብ ከ 500 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል።

👉ለዚህም በክልሉ የሚገኙ 138 የታክስ ማዕከላትን ጨምሮ 50 ተጨማሪ ማዕከላት በመክፈት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል።

👉በዘንድሮው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሉ የሚገኙ ከ 30 ሺ በላይ የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግብራቸዉን እንደሚከፍሉ ተገልጿል።

👉በአጠቃላይ በሁሉም የግብር ደረጃዎች ያለዉን የገቢ አሰባሰብ እስከ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል።

👉በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ 120 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች ሲኖሩ በበጀት ዓመቱ ከ 20 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዟል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 04/07/2024

የ2017 የፌዴራል በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ

ኦፋ ፡ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀትን 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር አድርጎ አፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 36ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በጀቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገትን ለማፋጠን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 04/07/2024

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ለ16ኛ ዙር በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 859 ተማሪዎችን አስመረቀ

ኦፋ፤ሰኔ 27/2016 ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ለ16ኛ ዙር በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ የቅድመ ፣ ድህረ ምረቃና በሦስተኛው ድግሪ ትምህርታቸውን ተከታተሎ ያጠናቀቁትን 859 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ክቡር እንግዳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሮፈሰር ገብረ ያንትሱ ምረቃ ደስታ የሚጎናጸፍበት እንዲሁም የምኞታችን ሰኬት ቢሆንም ለተመራቂ ተማሪዎች አሁንም ብዙ የቤት ሥራ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በሰለጠናችሁ መስክም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የመረዳዳት ባህልን በማደበር በሚስበሩበት ቦታ ነው ብለዋል።

ባህላዊና ሞራላዊ ዕሴቶችን ተግባራዊ በማድረግ ተመራቂዎች መልካም አቅምን የመፍጠር ሥራ ለማስቀጠል ትጋትና ጥንካሬ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል

ትውልድን በሚያነጽ መስክ በመሰማራት የቀሰማችሁ ዕውቀት ተግባራዊ ማድረግ ይገበዋል ብለዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ ጥራት ያለውን ትምህርት በአገርቱ ለማዳረስ የትምህርት ሚኒስትር ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው በግብርና፣ በጤና፣በቴክኖሎጂ በሥነ ሰብና በሌሎች መስኮች እያሰለጠነ እንደሚገኝና በተለያዩ ጥናታዊ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዩኒቨርስቲው የተማሩ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በስኬት በማጠናቀቅ ለምረቃ መብቃታቸውን አስረድተዋል ።

በርካታ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎቶች እያከናወነና ተቋሙን የተሻለ ለማድረግ እየሠሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ሠላም የብልጽግና መሠረት በመሆኑ ትምህርትም በሠላም ውስጥ የሚገኝ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ተጠባባቂ ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር አክበር ጬፎ ከአጠቃላይ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል፦ በዶክትሬት ድግሪ/PhD 04፣ በማስተርስ ድግሪ 446 እንዲሁም በመጀመሪያ ድግሪ 409 ሲሆን ከሚመረቁ ተማሪዎች 671 ወንድ እንዲሁም 188 ሴቶች መሆኑ ገልጿል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 01/07/2024

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

ጉብኙቱን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ የማጠቃለያ ግምገማ ከማድረጋችን በፊት በሪፎርሙ ምን ያህል ስራዎች እንደተከናወኑ ለመገምገም እና የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ይዘን የበለጠ አጠናክረን ለማስቀጠል የተዘጋጀ ጉብኝት ነው ብለዋል።

ተቋሙ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ስኬታማ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው በተቋሙ ስትራቴጂክ አመራር ቁርጠኝነት መላውን የተቋሙን አመራርና አባላት በማሳተፍ በ2016 ዓ.ም መጠነ ሰፊ ችግሮችን ተቋቁሞ ስኬታማ ስራዎችን ያከናወነበት ዓመት ነው ብለዋል።

አያይዘውም የተዘጋጀው የአመራር ጉብኝት የ2016 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ከመጀመራችን አስቀድመን በሪፎርሙ ያስመዘገብናቸው ስኬቶችን በመጎብኘት ለቀጣይ ዓመት የበለጠ መነሳሳትን ለመፍጠር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሕዝብና ከመንግስት የተሰጠውን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ተልዕኮ በላቀ ደረጃ መወጣት እንዲችል በየጊዜው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየታጠቀ፣ ምቹ የሥራ አከባቢዎችን አየፈጠረ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችን እያስገነባ፣ ሀገራዊ ሪፎርሙን ተቀብሎ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ተግባራዊ እያደረገ ታላላቅ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል።

አመራሮቹ ጉበኝቱን የጀመሩት በዋና መሥሪያ ቤት የተደራጀውን አዲሱን የዳታ ቤዝ ሶፍትዌር ማበልፀጊያ፣ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ማዕከልን በመጎብኘት ሲሆን በፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነቡ አዳዲስ ህንጻዎች፣ የከተማን ውበት የሚመጥን የሆስፒታል ቅጥር ግቢ (compound)፣ በአዲስ መልክ የተደራጀ የህክምና መሳሪያዎችን ያሟላ ዘመናዊ ላብራቶሪ፣ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ሰጪ ፋርማሲ፣ የMRI፣ CITY SCAN እና የራዲዮሎጂ ክፍሎችንም ጎብኝተዋል።

በተመሳሳይ በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ጽ/ቤትን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጀግኖች ማዕከልንና በማዕከሉ የሚገኘውን የንብና የእንሰሳት እርባታ፣ ልዩ ልዩ የሥልጠና መስጫ ክፍሎችና ጅምናዝየም፣ እንዲሁም በልዩ ፀረ-ሽብር መምሪያ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራና የፖሊስ ሠራዊት መኮንኖች ክበብን እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መመሪያ ዘመናዊ የምርመራ ቴክኖሎጂዎችን፣ የተጠርጣሪ ማቆያ ክፍሎችን፣ የህፃናት ማቆያ ማዕከልንና የተፈጠሩ ምቹ የሥራ አካባቢዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በነገው ዕለትም ጉብኝቱ እንደሚቀጥል ታውቋል።

#ኢፌፖሚ

01/07/2024

ፕሮፌሰሮቹ አባት እና ልጅ

ኦፋ፣ ሰኔ 24፣ 2016 ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያፈራቸው ምሁራን ናቸው፡፡

ሁለቱም የከፍተኛ ትምህርት ሕይወታቸውን በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀምረው በሞያቸው ዩኒቨርሲቲውን እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 44 ዓመታትን እንዲሁም ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ 15 ዓመታትን በመምህርነት፣ በተመራማሪነት፣ እንዲሁም በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች ያገለገሉ እና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።

ሁለቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ ልክ በ10ኛው ዓመት የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማግኘታቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው ዓመት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ምሁራን መካከል ናቸው።

ማዕረጉ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው 13 ጥናታዊ ጹሑፎች፣ለማህበረሰብ ላበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Photos from Offa Woreda Administration's post 01/07/2024

የኦፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የ4ኛ ሩብ ዓመት የመሠረታዊ ድርጅት አባላት ኮንፈረንስ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ከመ/ድርጅት አመራሮች ጋር ተወያየ።

ኦፋ፤ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የ4ኛ ሩብ ዓመት የመሠረታዊ ድርጅት አባላት ኮንፈረንስ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ከአጠቃላይ መሠረታዊ ድርጅት አመራሮች ጋር ተወያየ።

የ2016 4ኛ ሩብዓመት ማጠቃለያ የመሠረታዊ ድርጅት ኮንፈረንስ በየማህበራዊ መሰረት ማለትም ኢኮኖሚያዊ ቁ-1 እና ቁ-2 ፣ አስተዳደራዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ በድምቀት ይካሄዳል ።

የመ/ድርጅቷ በ2016 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አባላትና ህዋሳት ዕውቅና ይሰጣል።

በኮንፈረንሱ የዕጩነት ጊዜያቸውን የጨረሱ አባላትን ወደ ሙሉ አባልነት የማሸጋገር ፣ የመ/ድርቷ፣ የህዋሳትና የአባላት የምዘና ውጤት ዝርዝር ቀርቦ ይፀድቃል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 01/07/2024

የተማረ የሰው ሀይልን ለመገንባት ብልፅግና ፓርቲ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ቅርጾ እየሰራ ይገኛል፦ አቶ ጎበዜ ጎዳና

ኦፋ፤ሰኔ 24/2016 በወላይታ ዞን የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስፈጻሚ ግብረኃይል በማስፈፀሚያ ዕቅድ እየተወያየ ነው።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎዳና የተማረ የሰው ሀይልን ለመገንባት ፓርቲያችን ብልፅግና የተለያዩ ፖሊሲዎችን ቅርጾ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ጀምሮ ሰፋፊ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

በትምህርት ዘርፍ የሰው ሀይልን መገንባት ከቻልን የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ማድረግ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።

የትምህርት ስራን ለማሳለጥ የትምህርት አመራር ብቻ ሳይሆን ሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎን የሚጠይቅ ተግባር እንደሆነም አመላክተዋል።

የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ተማሪዎች ተረጋግቶ እንዲሰሩና ፈተናው በሠላም እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን የሠላምና ፀጥታ ስራ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ግብረኃይሉ የሚጠብቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣና ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ሳሙኤል፣ የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ማርቆስ ጩምቡሮ የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎች ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

Photos from Offa Woreda Administration's post 28/06/2024

በወላይታ ዞን የ2016 ግብር ዘመን የግብር መክፈያ ወቅት ማስጀመሪያ እና የ2017 አዲስና ነባር ፊቃድ ዕድሳት ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 21/2016 በወላይታ ዞን የ2016 ግብር ዘመን የግብር መክፈያ ወቅት ማስጀመሪያ እና የ2017 በጀት ዓመት አዲስና ነባር ፊቃድ ዕድሳት ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ንቅናቄው መድረኩን የወላይታ ዞን ገቢዎች መምሪያና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በጋራ በመሆን እያካሄዱ ናቸው።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤልን ጨምሮ የዞኑ አጠቃላይ አመራር፣ የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

27/06/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋና ወግ እጅጉን የተጋመዱና የተሳሰሩ ህዝቦች ናቸው። አንዱን ከአንዱ ነጥሎ ማየት ፈፅሞ አይቻልም።

የነጠላ ቡድን ትርክቶች ህዝቦችን የሚያቀራርቡ ሳይሆን እርስ በእርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ የሚያደርጉ፣ የጋራ ጥቅምና ዕድገትን ሳይሆን የአንድ ወገን ጥቅምና ፍላጎትን ብቻ የሚያንፀባርቁ በመሆናቸዉ ጥፋታቸው የከፋ ነዉ።

በመሆኑም አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እና ፀጋዎቻችንን በአግባቡ በመጠቀም ለጋራ ዕድገታችንና ራዕያችን ከወዲሁ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 26/06/2024

ፓርቲን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት ጠንካራ አባልና አደራጃጀትን መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ።

ኦፋ፤ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሱፐርቪዥን ቡድን በኦፋ ወረዳ በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ ተግባራትን ምልከታ አካሂደዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሱፐርቪዥን ቡድን በኦፋ ወረዳ በፓርቲ መሪነት የአደረጃጀት ስራዎችን በማጠናከር አባሉ በፓርቲው እሴትና መርሆዎች ማዕቀፍ ዉስጥ በመሆን ያከናወናቸው ተግባራትን በቀበሌያት ምልከታ አካሂዷል።

በምልከታው በኦፋ ወረዳ ቡሻ ቀበሌ ሻሩና መ/ድርጅት ጡጡዋ ህዋስ ምልከታ በማድረግ አደረጃጀቶች የልማት አቅም በመሆናቸው ሕዋስ እና መሠረታዊ ድርጅቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።

ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ የተደራጀና ጠንካራ ሕዋስ እና መ/ድርጅት ቀዳሚው በመሆኑ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀቶችን እና አሰራሮችን በመፍጠር የብልጽግናን ጉዞ ለማሳካት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

አክለውም እንደ ወረዳችን ባለፉት ጊዜያት ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም አባላት በንቃት ባሳተፍ መልኩ የህዝቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለማረም ባደረገው ርብርብ ሁሉን አቀፍ ድል ማስመዝገብ መቻሉና ዕድልን ወደ ድል የቀየረበት እንደሆነም ተጠቁሟል።

የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮውና አሰራሩ ወጥነት እንዲኖረው አሁን ከደረስንበት የዕድገት ደረጃ በመነሳት በየደረጃው ያሉ አባላት የተሰጡ ስልጠናዎች ፍሬ ማፍራታቸውም ተመልክቷል።

መሠረታዊ ድርጅትና ህዋስ አመራሮች ለፓርቲው አባላት ሞዴልና አርዓያ በመሆን የፓርቲ ግንባታ ሥራዎቻችንን ይበልጥ እንዲጠናከር እና የለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚነት እንዲሰፋ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 26/06/2024

በዘንድሮ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ሁሉም ሰው በመሳተፍ የራሱን አሻራ ማበርከት ያስፈልጋል፦ አቶ ሳሙኤል ፎላ

ኦፋ፤ ሰኔ 19/2016 በወላይታ ዞን የ2016 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራን ለማስመጀር የተዘጋጀው የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የዞኑ ዐብይ ኮሚቴ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በጎ ተግባር መስጠትን፥ ቅንነትን የሚጠይቅ እና የህልና እርካታ የሚሰጥ መልካም ተግባር ነው ብለዋል።

የወጣቶች አቅምን፣ ጉልበትንና እውቀትን ለተሻለ ዓላማ በማዋል ከመንግሥት የሚባክነው ሀብት ማዳን ይችላል ብለዋል።

በጎነትን ባህል አድርገን መተግበር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የእርስበርስ የመተባበርና የመተጋገዝ ባህላችን ማጠናከር እንደሚገባም አመላክተዋል።

የክረምት ወራት በጎ ፊቃድ አገልግሎት ተግባር አካል የሆነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በአንድ ጀንበር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ሌሎችን በማስተባበር አቅም የሌላቸውን እና አረጋዊያኑን ቤት ለመገንባትና ለመጠገን ከወዲህ አስፈላጊ ዝግጅት መድረግ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

ህይወታቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉትን የማንሳትና በዘላቂነት የሚተዳደሩበትን የማመቻቸት ስራ የበጎ ተግባር አካል ተደርጎ መምራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የዘንድሮው በጎ ፊቃድ አገልግሎት ተግባር ዓላማውን ለማሳካት የዐቢይ ኮሚቴ ለውጤታማነቱና ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል በበኩላቸው ዘንድሮ በክረምት ወራት በጎ ፊቃድ አገልግሎት ስራ ዓላማውን እንዲሳካ ያለውን ምቹ ሁኔታዎች በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ቤት የመገንባትና የማደስ ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዘውዱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቂ ዝግጅትና ባለድርሻ አካላት መሳተፍ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

ተግባሩ በታቀደው መሠረት ለመተግባር በየደረጃው ተግባቦት መፍጠርና ሀብት መሰብሰብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

ለስራው ውጤታማነት ቅንጅታዊ አሠራር መጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዘውዱ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከራሳቸው የሚጠብቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የተሰሩ ስራዎችን መለየትና መደራጀት ስራ በመስራት በተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን በየወቅቱ እየተገመገመ መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በዞኑ በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ከ590 ሺህ በላይ ወጣቶች በአሥራ አምስት የስምሪት መስኮች ተሰማርተው ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለመድረግ መታቀዱን ተገልጿል።

"በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር እንደሚከናወን ተመላክቷል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 26/06/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በ2016 ዓመት በኦዲት ግኝት ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በዲላ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው

ኦፋ፤ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በ2016 ዓመት በኦዲት ግኝት ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በዲላ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ በተሰብሳቢ፣ በተከፋይ፣ ከማዳበሪያ ዕዳ፣ ከሕብረት ስራ እንዲሁም ከኦሞ ዕዳ ጋር ተያይዞ ሳይመለስ የቀረ ከፍተኛ የኦዲት ግኝት ስለመኖሩ በዚሁ ወቅት ተነስቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሀላፊ አቶ አበባየሁ ኤርሚያስ ውስን የሆነውን የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ከምዝበራ ለመከላከል የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በክልሉ ሲከናወኑ የቆዩ ቢሆንም አሁንም በሚፈለገው ልክ ውጤት ለማምጣት ጠንካራ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ደረጃ የኦዲት ግኝት መኖሩ የተነሳ ሲሆን አላግባብ የባከነ የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለማስመለስ ጥረት የሚያደርጉ መዋቅሮች ቢኖሩም ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንፃር በቂ ባለ መሆኑ የተጠናከረ ክትትል ይጠይቃል ብለዋል።

የፋይናንስ አሰራር ጥሰቶችን ተከትሎ በተለያዩ ሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች አላግባብ የሚባክን እና ለምዝበራ የሚጋለጥ የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ለማዳን ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እና ተጠያቂነት ማስፈን ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ወራሳ ተናግረዋል።

በኦዲት ግኝት ክትትልና ቁጥጥር ግብረ ሀይል በኩል የተሰሩ ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ አሁን ላይ የሚታየውን የኦዲት ግኝት እንዲስተካከል በአሰራር ላይ ግልፀኝነት መፍጠር እንደሚያስፈልግም አፈ-ጉባኤዋ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ 12 ቱም ዞኖች የተወጣጡ አፈ- ጉባኤዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ሀላፊዎች እና የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 26/06/2024

የቀድሞው የወላይታ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አዲስ ለተሾሙት ለአቶ መስፍን ዳዊት የስራ ርክብክብ አደረጉ

ኦፋ፤ ሰኔ 19/2016 የቀድሞው የወላይታ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል አዲስ ለተሾሙት ለአቶ መስፍን ዳዊት የስራ ርክብክብ አድርገዋል።

በርክብክቡ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን እርስበርሳቸው መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።

አዲስ ተሾሙት የወላይታ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት ርክብክብ አድርገው ስራቸውን ጀምረዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 26/06/2024

የወላይታ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ስብሰባ አካሄዱ

ኦፋ፤ ሰኔ19/10/2016 የወላይታ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ ከተረጂነት ለመላቀቅ ሀብት የማፍራት እና አምራች የመሆን አስተሳሰብ ላይ በሁሉም ደረጃ መግባባት መፍጠርን ታሳቢ በማድረግ ምክክር ተደርጓል።

በምክክሩ በየመዋቅሮቹ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ከልማት አጋሮች ጋር በማቀናጀት ወደ ማምረትና ሀብት ማፍራት ተግባር እንዲሸጋገሩ የማድረግ ሥራ በትኩረት እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች መረጃ የማጥራት ሥራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትክክለኛ መረጃ በመንተራስ ቀጣይ አስፈላጊ ውሳኔዎች እንዲወስኑም ምክር ቤቱ አመላክቷል።

24/06/2024

ዜና ሹመት!
የወላይታ ዞን አስተዳደር ለዞን ማዕከል አመራር አካላት በሽግሽግና በአዲስ መልክ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ።

በዚህም መሠረት

1. አቶ ጎበዘ ጎዳና የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ
2. አቶ መስፍን ዳዊት የወላይታ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ
3. አቶ ክፍሌ ታውሌ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ
4. ወ/ሮ ፀጋ ፋንታ የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ
5. አቶ መሪሁን መና የዞኑ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ
6. አቶ ምህረቱ ሳሙኤል ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ
7. አቶ ታምራት በለጠ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ
8. አቶ ግርማቸው ከፍያለሁ የዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ
9. አቶ ኃይሌ ስላስ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ
10. አቶ ጳውሎስ ጩምአ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ

11. አቶ መብራቱ ጳውሎስ የዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ፣
12. አቶ ታደሰ ኩማ የዞኑ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
13. አቶ ኢያሱ ላቾሬ የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ
14. ወ/ሮ ብርሃነሽ ሞጃ የዞኑ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ

15. አቶ ዘካሪያስ ታደሰ የዞኑ አስተዳዳሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
16. አቶ ወንድሙ ወርስሶ የመልካም አስተዳዳር ጽ/ቤት ኃላፊ
17. ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
18. አቶ ማቱሳላ ቦሻ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነምግባር ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
19. አቶ ፃድቁ ፈለቀ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ የሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ
20. አቶ ሲሳይ ሳሙኤል የዞኑ ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ

21. አቶ ጰጥሮስ ወ/ማርያም የዞኑ ግብርና መምሪያ የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ
22. ወ/ሪት ዝናቧ በየነ የዞኑ ግብርና መምሪያ የገጠር መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
23. አቶ ፋታሁን ዮሐንስ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና የማስፈጸም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
24. አቶ ደሳለኝ በቀለ የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና ዩራፕ ዘርፍ ኃላፊ
25. አቶ አበባየሁ ኡኩሞ የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ
26. ወ/ሪት ብሩክ ጰጥሮስ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ም/ኃላፊ
27. አቶ ማቴዎስ ማሞ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና የቤቶች ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/06/2024

በሁሉም ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ከፍ ለማድረግ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል፦ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል

ኦፋ፤ሰኔ 17/2016 የወላይታ ዞን ሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የ2016 ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገምና በቀጣይ አቅጣጫ ላይ መክረዋል።

መድረኩን የመሩት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ከፈፃሚ ማዘጋጃ ዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ የሴቶች ሁሉ-አቀፍ ተጠቃሚነት የተሰሩ ስራዎችን በጥልቀት መገምገም ያስፈልጋል ብለዋል።

በሁሉም ዘርፍ ከሴቶች ተጠቃሚነት አንጻር የተሰሩ ጀምር ስራዎች አበረታች መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሰላማዊት ውጤታማነቱ በወቅቱ መገምገም እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴ ተግባራዊ እንዲሆን ሴቶችን በአመለካከት በመቅረጽ የተግባር ባለቤት እንዲሆኑ የተሰሩ ስራዎች መጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የገቢ አሰባሰብ እና አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ ከአንድ እናት በሚል ቃል የተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ግንባር ቀደም የሆኑ መሠረታዊ ድርጅትና ህዋሳት መለየት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት የተለዩ መሠረታዊ ድርጅትና ህዋሳት ምርጥ ተሞክሮ ተቀምሮ መቀመጥ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ጠንካራ የሴቶች ሊግ መዋቅር መገንባት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ለዚህም አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል መደረግ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ድርሻዬ በለጠ በጀት ዓመቱ ከሴቶች ተጠቃሚነት አንጻር የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል።

በዞኑ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ዘርፈብዙ ተግባራት መከናወኑንም አስታውቀዋል።

በ2016 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ለመገምገም እና ቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ላይ የተዘጋጀው ቼክ-ሊስት መነሻ ወረዳና ከተማ መዋቅሮች በመገምገምና ቀጣይ እንደሚያስቀምጡ ተመላክቷል።

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/06/2024

መከባበርና መቻቻል ማለት አንዱ የሌላውን ማንነት ሀሳብ፣እሴትና ልዩነት ማክበር እንደራሱ አድርጎ መቀበል ማለት ነው፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች ተከባበረውና ተቻችለው በእኩልነት የሚተሳሰቡበት የሚኖሩበት የራሳቸውን ብሎም የክልላቸውን ሠላምና ዕድገት በጋራ ተልመው እየፈጸሙ ያሉበት ነው፡፡

ስለሆነም በህዝቦች ዘንድ የላቀ መከባበርና መቻቻል እንዲፈጠር ሁሉም ተከባብሮና ተቻችሎ የሚኖሩባት የበለፀገች ክልል እውን እንድሆን የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር እየተጋ ይገኛል፡፡

Photos from Offa Woreda Administration's post 24/06/2024

ከተሞችን አቀናጅተን፣ አደራጅተንና ፍላጎታቸዉን ለይተን ካልመራን የስልጣኔ ማዕከል ሊሆኑ አይችሉም- አቶ ብርሃኑ ዘዉዴ

ኦፋ፣ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በከተማ ነክ ጉዳዮች ላይ በፀደቁ አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት በአርባ ምንጭ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነዉ።

ስልጠናው በክልሉ ምክር ቤት በፀደቁ አዋጆች፣ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በፀደቁ ደንቦች እንዲሁም በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ማኔጅመንት በፀደቁ የአፈፃፀም መመሪያዎች ዙሪያ በየደረጃው ለሚገኙ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ነዉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘዉዴ ክልሉ 2016 ዓመተ ምህረትን በነባሩ ክልል በፀደቁ አዋጆች ሲተዳደር መቆየቱን አዉስተዋል።

ስራ ላይ የቆዩ ህጎች ጊዜያቸው በማብቃቱ እና ወቅቱን ያገናዘቡ አዳዲስ ህጎች ማዉጣት በማስፈለጉ በተያዘው ዓመት በክልል ምክር ቤት የፀደቁ 2 አዋጆች፣ በክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት የፀደቁ 10 ደንቦች እንዲሁም ቢሮዉ ያዘጋጃቸዉ 13 መመሪያዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀዋል።

የከተሞች ፕላን የከተሞች ህገ መንግስት ሆኖ እንደሚያገለግል አቶ ብርሃኑ ጠቅሰው ከተሞችን በተቀመጠላቸዉ ፕላን መሠረት አቀናጅቶ፣ አደራጅቶና ፍላጎታቸዉን ለይቶ መምራት ካልተቻለ የስልጣኔ ማዕከል ሊሆኑ እንደማይችሉ አስረድተዋል።

የአንድ ሀገር ዕድገት የሚለካው በህዝቡ አኗኗና አሠፋፈር መነሻነት በመሆኑ ከተሞች ደረጃ እንዲኖራቸዉና በፕላን እንዲመሩ ለማድረግ የፀደቁ አዋጆች፣ መመሪያዎች እና ደንቦችን በሚገባ ተገንዝቦ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጋሞ ዞን የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ልሳነ ወርቅ ካሳዬ አዲሱ ክልል ከተደራጀ ወዲህ የክልሉን ህዝቦች በሁሉም ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዕንቁ ዮሀንስ፣ የርዕሰ መስተዳድሩ የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ለማ ጉዙሜን ጨምሮ የቢሮ ኃላፊዎች፣ ከንቲባዎች፣ የማዘጋጃ ቤቶች ስራ አስኪያጆችና ባለ ድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።

23/06/2024

🇪🇹የምትተክል ሀገር! የሚያፀና ትውልድ!!

"የተቆረጠ ዛፍ በጥቂት አመታት ስራ ሊተካ ይችላል!
የተተከለ ዛፍ ባለመኖሩ በጎርፍ የሚወሰድ አፈር ግን በአመታት ሊተካ አይችልም፣
ስለዚህም ኢትዮጵያ ዛፍ የሚተክል ዜጋ፣ የተተከለውንም የሚያፀና ትውልድ ያስፈልጋታል!ለትውልድ ምቹ ሀገርን እንጂ እዳን አናወርስም!!"

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

Videos (show all)

ድንቅ ወላይታ❤
#ኦፋ ወረዳ የሴቶች ክረምት በጎ ተግባር !!

Website