Tarekegn Tesfaye

Tarekegn Tesfaye

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tarekegn Tesfaye, College & University, .

23/02/2022

በኢትዮጵያ አንድ 10 እና 15 ዓመት በማስተማር ያገለገለ ሌክቸረር 8056 ብር ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለዋል ይሄ ማለት አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የቀን ገቢው 268.5 ብር ብቻ ነው።በኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞች አንድ የቀን ሰራተኛ በአማካይ 500 ብር ያገኛል።ተመልከቱ ሀገር በትንንሽ ሰዎች ወይም ባላዋቂዎች ስትመራ ምሁራን አይከበሩም።ይቅርታ አድርጉልኝና ከ2010 ዓ.ም በፊት ቢያንስ ሰብስቦ የሚያወያየን ድምፃችንን የሚሰማ ትምህርት ሚኒስቴር ነበረን።
KB ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ

23/02/2022

ማሳሰቢያ
ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲ መምህር ይሄን ጽሁፍ በተቻለው መጠን አባዝቶ በየዩኒቨርሲቲው ግቢ፣ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ይበትን።
*ለመምህርነት ሙያ ክብር ይሰጠው!
*የዩኒቨርሲቲ መምህራን የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣቸው!
*እኛ መምህራን ግዴታችንን እንወጣለን መብታችንንም እንጠይቃለን!
*ትውልድ የሚቀርጽ መምህር ስለ ኑሮው፣ስለ ጓዳውና ስለ ቤት ኪራይ መጨነቅ የለበትም!
*መምህራን ዘመን የማይሽረው የሃገርና የትውልድ ባለውለታዎች ናቸው!
*መምህራንን በክብር የያዘ ማህበረሰብ ይከብራል!
*መምህር የአንድ ሀገር ምሰሶ ባላና ማገር ነው!
*ያለ መምህራን ንቁ ተሳትፎ የትምህርት ጥራት የማይታሰብ ነው!
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ድምጽ
የካቲት 15/2014 ዓ.ም

Website