የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት - Ziquala Woreda Justice Office

የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት - Ziquala Woreda Justice Office

የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በአብክመ ፍትህ ቢሮ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ስር የሚገኝ ፍትህ ጽ/ቤት ነው።

Photos from የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት - Ziquala Woreda Justice Office's post 31/01/2023

የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ጥር 9/5/2015 ዓ/ም ለወረዳው ጠቅላላ አመራር ፣ ለቀበሌ ሊቀመንበር ፣ ለቀበሌ ምድብተኛ ፖሊስና ፀጥታ አካላት እና ለማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በአብክመ በተሻሻለው የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 246/2009 ዓ/ም እና ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከልና የሚያስከትለው ተጠያቂነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የተሰጣቸው ኃላፊነት ሰፊውን ማህበረሰብ ክፍል የሚያገለግል በመሆኑ ስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸውና ከዚህ ቀደም አዋጁ ከሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት ውጭ በልምድ እየሰሩ እንደነበር ገልፀው ከዚህ በዃላ ትኩረት ሰጥተው በአዋጁ መሰረት እንደሚሰሩ እንዲሁም አሁን የጋብቻ ወቅት በመሆኑ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ላይ ግንዛቤ መሰጠቱ ለቅድመ መከላከል ስራ እንደሚያግዛቸውና በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ በመግለፅ ስልጠናው ቀጣይነት እንዲኖረው እና የፍትህ ፅ/ቤቱ ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል።

10/01/2023

📌 በፍትሐብሔር ክርክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት በቀነ ቀጠሮ ተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል?
----------------------------------------------------------

ፍርድ ቤት አንድ ጉዳይ ለማየት እና ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለያዩ ቀጠሮዎች እንደሚሰጥ የታወቀ ነው፡፡ የመጀመሪያ ተከሳሽ መከሰሱን አውቆ ለቀረበበት ክስ መከላከያ የሚሆኑ ማስረጃዎችን በፅሁፍ የሚያቀርብበት ነው፡፡ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት መልሱን ይዞ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክሱን ለመስማት ይቀጥራል፡፡

ክስ ለመስማት ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ቀጠሮ ሁለተኛ ቀጠሮ ነው፡፡ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክስ መስማት ሁለት ሂደቶችን የያዘ ነው፤ የመጀመሪያው ስለ መጀመሪያ ክስ መስማት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለዋናው ክስ መስማት ነው፡፡ የመጀመሪያው ክስ መስማት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለዋና ክስ መስማት የሚያዘጋጅበት ሂደት ሲሆን፤ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስን እና የተከሳሽን መልስ የሚያነብበት፣ የግራ ቀኙን አቋም የሚሰማበት፣ ተቀዳሚ መቃወሚያ ላይ ብይን የሚሰጥበትና ጭብጥ የሚመሠርትበት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዋና ክስ መስማት ሂደት ማለትም የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር መስማት፣ ምስክሮችን መስማት እና ማስረጃዎችን መርመር እንዲሁም የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት ነው፡፡

ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በየትኛው ቀነ ቀጠሮ መቅረባቸው እጅግ አስፈላጊ ነው? በሁሉም ቀጠሮዎች ወይስ መከላከያ ማስረጃ በሚቀርበበት ወይስ ክስ በሚሰማበት? ወደሚሉት ነጥቦች ስንገባ በእርግጥ ተከራካሪ ወገኖች እራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ፍርድ ቤት በሚወስነው በማንኛውም ቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በቀጠሮዎች አለመገኘት የክስ መዝገብ መዘጋት፣ የመከለከያ ማስረጃ የማቀረብና የመከላከል መብትን ማጣት እና ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች ቢቀርቡ ሊቀሩ የሚችሉ ትዕዛዞች እንዲሰጡ ይሆናል፡፡

በፍትሐብሔር የሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንዲሁም ሰበር በተለያዩ መዝገቦች የሰጣቸውን ውሳኔዎች (ለምሳሌ በመዝገብ ቁጥር 14184፣ 15835፣ 36412፣ 36390፣ 58487 እና 95638) ስንመለከት ለመልስ በተቀጠረበት ቀጠሮ የከሳሽም ሆነ የተከሳሽ አለመገኘት መዝገብ እንዲዘጋ ወይም ክርክሩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይም የማድረግ ውጤት አይኖረውም፡፡ ከሳሹ ወይም መጥሪያ እንዲያደርስ ታዞ የነበረው አካል ማድረሱን ወይም አለማድረሱን እንዲያረጋግጥ መጥሪያ በመላክ ወይም በሌላ ማንኛውም ዘዴ ማረጋገጥ አለበት፡፡ ተከሳሹ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ የመጀመሪያ ክስ ለመስማት ቀጠሮ መስጠት የሚችል ሲሆን ተከሳሹ ካልደረሰው ደግሞ ድጋሚ መጥሪያ ለተከሳሹ መላክ ይኖርበታል፡፡

በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህጉ አንቀጽ 69 መሰረት ፍርድ ቤቱ ቃል/ጉዳዩ ሊሰማ (hearing of suit) በወስነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ (ክስ ያቀረበው) እና ተከሳሽ ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መቅረብ አለባቸው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 69) ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት እንደ ቀሪው ተከራካሪ ወገን ይወሰናል፡፡ ሁለቱም ተከራካሪዎች ሳይቀርቡ ሲቀር፣ ከሳሽ ሲቀር እና ተከሳሽ ሲቀር ተፈጻሚ የሚሆነው ሥርዓት የተለያየ ነው፡፡

ሁለቱም ወገኖች ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል፡፡ ከሳሽ በቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ ተከሳሽ ቀርቦ የቀረበበትን ክስ የካደ ከሆነ መዝገቡን በመዝጋት ተከሳሽን ያሰናብተዋል (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 73)፤ ሆኖም ግን ከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በቀዳሚ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረበትን በቂ ምክንያት ገልጾ መዝገቡ እንዲታይ አቤቱታ ካቀረበ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የከሳሽ አቤቱታ እንዲደርሰው በማድረግ መዝገቡን እንደገና ከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ስራ መጥሪያው ለተከሳሹ መድረሱን ማረጋገጥ ነው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 70)፡፡ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የላከው መጥሪያ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ በሌለበት ጉዳዩን መስማት ይቀጥላል፡፡ መጥሪያው ለተከሳሽ በአግባቡ ያልደሰረው መሆኑን ካረጋገጠ ወይም አጠራጣሪ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ተከሳሽ መጥሪያው የደረሰው መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳን ለተከሳሹ የተሰጠበት ቀን ለክሱ መልስ ለማዘጋጀት በቂ ሆኖ በማይገመት አጭር ጊዜ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው ከሆነ ፍርድ ቤቱ የክርክሩን መሰማት ለሌላ ቀነ ቀጠሮ ያስተላልፈዋል፡፡ አንድ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተከሳሾች የተላከው መጥሪያ ለአንዱ ወይም ለአንዳንዶች ሳይደርስ የቀረው በከሳሽ ቸልተኘነት ወይም ጉደለት ከሆነ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ መጥሪያ ባልደረሰው ወይም ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የቀረበውን ክስ ሊዘጋ ወይም ቀነ ቀጠሮ ሊቀይር ይችላል፡፡

ክርክሩ በሌለበት እንዲቀጥል የተወሰነበት ተከሳሽ በቀጣይ ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ በቂ በሆነ ምክንያት በመጀመሪው ቀነ ቀጠሮ ያለመቅረቡን ካስረዳ መከላከያውን አቅርቦ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 72 ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም መከራከሪያውን ሳያሰማ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ መሰጠቱን ካወቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ መጥሪያው በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን ወይም በቂ ምክንያት በማቅረብ ትዕዛዙ ወይም ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78 መሰረት መጠየቅ ይችላል፡፡ በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ያቀረበውን አቤቱታ አግባብ መሆኑን ከተረዳ ለከሳሽ አቤቱታው እንዲደርሰው በማድረግ ትዕዛዙን ወይም ውሳኔውን በማንሳት ክርክሩን እንደገና ስምቶ ይወስናል፡፡

ሆኖም በቂ ምክንያት ምንድን ነው? የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሊሆን ይችላል፡፡ የቀረበው ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑ እንደ ጉዳዩ ዓይነት የሚታይ በመሆኑ አንድ ዓይነት ትርጉም መስጠት አይቻልም፡፡ ነገር ግን የተከራካሪ ወገኖች በእኩል የመዳኘት መብት እንዲሁም ተከሳሽ ለቀረበበት ክስ የበኩሉን መልስ የመስጠት መብቱ፤ የመሰማት መሠረታዊ መብት (The right to be heard) ይበልጥ ሊያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጎም አለበት፡፡ እንዲሁም የስነ ስርዓት ህጉ ዓላማን ፍትሐዊ በሆነ ስርዓት በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ውጪ እና ድግግሞሽን ባስቀረ ሁኔታ የተከራካሪ ወገኖችን ጉዳይ መቋጨትን በሚያሳካ መልኩ መተርጓም አለበት፡፡

ሳሙኤል ግርማ
ሕግ ባለሙያ እና ጠበቃ

#የኢትዮጵያን ሕጎች በነጻ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ 👇👇

https://t.me/joinchat/AAAAAFGPiPiWrEKfDOWAcA
https://t.me/joinchat/AAAAAFGPiPiWrEKfDOWAcA

.1 📱 +251911190299

05/12/2022

ሁለት ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገችው ህይወት መኮንን በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ

ህዳር 26/2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿን በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 02/2006 መሰረት በእርከን 39 ስር በማሳረፍ በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡ በተከሳሽ ላይ የተወሰነው እስኪፈፀም ድረስ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንድትቆይ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የሁለት ህፃናትን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ አድርጋለች ሲል በከባድ የግድያ ወንጀል እና እንዲሁም ተከሳሽ የሟቾችን የቤተሰብ ሰነድ ማስረጃዎች ማጥፋት ወንጀል ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በህይወት መኮንን ላይ ተደራራቢ ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

ተከሳሽ አስቀድማ ለፖሊስ በፖሊስ ጣያ እና በፍርድ ቤት የሰጠችውን የእምነት ቃል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶ ፍርድ በቤት ቀርባ ወንጀሉን ስለመፈጸሟ ስትጠየቅ “ድርጊቱን አልፈጸምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም” በማለት ብትክድም ወንጀሉን ስለመፈጸሟ ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ ለችሎቱ በማስረዳቱ፣ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በክሱ ዝርዝር የተመለከቱትን ያስረዱ በመሆኑ ተከሳሽ በተከሰሰችባቸው ከባድ የሰው ግድያ እና ሰነድ ማጥፋት ወንጀል እንድትከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለት የገለፀች በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል፡፡

ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰየመው ችሎትም ተከሳሽ ጥፋተኛ መባሏን ተከትሎ የዐቃቤ ህግን የቅጣት አስተያየትና የተከሳሽን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም ዐቃቤ ህግ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ወንጀሉ ከባድ ደረጃ ተብሎ እንዲሰላለትና በሞት እንድትቀጣ አስተያየት ሰጥቷል፡፡

በተከሳሽ በኩልም ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣ ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣ እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት 5 የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት የጠየቀች ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ማቅለያዋን አልተቀበለውም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡ ምንጭ -የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

06/11/2022

❗የመንደር ውል አደጋዎች

የመንደር ውል ሕጋዊ ነው አይደለም የሚለውን ሙግት እረፍት እንስጠውና ወደ አንድ ቁልፍ ነጥብ እንሻገር።

የመንደር ውል ይዞብን የሚመጣው ፈተና ምንድነው?

1/ አንድ የቤት ገዥ በመንደር ውል ከተዋዋለ በኋላ ያን ይዞ ክፍለ ከተማ ሄዶ ስም ይዙርልኝ ቢል ተቀባይነት የለውም።

2/ አንድ ቤት ገዥ ቤቱን በመንደር ውል ገዝቶ አገር ሰላም ብሎ እየኖረ ድንገት የ3ኛ ወገን ጥያቄ ቤቱ ላይ ቢነሳ ለከፍተኛ ቀውስ ይጋለጣል። ይህም ከሻጭ ባል/ሚስት የሚመጣ፣ "ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ" የሚል ጥያቄ ሊሆን ይችላል።

በመንደር ውል ያገባ/ያላገባ ሰነዶች ጋር ተያይዞም ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች አሉ። ኋላ ላይ በሚመጣ መቃቃር ፍቺ ቢኖር ገዢ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል።

አንድ ቤት ገዥ አገር ሰላም ብሎ ቤት በመንደር ውል ገዝቶ እየኖረ፣ የሻጭ ባል/ሚስት ሽያጩ አይመለከተኝም ይፍረስልኝ ብትል/ቢል፣ ቤት ገዢ ከፍተኛ የፋይናንስና የሥነ ልቡና ጉዳት ይደርስበታል።

የመንደር ውሉን ይዞ ፍርድ ቤት ቢሄድም አትስተናገድም ባይባልም፣ ከሻጭ ገንዘቡን መልሶ የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ነው የሚሆነው።

እንዲህ ዓይነት በርካታ ጉዳዮች ያጋጥማሉ፣ ሽያጭ ውሉ አይመለከትኝ የሚሉ የትዳር አጋሮች ይኖራሉ። በቤተሰብ ሕጉ ከ500 ብር በላይ የሚደረግ ሽያጭ የሁለቱንም ይሁንታ ማግኘት አለበት፤ በዚህ የተነሳ የመንደር ውል ያልታሰበ ጣጣ ይዞ ይመጣል። ብቻ በአጠቃላይ በመንደር ውል ገዥው በራሱ ላይ የሚጋብዘው አደጋ የትየሌሌ ነው።

በመንደር ውል ስንዋዋል አንዳንድ ጊዜ ይሆናሉ ብለን የማንጠብቃቸው ነገሮችም እንደሚከሰቱ መዘንጋት የለብንም። ለምሳሌ በመሀል ሞት አለ። ከአገር መውጣት አለ። ውክልና ማንሳት አለ። በሰው ላይ ነገ ምን እንደሚደርስ ማን ያውቃል?

በመንደር ውል የተፈራረመ ሻጭ ቢሞት የውርስ ጉዳይ ይከተላል፣ ጋብቻ ቢፈርስ የቤተሰብ ክርክር ውስጥ ይገባል፣ ወራሾች ቤቱ በሕገ ወጥ ውል የተፈጸመ ነው ብለው ሊያሳግዱት ይችላሉ። ጣጣው ብዙ ነው።
በጠበቃ ሳሙኤል ግርማ

Photos from ANRS Justice Bureau የአብክመ ፍትሕ ቢሮ's post 05/11/2022
Photos from የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት - Ziquala Woreda Justice Office's post 22/10/2022

የዝቋላ ወረዳ ፍትህ አካላት የሆኑት ፍርድ ቤት ፣ ፍትህ ፅ/ቤት እና ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ዳኞች ፣ ዓቃብያነ ህግ እና መርማሪ ፖሊሶች ጥቅምት 10/2015 ዓ/ም ላይ የ2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ መልካም ስራዎችን እና በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት ላይ ያሉ ክፍተቶችንና ያጋጠሙ ችግሮችን በጥልቀት ሃሳቦችን በማንሳትና በመወያየት የ2015 በጀት ዓመት ስራዎችን ለማከናወን ካለፈው ዓመት ያጋጠሙ ክፍተቶችን በማስተካከልና በተሻለ መልኩ የቅንጅት አሰራርን በማጠናከር ህግና ስርዓትን በመከተል የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና ፍትህን ማስፈን እንደሚገባ ውይይት ተደርጓል። በዚህ የመጀመሪያ ዙር የጉድኝት ውይይት ላይ ህገ ወጥ ንግድ ፣ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ህገ ወጥ የመሬት ወረራን መከላከልና ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ እና የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ የተከሳሽና ምስክር አቀራረብ ፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ማክበር እና የአፈፃፀም ክሶች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ እንዲሁም ማህበረሰቡን በቅንነት በማገልገል የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኝ መስራት እንደሚገባ መግባባት ላይ ተገርሷል። በመጨረሻም የፍትህ አካላቱ የጉድኝት ውይይት በየ ሩብ ዓመቱ እንደሚካሄድ በመደምደም ውይይቱ ተጠናቋል።

Photos from የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት - Ziquala Woreda Justice Office's post 19/10/2022

በዋግ ህምራ ብሔረሰብ አስተደደር የዝቋላ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ከUNDP በተገኘ የበጀት ድጋፍ ለተመረጡ የቀበሌ ሊቀ መንበሮች ፣ ለሃይማኖት አባቶች እና ለባለድርሻ አካላት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ መስጠት ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው ወቅቱን ያገናዘበና አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲሆንና ቀጣይነት እንዲኖረው ፣ በቅንጅትና በመቀራረብ መስራት እና ጥቃት ፈፃሚዎችንም በአፋጣኝ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ ከሰልጣኞች አስተያየት ተሰጥቷል። እንዲሁም በቀጣይ የሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት እንዴት በቅንጅት መስራት እንዳለብን አቋም ተይዟል።
ፅፅቃ
ጥቅምት 2015 ዓ.ም

15/10/2022

ገደብ /የወንጀል ቅጣት ገደብ ምንድነው?/
➖➖➖➖➖➖➖➖
ፍርድ ቤት አንድ ጥፋተኛ የተባለን ሰው ለጥፋቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት በጥፋተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዲታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዲሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን አረጋግጦ ከእስር እንዲፈታ የሚያደርግበት አግባብ
በተከሳሽ ላይ የተወሰነ የቅጣት ውሳኔ ከመገደቡ ወይም የገደብ ውሳኔው ከመሻሩ በፊት የቅጣት ገደብ ስለሚከለከልበትና ስለሚሻርበት ሁኔታ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 እና 197 ስር የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ማገናዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉ በተወሰነ ገደብ ቅጣትን ማቆም የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ከአንቀጽ 190 እስከ 200 ስር አስፍሮ ይገኛል፡፡ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 190 ሲታይም ከእስር በገደብ መለቀቅ ማለት ፍርድ ቤት አንድ ጥፋተኛ የተባለን ሰው ለጥፋቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን በጠቅላላው በመመልከት በጥፋተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዲታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዲሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን አረጋግጦ ከእስር እንዲፈታ የሚደረግበት አግባብ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ተከሳሽ የቅጣት አፈፃፀም እንዲገደብ ፍ/ቤቶች ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉባቸው ሁኔታዎችም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194 በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ በሌላ አገላለፅ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን በገደብ የሚያስቆመው የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲሆን እነዚህም፡- • ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ሆኖ ጠባዩም አደገኛነት እንደሌለው የሚታመንበት እንደሆነ፣ • ጥፋቱ በመቀጮ፣ በግዴታ ስራ ወይም ከሶስት አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ • ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፊት ጠባዩን ለማረም እንደሚችል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑና በዚህ ውሳኔ ብቻ እስከ መጨረሻው ሊሻሻል የሚችል መሆኑን ያመነበት እንደሆነ አስተያየት ከሰጠ በኋላ ቅጣት ሳይወስን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ሊሰጠው የሚችልበት አግባብ መኖሩን ሕጉ ያሳያል፡፡
እንዲሁም ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት ከማድረግም የሚታገድ መሆኑና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ ፍርድ ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከአፈፃፀም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ እንደሚችል የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 192 ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡ ከላይ የተመለከቱትን የገደብ አሰጣጥ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ ግን ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተመለከቱትን ቅድመ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በማየት የተሟሉ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡ በዚህ አግባብ የገደብ ውሳኔ ካልተሰጠ የወንጀል ሕጉን መሰረታዊ አላማ ለማሳካት የማይቻል መሆኑ ይታመናል፡፡
የወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 196 ስር እንደአስቀመጠው ፍርድ ቤቱ ለጥፋተኛው የሚሰጠውን የፈተና ጊዜ የሚወስነው የወንጀሉን ከባድነት፣ በወንጀል ድርጊት መደጋገም ሊደርስ የሚችለውን ጉዳትና በጥፋተኛው ላይ ሊጣልበት የሚችለውን እምነት ከግምት ውሰጥ በማስገባት ስለመሆኑ ሕጉ ያሳያል፡፡ የተከሳሹን የገደብ ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ከመቀበሉ በፊትም ተከሳሹ ቀድሞ የነበረውን ጠባይ ፣ የአኗኗርና የስራውን ሁኔታ ምን አይነት እንደነበር ፍርድ ቤቱ መረጃ መሰብሰብ እንደሚችልም ሕጉ ያስገነዝባል፡፡
የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197/1/ ሲታይም ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ለማድረግ በቅ

Website