North Gondar Livestock

North Gondar Livestock

HIH

Photos from North Gondar Livestock's post 27/04/2024
Photos from North Gondar Livestock's post 27/04/2024

የሰሜን ጎንደር ዞን እንስሣትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በስሩ ካሉ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጋር የ2016 በጀት አመት የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ዞን ም/አስተዳዳሪና የንግድ ገቢያ ልማት መምሪያ ሃላፊ ናቸው።

ስለሆነም በቀጣይ ወራት መልካም አፈጻጸሞችን በማስቅጥልና ድክመቶችን በማረም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማርጋገጥ ሁሉንም የፕሮጀክት ስራዎች በወቅቱና ለታለመለት አላማ ብቻ በማዋል የተሻለ አፈጻጸም ይዘን ተጨማሪ ሃብት ማምጣትና መተግበር እንዳለብን ተግባብተናል።

30/03/2024
Photos from North Gondar Livestock's post 30/03/2024

በፌደራል ድጋፍ በዳባት ወረዳ የስናር መኖ በመስመር የተዘራ በሞዴል አ/አደር

29/03/2024

በዳባት ወረዳ በጫርቢጣ ቀበሌ ስናር መኖ በመስመር በመዝራት 2 ጊዜ በማጨድ ተጠቃሚ የሆነ አርሶ አደር አቶ ዳኘው ፈንቴ።

Photos from Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን's post 23/02/2024

በዶሮ እርባታ ዘርፍ መሰማራት እጅግ አዋጭ እና ዘርፉን ሁሉም አካላት በቀላል ፣በውስን ገንዝብና ቦታ መስራት ይቻላል

Photos from Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን's post 23/02/2024
Photos from North Gondar Communication's post 23/02/2024
Photos from Adiarkay woreda communication's post 26/07/2023
Photos from Amhara Livestock and Fisheries Resources Development Office's post 09/06/2023
Photos from North Gondar Livestock's post 12/05/2023

በበየዳ ወረዳ በ4.5 ሄክታር በመስኖ ልማት እየለማ ያለ የመኖ ጓያ ለእንሰሳት ሃብት ስራው ትልቅ ፋይዳ ያለው እና የመኖን ስራ ለማዘመን ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው።

Photos from North Gondar Livestock's post 08/05/2023

በደባርቅ ወረዳ በslmp ፕሮጀክት ትሪሉሰርንና የተለያዩ ሳር ዝርያዎች በችግኝ ጣቢያ በማባዛት ላይ እና ለእንሰሳት ሃብት ስራው ትልቅ ፋይዳ ያለው እና የመኖን ስራ ለማዘመን ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው።

Photos from North gondar communication's post 09/04/2023
Photos from North Gondar Livestock's post 23/03/2023

በደባርቅ ከተማ አስተዳደር በዳልጋ ከብት ማድለብ የተሰማሩ ግለሰቦች ውጤታማ ስራ እየሰሩ መሆኑን ገለጹ።

Photos from North Gondar Livestock's post 23/03/2023

#ደባርቅ ከተማ እንስሳትእናአሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት

በደባርቅ ከተማ አስተዳደር በደሮ እርባታ ስራ ተደራጅተው ውጤታም ስራ እየሰሩ ያሉ ኢንተር ፕራይዞችን በመደገፍ በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦችን ውጤታማ እንዲሆን የባለሙያዎች እገዛ የተጨመረበት መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በላይ የገበያ ትስር ቢኖር ውጤታማ እንደሚሆኑ እና ከ5500 በላይ እንቁላል የተሸጠ እና አሁን ፆሙን ምክኒያት በማድረግ ከ3000 በላይ እንቁላል የተሰበሰበ መሆኑን እና በተጨማም ማብቃት የእንስሳት መኖ በማእከል ደረጃ በማቅረብ እያከፋፈሉ እንደሚገኙ እና ምርታቸውን የሚፈልግ ሁሉ በ0924400803/0967148646/ በመደወል የሚፈለገውን ምርት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ገልፀውልናል።

ለውጤታማነት እንስራ!

#ደባርቅ ከተማ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት።

Photos from በየዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት's post 05/02/2023
Photos from North Gondar Livestock's post 17/01/2023

"የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ ሁሉንም ከደጀ አመርታለሁ!" በሚል መሪ ቃል በሰሜን ጎንደር ዞን እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ዞን አቀፍ የሌማት ቱርፋት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አካሄደ።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የፓርቲና የሚመለከታቸው የመንግስ ተቋም ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ የሰሜን ጎንደር ዞን ም/አስተዳዳሪና ከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ደብረወርቅ ይግዛዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸዉም ጠግቦ መመገብ መቀንጨርን አያስቀርም ነገር ግን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ከዘርፈ ብዙ በሽታዎች ልንድን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አያይዘዉም ዞናችን በተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ሀብቶች የታደለ ቢሆንም ይህን ፀጋ ለይቶ በምግብ እራስን መቻልና የተመጣጠነ ምግብ በማግኘት በኩል ሰፊ ክፍተት ያለብን በመሆኑ ጥሪ የተደረገላችሁ አካላት በሙሉ ትኩረት በመስጠት ወደ ተግባር እንድትቀይሩ በማለት መድረኩን የከፈቱ ሲሆን ከመክፈቻ ንግግሩ በመቀጠል የሰሜን ጎንደር ዞን እንስሣትና አሳ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸጋው ጌታቸው የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ መድረኩን አስመልክቶ በሰነድ የተደገፈ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ደግሞ በዞኑ ያለዉን የእንስሣት ሀብታችን በአግባቡ ከመያዝና የተሻሻሉ ዝርያዎችን ከመጠቀም አንፃር የተሻለ ነገር ቢኖረዉም ተዋፅኦችን በአግባቡ ከመጠቀምና የገቢያ ትስስር ከመፍጠር አንፃር አሁንም ስራ የሚጠይቅ መሆኑን በሰነዳቸው አብራርተዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ኃላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት አዛናዉ በበኩላቸው ሴቶች በምግብ እራስን ከመቻል ባለፈ ለገብያ ፍጆታ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ተግባር መገባቱን አሳውቀዋል።
በተጨማሪም የሌማት ትሩፋት ውጤቶች በሁሉም የዞናችን ወረዳዎች እንደየ አግሮኢኮሎጂው አቅዶ በመስራት የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት በኃላፊነት መስራት እንደሚገባ ገልፀው ለፕሮግራሙ ስኬት ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዲ/ን ሸጋዉ ዉቤ የሌማት ትሩፋትን የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ እስከ ቀበሌ በማዉረድ በምግብ እራስን የመቻልና የተመጣጠነ ምግብ በማዘጋጀት ንፁህና ለሀገር የሚጠቅም በአስተሳሰብ የተሻለ ትዉልድ መፍጠር ይገባናል በማለትና የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቁል።
በመጨረሻም በደባርቅ ከተማና በዳባት ወረዳ በማህበርና በግል ደረጃ እየተሰሩ ያሉ የእንስሳት እርባታ፣ዝርያ ማሻሻል፣ደሮ እርባታ፣በንብ ማነብና ማድለብ እንዲሁም የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በመጎብኘት የንቅናቄ መድረኩ ተጠናቋል።
~~~

Photos from Beyeda Communications's post 31/12/2022
Photos from Dabatworeda comunication/ዳባት ወረዳ ኮሙኒኬሽ's post 31/12/2022
28/10/2022

የ1 ቀን ጫጩት ለመግዛት የ42 ቀን ክትባት መውሰድ አለባቸው። በአንዳንድ ቦታ ገና ቀኑ ሳይደርስ ወደ ገበያ እያወጡ ነው። ለህዝባችን ጥቅም ሲባል መስራት ያለብንን ሙያዊ ግዴታችን እንወጣ።

Videos (show all)

በዳባት ወረዳ በጫርቢጣ ቀበሌ  ስናር መኖ በመስመር በመዝራት 2 ጊዜ በማጨድ ተጠቃሚ  የሆነ አርሶ አደር  አቶ ዳኘው ፈንቴ።

Website