ጉና በጌምድር ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

ጉና በጌምድር  ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

ማንኛውም ጠቃሚ መረጃ ከዚህ ገጵ ያግኙ

Photos from ጉና በጌምድር  ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት's post 19/01/2022
Photos from ጉና በጌምድር  ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት's post 19/01/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
በአሉ የደስታ፤ የፍቅርና የመቻቻል ይሁንላቹ፡፡

29/10/2021

የታክስ ሰራተኛው ሥራውን ሲሰራ ያለማደናቀፍ የሁሉም ሰው
ግዴታ ነው
በታክስ ሕጉ መሰረት ግዴታውን እየተወጣ እና በማጣራትና
በምርመራ ላይ ያለን የታክስ ሰራተኛ ያደናቀፈ ወይም
ለማደናቀፍ የሞከረ ማንኛውም ሰው በወንጀል የሚቀጣ
ስለመሆኑ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አ.ቁ
125 (1) ላይ የተደነገገ በመሆኑ የታክስ ሰራተኛው ሥራውን
ሲሰራ ወይም ሲያጣራ ያለማደናቀፍ የሁሉም ሰው ግዴታ ነው፡፡
 የሚከተሉት እና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶች የማደናቀፍ
ተግባራት ተደርገው ይወሰዳሉ፡-
I. ባለስልጣኑ ታክስ ከፋይ ቢሆንም ባይሆንም በሚሰጥ የጽሁፍ
ማስታወቂያ መሠረት አለመፈፀምን ጨምሮ፣
II. ሰነዶችን ለመመርመር ከባለስልጣኑ የሚቀርብ ጥያቄን
አለመቀበል፣
III. ሪፖርቶችን ወይም የታክስ ከፋዩን ጉዳዮች የሚመለከት
መረጃን ለማቅረብ ፈቃደኛ አለመሆን፣
IV. ቀርቦ የራሱን ወይም የሌላ ማንኛውም የታክስ ጉዳይ
ማስረጃ እንዲሰጥ በተሰጠው ማስታወቂያ መሠረት
አለመፈፀም፣
V. የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይም ዋና ዳይሬክተሩ
የወከለውን የታክስ ሰራተኛ ማንኛውንም ማስረጃ ለማግኘት
ያላቸውን መብት (በማንኛውም ጊዜና ያለምንም ማስታወቂያ
በማንኛውም ግቢ ወይም ቦታ፣ ማንኛውንም እቃ ወይም ንብረት፣
ሰነድ፣ የመረጃ ማከማቻ) እንዳይጠቀሙ መከልከል፣
VI. አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት ወይም መገልገያ
ለማቅረብ ፈቃደኛ አለመሆን፣ ማለትም ምርመራው
በሚደረግበት ግቢ ወይም ቦታ የሚገኙ በመረጃ ማከማቻ
ወይም በሌላ ማንኛውም መልክ የተያዙ ማናቸውንም ሰነዶች
በተመለከተ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በቃል ወይም በጽሁፍ መልስ
መስጠት፣
VII. በባለስልጣኑ ቢሮ ውስጥ ሁከት መፍጠር ወይም የታክስ
ሰራተኞች የቅጥር ግዴታቸውን እንዳይወጡ ማደናቀፍ፣
VIII. ማንኛውም የታክስ ሰራተኛ ፈቃድ የተሰጠው መሆኑን
የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ በባለቤቱ ወይም ህጋዊ ባለይዞታ
በሆነ ሰው ሲጠየቅ ማቅረብ ካልቻለ ወደ ማንኛውም ግቢ
ወይም ቦታ መግባት ወይም ገብቶ መቆየት አይችልም።

29/10/2021

ሂሳብ መዝገብ ንግድን እዴት ያሻሽላል
የሂሳብ መዝገብ ማለት ለንግድዎ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን
በሙሉ በፅሁፍ መዝግቦ መያዝ ነው፡፡ ለምሳሌ፡
• ንግድዎ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚቀበል፣
• ንግድዎ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚከፍል፣
• በዱቤ የሸጡት ስንት እንደሆነ፣
• ንግድዎ ምን ያህል እዳ እንዳለበት፣
• የንግድዎ መሳሪያዎችና እቃዎች እሴት ምን ያህል እንደሆነ፣
• በንግድዎ ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ምን ያህል እንደሆነ፣
• ንግድዎ ከአቅራቢዎችና ከደንበኞች ጋር ያደረጋቸው ውሎችና
ኮንትራቶች፣ ለማንኛዉም ንግድ የሂሳብ መዝገብ መያዝ
ያስፈልገዋል፡፡
የጠራና ትክክለኛ የሂሳብ መዝገብ ችግሮችን ለይቶ በማወቅ
መፍትሄ ለመፈለግ ያስችላል፡፡
በሂሳብ መዝገብ ተጠቅመው፤
• ጥሬ ገንዘብዎን ይቆጣጠሩ፤
• የንግድዎን አፈፃፀም ይከታተሉ፤
• ለባንኮች፣ ለኢንቨስተሮችና ለሌሎች ለሚመለከታቸው
ተቋሞች የንግድዎን አፈፃፀም ያሳዩ፡፡
• ንግድዎን ለወደፊት ያቅዱ፡፡
የሂሳብ መዝገብ መያዝ ለበዙ ንግዶች ህጋዊ ቅድመ ሁኔታ
ነው፡፡

29/10/2021

ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ እንፍጠር!

19/10/2021

ስለ ሂሳብ መዝገብ ምን ያህል ያውቃሉ????

19/10/2021

የግብር /ታከስ አስፈላጊነት
ግብር/ታክስ ከእያንዳንዱ ግለሰብ የየእለት እንቅስቃሴ ጋር
በእጅጉ የተቆራኘ ሲሆን ጠቀሜታወቹ አያሌ እና ዘርፈ ብዙ
ናቸዉ፤
የተወሰኑትን ለመጠቀስ ያህል፤
 ለኢኮኖሚ ልማት፣
 ለማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት፣
 ለባህል እድገት፣
 ለሀገር ደህንነት፣
 ለፍትህና መልካም አስተዳደር መስፈን፣
 ለአካባቢ ጥበቃ፣
 ሀገርን ከጠላት ለመከላከል፣
 ዜጎች በሠላም ወጥተዉ በሠላም ሰርተዉና ዉለዉ
ለመግባት፣
 ደህንነታቸዉንና ሰላማቸዉን ለመጠበቅ፣
 ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች፣
 መንገዶች የሃይል አቅርቦቶችን ለማስፋፋት፣
 ኢኮኖሚዉን ለማነቃቃት፣
 ንግድና ኢንቨስትመትን ለማበረታታት፣
 ልማት ለማፋጠን፣
 የሕብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣
 ኢኮኖሚዉን ለማረጋጋት፣
 በዜጎች መካከል ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር
ለማድረግ እና የመሳሰሉት ስራወችን ለማከንወን የሚዉል
ገንዘብ ነዉ።
የተጣለብነን ግብር/ታክስ በወቅቱና በጊዜዉ በመክፈል
ለህልዉና ዘመቻዉ የድርሻችን እንወጣ

08/08/2021
Photos from ጉና በጌምድር  ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት's post 07/07/2021

እንኳን ለ2014 አም የግብር ዘመን አደረስን።

09/03/2021

የታክስ ከፋይ የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ እንዲፈቀድለት
የሚጠይቅ ታክስ ከፋይ ማሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ
በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት የሚፈለግበትን የታክስ ዕዳ
በወቅቱ ወይም በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችል ታክስ ከፋይ
ቢሮው ክፍያ ጊዜ ለማራዘም እንደሚችል የተደነገገ በመሆኑ፣
ቢሮው ታክስ ከፋዮች የክፍያ ጌዴታቸውን እንዲወጡ ተገቢነት
ያላቸውን ሁኔታዎች በማመቻቸት ድጋፍና እገዛ ማድረግ
የሚጠበቅበት በመሆኑ፣
ታክስ ከፋዩ የሚፈለግበትን የታክስ ዕዳ በአንድ ጊዜ መክፈል
በማይችልበት ጊዜ የተራዘመ የእዳ መክፈያ ጊዜ ስምምነት
በማስገባትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት
ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገድበትን ሁኔታ መፍጠር ተገቢ
ስለሆነ፤
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በታክስ
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 32(2) በተሠጠው
ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
1.”የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ” ማለት ማንኛውም ታክስ ከፋይ
በአዋጁ መሠረት የመክፈያ ጊዜው የደረሰ ወይም በወቅቱ
ያልተከፈለ የታክስ እዳን ለመክፈል ጊዜ እንዲራዘምለት
ሲያመለክት በታክስ ህጎች ከተቀመጠው ጊዜ ገደብ እንዲከፍል
የሚሰጥ የክፍያ ስምምነት ነው፡፡
2. ”የክፍያ ጊዜ ስምምነት” ማለት ታክስ ከፋዩ የሚፈለግበትን
የታክስ ዕዳ (ታክስ፤ወለድ እና ቅጣት) በአንድ ጊዜ መክፈል
ሳይችል ሲቀር ታክስ ከፋዩ እና ቢሮው ክፍያው የሚፈጸምበትን
ጊዜ እና ሁኔታ በተመለከተ በጽሁፍ የሚያደርጉት ስምምነት ነው፡፡
3. ‘’የታክስ ዕዳ” ማለት እንደአግባቡ በታክስ ህጎች መሰረት
በመክፈያ ጊዜው መክፈል ሲገባው ያልተከፈለ ታክስ እና ወለድ
እንዲሁም አስተዳደራዊ መቀጫዎችን ይጨምራል፡፡
4. ‘’የማይነሳ አስተዳደራዊ ቅጣት” ማለት በአስተዳደራዊ ቅጣት
አነሳስ መመሪያ መሰረት እንዲነሳ ያልተፈቀደው እና የክፍያ ጊዜ
ማራዘሚያ ስምምነቱ አካል የሆነው ተከፋይ አስተዳደራዊ ቅጣት
ነው፡፡
5. የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች
 የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት የሚፈቀደው፡-
ሀ. ታክስ ከፋዩ የታክስ እዳውን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችል
ሲሆን፣
ለ. ታክስ ከፋዩ የታክስ ማስታወቂያ ወይም የታክስ ስሌት
ማስታወቂያ በደረሰው ጊዜ በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ዉስጥ
የማይገኝ መሆኑ ሲረጋገጥ፣
 በከፍተኛ የስጋት ደረጃ የተለየ ወይም ሀብቱ በእዳ የተያዘበት
ወይም ሀብቱን ለመሸጥ ግልጽ ጨረታ የወጣበት ታክስ ከፋይ
እዳውን ለመክፈል ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ለዕዳው ተመጣጣኝ
የሆነ የባንክ ዋስትና ሲቀርብ ብቻ ይሆናል፡፡
6. የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የማይፈቀድባቸው ሁኔታዎች፤-
 የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት የማይፈቀድባቸው
ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ. በታክስ ማስታወቂያ ጊዜ መከፈል ያለበት የታክስ እዳ
ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ ወይም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ገቢ
መደረግ ያለበት ሲሆን፣
ለ. ታክስ ከፋዩ አስቀድሞ የክፍያ ጊዜ ስምምነት የተሰጠው ሆኖ
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት
ሳይኖር እዳውን ያልከፈለ ሆኖ ሲገኝ፣
ሐ. የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የተጠየቀበት የታክስ እዳ
መጠን እንደ ታክስ ከፋዩ አመዳደብ ከተቀመጠው አነስተኛ
የገንዘብ መጠን በታች ከሆነ፣
 ታክስ ከፋዩ፡-
ሀ. በታክስ ዘመኑ በከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ፣
ለ. ለዕዳው ማስከፈያ ሀብት እና ንብረት የታያዘበት ከሆነ፣
ሐ. በእዳው የተያዘበትን ንብረት ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ
የወጣበት ከሆነ፣
7. የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት የሚሰጠው ለእዳው
ተመጣጣኝ የሆነ የባንክ ዋስትና ሲያቀርብ ብቻ ይ

06/03/2021

# በስመ #ንብረት #ዝውውር ጉዳይ የሚነሱ ችግሮችን የሚፈታ
#የውሳኔ #ሀሳብ # ፀደቀ ።
------------------------
የካቲት 26/2013 ዓ.ም.
በገቢዎች ተቋም በበጀት አመቱ 18 የሚሆኑ የመልካም
አስተዳድር ችግርሮችን ለመፍታት ለይተን አቅደናል። 4ቱን
ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ስርአት ማሻሻያ
አድርገን ወደ ታች ማውረዳችን ይታወቃል። ከቀሪ 14ቱ ውስጥ
አንዱ #ከስመ #ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳ ችግር
ነው።
------------------------
በመሆኑም # ከስመ # ንብረት ዝውውር ጋር በተየያዘ የሚነሱ
ቅሬታዎች ለመፍታት የሚያስችል #የውሳኔ # ሀሳብ ለካቤኔ ቀርቦ
# ተቀባይነት አግኝቷል!
# ገቢዎች ፣ # ከተማ #ልማትና ገንዘብ ትብብር ቢሮ በጋራ
በመሆን የችግሩ #መነሻዎችን ከምንጩ ለመፍታት 9 ጉዳዮችን
በመለየት የውሳኔ ሀሳብ # ለካቢኔ በ26/6/2013 አቅርበናል።
ውሳኔውም ተቀባይነት አግኝቶ ወደ # ክልል #ምክር ቤት በጀትና
ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ እንዲላክ ተወስኗል። ወደ ምክር ቤት
የተላከበት ዋናው ምክንያትም ችግሩን ከስሩ ለመፍታት # የአዋጅ
# ማሻሻያ የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው።
ስለሆነም በቅርብ በክልል ምክር ቤት # በጉባኤ #የሚፀድቅ
ይሆናል የሚል ማጠቃልያ በርዕሰ መስተዳድራችን "በክቡር አቶ
አገኘሁ ተሻገር" አቅጣጫ ተቀምጧል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ለግንዛቤ ያክል ይነሱ የነበሩ ችግሮች ወይም ህዝቡ
ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች ምን ነበሩ ?
1.ህንፃው ከመተላለፉ በፊት ለሁለት አመት ተኖረበት/
አልተኖረበት ብሎ መለየት አስቸጋሪ መሆኑ፣ ለብልሹ አሰራር በር
ከፋች መሆኑ፣
2.የማውቅራዊ ፕላኑ፣የቤቱ ፕላን፣እና ካርታው ለመኖሪያ ቤት
ከሆነ ለምን ካፒታል ሀብት በማስተላለፍ በተገኝ ጥቅም ለምን
ግብር ይከፈላል?
3.ቅይጥ አገልግሎት(መኖሪያና ድርጅት)የሚሰጡ ህንፃወች
ሁሉም በድርጅት እንዲተላለፍ መደረጉ ተገቢ አይደለም?
4.በውርስ ህንፅ ወይም ግንባታን ለማስተላለፍ የስም ንብረት
ዝውውር ላይ የሚከፈል ክፍያ የተጋነነ ነው?
5. #ሰነድ # አልባ ወይም የተሟላ ሰነድ የሌላቸው ቤቶች ቤቱ
የተገኘበት (የተገዛበት) ባለመኖሩ ያላግባብ ግብር እንድንከፍል
ለምን እንከፍላለን?
7.በባንክና በፍርድ ቤት በጫራታ የተሸጠ ወይም በፍርድ ቤት
ለእዳ ማካካሻ የሚውሉ ቤቶች የሚከፈል ክፍያ የተጋነነ ነው ።
8.ወቅታዊ የገበያ ጥናት ግምት የተጋነነ ስለሆነ ያላግባብ ክፍያ
እየተጠየቅን ነው።
9. በየደረጃው የሚገኙ የገቢና የከተማ ልማትና ቤቶች
ኮንስትራክሽን ተቋም የቅንጅት ችግሮች የሚሉት ዋና ዋና
ችግሮች ናቸው።
እነዚህን የአሰራር ችግሮችን ለመፍታት በቅድሚያ አዋጁን
ማሻሻል ያስፈልጋል።
በመሆኑም ችግሮችን ለመፍታት እየሰራን በመሆኑ በቅርብ ወደ
መመሪያና አሰራር ተቀይሮ በሚመለከታቸው ተቋም በየራሱ
የሚወርድ ይሆናል።
እንደ ገቢዎች ተቋም በዚህ ተግባር ላይ የሚወጣን መመሪያና
የሚፀድቅን አዋጅ በተገቢው ተረድቶና አሰራር ዘርግቶ ለመፈፀም
እንዲቻል ከወዲሁ የተሟላ ግንዛቤ እንዲያዝበት እናደርጋለን!!
ግልፅ አሰራርን እንዘረጋለን፣ተጠያቂነትን እናሰፍናለን!!
"የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ"

11/02/2021

የተጨማሪ እሴት ታክስ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች
////
የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀጥተኛ ካልሆኑ የታክስ ዓይነቶች አንዱ
ሲሆን ታክሱ በእቃዎችና በአገልግሎቶች አቅርቦት ላይ የሚጣል
የፍጆታ ታክስ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ታክሱ በእቃዎች የማምረትና
ስርጭት ሂደት በየደረጃው በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት /
Value added/ ላይ የሚጣልና የታክስ መሠረቱን በማሥፋት
ለመንግሥት ተጨማሪ ገቢ የማስገኘት ዓላማ አለው፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ በምርትና በሥርጭት ሂደት በግብይቶች /
Input/ ላይ የተከፈለውን ታክስ እንዲቀናነስ በማድረግ የታክስ
ተደራራቢነትን ለማስቀረት የሚያስችል፤ በካፒታል እቃዎች ላይ
የማይጣል የፍጆታ ታክስ ከመሆኑም በላይ ቁጠባንና
ኢንቨስትመንት በማበረታታት ወደ ወጭ ለሚላኩ ምርቶች
የተከፈለውን የግብይት ታክስ ተመላሽ ሆኖ ካፒታልን በማሳደግ
ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
ታክሱ የንግድ እንቅስቃሴው እንዲጎለብት ከማስደረጉም በላይ
በተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ /VAT Invoice/ የታክስ
አስተዳደሩ በተለይ አስቀድሞ አውቆት በፈቀደውና
በሚቆጣጠረው የሚከናወን በመሆኑ የታክስ ስወራን ለመከላከል
ከማስቻሉም በላይ እራሱን በራሱ የሚቆጣጠር የታክስ ሥርዓት
ይዞ የሚገኝና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ባለሀብቶችን ከሌሎች
ሀገራት የታክስ ሥርዓት ጋር በማወዳደር ሀብታቸውን በማስገባት
ሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያበረታታና የሚጋብዝ የታክስ ሥርዓት
ነው፡፡
ተጨማሪ እሴት ታክስ መሠረቱ ሰፊ የሆነ በፍጆታ ዕቃዎችና
አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ታክስ ነው፡፡ ታክሱ ከአስመጪዎችና
ጥሬ ዕቃ አምራቶች አንስቶ እስከ ችርቻሮዎች ድረስ በሚደረጉ
የማምረት የማከፋፈል /የማሰራጨት /ሂደቶች በሁሉም
ደረጃዎች በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ ይሰበሰባል፡፡
በዚህም ምክንያት
• ምርት ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላው በሚተላለፍበት ወቅት
የሚፈጠርን የታክስ ተንከባላይነት ባህሪይ ቀደም ብሎ
የተከፈለውን ታክስ በማቀናነስ በታክስ ላይ ታክስ የማሰብ ሁኔታ
እንዳይፈጠር ያደርጋል፤
 ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከተሉት
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች አሉት፡-
• ወደ ወጭ ለሚላኩ ምርቶች የተከፈለውን የግብይት ታክስ
ተመላሽ በማድረግ የአገሪቱ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያዎች
ላይ በዋጋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
• በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች
ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡
• ለካፒታል ዕቃዎችም የሚደረገው የታክስ ነፃ እድል ቁጠባንና
ኢንቨስትመንትን ያበረታታል፡፡
• ታክስን ላለመክፈል የሚፈጸመውን ተግባር ለመከላከል የግበር
ከፋዩን ትርፍ ለማረጋገጥ አንዱ ታክስ መረጃ ምንጭ መሆኑ፣
ይህ ታክስ በፍጆታ ላይ ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ
የተመሰረተ ታክስ ነው፡፤ የሚሰበሰበው ወይም የሚቀረጠው፤
ምርት ከውጪ አገር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም ማንኛውም
የዕቃና የአገልግሎት ግብይት ሲካሄድ ነው፡፡

Timeline photos 23/01/2021

ሰንጠረዥ ሀ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ፡-
ማንኛውም ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከመቀጠር ከሚያገኘው
ጠቅላላ የወር ወይም የወሩ ከፊል ገቢ ላይ በምጣኔው መሰረት
በእያንዳንዱ ወር ግብር ይከፍላል፡፡
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ማስከፈያ ምጣኔ
ተቀጣሪው በመቀጠር የሚገኘውን ገቢ ለማግኘት የሚያወጣው
ማንኛውም ወጭ በተቀናሽነት ሊያዝለት አይችልም፡፡
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢዎች የሚባሉት፡-ሠራተኛው ካለፈው፣
አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው ቅጥር ጋር በተያያዘ
የተቀበለው
• ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣
• ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣
• የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም
• ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፣
• የዓይነት ጥቅማ ጥቅም ፣
• ተቀጣሪው ከሥራ ሲቀነስ፣
• ሥራውን ሲለቅ ወይም ሥራውን እንዲለቅ ለማግባባት
የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ
• የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣
• በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ የተቀበለው የገንዘብ
መጠን፣
• ከግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም፡፡

Timeline photos 21/01/2021

የሒሳብ መግለጫ
1. መዘጋጀት ያለበት የሒሳብ መግለጫ
1) ታክስ ከፋዩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሒሳብ
መግለጫዎች ማዘጋጀት እና ለገቢዎች ቢሮ ማቅረብ አለበት።
 መጀመሪያና መጨረሻ የሚዘጋጁ የንግድ ድርጅቱ የሒሳብ
መግለጫ፣
 የሀብት እና የዕዳ መግለጫ (balance sheet)፣
 የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ መግለጫ (Cash flow
statement)፣
 የድርጅቱ የካፒታል ለውጥ መግለጫ (Change of
capital statement)፣
 የትርፍና ኪሣራ መግለጫ (Profit and loss
statement)፣
 አምራች ድርጅት ከሆነ የምርት ሂደት መግለጫ
(Production statement) እና
 ለተመረተ ምርት የወጣ የምርት ወጪ መግለጫ
(Statement of Cost of Goods
Manufactured) ።
2) ታክስ ከፋዩ ንግድ ፈቃድ ያወጣበት የንግድ መስክ ከአንድ
በላይ በሆነ ጊዜ ንዑስ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ተጠቅሞ
እያንዳንዱን የንግድ እንቅስቃሴ በተናጠል በተዘጋጀ በሂሳብ
መዝገብ በመመዝገብ በዓመቱ መጨረሻ በዋናው የታክስ ከፋይ
መለያ ቁጥር የተጠቃለለ የሒሳብ መግለጫ ማዘጋጀት አለበት።
3) ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ቢኖርም ከአንድ በላይ በሆኑ
ክልሎች ወይም የከተማ አስተዳደሮች ቤት በማከራየት ወይም
የንግድ ሥራ በማከናወን የተሰማራ ግለሰብ ታክስ ከፋይ
ለእያንዳንዱ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር በተናጠል የተዘጋጀ
የሒሳብ መግለጫ ማቅረብ አለበት።

Timeline photos 21/01/2021

የሒሳብ መዝገብና ሰነድ አያያዝ ሥርዓትን ለመወሰን
የወጣ መመሪያ ቁጥር አገቢ 14/2012
በአማራ ሬዲዮ ቅዳሜ ጥር 15 /2013 ዓ.ም ከቀኑ 9:25
ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በግብር ትምህርት ባለሙያ አቶ አለልኝ
አበጀ ስለሚቀርብ እንድትከታተሉ ማሳሰብ እንወዳለን።
የሒሳብ መዝገብና ሰነድ አያያዝ ሥርዓትን ለመወሰን የወጣ
መመሪያ ቁጥር አገቢ 14/2012
የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የተጣለበት ታክስ ከፋይ
የሚይዘው የሂሳብ መዝገብ ሊያሟላ የሚገባውን ዝርዝር ሁኔታ
መደንገግ በማስፈለጉ፣
ታክስ ከፋዩ ከሚይዘው የሂሳብ መዝገብ ጋር ተያይዘው መቅረብ
ያለባችውን ሰነዶች በዝርዝር ማመላከት በማስፈለጉ፣
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በገቢ ግብር
አዋጅ ቁጥር 240/2008 አንቀጽ 79 ንዑስ አንቀጽ 7 እና በገቢ
ግብር ደንብ ቁጥር 162/2010 አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 1
ላይ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የሒሳብ መዝገብና ሰነድ አያያዝ ሥርዓትን
ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር አገቢ
14/2012” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
2. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ ትርጉም ያልተሰጣቸው ቃላትና ሀረጎች
በክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ እና በታክስ አስተዳደር አዋጅ
የተሰጣቸውን ትርጉም ይይዛሉ። ከዚህ በተጨማሪ የቃሉ አገባብ
ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር ለዚህ መመሪያ
አፈፃፀም ሲባል፡-
1) “ሰነድ” ማለት የክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ(Voucher)፣ የውል
ስምምነት፣ የጉምሩክ ዲክለራሲዮን፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ለታክስ ወኪል የተሰጠ
የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት፣ ለሒሳብ ባለሙያነት ወይም
ለግል ኦዲተሮች የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት
እንዲሁም ለታክስ አስተዳደር እና አወሳሰን የሚረዱ መሰል
መረጃዎችን የያዘ ሰነድ ነው፡፡
2) “የሒሳብ መዝገብ” ማለት ታክስ ከፋዩ የንግድ ሥራ ሀብትና
ዕዳ እንዲሁም የዕለት ተዕለት ገቢውን እና ወጪውን
የሚመዘግብበት በሂሳብ ባለሙያ የተዘጋጀ መዝገብ (Journal
and Ledger ) ነው።
3) “የሒሳብ መዝገብ መግለጫ” ማለት የታክስ ከፋዩ የንግድ
እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ሰነድ ሲሆን የሀብትና ዕዳ
መግለጫ፣ የትርፍና ኪሳራ መግለጫ እና የገንዘብ ፍስሰት
እንቅስቃሴ መግለጫ የሚያካትት ነው።
4) “የሦስተኛ ወገን መረጃ” ማለት ከታክስ ከፋዩና ከገቢዎች
ቢሮ ውጭ በሆነ ሰው እጅ የሚገኝና ታክስ ከፋዩ ያደረጋቸውን
ግብይቶች የሚያሳይ የግዥ ወይም ሽያጭ የሰነድ መረጃ ነው።
5) “ ገቢዎች ቢሮ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ገቢዎች ቢሮ ማለት ሲሆን በየደረጃው እርከን የሚገኙ የገቢ
ተቋማትንም ይጨምራል።
6) “አዋጅ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገቢ
ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 ነው
7) “ደንብ” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገቢ
ግብር አዋጅን ለማስፈጸም የወጣ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት
ደንብ ቁጥር 162/2010 ነው
8) “ ኃላፊ “ ማለት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይም ሚወክለው
የሥራ ኃላፊ ወይም በየደረጃው የሚገኝ የገቢ ጽ/ቤት ኃላፊ
ነው፡፡
3. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ባለበት ታክስ
ከፋይ እና በፈቃደኝነት የሂሳብ መዝገብ በሚይዝ ታክስ ከፋይ
ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
ክፍል ሁለት
የሒሳብ መዝገብ እና የሂሳብ መግለጫ ይዘት
4. የሒሳብ መዝገብን ስለመያዝ
1) በአዋጁ አንቀፅ 79 መሠረት፡-
ሀ) የደረጃ “ሀ”፣ የደረጃ “ለ” ታክስ ከፋይ
ለ) በፈቃደኝነት የሒሳብ መዝገብ የሚይዝ የደረጃ “ሐ” ታክስ
ከፋይ እና
ሐ) የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ ጥቅም የሚያገኝ ሰው
የሒሳብ መዝገብ መያዝ ግዴታ አለበት፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም
ለእያንዳንዱ ሠንጠረዥ ራሱን የቻለ የሂሳብ መዝገብና
መግለጫ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
5. የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ ለሚገኝ ጥቅም የሚያዝ
የሂሳብ መዝገብ
1) የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ ከሚገኝ ጥቅም ታክስ
የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ማንኛውም ታክስ ከፋይ
ሀ) የተላለፈው የካፒታል ሀብት የተገኘበትን ቀን፣
ለ) የተላለፈው የካፒታል ሀብት የተገኘበትን ዋጋ
ሐ) ሀብቱን ለማሻሻል የወጣ ሌላ ማንኛውም ወጪ እና
መ) ሀብቱ በሚተላለፍበት ጊዜ ለታክስ ከፋዩ የተከፈለ
የማስተላለፊያ ዋጋ አጠቃሎ የሚያሳይ ሂሳብ መዝገብ የመያዝ
ግዴታ አለበት፡፡
2) ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም “የካፒታል ሀብት ማስተላለፍ” ማለት
የካፒታል ሀብት በሽያጭ፣ በስጦታ፣ በእርዳታ፣ በአይነት መዋጮ
መልክ ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
3) ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 አፈጻጸም የካፒታል
ሀብት በአይነት መዋጮነት ሲተላለፍ የካፒታል ሀብት
በማስተላለፍ በሚገኝ ጥቅም ላይ ግብር የሚወሰን ባይሆንም
የተላለፈው የካፒታል ሀብት ማስተላለፊያ ዋጋ የካፒታል ድርሻው
ዋጋ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
6. የደረጃ ለውጥ ስለማድረግ
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ የደረጃ ለውጥ በሚደርግበት ጊዜ
ታክስ ከፋዩ በአዲስ በአገኘው የታክስ ከፋይነት ደረጃ መሠረት
የሚጠበቀውን ሒሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ወይም ያለመያዝ
መብት ተግባራዊ የሚያደርገው የደረጃ ለውጥ ከተደረገበት
የሂሳብ ጊዜ ቀጥሎ ባለው የታክስ ዘመን የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ
ነው
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም ቀጥተኛ
ያልሆነ ታክስ የሚከፍሉ ታክስ ከፋዮችን በተመለከተ ታክስ ከፋዩ
ለታክሱ ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ እንደ አግባብነቱ ለተጨማሪ
እሴት ታክስ ወይም ለተርን ኦቨር ታክስ በተቀመጠው የታክስ
ማስታወቂያ ጊዜ ውስጥ ታክሱን አስታውቆ መክፈል አለበት፡፡
7. ታክስ ከፋይ መያዝ ያለበት የሰነድ ዓይነት
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ሰነዶች መያዝ ያለበት
ሲሆን ሲጠየቅ ለገቢዎች ቢሮ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ሀ) የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርትፊኬት፣
ለ) የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት
ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣
ሐ) ከተከፋይ ሒሳብ ላይ ታክስ ቀንሶ እንዲያስቀር ግዴታ
የተጣለበት ከሆነ የምዝገባ ምስክር
ወረቀት ፣
መ) የንግድ ዋና ምዝገባና የንግድ ሥራ ፈቃድ፣
ሠ) የሙያ ሥራ ፈቃድ፤
ረ) በውል መሠረት ለሚፈፀሙ ሥራዎች የተረጋገጠ የውል
ሰነድ፣ የክፍያ ሠርተፊኬት፣ የልኬት
ማስረጃ (bill of quantity) እና ሌላ በሶስተኛ ወገን
ሊረጋገጥ የሚችል የሶስተኛ ወገን
ማስረጃ/ካለ/፤
ሰ) ክፍያ የፈጸመው ባንክ ክፍያ ለመፈጸም ማረጋገጫ የሰጠበት
የባንክ ፈቃድ፤
ሸ) ለድርጅት ታክስ ከፋዮች በሚመለከተው አካል የፀደቀና
የተመዘገበ የካፒታል መጠን የሚገልጽ
ሰነድ፣ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ፣
ቀ) ከደንበኛ እና አቅራቢ የሚሰጥ ሕጋዊ የግብይት ደረሰኝ
ወይም ታክስ የተከፈለበት ሕጋዊ
ሰነድ፤
በ) የሠንጠረዥ “ሀ” ታክስ ከፋይ ለተቀጣሪዎቹ በየወሩ ደመወዝ
የከፈለበትን እና ተቀናሽ
ያደረገውን ታክስ የሚያሳይ የደመወዝ መክፈያ መዝገብ
(Payroll),
ተ) የንግድ ሥራ ሀብት ትክክለኛው ዋጋ ያልተገኘለት እንደሆነ
የንግድ ሥራ ሀብት ዋጋ የመገመት
ሥልጣን ከተሰጠው አካል የተዘጋጀ የዋጋ መግለጫ ሰነድ፣
ቸ) በታክስ ዘመኑ የተወገደ የንግድ ሥራ ሀብት የሽያጭ ዋጋ፣
በተፈጥሮ አደጋ ለወደመ ወይም
በሌላ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ለውጥ ለተደረገበት
ሀብት የተፈጸመ የካሣ ክፍያ ካለ
የክፍያ ማስረጃ፤
ኀ) የታክስ እፎይታ ወይም የታክስ ነፃ መብት ያለው ታክስ ከፋይ
ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ
ማስረጃ፤
ነ) የታክስ ስሌት የተዘጋጀው በተፈቀደላቸው የሒሳብ
ባለሙያዎች ወይም በውጭ ኦዲተሮች ከሆነ
ለሒሳብ ባለሙያዎች ወይም ለውጭ ኦዲተሮች የተሰጠውን
የምስክር ወረቀት፣
ኘ) ታክስ ከፋዩ ታክስ ያስታወቀበት የታክስ ማስታወቂያ ሰነድ እና
ታክስ የተከፈለበት ሕጋዊ ሰነድ፤
አ) ፈቃድ በተሰጠው የታክስ ወኪል ለታክስ ከፋዩ በየጊዜው
የተሰጠ የምስክር ወረቀት ወይም
መግለጫ፤
ከ) የሒሳብ መዝገቡን ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ማንኛውም
ሌላ ሰነድ፤
8. ታክስ ከፋዩ የሚይዘው የሒሳብ መዝገብ
1) የደረጃ ሀ ታክስ ከፋይ የሒሳብ መዝገቡን የሚይዘው
በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ መሠረት መሆን
አለበት።
2) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም ታክስ ከፋዩ
የኦዲት ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራዊ እስከሚያደርግ
ድረስ አጠቃላይ ተቀባይነት ያለውውን ሒሳብ መዝገብ መርህ
(Generally Acceped Accounting Principles -
GAAP) መሠረት በማድረግ የሂሳብ መዝገቡን ማዘጋጀት
አለበት፡፡
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) የተደነገገው
ቢኖርም የደረጃ “ለ” ታክስ ከፋይ ቀለል ያለ የሂሳብ አያያዝ
ሥርዓት በመጠቀም የሒሳብ መዝገብ መያዝ ይችላል፡፡
4) ታክስ ከፋዩ የሚያከናውነውን እያንዳንዱን ግብይት
የሚመዘግብበት የሒሳብ መዝገብ ሕጋዊነት እና ትክክለኛነት
የሚያረጋግጥ የጊዜ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ የተዘጋጀ ደጋፊ
ሰነድ መያዝ አለበት፡፡
5) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጥ (4) የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ ታክስ ከፋዩ የሚይዘው የሂሳብ መዝገብ ከንግድ ሥራ ጋር
በተያያዘ በየቀኑ የሚገኘውን ማናቸውንም ገቢ እና
የሚያወጣውን ወጪ የሚያሳይ ሆኖ የሚከተሉትን ሰነዶች መያዝ
አለበት፡፡
ሀ) በታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ መሠረት
ተቀባይነት ያለው ሕጋዊ የእጅ በእጅና ሽያጭ ደረሰኝ፣ የዱቤ
ሽያጭ ደረሰኝ እና የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ እንዲሁም የዴቢት
ወይም ክሬዲት ሰነድ፤
ለ) በኤሌክትሮኒክስ የመረጃ ማከማቻ መሣሪያ ውስጥ
ተከማችቶ የተያዘ ማናቸውም መረጃ ፤
ሐ) ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ተቀናሽ በሚሆንበት ጊዜ ተቀናሽ
የተደረገውን ግብር የሚያሳይ ደረሰኝ፣
መ) ታክስ ከፋዩ ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀናሽ የተደረገበትን
የግብር ዘመን የሚያሳይ ደረሰኝ፣
ሠ) ታክስ ከፋዩ ወደ አገር ውስጥ ላስገበው እቃ ቀረጥና ታክስ
የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን እንዲሁም
የዕቃ መልቀቂያ ሰነድ እና የክፍያ ደረሰኝ፤
ረ) ታክስ ከፋዩ ወደ አገር ውስጥ እቃ ሲያስገባ የተቀነሰበትን
ሶስት በመቶ (3%) የንግድ ትርፍ ግብር እና በአገር ውስጥ
ግብይት ሲያከናውን የተቀነሰበትን ሁለት በመቶ (2%) የንግድ
ትርፍ ግብር ከኣመታዊ ግብሩ ያቀናነሰበትን ሂሳብ የሚያሳይ
ዝርዝር ሠንጠረዥ እና ደረሰኝ
6) ማንኛውም የሒሳብ መዝገብ የሚይዝ ታክስ ከፋይ
የሚያከናውነውን እያንዳንዱን ግብይት እንዲሁም የገንዘብና
የንብረት (ሀበት) ገቢ እና ወጪ የሚመዘግብበት የሒሳብ
መዝገብ መያዝ አለበት፡፡
7) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 የተመለከተው እንደተጠበቀ
ሆኖ ማንኛውም የደረጃ “ሀ” እና የደረጃ “ለ” ታክስ ከፋይ
በታክስ ከፋይነት ለተመዘገበበት እና የንግድ ፈቃድ ላወጣበት
ለእያንዳንዱ የንግድ መስክ ያዋለውን ሀብት እና ኢንቨስትመንት
እንዲሁም በእያንዳንዱ ዘርፍ ከተደረገው የንግድ እንቅስቃሴው
የተገኘው ትርፍ ወይም ኪሣራ በትክክል የሚያሳይ በሀርድ ኮፒ
እና በሶፍት ኮፒ ተደራጅቶ የተያዘ ሰነድ መያዝ አለበት፡፡
8) ማንኛውም የሒሳብ መዝገብ የሚይዝ ታክስ ከፋይ፡-
ሀ) ጥቃቅን የጥሬ ገንዘብ ወጪዎች (petty cash)
የተመዘገበበት፣
ለ) የሣጥንና የባንክ ሒሳብ የተመዘገበበት፤
ሐ) ተሰብሳቢ ሒሳብ የተመዘገበበት፣
መ) የሚተላለፉ የሂሳብ ሰነዶች (Transferable
commercial instruments) የተመዘገቡበት፣
ሠ) የቅድሚያ ክፍያ ወጪዎች (Prepaid) እና የአጭር ጊዜ
የኢንቨስትመንት ወጪዎች
የተመዘገቡበት፣
ረ) የንግድ ግብዓቶች (supply, spare part, accessory
and others) ጥቅም ላይ ሲውሉ
ወጪው የተመዘገበበት፣
ሰ) ለንግድ የሚውል ያልተሸጠ ንግድ ዕቃ (stock) እና
የኮንስትራክሽን ግብዓትና ጥሬ ዕቃ
በዓይነት፣ በመጠንና በዋጋ ጥቅም ላይ የዋለ እና ያልዋለ
ተለይቶ የተመዘገበበት፣
ሸ) በምርት ሂደት የወጡ ወጪዎችና ጥቅም ላይ የዋሉ
ግብዓቶችን ወይም በግንባታ ላይ ላለ
ኮንስትራክሽን የወጣ ወጪ (የተሰራ ስራ መጠን በመቶኛ)
እንዲሁም ተመርቶ የተጠናቀቀ
ምርት ዋጋ (Value of finished goods) የተመዘገበበት
መሆን አለበት።
9. የንግድ ዕቃ ቆጠራ (Stock Inventory)
ዕቃዎችን በነጠላ መመዝገብ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ታክስ
ከፋዩ ይህንኑ ለገቢዎች ቢሮ አሰቀድሞ በማሳወቅ የእቃው ብዛት
እና ዋጋ በጥቅል ወይም በእሽግ እየተገለጸ በንብረት
መመዝገቢያ መዝገብ እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡
10. የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ
1) ታክስ ከፋዩ ያለውን የንግድ ስራ ሀብት እንደ ዓይነቱ እና
እንደ አገልግሎቱ በመለየት የሚመዘግብበት የንግድ ሥራ ሀብት
መዝገብ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን የዚህ ኣይነት መዝገብ፣
ሀ) እያንዳንዱ የንግድ ሥራ ሀብት የተገዛበት ወይም የተገኘበት
ቀን እና ዋጋ፣
ለ) የንግድ ሥራ ሀብቱን ለማሻሻል የተደረገ ማንኛውም ከሀያ
በመቶ (20%) በላይ የሆነ ወጪ፣
ሐ) በየዓመቱ መጨረሻ የንግድ ሥራ ሀብቱ ያለውን የተጣራ
የመዝገብ ዋጋ፣
መ) የእያንዳንዱ የተጠራቀመ የእርጅና ቅናሽ መጠን የሚሳይ
መሆን አለበት፡፡
2) ኢንቨስትመንት የሚያካሂድ ታክስ ከፋይ የኢንቨስትመንት
ሥራው ተጠናቆ የኢንቨስትመንቱ አጠቃላይ ካፒታል እስኪታወቅ
ድረስ በጊዜው የሚያወጣውን ወጪ የሚመዘገብበት ራሱን የቻለ
መዝገብ (Ledger) ሊኖረው ይገባል፡፡
11. የዕዳ ወይም የተከፋይ ሂሳቦች መዝገብ (book of
liability)
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ ብድር በሚወስድበት ጊዜ ወይም
የዱቤ ግዥ በሚፈጽምበት ጊዜ የእዳ መመዝገቢያ መዝገብ
መያዝ ያለበት ሲሆን መዝገቡ የሚከተሉትን አካቶ የያዘ መሆን
አለበት፡፡
ሀ)የብድር ወይም የዱቤ ሽያጭ ስምምነት፣
ለ) የእዳ አከፋፈል ሁኔታ (Mode of payment)፣
ሐ) የአበዳሪው ወይም እቃ ወይም አገልግሎት በዱቤ የሸጠው
ሰው ሙሉ መረጃ።
መ) የተመዘገበ የእዳ መያዣ(ዋስትና)
2) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ቢኖርም ታክስ ከፋዩ
የፋይናንስ ተቋም ካልሆነ አካል የሚበደረው ገንዘብ ከብር
አምስት መቶ በላይ ከሆነ የብድር ውሉ በሚመለከተው አካል
የተመዘገ መሆን አለበት፡፡
12. የተጣራ ካፒታል ሒሳብ መዝገብ
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ የድርጅቱን ካፒታል የሚመዘግብበት
የሂሳብ መዝገብ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን መዝገቡ የሚከተለውን
መያዝ አለበት፡፡
ሀ) ካፒታሉ የግል ወይም በአክስዮን መዋጮ የተገኘ መሆኑን
የሚያሳይ ሰነድ፣
ለ) በአክሲዮን ድርሻ የተያዘ የካፒታል መጠን፣
ሐ) የተከፈለ እና ያልተከፈለ የካፒታል መጠን፣
መ) ያልተከፋፈለ የትርፍ መጠን፣
ሠ) ለካፒታል ማሳደጊያ የዋለ የትርፍ መጠን፣
ረ) የተከፋፈለ የትርፍ ድርሻ መጠን፣
2) ታክስ ከፋዩ የግለሰብ ንግድ ድርጅት ከሆነ የባለቤቱ የግል
ወጪ ራሱን ችሎ የሚመዘግብበት መዝገብ መያዝ አለበት።
13. ጊዜያዊ የሒሳብ መዝገብ (temporary book of
account)
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ የድርጅቱን ጊዜያዊ ግዥ እና ሽያጭ
የሚመዘግብበት የሂሳብ መዝገብ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን
መዝገቡ የሚከተለውን መያዝ አለበት።
ሀ) ለሽያጭ የተገዛ እቃ (merchandise goods)
ለ) በአንድ ዓመት ውስጥ የሚሸጥ ወይም ወደ ምርት የሚቀየር
የምርት ወይም የኮንስትራክሽን
ግብዓት ግዥ፣
ሐ) ተመላሽ የተደረገ ግዥ (Overage),
መ) በቅናሽ የተደረገ ግዥ (Purchase on Discount)
ሠ) በአመቱ ውስጥ የተደረገ የእጅ በእጅ ሽያጭ፣ የዱቤ
ሽያጭ፣
ረ) የሽያጭ ተመላሽ (Sales Return) ፣
ሰ) በድርጅቱ የሽያጭ ፖሊሲ መሠረት የተፈቀደ የሽያጭ ቅናሽ
(Sales Discount)
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው እንደተጠበቀ
ሆኖ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ሽያጭ ወይም ኮንስትራክሸን
ወይም የምርት ስራን ሲከናውን ያወጣው የተለያየ አስተዳደራዊ
ወጪ እና በዓመቱ መጨረሻ የሚደረግ የሒሳብ ማስተካከያ
የሚመዘገብብት መዝገብ መያዝ አለበት።
3) ታክስ ከፋዩ ከዋናው የንግድ እንቅሰቃሴ ውጪ የተገኘ ገቢ
ወይም የወጣ ወጪ የሚመዘገብበት መዝገብ መያዝ ያለበት
ሲሆን በቻርት የተደገፈ የሒሳብ ዝርዝር አካውንት መግለቻ
(chart of account) ሰነድ መያዝ አለበት።
14. የሒሳብ መግለጫ
1) ታክስ ከፋዩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሒሳብ
መግለጫዎች ማዘጋጀት እና ለገቢዎች ቢሮ ማቅረብ አለበት፡፡
ሀ) መጀመሪያና መጨረሻ የሚዘጋጁ የንግድ ድርጅቱ የሒሳብ
መግለጫ፡
ለ) የሀብት እና የዕዳ መግለጫ (balance sheet)፣
ሐ) የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ መግለጫ (Cash flow
statement) ፣
መ) የድርጅቱ የካፒታል ለውጥ መግለጫ (Change of
capital statement) ፣
ሠ) የትርፍና ኪሣራ መግለጫ (Profit and loss
statement) ፣
ረ) አምራች ድርጅት ከሆነ የምርት ሂደት መግለጫ
(Production statement) እና
ሰ) ለተመረተ ምርት የወጣ የምርት ወጪ መግለጫ
(Statement of Cost of Goods
Manufactured)
2) ታክስ ከፋዩ ንግድ ፈቃድ ያወጣበት የንግድ መስክ ከአንድ
በላይ በሆነ ጊዜ ንዑስ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (Sub-TIN)
ተጠቅሞ እያንዳንዱን የንግድ እንቅስቃሴ በተናጠል በተዘጋጀ
በሂሳብ መዝገብ በመመዝገብ በዓመቱ መጨረሻ በዋናው
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የተጠቃለለ የሒሳብ መግለጫ
(consolidated financial statement) ማዘጋጀት አለበት፡፡
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተጠቀሰው ቢኖርም
ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ወይም የከተማ አስተዳደሮች ቤት
በማከራየት ወይም የንግድ ሥራ በማከናወን የተሰማራ ግለሰብ
ታክስ ከፋይ ለእያንዳንዱ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር
በተናጠል የተዘጋጀ የሒሳብ መግለጫ ማቅረብ አለበት፡፡
15. መረጃ እንዲቀርብ ስለሚሰጥ ማስታወቂያ
1) ገቢዎች ቢሮ ለታክስ አስተዳደር ወይም ለታክስ አወሳሰን
የሚጠቅም ማንኛውንም መረጃ እንዲያቀርብ ታክስ ከፋዩን
ወይም መረጃውን ይዞ የሚገኝ ማንኛውንም ሰው ሊያዝ
ይችላል፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ገቢዎች ቢሮ መረጃ
እንዲቀርብለት የሚልከው ማስታወቂያ መረጃው የሚቀርብበትን
ጊዜ እና የመረጃውን ዓይነት መግለጽ አለበት፡፡
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ቢኖርም ገቢዎች
ቢሮ መረጃ እንዲቀርብለት በሚልከው ማስታወቂያ የሚወስነው
ጊዜ መረጃውን ለማደራጀት የሚያስፈልገውን ጊዜ እና መረጃው
የሚገኝበት ቦታ እርቀት ከግምት ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን
መረጃውን ለማቅረብ የሚሰጠው ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ ከአስር
ቀን ያነሰ መሆን የለበትም፡፡
4) ገቢዎች ቢሮ ማንኛውንም ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ወይም
መረጃ እንዲያቀርብ ለተጠየቀው ሰው የሚያደርሰው በታክስ
አስተዳደር አዋጁ አንቀጽ 80 መሠረት ሆኖ በህጉ በተደነገገው
መሠረት ማስታወቂያውን ለታክስ ከፋዩ ወይም መረጃ
እንዲያቀርብ ለተጠየቀው ሰው ማድረስ ያልተቻለ እንደሆነ
ማስታወቂውን በታክስ ከፋዩ ወይም መረጃውን እንዲያቀርብ
በተጠየቀው ሰው የንግድ አድራሻ ወይም መኖሪያ ቤት ግቢ
ውስጥ ወይም በር ላይ በመለጠፍ ማስታወቂያው በትክክል
መድረሱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
5) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት ማስታወቂያውን
ለታክስ ከፋዩ ወይም መረጃ እንዲያቀርብ ለተጠየቀው ሰው
ለማድረስ የንግድ አድራሻ ወይም መኖሪያ ቤት አድራሻ ከጠፋ
የሕዝብ ማስታወቂያ በሚለጠፍበት ቦታ በመለጠፍ
ማስታወቂያው በትክክል መድረሱን ማረጋገጥ አለበት፡
16. የሒሳብ መዝገብ ለማዘጋጀት ሶፍትዌር ስለመጠቀም
1) ማንኛውም ታክስ ከፋይ የሂሳብ መዝገብ ለማዘጋጀት
ሶፍትዌር የሚጠቀም ከሆነ ሶፍትዌሩን ከአጠቃቀም ማንዋል ጋር
ለገቢዎች ቢሮ ማቅረብ አለበት፡፡
2) ገቢዎች ቢሮ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የሂሳብ
መዝገብ ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የሚውል ሶፍትዌር ሲቀርብለት
ሶፍትዌሩ ለታክስ አስተዳደሩ አመቺ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
3) ታክስ ከፋዩ የሒሳብ መዝገብ ለማዘጋጀት በሚጠቀምበት
ሶፍትዌር ላይ ለውጥ በሚደርግበት ጊዜ ለገቢዎች ቢሮ ማሳወቅ
አለበት፡፡
17. የሂሳብ መዝገብ ባለመያዝ ከሚጣል መቀጫ ነጻ ስለመሆን
1) በፈቃደኝነት የሒሳብ መዝገብ የሚይዙ የደረጃ “ሐ” ታክስ
ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ ሳይዙ በመቅረታቸው ወይም
መዝገባቸው ተቀባይነት በማጣቱ ምክንያት መዝገብ ባለመያዝ
የሚጣለው መቀጫ ተፈጻሚ አይሆንባቸውም፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
በፈቃደኝነት ሂሳብ መዝገብ ለመያዝ ደረሰኝ ያሳተመ ታክስ ከፋይ
በበጀት አመቱ መጨረሻ ሂሳብ መዝገብ የማያቀርብ ከሆነ
ያስፈቀደውን ደረሰኝ ለገቢ ተቋሙ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
18. ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ስለሚይዙት የሒሳብ መዝገብ
ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች እንደ ግለሰብ ታክስ ከፋይ ተቆጥረው
ዓመታዊ ገቢያቸውን መሠረት
በማድረግ በሚመደቡበት የግብር ከፋይ ደረጃ መሠረት የሒሳብ
መዝገብ እንዲይዙ ይደረጋል፡፡
19. የወጪ ማስረጃ ውድቅ ሲደረግ ተቀናሽ ስለሚደረግ ወጪ
1) የሒሳብ መዝገብ የሚይዝ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ያቀረበው
የወጪ ማስረጃ በገቢዎች ቢሮ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውድቅ
ሲደረግ ወጪው ገቢውን ለማመንጨት ወይም የድርጅቱን
እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ወይም ለድርጅቱ ዋስትና ለመስጠት
የወጣ ወጪ መሆኑ ተረጋግጦ፡-
ሀ)ለቋሚ የንግድ ሥራ ሀብት ዕቃዎች በተሰራበት ወይም
በተገዛበት ወቅት የእቃው የገበያ ዋጋ
ሰባ በመቶ (70%)
ለ) ሌሎች እቃዎች ግዥ የእቃዎቹ የገበያ ዋጋ ስልሳ አምስት
በመቶ (65%) በወጪነት በመያዝ
ተቀናሽ ይደረጋል።
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም
የቀረበው ወጪ ገቢውን ለማመንጨት ወይም የድርጅቱን
እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ለድርጅቱ ዋስትና ለመስጠት የወጣ
ወጪ አለመሆኑ ከተረጋገጠ ወጪው ሙሉ በሙሉ ውድቅ
ይደረጋል።
20. በውጭ ምንዛሪ እና በዋጋ ልዩነት ላይ ስለሚከፈል ግብር
1) ታክስ ከፋዩ እቃ ወደ አገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ
የባንክ ክፍያ ማዘዣ (Letter of Credit) ሲከፈት በነበረው
የውጭ ምንዛሪ እና እቃው ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ባለው
የውጭ ምንዛሪ መካከል በሚኖረው ልዩነት ላይ የንግድ ትርፍ
ግብር መከፈል አለበት፡፡
2) በውጭ ንግድ የተሰማራ ታክስ ከፋይ እቃ ወደ ውጭ አገር
በሚልክበት ጊዜ ለጉምሩክ ባሳወቀው የእቃ መሸጫ ዋጋ እና
በባንክ በተላከው የመሸጫ ዋጋ የውጭ ምንዛሬ ልዩነት ላይ
የንግድ ትርፍ ግብር መከፈል አለበት፡፡
3) እቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባ ታክስ ከፋይ ለጉምሩክ
ያቀረበው የግዥ ኢንቮይስ ውድቅ ተደርጎ ለእቃው በኢንቮይሱ
ከተገለጸው ዋጋ በላይ በሚሰጥበት ጊዜ ታክስ ከፋዩ የእቃውን
የአገር ውስጥ መሸጫ ዋጋ ሲወስን ለእቃው ጉምሩክ የሰጠውን
ዋጋ መነሻ ማድረግ ያለበት ሲሆን ሌሎች ወጪዎች
እንደተጠበቀ ሆኖ የእቃው የመግዣ ዋጋ (Cost) ተደርጎ
መወሰድ ያለበትም ጉምሩክ ለእቃው የሰጠው ዋጋ ነው።
21. የሥራ ግብር ሲከፈል ተቀናሽ ለሚደረግ ወጪ መቅረብ
ያለበት ሰነድ
1) ታክስ ከፋዩ የሥራ ግብር በሚከፍልበት ጊዜ ያወጣው ወጪ
የሚያዝለት የሥራ ግብሩ ተቀናሽ የተደረገበት ተቀጣሪ ሙሉ
ስምና የሚከፈለውን የደመወዝ መጠን የያዘ ማስረጃ ሲያቀርብ
ነው’
2) ቀጣሪው ለገቢዎች ቢሮ የሚያቀርበው የደመወዝ መክፈያ
ሰነድ ክፍያው በባንክ ወይም በሦስተኛ ወገን የተከፈለ ካልሆነ
በስተቀር በሰራተኛው የተፈረመበት መሆን አለበት።
22. ሰነድን በሚመለከተወው አካል ስለማስመዝገብ
1) ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የኪራይ ውሎች ሶስት ወር እና ከዚያ
በላይ የሚቆዩ ከሆነ የውል ስምምነቱ በተፈረመበት ጊዜ
በሚመለከተው አካል መመዝገብ አለበት።
ሀ) ለንግድ ዓላማ የሚውል የቤት ኪራይ፤
ለ) የጥናት አገልግሎት ግዥ፣
ሐ) የመጋዘን ኪራይ፤
መ) ማንኛውም ዓይነት የማሽነሪ ኪራይ፤
ሠ) የንግድ ተሽከርካሪ ኪራይ፣
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም የኪራይ
ውሉ የተደረገው ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር ከሆነ ውሉ
መመዝገብ አያስፈልገውም፡፡
3) ማንኛውም በሚመለከተው አካል ያልተመዘገበ የውል ሰነድ
በማስረጃነት በሚቀርብበት ጊዜ ሁለት እጥፍ የቴምብር ቀረጥ
ሊከፈልበት ይገባል።
4) በዚህ አንቀጽ ንዑስ 1 እና 3 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
ሶስት ወር እና ከሶስት ወር በላይ የቆየ የኪራይ ወይም የጥናት
አገልግሎት ውል ስምምነት ያልተመዘገበ መሆኑ ከተረጋገጠ
ሰነዱ ውድቅ ተደርጎ ወጪው በግምት ይወሰናል።
23. የሒሳብ መዝገብ ሰነድ ስለማዘጋጀት
የሒሳብ መዝገብ መያዝ ያለበት ታክስ ከፋይ የሂሳብ መዝገቡ
የሙያ ፈቃድ ባላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ወይም ሙያው እና
የትምህርት ዝግጅቱ ባላቸው ተቀጣሪ የሒሳብ ሠራተኞች
እንዲዘጋጅ ማድረግ ያለበት ሲሆን ታክስ ከፋዩ የትምህርት
ዝግጅት እና ሙያዊ ብቃት ያለው ከሆነ የሒሳብ መዝገቡን ራሱ
ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
ክፍል ሶስት
የተወገደ ዕቃን በወጪነት ስለመመዝገብ
24. መርህ
1) በዚህ መመሪያ አንቀጽ 25 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
ማንኛውም ታክስ ከፋይ አገልግሎት የማይሰጡ ወይም ጥቅም
ላይ የማይውሉ የተበላሹ ወይም የተጎዱ ዕቃዎችን የገቢዎች
ቢሮ ተወካይ በተገኘበት ማስወገድ ይችላል።
2) ታክስ ከፋዩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የንግድ
ዕቃ ሲያስወግድ ለገቢዎች ቢሮ ማሳወቅ አለበት።
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 መሠረት የተወገደ እቃ
ዋጋ ለታክስ ከፋዩ ተቀናሽ ይደረግለታል።
25. በተቆጣጣሪ አካለት የሚወገዱ ዕቃዎች
1) ታክስ ከፋዩ በተቆጣጣሪ አካላት ውሳኔ የሚወገዱ እቃዎች
ዋጋ ተቀናሽ እንዲደረግለት ጥያቄ ሲያቀርብ እቃው ስለመወገዱ
የሚያረጋግጥ ከተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት ማቅረብ አለበት።
2) ዕቃው በተቆጣጣሪ አካል የሚወገድ ሆኖ የማስወገጃ ቦታ
ባለመገኘቱ ምክንያት ሊወገድ ካልቻለ ታክስ ከፋዩ አስወጋጁ
ዕቃውን ስለመረከቡ የሚገልጽ ማስረጃ ከተቆጣጣሪው መስሪያ
ቤት ሲያቀርብ የአቃው ዋጋ በወጪነት እንዲያዝለት ይደረጋል።
26. ዕቃ ለማስወገድ ስለሚቀርብ ማመልከቻ
1) ታክስ ከፋዩ ዕቃ ለማስወገድ ለገቢዎች ቢሮ ማመልከቻ
ማቅረብ ያለበት ሲሆን ማመልከቻው
ሀ/ የዕቃውን ዓይነት እና መለያ እንዲሁም የእቃውን ሞዴል
አምራች ፤
ለ/ ዕቃው የተመረተበት ወይም የተሠራበት ዘመን፤
ሐ/ ዕቃው ሀገር ውስጥ የተመረተ ከሆነ ዕቃው የተገዛበት
ደረሰኝ፤
መ/ ዕቃው ከውጭ ሀገር የመጣ ከሆነ የዕቃው ኢንቮይስ እና
የጉምሩክ ዲክላራሲዮን፤
ሠ/ ዕቃው የሚወገደው መለዋወጫ ባለመገኘቱ ከሆነ ዕቃው
መለዋወጫ የማይገንለት ስለመሆኑ
ከአምራች ወይም ከሦስት መለዋወጫው አስመጪዎች
የተሰጠው ማረጋገጫ ፤
ረ/ ዕቃው የሚወገደው የማስጠገኛ ወጪው ከፍተኛ በመሆኑ
ምክንያት እቃውን ለመተካት
ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ሲነፃፀር የጥገና ወጪው
ከሚወገደው ዕቃ ከ50 በመቶ በላይ
ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
ሰ/ ዕቃው የሚወገደው የመጠቀሚያ ጊዜው በማለፉ ምክንያት
ከሆነ የመጠቀሚ ጊዜው ያለፈ
መሆኑን ለማረጋገጥ የሚስችል የምርቱን ሌብል ወይም
ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ፣
ሸ/ ዕቃው የሚወገደው ዘመን ያለፈበት በመሆኑ ምክንያት ከሆነ
የተፈላጊነት ጊዜው ያለፈበት ዕቃ መሆኑ የሚያስረዳ መግለጫ፣
27. የዕቃ አስወጋጅ ኮሚቴ ስለማቋቋም
1) ገቢዎች ቢሮ በእያንዳንዱ መምሪያ ወይም ጽ/ቤት ወይም
የቀበሌ ማዕከላት ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የተውጣጣ
አምስት አባላት ያሉት የዕቃ አስወጋጅ ኮሚቴ ያቋቁማል።
2) የዕቃዎቹን አወጋገድ በተመለከተ ታክስ ከፋዩ ወይም ተወካዩ
በኮሚቴው ውስጥ ያለ ድምጽ እንዲሳተፍ ሊያደርግ ይችላል።
3) የኮሚቴው አባላት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን
እንደአስፈላጊነቱ ለአንድ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡፡
4) ገቢዎች ቢሮ ኃላፊነቱን በአግባቡ የማይወጣ የኮሚቴ አባል
ሲኖር በማንኛውም ጊዜ ከኮሚቴ አባልነቱ ሊያነሳው ይችላል፡፡
28. የዕቃ አስወጋጅ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት
የዕቃ አስወጋጅ ኮሚቴ
1) የቀረበውን የዕቃ ማስወገድ ጥያቄ እና የማስረጃዎቹን
አግባብነት ይመረምራል፤ እንደአስፈላጊነቱም ታክስ ከፋዩ ቀርቦ
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
2) እንዲወገድ ጥያቄ የቀረበበት ዕቃ መወገድ የለበትም ብሎ
ካመነ የውሳኔ ሀሳብ ለበላይ ኃላፊው በጽሁፍ ያቀርባል፡፡
3) እንዲወገዱ ጥያቄ በቀረበበት ዕቃ ላይ የውሳኔ ሃሳብ
ለመስጠት የዕቃውን ሁኔታ በአካል ማየት ካስፈለገው ዕቃው
ባለበት ቦታ በመገኘት ምርመራ ያደርጋል፡፡
4) ዕቃው መወገድ ያለበት መሆን አለመሆኑ መርምሮ የውሳኔ
ሃሳብ ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል፤
5) የላይ ኃላፊው ዕቃው እንዲወገድ ከወሰነ ታክስ ከፋዩ ዕቃውን
ለማስወገድ የሚያስፈልግ በቂ ዝግጅት በማድረግ ለገቢዎች
ቢሮ ዕቃው የሚወገድበትን ጊዜና ቦታ ያሳውቃል፡፡
6) የበላይ ኃላፊው ዕቃው መወገድ የለበትም ብሎ የወሰነ
እንደሆነ ውሳኔውን ከአስር ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለታክስ
ከፋዩ በፅሁፍ ያሳውቃል፡፡
7) ሥራውን በአግባቡ ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን
ያከናውናል፡፡
29. የውሳኔ ሀሳብ
1) የኮሚቴው አባለት ሰብሳቢውን ጨምሮ ከግማሽ በላይ
ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
2) ኮሚቴው የሚያቀርበው የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ
የሚወሰን ሲሆን በድምፅ አሰጣጥ ላይ የአባላት ድምፅ እኩል
ከሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ድምፅ ወሳኝ ይሆናል፡፡
3) በአብላጫ ከተወሰነው የተለየ ሃሳብ ያለው የኮሚቴው አባል
የተለየበት ሃሳብ በፅሁፍ መስፈር አለበት፡፡
4) እያንዳንዱ የኮሚቴ አባል በውሳኔ ሃሳቡ ላይ መፈረም
አለበት፡፡
5) የውሳኔ ሃሳቡ በተፈረመ በሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለበላይ
ኃላፊው መቅረብ አለበት፡፡
30. የዕቃዎች አወጋገድና አፈፃፀም
1) የእቃ አወጋገድ ኮሚቴው ዕቃው በሚወገድበት ጊዜና ቦታ
በመገኘት የዕቃ አወጋገዱን አፈፃፀም ይቆጣጠራል፣ ስለዕቃው
አወጋገድ ለበላይ ኃላፊው ሪፖርት ያቀርባል፡፡
2) የሚወገድ ዕቃ ሁሉም የኮሚቴ አባላት ወይም አብላጫ
ቁጥር ያላቸው አባላት እና ታክስ ከፋዩ ወይም ወኪሉ በተገኙበት
ይወገዳል፡፡
31. የተወገደውን ዕቃ በወጪነት ስለመመዝገብ
1) የተወገደው ዕቃ ዋጋ ዕቃው ከመወገዱ በፊት ከተመዘገበበት
መዝገብ ተሰርዞ አግባብነት ባለው በወጪ የሒሳብ መመዝገቢያ
መደብ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
2) ታከስ ከፋዩ በተወገደው ዕቃ ላይ አስቀድሞ የከፈለው
የግብዓት ታክስ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር
285/1994 መሠረት ከተሰብሳቢ ታክስ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
3) ገቢዎች ቢሮ የተወገደውን እቃ ዋጋ በመግለጽ ታክስ ከፋዩ
በወጪነት እንዲይዘው መፍቀዱን በጽሁፍ ያሳውቀዋል፡፡
32. ተጠያቂነት
የዕቃ አወጋገድ ኮሚቴ አባላት በእቃ አወጋገድ ሂደት ለሚፈጸም
ጥፋት የህግ ተጠያቂነት
አለባቸው፡፡
ክፍል አራት
ቀላል የሒሳብ አያያዝ ዘዴ
33. ቀላል የሒሳብ አያያዝ ዘዴ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ
ከፋይ
1) የደረጃ “ለ” ታክስ ከፋይ እና በፈቃደኝነት የሂሳብ መዝገብ
የሚይዝ የደረጃ “ሐ” ታክስ ከፋይ ቀለል ያለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ
በመጠቀም የሂሳብ መዝገብ መያዝ ይችላል፡፡\
2) ቀለል ባለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴ የሂሳብ መዝገብ እንዲይዝ
የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 34 ንዑስ
አንቀጽ 2 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ክፍያ እንደተፈጸመ
ወጪዎቹ ተቀናሽ ይደረጉለታል፡፡
34. ቀለል ያለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴን ተጠቅሞ የሂሳብ መዝገብ
የሚይዝ ታክስ ከፋይ ስለሚይዘው መረጃ
1) ቀለል ያለ የሂሳብ አያያዝ ዘዴን ተጠቅሞ የሂሳብ መዝገብ
የሚይዝ ታክስ ከፋይ ሂሳብ መዝገብ መግለጫ በሚያቀርብበት
ጊዜ የሚከተሉትን መረጃዎች አሟልቶ ማቅረብ አለበት፡፡
ሀ) ታክስ ከፋዩ አስቀድሞ የተመዘገበውን የቋሚ የንግድ ሥራ
ሀብት ብዛት፣ዓይነት እና የመዝገብ
ዋጋ የሚያሳይ ሠንጠረዥ
ለ) በግብር ዓመቱ ውስጥ የተገዛ እና 100% የአርጅና ቅናሽ
የተፈቀደለት የንግድ ስራ ሀብት ብዛት
፣ ዓይነትና ዋጋ
ሐ) በግብር ዘመኑ የተላለፈ ወይም የተወገደ የንግድ ሥራ
ሀብት ብዛት ፣ዓይነት እና ዋጋ
የሚገልጽ ደረሰኝና ተያያዥ ማስረጃዎች፣
መ) ለቀጣይ የግብር ዘመን የዞረ ቋሚ ንብረት ብዛት ፣ዓይነት
እና ዋጋ የሚያሳይ ሰንጠረዥ
ሠ) ካለፈው የታክስ ዘመን ሳይሽጥ የቀረ ንግድ ዕቃ ብዛት፣
ዓይነት እና ዋጋ የሚያሳይ ሠንጠረዥ
ረ) ታክስ ከፋዩ አምራች ከሆነ በግብር ዘመኑ በምርት ሂደት ላይ
ያለና ወይም ጥቅም ላይ ያልዋለ
ጥሬ ዕቃ ብዛት፣ዓይነት እና ዋጋ የሚያሳይ ሰንጠረዥ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
ሰ) በግብር ዓመቱ ውስጥ የተፈጸመ የንግድ ዕቃ ሽያጭ እና
ግዥ ዝርዝር ከግብይት ደረሰኝ ጋር
ሸ) በግብር ዓመቱ ውስጥ ለቤት ኪራይ የተከፈለ ወጪ እና ቤት
በማከራየት የተገኘ ገቢ መግለጫ
2) ታክስ ከፋዩ ግንባታ ሥራ የሚከናውን ከሆነ ወጪው
የሚመዘገበው ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን የግንባታውን
መጠናቀቅ የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ
አለበት፡፡
ክፍል አምስት
የሒሳብ መግለጫ ላይ ስለሚደረግ ማስተካከያ
35. በሒሳብ መግለጫ ላይ ማስተካከያ ስለማድረግ
1) ታክስ ከፋዩ የሚቀርበው የሒሳብ መዝገብ መሰረታዊ ጉድለት
ካልተገኘበትና ለታክስ አወሳሰን የሚስፈልጉ መረጃዎችን ያልያዘ
መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ውድቅ አይደረግም፡፡
2) ታክስ ከፋዩ ያቀረበው የሂሳብ መዝገብ ከዚህ በታች
የተዘረዘሩት ጉድለቶች የተገኙበት እንደሆነ መዝገቡን ውድቅ
ማድረግ ሳያስፈልግ ጉድለቶቹ እንዲስተካከሉ ተደርጎ ታክሱ
በመዝገቡ መሰረት ይወሰናል፡፡
ሀ) በሒሳብ መግለጫው ላይ በሙሉ ወይም በከፊል ያልተገለጸ
ገቢ መኖሩ ሲረጋገጥ፣
ለ) በደረሰኝ ላይ የተሰበሰበው ገቢ ድምር በሒሳብ መግለጫ
ላይ ከሠፈረው ገቢ ጋር ሲነፃፀር
ልዩነት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ፣
ሐ) ታክስ ከፋዩ ያስታወቀው ንግድ ሥራ ገቢ ከታክስ ነፃ
የተደረገውን ግብይት ሳይጨምር
ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ ወይም ተርን ኦቨር ታክስ ያስታወቀው
ዓመታዊ ገቢ ጋር ሲነፃፀር
ልዩነት የተገኘበት ሲሆን፤
መ) በታክስ ከፋዩ የሒሳብ መግለጫ ላይ የተገለፀው ያልተሸጠ
ዕቃ ዋጋ በቆጠራ ከተገኘው የዕቃ
ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ልዩነት ያለው ሆኖ ሲገኝ፤
3) ታክስ ከፋዩ ያቀረበው የሒሳብ መግለጫ በወጪ አመዘጋገብ
ረገድ የሚከተሉት ጉድለቶች ሲገኙበት መዝገቡን ውድቅ
ማድረግ ሳያስፈልግ ማስተካከያ (Adjustment) በማድረግ
ታክሱ በመዝገቡ መሰረት ይወሰናል፡፡
ሀ. ታክስ ከፋዩ ባቀረበው ያልተመዘገበ ውል ላይ ያልተገለጸ
የንግድ ቤት እና የመጋዘን ኪራይ ፣የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ኪራይ
፣የንግድ ተሽከርካሪ ኪራይ ወይም የረዥም ጊዜ ጥናት
አገልግሎት ወጪ ሲገን፣
ለ .ከፋይናንስ ተቋም ውጪ የተወሰደ እና ያልተመዘገበ የጥሬ
ገንዘብ የብድር ስምምነት ሲቀርብ
ሐ. በደረሰኝ አስተዳደር መመሪያ መሠረት ተቀባይነት በሌለው
ደረሰኝ ተገልጾ የቀረበ ወጪ ሲቀርብ ፤
መ. በአዋጁ ያልተፈቀደ ወጪ ተይዞ ሲገኝ ፤
4) ታክስ ከፋዩ .ከፋይናንስ ተቋም ውጪ የወሰደው የጥሬ
ገንዘብ ብድር ውል ስምምነት ውል የማዋዋል ስልጣን ባለው
አካል ያልተመዘገበ ከሆነ ብድር ነው ተብሎ በተገለጸው
የገንዘብ መጠን ላይ ታክስ ይወሰናል፡፡
5) ታክስ ከፋዩ በገቢነት ያልገለጸው ሆኖ በታክስ ከፋዩ ባንክ
ሂሳብ ገቢ የተደረገ ገንዘብ ከንግድ ሥራ ያልተገኘ ወይም ግብር
የማይከፈልበት ገቢ ስለመሆኑ በተገቢው ህጋዊ ማስረጃ
ማረጋገጥ ካልቻለ በተገለጽው የገንዘብ መጠን ላይ ግብር
ይወሰናል፡፡
36. ታክስ ከፋዩ ያቀረበው የሒሳብ መግለጫ ተቀባይነት
የሚያጣበት ሁኔታ
1) ታክስ ከፋዩ ያቀረበውን የሂሳብ መግለጫ ውድቅ ለማድረግ
የሚያስችሉ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ) የቀረበውን የሒሳብ መግለጫ ትክክለኛነት ታክስ ከፋዩ
ወይም የሂሳብ መግለጫውን ያዘጋጀው
ባለሙያ በገቢዎች ቢሮ ሲጠየቅ በተገቢው ማስረጃ ያላረጋገጠ
እንደሆነ፣
ለ) ታክስ ከፋዩ የሒሳብ መዝገብና ለታክስ አወሳሰን አስፈላጊ
የሆኑ ደጋፊ ሰነዶችን እንዲያቀርብ
በጽሁፍ ተጠይቆ ያላቀረበ እንደሆነ፣
ሐ) በደረሰኝ አስተዳደር መመሪያ መሠረት በገቢዎች ቢሮ
ያልተፈቀደ ደረሰኝ ተጠቅሞ የተዘጋጀ
የሒሳብ መዝገብ ሲሆን፤
መ\) በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ቁጥጥር ወይም በደረሰኝ
ክትትል ወቅት በታክስ ዘመኑ ውስጥ
ደረሰኝ ባለመቁረጥ ቢያንስ ለ3 ጊዜ ማስጠንቀቂያ ከደረሰው
ወይም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ
ከተሰጠው ወይም አስተዳደራዊ ቅጣት ከተቀጣ ወይም
የኦፕሬሽን ሥራ ከተሰራበት፤
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ ሀ እና ለ መሠረት
የሂሳብ መግለጫ ውድቅ የሚደረገው ኦዲተሩ ደጋፊ ሰነዶች እና
የሂሳብ መግለጫው እንዲያቀርብ ጠይቆ በአስር ቀን ውስጥ

Timeline photos 15/01/2021

“ተርን ኦቨር ታክስ” Turn Over Tax (TOT) ምንድነው?
ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም
የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት የሚጣል የታክስ አይነት ነው።
ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ የማን ነው?
ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም ዓመታዊ የንግድ
አንቅስቃሴው ከብር 1 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ
ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ
ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ሰብስቦ
ለሚመለከተው የታክስ ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ገቢ ያደርጋል።
ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው
ወይም ድርጅት በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው
ሰብስቦ ለታክስ ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ገቢ የማድረግ ግዴታ
አለበት። ስለሆነም ሻጩ ለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይሆናል።
የተርን ኦቨር ታክስ ምጣኔ
 በማናቸውም በአገር ውስጥ በሚሸጡ ዕቃዎች ላይ
እንስሳትንም ጨምሮ ሁለት በመቶ
 በአገር ውስጥ በሚሸጡ በተወሰኑ አገልግሎቶች ላይ
ማለትም (የሥራ ተቋራጮች፣ የእህል ወፍጮ ቤቶች፣
የትራክተሮችና ኮምባይነር ሀርቨስተሮች) 2 በመቶ እና
 ሌሎች አገልግሎቶች ላይ 10 በመቶ የተርን ኦቨር ታክስ
ይከፈላል።
የተርን ኦቨር ታክስ የስሌት መሠረት
ተርን ኦቨር ታክስ የሚሰላበት የዋጋ መሠረት የዕቃው ወይም
የአገልግሎት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ነው።
የተርን ኦቨር ታክስ ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ሃላፊነት
ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው
በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው ሰብስቦ ለገቢ
ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት። ስለሆነም
ሻጩ ሳይሰበስብ ቢቀር ለታክሱ ከራሱ እንዲከፍል ስለሚደረግ
የመጀመሪያው ተጠያቂ ይሆናል።
የሚከተሉት ከተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ነፃ ናቸው፡-
 ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭና
የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣
 የፋይናንስ አገልግሎቶች፣
 ለሳንቲሞችና ሜዲሊያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት
በስተቀር የአገር ውስጥና የውጪ አገር ገንዘቦችና የዋስትና
ሰነዶች ማሰራጨት፣
 በኃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ
ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች፣
 የሕክምና አገልግሎትና አግባብ ባለው የመንግስት መ/ቤት
በሚወጣ መመሪያ መሠረት በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፣
 በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች
እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋዕለ ሕፃናት የሚሰጡ
አገልግሎቶች፣
 የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲን የውሃ አቅርቦት፣
 የትራንስፖርት አገልግሎት፣
 ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚሰጥ ፈቃድ
ለመንግስት የሚፈፀም ክፍያ፣
 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ
የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣
 መጽሐፍት፣
 ሌሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ ሁሉ ናቸው።
የተሰበሰበን የተርን ኦቨር ታክስ ስለማስታወቅ
የደረጃ ‹‹ሀ›› ግብር ከፋዮች ተብለው የሚታወቁና ለተጨማሪ
እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታ የሌለባቸው ታክስ ከፋዮች
እያንዳንዱ የሂሳብ ጊዜ በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ለታክስ ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱ የተርን ኦቨር ታክስ ማስታወቂያ
ማቅረብ አለበት፣
የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በኢትጵያ የበጀት ዓመት ወይም
በገቢ ሰብሳቢው መ/ቤት ሲፈቀድ በአውሮፓ ዘመን አቆጣጠር
ከዓመቱ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የሶስት ወር ጊዜ ባበቃ በቀጣዩ
አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስታወቅና መክፈል አለበት፣
የደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች የበጀት ዓመቱ እንዳለቀ /ከሐምሌ
1 – 30/ ነው።
የተሰበሰበን የተርን ኦቨር ታክስ በወቅቱ ያለማስታወቅ
አስተዳደራዊ መቀጫዎችን ያስከትላል
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 መሠረት
በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የታክስ ማስታወቂያ ግዴታውን
ያልተወጣ የተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር
ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ያልተከፈለውን ታክስ 5 በመቶ፤
25 በመቶ እስኪ ሞላ ድረስ፣ የሚከፈለው መቀጫ ከብር ሃምሳ
ሺህ አይበልጥም።
በማናቸውም ሁኔታ የሚጣለው ቅጣት ቀጥሎ ከተመለከቱት
ከዝቅተኛው ያነሰ አይሆንም፣ ብር አስር ሺህ፣ በታክስ
ማስታወቂያው ላይ መመልከት ከነበረበት የታክስ መጠን 100%
ይሆናል።
የተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ማዘግየት አስተዳደራዊ መቀጫዎችን
ያስከትላል
መከፈል በነበረበት ወር ላልተከፈለ ታክስ መከፈል ከነበረበት ቀን
ባለው ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ ወለድ የመክፈል ግዴታ አለበት።
የሚከፈለው ወለድ የማስከፊያው ልክ ባለፈው የሩብ ዓመት
በንግድ ባንኮች ስራ ላይ በዋለው ከፍተኛ የማበደሪያ ወለድ
ምጣኔ ላይ 15 በመቶ ታክሎበት ነው።
ታክስን አሳንሶ ማሳወቅ የሚያስከትለው ቅጣት
 በታክስ ማስተወቂያው የተገለጸው የታክስ መጠን ከታክስ
ከፋዩ ሊከፍል ከሚገባው ትክክለኛ የታክስ መጠን ያነሰ እንደሆነ
ልዩነቱን መጠን 10% (አሥር በመቶ) ቅጣት ይከፍላል፡፡
 ታክስ ከፋዩ ለሁለተኛ ጊዜ ልዩነት በሚኖርበት ጊዜ የቅጣቱ
መጠን ወደ 30% (ሰላሳ በመቶ) ከፍ ይላል፡፡
 ታክስ ከፋዩ ለሶስተኛ ጊዜ እና ከዚያ በላይ ልዩነት
በሚኖርበት ጊዜ የቅጣቱ መጠን ወደ 40% (አርባ በመቶ) ከፍ
ይላል፡፡
ስለሆነም በወቅቱ ትክክለኛውን ታክስ አሳውቆ መክፈል ከነዚህ
ሁሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች ያድናል።

Videos (show all)

ስለ ሂሳብ መዝገብ ምን ያህል ያውቃሉ????

Website