ANRS North Shewa Zone Department of Industry and investment

ANRS North Shewa Zone Department  of  Industry and investment

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS North Shewa Zone Department of Industry and investment, Government Organization, .

Photos from ANRS North Shewa Zone Department  of  Industry and investment's post 17/07/2024

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2016 ዓም እቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 10/2016 ዓም በመምሪያው ቢሮ ከአጠቃለይ ሰራተኞች ጋር እያደረገ ይገኛል ። በግምገማው ላይ የሁሉም የሥራ ቡድኖች የዓመቱ የሥራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

Photos from ANRS Mines Resource Development Bureau/የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ's post 11/06/2024
በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ የምረቃ ሥነ-ስርዓት 11/06/2024

በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ የምረቃ ሥነ-ስርዓት በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ የምረቃ ሥነ-ስርዓት

15/05/2024

በሰሜን ሸዋ ዞን ያለው የባለሃብቶች ተሳትፎ የሚበረታታ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።
ባሕር ዳር: ግንቦት 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ርእሰ መሥተዳድሩ በሰሜን ሽዋ ዞን ቡልጋ ከተማ አሥተዳደር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል በኾነው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተገኝተው ከባለሃብቶች እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ከአማራ ክልል ጸጋዎች መካከል አንዱ የኾነው የሰሜን ሽዋ ዞን ከሥነ መንግስት ምስረታ፣ ፍልስፍና እና የፊደል ገበታ መነሻነት ባሻገር ታላቅ የሃብት ባለጸጋ መኾኑን ያወሱት የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ ቅርብ መኾኑ እና የጂቡቲ የንግድ ኮሪደር ላይ መገኘቱ በርካታ የኢንዱስትሪ ሃብቶች መገኛ እንዲኾን ያስችለዋል ብለዋል።
ይኽን ተከትሎ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በቀጣናው ያለው የባለሃብቶች ተሳትፎ የሚበረታታ እና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል።
ከቡልጋ እስከ ደብረ ብርሃን በተዘረጋው የኢንዱስትሪ ቀጣና ኢንዱስትሪዎች ሥራ ላይ ቢኾኑም በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸውም ርእሰ መሥተዳድሩ አንስተዋል።
ይኽን የርእሰ መሥተዳድሩን ሃሳብ የሚጋሩት በመድረኩ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡ ባለሃብቶችም የመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ የብድር አገልግሎት በሚፈለገው መጠን አለማግኘት እና የጸጥታ ችግሮች ዘርፉን በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ አድርገውታል ብለዋል።
ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በሰጡት ማብራሪያም አካባቢው አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ውጤት እንዲያመጣ እና በባለሃብቶች የተነሱ ጥያቄዎች እንዲፈቱ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
በተለይም ኢንዱስትሪዎች በዘመናዊ መልኩ እንዲመሩ ማድረግ እና በባለሃብቱ ላይ የሚያጋጥሙ የመንግሥት ቢሮክራሲዎች እንዲቀንሱ መሥራት አለብን ሲሉ ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ባለሃብቱ በሥራ እንቅስቃሴው ላይ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ታሳቢ ያደረገ ማኅበራዊ ኀላፊነት ላይ እንዲሳተፉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ በሰሜን ሽዋ ዞን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደረጉ ባለሃብቶች እና ተባባሪ አካላት ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Photos from Amhara Industry and Investment Bureau's post 15/05/2024
Photos from Arega  Kebede Legas/አረጋ ከበደ ለጋስ's post 15/05/2024
Photos from Amhara North Shewa Zone  Communication's post 15/05/2024
Photos from በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 15/05/2024
02/05/2024

የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ የዞናችን ባለሃብቶች እና ዉድ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት፤
የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንደሱትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር የ2016 የባለሃበት ፎረም በቡልጋ ከተማ አስተዳደር ለማክበር ፕሮግራም ስለተያዘ በ06/09/2016 ማክሰኞ በኦ አዝመራው በቀለ ማዳበሪያ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ ቅጽር ጊቢ ከጠዋቱ 2፡30 እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

11/07/2023

የለሚ ናሽል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ 65 ከመቶ ደርሷል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እየተገነባ የሚገኘው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ግንባታ 65 ከመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የፋብሪካው ግንባታ እየተፋጠነ ነው። አስፈላጊ የሚባሉ ማሽኖችም ከቦታው እየደረሱ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት 3000 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፤ አንድ ሺህ 500 ቻይናውያን በፋብሪካው ግንባታ ላይ እየተሳተፉና የዕውቀት ሽግግር እየተፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፋብሪካው ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ ምርት እንደሚጀምርም አቶ ያየህ ገልጸዋል።

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ በኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና በቻይናው ዌስት ቻይና የሲሚንቶ አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሽርክና የተመሰረተ ነው፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም

Photos from ANRS North Shewa Zone Department  of  Industry and investment's post 08/03/2023
Photos from ANRS North Shewa Zone Department  of  Industry and investment's post 08/03/2023

የሰሜን ሸዋ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2015 ዓም የ6ወር ዕቅድ ክንውን አፈፃፅም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ውይይት በደብረ ብርሐን ከተማ እየተካሔደ ነው ።

Photos from ANRS North Shewa Zone Department  of  Industry and investment's post 17/02/2023

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2015 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት የዕቅድ ከንውን አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል፡፡

06/01/2023

የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ እንኳን ለ2015 የገና በዓል አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ መምሪያው ዞኑ የኢንቨስትመንተ መዳረሻ እንደመሆኑ በተለይ በማኑፋክቸሪነግ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በግብርና እና በአገልግሎ ዘርፎች ባለሃብቶች መጥተው እንዲያለሙ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ ኑ በመልካም መስተንግዶ እንቀበላችኋለን፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምን ለውጥ አመጣ? Etv | Ethiopia | News 29/12/2022

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምን ለውጥ አመጣ? Etv | Ethiopia | News የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተካሄደባቸው ባለፉት አምስት ወራት ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ማስገባት ጨምሮ የወጭ ገቢን ማሳደግ የቻለ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ። ...

Photos from Asagirt Industry and investment's post 29/12/2022
06/12/2022

ኑ! አሳግርትን በጋራ እናልማ!! በአሳግርት ወረዳ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች !
********************/***************
ኢኢቢ: ህዳር 18/03/2019 ዓ.ም : ባህር ዳር
በአግሮ ፕሮሰሲግ ዘርፍ
_ በጌሾ ማቀነባበርና ማሸግ
_ አትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበር
_ ጦስኝ ማቀነባበር
_ የአልኮል መጠጥ ማምረት
_ የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበር
_ የታሸጉ ውሃዎች ማምረት/ከርሰምድር
;;////::በግብርና ዘርፍ
* ቢራ ገብስ ማምረት
* ማሾ ና ሌሎች ጥራጥሬ ሰብሎች ማምረት
* እንሰሳት ማድለብ
* ወተት ልማትና እንሰሳት እርባታ
* በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት
* በንብ ማነብ

;;;;;;;//// #በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ
;;::::::::: #በንፋስ ሃይል ማመንጨት

;;;;;;;;;;;;;; #በኮንስትራክሽን ዘርፍ
* የህንፃ ስራ ተቋራጭነት
# # #በእንጨት እቃዎች አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ
* የእንጨት መሰንጠቅና ጣውላ ማምረት
* በበርና መስኮት ስራዎች
* በአጣና ማምረት
;;;;;;;;;;;; #በጨርቃጨርቅና አልባሳቶች ዘርፍ
* የልብስ ስፌት
* የሽመና ውጤቶች
* የጥልፍ ስራ
;; #በብረታብረት እቃዎች አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ
* በርና መስኮት ስራዎች
* ለግብርና አገልግሎት የሚሆኑ ግብአቶች ማምረት
* ኮንቲነር ማምርት
;;;;;;;;; #የፋይናንስ አገልግሎትን በተመለከተ
* ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
* አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም/አ.ብ.ቁ.ተ/በአሁኑ ፀደይ ባንክ
* አቢሲኒያ ባንክ
* ቡና ባንክ
* አማራ ባንክ
* አባይ ባንክ እና ሊሎችም በመግባት ላይ ያሉ ባንኮች ስላሉ ለስሪያዎ ስኬት አጋዥ ናቸው፡፡
እነዚህን ምቹ ሁኔታዎችና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ስናስተዋውቃችሁ በወረዳችንና በከተማችን ያለውን እውነተኛ ፀጋ መሰረት አድርገን ስለሆነ መጥቶ ለማልማት ጥርጥር አይግባዎት ከቀልጣፋ አገልግሎትና መስተንግዶ ጋር እንጠብቅዎታለን፡፡

የአሳግርት ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት
አሳግርት ወረዳ ማነች፤ የት ነች?
#የወረዳዉ ገፅታ #
የአሳግርት ወረዳ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር ከሚገኙ 31 ወረዳእና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን ወረዳዋ በሰሜንና በሰሜን ምዕራብ አንጎለላና ጠራ ወረዳ ፣ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ አንኮበር ወረዳ ፣ በደቡብ በረኽት ወረዳ ፣ በምዕራብ ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ እና በምስራቅ የአፋር ክልል ያዋስኗታል፡፡ወርዳዋ በጠቅላላው የአስራ ሶስት(13) የገጠር ቀበሌና የሁለት ከተሞች ባለቤት ናት፡፡
ወረዳዋ ከሀገሪቱ ርዕሰ ሚዲና ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ125 ኪ.ሜ፣ ከክልላችን ርዕሰ መዲና ከባህር ዳር ደግሞ 614 ኪ.ሜ እንዲሁም ከዞናችን ርዕሰ መዲና ደ/ብርሃን ደግሞ በስተደቡብ አቅጣጫ 72 ከ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ወረዳዋ ከሰንቦ-አረርቲ-ሞጆ የአስፋልት መንገድ በ26 ከ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
የወረዳዋን የሙቀት መጠንም ዝቅተኛ7.50.c ከፍተኛ250.c ሲሆን የአየር ንብረት ሁኔታ ስንመለከት በደጋ፣ በወይና ደጋ በቆላ ውርጭ የአየር ንብረት ክልሎች የተከፋፈለች ስትሆን
የሚሸፍኑት የቆዳ ስፋትም ፡-
ደጋ 20432 ሄ/ር /39.21%/ ፣
ወይናደጋ 20762 ሄ/ር /39.84%/ እና
ቆላ ፡ 6955 ሄ/ር /13.35%/
መሬት የሚሸፍን ሲሆን አመታዊ የዝናብ መጠኗን ስንመለከት ዝቅተኛ ከ900-1200 ሚሊ ሜትር መካከለኛ 1200- 1500 ሜትር ከፍተኛ 1500-1800 ሚሊ ሜትር ነው፡፡
የአየሩ ሁኔታ
ደጋ =13.79%
ወይና ደጋ =40.46%
ቆላ =38.65%
ውርጭ =7.08%
የወረዳው የኢኮኖሚ መሰረቶች
-------በግብርና ልማት--------
በመኸር የሚታረስ የእርሻ መሬት 9817 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የእንዱስትሪ ሰብል/ቢራ ገብስ 100 ሄ/ር፣የኢንዱስትሪ ሰብልማሾ 408 ሄ/ር እና ሌሎች የጥራጥሬ ሰብል 2182 ሄ/ር የሚሸፍኑ ሲሆን ቀሪው 6452 ሄ/ር ለአካባቢ ገበያ እና ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ሌሎች ሰብሎች የሚመረትበት የመሬት ፖቴንሻል መኖሩን መረጃችን ይጠቁማል፡፡
መስኖ፣አትክልትና ፍራፍሬ ልማት በተመለከተ ወረዳዋ ከ929.99 ሄ/ር በላይ በመስኖ የሚለማ መሬት ያለ ሲሆን፡-
አመታዊ ሰብል = 914.01ሄ/ር
ቋሚ ተክል =15.5 ሄ/ር
እንሰሳት ሀብት ልማትን በተመለከተ በወረዳዋ
የዳልጋ ከብት =37506
በግ =24191
ፍየል =23540 ይገኛሉ።
#በወረዳዋ ለኢንቨስትመንት ያሉ ምቹ ሁኔታዎች #
* አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ መኖሩ
* በወረዳዋ በቅርብ ርቀት/በ26 ኪ.ሜ/የአስፋልት መንገድ መኖር
* ሰፊ የስነ-ምህዳር ቀጠና እና ምቹ የአየር ንብረት በመኖሩ በብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ እድል ይፈጥራል፡፡
* በርካታ የሰው ሃይልና ተመጣጣኝ የጉልበት ዋጋ መኖሩ
* በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሀይማኖታዊ የመስህብ ቦታዎች መኖራቸው
* በወረዳው የግብርና ምርትና ምርታማነት እያደገ መምጣቱ
ወረዳዋ በርካታ የማዕድን ሀብት ባለቤት መሆኗ
* ወረዳው ለደብረብርሀን የኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርብ መሆኑ ለየት ያደርገዋል።
ኑ! አሳግርትን በጋራ እናልማ!!

የ አሳግርት ወረዳ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት።

የፀጋዎች ምድር ክፍል ሁለት 25/11/2022

የፀጋዎች ምድር ክፍል ሁለት የፀጋዎች ምድር Amhara industry and investment Promotion DocumentaryInvest Amhara/ Industry/ Wealthy Nation Amhara.

25/11/2022
Photos from ጣርማበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት's post 18/11/2022
18/11/2022

ኢንቨስትመንት ለትውልድ የሚተላለፍ ሀብት ማስቀመጥ ቢሆንም በወረዳችን የሚገኙ ኢንቨስተሮች በአካባቢያችን የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶችን አካታች አድርገው ለጋራ ብልፅግና ሊሰሩ ይገባል።

የጣርማበር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ሳሙኤል መርሻ

Videos (show all)

North shewa zone investment potential, mine

Website