Sn1khc Theological college

Sn1khc Theological college

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sn1khc Theological college, College & University, .

25/08/2024

ተጀመረ...

28/07/2024
Photos from Sn1khc Theological college's post 25/07/2024

የቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ወቅታዊ ጉዳይ‼️
ሐምሌ 18/2016
መጋቢ ጌትነት ለማ የኩሪፍቱ ቃለ ሕይወት ማዕከልን አስመልክተው ወቅታዊ መግለጫ ሰተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬቶ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት በደረሰው አደጋ ካውንስሉ የተሰማውን ሃዘን በመግለፅ፤ በአደጋው ለተጎዱ ወገኖቻችን ማቋቋሚያ የሚሆን ድጋፍ እያሰባሰበ እንዳለ መጋቢው በመግለፅ፤
በዋናነት ዛሬ መግለጫ ሊሰጡ ወደ ተዘጋጁበት የቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ጉዳይ በማምራት፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለፉት 90 ዓመታት በላይ በተለያዩ ማኅበራዊ እና የልማት ስራዎች ላይ የተሰማራች መሆኗን በመግለፅ እንዲ ያሉ ተቋማትን በልማት ስም መክሰስ የሃይማኖት ተቋማትን የልማት እንቅስቃሴ ከመናቅ እና ወንጌላውያን አማኞችን የማይወክል መሆኑን አንስተዋል።
በመግለጫቸው እስከ አሁን የተጀመረ ምንም ዓይነት ንግግር አለመኖሩን በመገንዘብ፤ ከከተማ መስተዳደሩም ሆነ፣ ከክልሉ መንግስትም እንዲሁም ከፌደራል መንግስት የተሰጠ ምንም ዓይነት ምላሽ አለመኖሩን በመገንዘብ ወንጌላውያን አማኞች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥያቄያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዩን ዕግድ በፍርድ ቤት አሰጥታ በፍርድ ቤት እየተከታተለች ቢሆንም ጉዳዩ የክልሉን እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን የሚፈልግ በመሆኑ ማንኛውም የወንጌላውያን አማኝ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጎን በመቆም ድምፅ በማሰማት የተጀመረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ህዝብን በማደናገር እና የወንጌላውያን አማኞችን ለመከፋፈል እና የተጀመሩ ሰላማዊ ጥያቄዎችን ለመቀልበስ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት እያስተላለፉ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማትን በተመለከተ ህጋዊ የሆነ አካሄድ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት መሰል ስራ ላይ የተሰማሩ የሚዲያ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አንስተዋል።
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/
ይከታተሉን፡

24/07/2024

- ነሐሴ 3/ 2016 ዓ.ም
:00 ሰዓት አይቀርም!
:00 ሰዓት ጀምሮ!

የሺንሽቾ ከተማ ቁ.1 ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ለወጣቶች ከሐምሌ 18-ነሐሴ/2016 ዓ.ም ድረስ ልዩ የወጣቶች ሥልጠና ድግስ አዘጋጅታለች።

ወጣቶች ባለመቅረት እንዲትሳተፉ ቤተክርስትያኒቱ ጥሪዋን ታስተላልፋለች!

መርሀግብሩም እንደሚከተለው ተዘርዝሯል...

፩. ከሐምሌ 18-21/2016 ዓ.ም ድረስ "እውነተኛ አምልኮ" በሚል እጩ ዶክተር መምህር ተሰማ ፎርሲዶ ስልጠናውን የሚሰጡን ይሆናል።

፪. ከሐምሌ 22-26/2016 ዓ.ም ድረስ "በአገልግሎትና በሥራ ማደግ" በሚል መጋቢ አበራ አዋኖ የሚያሰለጥኑን ይሆናል።

፫. ከሐምሌ 29- ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም ድረስ "በመንፈሳዊነት ማደግ" በሚል መጋቢ ዳዊት ቆጥሶ ስልጠናውን የሚሠጡን ይሆናል።

!
#ለሌሎችም በማድረግ ይጋብዙ!

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችን ይሁን! አሜን!

የቴሌግራም አካውንታችን https://t.me/ShinshichoNo1KHC

Photos from Sn1khc Theological college's post 24/07/2024

በጎፋ ዞን ሕዝብ ላይ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፣ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። (2ኛ ቆሮ. 1፣4)

ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በአንድ ቀን ውስጥ በሦስት ዙር በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ229 ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉ ቤተ ክርስቲያናችንን እጅግ አስደንግጧታል፡፡ እሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ለሰኞ አጥቢያ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ከነሙሉ የቤተሰብ አባላትና ንብረት ጭምር በናዳው መቀበራቸውን ተከትሎ የተጎጂዎቹን ሕይወት ለመታደግ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱት ወገኖችም ሳያስቡት በድንገት የቆሙባት ምድር ከድታቸው እነርሱም ለተመሳሳይ አደጋ መዳረጋቸውን ተረድተናል፡፡

ይህ አሳዛኝ ትዕይንት በዚህ ብቻ ሳያበቃ በሁለተና ዙር የተሰወሩትን ሰዎች ሕይወት ለመታደግ በቁጥር ከፍ ያለ ሕዝብ ወደ ስፍራው አምርቶ ለሦስተኛ ጊዜ በተንሸራራተተው መሬት ምክንያት ሳይመለሱ መቅታቸው የፈጠረብንን መሪር ሃዘን በቃላት መግለጽ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ወገኖቻችን ለከባድና ቀላል አካላዊ ጉዳቶች ተጋልጠው በሳውላ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ በመከታተል ላይ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡ ከሁሉ በላይ ልብ የሚሰብረው ደግሞ በርካታ ሰዎች የት እንደደረሱ እንኳን ሳይታወቅ በመሰወራቸው ፍለጋው የመቀጠሉ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ከጎፋ ሕዝብ ጋር ፈርጀ ብዙ በሆነ መንገድ ቀና ትስስር ለፈጠረችው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ልትሸከመው የማትችለው ሃዘን ሆኖባታል፡፡

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የመሃል ደቡብ ቀጣና መቀመጫ በሆነችው የሳውላ ከተማ ዙሪያ የተፈጠረው ይህ የተፈጥሮ አደጋ የቤተ ክርስቲያን አባሎቻችንን ጨምሮ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ውድ ሕይወት በመቅጠፉ የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን በጸሎትና አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ወገኖቿን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን እናሳውቃለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ በአደጋው ቤተሰቦቻችሁን ላጣችሁ ወገኖቻችን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን አባላት፣ ለጎፋና አካባቢው ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን!
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EKHCHeadoffice
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianKaleHeywetChurch
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/
ይከታተሉን፡

Photos from Ethiopian Kale Heywet Church Head Office's post 19/07/2024
#የቢሾፍቱ_ባለስልጣናት_የቃለ_ህይወት_ቤተክርስቲያን_አመራሮች_ላይ_የፈፀሙት_በደል.. 15/07/2024

#የቢሾፍቱ_ባለስልጣናት_የቃለ_ህይወት_ቤተክርስቲያን_አመራሮች_ላይ_የፈፀሙት_በደል.. ይህ የኢቫንጀሊካል ቲቪ ነው ። ስርጭቱን በ Frequency 11105 - Symbol rate 45000 - Polarization Horizontal ላይ ታገኙታላችሁ። መረጃውን ለሌሎችም በማጋራት እንዲያገኙን ያድርጓቸው።አዳዲስ የኢቫንጀሊካል ቲቪ ...

Photos from Sn1khc Theological college's post 11/07/2024

በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤ/ክ ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ ኢ-ህገ መንግስታዊ በደል ደርሷል። ድርጊቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል መግለጫ ሰጥተዋል‼️

የጽ/ቤቱ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ፡ ማዕከሉ በባለቤትነት ከያዘው መሬት፡ 40ሺህ ካሬ ሜትር የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር፡ በሃይል ለሁለት ግለሰቦች ተሰጥቷል ብለዋል።

ፍርድ ቤት የመሬት ባለቤትነቱን ለቢሾፍቱ ቃለ ህይወት ኩሪፍቱ ማዕከል ቢያረጋግጥም፡ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታና ስራ ሂደትን የከተማ አስተዳደሩ፡ እያዘገየ ቆይቷል። ትላንት ሰኞ ሃምሌ 3 ወታደር ይዞ ወደ ቤ/ክ ግቢ ገብቶ ችካል በመትከል ህገ ወጥ ስራ ሰርቷል።

የከተማ አስተዳደሩ መሬቶችን የማልማት ትልቅ ፍላጎት እንዳለው የሚታወቅ ቢሆንም፡ ስፍራው ለልማት ከሆነ፡ ቤ/ክኗ እየሰራች ቆይታለች ብለዋል የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ።

እኛ ወንጌላዊያን አመጸኞች አይደለንም፡ መንግስት ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥና ውሳኔ እንዲያስተላልፍ፡ እንጠይቃለን። ድርጊቱን የክልል፡ የፌደራል የመንግስት ሃላፊዎች በታችኛው የመንግስት መዋቅር እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች መፍትሄ እንዲሰጡ እንጠይቃለን።

ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።

ከዚህ ቀደምም በቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ እንዳየነው፡ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የፍርድ ቤትን ውሳኔ አያከብርም። እነዚህ ድርጊቶች የመንግስት አካላት ከግል ባለሃብቶች ጋር በመሻረክ የሚሰሩት ነው።

መሰል ድርጊቶች በተለይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ አይተናል፡ መጠየቃችንንም አናቆምም። ጥያቄው ዛሬ ባይመለስም፡ ለልጆቻችን እናወርሰዋለን። እንደ ከዚህ ቀደሙ ማርክሲስት መንግስት ሁሉ፡ ወንጌልን የሚያሳድዱ ይጠፋሉ፡ ወንጌል ይቀጥላል። ካስፈለገ ሃገራዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተን ጥያቄያችን እናቀርባለን።

የቢሾፍቱ ከተማ ካብኔ እና ከንቲባ ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንሱ! ሲሉ መጋቢ ጌትነት ለማ በመግለጫው አንስተዋል።
ክርስቲያኖች ጸልዩ። ካውንስሉ በቀጣይ ሁኔታዎችን እየተከታተለ ያሳውቃል።

Photos from የሺንሽቾ ከተማ ቁ.1 ቃለሕይወት ቤተ ክርስቲያን's post 04/07/2024
24/01/2024

ከ1:00 ሰዓት በኋላ በሠራራና አካባቢው "በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የንስሐ ጥሪ አዋጅ!" የሺንሽቾ ከተማ ቁ.1 ቃለ ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በመተባበር የሚያካሄደውን የአደባባይ ፀሎትና የንስሐ ጥሪ አዋጅ ፕሮግራም እየተከታተሉ አብረውን ይፀልዩ!

Photos from የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት's post 08/01/2024
11/07/2021

እነሆ ታላቅ የምሥራች
እግዚ/ር አምላካችን ታላቅ ነገር አደረገልን።

09/07/2021

Breaking news...!

Website