EEU

EEU

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from EEU, Government Official, .

Photos from Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት's post 20/07/2021
08/03/2021

የሀዘን መግለጫ
በሀገረ ማሪያም ደንበኞች አገልግሎት መስጫ መዓከል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በሹፍርና የስራ ዘርፍ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አውግቸው ቸሬ በአደረባቸው ህመም በእክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።
አቶ አውግቸው ለስራ ታታሪ ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቀና ሰው አክባሪና ከሰው ተግባቢ መልካም ሰው ነበሩ ።
አቶ አውግቸው የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጆች አባት ነበሩ ።
ለወዳጅ ዘመድና ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል። መልካም ረፍት
የደ/ዲ/ሀ/ደ/አ/መ/ማዕከል

26/02/2021

ደንበኞች እንዴት የተጠቀሙበትን የፍጆታ ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ?
***************************
በርካታ የድህረ ክፍያ ደንበኞች የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት እንደሚሰላ ባለማወቃቸደው የተጋነነ የፍጆታ ሂሳብ ተጠየቅን የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡
ይሁን እንጂ ቅሬታው የሚነሳው ደንበኞች የተጋነነ ሂሳብ እንዲከፍሉ በመደረጉ ሳይሆን የፍጆታ ሂሳብ እንዴት መሰላት እንዳለበት በቂ ግንዛቤ ስለሌላቸው ነው፡፡ ይህን ክፍተት ለመሙላት የሚከተለውን መረጃ አስቀምጠናል፡፡

ደንበኞች በመኖሪያ ቤታቸው የሚጠቀሙባቸውን የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን መነሻ በማድረግ ምንያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደተጠቀሙና ምን ያህል የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍሉ መረዳት ይችላሉ፡፡

ለምሳሌ አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ 3000 ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም እና 1000 ዋት ሰ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት ለ30 ቀናት ቢጠቀምና ምን ያህል ኪ.ዋ.ሰ እንደሆነና ምን ያህል የፍጆታ ሂሳብ እንደሚከፍል ለማወቅ የተጠቀመበትን የኤሌክትሪክ ሃይል በመደመር ወደ ኪ.ዋ.ሰ መቀየር ይጠበቅበታል፡፡
• 4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት ሰ ፣
• 3000 ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት=60,000 ዋት ሰ፣
•1000 ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት=150,000 ዋትሰ
43,200 ዋት ሰ+ 60,000 ዋት ሰ + 150,000 ዋት ሰ= ጠቅላላይ ድምር 253,200 ዋት ሰ ይሆናል፤ ይህ ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት መቀየር አለበት፤ በመሆኑም 1 ኪሎ ዋት ሰዓት=1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡

የመኖሪያ ቤት የታሪፍ ስሌት 7 ደረጃዎች ያሉት ሲሆን አንድ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ በወር የተጠቀመበት የኤሌክትሪክ ሃይል በሚያርፍበት የታሪፍ እርክን ተባዝቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት አንድ ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ሃይል ቢጠቀም በቀጥታ 4ኛው እርከን ላይ የሚያርፍ በመሆኑ በ1.6375 ብር የሚባዛ ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት 253.2 x 1.6375 ብር= 414.615 ብር ይሆናል፤ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42 ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው የፍጆታ 456.615 ብር ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከታህሳስ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ተከታታይ አመታት የሚተገበር የታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ስሌት የተሰራው ከታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 2014 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ በሚቆየው የታሪፍ እርከን በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን የተጠቀማችሁበትን የፍጆታ ሂሳብ ለማስላት ይረዳችሁ ዘንድ ከታች የተቀመጠውን የታሪፍ ማስተካከያ እርከን እና የአገልግሎት ክፍያ ሰንጠረዥ መመልከት ትችላላቸሁ፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ ፈጣን መረጃ ያግኙ።
https://t.me/eeuethiopia

08/01/2021
28/10/2020

በቀጣዮቹ ቀናት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል
****************************
አርብ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በኮተቤ ላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካዔል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምህርት ስርጭት፣ በእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስትያን፣በሜጋ እና አካባቢዎቻቸው፣በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በቼራሊያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣በማሩ ብረታ ብረት፣በወህይኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ በቦሌ ሚካዔል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ-
•በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በፍየል ቤት፣ በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤

በተጨማሪም ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በኮተቤ ላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካዔል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምርት ስርጭት፣በእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስትያን፣ በሜጋ፣ በኮተቤ ብረታ ብረት፣ በኮተቤ ኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በአንቆርጫ ሰፈር፣ በእፎይታ ሰፈር፣ በጎተራ ላንቻ፣ በግሎባል ሆቴል፣ በጨርቆስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-

•በኦሎምፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮምያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ እና አካባቢዎቻቸው፤
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Photos from Gambella Regional State Electric Utility /የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት/'s post 02/10/2020
Photos from Oromia Electric Utility's post 29/09/2020
21/09/2020
21/09/2020

የቋሚ ንብረት ቆጠራና ዋጋ ክለሳ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ
***************************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለውን ሃብትና ንብረት በትክክል ለማወቅና ጥቅም ላይ ለማዋል ተግባራዊ እያደረገው የሚገኘው የቋሚ ንብረት ቆጠራና ዋጋ ክለሳ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የአይ ኤፍ አር ኤስ እና ፌር ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ለገሰ ገልፀዋል፡፡

የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ቋሚ ንብረቶችን በመቁጠር፣ በመመዝገብ፣ የዋጋ ተመን በማስቀመጥ እና ክለሳ በማድረግ ተቋሙ ያለውን ሃብትና ንብረት በትክክል ለማወቅና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶች ለመለየት መሆኑን ዳይሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ 63 ሺህ 36 ኪ.ሜ የመካከለኛና 49 ሺህ 57 የዝቅተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች፣ 277 ኪ.ሜ ከመሬት በታች ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች፣ 42 ሺህ 350 ትራንስፎርመሮች፣ 3 ሚሊዮን 672 ኢነርጂ ሜትሮች፣ 11 ባለ 45 ኪሎ ቮልትና 29 ባለ 66 ኪሎ ቮልት ማከፈፋያ ጣቢያች፣ 11 ባለ 45 ኪሎ ቮልትና 29 ባለ 66 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመሮች የቆጠራ ስራ ተከናውኗል፡፡

እንዲሁም 253 የመሬት ይዞታዎች፣ 1 ሺህ 392 ተሸከርካሪዎች፣ 40 ማምረቻ ማሽኖች፣ 237 የህንጻ ግንባታዎች፣ 97 የነዳጅ ማከፋፋያ ጣቢያዎች፣ 11 የፖል ማምረቻ ቦታዎች፣ 11 የብረትና እንጨት ወርክ ሾፖች፣ 8 የእንጨት ፖል ማምረቻ ማሳዎች ቆጠራና ምዝገባ ስራ ተጠናቋል፡፡

የፕሮግራም ዳይሬክተሩ አክለውም በአሁን ወቅት የቋሚ ንብረት የቆጠራ ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልፀው፤ የዋጋ ትመናና ክለሳ ስራዎችን ግን በቀጣይ Price water house Coopers Associates Africa Limite (PWC) ከተሰኘ አማካሪ ድርጅት ጋር እንደሚከናወን አንስተዋል፡፡

የቋሚ ንብረት ምዝገባና ዋጋ ትመና ፕሮግራም ስራው በሙሉ ሲጠናቀቅ ተቋሙ በቅርብ ጊዜ ለተገበረው ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላንግ የዘመናዊ አሰራር ስርዓት ግብዓት ይሆናልም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተቋሙን ቋሚ ንብረት የትና በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ለማወቅ፣ የንብረት ቆጠራና ኢንስፔክሽን አሰራሩን ለማቀላጠፍ፣ የተቋሙን ቋሚ ንብረት መጠንና ወቅታዊ ዋጋ ለማወቅ እንዲሁም የቋሚ ንብረት መጠንና ወቅታዊ ዋጋ በሂሳብ መግለጫዎቸ ላይ እንዲታይ ለማድረግ እንደሚረዳ አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ ፈጣን መረጃ ያግኙ።
https://t.me/eeuethiopia

27/08/2020

የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ አድማሱ ወንድምአገኝ ህልፈተህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በሪጅናችንና በተቋማችን ሰራተኞች ስም ይገልፃል

የአቶ አድማሱ ወንድምአገኝ አጭር የሕይወት ታሪክ

አቶ አድማሱ ወንድምአገኝ መኩሪያ ከአባታቸው ከአቶ መኩሪያ ፈለቀ እና ከእናታቸው በወ/ሮ መርሻ ወርቁ በ1958 ዓ.ም በቀድሞው በሸዋ ክፍለ ሀገር ሸንኮራና ምንጃር አውራጃ በባልጨ ወረዳ ልዩ ቦታው ሸንኮራ ተወለዱ፡፡
ከትውልድ ቦታቸው ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኮከበ ፅባ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በምስራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን ከዚሁ ት/ቤት በአውቶሜካኒክስ የትምህርት ዘርፍ በሰርቲፊኬት ተመርቀዋል፡፡
አቶ አድማሱ መኩሪያ በነሀሴ 16 ቀን 1985 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መብራትና ሀይል ባለስልጣን ከመቀጠሩ በፊት በውትድርና ሙያ በመሰማራት አገራቸውንና ህዝባቸውን አገልግለዋል፡፡ በተቋሙም ከተቀጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ላለፉት 27 አመታት ለተቋሙ ስኬት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ጥረት አድርገዋል፡፡
በተቋሙ የስራ ዘመናቸው ከ1985 - 1992 ዓ.ም ድረስ በጥበቃ ሰራተኝነት፣ 1992 - 1993 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ሪጅን ምስራቅ ዲስትሪክት በቴክኒክ ባለሙያነት፣ 1993 - 1999 ዓ.ም ድረስ በምስራቅ ዲስትሪክት በዲስትሪቢውሽን ላይን ማንነት፣ ከ1999 - 2001 ዓ.ም በጁኒየር ዲስትሪክት ላይን ማንነት፣ ከ2001 - 2004 በሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት በከስተመር ኬር ቴክኒሺያንነት 2ኛ፣ ከ2004 - 2006 ዓ.ም በከስተመር ኬር ቴክኒሺያንነት 3ኛ፣ በምስራቅ አዲስ አበባ የሽያጭ ቢሮ ሰራተኛነት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የመሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ስራ አሰፈፃሚነትና በሌሎችም የስራ ክፍሎች ተመድበው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ እንዲሁም እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ሊቀ-መንበር በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
አቶ አድማሱ ወንድምአገኝ መኩሪያ በህይወት በነበሩበት ወቅት በስራቸው ታታሪ፣ ቀና እንዲሁም በሁሉም የስራ ባለደረቦቻቸው ዘንድ መልካም ተቀባይነት የነበራቸው መልካም ሰው ነበሩ፡፡ በስራቸው ላይ ባሳዩት ትጋት በተለያየ ወቅት ከተቋሙ፣ ከዞንና ወረዳ መስተዳድሮች እንዲሁም ሌሎች ተቋማት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ነሀሴ 20፤ 2012 ዓ.ም በአፋር ክልል ለስራ በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩበት ወቅት ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ በ54 አመታቸው ከዚህ አለም ተለይተዋል፡፡
አቶ አድማሱ ባለትዳርና የሁለት ወንድና የአንዲት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞችና አመራሮች በስራ ባልደረባችን በአቶ አድማሱ ወንድምአገኝ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!

25/06/2020

Sabrin shefa Ahmed ከኦስትሪያ #ቪያየና አዲስ አበባ ተወልዳ ሳዑዲ ያደገች፣ አሁን ነዋርነትዋን #ቪየና በማድረግ በዓረበኛ ቋንቋ ስለህዳሴ ግድብ የተለያዩ ፅሁፎችን ትፅፋለችተ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ህዳሴ ግድብ ትሞግታለች ፣ ታደራጃለች፣ የኛ ጀግና!

የ ሁለተኛዋ እንስት ! ጀግኒት!

ተጠራርተናል ስልህ 👇👇🇪🇹🇪🇹
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
http://t.me/erkebmeana

11/06/2020

የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ደንበኞቻችን ሊያደርጉልን የሚገቡ ድጋፎች
***********************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞቹ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ዘረፈ ብዙ ሥራዎች እያከናወነ ሲሆን፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንደዚሁ የተለያዩ ዘመናዊ የአገልግሎት አማራጮችን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ደንበኞቻችን ሊያደርጉልን የሚገቡ ድጋፎችም አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡

• የፍጆታ ሒሳብ በወቅቱ መክፈል፤

• የሚገለገሉበትን ቆጣሪ ከጉዳት መከላከል፤

• የቆጣሪ ወይም ሌላ ማንኛውም የኤሌክትሪክ አውታሮች ላይ ጉዳት/አደጋ ሲያጋጥም ወዲያው ማሳወቅ፤

• የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳይባክን በአግባቡ መጠቀም፤

• የመስሪያ ቤታችን ሰራተኞች ለስራ በሚመጡበት ወቅት ተገቢውን ትብብር ማድረግ፣ እንዲሁም የተቋሙን ሰራተኛ ተመሳስለው ህገወጥ የሚፈጽሙትን ማጋለጥ፤

• በየሪጅኑና በየዲስትሪክቱ በመካሄዱ የህዝብ መድረኮች በመካፈል ገንቢ አስተያየቶች በመስጠት የመፍትሄ አካል መሆን፤

• ደረጃውን የጠበቀ እና ኃይል ቆጣቢ ዕቃዎችን መጠቀም፤

• በኤሌክትሪክ መስመሮች አካባቢ የሚገኙ ዛፎችን በመቁረጥ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን መቀነስ፤

• ያልተፈቀደ ኃይል አለመጠቀም እንዲሁም የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች ላይ ስርቆት የሚፈጽሙ አካላትን በማጋለጥ ወንጀልን መከላከል የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ራስዎንና ቤተሰብዎን እንዲሁም ማህበረሰቡን ከኮሮና ቫይረስ እየተከላከሉ፤ የሚጠበቅብዎትን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ ፈጣን መረጃ ያግኙ።
https://t.me/eeuethiopia

11/06/2020

የኃይል ማቋረጥ ማስታወቂያ
=====================
ለክቡራን ደንበኞቻችን!! የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም አማካይንት ያሰራቸውን አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ለማገናኘትና ለነባር መስመር ጥገና ለማድረግ ሲባል፡-
- ከሰበታ አንድ ሰብስቴሽን መጋቢ መስመር ቁጥር 5 እና 11፤
- ከሰበታ ሁለት ሰብስቴሽን መጋቢ መስመር ቁጥር 5፤ እና
- ከጌጃ ሆራ ሰብስቴሽን ኤሌክትሪክ የሚታገኙ የአለም ገና፣ ሰበታ፣ ጌጃ ሆራ እና ተፍኪ አከባቢዎች ሰኔ 5፣ 6፣ 7 እና 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

06/06/2020

የሱማሌ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
************************************
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሃገራችን ከተከሰተ ጀምሮ በሪጅን ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ የተለያዩ የጥንቃቄና የመከላከል ስራዎች እየስሩ እንደሚገኙ የሱማሌ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከቫይረሱ መጨመር ጋር ተያይዞ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከሪጅን ጽ/ቤት እስከ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ድረስ በመናበብ የክትትል ድጋፍና የቁጥጥር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ስርጭቱን ለመከላከል የሚረዱ አሰራሮችን እና ለጥንቃቄ የሚረዱ የግብዓት አቅርቦቶችን የማዳረስ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስፈፀምና ድንጋጌዎችን የማስተግበር፣ ስራተኛውም ሆነ አግልግሎቱን ፈልገው ለሚመጡ ደንበኞች ሙቀታቸውን ተለክተው እንደሚገቡ እና ሰራተኛው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ተጠቅመው እየሰሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በቀጣይም የበሽታው ስርጭት እንዳይስፋፋ የሚረዱ የተለያ ዘመናዊ አሰራሮችን የመተግበር ስራዎች እንደሚቀጥሉ ገልፀው፣ ቫይረሱን የመከላከል አቅምን ከማሳደግ አንፃር በየወቅቱ ለሰራተኞቹ የጥንቃቄ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

የሱማሌ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ አንተነህ መላኩ ሰራተኞች እንዲሁም ደንበኞች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፤ ፈጣን መረጃ ያግኙ።
https://t.me/eeuethiopia

Photos from ቀልብን ሰሊም ኔት's post 31/05/2020
17/05/2020

ንኩትና ውርድ ከራስ !!

ነዳጅ የጫነ ግዙፍ የኢራን መርከብ በትላንትናው ዕለት ውቅያኖስን እያቋረጠ ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ቬንዙዌላ ጀምሯል ።
በኢራን ላይ የነዳጅ ሽያጭን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ የጣለችው አሜሪካ መርከቧ ጉዞዋን እንዳትሞክር ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ ብትሰጥም ኢራኖች ግን የሚበገሩ አልሆኑም ።
በአለም አቀፍ ውሃ ላይ የነዳጅ ታንከር መርከባችንን እያንሸራሸርን ንግድ እንለዋወጣለን ማንኛውንም አለም አቀፍ ህግን አልጣስንም ከጉዞአችን ሊያቅበን የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ኃይል ከባህር ላይ ዘራፊ ወንበዴዎች ለይተን አናያቸውም ፡ በማለት አሻፈረን ብለዋል
የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ አሊ ራባይ እንደገለፁት
" ኢራን እና ቬንዙዌላ ሁለቱም ነፃ ሀገራት ናቸው በወደዱት እና በመረጡት መልኩ የማንንም ፍቃድ ሳይሹ የንግድ ልውውጣቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ ይህንን ጤናማ እንቅስቃሴ ለማገድ አሜሪካን ሙከራ የምታደርግ ከሆነ አደጋ ይኖረዋል ለትንኮሳው ምላሽ እንደምንሰጥ እርግጥ ነው "

አሜሪካን በበኩሏ ነዳጅ የጫነችዋና የኢራን መርከብ ከጉዞዋ እንደምታቅብ የገለፀች ሲሆን እርምጃውን እንዴት ? እና በምን ? አይነት መንገድ እንደምትወስድ አልገለፀችም

12/05/2020

⚡ በዘረኝነት ምክንያት ብዙ እጅግ የተማረረው ማሪዬ ባላቶሊ ለአፍሪካዊያን ተጨዋቾች ይህንን መልእክት አስተላልፏል :

" በአውሮፖ ያላችሁ አፍሪካዊያን አንድ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ እሱም በአውሮፖ የምንገኝ አፍሪካዊያን ገንዘባችንን አንድ ላይ በመሰብሰብ ይህችን ዘረኛ የሆነች አውሮፖን በመልቀቅ በአፍሪካ ጥራታቸውን የጠበቁ ስታዲዬሞችን በመስራት እና የራሳችንን ወጣቶች ማሳደግ አለብን ገንዘቡ አለን በየሀገሩ ጥራታቸውን የጠበቁ 5 ስታዲዬሞችን መስራት እንችላለን ከዛም ማንም አፍሪካዊ ወደአውሮፖ ኳስ ለመጫወት እንደማይሄድ እንፈራረማለን በሀገራችን በአፍሪካ ወንድሞቻችን የማንንም ዘረኛ የዘረኝነት ድምፅ ሳይሰሙ በሚወዷቸው እህት እና ወንድሞቻቸው ፊት እንዲጫወቱ ማድረግ እንችላለን እኛ ከእነሱ የተሻልን እና ጥሩ የእግር ኳስ ክህሎት ያለን ሰዋች ነን." ማሪዬ ባላቶኒ

Timeline photos 12/05/2020

+++ ከጣልያን የተላለፈ መልህክት +++
" እባካችሁ ሳይመሽ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችሁንና
የምትወዷቸውን ሁሉ ጠብቁ !!! "

ሰላም ለሁላችሁ፡
እኛ በጣሊያን አገር ሚላን ነው የምንኖረው፡፡ አሁን ላይ በሚላን
ህይወት ምን እንደሚመስል ልገልጽላችሁና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ
ውስጥ ሆኜ እናንተ እኛ ከሰራነው ስህተትና በውጤቱም ከገባንበት
አጣብቂኝ ህይወት የምትማሩት ቁም ነገር አለ ብየ ነው ይህንን
የምጽፍላችሁ፡፡
አሁን ላይ ሁላችንም በማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው
ያለነው፡፡ ፖሊሶች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ሲሆን ማንኛውንም
ከቤት ውጪ ሲዘዋወር ያገኙትን ሁሉ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፡፡
ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡- የንግድ ሱቆች፣ ሞሎች፣ የሽያጭ እቃ
ማዕከሎች ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡፡ የአለም ፍጻሜ ነው
የሚመስለው! ለኑሮ ተስማሚና ጤና ማህይወት ታስተናግድ
የነበረችው ጣልያን ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሰዓታትና ቅጽበት
ከጨለማ ውጪ ምንም የሌለባት የተወረረች ከተማ መስላ ነው
የምትታየው፡፡ እኔ ራሴ ተመልሼ በዚህች መሬት ላይ እንደ
ቀድሞው በህይወት እኖራለሁ የሚለው ተስፋየ ጨልሟል፡፡ እዚህ
አገር ህዝቡ ግራ ገብቶታል፣ በመከፋት አንገቱን አቀርቅሯል፤ ተስፋ
በመቁረጥም ይህ ሁሉ መዓት እንዴት እንደታዘዘበትና ይህም
በቅዠት እንጂ በውን የማይመስል የጭንቅ ወቅት መቼ
እንደሚያበቃ ግራ ገብቶት በየቤቱ ተዘግቷል፡፡
ይህ ክፉ ቀን ግን የጀመረው ዝም ብሎ አልነበረም ! አንድ ትልቅ
ስህተት ነበር ! ገና የኮሮና ቫይረስ (COVID – 19) አገራችን
ጣሊያን እንደገባ በይፋ በተነገረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት
ህዝቡ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ አኗኗሩን እንደተለመደው
ቀጠለ፣ ህዝቡ ወደ ስራ መሄዱን አልተወም፣ ወደ መዝናኛ
ቦታዎች እንደ ተለመደው በጋራ ይሄዳል እንደእረፍት ጊዜ ከጓደኞቹ
ከሌሎቹም ጋር እንደተለመደው በብዙ ቁጥር መንጎዱን
አላቆመም፡፡ ሁሉም መጨረሻውን ሳያስብ ትክክል ያልሆነ የኑሮ
ዘይቤውን ቀጠለ፤ እናንተም እንደዚህ እየሆናችሁ ነው !
ልለምናችሁ ! እየቀለድኩ አይደለም፤ እባካችሁ ተጠንቀቁ !
የምትወዷቸውን ሁሉ፣ ቤተሰቦቻችሁን፣ ወላጆቻችሁን፤ አያቶቻችሁን
ከዚህ መቅሰፍት ጠብቁ ! ይህ በሽታ በተለይ ለነሱ እጅግ አደገኛ
ነው፡፡
እዚህ በቫይረሱ ምክንያት በየእለቱ የ200 ሰዎች ህይዎት
እየተቀጠፈ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ሚላን ውስጥ ያለመድሀኒት
ስለማይረባ አይደለም፤ ከመድሀኒት ጋር ባለ ብቃት ሚላን ከዓለም
ከፊት ተርታ ከሚሰለፉት አንዷ ነች፡፡ ለበርካቶች በየእለቱ ሞት
ምክንያት እየሆነ ያለው ደግሞ ለእያንዳንዱ ለቅርብ ክትትል
የሚበቃ በቂ ቦታ ባ ለመኖሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብታምኑም
ባታምኑም ሀኪሞች ማንን እናትርፍ ሳይሆን ማን ቢሞት ብዙዎችን
መታደግ ይቻላል የሚል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል፡፡ይህ
ሁሉ የሆነው ቫይረሱ ወደ ዚህ ቦታ መግባቱ በተነገረበት
የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በህዝቡ ዘንድ የነበረው ሞኝነትና ችግሩን
ተገንዝቦ ፈጥኖ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ህይወት በነበረው ሁኔታ
እንዲቀጥል በማድረጉ ነው፡፡
እባካችሁ ከእኛ ስህተት ተማሩ! የእኛ አገር ትንሽ የህዝብ ቁጥር
ያለበት ነው፤ እናም በአገር ደረጃ እጅግ የከፋ ፍጻሜ እንዳይኖረን
ያሰጋል፡፡ እባካችሁ በደንብ አዳምጡኝ፡-
• ህዝብ በብዛት ባለባቸው ስፍራዎች አትሂዱ፤
• ብዙ ህዝብ በሚጋራቸው ቦታዎች ላይ ላለመመገብ ሞክሩ፤
• በዚህ ወቅት ብዙ ጊዜ በቤታችሁ ተቀመጡ፤
• ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጡ መመሪያዎችን አዳምጡ፤
አዳምጣችሁም ተግብሩ (እንደቀልድ አትዩአቸው !)
• ከማንኛውም ሰው ጋር ስታወሩ ከአንድ ሜትር በላይ በሆነ ርቀት
ላይ ሆናችሁ አውሩ፣ አትጠጋጉ፣ አትተቃቀፉ፣ አትጨባበጡ፤
• ማድረግ ያለባችሁን የመከላከያ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ከሌሎች
ስህተትም ተማሩ፤
• በሽታ የመከላከል አቅማችሁ እንዳይዳከም‘ቫይታሚን “ሲ”
ተጠቀሙ
• የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመከላከልና ስርጪቱን
ለመቆጣጠር ለሚያደርጉት ጥረት አጋዥ ሁኑ
ጣሊያን ውስጥ መላ አገሪቱ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ
እንዳለች ቁጠሩት፤ 60 ሚሊዮን ህዝቧ ማቆያ (Quarantine)
ውስጥ ነው እነደማለት !ታዲያ ህዝቡ በመጀመሪያ ላይ የተሰጡ
ማስጠንቀቂያዎችን አዳምጦ ተግባር ላይ ቢያውል ኖሮ ይህ ሁሉ
መጥፎ ቀን እንዳይመጣ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡
እናም እባካችሁ ሳይመሽ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችሁንና
የምትወዷቸውን ሁሉ ጠብቁ !!!

መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ
ከአንድ ጣሊያናዊ/ት ወዳጅ (Jsca)
ይህ ለእኛ የማንቂያ ደወል ነውና እንጠቀምበት !

11/05/2020

#ኤርዶጋን ዛሬ ትዊተር ላይ ደምቆ አመሸ ኤርዶጋን የሚል #ሃሽታግ ነበር
ፕሬዚዳንቱ አሁን በትዊተርም በኩል ምላሽ ሰጡ



❤❤🌙

❤❤❤❤🌙
በቴሌ ግራም መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ካስፈለገ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን
http://t.me/erkebmeana

08/05/2020

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች በሙሉ
********************
በአለም ደረጃ እየተስፋፋ የመጣውን የኮረና ቫይረስ /ኮቪዲ-19/ የተባለው ወርሽኝ በሽታ የተለያዩ ጉዳቶች እያመጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሃገራችንም ከተከሰተ በኃላ በመንግስት በኩል ስርጭቱን ለመከላከልና በቶሎ ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ተቋማችንም ወረርሽኙ እንዳይሰራጭና ሠራተኞቻችንና ደንበኞቻችን እራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ የተለያዩ የመከላከያ አማራጮችን ሂደት በሂደት ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡

ሆኖም የኤሌክትሪክ አቅርቦት ዘርፉ ወረርሽኙን መከላከል ሂደት ሚናው እጅግ የላቀ በመሆኑ፤ ተቋማችን በዚህ ረገድ ከፍተኛና ድርብ ሃላፊነት አለበት፡፡

በመሆኑም ውድ የተቋማችን ሠራተኞች፤ ዛሬ በሚኒስትሮች ም/ቤት ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል መንግስት ሠራተኞች በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የተባለው መመሪያ የኛን ተቋም የማይመለከት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመንግስት የልማት ድርጅት በመሆኑና ዘርፋችን ባለው ድርብ ሃላፊነት ምክንያት መመሪያው እኛን የማይመለከት መሆኑን ተገንዝባችሁ እንደሁልጊዜው በሥራ ገበታችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ነገር ግን መላው ሠራተኛችን ከበሽታው ለመከላከል አስፈላጊውን የመከላከያ ቁሳቁሶችን በተከታታይ የምናቀረብ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አገልግሎት የምትሰጡና በቀጥታ ከደንበኛ ጋር የምትገኛኙ ባለሞያዎች አስፈላጊውን ርቀት በመጠበቅ እንዲፈፀምና የሚመለከታችሁ የሥራ መሪዎች ይህንን እንድታስፈፅሙ በአፅንኦት እናሳስባለን፡፡

ደንበኞቻችንም አገልግሎት ፈልጋችሁ ወደ እኛ ስትመጡ ቢሮ ከመግባታችሁ በፊት እጃችሁ እንድትታጠቡና ርቀታችሁን ጠብቃችሁ እንድትስተናገዱ እንጠይቃለን፡፡

በተለይ የቢሮ ጥግግትና ርቀትና ለማስጠበቅ እንዲሁም በሽታውን በተቋም ደረጃ እንዳይስፋፋ ለመከላከል የተቋሙ ከፍተኛ ማኔጅመንት የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈ በመሆኑ፣ በቀጣይ በተለያዩ የግንኙነት አማራጮች የምናሳውቃችሁ መሆኑን በዚህ አጋጣም ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Photos from Benishangul Gumuz Electric Utility.የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት's post 30/04/2020
29/04/2020

ስለ ሰሜን ኮሪያ ስንቶቻችን እናውቃለን?
1. ሀገሪቷ ላይ በየ 5 ዓመት ምርጫ ይደረጋል ነገር ግን የምርጫ ካርዱ ላይ የአንድ ፓርቲ ስም ነው ያለው።
2. Computer ወይንም መኪና ለመግዛት ከመንግስት ፍቃድ ያስፈልጋል።
3. 1 የረዲዮ ጣብያ ነው ያላት ረዲዮ ድምፅ መቀነስ እንጂ መዝጋት አይቻልም።
4. የሀገሪቷ ዋና ከተማ Piyongyang ውስጥ መንግስት የፈቀላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው መኖር የሚችሉት።
5. ሀገሪቷ 3 የTV ጣብያ ነው ያላት። የነሱ ካላንደር 1912 ነው First kim jong ከተወለደበት ቀን አንስቶ ነው የሚቆጥሩት።
6. Blue ጅንስ ልብስ መልበስ አይቻልም Blue ጅንሶች የአሜሪካ ነው ብሎ ያምናሉ።
7. ሁለም ማታ ማታ ሙሉ ሀገሪቷ ላይ ማብራት ይጠፋል።
8. ሀገሪቷ ውስጥ አካል ጉዳተኛ የለም አካል ጉዳተኛ ስወለድ ይገደላል።
9. የKim jong የፀጉር አቆራረጥ መቆረጥ አይቻልም በህግ በሞት ፍርድ ያስቀጣል።
10. ሁሉም ሙሹሮች በሰርጋቸው ቀን የ2ኛ king jong ቀብር መጎብኘት ግዴታ ነው።
11. አንድ ሰው ወንጀል ከሰራ ሙሉ ቤተሰቡም ጭምር የሚጠየቀው።
ምንጭ General Knowledge ጠቅላላ እውቀትዎን