Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት

Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት, Government Organization, .

03/05/2024

የስቅለት እና ትንሣኤ በዓል አስመልክተው የሁምቦ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አመኑ ጎአ ያስተላለፉተሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችን ኃጢያት ስርየት ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፣ በሰው ልጆች እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የሞት የጥል ግድግዳ አፍርሶ ዳግም ዘላለማዊ ህይወት የሰጠን ዕለት በመሆኑ ለዚህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል አንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን!!

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የኃጢያት ቤዛ በመሆን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞቱና በሦስተኛው ቀን ከሞት በመነሳት የትንሳዔን ህይወት የሰጠን እሱ ለፈጠረው ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ታላቅ ፍቅሩን የገለፀበት መንገድ ነው።

ይህም ከራስ ይልቅ ለሌላው መሰቃየትን፥ ከራስ ሰላም ይልቅ ለሌላው መሞትን፥ ከራስ ጥቅም ይልቅ ለሌላው ዋጋ መክፈልን በአጠቃላይ ለሌላው ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነት ምን ያህል ዋጋ ታላቅ እንደሆነ አስተምሮናል።

የፋሲካ በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን እኛ የሰው ልጆች ከዘላለማዊ ሞት ዳግም ወደ ህይወት የተሸገርነበት ዕለት ነዉ።

የዘንድሮዉን የፋሲካ በዓል እያከበርን የምንገኝበት ወቅት በአንድ በኩል በሀገራችን እየተመዘገበ ያለዉ ለዉጥ በብሩህ ተስፋና ራዕይ ተነቃቅተን ያለንበት ነዉ።

በዓሉ ስለሰው ልጆች ፍቅር በመስቀል ላይ በተከፈለ ዋጋ የተገኘ መሆኑን በማስታወስ ያለንን ማሕበራዊ አንድነታችንን በማጠናከር፣ በመዋደድና በመከባበር ማክበር ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ለሁላችንም የጋራ የሆነችውን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ሆነው ባስተማረን ትህትና መሰረት ህዝባዊ ጥቅምን አስቀድመን ችግሮችና ፈተናዎች ሳንበገር መክፈል ያለብንን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለን የህዝባችንን ሰላም በማረጋገጥ የልማትና የብልፅግና ትንሳዔያችንን አናፋጥን ሲሉ አሳስበዋል።

በዓሉ ሲከበር በእምነታችን መሠረት ተርፎን ሳይሆን ካለችን አካፍለን፣ ተጠያይቀን፣ በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ ባህልና እሴታችን መሰረት በተለያየ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖችን አስበን ያለንን በማካፈል፣ ማእዳችንን በማጋራት ሊሆን እንደሚገባ አደራ በማለት ጥሪውን አስተላልፈዋል።

በድጋሚ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የበለጠ የሚንተሳሰብበት የትንሳኤ በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።

አቶ አመኑ ጎአ
የሁምቦ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ
እና
የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
ሚያዝያ 25 /2016 ዓ.ም
መልካም በዓል!

03/05/2024

የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ፀጋዬ ቀልታ ለስቅለት እና ትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና የትንሳኤ በዓል በሠላምና ጤና አደረሳችሁ ።

የክርስትና አስተምህሮት እንደሚያስረዳን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ህይወቱን የሰጠው ስለ ሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ነዉ። እኛም አርዓያውን ተከትለን በፍቅር እንድንኖር እና መስጠትን የህይወታችን አካል እንድናደርግ ነው ።

ስለሆነም የስቅለት እና የፋሲካ በዓል የመስዋዕትነት፣የይቅርታ ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

በመሆኑም ይህን ታላቅ ሐይማኖታዊ በዓል ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም የአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ጥሪ አቀርባለሁ ።ንፁህ ሆነን እንደተፈጠርነው ሁሉ በንፅህናና በቅንነት መኖር እና ህዝባችንን ከልብ ማገልገል ይጠበቅብናል።

የስቅለትና የትንሳኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብን ፍቃድ ለመፈጸም ተላልፎ የተሰጠበት፤ የእኛን በደልና ኃጥኣት በራሱ ላይ ያኖረበት፣ ሞቶ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት እንድሁም ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የሆነበት በዓል ነው ብለዋል።

በወረዳችን 2016 በጀት ዓመት በጀመርነው በበልግ ምርቶቻችንን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁላችንም በተሰማራንበት ጠንክረን በመስራት ይህንን ወኔ ስንቅ በማድረግ ድህነታችንን ለማስወገድ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል።

የበዓላቱን ጥልቅ ተምሳሌትነቶች በእለት ተለት ህይወታችን ተግባራዊ በማድረግም በአምላክ አርአያ የተፈጠሩትን ወገኖቻችንን በማገልገልና ለችግሮቻቸው በመድረስ መንፈሳዊም ሆነ ሀገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ አደራ እላችኋለሁ፡፡

በድጋሜ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅላት እና ትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! አደረሰን !!!
አቶ ፀጋዬ ቄልታ
የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ሚያዝያ ፤2016 ዓ.ም
መልካም በዓል!!

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 29/04/2024

በሁምቦ ወረዳ የህብረት ስራ ጽ/ቤት የህብረት ሥራ ማህበራትን ሪፎርም እና ቀጣይ 100 ቀን ዕቅድ ላይ ያተኮረ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ሁምቦ፣ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን የሁምቦ ወረዳ የህብረት ስራ ጽ/ቤት የህብረት ሥራ ማህበራትን ሪፎርም እና ቀጣይ 100 ቀን ዕቅድ ላይ ያተኮረ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የንቅናቄ መድረኩ አሁናዊ ገበያ አለመረጋጋትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ማህበራት በአዲስ መልኩ ሪፎርም መደረጉ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

ህብረት ሥራ ማህበራት መልሶ ለማጠናከር የተጀመረው ሪፎርሙ ውጤታማ እንዲሆን ማህበራት እና ለሎች ባለድርሻ አካሌት የሚጠበቅበትን ኃላፊነትእንዲወጡ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነም ይጠበቃል።

በንቅናቄው መድረክ የሁምቦ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አመኑ ጎአ፣ የሁምቦ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ደነቄ ጊታ እና የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ በለጠች ባቢሶን ጨምሮ የወረዳው አጠቃላይ አመራር፣ የዞን ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የህብረት ሥራ ማህበራት፣ የቀበሌያት አስተዳዳሪዎች እና ለሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 26/04/2024

የህብረት ስራ ማህበራትን ሪፎርም ሲደረግ መሠረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ሊሆን ይገባል፦ አቶ ሳሙኤል ፎላ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዚያ 17/2016 የወላይታ ዞን ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ማህበራትን ሪፎርም ማስጀመሪያ፣ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ቀሪ 100 ቀናት ዕቅድ ላይ የተካሄደው መድረክ ተጠናቀቀ።

ማጠቃለያ ሀሳብና ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ህብረት ስራ ማህበራት ለህብረተሰቡ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረት ስራ ማህበራት በአዲስ መልኩ ሪፎርም መደረጉ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግር ለመቅረፍ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አስረድተዋል።

ገበያን ማረጋጋት የሚችል ጠንካራ ህብረት ስራ ማህበራት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የምርት ትስስርን በመፍጠር የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የህብረት ስራ ማህበራት ሚና የላቀ ድርሻ እንዳለውም አስገንዝበዋል።

ህብረት ስራ ማህበራት ገበያን የሚያረጋጉ ተቋም ናቸው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህም አባልን ማፍራትና ማሳደግ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ቁጠባንና ኢንቨስትመንት ማጣጣም ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ማህበራት ከሚያገኛቸው ገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

ሪፎርም ሲደረግ መሠረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ሊሆን እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁ ህብረት ሥራ ማህበራት መልሶ ለማጠናከር የተጀመረው ሪፎርሙ ውጤታማ እንዲሆን አመራሩ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት ይገባል ብለዋል።

ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚናደርገው ጉዞ ህብረት ሥራ ማህበራት ሚናቸውን እንዲወጡም ለማስቻል ሪፎርሙ ውጤት በሚያመጣ መልኩ መመራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

እንደ ሀገር የወጠነው ውጥን እና ለኢኮኖሚ ዕድገት ማህበራት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

የወላይታ ዞን ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ገቡ የህብረት ስራ ማህበራት ለዘላቂ ልማት የላቀ ድርሻ ያላቸው በመሆናቸው መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎችን የኅብረት ስራ ማህበር አባል እንዲሆኑ በማድርግ የማህበራት የውስጥ አቅም ማሳደግና ተደራሽ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 21/04/2024

ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለፀ
*****************

ለ2016/17 ምርት ዘመን 1 ሚሊዮን 78 ሺህ 257 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገልጿል፡፡

በ20 መርከቦች ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 96 ነጥብ 61 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱም ነው የተገለጸው፡፡

በአንፃሩ 37 ሺህ 792 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በጅቡቲ ወደብ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በ62 የባቡር ምልልስ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው 1 ሚሊየን 78 ሺህ 257 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ከ120 በላይ ወደሆኑ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በከባድ ተሽከርካሪዎች መጓጓዙም ተመላክቷል፡፡

ዘንድሮ ከ60 ሺህ እስከ 96 ሺህ ሜትሪክ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው በርካታ ግዙፍ መርከቦች ማዳበሪያውን ማጓጓዛቸውም በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል፡፡

በቀጣዩ ሳምንት 63 ሺህ 660 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል፡፡

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 19/04/2024

በሁምቦ ወረዳ ከ10 ሺህ በላይ የዲጂታል ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ያለመ ወረዳዊ ንቅናቄ ተጀምሯል።

ሁምቦ፤ ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ከ10 ሺህ በላይ አድስ የዲጂታል ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ያለመ ወረዳዊ ንቅናቄ ተጀምሯል።

በወረዳዊ የዲጂታል ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ዓላማ አድርገው በተጀመረው ንቅናቄ የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች በይፋ ተቀላቅለዋል።

ንቅናቄውን የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አመኑ ጎአ፣ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ደነቄ ጊታ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በለጠች ባቢሶ በጋራ በመሆን አስጀምረዋል።

አሁን ያለውን የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ የሚሻገር ጠንካራ አመራርና አባል ለማፍራት እጅግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጿል።

እንደሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያ እና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ ገለጻ በቀጣይ 100 ቀናት ከ10 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ ዘመቻ ሁሉንም ማህበራዊ መሰረት ባሳተፈ መልክ ለማካሄድ ታቅደው የአጭር ጊዜ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ተቀይሶ እየተሰራ ይገኛል።

ንቅናቄው በዋናነት ብልፅግና ፓርቲ አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ዳር ለማድረስ የዲጂታል ሚዲያው አዎንታዊ ሚናን ያበረክታል። ለዚህም መላው አመራርና አባል ለማሳተፍ ያለመ ነው።

ንቅናቄው ግቡን እስከሚመታ ድረስ በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ለተግባሩ ስኬታማነት ሁሉም የፓርቲው አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች የጀመሩትን የነቃ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 18/04/2024

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ የተመራ ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በጋራ ለመስራት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ልዑኩን ተቀብለው ያነጋገሩት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ክልሉ በአዲስ መልክ ሲደራጅ በነበረው ሂደት የሚዲያዎች ሚና ትልቁን ድርሻ የተወጣ መሆኑን አመልክተዋል።

ገዢ ሀገራዊ ትርክቶችን ወደ ህብረተሰቡ ለማስረፅ ሚዲያ ወሳኝ እንደሆነ የገለፁት ርዕሰ መሰተዳድሩ የሚዲያ ተቋሙ ከክልሉ ጋር በይበልጥ አብሮ ለመስራት በማሰቡ ምስጋና አቅርበዋል

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው ከተመረሰት ከ80 ዓመት በላይ ያስቆጠረው ሚዲያ አሰራሩን በማሻሻል ከክልሎች ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አንሰተዋል።

ተቋሙ እራሱን በዘመናዊ ስቱዱዮ ከማደራጀት ባለፈ የክልሎችን ሀብት እና ብዘሃ ማንነት በጥልቀት በመፈተሽ በአግባቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል ብለዋል።

መቀመጫውን በክልሉ በማድረግ የዘገባ ሽፋን ለመሰጠት እንዲቻል ባለሙያ በቅርብ ጊዜ እንደሚመደብ በውይይቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን የቀጥታ ስርጭት ስቱዱዮ ለማደራጀት የሚያስችል ቢሮ ርክክብም ተደርጓል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 18/04/2024

"ለወጣቱ የሚፈጠረው የስራ ዕድል ክህሎት መር መሆን ያስፈልጋል” አቶ ተስፋዬ ይገዙ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 10/2016 በወላይታ ዞን በሰባት መዋቅሮች የሚተገበር ለወጣቶች ስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ማያ (MaYEa) የተሰኘ ፕሮግራም ማብሰሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

በማብሰሪያ መርሃግብር የተገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ስራ ያላገኙና ነገን ተስፋ ለሚያደርጉ ዜጎች ስራ ዕድል መፍጠር የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

አንገብጋቢነቱ የወጣቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን ከማህበራዊ እና ከሠላምና ሀገራዊ ደህንነት ጋር የሚገናኝ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም ለትግበራው ርብርብ ማደረግ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የሚሰራው ስራ ክህሎት መር ባለመሆኑ የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ፕሮጀክት የሚተገብርባቸው አከባቢዎች ዕድሉን አሟጦ መጠቀም እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ለወጣቱ የሚፈጠረው ስራ ክህሎት መር መሆን እንዳለበትም ያሳሰቡት አቶ ተስፋዬ ክህሎት መር ከሆነ የማደግና የመዝለቅ አቅም እንዳለውም አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በሴቶች ላይ የሚተገብርው ፋይዳን በሚገባ መረዳት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተስፋዬ ሴቶች በጥራት ተመልምለው ክህሎታቸውን በማሳደግ ከተሰራ እጅግ በጣም ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አስገንዝበዋል።

ፕሮግራሙ ህብረተሰቡን ለመለወጥ እጅግ ወሳኝ አቅም እንዳለው ያስረዱት አቶ ተስፋዬ ለውጭ እና ለውስጥ ሀገር የስራ ስምሪት ለመስጠት ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነም አስገንዝበዋል

ለፕሮግራሙ ስኬታማነት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመገለጽ ፕሮግራሙ የሚተገብርባቸው መዋቅሮች ለስኬቱ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ፕሮጀክቱ በሰባት መዋቅሮ የሚተገበና አምስት ዓመት የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ከ36 ሺህ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችል መሆኑን የገለጹት አቶ ተፈሪ ከ209 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

የክልሉን ፋይናንስ አሠራር በመከተል የመደገፍና የማበረታታት ስራ በመስራት ጉድለቶችን በማረም ለወጣቱ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በበኩላቸው "የማያ" ፕሮግራም ዓላማው ባህላዊውን የኢትዮጵያ የንብ ማነብ ስራ በማሻሻል ከ1.8 ሚሊዮን ወጣቶች የክህሎት ስልጠና እና ፋይናንስ ተደራሽነት በማረጋገጥ ከአንድ ሚሊዮን ስራ አጥ ወጣቶች (80% ሴቶች) የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደዞን ተመርቀው ስራ ያላገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሚናው የጎላ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ይህንን በተገቢው ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ምቹ ሁኔታዎች አሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በተገቢው መርተን ውጤታማ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

በመድረኩ የክልሉና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና ፕሮግራሙ የሚተገብርባቸው መዋቅር ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 18/04/2024

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ነው!!

የመደመር ትውልድ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ ግጭትን በውይይት የሚተካ ትውልድ ነው።

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ፤ ጽንፈኝነትን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።

የመተማመን ክበቡ በብሄርና በመንደር ሳይታጠር ኢትዮጵያዊነትን በአርበኝነት መንፈስ የሚያፀና ነው።

በመሆኑም ከራስ ወዳድነት የፀዳ፣ ለሌሎች የሚራራ፣ ሀላፊነት የሚሸከም ፣ እውነተኛና የሌላው ህመም የሚያመው ትውልድ መቅረጽ የጋራ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።

በመደመር ትውልድ ተሠናስለን ተከባብረንና ተባብረን ለጋራ ግብ ቋሚ ተሰላፊ በመሆን ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን።

(ከወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 18/04/2024

የሁምቦ ወረዳ ሣምንታዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

ሁምቦ፦ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን የሁምቦ ወረዳ ሳምንታዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

በመድረኩ ሁሉም የትራንስፎርሜሽን ንቅናቄ አጀንዳዎች፣ የወቅታዊ ተግባራት አፈፃፀም እና የውስጤ ፓርቲ ተግባር አፈጻጸም ግብረ-መልስ በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እና ንቅናቄ አጀንዳ ሴክተር መ/ቤቶች በኩል የተዘጋጀው ሰነድ በጥልቀት ቀርበው ተገመገመ።

መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የሁምቦ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አመኑ ጎአ እንደገለጹት አርሶአደሮችን መሠረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለተሻለ ውጤት ዕለተ ዕለት በመትጋትና ለጋራ ተጠቃምነት ቅድሚያ በመስጠት ምርታማነትን ለመጨመር አመራሩና የዘርፉ ባለሙያዎች በሙያና በክህሎት መደገፍ እንዳለበት ገልጸዋል።

አቶ አመኑ አክለውም በአፈጻጸም የታዪት ውስንነቶች ጊዜ ሳይሰጥ በማረምና በመረባረብ ሁሉም አመራርና የሚመለከታቸው አካላት በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲያቀኑና ተግባራትን የእኔ ነው ብለው ሳይዘናጉ ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ ገለጸዋል ።

በየደረጃው ያለው ባለድርሻ አካላት ውዝፍ የአፈር ማዳበሪ እዳን የማስመለሱን ተግባር በቁርጠኝነት መምራት መስራት እንደሚያስፈልግ የተገለፀ ስሆን አሁናዊ ሁኔታ በመረዳት መምራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ እንደሆነም አስተዳዳሪው አሳሰቡ።

የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ እዳ አመላለስን በተመለከተ ለዘርፉ ውጤታማነት ውስንነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባሩን በዕቅድ በተቀመጠው ልክ ያልተመራ መሆኑን አውቀው በቀሪ ቀናቶች ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ የወጣቱን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ቁመና ላይ መገኘት እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።

የወረዳው ም/አስተዳደር እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደመ በበኩሉ ሁሉም አመራር ተቆጥሮ የተሰጠውን ተልዕኮ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር መሥራት እንዳለበት በግልጽ አስታውቋል።

አቶ ተገኝ አክለውም ሁሉም አመራር የአርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መምራትና መሥራት እንዳለበት ጠቁመው በዘመቻ የተጀመረው ከእርሻ ማሳ ባህር ዛፍ የመንቀል ንቅናቄ፣ ገቢን አሟጦ ማሰባሰብ፣የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ማስመለስ፣ልዩ ልዩ መዋጮ አፈጻጸም፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕዳ ማሰባሰብ፣ የጤና ሞዴልንግ፣የፓርቲ ሥራዎች ጨምሮ ሌሎች ወቅታዊ ተግባራት በአጭር ጊዜ ግብ ተጥለው መመራት እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።

በወቅታዊ ተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአፈጻጸም ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ፈጻሚ አካላት እና ተግባሩን የመሩ ባለድርሻ አካላት በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ የተግባር ማሳኪያ ውል በመግባት ለውጥ ለማምጣት ያሏቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 18/04/2024

በዞናችን አረንጓዴ ወርቅ የሆነውን "የወላይታ ቡናን" ለዓለም ገበያ በጥራትና ብዛት ለማቅረብ እና አርሶአደሩንም ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈብዙ ተግባራት እያከናወንን እንገኛለን። የቡናን ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከሌሎች አከባቢዎች የቡና ምርጥ ዘር በማምጣት የማባዛት ስራም እየተሰራ ይገኛል። በቡናው ልማት ዘርፍ ትልቅ እምርታዊ ለውጦች እየተገኙ በመሆኑ አጠናክረን ለማስቀጠል የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 16/04/2024

40,000/ አርባ ሺህ / ብር ድጋፍ

#ጋልቻ ሁለገብ ኅ/ሥራ ማህበርና ጋልቻ ገጠር ቁ/መ/ኅ/ሥራ ማህበር "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" በሚል የተጀመረው ወረዳዊ ንቅናቄ መድረክ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለማድረግ ቃል የተገባውን #40,000 /አርበ ሺህ /ብር ድጋፍ ገቢ አድርጓል።

ከልብ እናመሰግናለን!!

በዚህም ለነገ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት የትውልድ ባለአደራ የሆናችሁ መላው ህብረተሰብ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!!

CBE 1000617719774

09/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የመተሳሰብ፤ የአንድነት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።ኢድ ሙባረክ!

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፅ/ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ

ኢድ ሙባረክ!
Ciid wanaagsan!
Iid Mubaarak!
Eid Mubarak!

09/04/2024
09/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!፡- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር እንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዝበ መስሊሙ በረመዳን ወር ያዳበራቸውን መልካም ስራዎች ሁሉ ከረመዳን ውጪም የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት ለወገን አለኝታነቱን ማሳዬት ይኖርበታል።

በየጊዜው እና በየወቅቱ የሚገጥሙንን ፈተናዎችን በጥበብ ለመሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም ያስፈልጋል፡፡

በወንድማማችነት ጥላ ስር ተሰባስበን አንድነታችንን ይበልጥ የሚያጠብቁ እና የሚያደምቁ መርሃ-ግብሮችን ሃገራዊ መሠረት እና ይዘት እንዲኖራቸው የበለጠ መስራት የሚይቅበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

በክልላችን የሚትገኙ ውድ የሙስሊም ወገኖቼ፣ ከኢድ በዓል ያገኘናቸውን ዕሴቶች በሁሉም ዘርፎች እንደምንተገብራቸው እተማመናለሁ።

የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ ዒድ አልፈጥር በዓልን እርስ በርስ በመተሳሰብና በመረዳዳት የቆዬ የኢትዮጵያዊነት መገለጫን ዳግም በአደባባይ ማሳዬት ይገባቸዋል ብዬ አምናለሁ።

ከዒድ እስከ ዒድ፣ ሁላችንንም የሚመለከት የህዝብ በዓል፣ የሀገር በዓል ይሆንልናል። የዚህ በዓል በደመቀ ሁኔታ መከበር፣ የሁላችንም ድምቀት፣ የሁላችንም ክብር እንደሆነ ማወቅ ይገባናል።

በድጋሚ፣ እንኳን ለታላቁ የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ዒድ ሙባረክ!

09/04/2024

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ 1445ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

"መላው የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በወላይታ ዞን አስተዳደር ስም እንኳን አደረሳችሁ/እንኳን አብሮ አደረሰን ለማለት እፈልጋለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነትና የአብሮነት ዕሴቶቻችን ጎልተውና ደምቀው የምናከበርበት በዓል እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን ለመግለፅ እወዳለሁ።

ብዝሀነታችንን እንደፀጋ ተጠቅመን ያለ ልዩነት አንዳችን ከሌላችን ጋር የመተጋገዝ ኢትዮጵያዊ ባህላችን አብሮነትንና መቻቻልን የሚያሰፍን አርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን።

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ወር ያሳየው የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመረዳዳትና የመቻቻል ተምሳሌትነት ትምህርት የተወሰደበት ስለሆነ በሌሎች ከነቶችም ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል።

ልዩነቶቻችንን በመቻቻልና በመተሳሰብ ስናስኬድ ውበታችንና አቅማችን በመሆኑ ያለንን የመቻቻልና የመደጋገፍ ዕሴቶቻችን ቀጣይ እንዲሆኑ ትውልድን በጋራ ዕሴቶቻችን ፋይዳዎች ዙሪያ ከቤተሰብ ጀምሮ ተከታታይነት ባለው መንገድ መቅረጽና መገንባት ኃላፊነት በብቃት መወጣት ይገባናል።

በዚህም አጋጣሚ ህዝባችንን ለማስገንዘብ የምፈልገው እንደ ዞናችን የበልግ ዝናብ በሁሉም አካባቢ በተሻለ ሁኔታ እየጣለ ስለሆነ ውሃ በመያዝ እና እርጥበት ተጠቅመን ትርፍ በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሙሉ አቅም ርብርብ ማድረግ ላፍታም መዘንጋት ያለብን ስላልሆነ አንድነታችንን አጠናክረን ሠርቶ መቀየር እንደሚቻል ካሳለፍናቸው ድሎች ተምረን ቃልን በተግባር መርህ ተከትለን የበለጠ በየደረጃው ሁላችንም ተቀናጅተን የመፍጠን እና መፍጠር እሳቤን በመጠቀም መሥራት ተገቢ ይሆናል።

በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች የጀመርናቸው ኢንሸቲቮች ለአብነት የርግብ አተር፣ የእንሰት፣ የካሳቫ እና የሙዝ ልማት ሥራ በውጤታማነት በማልማት ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት አለብን።

በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንንና ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች እገዛችን እንዳይለያቸው አሳስባለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ /እንኳን አብሮ አደረሰን።"

ኢድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ሳሙኤል ፎላ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 09/04/2024

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለ1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በተመለከተ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

"እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ አል ፈጥር በእስልምና እምነት ተከታዮች ልዩ ትርጉም ያለው የቅዱሱ የረመዳን የፆም ወር ማሳረጊያ ታላቅ በዓል ነው፡፡

ዕለቱ ሕዝበ ሙስሊሙ በቅዱሱና በታላቁ የረመዷን ወር ለሀገራችን ሰላምና ፀጋ፤ ለመላው ህዝባችን ፍቅርና አንድነት ወሩን ሙሉ በፆምና በዱአ አሳልፎ ከፈጣሪ እዝነትና በረከት የሚቀበልበት ልዩ ቀን ነው፡፡

የዒድ አል ፈጥር በዓል የመተሳሰብና የመጠያየቅ፤ የመረዳዳትና የአብሮነት በዓል ነው፡፡ በዓሉ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት ሲያደርገው እንደነበረው በአንድነት ተሰባስቦ ያለው ለለሌው በማካፈል ማህበራዊ ትስስሩን ይበልጥ አጠንክሮ በአብሮነት የሚያከብረው በዓል ነው።

አንድነትና ኅብረት፤ መደጋገፍና መረዳዳት በእስልምና ልዩ ስፍራ እንደሚሰጠው የእምነቱ አስተምህሮ ያስረዳል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን የበርካታ ዕሴቶች ባለቤት የሆንን ህዝቦች ብቻ ሳንሆን ልዩነቶቻችን የኅብር ማንነትን ውበት ያጎናፀፉን ድንቅ ህዝቦች ነን፡፡

በአሁኑ ወቅት በኅብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት አንድነታችንን አጽንተን የዘመናት ጠላታችን የሆነው ድህነትና ኋላ ቀርነት ታርክ የማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡

ይህ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረታችንን እና መደጋገፋችንን የሚፈልግ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙም የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘውና በሚፈቅደው መሰረት በመተጋገዝና አብሮ በመስራት ለጋራ ቤታችን ዘላቂ ሰላም፤ ዕድገት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ይበልጥ መትጋት ይገባዋል።

በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር ለዘመናት የገነባነውን የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበር እና የመደጋገፍ እሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዟችንን ከዳር ለማድረስ በየተሰማራንበት ዘርፍ ሀገራችንን በሐቀኝነት በማገልገል የድርሻችንን እየተወጣን እንዲሆን ስል አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።"

ዒድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ሀገራችንን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

09/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፦ አቶ አሳምነው አይዛ
ኢድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታ ሲል የሰጠውን የዒድ በዓል መላው ሕዝበ ሙስሊም በሐሴት የሚከበሩበት ለታላቁ የኢድ- አልፈጥር በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ኢድ አልፈጥር በዓል ሕዝበ ሙስሊሙ ወሩን ሙሉ በጾምና በስግደት፣ እንዲሁም በመልካም ተግባራት አሳልፎ ከፈጣሪ የመጨረሻውን ምንዳ የሚቀበልበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ ያሉትን መልካም ነገሮች ይዞ እርስ በእርሱ እየተጠያየቀ፣ አብሮነቱንና አንድነቱን የሚያሳይበት፣ ያለው ከሌለው የሚረዳዳበት፣ ያገኘው ካላገኘው ምግብና ፍቅርን ተጋርቶ የሚያሳልፍበት ዕለት ነው። እነዚህ እሴቶችና የበዓሉ ትሩፋቶች ከእምነቱ ተከታዮች ባለፈ ለሌሎችም መትረፍ የሚችሉ ናቸው።

በእስልምና ዕምነት ፆም ምዕመኑን ትዕግሥት፣ ትህትና እና መንፈሣዊ ትምህርት ይሰጠዋል ተብሎ ይታመናል። ረመዳን ለ"አላህ" ሲባል የሚፆም ፆም እንደሆነና ሙስሊሙ ምዕመን ለሠራው ኃጢያት ምህረትን የሚጠይቅበት፣ ዕለት ተዕለት ለሚሠራቸው ኃጢያቱና ከሠይጣን ፈጣሪው ይጠብቀው ዘንድ የሚፀልይበት እንዲሁም የዕምነቱ ተከታዮች ራሳቸውን ከኃጢያት የሚያነፁበት ወቅት መሆኑን የእምነቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ።

ሕዝበ ሙስሊሙ “በረመዳን የሰራናቸውን መልካም ተግባራት ሁሉ ከበዓሉ በኋላም ከማሕበራዊ ሕይወታችን ጋር ተቀናጅተውና ኢስላማዊ ስብእናን አድምቀው ማሳየት ይገባቸዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በርስ በመተሳሰብ ምስኪኖች በዒድ ዕለት ከመለመን እንዲዱኑና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ለዚህም ነው ነብዩ ሙሃመድ "አንተ የምትወደውን ለሌላው ወንድምህ እስካልወደድክለት ድረስ በትክክል አላመንክም" ሲሉ ያስተማሩት።

በተሰማራንበት መስክ ወደኋላ የሚጎትቱ እንቅፋቶችን በወንድማማችነት እሴት አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለን ፈተናዎችን በፅናት መሻገር ያስፈልጋል፡፡ ብሩህ ተስፋ እና አዲስ ዘመን ከፊታችን አለ! ስለዚህ አንዳችን ለሌላችን ድርና ማግ፤ ዋልታና ማገር ሆነን ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም አለብን፡፡

በዞናችን የሚትገኙ ውድ የሙስሊም ወንድምና እህቶቼ፣ በተቀደሰው የረመዳኑ ወር ለሀገራችሁ ብሎም ለአከባቢያችን ጸጋና በረከት፣ ሰላምና ፍቅር እንደ ጾማችሁና እንደ ጸለያችሁ ሁሉ፥ በክብረ በዓሉም፣ ከዚያ ወዲያ ባሉት ቀናትም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ዱዐ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በትሕትና እጠይቃለሁ።

በዚህ ጊዜ ክፋትን አርቀን መልካምነትን፣ ጠብና ጥላቻን ንቀን በምትኩ እርቅና እዝነትን በሀገራችን ብናነግሥ ምድራዊ ረድኤቶች ብቻ ሳይሆን ሰማያዊ ምንዳዎች በዝተው እንደሚጠብቁን አልጠራጠርም።

ሰሞኑን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ወደ ልህቀት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰቢያ ህዝቡ እያሳየ ያለው ድጋፍና አጋርነት እጅግ የሚመሰገን በመሆኑ በሌሎች ልማት ዘርፎችን ከተባበረንና ከተጋገዝን ከሰራን ታሪክ መስራት እንደሚቻል አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ዘላቂ ሠላም ሲናስብ ልማት፣ ዕድገት፣ ለውጥ፣ ብልፅግና እና ዴሞክራሲ ግንባታ ማሰብ ነዉና ሠላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክት በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የተስፋና የበረከት ዒድ እንዲሆን እመኛለሁ።

ዒድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

አሳምነው አይዛ

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 07/04/2024

የሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤፌሶን በለጤ የምሁራን መፍለቂያ የሆነውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የድጋፍ ጥሪን በመቀበል 500/ አምስት መቶ ብር/ ድጋፍ አድርጓል።

እናመሰግናለን!!

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 07/04/2024

የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የወልማ ቦርድ ም/ሰብሳቢ አቶ አሳምነዉ አይዛ ለሊቃ ድጋፍ የልጆቼን ድርሻ በማለት 3,000 ብር አበርክተዋል በጣም እናመሰግናለን
Asaminew Ayza Ushacho ✍️💪💪💪💪

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 07/04/2024

የቀድሞ የጠበላ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ከንቲባ እና የአሁኑ የወላይታ ዞን ሕብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ Getachew Gebu "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ቃል ከ1ኛ-6ኛ ክፍል መጽሐፍት ህትመት ለማድረግ የቀረበውን የድጋፍ ጥሪውን በመቀበል 2,000/ ሁለት ሺህ/ ድጋፍ አድርጓል።

ከልብ እናመሰግናለን!!

በዚህም ለነገ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት የትውልድ ባለአደራ የሆናችሁ መላው ህብረተሰብ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፣

CBE 1000617719774

06/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረቡ

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልላቸ‍እን በሁሉም አከባቢዎች ከለውጡ በኃላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል በተካሄደው ህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ለክልሉ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ምድራዊ ሃይል ሊያስቆመው የማይችለውን የለውጥ ጉዞ ገብቷችሁ ድጋፋችሁንና ደስታችሁን ለገለፃችሁ በሙሉ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

በህዝባችን የለውጥ መሻት የተጀመረው ጉዞ ብልፅግና ፓርቲን ወልዶ፣የዴሞክራሲ ባህላችንን አሻሽሎ፣ኢትዮጵያን ከብተና ስጋት ታድጎ፣በግብርና፣በኢንዱስትሪው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሊታዩ የሚችሉ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቦ እነሆ መገስገሱን ቀጥሏል ነው ያሉት።

እንደሀገር ባለፋት ስድስት ዓመታት የተገኙ ውጤቶች የጋራ ስኬቶችና ድሎች ናቸው ያሉት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን አጠናክረን ለማስቀጠል ህብረብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር እና ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ክልላችን የሠላም፣ የብልፅግና እና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ አቅደን እየሰራን ባለው ሂደት የህዝባችን ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል።

የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙና ወደ ፊትም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአብሮነትና በወንድማማችነት ለመሻገር ሁላችንም ከችግር በላይ ሆነን በተሰማራንበት መስክ ቁርጠኛ ሆነን መስራት ይጠብቅብናል ብለዋል።

በለውጡ ጥቅማቸው የሚነካባቸው ግለኛና ስግብግብ አደናቃፊ ሃይሎች እዚህም እዚያም የሚፈጥሩትን ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በማውገዝ ህዝባችን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የማጋለጥና ዕድል እንዳይኖራቸው የማድረግ ሚና በላቀ ደረጃ በቀጣይነት ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት።

በመጨረሻም ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 06/04/2024

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ስድስት የመሪነት ዓመታት የተገኙ ድሎችን ዕውቅና የሚሰጥና የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ወላይታ ሶዶ፣ መጋቢት 28/2016 (ወዞመኮጉመምሪያ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ዓለማየሁ ባውዲ በድጋፍ ሰልፉ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ስድስት የለውጡ ዓመታት በርካታ ዓለም የመሰከረላቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

የተለየ የፖለቲካ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች ከሚሰደዱበት ሁኔታ አልፈን በጠረጴዛ ዙሪያ በመመካከር የሚፈቱበት የውይይት ባህል መፈጠሩን ተናግረዋል

ለክልል ብሎም ለአገር ዕዳ የነበረው የክልሎች የአደረጃጀት ጥያቄ የተመለሰበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል

ዜጎች በነባር የሀገር በቀል ዕውቀት ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት እንዲሁ የጋራ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ የምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል።

ከለውጡ ጊዜ በፊት አገራችን ከመፍረስ ድና በአገር በቀል የልማት መንገዶች መሠረታዊ የልማት ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በዚህም በስንዴ ልማት በሌማት ትሩፋትና በሌሎች ዘርፎችም በርካታ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ተመዝግበዋል ብለዋል።

ዛሬ የሚደረገዉ የድጋፍ ሰልፍ በብልጽግና ጉዞአችን የተመዘገቡ ድሎች ይበልጥ እንዲጎለብቱና ያለምነው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ለማጽናት ነው ብለዋል።

ሀገራዊ አንድነታችንን ለማፍረስ የሚጥሩ ፅንፈኛ ኃይሎችን በመታገል ለልማት በጋራ መቆም ይገባናል ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ በጋራ እንደቆሙ ሁሉ ድህነትን ለማሸነፍ በአርበኝነት ስሜት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 06/04/2024

የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች "አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" የተጀመረው ንቅናቄ እያንዳንዳቸው 5000ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

"አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ገቢ ማሳሰቢያ ንቅናቄ አሁን ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገንና የመጽሐፍ እጥረት ለመቅረፍ ወሳኝ ነው።

ድጋፉ ለልጆቻችን፣ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ስለሆነ ሁሉም የበኩሉን አሻራ ማበርከት ያስፈልጋል።

ለመጽሐፍ አቅርቦቱ የሚሆን ገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አካውንት በየመዋቅሩ በጣምራ ተከፍቶ ሀብት የማሰባሰብ ስራው በሁሉም አከባቢዎች ተጀምሯል።

አሁን የወደቀውን የትምህርት ስርዓትን መልሶ ለማንሰራራት ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ በማበርከት የትውልድ አደራውን መወጣት ያስፈልጋል።

በዚህም መላው የወላይታ ህዝብ፣ የመንግስትና ሀይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ትምርህት ቤቶችና ጤና ተቋማት፣ ዕድሮች እና ሌሎች የመንግስት አመራሮችና ሠራተኞች የበኩላቸውን ዐሻራ ሊያበረክቱ ይገባል።

ዞናዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
👉1000617379191

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 06/04/2024
Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 14/11/2023

በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የሌማት ቱሩፋት ስራዎች እየቀጠሉ ይገኛሉ።

እንቁላልን ከቅንጦት ምግብነት ወደ መደበኛ የመሶብ(የሌማት) ምግባችን አካል እንዲሆን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በሁምቦ ወረዳ በኮይሻ አጎዳማ ቀበሌ በወረዳው የተጀመራዉ ሌማት ትሩፋት አንዱ ዘርፍ የሆነውን የዶሮ መንደር ውጤታማ ለማድረግ ሥራ አጥ ወጣቶችን በማህበር ተደራጅተው በዶሮ እርባታ መስክ በ1 ቀን ጫጩት የተመዘገበው ውጤት በፎቶ

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 13/11/2023

"አመራሩ ተግባራትን ከተግዳሮትና ችግር በላይ ሆኖ በማሳካት ውጤት ማስመዝገብ አለበት::" ሲሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ገለጹ

የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ከወረዳና ከተማ አመራሮች ጋር በጋራ የቡና ግብይትና የመስኖ ተግባራት አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግሞ ለመዋቅሮች ግብረ መልስ ሰጥቷል።

በቡና ግብይት ላይ ግብረ ኃይሉ ጠንካራ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ተግባር ሊከናወን ይገባል ሲሉም የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ጠቁመዋል።

በመስኖ ሥራ ቶሎ በሚደርሱ ገበያ ተኮር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ርብርብ ሊደረግባቸው ይገባልም ብለዋል።

የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄውን ለመመለስ ተግባራት በአመራር ቁጭት መመራት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ አሳምነው አክለው ካሉብን የአፈጻጸም ችግሮች ፈጥነን በመውጣት ውጤት ለማስመዝገብ ተግባራት በትግል ሊመሩ ይገባል ሲሉም አንስተዋል።

ከቡና ግብይትና ቁጥጥር አንጻር የግብረ ኃይል ውይይት አናሳ መሆን፣መድረኩን ከቀበሌ ጀምሮ መግባባት እየፈጠሩ አለመምራት፣ ቅንጅታዊ አሠራር ጉድለት፣ የቡና ምርት የአያያዝ ጥራት ችግር፣ ነጋዴ እና ማህበራትን አቀናጅቶ ያለመምራት፣ ለህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ኬላ አለማቋቋም የመሳሰሉት በጉድለት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው።

ህገ ወጥ የቡና ዝውውር እና ግብይት ለመከላከል በተሠራው ሥራ ባለፉት ሶስት ወራት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ መረጃ አመላክቷል።

ዎላይታ ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6

በማንኛዉም ሰዓት ጥቆማና አሰተያየት ለመስጠት

የስልክ መስመራችን ክፍት ናቸው ይደውሉ
ስልክ - 0461809999
0461801609
0964647777
በተጨማሪም ይህንን የፌስቡክ ገጻችንን Follow, Share, Like, በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

ትጋትና ታማኝነት ለብልፅግና !

Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 12/11/2023
Photos from Humbo Woreda Cooprative office = ሁምቦ ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት's post 04/11/2023

መላው የሁምቦ ወረዳ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፣ ደስ አለን!!!

ሁምቦ ወረዳ በ2015 ዓ.ም ክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሰራው ጠንካራ ሥራ በወላይታ ዞን ደረጃ 1ኛ በመሆን ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ሁምቦ ወረዳ አንደኛ በመሆን ዋንጫውን የተቀበለው በዛሬው ዕለት በዞን ደረጃ የ2015 ዓ.ም ክረምት ወራት ማጠቃላያና የ2016 ዓ.ም የበጋ ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመርያ መርሃግብር ላይ ነው።

ሁምቦ ወረዳ በ2015 ዓ.ም ክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንደኛ መሆኑን ተከትለው የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፀጋየ ቀልታ መላው የሁምቦ ወረዳ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አጠቃላይ በበጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ የየራሳቸውን አሻራ ያሳረፉትንና ለበርካታ ማህበረሰብ ክፍል እፎይታ የሰጡት አካላትን አመስግነዋል። በገንዘብ የማይተካውን ደም በመለገስ፣ ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ያበረከቱ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ጨምሮ በሁሉም ዘርፍ በነቂስ የተሳተፉትንም አመስግነዋል።

በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍተኛ የህሊና እርካታ የሚሰጥና ከፈጣሪ ዘንድም ትልቅ ዋጋ ያለው ተግባር በመሆኑ በክረምት ወራት ብቻ ሳይሆን በበጋም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና እንዲሁም በወረዳችን ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ሁሉም የወረዳው ህዝብ የየራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

አንድ ሆነን ለአንድ አለማ በጋራ ተሰለፈን ከሰራን የማናመጣው ለውጥ የለም ያሉት አቶ ፀጋዬ በቀጣይ በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣትና ህብረተሰባችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደትላንቱ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ ጠንክረን መስራት ይጠበቃል ስሉ አሳሰቡ።

የሁምቦ ወረዳ ዋና የመንግሥት ተጠሪና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰብሳቢ አቶ አመኑ ጎአ ወረዳው በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንደኛ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አቶ አመኑ አክለውም በክረምት ወራት በወረዳው ሁሉም አከባቢዎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ትኩረት መስኮች በርካታ ሥራዎች መሰራቱን ገልጸዋል።

በቀጣይ በሁሉም ዘርፎች የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት መረባረብ አለብን ስሉ አሳሰቡ።

በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሳተፉትን ባለድርሻ አመስግነው፣ በ2015 ዓ.ም በበጋ ወራትም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ፣ ደስ አለን!!!

Website