Geze prosperity

Geze prosperity

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Geze prosperity, Health/Beauty, .

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 27/02/2024
16/02/2024
11/01/2024

መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው።

መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው፤ ቁስሎች እንዲጠገኑ፣ ሕመሞች እንዲድኑ፣ ችግሮች እንዲፈቱ፣ ፈተናዎች እንዲታለፉ፣ ያለፈውን ጉዟችንን መመልከቻና የቀጣይ ጉዟችን ጠቋሚ፤ አዲስ የእሳቤ ማዕቀፍ ነው፡፡

ከመደመር ትውልድ መጽሀፍ ገጽ v የተወሰደ

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 11/01/2024
11/01/2024

ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ

እኛ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጥር 01፣ ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የተገኘን የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄድነው ስብሰባ :

1ኛ በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን " መግባቢያ ሰነድ" በተመለከተ የስምምነቱን ማዕቀፍ ፣ዝርዝር ይዘቱን እና ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ባሉት እድሎችና ስጋቶች ላይ በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ስምምነቱን ያለልዩነት የምንደግፍ መሆናችንን አረጋግጠናል::ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር መክረን ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናችንን ለመወጣት ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን:: መንግስት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህብረተሰባችን የበኩላቸውን አውንታዊ ሚና እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::

2ኛ. አካታች ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ ስራው የደረሰበትን ደረጃ ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በመፍትሄ አቅጣጫወች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናን አስመልክቶ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በቀረበው ሪፓርትና ማብራሪያ ላይ ውይይት ካደረግን በኋላ ለምክክሩ ውጤታማነት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል:: በሂደቱ ሁሉም የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሳተፉም ጥሪያችንን እናቀርባለን:: ለምክክር ኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬት እንቅፋት እየሆነ ያለውን የሰላምና የጸጥታ ችግር በመቅረፍ መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህዝባችን እንዲረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን::

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ጥር 02 ፣ 2016 ዓ/ም

03/01/2024

ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ!

ኢትዮጵያዊያን እንደ ድር ተጋምደን ያስመዘገብናቸው በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉን አንፀባራቂ ታሪኮች አሉን።

ለአፍሪካውያን እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት፣ የእኩልነትና የአትንኩኝ ባይነት አብነት የሆነው የአድዋ ድል የብሔር፣ የሀይማኖት እና መሰል ልዩነቶች ሳይገድቧቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራቸውን ያሳረፉበት የወል ታሪካችን ነው።

አባት እናቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በጋራ ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ ሰርተዋል፤ የጋራ ታሪካችንን በአብሮነት ለመዘከር ግን በረባ ባልረባው ስንነታረክ ቆይተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቧራ ተነስንሶበት የነበረው የአድዋ ድል ታሪክ ተገልጦ ወርቅነቱ እንዲታይ ለማድረግና በዓመት አንድ ጊዜ ከመዘከር ባለፈ ዓመቱን ሙሉ እንዲወሳ የሚያደርገውን ግዙፉን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሲገነባ ቆይቷል።

ሙዚየሙ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ድል ታሪክ በአብሮነት እንዲዘክር የሚያስችል ቦታ ላይ ያረፈ ከመሆኑም በላይ ታሪኩን በተሟላ መልኩ እንዲዘክር ተደርጎ የተሰራ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ አገራዊ ፕሮጀክት ነው።

የአድዋን የድል ታሪክ ከአርበኞችና ከመሪዎች ነጥሎ ማየት ስለማይቻል በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም በተገቢው መልኩ የሚዘከሩበት ዕድል ተፈጥሯል።

የአድዋን ድል ስናነሳ የፈረሶቻችን ውለታ ባናወሳ የአድዋ ተራሮችም ጭምር ይታዘቡናል። በመሆኑም በሙዚየሙ የፈረሶቻችንን አሻራ የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችም ተካተዋል።

የአርበኞቻችንን ድል ከፍ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዘመናዊ ጦር ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ሀይል ጦር፣ ጋሻ፣ እና ጎራዴን በመሳሰሉ መሳሪያዎች በልበ ሙሉነት ገጥመው ድል ማድረጋቸው ነው።

በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየምም የመሰባሰቢያ አዋጁ የተጎሰመበትን ታሪካዊ ነጋሪት ጨምሮ ጋሻ እና ጦራችን በሚገባ እንዲዘከሩ ሆኗል።

የአርበኞቻችንን መውጣትና መውረድ ለማሳየት በአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች አምሳል የተገነባው የአድዋ ሙዜም ባረፉበት የጥበብ አሻራዎች ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ ነው!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

02/01/2024

ቅንነትንና ብቃትን የተላበሰ አገልግሎት ለህዝባችን ተጠቃሚነት!

የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በአገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ቢሆንም ዘመኑን በሚመጥን መልኩ ባለመዘመኑ የችግር ፈችነት ሳይሆን የችግር ፈጣሪነት ምስል ሸፍኖት ቆይቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ተገልጋዩ ጊዜውን፣ ሀብቱን እና ጉልበቱን ሳያባክን ጉዳዩን አስፈፅሞ እሱም በተራው ወደ ተሰማራበት የስራ መስክ በፍጥነት ለመመለስ ሲያስብ በህሊናው የሚደቀነው እንደ ራስዳሽን ተራራ መውጣት እና እንደ ዳሉል ዝቅተኛ ቦታዎች መውረድ የሚጠይቀው፣ መሰናክሎች የበዙበት፣ ጠመዝማዛው የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ነው።

በመንግስት ተቋማት የሚስተዋለው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በአገራችን ከሚስተዋሉ ስር የሰደዱ ችግሮች ዋናው መሆኑን በመረዳት በፓርቲያችን የሚመራው የለውጡ መንግስት ሁሉም ተቋማት ምቹ የስራ አካባቢ እንዲፈጥሩ ማድረግን ጨምሮ በርካታ አበረታች እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን አርአያነት ተከትሎ ከንቲባ ፅ/ቤትን ጨምሮ ሁሉም ተቋማት ቢሯቸውን በማደስና በማስዋብ እንዲሁም አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላት ለሰራተኞቻቸው እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ምቹ አካባቢን እንዲፈጥሩ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፤ በዚህም አንዳንድ ተቋማት ለከተማችን ውበትም ተጨማሪ ድምቀት እስከመሆን ደርሰዋል።

ተቋማት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ህጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እና አሰራሮችን በመፈተሽ አሳሪዎችን አሰሪ በማድረግ ወደ ፊት መራመድ ጀምረዋል።

ተገልጋዩ ብሔሩ፣ ሀይማኖቱ፣ ፆታው፣ የፖለቲካ አመለካከቱ፣ የስጋ ዝምድናው እና መሰል አግላይ አስተሳሰቦች ግምት ውስጥ ሳይገቡ ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት ህገ-መንግስታዊ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አሉት።

"ደንበኛ ንጉስ ነው" የሚለው ድንቅ አባባል የተወሰኑ ተቋሞችን ተገልጋይ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተገልጋዮች የሚወክል ነው። በሁሉም ተቋሞች የሚገኝ ሁሉም አመራር እና ባለሙያ የህዝብ አገልጋይ መሆኑ ላይ የጠራ አቋም ሊኖረው ይገባል። ግለሰቦች ብቻም ሳይሆኑ ፓርቲያችን ብልፅግናም አምስት ዓመታት ህዝባችንን ለማገልገል ከህዝባችን ይሁንታን ያገኘ የህዝብ አገልጋይ ፓርቲ ነው።

ፓርቲያችን ብልፅግና ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች ሲቪል ሰርቪስ እንዲገነባ አቅጣጫዎችን ቀይሶ ተግባራዊነታቸውን በልዩ ትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።

አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የህዝባችንን መጉላላት ለማስቀረት፣ የጊዜ፣ የጉልበት እና የሀብት ብክነትንም ለመቅረፍ በከተማችን የሚገኙ ተቋማት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፈጣን መሻሻል እያሳየ መሆኑን የጤና እና የመሬት ተቋማት እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

አመራሩም ሰራተኛውም በቅንነትና በቅንጅት በተረባረበባቸው ዘርፎች አመርቂ ውጤቶች መመዝገብ መጀመራቸውን ህዝባችን ይመሰክራል፤ ዓለም አቀፍ እውቅናዎችም ተችረውናል።

ሰሞኑን በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረው የሲቪል ሰርቫንቱ ምዘናም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት አሰጣጥ ለመፍጠር የተጀመረውን ጥረት ማጠናከር፣ በዘርፉ የሚስተዋለውን በአንድ በኩል የሰው ሀይል እጥረት በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ሀይል ብክነትን በማስተካከል በሁሉም መስክ ፍትሀዊነትን ለማስፈንና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዓላማው ያደረገ መሆኑን ልብ ይሏል።

ቅንነትን በመላበስ፣ እውቀትና ክህሎታቸውን በማሳደግ ግለሰቦች አገልግሎት አሰጣጡ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የማይተካ ሚና ቢኖራቸውም የማይዋዥቅ አገልግሎት አሰጣጥ ለመስጠት፣ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ጉድለቶችንም በዘላቂነት ለማረም ቁልፉ ተቋም ግንባታ መሆኑን ማስመር ይገባል።

ታታሪዎች የሚበረታቱበትና የሚበራከቱበት፣ ደካሞች ደግሞ የሚደገፉበት፣ አጥፊዎችም የሚታረሙበት ግልፀኝነት ያለው አሰራርና ስርዓት በመዘርጋት ቅንጅታዊ ርብርብ የማድረጉ ጉዳይም ልዩ ትኩረት ይፈልጋል።

ብቃትንና ውጤታማነትን ከብዝሀነትና አካታችነት ጋር በማጣጣም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የህዝባችንን እርካታ ለማሳደግ ለተጀመረው ሪፎርም ስኬታማነት እንረባረብ!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

02/01/2024

ታሪክን መስማት ብቻ ሳይሆን ታሪክን በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና የምናፀና የመደመር ትውልዶች ነን።

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ነባርና ገነና ስሟን በማደስ ዘመኑን የዋጀ ከፍታና ሀገራዊ የታላቅነት ምዕራፍ ላይ ለማድረስ ታሪካዊ የሆኑ አሻራዎችን በማስቀመጥ በወጥነት እየሰራ ይገኛል፡፡ ፓርቲው ፈተናዎችን ተሻግሮ የኢትዮጵያን የታሪክ ስብራት በማረም ዘላቂነት ባለው መሰረት ወደፊት እንድትራመድ ለማድረግ በትጋት እየሰራ ታላላቅ አስደማሚ ዕምርታዎችን ማስመዝገብ ችሏል።

ብልጽግና ከነበሩብን የታሪክ ዕዳዎች ተላቀን የኢትዮጵያን አኩሪና ነባር ታሪካዊ ዕድሎች በመጠቀም ያሉንን በጎ አጋጣሚና ሁኔታ ያገናዘበ ዘመኑንን የዋጀ ውሳኔና ተግባራትን በመፈጸም የሀገሪቷን ከፍታ ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ስንተባበር በተለያዩ አጋጣሚዎች ያባከናቸውንና ያጣናቸውን ዕድሎች በማረምና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ፀንተን በመቆም ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ብልፅግናችንን ማረጋገጥ እንደምንችል በምንከውናቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ዓለም ዓቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን አመላካች ናቸው።

ፓርቲያችን ኢትዮጵያ ሙሉ ትኩረቷን ወደ ትብብርና ልማት በማዞር
በፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ እየገነባች አፍሪካውያን ችግሮቻችንን በውይይትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የፀና ይሆን ዘንድ በተግባር እየሰራ ነው። ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ በወደብና ባህር አጠቃቀም ቀጠናውን በልማት የሚያስተሳሰር አፍሪካዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በማዳበር አብሮ ለማደግ የሚያስችል ይሆን ዘንድ አቋም ይዞ እየሰራ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የወደብ አጠቃቀምና ባለቤትነት የፓርቲያችንን የልማት አርበኝነትና የዲፕሎማሲ አቅም ውጤት የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያውያን ዕዳዎችን ወደ ምንዳ በመቀየር አዳዲስ ታሪክ በመጻፍ መጭው ትውልድ ሲዘከረው የሚኖር ደማቅ አሻራዎችን በማሳረፍ የኢትዮጵያን ብልጽግና ዕውን እናደርጋለን።

የሀገራችን ሙሉ አቅምና ብልፅግናዋ ሊረጋገጥ የሚችለው ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ አሻራዎችን በማሳረፍ ዘላቂ ሰላምና ሀብትን መፍጠር የሚችል ሁኔታ ሲፈጠር ብቻ ነው። በመሆኑም ታሪካዊ ስብራቶችን በጥበብ እና በማስተዋል በቆራጥነት እየጠገንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ዕውን በማድረግ አዳዲስ አኩሪ ታሪኮችን ሰርቶ ለትዉልድ ማሻገር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊያን ነባር አኩሪ ታሪኮቻችንን ጠብቀን ጉድለቶችን በማረም ለትውልድ የምትመች የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደረጋለን!

Videos (show all)

Website