Haile dechasa

Haile dechasa

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Haile dechasa, Health/Beauty, .

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 23/03/2024
23/03/2024

ቃልን በተግባር የሚፈፅም ፓርቲ ብልፅግና !!!

ፓርቲያችን ብልፅግና በ6ተኛው ሀገራዊና ከተማዊ ምርጫ ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት ባለፉት ሁለት ዓመት ከግማሽ በዴሞክራሲ ግንባታ፤ ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የጋራ ብልፅግናን በሚያረጋግጥ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት በመከተል በርካታ ዉጤቶችን ማስመዘብ ችሏል፡፡

በተለይም በግብርና፤ በአምራች ኢንዱስትሪ፤ በማዕድን፤ በቱረዝም ዘርፎች፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፤ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፤ የህዝባችንን ፍላጎት የሚያሟላ ፍትሃዊ የማህበራዊ አገልግሎት ከማቅርብ አንጻር በርካታ ዉጤቶችን አስመዝግቧል፡፡

በከተማችንም በምርጫ ወቅት ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የተጀመረው ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ለማሳካት በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊና በዉጭ ግንኙነት ሥራዎች ላይ ተጨባጭ ዉጤቶች ባለፉት ሁለት ዓመት ከግማሽ ማስመዘገብ ተችሏል፡፡

በባለፉት ዓመታት በርካታ ፊተናዎች የገጠሙን ቢሆንም ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር የላቀ ዕድገት በማስመዝገብ እንደ ከተማ የያዝነው የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ ራዕያችንን ዕውን ለማድረግ ስኬታማ ተግባራት ማከናወን ተችሏል፡፡

21/03/2024

"ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና"

ብልፅግና ፓርቲ ህብረ- ብሔራዊነት በማጽናት የበለፀገችና የግዛት አንድነቷ የተከበረ ሀገርን ለመገንባት በፅናት እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ይሁንታ አግኝቶ መንግስት ከመሰረተ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታ በመትጋት በርካታና ተጨባጭ የሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎችን ማስመዝገብ ተችሏል። በተለይም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስብራቶች በሚቀይር መልኩ በወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ የተመሰረተ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር አካታችና አሳታፊ የሆነ ሁሉን ዓቀፍ የፖለቲካ ስርዓትን ዕውን አድርጓል።

ከኢኮኖሚያዊ ሪፎርም አንፃርም ፓርቲያችን ብልፅግና በዘረጋው ሰው ተኮር ተግባር ማህበረሰቡን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በታሰበላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ሰፊ ዕምርታን አስመዝግቧል። በተለይም ያሉንን ፀጋዎች በመለየትና በአግባቡ በማስተዳደር ከዕዳ ወደ ምንዳ የሚደረገው ሽግግር የኢትዮጵያን አይቀሬ ብልፅግና እርግጠኝነት አመላካች ናቸው።

በዚህም በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን በስኬት በመፈጸም የማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል። ፓርቲያችን እያስመዘገባቸው የሚገኙትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድሎች አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ የምርጫ ጊዜ ለህዝብ የገባቸውን ተግባራት በቁርጠኝነት ለመተግበር ከመላው አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ከሰላም ዕሴት ግንባታ ጋር ተያይዞም ምንም እንኳን በፀረ ሰላም ሀይሎች የጽንፈኝነት አስተሳሰብ ተግዳሮቶች የነበሩ ቢሆንም ከመላው የፓርቲው አባላትና ደጋፊ ጋር በመቀናጀት ህዝባችንን በማስተባበር የኢትዮጵያን ሰላምና ብልጽግና ለማስቀጠል የተጀመሩ ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠል በኮንፈረሱ ላይ አረጋግጧል።

እየተደረገ ባለው የመላው አባላችን ኮንፈረንስ ላይ የተጀመሩ የልማት ኢንሸቲቮችን በማጠናከር በተለይም በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ ስንዴና እንሰሳት እርባታ ስራዎችን እናስቀጥላለን። የፓርቲያችንን ህዝባዊ ቅቡልነት በማጽናት ጉድለቶችን እያረምን ቀሪ ተግባራት በትኩረት በመፈጸም የስራ ዕድልና የልማት ስራዎችን በማስቀጠል በብሔራዊ ገዥ ትርክት አንድነታችንን እያፀናን ህብረብሔራዊ የመደመር ጉዟችን እንደሚቀጥል ማረጋገጥ ተችሏል።

በአጠቃላይ በከተማችን እየተካሄደ በሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረስ ፓርቲያችን የጀመረው የሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ በማስቀጠል ህዝብ የሰጠውን አደራ በብቃት ለመፈጸም ቃልን ማደስ የተቻለበት አውድ ተፈጥሯል። የህዝብን ድምጽ በማክበር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍታትና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የጽንፈኝነት አስተሳሰብን በመታገል የሰላም ዕሴቶቻችንን ጠብቀን ከነጠላ ዕውነት ወደ ወል ዕውነት በመሻገር ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በመትከል ሀብቶቻችንን በአግባቡ በመጠቀምና በማስተዳደር ከዕዳ ወደ ምንዳ የሚደረገውን ብልፅግናዊ ጉዞ ለመፈጸም ቃልን ያደሰበት ሆኗል።

20/03/2024

የብሄራዊነት ትርክት ለኅብረ-ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት መሰረት ነው፡፡

ኅብረ-ብሔራዊ ፌደራል ሥርዓት 'በብሄራዊነት ቅኝትና በአርበኝነት ስሪት 'የጸናች፣ ብዝሀነትን በአግባቡ ማስተናገድ የምትችል ኢትዮጵያን መገንባት መቻል ነው። ብሄራዊነት አካታችነት ነው። በተናጠልና በወል ማንነቶችና መብቶች መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ በትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አንድነት መገንባት ነው፡፡

ከእነዚህ ነባራዊ እውነታዎች ተነስተን ካየን ኅብረ-ብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት የሀገረ-መንግስታችን ስር የሰደዱ ፈተናዎችን በመፍታት በብዝሃ-ማንነትና የግለሰቦች መብት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ የሀገረ-መንግስቱን ቁልፍ መሰረታዊ ክፍተቶች በመሙላት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲተከል ያግዛል፡፡

ያለን አንድ ሀገር ብቻ ናት፡፡ የሀገራችንን የግዛት አንድነት በማጽናት ኅብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የሁልጊዜ ግባችን መሆን ይኖርበታል፡፡

18/03/2024
18/03/2024
14/03/2024

"ለነገዋ..."

ዛሬ ምሽት ይጠብቁን!

14/03/2024

ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ህብረ- ብሔራዊ አንድነት ማጽናት !

የብልፅግና ፓርቲ የነደፋቸው የፖለቲካ ተልኮና ዓላማዎች ይሳኩ ዘንድ በትኩረት ከሚሰራባቸው ነገሮች አንዱና ዋናው የሀገራዊ መግባባት ጉዳይ ነው። ፓርቲው ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር፣ ለዴሞክራሲ ስርዓት ማበብና አጠቃላይ ሀገራዊ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት ይመጣ ዘንድ ከተቃርኖ ትርክት በመላቀቅ ገዥ ብሔራዊ ትርክትን በማጽናት ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በጽኑ እየሰራ ይገኛል።

የብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ ለረጅም ዓመታት የገነገነ በልሂቃን መካከል የሚታይ ዋልታ-ረገጥ የጠቅላይነትና ተገጣይነት ጤናማ ያልሆነ ትርክት በህዝቦች መካከል አለመተማመንን እየፈጠረ መሆኑን ይገነዘባል። በብልጽግና ፓርቲ ዕምነት የሃሳብ ልዩነቶችም ሆኑ የጥቅምና የፍላጎት አለመጣጣሞች ተፈጥሯዊ በመሆናቸው ልዩነቶችን ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ማስተናገድ ጠቃሚና ገንቢ ናቸው። ፓርቲያችን ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ በሀገራችን የቂምና የጥላቻ ታሪክ ምዕራፍ እንዲዘጋና በብሔራዊ አርበኝነት የተገነባ ብዝሃነትን ያማከለ አካታች የፖለቲካ ስርዓት ይኖር ዘንድ ነው ።

የብልፅግና ፓርቲ በሀገራችን የምንፈጥረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የጠበቀና የሁሉም ማንነቶች ነፀብራቅ የሆነ፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ማንነት ያከበረ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል። ለዚህም ብሔራዊ አርበኝነትን የሚያፀና አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ወሳኝ ነው። ብሔራዊነት ስንፈልግ የምንይዘው ሳይመቸን የምንጥለው ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ከተቃርኖ የጠቅላይነትና የተገንጣይነት ነጠላ ትርክቶች ተላቀው ጠቃሚ የሆኑ የስልጣኔና የአብሮነት ዕሴቶቻቸውን በማዳበር የወል ዕውነትን በማጽናት በህብረብሔራዊ አንድነት ፀንታ የምትበለጽግ የጋራ ሀገር ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ ይገባል።

ብልጽግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት ጋር የምታደርገዉን ትንቅንቅ ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ኢትዮጵያዊያን ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን እንደፀጋ በመውሰድ ለጋራ ሀገራቸው በጋራ በአብሮነት መቆም ሲችሉ ነው ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሲቆሙ አስደማሚና ለዓለም ሁሉ ትግርት የሆኑ ታሪኮች ማስመዝገብ እንደሚችሉ አስመስክረዋል። ጀግኖች አባት/እናቶቻችን በአድዋ የጥቁሮች ሁሉ ቀንዲል የሆነ ድልን አስመዝግበው፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ሀረር ግንብ፣ አባጅፋርና የጥያ ትክል ድንጋይን የመሳሰሉ ታሪካዊ አሻራዎችን በማኖር ኩራትና ምንዳ አሳርፈዋል።

ኢትዮጵያዊያን በዚህ ዘመንም የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ኮይሻ፣ ጎርጎራና ሀላላ ኬላን የመሳሰሉ ሀገራዊ ገፅታን የሚቀይሩ ፕሮጀክቶችንና የዓለም ሪከርድን የሰበራንበት አረንጓዴ አሻራን ማሳረፍና በአንድ ስንቆም መበልጸግ እንደምንችል አስመስክረናል። ለዚህም ነው ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን በህብር ሲቆሙ አርበኞች ናቸዉ ብሎ በጽኑ የሚያምነው! ሁሌም በድል ለመራመድና ሀገራዊ የብልጽግናን ጉዞ ለማረጋገጥ በህብር ሀገራዊ ገዥ ትርክት የሆነውን ብሔራዊ አርበኝነት ማጽናት ይገባል። ብልጽግና ዜጎች ተደምረው የጋራ የምትሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት የሚችሉበት ዕርሾ አለ ብሎ በማመኑ የነበሩብንን ያለመግባባት ዕዳዎች በውይይትና ዕርቅ በመፍታት ነባር ምንዳዎቻችንን በማስቀጠል በሀገራዊ ገዥ ትርኮታችችን በመገባባት ከዕዳ ወደ ተትረፈረፈ ምንዳ መሻገር አለብን ብሎ ያምናል።

ፓርቲያችን ብልፅግና ብሔራዊነት ገዢ ትርክት እንዲሆን የፈለገበት ዋና ምክንያት አብሮነትን ክዶ ልዩነት ላይ ብቻ የሚያተኩር ወይም ብዝኃነትን ደፍጥጦ ፍፁማዊ አንድነት የሚፈልግ ትርክት ለምናስበው ሀገራዊ ብልፅግና አንድነት አይጠቅመንም በሚል አቋም ነው። በአጠቃላይ ብሔራዊነት አማካይ የሆነ ኅብረ ብሔራዊነትን የሚያፀና አካታች ፍትሀዊና እኩልነትን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚያረጋግጥ አሰባሳቢ ትርክት ከመሆኑ አንጻር ሁሉን አቀፍ አካታች ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠሪያ መንገድ ነው።

12/03/2024

የልማት ነጠብጣቦች በልማት ኮሪደር ፕሮግራም ይገናኛሉ ፤ አዲስ አበባ ታብባለች ፤ የህዝባችን ህይወትም ይለወጣል!

የለውጡ መንግስት በከተማችን እና በአገራችን ይዟቸው ከመጣው ቱሩፋቶች መካከል አካታችነትና ፍትሀዊ ልማት ተጠቃሽ ናቸው።

የከተማችንን ፈጣን ልማት ከማስቀጠል ባለፈ ፓርቲያችን ተግባራዊ እያደረጋቸው በሚገኙ ሰው ተኮር ፕሮግራሞች ባለፀጎችን እና በጎፈቃደኞችን በማስተባበር የኑሮ ውደነቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚያሳርፈውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ እርምጃዎች ከጊዜያዊ መፍትሄነት የተሻገረ ዓላማ ያነገቡ ናቸው።

ለአብነትም የተማሪዎች ምገባ ቁሳቁስ እና ምግብ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ትውልድ ላይ መስራት የሚገባንን መስራት ስላለብን ነገን ታሳቢ በማድረግ ጭምር እየተተገበረ ያለ ዓለም አቀፍ እውቅናም የተቸረው ፕሮግራም ነው።

ከለውጡ በፊት መሀል ከተማ ይኖሩ የነበሩ ዜጐች ለልማት ሲነሱ ማህበራዊ መሰረታችን ተናጋ የሚሉ ቅሬታዎች ጎልተው ይሰሙ እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ነው።

የከተማችን የልማት እንቅስቃሴ የመሀል ከተማ ነዋሪዎችን ማህበራዊ መስተጋብር ማላላት ብቻ ሳይሆን የከተማችንን አርሶአደሮችም ካለበቂ ካሳ ከይዞታቸው በማፈናቀል ከተማው መጣልን ሳይሆን መጣብን የሚል አስተሳሰብ እንዲይዙ አድርጐ መቆየቱም አይዘነጋም።

ነዋሪዎች ካሉበት ቦታ ሳይርቁ ኑሮአቸው የሚሻሻልበት ፣ አካባቢያቸው የሚለወጥበት የልማት ስትራቴጂ በመንደፋችን የልማት እንቅስቃሴአችን ገፊ ሳይሆን አካታች መሆኑን ህዝባችን የሚመሰክረው ነው።

የእሳት አደጋ ቢከሰት እንኳን አይደለም ተሽከርካሪ የእሳት አደጋ የሚከላከሉ ባለሙያዎች እንደልብ ተንቀሳቅሰው አደጋን የሚከላከሉበት መተላለፊያ የሌላቸው የከተማችን አካባቢዎች ነዋሪዎቻችንም የስጋት እንቅልፍ እንዲተኙ ምክንያት ሆነዋል።

የዘመሙ ቤቶች ካልታደሱ እና በአዲስ ካልተቀየሩ እጣፈንታቸው መውደቅ በመሆኑ አላስፈላጊ የጤና እክል እና ሰብዓዊ እንዲሁም ቁሳዊ ጉዳት ከማስተናገድ ውጭ ፋይዳ አይኖራቸውም።

ከተማ ደግሞ በባህሪው በማያቋረጥ ለውጥ ውስጥ ያልፋል። ትናንት በተደነቅንባቸው ግንባታዎች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ማድረግ ስለማይቻል ከጊዜ ጋር መራመድ ወሳኙ ጉዳይ ነው።

የአገራችን ብልፅግና ከእያንዳንዳችን መለወጥ እና አካባቢያችንን ከማሳደግ እንደሚጀምር ጠ/ሚ ዶ /ር ዐብይ አህመድ ከቤተመንግስት እድሳት እና የአንድነት ፓርክ ግንባታ ጀምረው የአቧሬ አካባቢ ነዋሪዎችን ህይወት እንዲሁም የአካባቢውን ገፅታ እየቀየሩበት ያለው አሰራር በከተማ አስተዳደራችን ለሚከናወኑ ስራዎችም አብነት ሆኗል።

የለውጡ መንግስት ፕሮጀክትን ጀምሮ የመጨረስን ጠንካራ የስራ ባህል በመላበስ ግርምትን የሚያጭሩ ስኬቶችን አስመዝግቧል። ከተማችን ለዚህ ምስክር ነች ::

በሰው ተኮር ስራዎቻችን የአጭር የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፈን የህዝባችንን ህይወት ለመለወጥ ከምናደርገው ርብርብ ባሻገር የዛሬውን ብቻም ሳይሆን የነገውንም ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ የአድዋ ድል መታሰቢያን የመሳሰሉ ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎቻችንን ማሳረፍ ጀምረናል።

የጀመርነው የብልፅግና ጉዞ ብልጭ ብሎ የሚቋረጥ ሳይሆን አገራችን ከሚገባት የዕድገት ማማ ላይ እንድትደርስ የሚያስችል በፅኑ መሰረት ላይ የሚገነባ ሁለንተናዊ ለውጥ ነው::

የምንወጣው ዳገት የምንወርደው ቁልቁለት ላብአችንን የሚያንቆረቁር አድካሚና ፈታኝ ቢሆንም ፣ አባቶቻችን የከፈሉትን የህይወት መስዋዕትነት ቢያስከፍለን ጭምር ዋነኛው የህዝባችን ነቀርሳ የሆነውን ድህነትን ሳንነቅል እርፍትም እንቅልፍም አይኖረንም ፤ ለዚህም ነው የፓርቲያችንን ስያሜም ፣ መዳረሻ ግብአችንንም ብልፅግና ያልነው።

ከዛም ከዚህም የጀማመርናቸውን የልማት ነጠብጣቦች ሰሞኑን ለህዝባችን ይፋ ባደረግነው የልማት ኮሪደር ፕሮግራም በማገናኘት አዲስ አበባ ታብባለች የህዝባችን ህይወትም ይለወጣል!

መልካም የስራ ሳምንት !

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

10/03/2024

እንኳን ለዓብይ ፆም እና ለታላቁ ረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ!

ፆሙ ለሀገር ሰላም የምንፀልይበት ፣ካለን ላይ በማካፈል የተቸገሩትን የምንረዳበት እና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Website