Gurame Investment
በህብረት ማደግ ያስተማምናል! Why invest with GURAME? The investment group outlined its vision and strategies to build a stable organization. That is not the case at all.
Since its birth, GURAME investment has very practical ideas and strategies to
establish a shareholders company which focuses to be a socially responsible organization. Creating a viable, financial institution would address the issues and solve basic forms of social issues if managed accordingly. We are a group of investors who would like to make a difference by satisfying the shareholders as well
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard!
Bereket Fekede, ሙሰብ ኑርሁሴን ሻካች, Addis Fikre, Metiku Mesifen, ፀግሽ ባባ, Abrar Zoskales, Kiyu Gm, ተመስገን ብላቱ, ደርጉ ተስፋዬ
መልካም በዓል!
2016 ዓ.ም. የጉራጌ ባንክ የሚመሰረትበት ዓመት እንዲሆን፣ በቁርጠኝነትና በህብረት እንነሳ!
የጉራጌ ባለሀብቶች እና ምሁራን፣ ዛሬ ነገ ሳትሉ ተንቀሳቅሳችሁ አንቀሳቅሱን!
Watch "Gurame introduction" on YouTube
Gurame introduction Introduction
Gurame.
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ጉራአሜ በረዥም እና ጠመዝማዛ ጉዞው፣ ጉራጌን አስተባብሮ በልማት ለማነቃቃት፣ የቻለውን ያህል አድርጓል ማለት ይቻላል፡፡
ሀሳቡ የመነጨው ሰሜን አሜሪካ ነዋሪ በሆኑ የጉራጌ ቤተሰቦች በመሆኑ ምክንያትና፣ በጊዜው እንደዛሬው የዳበረ የሶሻል ሚዲያ ግባት ስለአልነበረ፣ ወገኖቻችንን ከየአሉበት ፈልጎ ለማግኘት ብዙ ተጥሯል፡፡
አስራ አራቱ አደራጆች፣ በቀን ከሃያ ለአላነሱ ሰዎች ከኪሳችን እየከፈልን ስልክ እንደውል ነበረ፡፡
አብዛኛው ሰው ሀሳቡን ቢደግፈውም፣ የተለመዱ ጥያቄዎች ግን ይጎርፉልን ነበረ፡፡
ከጥያቄዎቹም መካከል፦
ጉራጌ መሆኔን እንዴት አወቃችሁ?
የየት አካባቢ ጉራጌዎች ናችሁ?
ለምን የመጀመሪያ ሳይቱ ጉብርየ ላይ ሆነ?
አሁን በጉራጌ ምድር ይህን የመሰለ ግንባታ ቢገነባ፣ ሕዝቡ አቅም የሌለው ድሀ ስለሆነ፣ ማን ሊገለገልበት ይችላል? እንዴትስ ያተርፋል?
እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማስተናገድ ብዙ ጊዜና ገንዘብ አጥፍተናል፡፡
ጥቂቶ የመከሩን ደግሞ፦
ይህን ያህል የተስፋፋ ፕላን፣ የሰለጠነ እቅድና ካፒታል ከአላችሁ፣ ፕሮጀክታችሁን ጉራጌ አገር ላይ ሳይሆን፣ አዲስ አበባ ላይ ብታስፈጽሙት፣ በአጭር ጊዜ ቢሊየነሮች ትሆናላችሁ ብለውን ነበረ፡፡
እኛ ግን «የራስን ጥሎ፣ የሌላውን አንጥልጥሎን» አልተቀበልነውም፡፡
አላማችን ትርፍ ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢ ልማት ነውና!
ሳይቶቻችንን መጀመሪያ አዋጭ ሉሆን ይችላል ተብሎ በተጠናው ጉብርየ ጀምረን፣ በተባበረ አቅም፣ በአስር አመታት ውስጥ፣ በመላው የጉራጌ ምድር፣ አስር የተለያዩ የኢንቨስትመንት ሳይቶችን ማቋቋም ነው እየአልን፣ በየ ስብሰባው አስረድተን ነበረ፡፡
ከአነጋገርናቸው ወደ 1200 ከሚደርሱ የጉራጌ ልጆች ውስጥ 30 የሚደርሱት ኢንቨስት አድርገዋል፡፡
እንግዲህ ወደውጭ በላካችኋቸው ልጆች ምን ያህል ልትተማመኑ እንደምትችሉ ይህ ማሳያ ይሆናችሁ ይሆናልና፣ ትኩረታችሁ እዚያው ሐገርቤት ቢሆን ይመርጣል ብለን እንመክራለን፡፡
የጉራአሜ ሀሳብ የተጸነሰው በአሜሪካ ምድር ይሁን እንጂ፣ ተወልዶ የሚያድገው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ፣ የሐገር ቤቱን አመራር አንቱታን በአገኙ ወገኖቻችን ከሁሉም የጉራጌ አካባቢ ተውጣጥተው እንዲዋቀሩ ተደረገ፡፡
ቦርዱ በየመስቀል ሬስቶራንት ባለቤቱ የህግ አማካሪ፣ አቶ በላቸው አንተዋን እንዲመራም ተደረገ፡፡
የቦርድ አባላቱም እነ ኢንጅንየር ደሳለኝ ደንቡን፣ የጉልባማውን ክንፈ ግርማን፣ የተግባረ እዱን ተዘራ ገብሬን፣ እውቁ የሙያ ሰው መቶ አለቃ በንቲ ስራኒን፣ እውቁ የጉራጌ ሞተር አቶ ቱርጋ ቡታን፣ ለየሳምንት ስብሰባችን ብለው ከጅማ አዲስ አበባ ሲመላለሱ የነበሩትን የጌቶ ባለሀብት አቶ አያልነህን የአካተተ ነበር፡፡
ለአመታት ሳይሰለቹ ጉራጌን አንድ እርምጃ ለማራመድ ለአደረጉት በጎ ተግባራት ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳቸው!
ከአስር ዓመታት በፊት ጉራአሜ የመስራች ጉባኤውን በአዲስ አበባ እና በወልቂጤ አካሂዶ ነበር፡፡ በስብሰባችን ላይ ተገኝተው የመረቁንም ክቡር አቶ ሀብቴ ቸሆ እና የተከበሩ ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ነበሩ፡፡
ይህ በእዚህ እንደአለ፣ የህልሞቻችን ሁሉ መሰረት የነበሩትን፣ ዛሬ ግን በህልፈተ ህይወት የተለዩንን የተከበሩ ባለሀብት አቶ አልፍሬድ ከማልን እና እንጅንየረ ፍቅሬ ኸግያነን እናስታውሳለን፤ ነብሳቸውን ይማርልን!
ሟች አቶ አልፍሬድ ከማል ለማንነታቸው የአደረጉትን ውለታ መዘርዘር ጊዜ አይበቃምና፣ እግዚአብሔር (አላህ) ይቁጠርላቸው እንላለን!
ሌላው ብልህ የልማት አርበኛና የጉራጌ ፈርጥ ወዳጃችን ዶክተር መኩሪያ ሀይሌ ነበሩ፡፡
ከጎናችን ሆነው፣ እግራችንን እንድንተክል የአገዙን ጉራጌ ናቸውና፣ ለአደረጉልን ሁሉ ከልብ እናመሰግናቸዋለን!
የስብሰባ ጥሪ
ለክቡራን የጉራአሜ ኢንቨስትመንት አክስዮን ማህበር አባላት በሙሉ
የጉራአሜ ኢ/አ/ማህበር የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 24 ቀን 2014ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው አዶት ህንፃ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። ጉባኤውም የሚከተሉት አጀንዳዎችን ይዟል፤
በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ
1ኛ) የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት የሥራ ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ማድመጥ፤
2ኛ) የውጭ ኦዲተር የሂሳብ መግለጫ ማድመጥ፤
3ኛ) በቀረቡት ሪፖርትና ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
4ኛ) የአክስዮን ማህበሩ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ መወያየት፤
በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
1ኛ) በአዲስ የገቡና ያልተመዘገቡ አባላትን መቀበል፤
2ኛ) የአክስዮን ማህበሩ ካፒታል ስለማሳደግ ናቸው፡፡
ሁሉም ባለአክስዮኖች በተባለው ዕለትና ሰዓት እንድትገኙ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በጉባኤው መገኘት የማትችሉ ባለአክስዮኖች ህጋዊ ወኪሎቻችሁ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911749653 ማነጋገር ይችላል።
የስብሰባው ተሳታፊዎች የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል በመጠበቅ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ