Ayehu Security Affair Office

Ayehu Security Affair Office

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ayehu Security Affair Office, Government Organization, .

Photos from Ayehu Security Affair Office's post 02/03/2019

የ123ኛ አድዋ ድል በአል በወረዳችን ለሁለተኛ ጊዜ አምበላ ከ2500 በላይ ሰራዊት ባለበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ዛሬ የካቲት 23/2011 ተከበረ። በክብር እንግድነት የተገኙት የወረዳው አዴፓ ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገደፋው ይስማው ጀግኖች ታግለው ለዚህ ባደረሱን ሀገር ክልላችንን ቆራርሰው ለመበተን ያሰቡ የውጭና የውስጥ አጀንዳ ጣዮች ላይ በዳግም ጥሪ መስዋትነት መክፈል አዲስ እንደማይሆንባችሁና ዝግጁ እንደሆናችሁ አልጠራጠርም ብለዋል። በአርበኞቹ በኩል ደግሞ በክልላችን ፣ በብሔረሰብ ዞናችንና በወረዳችን የጦር መሳሪያና የመበታተን ፌክ አካውንት አስከፍቶ የሚንቀሳቀስ ሀይልና በግልፅ ውግያ ለመክፈት በየተራራ ምሽግ ሚቆፍር በአስቸኳይ ማቆም ካልቻለ ያለማንም ይሁንታ አካባቢያችንን ለማዳን ሙሉ በወረዳው ያለ ሰራዊት እንደሚዘምት ጥርጥር የለውም ብለዋል። በዚህ አጋጣሚ በየትኛውም ስርአት ዘምቶ የተመለሰ ሰራዊት ለገጂዎች ሳይሆን ለሀገር ሉአላዊነት በመሆኑ የደርግ ፣ የሀይለስላሴ፣የኢሀዴግ ብሎ ክፍፍሉ ለክልላችን ጠቃሚ ባለመሆኑ በመደመር የክልላችንን አደጋ በጋራ እንከላከል የሚል መልዕክት ተሳታፊዎች አስተላልፈዋል። አየሁ ጓጉሳ ወረዳ

Photos from Ayehu Security Affair Office's post 09/09/2018

የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ከ170 በላይ በክብር ተመላሽ ሰራዊት አባላትን " በሀገራዊ ለውጥ የተመላሽ ሰራዊት አባላት ሚና " በሚል ፅሁፍ ቀርቦ ዉይይት በአዘና ከተማ ዛሬ ጳጉሜ 4/2010 ተካሄደ። በውይይቱ ላይ አሁን በአካባቢያችን ያለው ሰላም በተለያዩ ለውጥ ፈላጊ ባልሆኑ ሀይሎች እንዳይደናቀፍና እንዳይመለስ ከህዝና ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ስርቆትንና ሌሎች ወንጀሎችን መከላከል አለብን ሲሉም ገልፀዋል። እስከ አሁን የነበሩ አንዳንድ የፀጥታ ችግሮችም በየደረጃው የሚገኝ የፀጥታ አመራር ህዝቡንና የክብር ተመላሽ ሀይል አንድ ላይ አዋህዶ የጋራ ሀገራዊ ተልዕኮ ባለመስጠት የመጣ ነው ብለዋል ።በማጠቃለያም በስርቆትና ሌሎች ወንጀሎች ከዚህ በሇላ እጃችንን አስገብተን ህዝቡን ባለቤት በማድረግ እንሰራለን ብለዋል። ለዚህም የወረዳ አስ/ፀ/ጉ/ፅ/ቤት በተለያየ የፀጥታ ማስከበር አደረጃጀት እንዲያስገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

14/08/2018

የአዮጓጉሳ ወረዳ ከወረዳና ቀበሌ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሰላም ጉዳይ ዉይይት አካሄደ።
ማወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የፀጥታ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ነጋ ስዮም ዘመኑ የለውጥ፣የፍቅር ፣የይቅርታ በመሆኑ በየደረጃው የምንገኝ አመራሮች አገልግሎት አሰጣጣችን ቀልጣፋ ህዝብ አክባሪ መሆንና ለሰጠነው አገልግሎት ምንም አይነት ውለታ የማንጠይቅ መሆን ይገባናል ሲሉ ገልፀዋል።
በወረዳችን አሁን ያለው ሰላም አስተማማኝ መሆኑ ደግሞ የህዝባችንን የስልጣኔ ደረጃና በምክንያት የሚያምን አሉባልታ የማይበግረው የመልማት ጥያቄ ሲያነሳ የቀበሌ ሀቅም፣የወረዳ ሀቅም፣የዞን ና ክልል ሀቅም ምን ላይነው ብሎ ጠይቆ የሚረዳ ሀቅም በፈቀደው እንዲለማለት በትግስት የሚጠብቅ ፣ለአካባቢ ልማት ያለ ጥሩንባ የሚወጣ ህዝብ መሆኑ ይበልጥ አገልጋይ ተቀራርቦ እንዲሰራ ያደርጋል።
በመጨረሻም ሁሉም በየደረጃው ያለ አመራር የፀጥታን ስራ ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ በመስራት አሁን ያለው ሰላም ባለበት እንዲቀጥል መተማመን ላይ ተደርሷል።

14/08/2018

"ለውጥ ሊጥ አይደለም"
ሊጥ እንኳ ለምግብነት እስኪደርስ ጊዜ ይሰጠዋል። ሆደሰፊነት እንጂ ችኩልነት ባህላችን አይደለም።ጥሩ መሪ መጣ ፣አድማጭ መሪ መጣ ፣ለዚህ ህዝባችን ብዙ አመት ታግሏል ፤የህዝቡ ትግል ተሳክቷል ብለን ስንደሰት ጥርጣሬ የሚያመጣ ዶሴ የሚበትን ሰው ተገኘ።
አሁን እየመጣ ያለው" እነ የገሌ ሰፈር የበቀለው ግራር ለምን እኛ ሰፈር አላደገም ነው"።የወቅቱ አትክልተኛው እናንተ ሰፈር በሆነ ምክንያት ስላልተከለው ነው አሁን ወረፋው ደርሷል እንትከል ጊዜ ስጡን አንሰጥም ።መንግስትም የተረጋጋው ህዝብም ተቸገረ እኮ፡የሚያሳዝነው በተለያየ ችግር ወደ ውጭ ወጠው የነበሩ ወንድሞቻችንን ግቡ ሀገሩ ሰላም ሁኗል ተብለው ይህን ጦስ ማየታቸው ፡ለኛማ ክላሲካል ነው። ለማንኛውም ለመንግስት ሪፎርም እድል ይሰጥ ሆደ ሰፊ እንሁን።በሬ ወለደ ጎድቶናል እንጂ አልጠቀመንም።

13/07/2018

በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ፅ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ።
1.ጥቅም ያስኮረፋቸውና የግል ጥላቻን ከመደመር ጋር አቀላቅሎ የድጋፍ ሰልፍን ወደ መንደር ጥላቻ ለማዞር በማሰብ ብአዴን ሚባለው በአንድ ሌሊት የህዝብን ፍላጎት አሳክቶ ካላደረ እዚህኛው ተቋም የሚሰራ በተለይ ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋም ያለ ሰው ይውደም የሚለው የተደማሪ ዜጎችን አይወክልም ።
2.የዶክተር አብይን የፍቅርና የሰላም ጥሪ የወረዳችን አጠቃላይ አመራር፣የወረዳችን ሙሉ ሙያተኞችና ህዝባችን ከልብ ወዶታል።ስለመውደዱም ማረጋገጫ ጥያቄ በሰለጠነ መንገድ እየጠየቀ እዚህ ጎደሎ አለ? በዚህ ጅምር በርቱልን እያለ ይገኛል ።ለዚህም ለአየሁ ጓጉሳ ህዝብ አመራሩና ሙያተኛ ።
3.የብሄረሰብ ዞን የፀጥታ አመራሮች በዚገም ለፀጥታ ማስከበር በሄዱበት አጋጣሚ መሄዳቸው በወረዳው ላለው ከፍተኛ ለሆነ ብቀላ ወለድ ነፍስ ግድያ መፍትሄ እንጂ በወረዳው ላጡት ለመብራት እጦት፣መንገድ እጦት፣ወዘተ መፍትሄ አይሆንም ።ለዚህ መፍትሄ ለክልልና ፌደራል አመራር ጥያቄ ስርአቱ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ መጠየቅ ነው። በዚህ አጋጣሚ አቶ መለሰ አዳል ለረጅም አመት የወረዳዎች ኮር አመራር ሁኖ ቆይቶ እጁ ንፁህ መሆኑን የወቅቱ ህዝቡ በማረጋገጡ ገንዘብና ኢኮኖሚ ምክትል መምሪያ ሀላፊ በመሆን በማገልገል ላይ እያሉ ጠንቃራና ታማኝ አመራሮች ሲያድጉ አብሮ ያደገ ጠንቃራ አመራርና አብረውት ያሉትን በቅላጅ ከተማ መያዝን የመልማት ፍላጎት የመደመር ፍላጎት ነው ብሎ ተቋማችን አልወሰደውም ። ይህ ማለት በአካባቢው ልማት አልጋ በአልጋ ሁኗል ማለት አይደለም።ስለዚህ በአንድ ዞን ሁነን አንዱ አጋች አንዱ ታጋችነት የብሄረሰባችን ባህል ሳይሆን የብሄረሰቡን የመደመር ውጤት የማይፈልጉ ሀይሎች ሴራ ነው አለዚያ የእለታዊ አኩራፊ ወገኖቻችን መገፋት ነው።በየትኛውም አለም መንግስት ልማትን ባለስልጣንን የሆነ ቡድን እያገደ አልመጣም ።ለአዊ አዲስ ታሪክ ነው።
4.በአሁኑ ሰአት እየመጣ ያለው በጥቂት ባለስልጣን ጭፍን ጥላቻ ለረጅም አመት የተገነባ ያም ሁኖ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ ንብረት ቢኖር ለአካባቢው ህዝብ ኩራትም ገፅታም የሆነን ለማውደም የተሸረበው የአማራ ህዝብ ኢኮኖሚ ድቀት የሚፈልግ ሀይል እንጂ የህዝባችንን ምጥቀት የሚፈልግ ሀይልን አይወክልም።
5.ወረዳችን ለጋ ነች የተቋቋመችው ሁለት አመት አልሞላትም አሁን የምንፅፈው መጦ መዳሰስ የሚቻለውን ነው ።ሁለት አመት ሳይሞላት ሁሉንም የመንግስት መ/ቤቶች በግንብ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ ቆርሶ የገነባ ለነባርም ሆነ አዲስ ወረዳ የተሞክሮ ማእከል ሊሆን የሚችል፣ለሁሉም መ/ቤት ለሁሉም የስራ ሂደቶች ኮምፒውተር የገዛ ፣ የመብራትን ችግር ስለሚያውቅ ለአብዛኛው ሴክተር ጀኔተር የገዛ ወረዳ ነው።ሁሉም ወረዳ አዲስ ወረዳ መሆንን ሳያይ ያለፈ የለም ግን ልዩነቱ በአገልግሎት አሰጣጥ አጀማመር ላይ ነው የወረዳነት እድሜ ሳይሆን የአመራር ንፅህናና ለኔ ከሚል ለህዝብ ማለት አለበት ።በዚህ ደግሞ አካባቢው ላይ ይበልጥ ሰላምን አንግሷል።ውድ የፀጥታ ሀይሎች፣ውድበአዲሱ ወረዳ የምትሰሩ መንግስት ሰራተኞች፣ውድ የወረዳ አመራሮች ፣የተከበራችሁና የተረጋጋችሁ ህዝባችን በዚህ እርቀት አየሁ ጓጉሳ ወረዳንእንደ ዱባይ የንግድ ማእከል ለማድረግ በያዝነው መፈክር በሰላሙ እጅለእጅ እንያያዝ።
5.ድርብርብ እድል> በዞናችን ከሚገኘዉ 46 ኢንበስትመንት ዉስጥ 39 የወረዳችን ነው።ግን በዚህ ኢንበስትመንት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የነበሩት እነጅቦ ሲመቻቸው የባለ ሀብቶቹ ሳይመቻቸው የገሌ እየተባለ በመቀባታቸው ምክንያት በምርት ሽያጭ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል።ለአብነት የአየሁ ጓጉሳ ምርቶች ብራንድ አላቸው የትም ቦታ ምርቱ ተፈላጊ ነው ይህ ለአዊ ኩራት መሆን አለበት።አሁን ባለዉ ጥቂት የመንደር የሀሰተኛ የፓለቲካ ግርሻትን በመጠቀም ከወረዳችን ትንሽ እልፍ አንዳለ ለፍፍ ድርጅት፣ለአለም የምግብ ድርጅት ከወረዳችን የጫንነውን በቆሎ ማስቆም ኢትዮጵያዊነትን አይወክልም።ይህን ኢኮኖሚ ድቀት የሚያመጣ አመለካከትም ሆነ ተግባር ተቋማችን አምርሮ ይታገላል።
6.በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ በሁሉም ቀበሌ ያላችሁ ህዝቦች ለመጤ ዉዥምብር ጀሮ ባለመስጠታችሁ ለለውጥና ለልማት መነሳታችሁ የወረዳችን በሁለት እግር መቆም ለአንዳንዱ ህልም ስለሆነበት ለምን የአጀንዳየ ማስፈፀሚያ አልሆነም ብሎ ከዘገየ በኋላ ተነስቶ ትናንሽ ገንዘብና ወረቀት ሊበትን ስለሚችል በአቅራቢያ ላለ የፀጥታ አካል ጥቆማ ለመስጠት ለአፍታም እንዳትዘናጉ በዚህ አጋጣሚ ፅ/ቤታችን ጥሪውን ያስተላልፋል።አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ፅ/ቤት

Photos from Ayehu Security Affair Office's post 28/06/2018

በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ በእሁዲት ከተማ ከሙስሊም ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።በመድረኩ ላይ ከ200 በላይ የሀይማኖት አባቶችና የወረዳ አስ/ፀ/ጉ/ፅ/ቤት አመራርና ሙያተኛ የተገኙ ሲሆን እንደተሳታፊዎች ገለፃ የፀጥታ ሀይል ብቻውን መመደብ ሰላም አያመጣም የሀይማኖት አባቶችና መላ ማህበረሰብ ድምር ውጤት ብቻ ሰላም እንደሚያመጣ በምክክር መድረኩ አንስተዋል።በውስጣቸውም ጭምር አልፎ አልፎ ያለመግባባት ችግሮች የነበሩ መሆኑን አንስተው ጊዜው የመደመር፣አፉ የምንባባልበት፣ጥል ሀራም የሆነበት፣ማንኛውም ዳኢ ለወገንና ለሀገር ደፍሮ የሚሰብክበት፣በቀሪ ዱንያ ቦታችን ፍቅር ዘርተን የምንሄድበት በመሆኑ ፦ለሰላም ለአንድም ደቂቃ አንዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል።ጥብቅ ማሳሰቢያ ደግሞ በየትኛውም መንገድ ከየትም ቦታ ያለውን ቁርሾ ወደ አካባቢያችን ይዞ ለመምጣት በሩ ዝግ ሁኖ የአካባቢውን የመቻቻልና የመደመር ጥሪ ተቀብለው ከመጡ አካባቢያችን ትርፍ አምራች የትኛውንም ችግር በራሱ ሀቅም መቋቋም የሚችል የሚያማልል አካባቢ ነው።የሀይማኖት አባቶች እንዳሉት በአስቸጋሪ ዘመን ደርሰናል ብለዋል።ምክንያቱም የረጅም አመት ጅቦችን በአንድ ጀምበር ገጥመናል ሲፈልጉ በሀይማኖት የሚገቡትን፣ሲፈልጉ ከመንግስት ካዝና፣ሲፈልጉ ለመንግስት አገልግሎት ዉለታ ሲጠይቁ የሚውሉትን መንግስታችን በተናነቀበት ወቅት ደርሰናል።ስለዚህ ወረዳችን አዲስ በመሆኑና አመራሩ አዳዲስ በመሆኑ ለውጡ አሁን በመሆኑ ወረዳችንን በጋራ እናልማ ብለዋል ።በመጨረሻም በወረዳችን አሁን ያለው ሰላምየሀይማኖት አባቶችና የፀጥታ ሀይሉ የመደመር ውጤት ነውና አሁን ያለው ቅንጅታዊ ስራ ይጠናቀር ብለዋል።

24/06/2018

ትላንት በመስቀል አደባባይ አዲስቷን ኢትዮፕያ በአዲስ አስተሳሰብ ለመምራት በድጋፍ ሰልፍ ለሞቱት ወንድሞቻችን ቤተሰቦች የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ህዝብና ፅ/ቤታችን መፅናናትን ይመኛል።በዚህ አጋጣሚ የጥቂቶች ሴራን ማሸነፍ የሚቻለው በፅኑ መሰረት የቆመ አንድነት ሲኖረን ነው።ይህ እኩይ አላማቸው ደግሞ በድንገት የመጣ ሳይሆን በልዩነት መሀል ክብረት የፈለጉ የጥቂት አግበስባሾች ታስቦ የተሰራ ሴራ ነው።ይህ ለሀገራችን ህዝብ ማንቂያ ደወል መሆኑን መገንዘብ ስንችል ነውና በዚህም መሰረት የቀጣይ የሴራ ተልእኳቸው በተለያየ የስራ ዘርፍ አመሳስለው ሊያስገቡ ስለሚችሉ የተለያዩ ፀጉረ ልዉጦችን ህዝቡ አበክሮ አደጋውን በመገንዘብ እንዲከታተል ጥሪ እያስተላለፍነ በዚህ አጋጣሚ በየሰፈሩ ያሉ ጥሎችን እንደ መልካም አጋጣሚ እንዳይጠቀሙ መታረቅ ይቅር መባባል፣አንድ መሆን፣ቁርሾን ከውስጥ አውጥቶ መጣል ፣በነውር መካሰስንናየአንዱ ጉዳት ለአን ደስታ መሆንን በማስወገድ የሰላም፣መከባበርና መቻቻል ተምሳሌት እንድንሆን ተቋማችን ይጠይቃል።

Photos from Ayehu Security Affair Office's post 19/06/2018

የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ አስ/ፀ/ጉ/ፅ/ቤት የወረዳ ሀይማኖት አባቶች ጋር ኮንፈረንስ በወረዳ ከተማ አዘና ላይ አካሄደ።
በኮንፈረንሱ ላይ የሰላም እሴት ግንባታና የሀይማኖት አባቶች ሚና፣የወንጀል መንስኤናየሀይማኖት አባቶች አስተምሮ በሚሉ ርእሶች ጥናታዊ ፅሁፍ በወረዳው ተዘጋጅቶ የተሰጠ ሲሆን በኮንፈንሱ ላይ የእስልምና፣የክርስትናና የኘሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታዮች በድምሩ ከ60 በላይ ተገኝተዋል። ጥናታዊ ፅሁፉን ያቀረቡት የአስ/ፀ/ጉ/ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዮሀንስ በላይ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ሺህ የፀጥታ ሀይል ከመመደብ የአንድ ሀይማኖት መሪ ተመለስ ቢል ክብደት ይኖረዋል።ስለዚህ ግድያና ስርቆት ላይ የሀይማኖት አባቶች ያለመሰልቸት መስራት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።በመድረኩ ላይም ሁሉም አባቶች በሰላም ጉዳይ እስከ አሁን አልሰራንም ከዚህ በሗላ ከመንግስት ጎን በመሆን ትኩረት ሰጠን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

Photos from Ayehu Security Affair Office's post 16/06/2018

ማንኛዉም የፀጥታ ስራ አላማዉ የህዝብን ሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ለማስከበር መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ኪራይ ሰብሳቢነትን ፣ለአገልግሎት ውለታ መጠየቅን ፣ከህዝቡ የበለጠ በቅንቶት ለመኖር ሀብት ማግበስበስን ፣ሳይሰሩ መኖርን፣ለሚከፍለን ህዝብ አለመጨነቅን ወረዳችን አምርሮ ይታገላል። ይህን ትግል ደግፎ በሀቅ ለመበልፀግ ለሚፈልግ ሁሉ ወረዳችን ትርፍ አምራች በመሆኗ ኑ! አዲስቷን አየሁ ጓጉሳ ወረዳ በጋራ እናልማ።

Website