Hiwot Tsegaye

Hiwot Tsegaye

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hiwot Tsegaye, AIDS Resource Center, .

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 12/05/2024
12/05/2024

የትውልድ ግንባታ ሳምንት በመዲናችን አዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትውልድ ግንባታ ራዕይ ፍሬያማ እየሆነ ይገኛል!

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራር ከመላው ህዝብ ጋር በመተባበር ለመጪዉ ትዉልድ ተስማሚ እና ምቹ ከተማን ለመገንባት አበክሮ እየሰራና ውጤትም እያስመዘገበ ይገኛል።

በቆራጥ አመራር እየተመዘገበ ካለው ውጤት ልምድ ለመቅሰም ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ባለሞያዎች አዲስ አበባን መጎብኘት ጀምረዋል።

በተለይ በትዉልድ ግንባታዉ ላይ በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም (ECD) እየተሰራ ያለዉ ስራ መጪዉ ትዉልድ በራሱ እና በኢትዮጵያ አቅም እንዲያምን ፤ ዛሬ ላይ የተሻለች ነገን እንዲገነባ የሚያግዝ ስራ መሆኑን ያሳየናል።

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እዉን የሚሆነዉ የሀገር ምሰሶ በሆነዉ ቀጣይ ትዉልድ ላይ ሲሰራ መሆኑን በጽኑ በማመን በማኒፌስቶ ለህዝቡ ቃል በገባዉ መሰረት በርካታ የሚዳሰሱ ስራዎችን እየሰራ ያለ ሲሆን በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ከቀዳማዊ ልጅነት እስከ አዛውንቶች እንክብካቤ፣ ከከተማ ግብርና እስከ ትላልቅ እንዱስትሪ፣ ከትምህርት እስከ ጤና....ትላልቅ ስራዎች እየተሰሩ ውጤቶችም እየተመዘገበ ይገኛል።

12/05/2024

ለ #ጽዱኢትዮጵያ
For a

12/05/2024

የመደመር ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ይገነባል!!

የመደመር ትውልድ በሀገራችን ህብረ-ብሄራዊ አንድነት፣ ወንድማማችነትና እህታማማችነትን በአሰባሳቢው ገዥ ትርክት የሚመራ እና በሁለተኛ የአርበኝነት ምዕራፍ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋግጥ እየተጋ ያለ የነገዋን የሃገራችንን መፃዒ ዕድል የሚተነብይ ባለራዕይ ትውልድ ነው።

የመደመር ትውልድ የኢትዮጵያ እና የህዝቦችዋ ምሰሶ የሆነው የህብረ-ብሄራዊ አንድነት ትርክት ገዥ ዕሳቤ ሆኖ እንዲወጣ፣ ሚዲያዎችን ጨምሮ ተቋማት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያስተጋቡ ትክክለኛ የኢትዮጵያዊያዊያን ድምፅ እንዲሆኑ በማድረግ እየተገነባ ያለም ነው።

ይህ ትውልድ በሁሉ ለሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የአብሮነት፣ የህብረ-ብሄራዊ አንድነት፣ የወንድማማችነትና እህታማማችነትን ትርክት በህዝቡ ውስጥ በማስረፅ እና ዘርፈ ብዙ የጥላቻና አፍራሽ ትርክቶችን የሚገራ ነው።

አባቶቻችን በአድዋ ድል የውጭ ወረራን በአንድነት በመመከት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበሩበትና የጥቁር ሕዝቦችን የነፃነት ቀንዲል ያረጋገጡበትን ደማቅ ታሪክ ለማፅናት እና ገድላቸውን ለትውልድ ለማስተላለፍ የመደመር ትውልድ ደግሞ በሁለተኛው የአርበኝነት ግንባር፥ በልማት እና ድህነትን በመታገል ኢትዮጵያን ከልመና፣ ድህነት እና ጉስቁልና በማላቀቅ የበለፀግች ኢትዮጵያ በመገንባት የራሱን ደማቅ አሻራ ለማኖር የሚተጋ የዛሬው የሃገር ባለውለታ እና የነገው አርበኛ ትውልድም ነው።

05/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን ስናከብር በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ በህብረት ልናከብር ይገባል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን የቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችንን የመደጋገፍና የመተጋገዝ አኩሪ ባህል በዚህኛውም ትውልድ በማስቀጠል ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አረጋዊያንና ህፃናትን እንዲሁም ተቸግረው ያሉ ወገኖቻችንን በመደገፍና በመንከባከብ በዓሉን በአብሮነት ስናከብረው አንድነታችንን በማጠንከር ፅኑ መሠረት የምንጥልበት መልካም አጋጣሚ ይሆናልና በአሉን ስናከብር ያለንን እያካፈልን በአብሮነት እንድናከብረው ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

መልካም የትንሰኤ በዓል!

አቶ ሙሉጌታ ጉልማ
በብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

05/05/2024

የብልፅግና መሠረት ፤ ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ፤ ለዜጎች ተጠቃሚነት ቅድምያ መስጠት!


ፓርቲያችን ብልፅግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በአገር ደረጃ ሕዝባችንን የሚያሰባስብ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራትን በመስራት ለሕዝብ ግልጋሎት አውሎዋል።

በከተማችን አዲስ አበባም ዜጎችን ማዕከል ያደረገ በከተማ አስተዳደሩ እና በከተማው ሕዝብ ተሳትፎ በርካታ ልማታዊ ተግባራቶች ተሰርተዋል።

ፓርቲያችን በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብተው ለሕዝብ አስቦ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የማህረሰባችንን ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የፋሲካን በዓል ምክነያት በማድረግ በርካታ ቤቶችን በመሰራት እና በማደስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና ጠዋሪ የሌላቸው አቅመ ደካሞች ያስረክባል።

!
!

!

05/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ።በአሉ የሰላም የፍቅር፣የአንድነት፣የመቻቻል እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።

መልካም በዓል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ

05/05/2024

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዐል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በመስቀል ላይ እስከሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የለሽ ፅኑ ፍቅር ያሳየበት እና እንዲሁም ለበደሉት ሳይቀር ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት መታሰቢያ በዓል በመሆኑ እኛም፣ እርስ በርሳችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም ሰው በመውደድ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በመርዳዳት እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። በዚህ በኩል ለተዳከሙ እሴቶቻችንም ትንሳኤ ይሁን።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

05/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በክርስትና አስተምሮት በክርስቶስ ትንሳኤ ጥላቻ በፍቅር፣ ጨለማ በብርሃን፣ ልዩትነት በአብሮነት ድል ተነስተዋል፤ ሁላችንም ኢትዮጵያዊ አንድነታችንንና ህብረታችንን የሚሸረሽሩ አጀንዳዎችን፣ ጉስቁልናን እና ድህነትን ድል በመንሳት ህብረ ብሔራዊ አብሮነታችንን እና አንድነታችንን ከፍ በማድረግ በዓሉን ልናከብር ይገባል።

በዓሉንም እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ በህብረት ልናከብር ይገባል፡፡

መልካም የትንሰኤ በዓል!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ

03/05/2024

ኧረ እየሄድክ
እንደ ልብህ ታስረብሽና ወንጀልህ መጋለጥ የሆነ ሀይማኖት ተቋም ዉስጥ ራስህን ትደብቃለህ‼️

29/04/2024
29/04/2024

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት...

"ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የከተማችን የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱና ለነዋርዎቿ ምቹ የማድረግ ራዕያቸው አካል የሆነ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” የሚል አዲስ ሃሳብ የአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ጀምረዋል።

ይህ አዲስ ተግባር ነዋሪዎቻችንን በሚያሳፍር መልኩ በየመንገዱ ከመፀዳዳት ይልቅ፣ የከተማ ውበትን በሚጨምር መልኩ፣ ጤናማ አካባቢንም ለመፍጠር የሚያስችል ሲሆን ለነዋርዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በጀመሩት በዚህ ታላቅ ተግባር ላይ ከማንም በላይ መላው አመራራችን እና ተጠቃሚ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ማስተላለፍ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ"

25/04/2024

ብልጸግና አሰባሳቢ ትርክትን በመቅረፅ የበለጸገች ኢትዮጵያ ይገነባል!

ሀገራችን ኢትዮጵያን የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ በመገንባት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር መሆን ይኖርባታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የቀደመ ሀገረ-መንግስት ባለቤት ብትሆንም አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ትርክቶቿ በስርዓታት ፖለቲካ ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሆነው በመቆየታቸው ስርዓታት በወጡ እና በወረዱ ቁጥር የሚገለባበጡ ነጠላ ትርክቶች ገዥ እየሆኑባት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ተግባሯን ያለ ተቃርኖ ለማስቀጠል አልታደለችም። በአንፃሩ የአሜሪካን፣ የቻይናን የፈረንሳይን ሀገራዊ ገዥ ትርክቶች የሚነግሩን ስርዓቶች ቢቀያየሩም ገዥ ሀገራዊ ትርክታቸው መሰረቱ ሀገረ-መንግስቱ ላይ በመገንባቱ በየወቅቱ የሚነሱ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አይለዋወጥም።

ሀገራት ህዝባቸውን ከየት እንደተነሱና ወዴት እንደሚደርሱ በአሰባሳቢ ገዥ ትርክት በመገንባት ከአስተዳደራዊ ወሰናቸው አልፈው በዓለም ላይ የበላይነታቸውን ቅቡልነት አረጋግጠዋል።
የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚዘውሩት የትርክት የበላይነት በያዙ ሀገራት እና ተቋማት ፍላጎት ነው። እነዚህ ሀገራትም ይሁኑ ተቋማት የትርክታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ዓይነት ሀይል የማስጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ትርክት ቻይናን ከወደቀችበት አንስቶ የዓለም ተፆዕኖ ፈጣሪ ሀገር አድርጎ ከፊት አስቀምጧታል። ትርክት ሶሪያ ከዓለም ቀደምት ሀገርነት ወደ ፍርስራሽነት ቀይሩታል። ትርክት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲነገር የሚኖረውን በቅኝ-ገዥዎች ቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንዲትሰራ አስችሏታል።

ትርክት በህዝብ ውስጥ ለጋራ ዓላማና ራዕይ በአብሮነት በማነሳሳትን በአርበኝነት እንዲፈፅሙ የሚያንቀሳቅስ ታላቅ ሀይል መሆኑን በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ በተራራቀ ዋልታ የሚገኙትን የሀገራችን ትርክቶች ወደ አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለማምጣት በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረት ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችን ገዥ ትርክት እንዲሆን እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችንን ያልፈውን የጉዞ ምዕራፍ ፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ እና የነገን መዳራሻ የምንመለከትበት የጋር አሰባሳቢ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብሎ ያምናል።

በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት ገዥ ትርክት የትላንቱን ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ መሰረት አድርጎ የዛሬውን አስተሳስሮ ነገን ማመልከት የሚችል የህዝባችንን ዋና ዋና የጋራ እሴቶችን፣ ፍላጎቶችንና ግቦችን የሚያሳካና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል።

ፓርቲያችን ህዝባችን የጋራ ታሪክ ያለው፣ ብዙ ትላንቶችን በጋራ የተሻገረ አሁን ስንቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ አያሌ ታሪኮችን እንዳሉት ያምናል።

በዚሁ አግባብ ብልፅግና በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ አማካይነት ነባር የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት፣ ታሪካዊ እሴቶችን አውጥቶ በማበልፅግ እና በማህበራዊ ካፒታላችንን በመጠቀምና በእነዚህ ላይ እሴቶችን በመጨመር ለነገ ብልጽግናችን በሚሆን መንገድ ማልማት በሰፊው ቀጥሏል።

ከትላንት የተሻለ ሀገራችንንና ህዝቡቿን የሚጠቅም ታሪክ እንድሰራ፣ የትውልዶችን ድካም በማረም ለትወልድ የበለፅገች ሀገር ለማስረከብ እንትጋ። ስለዚህ ትርክታችን ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የዛሬን ዕድል እና የገነን ተስፋ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

25/04/2024

ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ምን ማለት ነዉ?

ብልጽግና ምሉዕ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ግንኙነት ልህቀት ውጤት ነው፡፡ ከፖለቲካው አንጻር ብልጽግና መካከለኛና አካታች የፖለቲካ እይታን ይከተላል፡፡

ከዚህ አንጻር ሲታይ ብልጽግና በቀኝና በግራ ዋልታዎች መካከል ሚዛን በመበጠበቅ በመደመር እሳቤ የተቃኘ የተረጋጋ የፖለቲካ ሀይሎች አሰላለፍና መስተጋብር የሰፈነበት ምህዳር የበለጸገ ፖለቲካ ማሳያ ነው፡፡ ሁሉም ማንነቶችና ፍላጎቶች እውቅናና ክብር አግኝተው የሚደመጡበት፣ ህግና ስርዓት የሰፈነበት አውድ ነው።
ቅቡልነት የተጎናፀፈ ሀገረ መንግሥት የተረጋገጠበት ነው። ፍትህና ርትህ እውን የሆነበት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሰፈነበት ነው፡፡

በሌላ በኩል ሁለንተናዊ ብልፅግና የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ እውን የሆነበት ነው፡፡ ሁለንተናዊ የግብርናና ኢንዱስትሪ ልማትና ዕድገት የተሰናሰለበት ነው፡፡ ገቢ ምርቶች በብዛትና በጥራት የተተኩበት፣ የኤክስፖርት ምርቶችም በዚያው ልክ በብዛትና በጥራት የተመረቱበትና የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ የተቻለበት፣ ለሰፊ የተማረ የሰው ኃይል ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለበት ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማፋጠን የግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፉን ትስስር የሚያጠናክርና ሀገራችንን በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀዳሚ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችሉ ስራዎችን በስፋት እየሰራ የሚገኘውም ከዚሁ እሳቤ በመነሳት ነው፡፡

Website