Azezo Tseda sub city Administration

Azezo Tseda  sub city Administration

0581140021

Photos from Gondar city communication's post 31/08/2024
27/08/2024

ሪፎርም ላይ አተኩሮ በመሥራት ህብረት ሥራ ማህበራት አሠራራቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን የከተማ አስተዳደሩ የህብረት ስራ ማህበራት መደራጃ ጽ/ቤት አስታወቀ ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ህብረት ሥራ ማህበራት ማደራጃ ተጠሪ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ አዳነ እንደገለፁት ሪፎርም ላይ አተኩሮ በመሥራት ህብረት ሥራ ማህበራት አሠራራቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ርብርብ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

የሪፎርም ተግባራትን በንቅናቄ ተግባራዊ በማድረግ 53 መሠረታዊ ማህበራትንና 2 ዩኒየኖችን በደረጃ የመፈረጅ እንዲሁም የሥራ አመራር ቦርድዶቻቸውና የቅጥር ሠራተኞቻቸው በግምገማ እንዲያልፉ በማድረግ አሠራሮቻቸው እንዲሻሻል ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

"ህብረት ሥራ ማህበራት ከመደራጀትም ባሻገር" በሚል መሪ ቃል የሪፎርም ንቅናቄ ተግባራትን አጠናክሮ በማሥቀጠል በደረጃ ያልተለዩትን የመለየት፣ በግምገማ ያላለፉትን የቅጥር ሠራተኞችና የማህበራት አመራሮች እንዲያልፉ የማድረግ ተግባራት በትኩረት ይከናወናሉ ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ሌላው በትኩረት የሚከናወነው ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ የመጣውን የገበያ አለመረጋጋትና የኑሮ ውድነት ለመከላከል ሸማች ህብረት ሥራ ማህበራትንና ዩኒየኑን በማጠናከርና ትሥሥር በመፍጠር የሠብል ምርትና መሠረታዊ የኢንዱሥትሪ ምርት ሸቀጣሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለአባላቶቻቸውና ለአካባቢው ህብረተሠብ እንዲሁም ለመንግሥት ሠራተኞች እንዲያቀርቡ ይስራል ያሉት የህብረት ስራ ማህበራት የተቋቋሙበትን ተልዕኮ እንዲወጡ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

የሐሙሥ ገበያን የማጠናከር ሥራንም እንሠራለን፤በዚህ ዘርፍ ዩኒየኑም ሆነ ሸማች ማህበራት የካፒታል እጥረት ሥላለባቸው ከተማ አሥተዳደሩ ትርጉም ያለው ብድር በማመቻቸት በኩል የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ አቶ ሲሳይ ተናግረዋል ።

በከተማው በሚገኙ 39 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራትም ቁጠባን በማጠናከር ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለአባላቶቻቸው ብድር እንዲያሠራጩና የአባላቶቻቸውን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

ለመሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራት የኦዲት አገልግሎት፣ የኢንሥፔክሽንና የህግ አገልግሎት እንደሚሠጥና የብቃት ምዘና ተግባራትም እንደሚከናወኑ አያይዘው ገልፀዋል።

ከ800 በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት በመመሪያው መሠረት ተደራጅተው የሚጠበቅባቸውን ቁጠባ የቆጠቡ ቢሆንም ከወቅታዊው የሠላም ችግር ጋር ተያይዞ በወቅቱ ቦታ መሥጠት እንዳልተቻለ ገልጸዋል ።

ከተማ አሥተዳደሩ ይህን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ፍላጎት መሠረት ያደረገ የቦታ አቅርቦት በማመቻቸት መፍትሄ እንዲሠጥ ሲሉም ጠይቀዋል ።

ማህበራት የመጋዘንና የመሸጫ ቦታዎች፣ የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸውና ከ80በ ላይ የእንሰሳት ባለሙያዎችን የያዙ 4 ማህበራት የቦታ ጥያቄ መፍትሄ ባለማግኘታቸው የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ እያሥነሡ ያሉ ችግሮች በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ሊሠጧቸው ይገባል ብለዋል።

Photos from Azezo Tseda  sub city Administration's post 22/08/2024

በጎንደር አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት አመት የመንግስት ስራዎች አፈፃፀምና የ2017 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ ዉይይት መደረጉ የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ዋና ስራአስፈፃሚ ገለፁ ።
የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ግርማቸዉ አስማማው እንደገለፁት አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት አመት የመንግስት ስራዎች አፈፃፀምና የ2017 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ ዉይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል ።
ዉይይቱን የመሩት የጎንደር ከተማ አስተዳደር እንስሳት አሳ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀይሉ አለሙ እና የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ግርማቸዉ አስማማው በተጨማሪ የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ የ
ብልፅግና ጽ/ቤት የአደረጃት ዘርፊ ሀላፊ አቶ ጌታቸዉ እሸቴ መራተዉታል።
የመወያያ ሰነዱ በአቶ ጌታቸዉ እሸቴ እና በአቶ አሰፋ ጌታነህ ቀርባል ።
በዉይይቱ የተነሱ ሀሳባች
የመልካም አስተዳደር ችግርች ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ፣ የኑሮ ዉድነቱ እያደረ የዋጋ ግሽበቱ መጨመር ፣የክትትልና ቁጥጥር ችግር ፣ የፋትሀዊነት ችግር ፣የብድር አሰጣጥ ችግር ፣የዉሀ ችግር በዘላቂነት ቢፈታ ፣የአዘዞ ጎንደር መንገድ ተሎ አለመጠናቀቁ ፣የመልካም አስተዳደር ችግርች በሰፊው ተነስተዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር እንስሳት አሳ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀይሉ አለሙ እንደገለጹት የተነሱ ችግሮችን መፍትሔ በማስቀመጥ ጽ/ቤቶች እቅዳችሁና አቅዳችሁ ተናባችሁ ተቀናጂታችሁ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በደንብና በመመሪያዉ መሰረት በጋራ በመቀናጀት መስራት አለባችሁ በማለት ገልፀዋል ።
የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ግርማቸዉ አስማማው እንደገለፁት የክ/ከተማዉ አመራር ብድን መሪ ባለሙያ የቀበሌ አመራርና ባለሙያዎች በመረዳዳት በመተማመን በመቀነጀት የ2017በጀት አመት ያቀድነዉን እቅድ ዉጤታማ ለማድረግ በቀጣይ ተባብረን መስራት አለብንበማለት ስብሰባውን አጠቃለዋል።

17/08/2024

የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል - ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ

በጎንደር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ወደ ክልሎችም ወርዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ስራው ከተሞችን ወደ ላቀ ምቹና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ፣ አረንጓዴ ልማትን በማስፋትና መሰረተ ልማትን በማሻሻል የህዝቡን ጤና መጠበቅ ብሎም የስራ እድል መፍጠር እንደሆነ በተግባር እየተረጋገጠ ከመጣው የአዲስ አበባ መልካም ተሞክሮ መረዳት ተችሏል።

በክልሎች የኮሪደር ልማት ተግባራዊ እያደረጉ ከሚገኙት ከተሞች መካከል ጎንደር አንዱ ነው።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማቱ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩም ባሻገር የከተማውን ታሪካዊ ስፍራዎች ለማስዋብና ለመጠበቅ ምቹ አጋጣሚ የፈጠረ ነው፡፡

በተለይ ዓለም አቀፍ ቅርስ በሆነው በአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት በቅርብ ርቀት በሚገኙ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች "የቅርሱን አካባቢ መንገዶች የትራፊክ ፍሰት ለማሳለጥና ቅርሱን ከአደጋ ለመጠበቅ የሚረዳ ነው" ብለዋል፡፡

በተለይ በከተማው የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ከትራፊክ አደጋ ስጋት ነጻ የሆነ የእግረኞችና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

''የኮሪደር ልማቱ በህዝቡ ዘንድ የልማት ተነሳሽነት መፍጠር አስችሏል'' ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤ የስራ ባህልን በማጎልበት አዲስ የልማት አውድ የፈጠረ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለኮሪደር ልማቱ ስኬታማነት የይዞታ ቦታውን በፈቃደኝነት ከመልቀቅ ጀምሮ ለልማት ከተፈለጉ ቦታዎች ንብረቶቹን በፍጥነት በማንሳት ቀና ትብብር በማድረግ ማገዙንም አስታውቀዋል፡፡

በከተማው ከመሃል ፒያሳ እስከ ጃንተከል ዋርካ የሚሸፍነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ተሞክሮውን በሌሎች የከተማው ክፍሎች በማስፋት በቀጣይ ተግባራዊ እንደሚደረግ አብራርተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

16/08/2024

በጎንደር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመሰረተ ልማት ዘርፍ አበረታች ስራ መሰራት መቻሉ ተገለፀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ልማት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ታዘባቸው ነጋ እንደገለፁት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመሰረተ ልማት ዘርፍ አበረታች ስራ መስራት መቻሉን ገልፀዋል።

በተጠናቀቀበው በጀት ዓመት የ9 ድልድዮችን ግንባታ ማጠናቀቅን ጨምሮ በከተማዋ በ18 አካባቢዎች የ13 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ጌጠኛ መንገድ ስራ፣ በ6 አካባባቢዎች የ17 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ፣ የ47 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር ዝርጋታ ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የዘመናዊ ቄራ ግንባታ ስራዎች ግንባታ ፣ የወጣቶች ማዕከል ግንባታ ፣ የውሃ ተፋሰስ ስራዎች፣ የነባር የጌጠኛ መንገድ ጥገና ስራዎችና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችዎችን ማከናወን መቻሉን ገልፀል፡፡

በከተመዋ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመሰረተ ልማት ስራዎችን የኮንትራክተሮችን ውል በማቋረጥ በሌላ ኮንትራክተር እንዲጠናቀቁ መደረጉን የገለፁት ምክትል ስራ አስኪያጁ በዋጋ መናር ምክኒያት የተጓተቱ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በህብረተሰብ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲጠናቀቁ መደረጉን ገለፀዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች በኮሪደር ልማት እያሳዩት ያለው ቀና ምላሽ የሚያበረታታ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የከተማዋ የኮሪደር ልማት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Website