አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት Addis Ababa City Bus Service Enterprise
Nearby transport services
Jalan Ekoperniagaan
Magdalena No. 434 Planta Baja, Local C
باب العامود/مقابل فندق القدس
Ismail
Mint Road Fordsburg
Cà Mau
Glen Cove, New York
Muscat
40532
Musaffah
Dubai, Al Ajman
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አዋጅ ቁጥር74/2014 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 144/2015 የተቋቋመ የልማት ድርጅት ነው።
"የቴክኒክ ባለሞያዎች የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምምድ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት ሸግግር እየተደረገ መሆኑ የድርጅታችንን የቴክኒክ አቅም ከፍ ያደርገዋል" ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ሲያደረጉ ገልጸዋል።
በእውቀት የተደገፈ ጥገና ለአዳዲሶቹ አውቶቡሶችን ለማድረግ እና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ የሚያሰችል ስልጠና እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የግብአት አቅርቦት እና የቴክኒክ ምርት አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ኢ/ር አዳነ አብደታ አብራርተዋል ።
ዘመናዊነትን ተረድተው ፈጣንና ውጤታማ የሆነ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ከሃይገር ካንፖኒ በመጡ ባለሞያዎች ለጅርጅቱ የቴክኒክ ባለሞያዎች እየተሰጠ እና የእውቀት ሽግግር አየተደረገ መሆኑ የቴክኒክ ምርት አገልግሎት ዳይሬክተርነት ዳይሬክተር አቶ እሱያውቃል መላኩ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለፁት ስልጠናው በዙር ለሁሉም የቴክኒክ ባለሞያዎች እንደሚሰጥና ITS ፣ ኤሌክትሪክ ፣አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ፣ኤር ብሬክ ሲስተም ፣አንቲ ብሬክ ሎክ ሲስተም እና የመሳሰሉትን ለጥገና ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ላይ ልምምድ እና ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል።
የአንድ ተቋም የአገልግሎት ጥራት ሊመጣ የሚችለው ተቋሙ በሚኖረው የሰለጠነ እና ብቃት ያለው የሰው ሃይል መሆኑን ይታመናል።
በስልጠና የሚያምነው የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር እና ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን የሚያግዘውን ለ5,000 ሰራተኞቹ ስልጠና አሰናድቶ በመስጠት ላይ ነው፡፡
በዚህ ሰፊ የስልጠና ፕረግራም ላይ በዘርፉ አንቱ የተባሉ ምሁራኞች በማሰልጠን ላይ ሲሆኑ ከእነዚህ ምሁራኞች መካከል የድርጅታችን ም/ዋና ስራ አስኪያጅና የፋይናስና ገቢ ምንጭ ማጎልበት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ አንዱ ናቸው፡፡
"የውሰጥና የውጭ ባለጉዳይና ደንበኞቻችን ሊገለገሉ ሲመጡ የመገልገለ ና የመናገር (የመጠየቅ) መብት እንዳላቸው እኛ አገልጋዮች ደግሞ የማስተናገድ እና የማዳመጥ ግዴታ እንዳለብን አውቀን መስራት አለብን"።
አቶ ግዛው አለሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ
ከጅማሬው ገና ከጥንስሱ ሰልጣኔን አሀዱ ብለን ስንተዋወቅ በመጀመሪያው አውቶቡስ ጎዳና ላይ አገልግሎት ይዘን ብቅ አልን።
እነሆ አመታትን ተሻግረን ዘንድሮ ላይ ከዘመኑ ጋር የተናበቡ ለህዝብ ምቾት የሚሰጡ አውቶቡሶችን ይዘን አገልግሎት ላይ አለን።
ከዘመኑ ጋር አብረን ተጉዘን ዛሬ ላይ ደርሰናል
ነገን በተሻለ አብረን ለመጎዝ ስንዱ ሆነን እንቀርባለን።
።
ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ለአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይና ካፒቴኖች ያዘጋጀውን ስልጠና በብቃት ላጠናቀቁ ከአምስቱም ቅርንጫፍ ለተውጣጡ 300 ሰራተኞቹ የምስጋና ምስክር ወረቀት አበረከተ።
በመረሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ከሰራተኞቹ ውይይት ያደረጉት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ከሰራተኝው ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።
ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በሚገባ ስልጠናቸውን አጠናቀው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የደንበኛን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዘውን ስልጠና ለ300 ካፒቴን እና አገልግሎት ሂሳብ ተቀባዮች ለሁለተኛ ዙር መስጠቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ገለፁ።
ዋና ስራ አስኪያጁ በስራ አመራር ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለውን ስልጠና ላጠናቀቁ የድርጅቱ ሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት "ደንበኛን ሊያረካ የሚችል አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዮቻችንን ማሰደሰት አለብን ብለዋል።
ተሳታፊ ሰልጣኞች በበኩላቸው እንደዚህ አይነት ስልጠና ድርጅቱ ማዘጋጀቱን አድንቀው በቀጣይም ለሌሎች የድርጅቱ ሰራተኞች ቢሰጥ ሲሉ ተናግረዋል።
" ስልጠናው የረሳንውን እንድናስታውስ ከማድረግ ባለፈ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ የፈጠረልን በመሆኑ፤ በቀጣይ የተሻለ ስራ እንድንሰራ እና ደንበኞቻችን በጥሩ ሞያዊ ስነ-ምግባር እንድናገለግል አቅም ፈጥሮልናል" ፡፡ ሰልጣኞች
ለመላው የድርጅታችን እንስት ሰራተኞች እና ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) አደረሳችሁ!!
በከተማችን ብሎም በሃገራችን የልማት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ተቋማዊ ዕድገት ላይ የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሆነ የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያምናል።
ድርጅታችን የጀመረውን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ የህብረተሰብ ዕርካታን የማሳደግ ጉዞ ላይ የሴቶች ተሳትፎና ሚና የጎላ በመሆኑ ሁልጊዜም ቢሆን አሳታፊ አድርገን እንሰራልን።
በቀጣይ ሴት አሽከርካሪዎቻችን እና በሁሉም የስራ ዘርፎች ላይ ያሉ እህቶቻችንን በይበልጥ በማበርታትና በመደገፍ አቅማቸውን በማሳደግ የተቋማችንን ራዕይ እናሳካለን።
ለመላው የድርጅታችን እንስት ሰራተኞቻች በሙሉ እንኳን ለዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉን በጠንካራ የሴትነት አቅም እንድናሳልፍ መልዕክቴን በታላቅ አክብሮት ማስተላለፍ እወዳለሁ።
ወ/ሮ ገነት ወልዴ
የህግና ሰው ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ
'' " አቶ ግዛው ዓለሙ
283 የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ድርጅቱ ያዘጋጀውን ስልጠና በተገቢ በማጠናቀቃቸው የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበረከተላቸው።
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለደንበኞች፤ ፈጣን፣ ምቹና ዘመናዊ የሆነ አገልግሎት ለህብረተስቡ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ያለውን ስልጠና ለአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይና ካፒቴኖች እየሰጠ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያ ዙር ሰልጠናቸውን ያጠናቀቁ ባለሞያዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከሰልጣኞች ጋራ ውይይት ያደረጉ ሲሆን "በውይይቱ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ዓለሙ ለተሳታፊዎች "ተገልጋዮቻችን አማራጭ ስላጡ እና ተቸግረው ሳይሆን መርጠውን እንዲገለገሉ ማድረግ አለብን" ሲሉ አደራ በማለት ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ለ5 ሽህ የአገልግሎት ሂሳብ ተቀባይ እና ካፒቴኖች ስልጠና እየሰጠ ነው።
ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር በመተባበር ፤በመንገድ ትራፊክ አደጋና አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ስልት፣የአሽከርካሪ ባህሪ እና ሞያዊ ስነ-ምግባር፣ እና ደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የድርጅቱ ፋይናስና ገቢ ምንጭ ማጎልበት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ ገልፀዋል።
የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰባችን በማቅረብ የደንበኛን እርካታን ለማሳደግ ድርጅታችን ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር የሚሰጠው ስልጠና በዙር የሚሰጥ መሆኑንና ሁሉንም ሰራተኛ ተሳታፊ እንደሚያደርግ የሰው ሀይል አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ወልዴ ተናግረው የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ዛሬ እንደሚያጠናቅቁ ገልፀዋል።
እንኳን ለ127ተኛው የዓደዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
ለመላው የድርጅታችን ሰራተኞች እና ተገልጋይ ደንበኞቻችን በሙሉ እንኳን ለ127ተኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን አደረሳችሁ።
ሄሎ..8981
?
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሚሰጠው አገልግሎት ዙሪያ ለጥቆማና አስተያየት 8981 ነፃ የስልክ መስመር ይጠቁሙ
የሚፈልጉትን መረጃ አሁኑኑ 8981ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ያላችሁ ሃሳብ ፤የጎደለውን ፣መሻሻል የሚገባውን ፣ ጠቁሙን። ሁሌም ለማረም ዝግጁዎች ነን።
?
በቅርበት ቆመናል!
ፒያሳ ፣መገናኛ፣ ሜክሲኮ፣ ጦር ሃይሎች ፣ጀሞ ፣አባዶ፣ ቱሊዲምቱ፣ ኮተቤ፣ አያት፣ አራብሳ ፣ሰሚት፣ እንጦጦ፣ ሰድስት ኪሎ፣ ገላን ፣ቱሉዲምቱ ፣ኮየፈጬ፣ ጎሮ ፣አስኮ፣ አለም ባንክ ፣ቤተል ፣ሰሚት ፣ሲኤምሲ.......ብቻ የእርሰዎን አቅጣጫ ተከትለን በትጋት እናገለግለዎታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ የተሻለ የከተማን ኑሮን ለመፍጠር አብዝቶ ይተጋል!!!
የከተማችንን የብዙሃን ትራንስፖርት ችግር ለመፍታት እና ለማቃለል ሁሌም የሚተጋው ድርጅታችን እነሆ ተጨማሪ ምቾት ያለው የአውቶቡስ አገልግሎት ይዞላችሁ ቀርቧል።
ባሻችሁ መስመር ጉዳያችሁን በሚደግፍ መልኩ ለተገልጋይ ቅርብ ሆነን በሁሉም አቅጣጫ ተሰይመናል።
Moving Faster & safer in the city with our new buses.
።
የሰሚት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በምደባ መመሪያው ዙሪያ ውይይት ማድረጉን የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያስ አለማየሁ ገለፀዋል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሀያ ሁለት በሚገኘው የዋናው መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ባካሄዱት ውይይት ለምደባና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይወክሉናል ያሏቸውን ተወካች መርጠዋል፡፡
በዚህ መሰረት አቶ የደብሩ ዱባለ እና ወ/ሮ ዘነበች ዮናስን የምደባ ኮሚቴ፤አቶ ይፍሩ ክፍሌ እና ወ/ሮ አልባሴን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማድረግ መርጠዋል፡፡
።
የቃሊቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምደባ መመሪያ ዙሪያ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የድርጅቱ የሰራተኞች የምደባ መመሪያ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ መቻሉን የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጁ አቶ መርሻ ሃይሉ ገለፁ፡፡
በዚህ የውይይት ወቅትም የቅርንጫፍ ሰራተኞቹን የሚወክሉ የኮሚቴ አባላት ተመረጠዋል፡፡
አቶ እንዳልካቸው እሸቱን እና ወ/ሮ ምንአስቧል ግዛውን የምደባ ኮሚቴ አድርገው ሲመርጡ አቶ ጋሻው በቀለ እና ኤልሳቤጥ አፈወርቅን ደግሞ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አድርጎገው መርጠዋል፡፡
በመጨረሻም ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ አዲስ የተመደቡ ዳይሬክቶሮች ከቅርንጫፍ ሰራተኞቹ የትውውቅ መርሃ ግብር ማከናቸወናቸውን እንዲሁም ለምደባ ያገለግላሉ ያሉት መረጃ ትክክል ሰለመሆኑ ሰራተኞች አጣርተው እንዲፈረሙ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጁ አቶ መርሻ ሃይሉ አሳስበዋል።
።
የመካኒሳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በምደባ መመሪያው ላይ ተወያዩ።
ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ባካሄደው የውይይት መድረክ የተቋሙ የሰራተኞች የመደባ መመሪያ በዝር ዝር ቀርቦ ሰፊ ውይይት መደረጉን የቅርንጨፍ ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሰፋ አሳውቋል፡፡
ከውይይቱ በኋላ የቅርንጫፍ ሰራተኞቹ ለምደባ እና ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የመረጡ ሲሆን፤ ከቀረቡት እጩዎች መካከል አብላጫ ድምፅ ያገኙት ደርቤ ዳባ እና አብዱልከሪም መሀመድ የምደባ ኮሚቴ፤ እንዲሁም አዲስአለም እና እቴነሽን ደግሞ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማድረግ መርተጠዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ተገኝተው ያወያዩቱ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ሰፋ ሰራተኛው ያለውን ማስረጃ በትኩረት በማረጋገጥ ለውድድሩ ብቁ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የሸጎሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመደባ መመሪያ ዙሪያ ሰራተኞቹን አወያዬ።
ድርጅቱ የምደባ መመራያ ለሰራተኛው በዝርዝር ቀርቦ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን የቅርንጫፉ ሰራተኞችም በመመሪያው መሰረት ይሰሩልኛል ያላቸውን የኮሚቴ አባላትን መርጠዋል።
ከቀረቡት እጩዎች መካከል ከፍተኛ ድምፅ በማሰመዝገብ አቶ ደሳለኝ ጋቢሳ እና ወ/ሮ ነገት ፀጋዬ በምደባ ኮሚቴ እንዲሁም ወ/ት ቤተልሄም ገ/ህይወት እና አቶ ካሳሁን ኮንሶ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሆነው
ተመርጠዋል።
የቅርንጫፉ ሰራ አስኪያጅ አቶ ሙሀመድ ጀማል እንደተናገሩት ሰራተኛው በመመሪያው መሰረት ለውድድር ብቁ ያደርገኛል የሚሉት መረጃ የተሟላ ሰለመሆኑ ማህደራቸውን በአስቼኳይ አረጋግጠው እንዲፈርሙ አሳስበዋል።
የየካ ቅርንጫፍ አመራርና ሰራተኞች በመደባ መመሪያ ዙሪያ ተወያይተው ኮሚቴዎችን መረጡ።
በዛሬው ዕለት በኮኮብ አዳራሽ በተደረገው ውይይት ላይ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ አመራሮች ተገኝተው ምርጫ አከናውነዋል።
የድርጅቱ የምደባ መመራያ በቅርንጫፉ የብዙሃን ትራንስፖርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃነ ከበደ ቀርቦ ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ሰራተኛውም የምደባ ኮሚቴ ሆነው ይሰሩልናል ያላቸውን መርጠዋል።
ከቀረቡት እጩዎች አብላጫ ድምፅ በማምጣት የምደባ ኮሚቴ አቶ ተስፋዬ አለማየሁ እና ወ/ሮ እጅጋየሁ ጌታቸውን እንዲሁም በቅሬታ ሰሚነት ወ/ሮ ሂሩት ተሰፋዬ እና አቶ አቢዮት አበራ ተመርጠዋል።
ውይይቱን ሲመሩ የነበሩት የቅርንጫፉ ሰራ አስኪያጅ ወ/ሮ አክሊለ ታደሰ ለውድድር የሚጠቅማቸውን የሰራተኛ ማህደር በአስቼኳይ አረጋግጠው እንዲፈርሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምችት ያለ ውጤታማ የስራ ቀን ይሁንላችሁ።
ከያንዳንዱ የስኬት መንገድ ጀርባ አገልጋይ ሆንን እንቀርባለን።
Measurement are the key፦
* if you can't measure it. you can't control it
* if you can't control it. You can't manage it
*if you can't manage it. You can't improve it
mulugeta Girma(Dr.)
ለዘመነ የከተማ ኑሮ፣ ጤናማ ለሆነ የንግድ ስርዓት፣ ለማህበራዊ ተሳትፎ፣ ለቤተሰባዊ ግንኙነት፣ አመቺ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ፣ ህይወትን ቀለል ለማድረግ ፣ድካምን ለመቀነስ የብዙሃን ትራንስፖርት (የከተማ አውቶቡስ )ሚና የጎላ ነው።
እኛም ይህን አውቀን በእያንዳንዱ አገልግሎት ጀርባ ሰላማዊ የአውቶቡስ አገልግሎት ለመሰጠት ጠንካራ አገልጋይ ሰራተኞቻችንን ይዘን ተደራሽ ሆነን እንቀርባለን!
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የጥር ወር ጎዞ ገመገመ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የጥር ወር አፈፃፃሙን ምን እንደሚመስል ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ተወያዩ።
በዛሬው ዕለት በማኔጅመንት አዳራሽ በተከናወነው ውይይት የድርጅቱ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስራ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመስራት ያሉ አቅሞችና ለስራ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ አስራሮች ሊታረሙበት በሚችልበት ጉዳይ ላይ ዝርዝር ሰነድ የፋይናንስና ገቢ ምንጭ ማጎልበት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋ/ስራ አስኪያጅ ሙልጌታ ግርማ ዶ/ር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።
በውይይቱ ላይ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ የስራ ምዘና ተግባራዊ እንደሚሆን አውቀው ፤ የአገልግሎት ጥራት፣ የአቅርቦት መጨመር እና ተደራሽነት ላይ መስራት እንዳለባቸው የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ገልፀዋል።
ያለ ዕረፍት በዓመት 365 ቀናት 12 ወራት 1ተጨማሪ የጳጉሜ ወርን ጨምሮ የማያቋርጥ አገልግሎት
በዘመናት መካከል የጎላ አሻራ አሳርፈን ሃገር ገንብተናል! ትውልድ ቀርፀናል ፣ ማህበረሰብ ውስጥ ትዝታ ሆነን ታትመናል፣ ዛሬም ከዘመኑ ጋር ተዋህደን ምቾት ያለውን አገልግሎት ጀባ ብለናል።
ከትላንት የተሻለ አገልግሎት ለመሰጠት አብዝተን እንቀርባለን።
መልካም ቀን
!!
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሁለት አገልጋይ ተቋማት ተዋህደው የተፈጠረ ድርጅት ነው፡፡
ለህብረተሰባችን ከትላንት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በአዲስ አሰራር፣ አደረጃጀት እና መዋቅር ወደ እናንተ እየቀረብን እንገኛለን፡፡
ከተማ አስተዳደሩ የህዝብን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ዘመኑ አምጦ የወለደውን ቴክኖሎጂን አሟጠው የሚጠቀሙ አውቶቡሶችን ግዥ ፈፅሞ ለድርጅታችን አስረክቧል፡፡
እኛም ለህብረተሰባችን ምቹ እና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የአገልግሎት ቁልፉን ተረክበናል፡፡
በመሆኑም አውቶቡሶቹ ከዛሬው እለት ጀምሮ እናንተን ክቡራን ደንበኞቻችን በምቾትና በክብር ለማገልገል ስራቸውን አሀዱ ብለው ይጀምራሉ፡፡
ይህን ምቹ አገልግሎት አውቶቡሶቹ በሚመደቡበት የስምሪት መስመር እንድትገለገሉ ጥሪችንን እያስተላለፍን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅትም በሁሉም የስምሪት መስመሮች እናንተን ክቡራን ደንበኞቻችን ለማገልገል ሁሌም ዝግጁ መሆኑን እየገለፅኩ ፤ የደንበኛን እርካታ ከፍ ለማድረግ ጠንክረን እንደምንሰራ እያሳወኩ፣ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
መልካም ቀን፣ መልካም አገልግሎት!!
ግዛው አለሙ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ
Adis_Ababa_City_Bus
የሸገር ባስ አውቶብሶች ለመምህራንና ትምህርት አመራሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን ከዚህ ቀደም የከተማ አስተዳደሩ የአንበሳ አውቶብስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም በቅርቡ የአንበሳ ባስና የሸገር ባስ ውህደት በመፍጠራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አመራሮች ባደረጉት ውይይት በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ሙያ ላይ የሚገኙ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ከሰኞ ማለትም ከ13/6/2015 ዓ.ም ጀምሮ የሸገር ባስን አሁን እየተጠቀሙበት ባለው መታወቂያ መጠቀም እንዲችሉ ተወስናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሎሎች ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ ከመምህራን የቀረቡ ጥያቄዎችን በተመለከተ በመድረኩ ላይ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ ችግሮችን በጥናት ለመፍታት እንዲቻል አጥኚ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል፡፡(ኮሙኒኬሽን ቢሮ)
ላሻችሁ ጉዳይ፣ ላሰፈለጋችሁ ተግባር ፣በመረጣችሁት ሰዓት ፣ጥራት ያለው አገልግሎት፣ በአዳዲስ ዘመናዊ አዉቶቡሶች። በቅርብ ቀን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Videos (show all)
Category
Contact the business
Website
Address
22 Mazorea/equatorial Guinea Street (adjacent To Mekelit Building), Addis Ababa
Rajshahi Division
Rajshahi Division
PRODUSE FARMACEUTICE TRANSPORT PERSOANE & MARFA(MUTARI) PRODUSE ROMANESTI MOBILA SH TESTERE PARFUM
Rajshahi Division
په هر حال د الله تعالی شکر ګذاره و اوسي 💚 الله تعالی مونږ او تاسې ډېر قیمتي مخلوق پيدا کړی يو، شکراً
Rajshahi Division, 54977
TransportationEZ23! Feel free to message at any time & I will get back to you as soon as possible :D
Rajshahi Division, 40532
Terima jasa angkut barang dalam dan luar kota. Wa : 081322918030