የሶስቱ መልአከ መልዕክት Three Angels Message

አላማችን በራዕይ 14፡6-10 ላይ ያለውን የሶስቱ መልአከ መልዕክት Verified

10/01/2024

ገጿ ሲቀያየር አለም አንዴ ክፉ አንዴ መልካም
ስታስመስል ስታጣጣ ነፍሴን ሲያስጨንቃት በጣም
የአቤሴሎምን ጦር ፈራው ሞቴም አንድ እርምጃ ቀረው
ቃልህን ላነብ ሳነሳው ምክርህ ፅልመቴን አበራው

በሞት ጥላ መካክል ብትረማመድም
በትሬና ምርኩዜ አልከኝ አይለዩህም
በሞት ጥላ መካክል ብትረማመድም
በትሬና ምርኩዜ አልከኝ አይለዩህም

ቃልህን አንብቤ ሰወርኩት በልቤ
ሆኖም አገኘሁት ብርሃን ለመንገዴ
ቃልህን አንብቤ ሰወርኩት በልቤ
ሆኖም አገኘሁት ብርሃን ለመንገዴ

17/07/2022

🌿የስብከት ርእስ- የአስቄዋ ልጆች 🌿
ወንድም ውብሸት ላቀው እንደፃፈው። ከ AY Bible Club የወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ (https://t.me/AYBCLUB)

The Sons of Sceva
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

በሐዋርያት ሥራ 19:1-20 ያለውን ያንብቡ

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

አይ የአስቄዋ ልጆች! ራቁታቸውን በኤፌሶን ከተማ አደባባዮች አጋንንት ከያዘው ሰው ለማምለጥ ሲሮጡ በምናቤ እያየሁ በሌሊት አሳቀኝ! አይ የአስቄዋ ልጆች! የተከበሩት የምኩራብ አለቃ ልጆች መለመላቸውን በከተማው መሃል እግሬ አውጪኝ ሲሉ ማየት የሚደንቅ ነው:: ስለዚህ ሩጫ በዝርዝር ከመግባቴ በፊት ስለኤፌሶን ከተማ ትንሽ ልበል፤-

🌿ኤፌሶን አሪፍ የሆነች የንግድና የመዝናኛ ከተማ ነበረች። አይሁዶችን ጨምሮ ብዙ አይነት አህዛብ ይኖሩባት ነበር። በከተማዋ የጣዖት አምልኮ በስፋት ሲገኝ የአይሁድ ምኩራብም ነበረባት። ከሌሎች ከተሞች ለየት ባለ መልኩ መናፍስትን ማውጣት (exorcism) እና የመናፍስትን ማውጣት ሳይንስ በሰፊው የተንሰራፋባት ከተማ ነበረች። እንዲያውም ሰው ሁሉ በዚህ ተግባር ከመሳቡ የተነሳ መጻሕፍትን እየገዛ ስለ መናፍስትን ማውጣት ይመራመር ነበር።

🌿በዚህ ዘመን ነበር ጳውሎስ በቆሮንቶስ ያለውን አገልግሎት ጨርሶ ወደ ኤፌሶን የመጣው:: በከተማዋ የመጥምቁ ዮሐንስን ስበከት ሰምተው ያመኑ 12 የሚሆኑ ወገኖችን አግኝቶ አዲሱን የክርስቶስን መንገድ ገለጠላቸው። አምነው በኢየሱስ ስም በተጠመቁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።

እንግዲህ የኤፌሶን ቤተክርስትያን ታሪክ በዚህ ይጀምራል። ከልብ ያመኑት በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በሃይል ከተማዋን በወንጌል ይንጧት ጀመር:: ወንጌል በኤፌሶን በመስፋፋት ታላቅና ስመጥር የሆነችው ቤተክርስትያን ተመሰረተች። በፍቅራቸውና ለጌታ ሥራ ባላቸው ትጋት የሚታወቁ ምዕመናን የነበሩባት፤ እንደነዮሐንስ አይነት አገልጋዮች የሰበኩባት ትልቅ ደብር ነበረች። ሥራውም በድንቅና በታምራት የታገዘ ነበር። የእግዚአብሔር ክብር በዚያ ከተማ ባሉት አማኞች ላይ በሃይል በመገለጡ የጳውሎስን ልብስ ጫፍ የሚነኩ ሁሉ ከአጋንንት አንዲሁም ከመንፈሳዊና ከሥጋዊ ደዌ ይፈወሱ ነበር።

🌿በኢየሱስ ስም ሰዎች መፈወሳቸው በከተማዋ ለነበሩ የመናፍስት አውጪ ሳይንቲስቶች አስደንጋጭ ዜና ነበር። ወሬው በከተማዋ መናፍስትን በማውጣት ላይ ወደ ተሰማሩት አይሁዶች ጋር ደረሰ። ከእነዚህ የመናፍስት ሐኪሞች ውስጥ በከተማዋ የምኩራብ አለቃ የሆነው የአስቄዋ ልጆች ይገኙበታል። እነዚህ አጋንንትን በአጋንንት መንፈስ ማስታገስ የለመዱ ወጣቶች የኢየሱስን ስም ተጠቅመው እንደለመዱት ደንበኞቻቸውን ለማስተናገድ አሰቡ። የቀድሞው ዘዴያቸው ፍቱን መድሃኒት እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ጳውሎስ የተጠቀመበትን አዋጭ ዘዴ ለመጠቀም ወሰኑ።

🌿ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ በአጋንንት የተያዘ ሰው ፈውስን ፍለጋ ወደእነዚህ ጎረምሶች መጣ። እነርሱም 'ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ" ስም እያሉ አጋንንቱን ያወጡ ዘንድ ሞከሩ። "ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፡— ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ፡ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ።"

ይህን ታሪክ ሳነብብ "አይ የአስቄዋ ልጆች" እልና ግን ማንነቴን ሳስብ ከእነሱ ብዙም አልለይም::

1. የምኩራብ አለቃ ልጆች

🌿እነዚህ ጎረምሶች (ሁሉም ወንዶች ናቸው) አባታቸው የምኩራብ አለቃ ስለሆነ በተወሰነ መልኮ ከጌታ ቃል ጋር ትውውቅ አላቸው። የቄስ ልጆች ናቸው። የሙሴ መጻሕፍት ሲነበብ፤ ሲዘመር እየሰሙ ቢያድጉም ልባቸው ግን ከጥቅም እንጂ ከእውነተኛው ሃይማኖት ጋር ግንኙነት አልነበረውም። ምናልባት አስቄዋ ራሱ የዚህ ተግባር ተካፋይ ስለሆነም ይሆናል ጥቅም ወዳድ አማኞች ነበሩ። በምኩራባቸው ጳውሎስ የሰበከውን የጌታ ኢየሱስን ወንጌል ሰምተው አልተቀበሉትም። ነገር ግን መናፍስትን በማውጣት የተሻለ ነገርን ያገኙ ዘንድ በማሰብ ያላመኑበትን ሃይል ለመጠቀም አሰቡ።

🌿ሃይል የለሽ እምነት እኮ ነው ጉድ ያረገን ወገን! በቃ ኑሮውን ሳይሆን በረከቱን፤ ዝናውን፤ ጥቅሙን፤ ገንዘቡን፤ እንጀራውን፤ መናውን ብቻ የሚፈልግ ሃይማኖተኛ ሆንን እኮ? ምነው መንፈሳዊ ፍርፋሪ ለምደን ቀረን? መቼ ነው እውነተኛውን፤ ሃይል ያለውን፤ በፍቅር የሚሰራውን፤ የደነደነውን ልብ የሚያቀልጠውን፤ ቤተክርስቲያንን በተሃድሶ የሚያጥለቀልቀውን ክርስትና የምንለማመደው?

🌿ስንቱ የአስቄዋ ልጅ አይደል እንዴ በየቤተክርስቲያኑ ሲያመልክ የሚውለው? ስንቱ የአስቄዋ ልጅ አይደል እንዴ በየሰንበት ሽክ ብሎ መጥቶ የfellowship time አሳልፎ የሚሄደው? ስንቱ ወጣት አይደል እንዴ ቤተክርስቲያንኑ ውስጥ መዝሙር አዘምሮ፤ ፕሮግራም መርቶ፤ ሰብኮ አገልጋይ እየተባለ ረክቶ የሚኖረው? በቃ በኢየሱስ ስም እኮ ነው ዝም ብለም የምንዳክረው? በስሙ የምንነግድ አስመሳይ የአስቄዋ ልጆች ነን!!


2. እናንተ እነማን ናችሁ?

አጋንንቱ የአስቄዋን ልጆች ተጫወተባቸው። "እናንተ እነማን ናችሁ? " በማለት ሰምተውን የማያውቁትን ስበከት ከአጋንንቱ ሰሙ።፡

🌿ስንቶቻችን እንሆን እናምነዋለን የምንለውን ነገር በሚገባ የምናውቀው? ጥቅስ አውጥተን፤ መጽሐፍ ገልጠን የምናስረዳው ስንቶች ነን? ጥቅስ ከጥቅስ አመሳክሮ፤ ጸልዮ፤ በጨለማ ላሉት ልድረስ የሚለው ማነው? We have an identitiy-less generation. We are in an identify crisis. የምሬን ነው! አድቬንቲስት ይሁን፤ ጴንጤ ይሁን፤ ሙስሊም ይሁን፤ ኦርቶዶክስ ይሁን እንኳን የማያውቅ ትውልድ እኮ ነው። ነገሩ ሁሉ የተቀላቀበት ትውልድ እኛ ነን።

🌿በተለይ ሃይማኖተኛ እና ወንጌል አለን ድነናል በምንለው ይብሳል እኮ! የሚዘምርውን፤ የሚሰብከውን፤ የሚጽፍውን፤ የሚደግፈውን፤ የሚቃወመውን ለይቶ የማያውቅ ትውልድ እኮ ነን! ማንነቱን የማያውቅ መልስ ያጣ ትውልድ! እንደ አስቄዋ ልጆች የሆነ ትውልድ። እንኳን ኢየሱስ ሰይጣን እንኳን እነማናችሁ ሲላቸው መልስ የሌላቸው ልጆች ነበሩ። አይ የአስቄዋ ልጆች።

🌿ጎበዝ ይህን ነገር ደግሜ ደጋግሜ የማነሳው ወድጄ አይደለም። በመለየት፤ በቅድስና፤ የጌታን ቃል በማመን የሚያዘዝ፤ ራሱን ዝቅ ያደረገ፤ ራሱን ያዋረደ፤ ለመዝሙርና ለትርኢት ሳይሆን ለወንጌል ሥራ የሚቀና፤ የነፍሳት መጥፋት፤ የመከሩ መብዛት፤ የሰራተኞቹ ማነስ የሚገደው ትውልድ ቤተክርስቲያን ስለሌላት ነው።

ቄሶቻችን ከሰባኪነት ይልቅ አስተዳዳሪ በሆኑበት፤ ምሁሮቻችን ወንጌል ከሚያስፈልገው ሰው ርቀው በየዩኒቨርሲቲውና በየኮሌጁ የተደበቁበት ዘመን ስለሆነ ነው። የሰይጣን ውጊያ በየመንደሩ በጦፈበት በዚህ ዘመን እኛ እየተዋጋን ያለነው በሳተላይትና እና በኢንተርኔት ነው።

👉🏽በሰይፍ ለሚደረግ ውጊያ ቢላዋ ይዘን ተሰልፈናል!! Don’t bring a knife to a sword fight የሚለው ተረት ቢግባን አሪፍ ነበር::

🌿ቤተክርስቲትያንን በወንጌል የሚንጥ አዲስ ትውልድ ያስፈልገናል። ቤት ለቤት የሚሄድ፤ ለታመሙት የሚጸልይ፤ ለተቸገሩት የሚደርስ፤ በየጎዳናው የሚያስተምር፤ በነገሥታትና በአለቆች ፊት የሚቀርብ ትውልድ ያስፈልገናል። በቴለቪዥን፤ በኢንተርኔት ብቻ ተደብቀህ ወንጌል አደርሳለሁ እያልክ ራስህን አትደልል። በሚድያ ያየህ ሰው "ማን ነህ" ብሎ አንተን ፍላጋ መምጣቱ አይቀርም። ለዚህ ማንነታችን፤ አላማችን፤ መልእክታችን፤ ጊዜውን ማዎቅ የግድ ነው።

3. ራቁታቸውን ሸሹ

እነዚህ ሰባት ጎረምሶች አጋንንቱ ከደበደባቸው በኋላ ልብሳቸውን በመግፈፍ ከተማ ለከተማ ያሯሩጣቸው ጀመር። ራቁታቸውን አስባችሁታል? መለመላቸውን በኤፌሶን ከተማ ጎዳናዎች እናወጣዋለን ያሉት አጋንንት ነፍሳቸው እስክትወጣ ያባርራቸው ነበር። አሳፋሪ ነው። ሚስቶቻቸውና ቺኮቻቸው የሚሰማቸውን ሃፍረት አስባችሁታል? ኧረ ይደብራል!

🌿ሃይል የሌለው ኑሮ መጨረሻው ይህ ነው። ውርደት ነው። መገፈፍ ነው። የጽድቅ ልብ የሌለን፤ ያለንም ደግሞ የመርገም ጨርቅ ነው። እሱን ስናምን ጌታ ያለብሰናል። ነገር ግን ስናስመስል እንዋረዳለን። እናፍራለን። ከተማው ሁሉ በአጋንንት አውጭነታችን የሚያውቀን ሰይጣን ሲያባርረን ሲያይ ምን ይላል? ኧረ ይደብራል!

🌿የአስቄዋ ልጆች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ የተቀመጠው በዚህ ዘመን ላለን ሰዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ ነው። በዚህ ዘመን ላለን አስመሳዮች ትምህርት ይሆን ዘንድ ነው። በዚህ ዘመን ላለን ከክርስትና ፍቅርን፤ ጌታን መምሰልን፤ ለሌላው መኖርን ሳይሆን ፍርድን ፈርተን፤ ሰማይ ገብተን ዘላለም ለመኖር ለምንመኝ ፈሪዎች ነው። ይህ ታሪክ የተጻፈው የሚንያብበው ሁሉ የጌታ ኢየሱስን ስም ለርካሽ አላማ መጠቀምን እንዲያቆም ነው።

🌿የጌታ ስም ግን በኤፌሶን ተከበረ። በአስቄዋ ልጆች ወራዳ ስራ የተነሳ ስሙ የተፈራ ሆነ። ከፍታችን እና እውነተኛ እምነታችንን ተጠቅመን ስሙን ካላስከበረን የሰይጣን መጫወቻ መሆናችን አይተው ሰዎች ጌታን የሚያከብሩበት ጊዜ ይመጣል።

👉🏽በኢትዮጵያ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተንሰራፋው የአስቄዋ ልጆች መንፈስ ይሰበር ዘንድ ምኞቴ ነው::

06/07/2022

ከበሮ 🥁ወደ አምልኮ ቤታችን ሲመጣ በሮ

“ማንም በክርስቶስ የሚያምን ሰው አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌው አልፏልና” የሚለውን የ2ተኛ ቆሮንቶስ መልዕክት ያስተዋለ ሰው እንዴት ወደ አሮጌው ተመለሰ? የሚለውን ጥያቄ አጫረብኝ ዛሬ የተመለከትኩት የእኛው ልጆች የዘመሩትን የመዝሙር ቪዲዮ አይቼ። እግዚአብሔር እውነትን አብርቶልኝ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ከጠራኝ በኋላ ለእሱ ክብር እና ለሰው ደንነት እኖር ዘንድ ጠርቶኛል፣ ጠርቶሻል፣ ተጠርተናል።
በቤተክርስትያናችን የምናደርገው እያንዳንዱን አገልግሎት የምናቀርበው ሰማይን እና ምድርን ለፈጠረው ለእግዚአብሔር ነው። በሰማይ ሺህ ጊዜ ሺህ፤ እልፍ ጊዜ እልፍ መላዕክት ያመሰግኑታል፣ ያመልኩታል። አምልኳቸው ምን እንደሚመስል በራዕይ መጽሐፍ 4 እና 5 እዲሁም በተለያየ ስፍራ ተጽፏል። ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ ከበሮ በአምልኮ ስፍራ ላይ ጥቅም ላይ ሲውል አላነበብኩም ያነበበ ሰው ካለ ቢነግረኝ እኔ እንኳን ባልከፍል እግዚአብሔር ወሮታውን ይከፍላችዋል።
በሌላ ቤተክርስቲያን እንደሚደረገው አይነት አዘማመር ወደ እኛ አምልኮ ስፍራችን ማምጣት ከመመልከት በላይ ልብን የሚሰብር ሌላ ነገር የት አለ? እግዚአብሔር የመዝሙር አራራ እንዳለበት አምላክ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” በሚመስል ቢሂል የምናደርገው ነገር ትክክል አይደለም። አንድ በአለማችን ዝነኛ ለሆነ ሰው የሚቀርበው ሙዚቃ እንኳን ተመርጦ፣ ከያኒው ሙዚቀኛ ተመርጦ ነው። እኛ የምንዘምርለት እኮ አለምን የፈጠረው እግዚአብሔር ቅዱስ አምላክ ነው እንዴት ጥሩ መልዕክት ያለውን መዝሙር በእንደዚህ መንገድ ይዘመራል ጐበዝ?
የሌሎችን ሰዎች (በክርስቶስ ኢየሱስ ያላመኑት ሰዎች) ሃሳብ ሳነብ በጣም ቆሰልኩ። ይህ አይነት መዝሙር ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ከመመለስ ይልቅ እነዚሀ ወገኖች የያዙት እምነት ትክክል እንደሆነ እንዲሰማቸው እና እኛ ይልቁንስ ከእነሱ ኮፒ እንዳደረገን ሲያዩ ወደ ክርስቶስ እንዳይመጡ ትልቅ መሰናክል ይሆናል።
እንዴትስ የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ ቄሶች ወዘተ ዝም ብለው ተመለከቱ? በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ትክክል ያልሆነ ነገር ተሰርቶ ወደ አደባባይ ሲወጣ እንዴት አንድ መካሪ ሰው አጣን ግን?
የእስራኤል ጠባቂዎች እንደ ዕውር ውሻ ሆነዋል ይበላሉ ግን አይጮሁም። ኢሳያስ 56፡10-11

እግዚአብሔር ምህረት ያድርግልን።

18/04/2022

አንተ ግን አስቀድመህ ጽድቁን መንግስቱን ፈልግ ሌላው ሁሉ ይጨመርልሃል።

ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ 🙏

27/11/2021

አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል
በሚኪ ሞሲሳ

ክርስቶስ ለእኛ (ሰው ልጆች) ከሰጠን ተስፋዎች ውስጥ አንዱ እና ምናልባትም ዋንኛው የእርሱን ዳግም ምጻት ነው። ከዳግም ምጻቱ አስቀድሞ ግን ሊሆን ያለው ምን እንደሆነ ለማዎቅ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ ኢየሱስ ቀርበው “ንገረን የምትለው ሁሉ መቼ ይሆናል? የመምጣትህ እና የዓለም መጨረሻ ምልክት ምንድነው? አሉት” ይህ ጥያቄ በዘመናችንም ሰዎች ማዎቅ የሚፈልጉት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ነው። ክርስቶስ ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ እየሰጠ እያለ በብሉይ ኪዳን የተፃፈውን አንድ ታሪክ አስታወሳቸው።

“ልክ በኖኅ ዘመን እንደሆነው የሰው ልጅ መምጣትም እንደዚሁ ይሆናል፤ ከጥፋት ውሃ በፊት ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉ እና ሲጠጡ፣ ሲያገቡ እና ሲጋቡ እንደነበሩ እስከዚያ ጊዜ ድረስም ምን እንደሚመጣ ሳያውቁ ድንገት የጥፋት ውሃ እንዳጥለቀለቃቸው የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ላይ ይውላሉ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል። ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች” ማቴ 24፡37-41

ይህ ከላይ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ቃል በቡዙዎች ዘንድ ተጠምዝዞ የተተረጐመ፣ መጻሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ማብራሪያ የተሰጠበት ክፍል ነው። ክርስቶስ እዚህ ክፍል ላይ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል ሲል ምን ማለቱ ነው? ይህንን ጥያቄ በዚህ ጽሁፍ እንመልሰዋለን። ከዚያ በፊት ግን ማስተዋል የሚያስፈልገን አንድ ነገር አለ። ይህም ክርስቶስ እየተናገረ ያለው በኖኅ ዘመን የነበረውን ሁናቴ በመጥቀስ የእሱ ዳግም መምጣትም እንዲሁ ይሆናል በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ለመግለጽ ፈለገ። ስለዚህ በኖኅ ጊዜ የሆነውን ክስተት ለማጥናት ደግሞ ወደ ዘፍጥረት መጽሐፍ ሂደን መመልከት ያስፈልጋል። “በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ደረስ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ **ተደመሰሰ** ከምድርም **ተደመሰሱ**። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን **ቀረ**” ዘፍ 7፡23 እዚህ ክፍል ላይ “... ብቻውን ቀረ” የሚለውን እና ክርስቶስ በማቴዎስ 24 ላይ የተናገረውን እናወዳድር “... አንዱ ይቀራል” ልብ እንበል በሁለቱም መጽሐፍቶች (ማቴዎስ እና ዘፍጥረት) ውስጥ የተጠቀሱት ሁለት ቡድኖች አሉ ከጥፋት ውሃ የተረፉት (የቀሩት) እና በውሃው የጠፉት (የተወሰዱት)። ሌላው ደግሞ ማቴዎስ 24፡40 “በዚያን ጊዜ ...” ብሎ ይጀምራል እራሳችንን መጠየቅ ያለብን የትናኛው ጊዜ? የሚለውን ጥያቄ ነው። መልሱም በዚያው ከፍ ብሎ ቁጥር 37 ላይ ተገልጿል። በኖኅ ዘመን ጊዜ እንደ ማለት ነው። እስኪ ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ይህ “ይወሰዳል” እና “ይቀራል” የሚለው እንዴት እንደተገለፀ አብረን እንመልከት።

"ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማይቱን እንደ ያዙ፥ የከተማይቱም ጢስ እንደ ተነሣ ባዩ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ። ሌሎቹም በላያቸው ከከተማይቱ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፤ አንድ እንኳ **ሳይቀር** ሳያመልጥም ገደሉአቸው።" ኢያሱ 8፡21-22
"ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፥ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ተመለሰ፤ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፥ እግዚአብሔርም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው። ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን ፈረሰኞችንም የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከእነርሱም አንድ ስንኳ **አልቀረም**።" ዘፀ 14፡27-28
"ባርቅም ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረረ፤ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ **አልቀረም።** " መሳፍንት 4፡16
"በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውሩ፥ አትደብቁ። ባቢሎን **ተወሰደች**፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ። ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።" ኤርሚያስ 50፡2-3
"የዚያን ጊዜም ቀንዱ ይናገረው ከነበረው ከታላቁ ቃል ድምፅ የተነሣ አየሁ፤ አውሬይቱም እስክትገደል፥ አካልዋም እስኪጠፋ ድረስ፥ በእሳትም ለመቃጠል እስክትሰጥ ድረስ አየሁ። ከቀሩትም አራዊት ግዛታቸው **ተወሰደ** ፤ የሕይወታቸው ዕድሜ ግን እስከ ዘመንና እስከ ጊዜ ድረስ ረዘመ።" ዳን 7፡11-12

እነዚህ ከላይ ለምሳሌነት የዘረዘርኳቸው ጥቅሶች የሚያመለክቱት **ተወሰደ** የሚለው ተማረከ ወይም ጠፋ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ሌላው **ቀረ** የሚለው ደግሞ ከጥፋት ያመለጠ ወይም ከጥፋት በህይወት የተረፈ ማለት ነው።

ሌላው ነገር ደግሞ ማቴዎስ 24፡41 ላይ የተጠቀሰው “... ሴቶች...” የሚለው ቃል በዋናው (ኦሪጂናሉ ማኑስክሪብት) ላይ የለውም። ይህንን ለማመልከት New King James የኢንግሊዘኛው ትርጉም ያንን ቃል አንጋድዶ (italics) አስቀምጦታል።

ስለዚህ ክርስቶስ በኖኅ ዘመን በውሃ ጥፋት **የተወሰዱት** እና ** የቀሩት** እንደ ነበረ ሲል በኖኅ በኩል የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል የሰሙት ከውሃ ጥፋት እንደቀሩ እና ሌሎች ያላመኑት በውሃ ጥፋት እንደተወሰዱ ሁሉ የሰው ልጅ ሲመጣም አካሄዳቸውን ከአለም **ያስቀሩት** በአየር ላይ ከክርስቶስ ጋር በመገናኘት ሺህ አመት ይነግሳሉ። በተቃራኒው በእርሱ ያላመኑ ሰዎች ሺህው አመት ሲፈፀም የመጨረሻ ዕጣፈንታቸው በእሳት ባህር **መወሰድ** ይሆናል። ራዕ 20፡15። አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች መገዛት አይችልም ያለው ጌታ ለዚህም አይደለ?

እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

21/09/2021

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈው በልሳን መናገር እንዴት ያለ ቋንቋ ነው? የሚታወቅ ወይስ የማይታወቅ? በዘመናችን ያለው በልሳን መናገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወይስ አይደለም? በ1ቆሮ 14 ላይ ያለው በልሳን መናገርስ? እነዚህን እና ሌሎችንም ጥያቄዎች የሚመልስ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ ትንታኔ የሚሰጥ መጽሐፍ በቀርብ ቀን።

ዋጋው፡ በነፃ

Want your business to be the top-listed Media Company in Tallinn?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

አካሔዴ ተበላሽቶ...
I must have tell Jesus
መጣው ወደ ማስቀልህ
መልካም ሰንበት
ከፀሐይ ማዶ መዝሙር

Category

Address


Kalevipoja 2
Tallinn
13625
Other Media in Tallinn (show all)
Vuuduu Media Vuuduu Media
Tallinn

An effective marketing campaign works best when print is integrated with other digital solutions. In fact, research has shown print’s ability to increase ROI by as much as 240%.

Eesti Majandusmeedia Eesti Majandusmeedia
õismäe Tee 199-9
Tallinn, 13517

Julgetele ja iseseisvatele; arukatele, kuid mitte ahnetele Majandusuudised omas mahlas toimetaja: Pe

Rikas Geenius Rikas Geenius
Volta 1
Tallinn, 10412

Rikas Geenius on investeerimisportaal, mis toob Sinuni praktilised ideed raha paigutamiseks.

Chatnewstv Chatnewstv
Tallinn

ChatnewsTV is an Independent African Online Multimedia Network https://buymeacoffee.com/chatnewstv

Journo Birds Journo Birds
Tallinn

Estonian journalists, trying to understand Moldova. Every month, we travel around this European country. We speak to Moldovans, we write about them, we film them. Find the stori...

ZeitEcht Verlag ZeitEcht Verlag
Sepapaja Tn 6
Tallinn, 11415

Mytv.ee Mytv.ee
Tallinn, Tehnopol Akadeemia Tee 21/1
Tallinn, 12618

MyTV siseraadio, sisetelevisioon ja meediahaldus. Teisaldatavate ekraanide müük ja rent. MyTV digital signage and internal radio.

Tourist Map Estonia Tourist Map Estonia
Tartu Maantee 63
Tallinn

Meediaagentuur. Tegevusalaks turismikaartide koostamine ja levitamine.

Kaubandus.ee Kaubandus.ee
Vana-Lõuna 39/1
Tallinn, 19094

Kaubandus.ee on Äripäeva teemaveeb Eesti kaubandusvaldkonna otsustajatele.

AVP Stuudio AVP Stuudio
Fr. R. Faehlmanni 12
Tallinn, 10125

AVP Stuudio kohandab audiovisuaalseid teoseid peamiselt Eesti keelde. AVP Stuudio provides adaptation services into Estonian language of audiovisual content.

Tissident Tissident
Tallinn

Tissident podcast koosneb kahest värvikast naisest, kes pole suu peale kukkunud ning arutlevad teemade üle, mis parasjagu pähe tulevad. Kõik taskuhäälingus räägitud lood, nimed j...

PÄRING.ee PÄRING.ee
Tallinn, 11314

Uued- ja kasutatud varuosad, teenused, pesula, service, värvimine, rehvid, klaasid, elektritööd jne.