Orthodox Young Unity 1

ይህ ፔጅ የተዘጋጀው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን መምህራን የሚዘጋጁ ነገር

Photos from Orthodox Young Unity 1's post 05/02/2023

🙏🙏🙏"እየሞቱ መብዛት"🙏🙏🙏

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳሰነችኛ #ቋንቋ ቅዱስ ወንጌልን ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል 1182 አዳዲስ አማንያን ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ እና ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ በተገኙበት በኦሞ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት በማግኘት የቤተ ክርስቲያን አባላት ሆነዋል፡፡

🙏አማኑኤል ሆይ ድልን ስለተቀዳጁ ሰማዕታት ሕይወትን ስላገኙ ነፍሳት እናመሠግንሃለን🙏

04/02/2023

ሠርፀ ፍሬስብሃት!

04/02/2023

"ይለመነናል ዓምላከ አብርሃም
ይታደገናል መድኃኒዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋ እና ዖሜጋ"

29/01/2023

"የሄሮድስ እና የጲላጦስ ማህተም ይፈታል፣የሀና እና የቀያፋ ድንፋታ ያከትማል፣የተበተኑ ሀዋርያት ይሰበሰባሉ፤እስቀመጨረሻ የፀናው ዮሀንስ ትንሳኤውን ያያል፤ አርብ ያልፋል፣እሁድ ይመጣል፣የተቀበረው እውነት(ኢየሱስ) ይነሳል።"

29/01/2023

🙏ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሠግንሻለች🙏

"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሳኤ የተፅናናችው፣ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሠግንሻለች🙏
በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውሃ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሠግንሻለች🙏 የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት፣ መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሠግንሻለች🙏"

አባ ዘጊዮርጊስ ዘጋስጫ

Photos from Orthodox Young Unity 1's post 28/01/2023

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


“በዓለም ሳለችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” 【ዮሐ 6፥33】

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የአንድነት ገዳማት ኅብረት መልእክት

ከቅዱስ ፓትርያርካችን ጀምሮ በየደረጃው ያላችሁ የመንጋው እረኞቻችንና ሕዝበ ክርስቲያን፣ ለአኀት አብያተ ክርስቲያናት፣ እውነተን ለምትፈልጉ እና ለምትከተሉ የሰው ልጆች በሙሉ ሰላምታችን ከያለንበት ቅዱሳን መካናት ይድረሳችሁ።
የምናስተላልፈውን መልዕክትም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጊዜያችሁን በመስጠት እንድትመለከቱት እኛ ታናሽ እና ደካማ የሆን ገዳማውያንና ገዳማውያት በአምላከ ቅዱሳን ስም
እንማጸናችኋለን፡፡

መልዕክታችንም ለሚከተሉት አካላት ይሆናል፡ -

፩. ለቅዱስ ፓትርያርካችን፡ - እስካሁን በአደረጉት በዕንባ የታገዘ የእረኝነት ተግባርዎት የረዳዎትን አምላክ እናመሰግናለን ወደፊትም እንለምናለን፡፡ ነገር ግን ይህ የተቀደሰ የመንጋው ጥበቃ ተግባርዎት በዚህ ከባድ የፈተና ጊዜ ይበልጡኑ ከዕንባዎት ጋር ለእርስዎ እና ለእኛ ይሆን ዘንድ እስከ አሁን ድረስ ከባዱን ፈተና ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደተወጡት አሁንም እግዚአብሔር በሚወደው እውነት ብቻ ጸንተው እንዲቆሙ እና በዚህም የሚቀበሉት መከራ ካለ የእውነተኛ እረኛነት ምድራዊ ደሞዙ ይኸው ነው እና ከእረኝነትና አባትነት ተግባርዎ አንዲትም እርምጃ ወደ ኋላ እንዳያፈገፍጉ እኛ ደካማ ልጆችዎት በቅዱሳኑ ስም እንማጸንዎታለን፡፡

፪. ለብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፡ - እስካሁን በዘመነ ሲመተ ክህነታችሁ ክፉውንም በጎውንም አሳልፋችኋል። የአሁነ ግን ከሁሉ የከፋ ይመስላል፤ የሚከፋው ግን በእውነት በመኖር እና ለእውነትም የሚከፈለውን መከራ የምትሸሹ የምታፈገፍጉ ከሆነ እንጂ በእውነት ላይ ለእውነት ከቆማችሁ እናንተም ከብራችሁ ቤተ ክርስቲያንንም የምታስከብሩበት ጊዜ አሁን ስለሆነ ደስ ሊላችሁ ይገባል። ይህ ግን ፍርሐትን፣ምቾትን፣ማስመሰልን ይጠላል በምትኩም

ጥብአት፣መከራ እና እውነት ይስማማዋል። ስለዚህም የእስካሁኑን ሁሉ ድክመታችሁን አስወግዳችሁ ማስፈራሪያቸውን ሳትፈሩ እውነትን እንድትገዟት እንጂ እንዳትሸጧት ደካሞች ልጆቻችሁ አደራ እያልናችሁ ምናልባትም አንድ አንድ ደካማ ጎኖችንና ማስመስያን እየፈለጉ የሚጠቃቅሱ ቢኖሩም በምትባሉት ነገር ሁሉ ግድ ሳይሰጣችሁ ለመንጋው እረኝነት ያበቃቻችሁን ቤተ ክርስቲያን ከማስከበር የበለጠ ምንም ተልዕኮ እንደማይኖራችሁ ታውቃላችሁና እውነትን በመኖር ለእኛ ለበጎቹ ምሳሌ ሁኑን፡፡

በቅድሚያ ስለልጅነት ድፍረታችን ይቅርታ አድርጉልንና ይህ ሁሉ የሆነው በእናንተ በእረኞቹ እና በእኛ በበጎቹ የክርስትናውን ዓላማ እና ተግባር እንደሚገባ ያለመኖር ነው፡፡ ስለሆነም ወደፊት እንዴት መኖር እንደሚገባን ከራሳችሁ ጋር እና በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ምከሩ። እኛንም መንገዱን በማሳየት ምሳሌ ትሆነን ዘንድ ደካሞች ልጆቻችሁ በቅዱሳን ስም እንማጸናችኋለን፡፡

፫. ሲመተ ኤጲስ ቆጶስ ሰጥተናል ላላችሁ ሊቃነ ጳጳሳት እና “ኤጲስ ቆጶስነት ተሹመናል" ላላችሁ መነኮሳት፡ - በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የፈጸማችሁት ተግባር ስህተት መሆኑን እኛ ደካሞች ገዳማውያን በትህትና ድፍረት ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም ያለው አማራጭ ሁለት ነው - አንደኛው በፍጹም ንስሐ ያሳዘናችኋትን ቤተክርስቲያን ደስ ማሰኘት እና እናንተም ምድራዊ እና ሰማያዊ ሰላም ማግኘት፤ ሁለተኛው ደግሞ ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን አንድነት መለየት ነው᎓᎓ ነገር ግን ሁለተኛው አማራጭ ለእናንተም ለእኛም ሀዘን ነውና የመጀመሪያውን አማራጭ ...

25/01/2023

«ነፍሴን አስይዤ እፋለማለሁ፣ የአባቶች አደራ አለብኝና'»

እኔ መጀመሪያ ስሾም የቀደስኩት በኦሮሚኛ ቋንቋ ነበር ብዙ አገልግሎቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ ነው የምናከናውነው። የነዚህ ሰዎች አላማ ምንድነው? ቅዱስ ሲኖዶስን ማክበር ያስፈልጋል።

ከዛ ያፈነገጠ አካሄድ ከባድ መለኮታዊ ቅጣት አለው። እኔ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን፥ በአንድ ቤተክህነት አምናለው ከዚህ ውጭ የሚደረግን እንቅስቃሴ ነፍሴን አስይዤ እፋለመዋለው የአባቶቼ አደራ አለብኝና።

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና የምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ አባታችን በረከታቸው ይደርብን።

24/01/2023

***************************************************

"መንግሥት ቤተ ክርስቲያንና አባቶችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ልጆቻቸው ለመጠበቅ ተዘጋጅተናል፤ በቂ ዝግጅትም አድርገናል።"
የመንፈሳዊ ማኅበራትና የኅብረቶች የጋራ መግለጫ
ዛሬ ጥር 16 ምሽት ማኅበረ ቅዱሳን፣ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት፣ ምእመናን ኅብረት ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በጋራ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም የማኅበራቱ ተወካዮች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካጋጠማት ታሪካዊ ክስተት አንጻር ከመቼውም ጊዜ በላይ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና የምናስጠብቅበት እና ከአባቶቻችን ጎን የምንቆምበት ወቅት በመሆኑ በኅብረት መክረን አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳንን ወክለው የተገኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም በመግለጫው እንደተናገሩት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ያቃለለ የነገ የሐዋርያዊ አገልግሎትን ያሰናከለ በመሆኑ አባቶቻችን ይህንን ያማከለ ውስኔ እንዲወስኑ እንጠይቃለን ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም መንግሥት እጁን ከዚህ ሂደት እንዲያነሳ ይልቁንም የእሱ ግዴታ የሆነውን ጥበቃ እንዳያነሳ ይህ ካልሆነ ግን ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን እስከሰማእትነት ለመታደግ የታመኑ ናቸው ብለዋል። ምእመናንም ሳይደናገጡ በጸሎት እንዲተጉ እና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከመንግሥት ጋርም በቀጣይ ችግሩን እንዲረዳና ቤተ ክርስቲያን የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ እድል እንዲሰጣት መወያየታቸውን በመግለጽ የዜጎችን ደህንነት ካልጠበቀ ግን ከተጠያቂነት አይድንም ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ ያደረገን ድርጊቱ ሕገ ወጥ መሆኑና ሀገርና ቤተ ክርስቲያን የሚንድ በመሆኑ ነው ያሉት ደግሞ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት ተወካይ አቶ ያሬድ ዮናስ ናቸው። ችግሩን ከማወገዝ ባለፈ ከእኛ የሚጠበቀውን ለማድረግ ተዘጋጅተናል፤ በእያንዳንዳችን መዋቅርም ስራዎችን ለመስራትም ተነጋግረናል ብለዋል።

የምእመናን ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳ ቤጥ አምዴ በበኩላቸው ውይይት በአንድ ሃሳብና ልብ መከናወኑን ገልጸው ቅዱስ ሲኖዶስ ተደፍሯል፣አባቶች ተደፍረዋል፤ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ካለችበት ችግር ለማውጣት ሁላችንም በቁርጠኝነት ተነስተናል ብለዋል። በውይይታቸውም በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንደማይደራደሩ አፅንዖት መስጠታቸውን ተናግረዋል።

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በአባቶች ላይ የተቃጣውን ለመመለስ በአባቶቻችን ጥሪና መመሪያ ተመስርተን ለመሄድ ቃል ገብተናል ያሉት ደግሞ የጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ተወካይ አቶ አያልነህ ተሾመ ናቸው። አክለውም ይህ የህልውና ጉዳይ ሀገር የማፍረስ ጉዳይ በመሆኑም ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።

የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ተወካይ ወ/ት ፌቨን ዘሪሁን በበኩላቸው ዛሬ በነበረን ውይይት ሁላችንም ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንድንሆንና የድርሻችንን ለመወጣት መስማማታቸውን በመግለጽ ለዚህም የአባቶችን መመሪያ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸዋል።

የቅድስት ቤተ ክርስትያንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተው ለማስረዳት ዝግጅት መጨረሳቸውንም በመግለጫቸው ገልጸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መንግስት ከለላውን አንስቷል ሲሉ ዛሬ ምሽት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ምንጭ EOTC MK

24/01/2023

"እኛ የመነኮስነው ለፍትፍት እንጀራ አይደለም"

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

ምንጃር ጎዳና
Adama
Other Education Websites in Adama (show all)
Mohii Qoute Mohii Qoute
Ginnir
Adama, 33

#Harmee

BichenaTvt BichenaTvt
Adama, 01

BICHENA

Uff ta'uu Uff ta'uu
Adama

Uff ta'uu page is descibes about what I post on this blogs

Akkaadaamii Afaan Oromoo Akkaadaamii Afaan Oromoo
Jeneral Tadese Biru
Adama

Afaan Oromoo

መንእሞ ይኽእሎ መንእሞ ይኽእሎ
Adama

to Get Information

Mudasir ahmed chala Mudasir ahmed chala
Adama City
Adama, BOLE

الإسلام ه‍و السلام

Ustaaz Abdallaah Idris Ustaaz Abdallaah Idris
Adama

Page kanarratti fedha Rabbiitiin da'awaalee gara garaatii fi barnoota adda addaa ni arkattu.

Malkaa media Malkaa media
Dadar
Adama, 19

kaayyoon keenya barannee barsiisuudha

ASTU STEM Center ASTU STEM Center
Kebele 14 Adama
Adama, P.O.BOX1888

The primary purpose of the Center is to inspire middle, high school, and university students as well as others to pursue science, technology, and engineering hobbies, academics, an...

General knowledge General knowledge
Adam
Adama, ADAMA

Educational and science, technology

Islaamummaan Faaya jireenyaati Islaamummaan Faaya jireenyaati
Adama

Amantiin tiya Islaamaa sabni ko Oromo Biyyii to Oromiyaa