Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia

The Ministry of Irrigation & Lowlands (MILLs) is FDRE's Ministry established in 2021.

The Ministry of Irrigation & Lowlands (MILLs), is a government institution established in 2021, mainly to ensure sustainable development by expanding irrigation infrastructure and to improve the lives of citizens living in lowland areas.

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 09/12/2023

የአመራርነት ስልጠና ለሴት መካከለኛ አመራሮችና ሰራተኞች ተሰጠ
ህዳር 29/2016 ዓ/ም፣ አዳማ
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ከቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ ዶሻ ሆቴል በአመራርነት ፅንሰ ሃሳብ ፣ የአመራርነትና ስርዓተ ፆታና የአመራርነት ክህሎት ላይ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡት ሴት ከፍተኛ የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ስልጠናው ተሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የአመራርነት ፅንሰ ሃሳብ ፣ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት አስፈላጊነት እንዲሁም ሴቶች ወደ አመራርነት እንዳይመጡ የሚያደርጉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ አሰልጣኝዋ ወ/ሮ ኤቨሪና ወ/መስቀል አብራርተዋል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ወ/ሮ አሊማ ባድገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ እንዳሉት በዚህ ስልጠና እንደተገነዘብኩት ብዙ አመራር ሊሆኑ የሚችሉ ሴት ሰራተኞች እንዳሉ ተገንዝበናል፡፡ለወደፊቱም አቅማችንን በማንበብ ማብቃት ይገባናል ፡፡በፎረማችንም በየጊዜው እየተገናኘን መወያየትና መማማር አቅማችንን ማበልፀግ ይገባል ፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናው ያለባቸውን የአቅም ክፍተት እንደሚቀርፍላቸው በመግለፅ ስልጠናው እንዲሰጥ ያሥተባበሩትን አካላት እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 08/12/2023

የሴቶች ፎረም የስራ አስፈፃሚና የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ አመራሮች ምርጫ ተካሄደ፡፡
ህዳር 28/2016 ዓ/ም ፣አዳማ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በአዳማ ከተማ በዶሻ ሆቴል በተካሄደው የሴቶች ፎረም መድረክ ላይ የፎረሙን ስራ አስፈፃሚና የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴን ለማጠናከር የአመራሮች ምርጫ ተካሂደዋል፡፡ምርጫውን ማካሄድ ያሥፈለገበት ምክንያት ፎረሙ ከተመሰረተ ሁለት አመታት የሞላው በመሆኑና በደንቡ ላይ በየሁለት ዓመት ምርጫ እንደሚካሄድ በመደንገጉ ነው፡፡
ምርጫውን ለማካሄድ በመጀመሪያ ሶስት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ከተካሄደ በኃለ የሥራ አስፈፃሚና የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ ጥቆማ ተካሂዶ በድምፅ ብልጫ አምስት የስራ አስፈፃሚ አመራር አባላት እና የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ተለይተዋል፡፡
የፎረሙ ስራ አስፈፃሚ አመራር አባላት
1.ወ/ሮ ለምለም ተስፋዬ …… ሊቀመንበር
2.ወ/ሮ ሙሽራ መኮንን….. .. ምክትል ሊቀመንበር
3.ወ/ሮ ዕፀገነት ጌታቸው……... ፀኃፊ
4.ወ/ሮ ያለምዘርፍ ላመስግን….ገንዘብ ያዥ
5.ወ/ሮ ሰዓዳ ሃሰን……………. አባል
እንደሁም የኦዲትና ቁጥር ኮሚቴ አመራር አባላት
1.ወ/ሮ ባንቺዓምላክ ስለሺ……ሰብሳቢ
2.ወ/ሪት ነፃነት ተስፋዬ…………ፀኃፊ
2.ወ/ሮ አጀቡሽ ተሰማ…………...አባል ሆነው ፎረሙን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡
የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ርክክብ በቀድሞ የፎረሙ ሊቀመንበር ወ/ሮ ጫልቱ ሳሙኤልና በወ/ሮ ለምለም ተስፋዬ አዲስዋ የፎረም ሊቀመንበር መካከል ተደርገዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 08/12/2023

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች ፎረም መድረክና የአመራር ስልጠና እየተካሄደ ነው፡፡
ህዳር 28/2016 ዓ/ም ፣አዳማ
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ከቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የሴቶች ፎረም መድረክና የሴት አመራሮችና ሰራተኞች አመራር ስልጠና በ28/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በአዳማ ዶሻ ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አሊማ ባድገባ እንዳሉት የሴቶች ፎረም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመ ሁለት ዓመታትን ያለፈ በመሆኑ አመራሩን የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡በተጨማሪም በሚ/ር መ/ቤታችን ከቡድን መሪ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ አመራር ድረስ ያሉት ሴት አመራሮች ቁጥራቸው በጣም አነስተኛ ነው በማለት በተቋሙ በተደረገው ዳሰሳዊ ጥናት መሰረት ሴቶች ወደ አመራርነት መምጣት ያልቻሉት ምክንያት የአቅም ማነስ፣ ዕድል ያለማግኘትና የጠባቅነት ችግሮች እንዳሉ መገንዘብ ተችለዋል፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ የአመራርነት ስልጠና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡ ሴት ከፍተኛ ባለሙያ ስልጠናው እንዲሰጥ ጥረት በመደረጉ ዛሬ ይህ ስልጠና ስለሚሠጥ በትኩረት መከታተል አለብን፡፡
የሴቶች ፎረም መድረክና የአመራርነት ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ እንዳሉት በዚህ መድረክ የሴቶች አደረጃጀትን (ፎረሙን) ማጠናከር ከሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት አንፃር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሲሆን በኢኮኖሚያዊ ፣በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች የሴቶችን አደረጃጀት ማጠናከር ለሴቶች ተጠቃሚነት መረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ በአስፈፃሚ አካላት የሚወጡትን የልማት ፖሊሲዎች ፣እስትራተጂዎች ፣ህጎች፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ታቅደው ሲተገበሩ የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት በተገቢው መካተታቸውንና መተግበራቸውን ለማረጋገጥ ፣ለመታገል እንዲሁም ህገ መንግስታዊ የሴቶች መብቶች በትክክል ተግባራዊ መደረጋቸውን ማረጋገጥ የሚቻለው በተደራጀ አኳኃን ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ የመ/ቤታችን የሴቶች ፎረም በአዲስ መልክ አጠናክረን በማደራጀት ጉድለቶቻችን አርመን ጥንካሬያችንን የበለጠ አጠናክረን ተሳትፎዓችንን ከፍ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም ያሉትን ክፍተቶችም ለመቅረፍ የአመራርነት ስልጠና ለሴት አመራሮችና ሰራተኞች መሰጠቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 07/12/2023

የአሁኑ ትውልድ ተጋድሎ አገራችንን ከድህነት አውጥቶ የበለፀገች ማድረግ ነው፡፡
ህዳር 27/2016 ዓ/ም ፣አዲስ አበባ
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የ18ኛው የብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ብዝሃነታችንና እኩልነት ለሃገራችን አንድነት” በሚል መሪ ቃል ህዳር 27/2016 ዓ/ም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት በተከበረበት ወቅት የአሁኑ ትውልድ ተጋድሎ አገራችንን ከድህነት አውጥቶ የበለፀገች ማድረግ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በዓሉ በተከበረበት ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ እንዳሉት ብዝሃነታችንና እኩልነት ለአገራችን አንድነት መሰረት ነው ካሉ በኃላ አባቶቻችን አገራችንን መስዋዕትነት ከፍለው በአንድነትዋ ያቆዩ ሲሆን የአሁኑ ትውልድ ተጋድሎ አገራችንን ከድህነት አውጥቶ የበለፀገች ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሪዋ እንደገለፁት ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት አላቀን የአገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራሮችና ሰራተኞች ትልቅ ኃላፊነት አለብን ፡፡በመሆኑም ጠንክረን ከሰራንና ኃላፊነታችንን በአግባቡ ከተወጣን ውጤታማ እንሆናለን ፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ትልቁ ኃላፊነት የውሃ ሃብታችን ለመስኖ ጥቅም ላይ እንዲውል በመሆኑ ጠንክረን ለመስራት ቃል የሚንገባበት ቀን ነው ፡፡ስለሆነም ሚኒስቴር መስሪቤታችን በወንድማማችነት ፣እህታማችነትና በመተሳሰብ ቃላችንን አድሰን የተሰጠንን ተልዕኮ ከደር እናደርሳለን ፡፡

በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የ18ኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመሪ መልዕክት፣ በመወያያ ሰነድ ገለፃና ውይይት ፣በዳቦ መቁረስና ሻማ ማብራት እንዲሁም በጥያቄና መልስ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተከብረዋል፡፡
የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ከ1-3ኛ ለወጡትና ለተሳታፊዎች እንደ ደረጃቸው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 07/12/2023

የመስኖና ቆላማ አካባቢ አመራሮችና መላ ሰራተኞች በተገኙበት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን "ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል። የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሀመድ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ የተሰጠን ሀገራዊ ተልእኮ ለማሳካት ለብዝኃነታችን እውቅና ሰጥተን አንድነታን በማጠናከር ተግተን በመስራት ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅብን አሳስበው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

06/12/2023

የ18ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሚኒስቴር መ/ቤቱ ይከበራል፡፡
ህዳር 26/2016 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የ18ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ህዳር 27/2016 ዓ/ም ከ7፡30 ጀምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በሚ/ር መ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 06/12/2023

በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውሃ ፓምፕ ሲስተም አጠቃቀም ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 26/2016 ዓ/ም ፣አዲስአበባ
በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውሃ ፓምፕ ሲስተም አጠቃቀም ስልጠና ከህዳር 10-21/2016 ዓ/ም ሲሳተፉ የነበሩ አራት (4) የሚኒስቴር መ/ቤቱ ባለሙያዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው ሠርተፍኬት ተበርክቷላቸዋል፡፡ ሠልጣኞቹ በቆይታቸው ውጤታማ እንደነበሩና ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት መሙላት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ ስልጠናዉ የመስኖ ዘርፍን ለማዘመን የተያዘዉን ዉጥን ከማሳካት አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 02/12/2023

የአርብቶ/ከፊል አርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የአርብቶአደር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓትን በቁርጠኝነት መተግባር ይገባል ተባለ፡፡
ህዳር 22/2016 ዓ/ም፣ አዳማ
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት ለሚኒስቴርና ክልሎች መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የአርብቶአደር ኤክሰቴንሽን አገልግሎት ሥርዓት ማኑዋል እንዲሁም የአርብቶ አደር እንስሳት ኤክስቴንሽን እና የአርብቶአደር የመስክ ትምህርት ቤት ስልጠና በተሰጠበት ወቅት የአርብቶ/ከፊል አርብቶአደሩን ኑሮ ለማሻሻል የአርብቶአደር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓትን በቁርጠኝነት መተግባር ይገባል ተባለ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ የእንስሳት ኤክስቴንሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ፀጋው በአርብቶአደር እንስሳት ኤክስቴንሽን እና የአርብቶአደር የመስክ ትምህርት ቤት ላይ ገለፃ ባደረጉት ወቅት የተለያዩ ሃሳቦችና ጥያቄዎች እንደ የእንስሳት ተዋፅዖ አጠቃቀምን በቴክኖሎጂ መደገፍ ፣ ውሃን ማዕከል ያደረገ ልማት ማተግበርን፣ በቅንጅትና በተናበበ ሁኔታ ለመስራት ጥረት ማድረግን፣ የእንስሳት መኖን በቴክኖሎጂ በመጠቀም ማከማቸትን ፣ የግጦሽ መሬት አጠቃቀም ዘመናዊ ማድረግን፣ የተሰጡት ስልጠናዎች እስከታች እንዲወርዱ ጥረት ማድረግን፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት መዘርጋት፣ ሴክተሩ ከላይ እስከታች ወጥ በሆነ ሁኔታ ቢደራጅ ወዘተ በስፋት ተነስተዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ኤክስቴንሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ፀጋው እንዳሉት አብዛኛው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ግብዓት የሚሆኑ ናቸው በማለት በፌዴራልና በክልል እንዲሁም እስከታች የመስተዳድር እርከን ያሉት ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በተናበበ ሁኔታ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡ በአርብቶአደርና ከፊል -አርብቶአደር አካባቢዎች ዝሪያቸው የተሸሻሉ እንስሳት በማስፋፋት ከእነርሱ የሚገኘውን ተዋፅዖ በፀሃይ ብርሃን ኢነርጂ በመጠቀም ማቆየትና ወደ ገበያ ማውጣት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሰራት ይገባል፡፡
የአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ አባ በተሰጠው ስልጠና ናውይይት በአርብቶአደር አካባቢ ያለውን ችግር እንደ መኖ ልማትና አጠቃቀም፣ የግጦሽ መሬት ልማትና አያያዝ፣ እንስሳት ልማትና ጤና አጠባበቅ ፣ ተፈጥሮ ሃብት ልማትና እንክብካቤ ፣የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅና የንፁህ ውሃ አቅርቦት በደንብ መገንዘብ የቻልንበት እና መሰራት ያለበትም እታች ቀበሌ ላይ በቅንጅትና በተናበበ ሁኔታ መሆኑን ተገንዝበናል ለተግባራዊነቱም ሁሉን አቀፍ በሆነ ሁኔታ ለመስራት ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሚ/ር መ/ቤታችን የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን እና ብሄራዊ ባንክ ያለበት ፕላት ፎርም ያቀፈ ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ ነው በማለት በመጨረሻም ያገኘነውን ስልጠና ከአሁን በፊት ያቀድነውን እቅድ ለመተግበር ሊንጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 02/12/2023

ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ይበልጥ ሊሰሩ ይገባል
ህዳር 22/2016 ዓ/ም፣ አዳማ
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት ለሚኒስቴርና ክልሎች መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የአርብቶአደር ኤክሰቴንሽን አገልግሎት ሥርዓት ማኑዋል ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይበልጥ በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ ፡፡
በተሰጠም ስልጠና ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎዋል፡፡በውይይቱም ወቅት የተነሱት ዋናዋና ሃሳቦች የግምገማና ክትትል ድጋፍ የተቀናጀ ቢሆን፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ቢሰሩ ፣ የአርብቶአደሩ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማስፋት ላይ ትኩረት ቢሰጥ ፣ ጥናቶች ወደ ታች ወርደው አርብቶአደሩን ተጠቃሚ ማድረግ ቢቻል፣ የአርብቶአደር ማሰልጠኛ ተቋማት አጠቃቀምን ማስፋፋት ቢቻል ወዘተ ናቸው፡፡
በተነሱት ሃሳቦች ላይ አቶ ዳንኤል ደንታሞ በግብርና ሚኒስቴር የኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ በማጠቃለያ ሃሳባቸው እንዳሉት ድርቅ በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸውና የቀንድ ከብቶች በድርቁ ከፍተኛ ጉዳት በሚደርስባቸው አካባቢዎች የአርብቶአደር ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመተግበር የቀንድ ከብት እርባታ ወደ ግመል እርባት ሊቀይር የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል፡፡አሁን ያለው ችግር የባለድርሻ አካላት የቅንጅት ችግር ነው ፡፡ በቅንጅት መስራት ከተቻለ ብዙውን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል ብለዋል፡፡
የአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ ኣባ በተነሱት ሃሳቦች ላይ በማጠቃለያው እንዳሉት አርብቶ/ከፊል አርብቶ አደር በባህሪው ተንቀሳቃሽና ከፊል ተንቀሳቃሽ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የትምህርት ፣የውሃና የጤና ሁኔታዎች ያሥፈልጋል የሚለውን ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል፡፡የተሳታፊዎች ስብጥር ከክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ተወካዩችም እንዲኖር የተፈለገበት ምክንያት በክልል ደረጃ ያሉትን ባለድርሻ አካላትን ሁኔታውን ተገንዝበው እንዲያሥተባብሩ ላመስቻል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ወደፊት የአርብቶአደር እና ቆላማ አካባቢዎች ላይ በተቀናጀ ሁኔታ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት የሚያሥችለው የቆላማ አካባቢ ፕሮግራም እየተጠና ነው፤ ይህም ፕሮግራም ሲተገበር ይበልጥ ተቀናጅተን እንድንሰራ ያስችለናል ብለዋል፡፡
የሚኒስትር ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባም በማጠቃለያው ላይ የሰጡት አስተያየት የቀረበው ስልጠና በግልፅ በጥሩ ሁኔታ እንደሆነ ገልፀው በተግባር ወደ ታች መሬት ላይ በቅንጅት መተግበር ይገባናል ብለዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ የእንስሳት ኤክስቴንስን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ፀጋው በአርብቶ አደር እንስሳት ኤክስቴንሽን እና የአርብቶአደር የመስክ ትምህርት ቤት ላይ ገለፃ እየተደረገ ነው፡፡

01/12/2023

During his address at the COP28 Climate Summit in Dubai, UAE, H.E. Abiy Ahmed Ali (PhD) underscored Ethiopia’s unwavering commitment to revolutionizing the food system acknowledging its intricate connections with climate, biodiversity, water, and people. The Prime Minister emphasized successful initiatives that include implementing and planting drought-tolerant crops. He further highlighted our dedication to eco-friendly and resource-efficient greening and farming methods, fostering .

Moreover, The Prime Minister indicated how Ethiopia’s investment in water management and investment in renewable energy-based is integral to our sustainable agriculture practices.
__
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት፣ ከብዝሃ ህይወት፣ ከውሃ እና ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ትስስር በመገንዘብና የምግብ ስርዓቱቷን ለመለወጥ ቁርጠኝነት እንዳለት አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘውየአየር ንብረት ለውጥ /ኮፕ28/ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ዘመናዊ #የመስኖቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግ እና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ሰብሎች መዝራትን ጨምሮ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ውጤት ማስገኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እና ለምግብ ዋስትና መሰረት የሆኑ የአረንጓዴ ልማት እና የግብርና ሥራዎችን በዘላቂነት ለመስራት ቁርጠኝነቷን አሳይታለች ብለዋል፡፡ ለዘላቂ የግብርና ልማት ወሳኝ በሆነው የውሃ አስተዳደር ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት በታዳሽ ኃይልና በዘመነ የመስኖ ስርዓት እንዲመራ ለማድረግ በቁርጠኝት እየሰራች መሆኑንም አስምረውበታል፡፡

----
Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://lnkd.in/eSY-SZfg
X:
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 01/12/2023

ለሚኒስቴርና ክልሎች መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የአርብቶአደር ኤክሰቴንሽን አገልግሎት ሥርዓት ማኑዋል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ህዳር 21/2016 ዓ/ም ፣አዳማ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት ለሚኒስቴርና ክልሎች መካከለኛ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የአርብቶአደር ኤክሰቴንሽን አገልግሎት ሥርዓት ማኑዋል ስልጠና ዛሬ ህዳር 21/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በናፍሌት ሆቴል እየተሰጠ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንድርያሥ ጌታ እንዳሉት በአገራችን በሁሉም አከባቢዎች የግብርና የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግበራዊ መደረግ ከጀመረ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ነው፡፡የኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ የነበረው በአብዛኛው አርሶአደር አካባቢዎች ላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ነበር፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታው እንደገለፁት በአገራችን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ሲጀመር የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ታሳቢ ያደረገው እንዲሁም አርሶአደሮችን የማሰልጠንና የመጎብኘት የኤክስቴንሽን ስልቶች መነሻቸውን የአርሶአደር አካባቢ ኃላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ ለማሻሻል ሲባል አሳታፊ ያልነበረና ከላይ ወደታች ተግባራዊ የተደረገ ነበር፡፡ይህ ሁኔታ የተወሰነ ለውጥ ቢያመጣም በሚፈለገው ልክ ለውጥ ማምጣት አልቻለም፡፡
ከ20 ዓመታት በፊት የአርሶአደርን ምርታማት ለማሳደግ ከችግር ልየታ ጀምሮ አርሶአደሩ ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወት ተደርገዋል፡፡ ይህም ሲተገበር የነበረው በእንስሳት ልማት፣ ተፈጥሮ ሃብት ልማትና እንክብካቤ ፣ ሰብል ልማት እንዲሁም መስኖ ልማት ባለሙያነት ወጣቶች ሰልጥነው በአርሶአደር ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ የስልጠና እንዲሁም በመስክ የሙያ ድጋፍና የምክር አገልግሎት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው ፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር እንድርያስ ጌታ እንደገለፁት በአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢዎች ተቀራራቢ የሆነ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ሲሰጥ አልነበረም፡፡በአገራችን በአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢዎች የአርብቶአደሩን የኑሮ ዘይቤና የኑሮ መሰረት ግምት ውስጥ ያላስገባ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ሲሰጥ ነበር፡፡ አርብቶአደር አካባቢ ሰፊ ለም መሬትና በርካታ ውሃ እንዲሁም አገር በቀል ዕውቀቶችና የተለያዩ መዓድናት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ለአገራችን የዕድገት ተስፋ ያለበት አካባቢ ነው፡፡ይሐንንም አካባቢ ትተን የትም መድረስ አንችልም፡፡
በመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው እንገለፁት ከለውጡ በኃላ የአርብቶአደር ልማት ፖሊሲና የማስፈፀሚያ እስትራተጂ ተቀርፆ ተግባራዊ መደረግ ጀምረዋል፡፡ ይሐንን ለመተግበር ስልጠናዎች በየደረጃው ተሰተዋል፡፡ በአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ ያለውን የድርቅና የጎርፍ ችግር ለመቅረፍ በአሁኑ ወቅትም የአርብቶአደር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓት ማኑዋል ማዘጋጀት በማስፈለጉ ተዘጋጅቶ ስልጠናዎች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡በማኑዋሉም ተጨባጭ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦች ያሉበት ነው፡፡
በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር እንድርያስ ጌታ እንደዓሉት የአርብቶአደር ልማት ሁሉን አቀፍ ቅንጅትና ትስስር የሚፈልግ በመሆኑ ከትምህርት ፣ከጤናና ከውሃ ተቋማት እንዲሁም ከግብርና ቢሮዎች ፣ አርብቶአደር ልማት ቢሮዎች እና መስኖና አርብቶአደር ልማት ቢሮዎች የመጣችሁ የስልጠናው ተሳታፊዎች አመሰግናለሁ በማለት ስልጠናው በይፋ መከፈቱን በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉና ወደ መጡበትም ሲመለሱ በተግባር ወደ ስራ እንዲትተገብሩ አሳስበዋል፡፡
የአርብቶአደር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓትን ገለፃ የሚያደርጉት አቶ ዳንኤል ደንታሞ በግብርና ሚኒስቴር የኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን አቅም ግንባታ ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ የእንስሳት ኤክስቴንሽን ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ፀጋው ደግሞ በአርብቶ አደር እንስሳት ኤክስቴንሽንና የአርብቶአደር የመስክ ትምህርት ቤት ላይ ገለፃ ያደርጋሉ፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 30/11/2023

ለሚኒስቴር መ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የኢፊሚስ ስልጠና ተሰጠ

ህዳር 20/2016 ዓ/ም ፣ አዲስ አበባ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያውች የኢፊሚስ ስልጠና ህዳር 20/2016 ዓ/ም በቢሾፊቱ ከተማ ከገንዘብ ሚኒስቴር የኢፊሚስ ፕሮጀክት ፅ/ቤት በመጡንባለሙያዎች ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን በንግግር የአስጀመሩት የሚንስትር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከፈለች ደንቦባ እንዳሉት ሚኒስቴር መ/ቤታችን ከተቋቋመ አጭር ጊዜ በመሆኑ አመራሮችና ባለሙያዎችም አዲስ በመሆናቸው በሚፈለገው ደረጃ የኢፊሚስ ሲስተም ተጠቃሚ በመሆን ስራዎችን ለማሳለጥና ውጤታማነትን ለመጨመር ማናቆ የሆኑ የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የሚያግዝ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም መንግስት በአስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የኢፊሚስ ሲስተም በመጠቀም የአሰራር ስርዓቶችን ማዘመን እንዲሁም ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን መሰረት በማድረግ አመራሩ በራሱ ዩዘር ኔምና ፓስወርድ የበጀት አያያዝንና አጠቃቀም ፣ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ፣የፕሮግራም በጀቲንግ በኢፊሚስ የተቃኘ ለማድረግ እንደዚሁም ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ሪፖርት ለማቅረብ ፣አፈፃፀምን ለመገምገምና አመራሩ በቅርበት መረጃዎችን እያገኘ ውሳኔ ለመስጠት ይጠቅማል ብለዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናው በሲስተሙ አጠቃቀም ዙሪያ ያለብንን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት የሞላልን በመሆኑ በተገቢው ጊዜ የተሰጠ ስልጠና ነው ብለዋል ፡፡

Ethiopian Investment Video Nov 27 30/11/2023

Ethiopia - a nation with immense investment potential! https://youtu.be/daQo6NrXZsw?si=zMwoIPr1rhfa9cSJ via

Ethiopian Investment Video Nov 27

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 30/11/2023

የመስኖ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ከአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ስልቶች ውስጥ ዋነኛ የሆነው የመስኖ ልማት ስታንዳርድ ለማዘጋጀት የሚያስችለው ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡
------
ፕሮጀክቱን የዓለም አቀፉ የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) በገንዘብ የደገፈ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚከናወን መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ፕሮጀክቱን ይፋ ለማድረግ ዛሬ በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሀመድ የመስኖ ልማት ስታንዳርዱ ከዲዛይን ጀምሮ ግንባታንም በማካተት በመስኖ ዘርፍ ወጥ የሆነ አሰራርን ለማስፈን ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከመስኖ ስታንዳርድ በተጨማሪ፣ ኮዶችን መመሪያዎችንና የህግ ማዕቀፎችን የሚያካትት ሲሆን በአገራችን በመስኖ ዘርፍ የሚታዩ የህግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን በመፍታት ሃገራዊ ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችል እንደሆነ ታምኖበታል፡፡
ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት ስነ-ስርዓት ላይ የዓለም አቀፉ የምግብ እና እርሻ ድርጅት /FAO/ የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራሂ ዙምቡዲ ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዘርፉ ምሁራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
-----
Exciting Announcement: We are thrilled to announce the official launch of the Standard Development Project by in collaboration with , , and the Institute of Ethiopian Standards. This initiative stands as a critical strategy in Ethiopia's Ten-year Development Plan.
In her address, H.E. Eng Aisha Mohammed, Minister of Irrigation and Lowlands, underscored the vital role of Irrigation development standards in establishing a consistent system nationwide. The project encompasses codes, guidelines, and legal frameworks, addressing existing gaps in the irrigation sector.
Furthermore, the introduction of these standards reflects our firm commitment to advancing initiatives that align with sustainable practices, contributing to the broader goals of development and environmental responsibility.
----

Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://facebook.com/MILLsEthiopia/
X: https://twitter.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 29/11/2023

በሃገራዊ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ሃገራዊ ጥቅል የኢኮኖሚ ሁኔታና አዝማሚያ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
አገራዊ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ባለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተስፋ ሰጪ መሻሻል ማሳየቱን ተገልፀዋል፡፡
በ2015 በጀት ዓመት አገራዊ የኢኮኖሚ እድገት 7.2% መሆኑን እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት አገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱ 7.9% እንደሚሆን ይገመታል፡፡
ሀጋረዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርትና በዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ እድገት የሚገለጥ መሆኑን የተናገሩት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንድርያስ ጌታ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ዓመታዊ ምርት እጥፍ ማደጉንና የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ የዛሬ 5 ዓመት ከነበረበት 882 የአሜሪካን ዶላር ወደ 1549 የአሜሪካን ዶላር ማደጉን ጠቅሰዋል፡፡
የአገር ውስጥ ምርት በ2015 በጀት ዓመት 164 ቢሊዮን ዶላር ደርሰዋል፡፡
የሃገር ውስጥ ጥቅል ገቢም በ2010 በጀት ዓመት 176.103 ትሪሊን የነበረው በ2015 በጀት ዓመት 442.027 ትሪሊየን መድረሱ ተገልፀዋል፡፡
የኢኮኖሚ እድገት መለኪያዎች በአጠቃላይ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማሳያዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ከአንዳንድ እኩይ አላማ ካላቸው ሃይሎች ከሚነዙት የሃሰት ወሬ በተቃራኒ የውጭ ኢንቨስትመንት በማደግ ላይ ነው ብለዋል፡፡
ሪፖርቱ ከቀረበ በኃላ አጠቃላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም አጠቃላይ አገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የተገኘ እድገት በመሆኑ ተወያዮቹ ከፍተኛ አድናቆት አለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሃመድ አገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ተስፋ ሰጪ ነው ካሉ በኃላ ሚኒስቴር መ/ቤቱም ለአገራዊ የኢኮኖሚ እድገት የራሱን ድርሻ ያበረከተ መሆኑን ገልፀው ይበልጥ ትኩረት አድርገን በበጀት ዓመቱ ያቀድናቸውን ስራዎች ማሳካት ይገባናል ብለዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምም በዚሁ መድረክ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 29/11/2023

ድህነትን በማሸነፍና ዜጎች በተረጋጋ የኑሮ ጎዳና እንዲጓዙ ለማድረግና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሙስናን መታገል ይገባል
ህዳር 19/2016 ዓ/ም ፣አዲስ አበባ

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚ/ር በአለምአቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን በግዮን ሆቴል አክብረዋል፡፡

‘ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በህብረት እንታገል!’’ በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ በሚከበረው የሙስና ቀን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚ/ር ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሃመድ እንዳሉት አንድ ሃገር ከድህትና ከኋላቀርነት ለመውጣት በተጨባጭ ሙስናን መታገል ቀዳሚ አጀንዳዋ ሊሆን ይገባል፡፡

ሀገርን ክፉኛ ከሚገዘግዝ፣ የዜጎችን ኑሮ በድህነት አረንቋ እንዲዘፈቅ ከሚያደርግ ሙስና በላይ ጠላት የለንም ያሉት ሚኒስትሯ እያንዳንዳችን ሙስናን ለመዋጋት የምናዋጣው አስተሳሰብም ሆነ ተግባራዊ ርምጃ ተደምሮ ውጤት እንደሚያስገኝ ለአፍታም መዘንጋት አይገባም ብለዋል፡፡

ሙስናን ለመዋጋት ከቤታችን መጀመር አለበት ያሉት ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ በተለይ እንደ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በምንገነባ ተቋማት ሃብት እንዳይባክን ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

በፌዴራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ስልጠና መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግም አላምረው የመወያያ ሰነድ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የመወያያ ሰነዱ ከቀረበ በኃለ ውይይት በስፋት ተከናውነዋል፡፡

28/11/2023

የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ነገ በሚኒስቴር መ/ቤታችን ይከበራል
ዓለም አቀፉ የፀረ-ሙስና ቀን በየዓመቱ ህዳር 30 ቀን ይከበራል፡፡ በህዳር 19/2016 ዓ/ም “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በሕብረት እንታል!/Uniting the World Against Corruption” በሚል መሪ ቃል በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ፣ በሃገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ በሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን የአለም ሃገራት የፀረ-ሙስና ትግል፣ በኢትዮጵያ ሙስና ያስከተለው ጉዳትና፣ ሙስናን ለመታገል የተወሰዱ ርምጃዎች ምን ይመስላሉ በሚሉ ጉዳዮች ላይ የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ ይመክራሉ፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በርካታ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና በማስተዳደር ላይ የሚገኝ ተቋም ከመሆኑ አንጻር አመራሩና ሠራተኛው በስነ-ምግባር የታነፀና በጠንካራ ዲሲፕሊን መመራት ይኖርበታል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት በሚኖረው ፕሮግራም ከፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሚመጡ ሃላፊዎች በመ/ቤቱ ሰፊ ውይይት የሚደረግበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረከ ይከናወናል፡፡
“ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በህብረት እንታገል!”

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 24/11/2023

የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች የኮርፖሬሽንኑን የዲጂታል ፕሮጀክት ማኔጅመንት ሲስተም ጎበኙ
-------
የሚኒስቴሩ አመራርና ሰራተኞች የአሰራር ቅልጥፍናን ለማጎልበትና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የዘመነ የፕሮጀክትና ሃብት ማኔጅመንት ሲስተም አተገባበርን በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመገኘት ጎብኝተዋል።
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ዘሪሁን መኩሪያ እንደገለጹት የፕሮጀክቶችን የየዕለት እንቅስቃሴ በቀጥታ በዲጂታስ ስራዓት በመከታተል፣ የፕሮጀክቶችን ግንባታ መዘግየት መቀነስና ማሳለጥ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው እንዳሉት ለድርጅታቸው ውጤታማትና ትርፋማነት የዲጂታል ልማት ሥራዎች ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ተናግረው በኮንስትራክሽንና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከ10 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ምርጥ አንደኛ የመሆን ራዕይ ሰንቀን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ባለሞያዎች ስለዲጂታል ፕሮጀክት ማኔጅመንት (Enterprise Resource Planning/ERP)፣ የህንጻ መረጃ ሞዲሊንግ (Building Information Modelling)፣ እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ ውጤታማነትና የአሰራር ሂደቶች ዙርያ ገለጻ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በርካታ የውሃ ግድብ፣ የመንገድ ግንባታና የሪል ሰቴት ግንባታ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የሚታወቅ የመንግስት ልማት ድርጅት ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአዲስ አባባና በተለያዩ የሃገራችን ከተሞች ለአቅመ ደካሞች በሚገነቡ የቤት ግንባታ ስራዎች ላይም በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

23/11/2023

ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://lnkd.in/eSY-SZfg
X: https://lnkd.in/e7tQ4-2A
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

mills.gov.et

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 23/11/2023

ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ከኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር ተውያዩ፣ ለልዑካን ቡድኑ አባላት እውቅና ተሰጠ፡፡

ህዳር 13/2016 ዓ/ም ፣ስዑል፣ ኮሪያ

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ከልዑካን ቡድኑ አባላት ጋር በመሆን ከኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር ዋንግጁ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ በመገኘት ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በመስኖ ሊለማ የሚችል ከ10 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያላት አገር መሆንዋን ገልፀዋል፡፡ የኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን በከርሰምድር መስኖ ውሃ ልማትና ገጠር ልማት ላይ ከፍተኛ ልምድ ያለው በመሆኑ እኛም ከዚህ ልምዳችሁ በጉብኝትና ልምድ ልውውጣችን ወቅት ብዙ ተምረናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ኮንሰብት ኖት በማዘጋጀት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እንደምጠይቁ ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ለስራ ሃላፊዎቹ ገልፀውላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በፊዚቢሊቲ ጥናት፣ በሪሃብልቴሽን፣ በአቅም ግንባታና በመስኖ መሰረተ ልማት አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስቴር ዴኤታው ጠይቀዋል፡፡

የኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ፓርክ ታኤ ሲአን እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ የከርሰምድር ውሃ መስኖ ልማትና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

በክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የሚመራው ልዑካን ቡድን በቆይታው በከርሰምድር የመስኖ ውሃ ልማት እና በገጠር ልማት የወዳጅነት ፕሮግራምን በተሳካ ሁኔታ ስለአጠናቀቁ ከኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የእውቅና ሰርተፊኬት ለሁሉም የልዑካን አባላት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመዝግያ ስነ -ስርዓቱ ላይ ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ባስተላለፉት መልዕክት የኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የሥራ ሃላፊዎችን በማመስገን ቆይታችን ውጤታማ ነበር ብለዋል፡፡ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ ጋር የረዥም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አገራችን እንዳላት በመግለፅ የኮሪያ ኤግዚም ባንክም በፋይናንስ ፕሮጀክቶቻችንን ለመደገፍ ፊንጭ ያሳየበት በመሆኑ ቆይታችንን ይበልጥ ፊሬያማ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡

በኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽንና በመስኖናቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መካከል ተመሳሳይ ተግባራትያሉን በመሆኑ በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው በማለት ከልምድ ልውውጡ አገራችን እጅጉን ተጠቃሚ እንደሆነች ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የአደጋ ስራ አመራር ማዕከል ለልዑካን ቡድን አባላት ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በዚህም ገለፃ ልምድ እንደተገኘበት የልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 21/11/2023

ከሳምዳሶ እስማርት የታሸገ የመጠጥ ውሃ ፋብሪካ የልዑካን ቡድን አባላት ከማናጅመንትና ከሰራተኛው የስራ ቁርጠኝነት ልምድ መማር እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
ህዳር 11/2016 ዓ/ም፣ ስዑል
የጄጁ ልዩ ራስ አስተዳደር ግዛት ውስጥ የሚገኘው የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም የታሸገ የመጠጥ ውሃን የምያመርተው የሳምዳሶ እስማርት የታሸገ የመጠጥ ውሃ ፋብሪካ የልዑካን ቡድን አባላት ከማናጅመንትና ከሰራተኛው የስራ ቁርጠኝነት ልምድ መማር እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡ፋብሪካው ለ942 ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የሚመራ የልዑካን ቡድን አባላት የሳምዳሶ እስማርት የታሸገ የመጠጥ ውሃ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም ወቅት ሚስተር ህዩን ኤንሄ የአር. ኤንድ ዲ. ኢኖቬዥን ዲቪዥን ኃላፊ ስለ ጄጁ አስተዳደር ግዛት የልማት ኮርፖሬሽን /የሳምዳሶ እስማርት የታሸገ የመጠጥ ውሃ ፋብሪካን / ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ያለበትን ደረጃ አብራርተዋል፡፡
ፋብሪካው የመንግስት የልማት ድርጅት እንደሆነና የፋይናንስ ድጋፍም ሙሉ በሙሉ የሚደረግለት ከጄጁ ልዩ ራስ ገዝ አስተዳደር ግዛት መሆኑን እንዲሁም ፈብሪካው በጣም ዘመናዊ እንደሆነና የምርት ሂደቱም ከሰው ቀጥተኛ ንኪኪ በአብዛኛው ነፃ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
ይህ ፋብሪካ እ.ኤ.አ. መጋቢት /1995 የተቋቋመ ሲሆን እ.ኤ.አ.በ2022 27 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2025 እስትራተጂክ እቅዳችን ነው ያሉት ሃላፊው በጄጁ ሃብቶች እሴት ጨምረን ለነዋሪዎቻችን ደስታና ልማት ማምጣት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የጄጁ ግዛት ልማት ኮርፖሬሽን የተለያዩ ቢዝነስ ስራዎች ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን እነዚህም የሳምዶስ የታሸገ የመጠጥ ሚንራል ውሃ ፣የመንደሪን ማቀነባበሪያ፣ የተሰጥዖ ድጋፍና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ የሚሳተፍ መሆኑን ሃላፊው አብራርተዋል፡፡
የጄጁ ግዛት ልማት ኮርፖሬሽን የፕራይም ሚኒስትር ሽልማትን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶችን በሰራቸው ስራዎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
ፋብሪካው የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎችን ከማምረት ጀምሮ እስከ መልሶ መጠቀም ድረስ የሚተገብር ነው፡፡
በመጨረሻም የፋብሪካው ማናጅመንትና ሰራተኞች በቁርጠኝነት ለጄጁ ግዛት ነዋሪዎች ደስታና ብልፅግና አስታውፅዖ ማድረግ እንዲሁም የኮሪያ የፐብሊክ ኢንተፕራይዝ ግንባር ቀደም ለመሆን እንደሚሰሩ ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 20/11/2023

የጄጁ ራስ አስተዳደር ግዛት የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ሪጂን ዋና መ/ቤትን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን አባላት ጎበኙ፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት የሲየንግ አፕ ግድብንም ጎብኝተዋል፡፡
ህዳር 11/2016 ዓ/ም፣ ስዑል
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ የሚመራው ልዑካን ቡድን አባላት የጄጁ ራስ አስተዳደር ግዛት የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ሪጂን ዋና መ/ቤትን ጎበኙ፡፡በጉብኝታቸውም ወቅት ሚስተር ዶንግ ቺኦል የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የሪጂን ዋና መ/ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ለልዑካን ቡድኑ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በመቀጠልም በቢሮ የሲየንግ አፕ የግድብን በተመለከተ ማብራሪያ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ተደርጎላቸዋል፡፡ የግድቡን ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም ግንባታውንም ያካሄደው የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን የጄጁ ሪጂን ነው፡፡1.25 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ስላለው፣ 400 ሄክታር ስለሚያለማውና በ62.025 ቢሊዮን የኮሪያ ዎን ስለተገነባው ግድብ ገለፃ ለልዑካን ቡድን አባላት ተደርጎላቸዋል፡፡
የሲየንግ አፕ ግድብን በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የሚመራ የልዑካን ቡድን አባላት ግድቡ የተገነባበትን ቦታ በአካል በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡የግድቡ መሰረተ ልማት አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችም በቦታው ተገኝተው ለልዑክ ቡድን አባላት ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
የልዑካን ቡድን አባላትም በተደረገላቸው አቀባበል እንዲሁም በቢሮና በግድቡ ቦታ በተሰጣቸው ገለፃ ልምድ ማግኘት እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 17/11/2023

የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ የመስኖ ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ ያሳድጋል
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ የተመራው የልዑካን ቡድን በደቡብ ኮሪያ የሚያደርገውን የሥራ ጉብኝት በመቀጠል በዛሬው ዕለት ከኮሪያ ኤግዚም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያይቷል፡፡
______
በዚሁ ውይይቱ ክብርት ሚኒስትሯ የኮሪያ ኤግዚም ባንክ ኢትዮጵያ በመስኖ ዘርፍ እያደረገች ያለችውን ልማት በተግባር እንዲደግፍ የጠየቁ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና አገራዊ ልማትን ለማስቀጠል መስኖን ቀዳሚ በማድረግ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ባንኩ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክቶችን፣ የመስኖ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ተያያዥ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ከመደገፍ ባሻገር በዕውቀት ሽግግርና ልምድ ልውውጥ ድጋፉን እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል፡፡
በኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው በባንኩ የፋይናንስና ቴክኒካል ድጋፍ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የአፍሪካ ሀገራት አትዮጵያ አንዷ መሆኗን በማንሳት ለባንኩ ምስጋና አቅርበው ባንኩ በተለይም በመስኖ ልማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ጥረት እንዲደግፍ ጠይቀዋል፡፡
የኮሪያ ኤግዚም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሁዋንግ ኪዮን በበኩላቸው፣ ባንኩ በኢትዮጵያ ያሉ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገምገም ለነዚሁ ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያሳድግም ተናግረዋል፡፡

---
Today, the Delegation led by the Minister of Irrigation and Lowlands, H.E. Eng. Ayisha Mohammed held courtesy meeting with executive director of Korean Eximbank.

During the discussion H.E. Eng. Ayisha Mohammed, the Minister of Irrigation and Lowlands ( ), urged Executive Director of the Korean Eximbank to support Ethiopia's development program. H.E. Eng. Ayisha Mohammed in her explanation emphasized the necessity of financing groundwater projects, irrigation infrastructure, and other related projects as the Ethiopian government has identified irrigation as a priority area for ensuring food security and sustaining national development.

In addition, the minister also emphasized the importance of sharing knowledge and experience in addition to financial support in the area.

H.E Dessie Dalkie ,Ethiopian Ambassador to the Republic of Korea, extended his gratitude to the for taking Ethiopia among top priority Africa nations for financial and technical support. The Ambassador further mentioned about the unique historical and friendly ties between Ethiopia and Republic of Korea. Hence, he added that the importance of strengthening this relations and requested the bank to continue support for development initiatives particularly those related to irrigation in infrastructure development in Ethiopia.

H.E. Hwang KIYEON,the executive director of Korean Eximbank,in his part, said that Korean Eximbank reviewing projects in Ethiopia and considering to fund those projects. He also assured that the bank will expand financial and technical assistance to the Ethiopia.

-----
Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://lnkd.in/eSY-SZfg
X: https://lnkd.in/e7tQ4-2A
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 16/11/2023

የመክፈቻ ስነ -ስርዓት ተካሄደ
ህዳር 6/2016 ዓ/ም ፣ስዑል
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ የሚመራው ልዑክ በደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የስልጠና፣ ጉብኝትና ተሞክሮ ልውውጥ ፕሮግራም የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በኖቮቴል ሆቴል ተከናወነ፡፡
በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ በኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን( Korea Rural Community Corporation /KRC/ ) የሰው ሃብት ልማት እንስቲትዩት /Director General of Human Resources Development Institute/ ,Choi,Byeony-Yoon በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችው ካሉ በኃላ የ115 ዓመት እድሜ ስላለው ካምፓኒ/KRC/ አጭር ማብራሪያ ሰጥተው የደቡብ ኮሪያ ቆይታችው የተሳካ እንዲሆን እመኛለው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ ስለተደረገ ላቸው አቀባበል በማመስገን አገራችን ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ በተላይ በከርሰምድር ውሃ አጠቃቀም በተግባር ልምድ አግኝተን ወደ አገራችን ሲንመለስ እንተገብረዋለን በማለት ይህ የተሰጠን እድል የኢትዮጵያንና ደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የረዥም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነትን ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ስለ የኮሪያ የገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን( Korea Rural Community Corporation ) ፣ ስለ ኦ.ዲ.ኤ. ፕሮጀክቶች (ODA Projects) እንዲሁም ስለ መስኖ ፖሊሲ ገለፃ ለልዑካን አባላት ተደርጎላቸዋል፡፡
The opening ceremony was held
November 16/2023, Seoul
The opening ceremony was held for Minister of Ministry of Irrigation and Lowlands ‚Her Excellency Eng. Ayisha Mohammed and member of her delegation that are participating on Training of Groundwater Irrigation Development and Rural Development Project ,visiting Irrigation Development related project sites and Experience Sharing at NOVOTEL Hotel.
At the opening ceremony, the Korea Rural Community Corporation, Director General of Human Resources Development Institute/ ,Choi,Byeony-Yoon expressed that his warm welcome message, and briefly introduced Korea Rural Community Coporation , Korean Government Corporation, that is established in 1908 with 115-year history.
The Minister of Ministry of Irrigation and Lowlands ‚Her Excellency Eng. Ayisha Mohammed ‚ thanked for the welcome message ,and said that we will gain practical experiences in the utilization of groundwater from the Republic of South Korea ,and we will implement it when we return to our country. The Minister also said that this opportunity will strength

Photos from Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia's post 15/11/2023

በክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ የተመራው የልዑካን ቡድን ጉብኝቶችንና የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ ደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ ገብቷል
_______
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ የተመራው የልዑካን ቡድን ደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የስራ ጉብኝት የሚያደርግ ሲሆን ደቡብ ኮሪያ ስዑል ኢንቺየን አየር ማረፊያ ሲደርስም በኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ አቀባባል አድርገውለታል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከመስኖ ልማት ጋር በተያያዘ ሰፊ ልምድ ያለውን የኮሪያ ገጠር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን (KRC) ስራዎችንና ተያያዥ የመስኖ ልማቶችን በመመልከት የተሞክሮ ልውውጥ የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአዳዲስ የፕሮጀክቶች የፋይናንስ ፍላጎት ላይ ምክክር እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
በልዑካን ቡድኑ ጋር አብረው ከተጓዙት መካካል የመስኖ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶና የኦሮሚያ ክልል መስኖና አርብቶአደር ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ዓለሙ ረጋሳ የሚገኙበት ሲሆን የሚኒስቴሩ ልዩ ልዩ የስራ ኃላፊዎችም ወደዚያው ተጉዘዋል፡፡

A delegation led by H.E. Aisha Mohammed M***a (Eng.) has officially touched down in the Vibrant city of Seoul, South Korea.
The group, led by the Minister of Irrigation and Lowlands embarks on a purposeful working visit to South Korea. Upon their arrival at Seoul Incheon Airport, they were warmly received by H.E. Dessie Dalke, the Ethiopian Ambassador to South Korea.

During their stay, the delegation will partake in significant discussions with the Korea Rural Community Corporation ( ), an organization renowned for its expertise in irrigation development. Additionally, they will explore potential financing options for new and forthcoming projects through consultations with the Korean Eximbank, aiming to strengthen collaboration and facilitate the exchange of valuable insights.

Accompanying the delegation are H.E. Birhanu M. Lenjiso (PhD), State Minister of Irrigation Development Sector, Mr. Alemu Regasa, the Deputy Director of the Oromia Irrigation and Pastoralist Development Bureau, and various officials of .

-----
Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://lnkd.in/eSY-SZfg
X: https://lnkd.in/e7tQ4-2A
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የዛሬው ፓርላማ ውሎJoin our social media community:Web: https://mills.gov.etFB: https://lnkd.in/eSY-SZfgX: https://lnkd.in/e7tQ...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል ከኢ.ፕ.ድ. ቴሌግራም የተወሰደ
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ህዝብና መከላከያ ሠራዊት ያስተላለፉት መልዕክትJoin our social media community: Web: https://mills.gov.etFB: https://...
116ኛው የሰራዊት ቀን በዚህ መልኩ በድምቀት ተከብሯል።#NationalArmyDay #EthiopiaJoin our social media community: Web: https://mills.gov.etF...
በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ  ለሚሰሩ የክልሎችና ሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና  ባለሙያዎች  በአዳማ ከተማ የተሰጠ የአቅም ግንባታ ስልጠና

Telephone

Address


Kasanchis
Addis Ababa
Other Addis Ababa government services (show all)
Addis Ketema woreda 5 Communication Addis Ketema woreda 5 Communication
Addis Ababa
Addis Ababa

This is woreda 5 communication office .

Addis Ketema Woreda12 Communication Addis Ketema Woreda12 Communication
Addis Ketema
Addis Ababa

በዚህ ወሳኝ ወቅት ከመንግስት ተቋማት የሚተላለፉትን መረጃዎ�

የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት
Addis Ababa

የቦሌ ሥራና ክህሎት ፅ-ቤት Official የፌስቡክ ገፅ ነው፤ እኛን የሚመለከት ጉዳይ ካለዎት ያግኙን።

Addis Ababa City Administration Trade Bureau Addis Ababa City Administration Trade Bureau
Addis Ababa
Addis Ababa

News

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency
604 Equatorial Guiene Avenue
Addis Ababa

Serving reliable cadastral services and information

Lafto woreda 05 Communication Lafto woreda 05 Communication
Addis Ababa

peace for Ethiopia

Ethio-engineering Group Ethio-engineering Group
Bole Sub City, Gerji, Amora Building
Addis Ababa

Ethio-engineering Group is a governement owned industrial enterprise established under the laws of the Federal Democratic Republic of Ethiopia /FDRE/ by the decree of the council o...

Meskel Square Facility Management Meskel Square Facility Management
Addis Ababa, 1000

Meskel Square is the project office under ECMDE that sale public services such as:-

ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB
Bole
Addis Ababa, SARIS

This page is created in order to share timely information regarding job, enterprise and industry dev